የጴንጤቆስጤ ሥነ መለኮት ታሪክ

በትምህርት 5 እንደጠቀስነው ሁላችንም የመረዳት ችሎታችን እውነትን ወደ አንድ አቅጣጫ ያዘነበለ ነው። ስለ ዝሆን ከፊል የሆነ መረዳት እንደ ነበራቸው እንደ አራቱ ዓይነ ስውራን እንደ መንፈስ ቅዱስ ባሉ መሠረታዊ የእምነት ትምህርቶች ላይ ሁላችንም ያላን መረዳት ከፊል ብቻ ነው። ይህ የሆነበትንም ምክንያት ተመልክተናል። ባሕላዊ መሠረታችን የመጣንበት ቤተ ክርስቲያን ዕድሜያችን በጥቅሉ በአማኞች ሕይወት ውስጥ የሚሆነውን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የምንረዳበትን ሁኔታ ይወስናሉ። ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በጥልቀት የምንመለከተው ጰንጠቆስጤ የሆኑ ክርስቲያኖችና ያልሆኑት በብርቱ የማይስማሙባቸውን ሁለት የመንፈስ ቅዱላ ሥራዎች ነው። እነርሱም «የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት» እና «የመንፈስ ቅዱስ ሙላት» ናቸው። 

ጥያቄ፡- ሀ) በመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንና በቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን መካከል ያሉትን አንዳንድ የሥነ መለኮት ትምህርት ልዩነቶችን ግለጽ። ለ) በቃላ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንና በሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን መካክል ያሉትን አንዳንድ የሥነ መለኮት ትምህርት ልዩነቶች ግለጽ። ሐ) እነዚህ እብያተ ክርስቲያናት በሚያምኑትና በሚለማመዱት ነገር መሠረታዊ ልዩነቶች የሚታዩት ለምን ይመስልሃል? መ) በቤተ ክርስቲያን ታሪክና ተግባር ላይ የሚካሄድ ጥናት እሁን ያሉትን መሠረታዊ የእምነት ትምህርቶች ተግባር ለመመርመር የሚረዳው ለምንድን ነው? 

አብዛኛዎቹ የቤተ ክርስቲያን የእምነት ክፍሎች የተፈጠሩት መሪዎቻቸው እንዳንድ እውነቶችን የሚረዱበት መንገድ ከሌሎች የተለየ በመሆኑ ነው። እነዚህን እውነቶች በሥዕላዊ መግላማችን (ትምህርት 5 ተመልከት) ሁለተኛ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ይህ ማለት የደኅንነታችንን ጉዳይ የማይነኩና መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ትምህርት የሚሰጥባቸው ናቸው ማለት ነው። ማርቲን ሉተር ክካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ወጥቶ የሉተራውያንን ቤተ ክርስቲያንን (መካነ ኢየሱስ) የጀመረበት ምክንያቱ የክርስትና እምነት መሠረታዊ ትምህርት ላይ በተለይ ደግሞ በድነት (ደኅንነት) ጉዳይ ላይ ልዩነት ስለተፈጠረ ነው። ላለመገንጠሉ ምክንያት የሆነው በዚያን ወቅት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ግልጽ ከሆነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድነት (ደኅንነት) ፈቀቅ ማለት ነበር። በዚህ ሁኔታ መለያዩቱ የመጣው በዋና መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት ማለትም በሥዕላዊ መግላማችን በውስጠኛ ክፍል ነበር። ስለሆነም ይህ መለየት እውነተኛውን እምነት ለመጠበቅ ተዚ ነበር። ፕረስቢቴሪያውያን ከሉተራውያኑ ተለይተው ሲወጡ መነሻው በጣም አናሳ በሆነ መሠረታዊ የእምነት ትምህርት ጉዳይ ማለትም እግዚአብሔር ሰውን የሚያድነው እንዴት ነው የሚል ነበር። የጰንጠቆስጤ አብያተ ክርስቲያናት ጰንጠቆስጤ ካልሆኑት ተለይተው የወጡበት ዋና ምክንያት አንዳንድ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶችን በመረዳት ላይ በተፈጠረ ልዩነት ነበር። እነዚህ ልዩነቶች ጴንጠቆስጤ ወይም ካሪዝማቲክ የሆነ የሥነ መለኮት ትምህርት ባላቸውና በሌላቸው መካከል ከፍተኛ ውዝግብን አስከትሏል። ጰንጠቆስጤ (ካሪዝማቲክ) የሥነ መለኮት ትምህርትን በሚከተሉት ዘንድ የሚታየው ክርክር ያተኮረው በመንፈስ ቅዱስ ሙላትና በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መካከል ያለውን ልዩነት በመረዳት ላይ ነው። 

(ማስታወሻ፡- ጰንጠቆስጤ የሚለው ስም የመጣው ከሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ሲሆን በመንፈስ ቅዱስ በደቀመዛሙርት ላይ በኃይል የወረደበት ቀን ነው። ጰንጠቆስጤ የሚለው የግሪክ ቃል ትርጉም አምሳ ማለት ሲሆን የሚያመለክተው አይሁድ ከመቅሰፍቱ ያመለጡበት አምሳኛውን ቀን መታሰቢያ የሚያከብሩትት በዓል ነው።) በኢትዮጵያ ይህ ቃል «ጴንጤ» ተብሎ በእህጽሮት የሚጠራ ሲሆን አንዳንድ ሰዎች በሥነ መለኮት ትምህርታቸው ጴንጠቆስጤ የሆኑትንም ሆነ ያልሆኑትን የወንጌል አማኞች በሙሉ ለማንጓጠጥ ተግባር ይጠቀሙበታል። «ካሪዝማቲክ» የሚለው ቃል ደግሞ የመጣው «የጸጋ ስጦታ» ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን የሚያመለክተውም በ1ኛ ቆሮ. 12 ላይ የሚገኙትን መንፈስ ቅዱስ ለክርስቲያኖች የሚሰጠውን መንፈሳዊ ስጦታ ነው። ይህ ቃል በአዲስ ኪዳን የሚገኙ መንፈሳዊ ስጦታዎች በሙሉ በተላይ በልሳን መናገርንና ፈውስን ጨምሮ በዚህ ዘመን ለሚገኙ ክርስቲያኖችም ያገለግላሉ የሚለውን የሥነ መለኮት አሳብ ያንፀባርቃል። «ካሪዝማቲክ» የሚለው ቃል በዋና ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው (እንደ መካነ ኢየሱስና ቃለ ሕይወት ባሉ) ስለ መንፈስ ቅዱስ ከላይ የተሰጠውን አመለካከት የሚያንጸባርቁ ሰዎችን ያጠቃልላል። ጰንጠቆስጤ የሚለው ቃል ግን ብዙ ጊዜ እንደ ሙሉ ወንጌል ላሉ ቤተ ክርስቲያኖች ሲሆን እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት በእነዚህ ትምህርቶች ላይ በመመሥረት የራሳቸውን የእምነት አቋም የመሠረቱ ናቸው። ሆኖም ግን በተለምዶ አጠቃቀም ካሪዝማቲክ የሚለው ቃል በተለይ የጴንጤቆስጤ ሥነ መለኮትን ለሚከተሉ ሁሉ በስሩት ያገለግላል። 

ጰንጠቆስጤ (እንደ ሙሉ ወንጌል ያሉ) ና ጰንጠቆስጤ ባልሆኑ (እንደ መካነ ኢየሱስና ቃለ ሕይወት ባሉ) አብያተ ክርስቲያናት ያለውን የሥነ መለኮት ትምህርት የመረዳት ልዩነት ለመገንዘብ ታሪካዊ አነሣሡን መመልከት እጅግ ጠቃሚ ነው። ስለዚህ በዛሬው ትምህርት የጰንጠቆስጤ የሥነ መለኮት ትምህርት ታሪክና እንደ ሙሉ ወንጌል ያሉ አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እንደተቆረቆሩ እንመለከታለን። ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የማጥመቅና የመሙላት ሥራዎች ምን እንደሚል እንመለከታለን። በሚቀጥለው ሳምንት የጴንጠቆስጤ ሥነ መለኮት ትምህርት መሠረት በመሆን የሚያገለግሉትን ዋነኛ ክፍሎች ለመመልከት ወደ ሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንመለሳለን። 

ከመቶ ዓመት በፊት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚሰጡ ትምህርቶች በመንፈስ ቅዱስ ላይ ያላቸው ትኩረት አነስተኛ ነበር። ይልቁኑ የተለያዩ የእምነት ” ክፍሎች (መካነ ኢየሱስና ቃለ ሕይወትን የመሳሰሉ ቤተ ክርስቲያናት የወጡባቸው) ያተኮሩት ሰው እንዴት እንደሚድን፥ በሥላሴ ህልውና፥ ሰው እንዴት መጠመቅ እንዳለበት፥ ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት ጋር ስላላት ግንኙነት፥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ወዘተ… አስመልክቶ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሰፈረው ሥነ መለኮታዊ መሠረታዊ የእምነት ትምህርት ላይ ነበር። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ በተፈጠረ ልዩነት እንደ ሉተራን፥ ባፕቲስት፥ ፕርስቢቴሪያን፥ ሜተዲስት የመሳሰሉት ዋና ዋና የእምነት ክፍሎች ተቆረቆሩ። ከርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ አካላዊ ህልውና ሁልጊ ያመኑ ቢሆንም የትምህርታቸው ዋና አትኩሮት እርሱ አልነበረም። 

በታሪክ አኳያ ስንመለከተው እብዛኛዎቹ የእምነት ክፍሎች የሚያስተምሩት መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቲያን ሕይወት የሚመጣው ክርስቶስ ኢየሱስን እንዳመነ ወዲያውኑ ነው የሚል ነው። በመንፈስ ቅዱስ ላይ በሚሰጡት በዚሁ ትምህርታቸው «ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች። ይልቅ «በመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች» ላይ ያተኩራሉ። የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ልዩ በሆነ መንገድ በሕይወታቸው ከመለማመድ ይልቅ በመንፈሳዊ እድገት ላይ ያተኩራሉ። (ማስታወሻ፡— በሌሎች ክርስቲያኖች ዘንድ አመርቂ ተቀባይነት ሳይኖራቸው፥ ስለ መንፈስ ያስተማሩና የመንፈስን ድንቅ እሠራሮች ይሹ የነበሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች በዘመናት መካከል ሁልጊዜ ተከስተዋል) ብዙ ጊዜ ትምህርታቸው እጅግ ትንሽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ስለነበረው ትምህርታቸውና ልምምዳቸው እብዛኛው ክርስቲያን ከተቀበለው ያፈነገጠ ነበር። 

ከመቶ ዓመት ወዲህ ግን ይህ ሁኔታ መለወጥ ጀመረና በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሰጠው ትምህርት አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ አጥለቀለቀ። እነዚህም ትምህርቶች አዳዲስ የእምነት ክፍሎችን ከማስገኘታቸውም በተጨማሪ ቀድሞ በነበሩ የእምነት ክፍሎችም ላይ ተጽዕኖ አሳደሩ። እነዚህን ለውጦች ለመረዳት 50 ዓመታት በታሪክ ወደ ኋላ ሄደን ጆን ዌስሊ የተባለውን ሰው ታሪክ መመልከት ያስፈልገናል። 

የዘመናዊው የጰንጠቆስጤ ሥነ መለኮት ትምህርት መሠረት ከ50 ዓመት በፊት የሚኖር (የነበረ) እግዚአብሔርን የሚፈራ ታዋቂ ወንጌላዊ ወደ ነበረው ጆን ዌስሊ ታሪክ የሚወስደን ነው። በአገልግሎቱ በእንግሊዝና በአሜሪካ የሚኖሩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ተነክቷል። በአገልግሎቱ የተቆረቆረው የእምነት ክፍል ‹ሜተዲስት› የእምነት ክፍል ይባላል። ለጆን ዌስሊ ትምህርት እጅግ መሠረታዊው አሳብ ክርስቲያን በክርስትና ሕይወቱ በሁለት ዋና ልምምዶች ያልፋል የሚለው ነው። በመጀመሪያ፥ የድነት (ደኅንነት) ልምምድ ውስጥ ያልፋል። ይህ ክርስቲያኖች ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ሲያምኑ የሚፈጸም ነው። መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ለመኖር የሚመጣውም በዚህ ጊዜ ነው። ሁለተኛው ልምምድ ደግሞ፥ (ሁለተኛ በረከት› በመባል ይታወቃል። ጆን ዌስሊ በብዙ ጸሎት የእግዚአብሔር ኃይል (በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በመባል የሚታውቀው) በክርስቲያን ላይ ይወርዳል ብሎ ያስተምር ነበር። በዚያን ጊዜ ክርስቲያን በፍጹም ቅድስና ለመኖር ይችላል። መንፈስ ቅዱስ በአንድ ድርጊት የተሳሳቱ ውስጣዊ እሳቦችን በሙሉ ፈጽሞ በማስወገድ ሰው የተፈጠረለትን ታላቅ ቅድስና ያጎናጽፋል። ይህ ሁለተኛ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጅማሬ ከቁጥጥር ያላፈ ለቅሶ ወይም የሳቅና የደስታ ጩኸት የመሳሰሉ ታላቅ ስሜታዊ ድርጊቶችን ያካትታል። 

ኋላም በ1901 ዓም በአሜሪካ የሚኖር የሜተዲስት ሰባኪ ስሙ ቻርልስ ፍክላ ፓርሃም ይባል የነበረ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ያስተምር ነበር። እርሱና ተማሪዎቹ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን ሊያጠኑ አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስን የመቀበሉ አንድ ማስረጃ በልሳን መናገሩ ነው ብለው እመኑ። በልሳን የመናገር ስጦታ ለመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ከተሰጠ ከዚያም በኋላ ላሉ ክርስቲያኖች ሁሉ መሰጠት አለበት ይሉ ጀመር። በዚህ ዓይነት የጰንጠቆስጤ የሥነ መለኮት ትምህርት ተወሰደና እንደ ሰደድ እሳት በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ተስፋፋ። ከመዳን ሌላ ሁላተኛ ዋነኛ ልምምድ እንደሚያስፈልግ ጆን ዌስሊ በሰጠው ትምህርት ላይ የጰንጠቆስጤ ሥነ መለኮት፥ ይህ ታላቅ በረከት ከመንፈስ ቅዱስ ለክርስቲያን ለመሰጠቱ ማረጋገጫው በልሳን መናገር ነው የሚለውን ያክልበታል። ይህ ትምህርት በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ክፍተኛ ውዝግብን በመፍጠሩ አብያተ ክርስቲያናት መክፋፈል ጀመሩ። በዚህ መሠረት ጉባዔ እግዚአብሔር (አሴምብሊስ ኦፍ ጎድንና ሙሉ ወንጌል የሚባሉ የእምነት ክፍሎች ተመሠረቱ። 

የጴንጠቆስጤ ሥነ መለኮት ትምህርት መሠረት መደበኛው ክርስቲያናዊ ሕይወት ሁለት ደረጃዎች አሉት የሚል ነው። የመጀመሪያው፥ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝ አድርጎ መቀበል ነው። ሁለተኛው ደረጃ ፥ «በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ» ነው። ይህ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ደግሞ ሁልጊዜ የሚረጋገጠው በልሳን በመናገር ነው። ደግሞ ክርስቲያኖች ሁሉ እግዚአብሔርን ቢጠይቁና ቢያምኑ ለሁሉም የሚሰጥ ነው። (ማስታወሻ፡-ከዚህ ጊዜ በፊት ሰላሳን የሚናገሩ ክርስቲያኖች የነበሩ ቢሆንም እንኳ ለመንፈስ ቅዱስ ህልውና ዋናው ምልክት ስለ መሆኑና ደግሞም ሁሉ ክርስቲያኖች ሊለማመዱት እንደሚያስፈልግ ቤተ ክርስቲያን ያስተማረችበት ይህ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው ጊዜ ነበር።) 

ጥያቄ፡- ይህ ትምህርት በኢትዮጵያ የሚገኙ ክርስቲያኖችን የነካው በምን መንገድ እንደሆነ አብራራ። 

ለመንፈስ ቅዱስ ህልውና ተቀዳሚ ምልክት በልሳን መናገር ቢሆንም የጰንጠቆስጤ ትምህርት ተከታዮች በአንደኛው ምእተ ዓመት ኢየሱስ የሠራውን ሐዋርያትም የፈጸሙትን ተአምራት በዘመናችን ያሉ ክርስቲያኖች ሊያደርጉት ይችላሉ በማለት አተኮሩበት። ስለዚህ በጸሎት አማካይነት በሚገኝ ፈውስ ላይ እየጎለበተ የሚሄድ ትኩረት ያደርጉ ጀመር። በአምልኮ ጊዜ በስሜታዊነት ማምለክ ሌላው የትኩረት አቅጣጫቸው ነበር። 

የጴንጤቆስጤ ሥነ መለኮት ትምህርት እንዲጀምርና በአሜሪካ+ በአውሮፓና አሁን ደግሞ በዓለም ሁሉ በፍጥነት እንዲስፋፋ ራሱን የቻለ ምክንያት ነበረው። ታሪካዊ የነበሩት አብዛኛዎቹ የእምነት ክፍሎች በመንፈሳቸው ሞተው ነበር። ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሄዱት ባሕላዊ ተግባር ስለሆነ ብቻ ነበር። በእንድ የእምነት ክፍል ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች ሆነው ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሄዱት ምርጫቸው ሆኖ ሳይሆን ወላጆቻቸው ይህንን ያደርጉ ስለነበር ብቻ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር የግል ግንኙነት አልነበራቸውም። የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከለዘብተኛ የሥነ መለኮት ሊቃውንት አስተሳሰብ በመውሰድ፥ መጽሐፍ ቅዱስ በስሕተት የተሞላ ስለሆነ ልንታመንበት አንችልም በማለት ማስተማር ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ መልካም የሥነ ምግባር ትምህርቶችን፥ ተአምራት፥ የኢየሱስ ትንሣኤ፥ በመሳሰሉ እውነተኛ ክስተት ባልሆኑ ጥንታዊ አፈ ታሪኮች የተሞላ ነው አሉ። ሃይማኖቶች በሙሉ ሰው የሠራቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ያልተገኙ ናቸው በማለት ማስተማር ጀመሩ። 

የእምነት ክፍሎች ከመካከላቸው የመንፈስ ቅዱስን ኃይል እየተገፋፉ ከእውነት እየራቁ ሲሄዱ ሰዎች ከሕያው እግዚአብሔር ጋር የግል ግንኙነት ለማድረግ መናፈቅ ጀመሩ። የእግዚአብሔር ኃይል በግልጥ ይታይበት የነበረውን የመጀመሪያዋን ምእተ ዓመት የክርስትና ሕይወት መራብ ጀመሩ። ስለዚህ ከእግዚአብሔርና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የግል ግንኙነት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ትኩረት ስለምትሰጥ ቤተ ክርስቲያን ሲሰሙ፤ በዚህ የግል ግንኙነት በልሳን መናገርን ተአምራት ማድረግን በመሳሰሉ አስደናቂ መንገዶች የሕያው እግዚአብሔርን ኃይል እንደሚያዩ ሲሰሙ ሕዝቡ ለአዲሱ ትምህርት ልባቸው ክፍት ሆነ። ሌሎች የእምነት ክፍሎች ከተመሠረቱበት ሁኔታ በተለየ የጰንጠቆስጤ ትምህርቶች በብዙ ክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም። ምክንያቱም ከሕያው እግዚአብሔር ጋር የግል ግንኙነት የሚያደርጉበትን ኃይል የመላማመዱ ስሜታቸው ጥማታቸውን ስለሚያረካ የእነርሱ እምነት በሥነ መለኮታዊ ይዘቱ ሌሎች የእምነት ክፍሎች ከሚያስተምሩት የበለጠ ትክክልና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ስለሚሉ ነው። ዋና ትኩረታቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተገለጸው ሁኔታ እውነትን መረዳት ሳይሆን እግዚአብሔርን መለማመድ ነበር። 

ጥያቄ፡– ሀ) አብያተ ክርስቲያናት ላብ እያሉ መሄዳቸውና ሃይማኖትንም ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ ግንኙነት አድርጐ ከማየት ይልቅ እንደ ባሕላዊ ተግባር የመቁጠር አደገኛ አዝማሚያ ዛሬም በኢትዮጵያ የሚከሰተው እንዴት ነው? ለ) ይህ ነገር ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ያሉ ሰዎች ታሪካዊ የእምነት ክፍሎቻቸውን በመተው የካሪዝማቲክ አብያተ ክርስቲያናትን የመቀበል ዝንባሌያቸው እንዲያይል የሚገፋፋው እንዴት ነው? 

የጰንጠቆስጤ የሥነ መለኮታዊ ትምህርትና የጰንጤቆስጤ አብያተ ክርስቲያናት በተመሠረቱ በአሥር ዓመታት ጊዜ ውስጥ በዓለም ሁሉ ተሰራጭ። ብዙም ሳይቆይ የጰንጤቆስጤ አብያተ ክርስቲያናት እያንዳንዳቸው ለመንፈስ ቅዱስ ህልውና ማረጋገጫ ነው የሚለውን ባክላ ቁጥር አብያተ 

ክርስቲያናቱ መከፋፈል ጀመሩ። ከዋና ዋና ክፍፍሎች አንዱ በ1911 ተገንጥሎ የወጣው «የኢየሱስ ብቻ» ቡድን ነው። ይህ ቡድን የተጀመረው በአሜሪካ ሲሆን ሥላሴ የሚባል ነገር የለም ብሎ ማስተማር ጀመረ። ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ፥ አብም መንፈስ ቅዱስም ነው ይላሉ። በእነርሱ እምነት ብቸኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥምቀት በኢየሱስ ስም የሚደረገው ነው። ሰው የሚድንበት ነው ብለው የሚያስተምሩት ይህ የውኃ ጥምቀት በልሳን በመናገር መረጋገጥ አለበት። አለበለዚያም ዋጋ የለውም ይላሉ። 

ጥያቄ፡- ይኽው ትምህርት ዛሬ በኢትዮጵያ የሚታየው እንዴት ነው? 

የጰንጠቆስጤ ትምህርት የመጀመሪያው አምሳ ዓመታት እንቅስቃሴ ብዙ ጊዜ የሚያመራው በተናጠል የሚቆሙ ከየትኛውም ቤተ ክርስቲያን ወይም የእምነት ክፍል ጋር ያልወገኑ አብያተ ክርስቲያናት ሦሥረታ ላይ ነበር። በ1947 ዓ.ም ግን ዋና ዋና የሚባሉ የጰንጠቆስጤ አብያተ ክርስቲያናት ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር እራሳቸውን በማጣመር እንደ ጉባኤ እግዚአብሔር አሴምብሊስ ኦፍ ጋድ)ን ሙሉ ወንጌል ባሉ የእምነት ክፍሎች ተደራጁ። 

በ1960 ዓ.ም. የጰንጠቆስጤ እንቅስቃሴ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሻገረ። ብዙ የሥነ መለኮት ትምህርት አስተማሪዎች ይህን እንቅስቃሴ አዲስ የጰንጠቆስጤ እንቅስቃሴ ይሉታል። አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት ከመመሥረት ይልቅ ይህ አዲስ ጰንጠቆስጠ ወይም በሌላው ስሙ የካሪዝማቲክ ተሐድሶ እንቅስቃሴ የሚባለው ታሪካዊዎቹን የእምነት ክፍሎች ላመለወጥ ጥረታቸውን ቀጠሉ። ለመጀመሪያ ጊዜ በልሳናት መናገር ሌሎች የጰንጠቆስጤ ትምህርቶች በባሕላዊዎቹና በቆዩት የእምነት ክፍሎች ውስጥ ባሉ አንዳንድ ሰዎች ተቀባይነት ማግኘት ጀመሩ። ብዙም ሳይቆዩ ዋና ዋና በሚባሉ የእምነት ክፍሎች ማለትም በሉተራውያን፥ በፕረስቢቴርያውያን፥ በባፕቲስቶችና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እንኳ ለእምነት ክፍላቸው ታማኝ ተከታዮች ሆነው በልሳናት መናገርን ግን የሚያስፋፉ ሰዎች እየበረከቱ መጡ። ይህ ብዙ ጊዜ አንደኛው ቤተ ክርስቲያን የካሪዝማቲክ ትምህርቶችን ሊቃወም ሌላኛው ቡድን ደግሞ በልሳን መናገርን የሚለማመድን የቤተ ክርስቲያን መከፋፈል አስከተለ። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ 51 ሚሊየን የሚደርሱ ጴንጠቆስጤ ክርስቲያኖች ያሉ ሲሆን ይህም በዓለም ላይ ካለው የፕሮቴስታንት ክፍል ትልቁ ያደርጋቸዋል። በዋነኞቹ የእምነት ክፍል ውስጥ ካሉት ክርስቲያኖች ደግሞ አሥራ አንድ ሚሊየኑ ካሪዝማቲክ ናቸው።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.