መንፈስ ቅዱስ እንድናመልክ ይረዳናል

መንፈስ ቅዱስ አንድ ሰው ከእግዚአብሔር አብና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲያደርግና እንዲያመልክ በልቡ ውስጥ የሚሰጠው አገልግሎት። 

በቤትህ ውስጥ ለብቻህ ሆነህ መጽሐፍ ቅዱስህን አንሥተህ ታነባለህ። የመነቃቃት መንፈስ በውስጥህ ይሰማህና ልዩ መዝሙር በመዘመር መጸለይ ትጀምራለህ። የእግዚአብሔር እውነት በጣም ያስተምርሃል። በጣም ቅርብህ እንደሆነና ባለህበት ክፍል ውስጥ እንዳለ ያህል ይሰማሃል። ወይም፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቁጭ ብለህ ስትዘምር፥ መዘምራን ሲዘምሩ ወይም ሰባኪው ሲሰብክ ስማዳመጥ ላይ ሳለህ በድንገት በኃይለኛ ስሜት ምስጋና ከውስጥህ ፈንቅሎ እስኪወጣ ድረስ የእግዚአብሔር ህልውና ይሰማሃል። ይህ ታላቅ የእግዚአብሔር ህልውና ስሜት የሚመጣው ከየት ነው? ስሜትህ ብቻ ነው ወይስ እየተፈጸመ ያለ ልዩ ነገር አለ? መልሱ፥ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔርን ለአንተ እውን ስላደረገልህ ነው። 

ጥያቄ፡- እግዚአብሔር በቅርብህ እንዳለ የተሰማህን አጋጣሚ ሁኔታ ግለጽ። ያ ጊዜ ልዩ የሆነልህ እንዴት ነው? 

ከመንፈስ ቅዱስ ዋና አገልግሎቶች አንዱ በሕይወታችን የእግዚአብሔርን ህልውና እውን ማድረግ ነው። እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ዘመን እንዳደረገው አሁን በሰው ሠራሽ ቤት ውስጥ አይኖርም። እግዚአብሔር የሚኖረው በቤተ ክርስቲያንም ሕንፃ ውስጥ አይደለም። እግዚአብሔር የሚኖረው በሰዎች ውስጥ ነው። እያንዳንዱ ክርስቲያንም ሆነ የክርስቲያኑ ማኅበረሰብ «የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ» ናቸው። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በዚያ ይኖራል። በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ህልውና አሑዱ ሥሉስ የሆነው አምላክ በዚያ ይገኛል። ስለዚህ ልባችን አሁን አምልኮ የሚካሄድበት ማዕከል ሆኗል ማለት ነው። መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን በሚኖርበት ጊዜ ኅብረታችንን ከእግዚአብሔር ጋር እውን የሚያደርጉና እርሱን እናመልከው ዘንድ የሚያነሣሡንን የተለያዩ አገልግሎቶች ይፈጽማል። 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። ሮሜ 8፡16፡26-27፤ 2ኛ ቆሮ. 13፡14፤ ገላ. 4፡6፤ ኤፌ. 2፡18፥ 22፣ 6፡17-18፤ ፊልጵ. 2፡1፤ 1ኛ ዮሒ ፡24፤ 4፡13 ይሁዳ 19። ሀ) በዚህ ስፍራ የተገለጹትን የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች ዘርዝር። ለ) እነዚህ አገልግሎቶች እያንዳንዳቸው ማበረታቻ የሚሆኑህ በምን መንገድ ነው? 

ከላይ ባነበብካቸው ጥቅሶች መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት ይረዳን ዘንድ በውስጣዊ ሕይወታችን እንደሚሠራ ለመመልከት እንችላለን። ይህ ቀንኙነት የበለጠ እውን ይሆን ዘንድ የሚያደርጋቸው ነገሮች አንዳንዶቹ ቀጥለው ተዘርዝረዋል (ቀርበዋል)። 

ሀ. አሐዱ ሥሉስ የሆነው እግዚአብሔር በውስጣችን እንደሚኖር ያስገነዝበናል (1ኛ ዮሐ 3፡24፤ 4፡13፤ ኤፌ. 2፡19-22)። እግዚአብሔር ያለው ሊደረስበት በማይችል ሩቅ ሰማይ ላይ አይደለም። እንዲሰማን መጮህ የለብንም። እግዚአብሔር በቅርባችን ነው። በልባችን ይኖራል። ሆኖም ቀን ሥጋዊ አካል ስለሌለው በቅርባችን መኖሩ ብዙ አይሰማንም። የልብ ራጅ ብንነሣ እንኳ እግዚአብሔር በዚያ መኖሩን ማረጋገጥ እንችልም። ስላ ህልውናው በስሜታችን ባንገነዘብም እንኳ እርሱ ከእኛ ጋር እንዳለ እናውቃለን። ይህን እንዴት እናውቃለን? በልባችን የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ለመንፈሳችን ህልውናውን ይመሰክርልናል በመመስከር ያረጋግጥልናል)። ክርስቲያኖች ሕያዋን ድንጋዮች መሆናቸውንና እኛም ለኃያሉ እግዚአብሔር መኖሪያ የሚሆን ሕያው ቤተ መቅደስ ሆነን እንድንሠራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም «ሕያዋን ድንጋዮች» አድርጎ እንደሚገጣጥመን፥ ጳውሎስ ከትላልቅ ውቅር ድንጋዮች የተሠራውን ጥንታዊ ቤተ መቅደስ ስማነፃፀሪያነት በማቅረብ ይነግረናል (ኤፌ 2፡19-22፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡4-5)። 

ለ. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆንን ይመሰክርልናል (ሮሜ 8፡16፤ ገላ. 4፡6)። እግዚእብሔርን ማምለክ አስገራሚ የሆነ የተለያዩ ስሜቶች ቅንብር ነው። በአንድ በኩል ‹ፍርሃት» እለ፤ የምናመልከው እግዚአብሔር ታላቅ፥ ብርቱ፥ ግርማ የተሞላና ቅዱስ ነው። እግዚአብሔር የሚባላ እሳት እንደሆነ ተጽፎልናል (ዕብ. 12፡29)። በመጽሐፍ ቅዱስ ሰው ወደ እግዚአብሔር በቀረበባቸው ማናቸውም ጊዜያት በእግዚአብሔር ፊት በፍርሃት ለመስገድ እንደሚገደው ተጽፏል። እግዚእብሔርን ሁሉን ቻይ ፈጣሪ አድርገን ማክበር ካለብን በልባችን ፍርሃትና አክብሮት ሁልጊዜ መኖር ይገባናል። 

በሌላ በኩል ደግሞ ጠንካራ የፍቅርና የቀረቤታ ስሜት አለ። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርት ከዚህ በኋላ ወዳጆች እንጂ ባሮች አይደላችሁም ብሎ ተናግሮአቸዋል (ዮሐ 5፡13-15)። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ አስደናቂ እውነቶች አንዱ ለጥፋት የተዘጋጀን የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነን ሳላን የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን ነው (ዮሐ 1፡12)። የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል ነን። ይህን እንዴት እናውቃለን? መሆን ያለብንን ያህል ጻድቅ ሳንሆንም እንኳ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን በማወቃችን የሚመነጨውን ይህን እጅግ የተትረፈረፈ የፍቅር ስሜት የሚሰጠን ምንድን ነው? በልባችን ውስጣዊ ክፍል መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን በሹክሹክታ ድምፅ ይመሰክርልናል፥ ይነግረናል፥ ያሳስበናል። በእግዚአብሐር እጅግ የተወደድን የኢየሱስ ወንድሞችና እህቶች ነን። ኃጢአትን በምናደርግበት ጊዜ እንኳ መንፈስ ቅዱስ ይህን አስደናቂ እውነት በየጊዜው ያስታውሰናል። 

ጥያቄ፡- የመንፈስ ቅዱስን የመጀመሪያ ሁለት አገልግሎቶች በሕይወትህ እንዴት እንደተለማመድካቸው ግልጽ። 

ሐ. መንፈስ ቅዱስ ወደ እግዚአብሔር ፊት የመቅረብ ዕድልን ይሰጠናል (ኤፌ 2፡18፤ 6፡17-18፤ ይሁዳ 19)። ወደ ከፍተኛ ባለሥልጣን ቢሮ ስንሄድ ወደ እርሱ ከመድረሳችን በፊት ማለፍ ያለብን በርካታ መሳናክሎች አሉ። በመጀመሪያ በቅጥሩ መግቢያ ላይ ወታደሮች ያጋጥሙናል። ቀጥሎ በቢሮው በራፍ ወታደር ያጋጥመናል። በመጨረሻም ቀጠሮ እየተቀበላች የምታገናኝ የባለሥልጣኑን ጸሐፊ እናገኛለን። ይህ ሁሉ የሚደረገው ሰዎች ወደ ባለሥልጣኑ ዘንድ በቀላሉ መቅረብ እንዳይችሉ ነው። እንድ ጠላት መሆኑ በግልጽ የሚታወቅ ሰው ወደ ባለሥልጣኑ ቢሮ ለመግባት ሲሞክር ፈጽሞ አይሳካለትም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ አስደናቂ እውነቶች አንዱ እግዚአብሔር ሰውን ከግራቅ ይልቅ ወደ እርሱ ይቀርብ ዘንድ መንገዱን ቀላል ማድረጉ ነው። አዎን የእግዚአብሔር ጠላቶች ነበርን። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕዳችንን በመስቀል በመክፈሉ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት እንዳንችል የሚያደርጉንን ዋነኛ መሰናክል አስወገደልን። ዋነኛው መሰናክል የተወገደ ቢሆንም እንኳ ወደ እግዚአብሔር አብ ህልውና የሚያቀርበን ያስፈልገናል። ይህም የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ነው። ወደ እግዚአብሔር ህልውና የሚያቀርበን እርሱ ነው። ይህንን እንዴት ያደርጋል? በተቀዳሚ በጸሎታችን አማካኝነት ነው። የአንድ ዕጣን ሽታ ከጢሱ ጋር እንደሚመጣ መንፈስ ቅዱስ ከጸሎታችን ጋር በመሆን ጸሎታችንንና እኛን ወደ እግዚአብሔር ህልውና ያስገባናል። ስለዚህ የምንጸልየው እጅግ ርቆ በሰማይ ላለና ልንደርስበት ወደማንችል እግዚአብሔር አይደለም። መንፈሳችን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ እግዚአብሔር ህልውና ይቀርብና ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ለማድረግ እንችላለን። ምን ዓይነት አስደናቂ አሳብ ነው። በመካከላችን አንዳችም መሰናክል ሳይኖር በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ እንደምንገኝ ሁልጊዜ ብንገነዘብ ጸሎታችን እንዴት እውነተኛ ይሆን ነበር! 

መ. መንፈስ ቅዱስ እንድንጸልይ መርዳት ብቻ ሳይሆን ራሱም °ጸልይልናል (ሮሜ 8፡26-27)። ሁለት ልጆች ስለነበሩት አንድ ንጉሥ አስብ፥ ንጉሡ እንደሚወድህ ታውቃለህ። ያ ብቻ ሳይሆን ከሁለት ልጆቹ ጋርም ልዩ ግንኙነት አለህ። አንድ ቀን ችግር ውስጥ ወደቅህ። ይህን ሁኔታህን ሁለቱም ልጆች እውቁት። ወደ ንጉሥ ቀርበህ ስለ ችግርህ ከመናገርህ በፊት እነዚህ የንጉሥ ልጆች ተራ በተራ ወደ አባታቸው በመቅረብ ላለ ችግርህ ላንጉሡ ያጫውቱታል። እንድ ላይ በመሆን ከችግርህ ትወጣ ዘንድ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ተመካከሩ። ወደ ንጉሡ ፊት ስትቀርብ ችግርህን እንዴት እንደምትፈታ ነገሩህ። ኃላፊነት በመውሰድ ችግርህን ሙሉ በሙሉ ለማቃለልም ፈቃደኞች ሆኑ። 

ጳውሎስ በሮሜ 8 ላይ በሥዕላዊ አገላለጽ ያቀረበው ይህ ነው። ጳውሎስ የእግዚአብሔር ልጆች የሚደርስባቸውን አብዛኛዎቹን ችግሮች ያውቅ ነበር። በውስጥ ኃጢአተኛና ደካማ የሆነ ተፈጥሮ በውጭ ደግሞ ጠላቶች፥ ስደትና ሞትም ይታገሏቸው ነበር። የሚያጋጥሙን ችግሮች አብዛኛዎቹ እኛ መፍትሔ ልናገኝላቸው የምንችል አይደሉም። በእንደዚህ ዓይነት ጥልቅ ችግር ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ ሊረዳንና ሊያበረታታን የሚችለው ምንድን ነው? ጳውሎስ ወደ ሦስት ነገሮች ያመለክተናል። በመጀመሪያ፥ እጅግ የሚወደን አባት አለን፥ ጥልቅ ከሆነ ፍቅሩም የሚለየን የለም (ሮሜ. 8፡39)። በሁለተኛ ደረጃ ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ ሆኖ ይማልድልናል። ጳውሎስ በዚህ ስፍራ ለማለት የፈለገው እግዚአብሔር አብ በእኛ ደስ ስለማይሰኝ ሊቀጣን እንደሚፈልግ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ቅጣቱን ለማስቀረት እንደሚማልድልን አይደለም። ይልቁኑ እግዚአብሔር አብ ይወድደናል። ነገር ግን ይህ በቂ ባይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእብ ጋር በመሆን ለችግሮቻችን መፍትሔ ይፈልጋሉ። በሦስተኛ ደረጃ ፥ ይህም በቂ ካልሆነ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር በመሆን መፍትሔ እንድናገኝ ይረዳናል። እርሱም ደግሞ ስለ እኛ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር አብ ይማልድልናል። 

እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሁላቸውም ስለ እኛ ይሠራሉ። ይህ ምን ዓይነት መተማመን ይሰጠናል! ከእቅማቸው በላይ የሚሆን ምንም ችግር የለም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ያሸንፈናል? ከእግዚአብሔር ፍቅር ማን ይለየናል? ታላቁ ጠላታችን ሞትም ቢሆን እንኳ ይህን ለማድረግ አይችልም (ሮሜ 8፡31-39)። 

የሚያጋጥሙን ችግሮች ሊያሽንፉን የሚያስቡበት ጊዜያት በሕይወታችን ይከሰታሉ። ለምሳሌ የምንወዳቸው በሞት ሲለዩን ለመጸለይ እንኳ ፈጽሞ እስከሚያቅተን ድረስ ልባችን ይሰበራል። ለእግዚእብሔር ልንነግረው የምንፈልገው እጅግ ብዙ ነገር ቢኖረንም እንኳ የምንናገርበት ቋንቋ እናጣለን። ለመጸለይ ባንችልም ከእግዚአብሔር የምንርቅበት ታላቅ የመለየት ጊዜ ከመሆን ይልቅ ታላቅ የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የሚገለጽበት ወቅት ይሆናል። በቅጽበት ከእኛ ጎን ይሆንና ስለ እኛ ይማልድልናል። ጳውሎስ እንደሚነግረን የእግዚአብሔርን አእምሮ የሚያውቀው መንፈስ ቅዱስ ስለ እኛ በመጸለይ ይቃትትልናል (ሮሜ. 8፡26፡27)። አንዳንድ የጴንጤቆላጤ ክርስቲያኖች ይህ ሊነገር በማይችል የእምልኮ ቋንቋ ለእግዚአብሔር በልሳን በምንጸልይበት ጊዜ የሚሆን ነው ብለው ያስተምራሉ። ጳውሎስ የሚናገረው ግን ስለ አምልኮ ሳይሆን ስለ ድካም ነው። ስለዚህ ይህ መቃተት በጸጥታ የሚሆን የመንፈስ ቅዱስ የጸጥታ ድምፅ ሆኖ ለእግዚአብሔር አብ ብቻ የሚሰማ ነው። 

ጥያቄ- ሀ) ለመጸለይ ጨርሶ ያቃተህን የሕይወት አጋጣሚ ግለጽ። መንፈስ ቅዱስ እንደሚጸልይልህ ማወቅ ለሕይወትህ ማበረታቻ የሚሆነው እንዴት ነው? ለ) በጸሎት አማካኝነት እንደ እግዚአብሔር ልጅ ስእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ መሆንህ ጸሎትህን የበለጠ ትርጉም ያለው የሚያደርገው እንዴት ነው? 

ሠ. መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ኅብረት ያደርጋል። ከመንፈሳችን ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት አለው (2ኛ ቆሮ. 13፡14፤ ፊልጵ. 2፡1)። በጊዜ ሂደት ከቅርብ ጓደኛ ጋር ያለን ግንኙነት እየጎለበተ እንደሚሄድ ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለን ግንኙነት ያድግና በመንፈሳዊ ይዘቱ የበሰለ ይሆናል። ዓመታት በተቆጠሩ መጠን ክእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት ይጨምራል። በሚናገረን ጊዜ እርሱን የመስማት ችሎታችን እያደገ ይሄዳል። እጅግ የቀረበ ጽኑ ጓደኛችን ይሆናል። 

ረ. መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔርን በሚያከብር መንገድ አምልኮ እንድናደርግ ይረዳናል (ፊልጵ. 3፡3)። ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላ ካዘዘኝ ሰኋላ መሞላታችን በቅኔና ዝማሬ እንዲሁም በመንፈሳዊ ዜማ ስሌሎች ክርስቲያኖች ፊት መረጋገጥ እና በተጨማሪ ልባችንን ወደ እግዚአብሔር በማቅናታችን መገለጽ እንዳለበት ይነግረናል (ኤፌ. 5፡19፤ 6፡18-19)። 

ጥያቄ፡- ሀ) እነዚህ ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች የእግዚአብሔርን ህልውና በሕይወታችን ዛሬ ለእኛ ተፈላጊና እውነተኛ የሚያደርጉት እንዴት ነው? ለ) መንፈስ ቅዱስ እነዚህን እገልግሎቶች በሙሉ ነበሕይወትህ ሲፈጸም እንዴት እንደተሰማህ ምሳሌዎችን ዘርዝር።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.