መግቢያ

ዮሐንስ ጌታን የሚወድ አዲስ ክርስቲያን ነበር። ኢየሱስ ከኃጢአቱ እንዳዳነው ያውቃል። ልቡ በደስታ የተሞላ ከመሆኑ የተነሣ እግዚአብሔር በሕይወቱ ስላደረገው ለውጥ ላገኛቸው ሰዎች ሁሉ ይናገር ነበር። አንድ ቀን አንድ ክርስቲያን አገኘውና መንፈስ ቅዱስ ተሞልተሃልን? በማለት ጠየቀው። ጥያቄውም ራ አጋባው። «ወመንፈስ ቅዱስ እርሱ ማን ነው? ወይም ምንድን ነው? መንፈስ ቅዱስ እንደተሞላሁ እንዴት አውቃለሁ?» በአእምሮው ጥርጣሬ ሞላሰትና ወዲያውኑ ደስታው ከእርሱ ተለየ። በርካታ ክርስቲያኖችን ስለ መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ጥያቄዎች መጠየቅ ጀመረ። አንዳንዶች ላላ መንፈስ ቅዱስ መጨነቅ አያስፈልግህም ኢየሱስ ብቻ ይበቃል አሉት። ይህን ወዳሉት ክርስቲያኖች ሕይወት ሲመለከት ግን ሕይወታቸው ደስታ፥ ኃይል እና መታዘዝም የማይታይበት መሰለው። ሌሎች ደግሞ ስለ መንፈስ ቅዱስ ከመጠን በላይ ይናገራሉ። እንዳ በሆኑ ቋንቋዎች እየጮችና ሰውነታቸው እየተንቀጠቀጠ ይጸልያሉ። ለመንፈስ ቅዱስ መገኘት እውነተኛ ምልክት ይህ ነውን? ትክክለኛው ማን ነበር? ሰው ስለ መንፈስ ቅዱስ እውነተኛውን ነገር ለማወቅ ወደየት ነው መሄድ ያለበት? 

ጥያቄ፡– መንፈስ ቅድስን በሚመለከት በክርስቲያኖች መካከል ያለውን እንዲህ ያለ ግራ መጋባት እንዴት አየኸው? 

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ዙሪያ እጅግ አስደናቂ በሆኑ መንገዶች እየሠራ ለመሆኑ ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለም። በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በእምነት ወደ ክርስቶስ እየመጡ እየጻኑ ነው። ሰዎች መንፈሳዊና ሥጋዊ ፈውስን እያገኙ ናቸው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ክፍተኛ መንፈሳዊ ረሃብ በሕዝቡ ሕይወት ይታያል። በዚህች ታላቅ ምድር ለመኖርና ለመሥራት መታደላችን እንዴት ደስ የሚያሰኝ ነው! 

ይሁንና፥ ይህ ዘመን በርካታ አብያተ ክርስቲያኖቻችንን እየበከሉ ኑፋቄዎችና ሐሰተኛ ትምህርቶች በምድሪቱ በፍጥነት የሚስፋፉበትም ነው። እራሱን የብርሃን መልአክ አድርጐ የሚያቀርበው ሰይጣን (2ኛ ቆሮ. 11፡14) በሥራ ላይ ነው። አብዛኛው የሰይጣን ሐሰተኛ ትምህርት የሚያተኩረው በመንፈስ ቅዱስ፥ ህልውናው በሚረጋገጥበት መንገድ እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባለው ተቀዳሚ ሚና ላይ የተሳሳቱ አሳቦችን በመናኘቱ ተግባር ላይ ነው። ሰይጣን ግራ መጋባትን ለመፍጠርና የእግዚአብሔርን ሥራ ለማደናቀፍ የሚያደርጋቸውን ሙከራዎች ነቅተን መገንዘብ አለብን። 

አንድ ሰው ስለ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ለመጻፍ በሚነሣበት ወቅት ከአሳቡ ጋር የማይስማሙ በርካታ ክርስቲያኖች ሊገጥሙት እንደሚችሉ ገና ከጅምሩ ያውቀዋል። መንፈስ ቅዱስ ማን ነው? ዛሬ በዓለም ላይ የሚሠራው ሥራና ዓላማው ምንድን ነው? ህልውናው የሚገለጠው እንዴት ነው? በልሳናት በመናገርና በተአምራታዊ ፈውሶች ነውን? እነዚህ ጥያቄዎች በሺህ በሚቆጠሩ ክርስቲያኖች የሚጠየቁ ሲሆን፥ በበርካታ የተለያዩ መንገዶችም ክርስቲያኖች መልስ ይሰጡባቸዋል። የሚያሳዝነው ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት እውነቶች አንዱ የሆነውን የመንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች ማደር ጉዳይ ወደ ጸብና ክርክር መለወጡ ነው። አንድነታችን እንቆብርና በኃይል ተሞልተን ወንጌል የሚጠይቀውን ዓይነት ሕይወት መኖር እንድንችል እግዚአብሔር ላቤተ ክርስቲያን የሰጠውን መንፈስ ቅዱስ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ይረዱታል። በዓለም ዙሪያ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ታላቅ መከፋፈልን ላማምጣት ሰይጣን ይህን ሁኔታ እየተጠቀመበት ነው። ይህ እንዴት አሳዛኝ እውነታ ነው! በክርስቲያኖች መካከል በሚከናወን እንዲህ ዓይነት መከፋፈል አንጀቱ የሚርሰው ሳይጣን ብቻ ነው። 

ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት በመንፈስ ቅዱስ ወይም ከአገልግሎቶቹ በአንዱ ክርስቲያኖች እንዴት ሊለያዩ እንዳየህ ግለጽ። 

የዚህ የጥናት መጽሐፍ ዓላማ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረውን መመርመር ነው። ጌታን የሚወዱና የሚያገለግሉ ግን ስለ መንፈስ ቅዱስ የተለዩ እምነቶች ያሏቸው ክርስቲያኖች እንዳሉ ሰላማውቅ፥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሚዛናዊ የሆነ አመለካከትን ለማቅረብ እሞክራለሁ። ጸሎታችን እግዚአብሔር በአብያተ ክርቲያናት መካከል አንድነትን ለማምጣት ይህን መጽሐፍ እንዲጠቀምበትሩ ክርስቲያኖች ዛሬ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሾልከው በመግባት የሚሰጡትን ትምህርቶች በመቀበል ወደ ስሕተት እንዳይወድቁና ሁሉ በላይ ደግሞ «በመንፈስ እንመላለስ። (ገላ. 5፡5) ዘንድ እንዲረዳን ነው። መልስ የምንሰጥበት ተቀዳሚ ጥያቄ «መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረው ምንድን ነው?» የሚለውን ነው።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

2 thoughts on “መግቢያ”

  1. yifat denbarga

    ይህንን እንድታዘጋጁ ጸጋዉን የሰጣችሁን እና በእናንተ ዉስጥ የሰራዉን እግዚአብሔርን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አመሰግናለሁ እባርካለሁ። በጣም ጥሩ ድህረ ገጽ ነዉ ባጣም እየተማርኩበት ነዉ ተባርኬአለሁ።ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባርካቸሁ ቀጥሉበት።

  2. ውድ ቤተ ሰቦቼ ተባረኩልኝ!!! የጌታ ጸጋ ከዚህ በላይ ይብዛላችሁ!!!
    (የዘወትር ተከታታያችሁ ገበየሁ ነኝ)

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading