Site icon

በክርስቲያኖች መካከል ከፍተኛ ልዩነት የሚፈጥሩ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ክፍሎች (ክፍል 1)

ጥያቄ፡- ሀ) በሕይወትህ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ህልውና ልዩ እውነታ ያደረገባቸውን ጊዜ ግለጽ። ላ) ይህ ጊዜ ከሌሎች ጊዜያት የተላየ ያደረገው ምንድን ነበር? ሐ) የመንፈስ ቅዱስ ህልውናና ኃይል በሕይወትህና በኦገልግሎትህ የተሰማህ ሌሎች ጊዜያት ነበሩን? አንቶንዶቹን ግለጽ። ) እነዚህ ልምምዶች ይበልጥ የሚመስሉት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ነው ወይም የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን ወይስ ሁለቱንም ይመስልሃልን? መልስህን በአብራራ። 

ባለፈው ሳምንት በካሪዝማቲክና ካሪዝማቲክ ባልሆኑ ክርስቲያኖች ዘንድ ሰመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ላይ ያለውን ክርክር ተመልክተናል። የሐዋርያት ሥራን መጽሐፍና የመልእክቶችን ተዛማጅ ክፍሎችም ተመልክተናል። ከጥናታችን የደረስንበት ማጠቃለያ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ሁለት የተለያዩ አገልግሎቶች መሆናቸውን ነው። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በክርስቲያኖች ሁሉ ሕይወት ውስጥ የተፈጸመ ኃላፊ ተግባር እንደሆነ ነው የተመለከትነው። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ግን በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ በተደጋጋሚ የሚፈጸምና ክርስቲያኖች አጥብቀን እንድንፈልገው እንኳ የታዘዝነው ነገር ነው። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ለአንዴና ለመጨረሻ የተፈጸመ ሆኖ ወደኋላ የሚጠቀስ ነው (የሐዋ. 1፡5-17)። ነገር ግን በአማኞች ሕይወት ዘመን በሙሉ ተደጋጋሚ የመንፈስ ቅዱስ ብዙ ሙላቶች እንዳሉ አይተናል። 

ጴንጠቆስጤ ያልሆኑ ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በቸልታ የተው ሲሆን ጴንጠቆስጤ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ትኩረት እንደተሰጠው ሁሉ በእማኞች ሕይወት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ስለሚያከናውናቸው ትኩረት መስጠታቸው ትክክለኛ ነገር ነው። ጰንጠቆስጤዎች በአገልግሎት ውስጥ የእግዚአብሔርን ኃይል አስፈላጊነት በተገቢ መንገድ ስላተኮሩበት እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ባርኳል። ነገር ግን ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ አካሄድና ከመልእክቶች ትምህርት ጋር ያለአንዳች ማወላዳት ተጣጥሞ እንዲታይ ከተፈለገ፥ አብዛኛዎቹ በሕይወታቸውና በአገልግሎታቸው የሚለማመዱትና ልዩ ኃይልንም የሚሰጣቸው የመንፈስ ቅዱስ ሙላት እንጂ እነርሱ እንደሚሉት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አይደለም። ከድነት (ደኅንነት) በኋላ በርካታ ጴንጠቆስጤ አማኞች የሚለማመዱት ታላቅ የመንፈስ ቅዱስ ልምምድ መንፈስ ቅዱስ ለእነርሱ ታላቅ ኃይልን የሚያጎናጽፍበት የሙላት አገልግሎት ነው። ጆን ዊምበር የተባላ በሥነመለኮት ትምህርቱ ሳይሆን በልምምዱ ጰንጠቆስጤ የሆነ የትልቅ ቤተ ክርስቲያን መጋቢ እንዳለው የጰንጠቆስጤ ልምምዶች ከሥነመለኮት ትምህርቶቻቸው የተሻሉ ናቸው። 

ለእምነታቸው መረማመጃ ስላሆኑትና በሁሉም ክርስቲያኖች ሕይወት መገላጽ ይገባዋል የሚሉትን የጰንጠቆስጤ ሥነመለኮት ቁልፍ ትምህርት፥ ገና ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ክፍሎች ማጥናት ይኖርብናል። እነዚህን ክፍሎች የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ሁልጊዜ ራሱን በልሳን የሚገልጸው የመንፈስ ቅዱስ ልዩ የድኅረ-ድነት (ደኅንነት) ሥራ መሆኑን ያስተምራሉን? ወይስ እነዚህ ክፍሎች ሌላ ትርጉም ይኖራቸው ይሆንን? በውዝግቡ ምንጭነት የታወቁ ክፍሎችን ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት እናጠናለን። 

የመጀመሪይቱ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ መጽሐፍ የሆነውን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ለመረዳት ቀላል መጽሐፍ ሊመስለን ይችላል። በአንድ በኩል ትክክል ነው። የተፈጸሙት ታሪኮች ግልጽ የሆኑና ለመረዳትም እጅግ የቀለሉ ናቸው። በሌላ በኩል ግን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደ ሌሎች ታሪካዊ መጻሕፍት ለመተርጐምና ከአሁኑ ዓለም ሁኔታ ጋር ለማዛመድ ያስቸግራል። የሐዋርያት ሥራን መጽሐፍ ጨምሮ ታሪካዊ መጻሕፍትን በሙሉ ለመረዳት አስቸጋሪ የሚሆነው ገላጭ» ስላልሆኑ ነው። ዓላማቸው ምን እንደተፈጸመ በመግለጽ ዛሬም እንዴት መኖር እንዳለብን ጠቃሚ ትምህርት ለመስጠት ነው። ነገር ግን፥ ጸሐፊው ስለተፈጸመ አንድ ድርጊት መልካምነትና ልንከተለው የሚገባ ስለመሆኑ ሳይገልጽ ምን ጊዜ ትረካ ብቻ እንደሚያቀርብ ወይም በታሪኩ ውስጥ እንደተጠቀሰው ሰው እንድንሆን ወይም የተገለጸው ድርጊት ለሁልጊዜ በምሳሌነት ልንከተላው የሚገባ መሆኑን መቼ እንደሚናገር ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። ለምሳሌ፡- የሳምሶንን ታሪክ ብንወስድ፡ ሳምሶን በምሳሌነቱ ልንከተለው የሚገባ ሆኖ ነው ታሪኩ የተጻፈው ወይስ ንጽሕና የጐደለውን ኑሮ መኖር ውጤቱ ምን እንደሆነ ለማስጠንቀቅ ይሆን? 

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በቀረበው የገላጭ ትረካ ዓላማ ላይ የተነጣጠረው ይህ ውዝግብ በካሪዝማቲክና ካሪዝማቲክ ባልሆኑ ክርስቲያኖች መካከል መለያየት ከፈጠሩት ምክንያቶች የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ከዘገባቸው አስደናቂ ታሪኮች ውስጥ ጳውሎስ በልብሱ ቁራጭ ወይም በመሐረቡ ሰዎችን ይፈውስ እንደነበር ወይም ጴጥሮስ በመንገድ በሚያልፍበት ወቅት ጥላው ያረፈባቸው በሽተኞች እንደተፈወሱ የሚናገሩ ይገኙበታል (የሐዋ. 5፡12-16፤19፡11-12)። መንፈስ ቅዱስ ለመጀመሪያ በእነርሱ ላይ በወረደ ጊዜ በልሳን የተናገሩ ሰዎች ታሪክም ተጽፏል። ብዙ ካሪዝማቲክ ያልሆኑ ክርስቲያኖች እነዚህ ታሪኮች የተጻፉት እግዚአብሔር የወንጌልን ሥልጣን ለማሳየትና ለማረጋገጥ በመጀመሪያ ክፍል ዘመን ያደረጋችው አስደናቂ ሥራዎች ናቸው ብለው ያምናሉ። እነርሱ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን እንደሚረዱት ከሆነ እነዚህ ድርጊቶች የተጻፉት ዛሬ በዘመናችን መራመድ ስለሚገባቸው ወይም ገና ለሚፈጸሙት በምሳሌነት ለመሆኑም ፍንጭ የላም። ብዙ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ግን እነዚህ ታሪኮች የተሰጡት መንፈስ ቅዱስ በማንኛውም ዘመን እንዴት እንደሚሠራ ለማሳየት ነው። ስለዚህ የጴጥሮስ ጥላ በቀደመው ጊዜ ፈውስን ካስገን ዛሬም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ጥላ ፈውስን ማምጣት አለበት በማለት ይከራከራሉ። እንደገና የምንመለከተው እመለካከታችን ወይም አስቀድሞ ያለን መረዳት መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እንደምንረዳ እንደሚወስን ነው። ቀደም ብሎ የነበረንን መረዳት ስንዘነጋ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ምን እንደሚያስተምር በጥንቃቄ መመልከት አለብን። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ያላውን ልምምድ በመልእክቶች ውስጥ በግልጽ ከተሰጡት ትምህርቶች ጋር ማወዳደር አለብን። 

ጥያቄ፡– ሁለት ክርስቲያኖች ከድነት (ደኅንነት) በኋላ ስለሚሆነው የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ይነጋገራሉ። አንደኛው መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቲያኖች የሚመጣው በሚድኑ ጊዜ ነው ይላል። ሌላው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቲያን የሚመጣው ከድነት (ደኅንነት) በኋላ እንደ ሁለተኛ የጸጋ ሥራ ሆኖ ነው ይላል። ስለዚህ ስለ መንፈስ ቅዱስ መምጣትና በልሳናት ከመናገር ጋር ስላለው ዝምድና ምን እንደሚያስተምር የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን በአንድነት ለማጥናት ወሰኑ። የሚከተሉትን ጥቅሶች በጥንቃቄ አንብብ። የሐዋ. 2፡1-13፤ 8፡14-17፤ 10፡23–48፤ 19፡1-7። ሀ) በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ያገኘሃቸውን፥ የሚከተሉትን እሳቦች የሚደግፉትን እውነቶች በዝርዝር ጻፍ። ) መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቲያን ሕይወት የሚመጣው በዳነበት ቅጽበት መሆኑን፤ 2) መንፈስ ቅዱስ የሚመጣው ከዳነ በኋላ መሆኑን፤ ለ) በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ የባላጠ ድጋፍ ያገኘው የትኛው አመለካከት ነው? ሐ) ስለ እያንዳንዱ ተግባር አፈጻጸም ሠንጠረዥ አዘጋጅና የሚከተሉትን ዘርዝር። ) መንፈስ ቅዱስን የተቀበለው ማን ነው? 2) የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ምልክት ተደርጐ የተጠቀሰው ነገር ምን ነበር? 3) በቡድኑ ውስጥ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ ስንቶች ናቸው? 4) መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ሰዎች ምን ማድረግ ነበረባቸው? 5) መንፈስ ቅዱስን በመስጠት ላይ አንዳንድ ጊዜ መዘግየት የነበረው ለምን ይመስልሃል? 6) መንፈስ ቅዱስን ወደሌሎች እንዲያስተላልፍ እግዚአብሔር የተጠቀመበት ማን ነበር? ) መንፈስ ቅዱስ እንዲተላለፍ ምክንያት በሆነው ሰው አማካኝነት ምን ድርጊት ተፈጸመ? መ) በእነዚህ ጥቅሶች ላይ ስለተመሠረተው የሁለቱ ክርስቲያኖች ውይይት ምን ትመልሳለህ? 

ከላይ የሰፈሩትን ጥቅሶች ከመመልከታችን በፊት የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የሚናገረው እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር ይሠራ ለነበረው ሥራ የሽግግር ወቅት መሆኑን ማስታወስ አለብን። የብሉይ ኪዳን ዘመን አልፎ ነበር። ኢየሱስ እዲስ ኪዳንን መሥርቷል። ነገር ግን የአዲስ ኪዳን በረከቶችን እጠቃለው ያልተቀበሉ በርካታ የብሉይ ኪዳን አማኞች ነበሩ። እግዚአብሔር እዲሱ ኪዳን በሚገባ ከተደላደለ በኋላ በሠራው ዓይነት መንገድ በመጀመሪያዪቱ ቤተ ክርስቲያን በነበሩ እማኞች ዘንድ ለጥቂት ዓመታት ያልሠራበትን ምክንያት ለመረዳት ይህ ሁኔታ ይጠቅመናል። 

1. መንፈስ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ በአይሁድ ላይ መውረዱ (የሐዋ. 2)።

 ከአብርሃም ዘመን ጀምሮ እግዚአብሔር የአይሁድ ሕዝብ ለእርሱ የተመረጡ ልዩ ሕዝብ እድርጐ ለያቸው። የአብርሃም በረከት ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉ ሁሉ አይሁድ ሊሆኑና የአይሁድን ባሕል በሙሉ ሊለምዱ ይገባ ነበር። የብሉይ ኪዳን ነቢያት በአዲስ ዘመን የእግዚአብሔር በረከት በአሕዛብ ሁሉ ላይ አልፎ እንደሚፈስስ ቢናገሩም እንኳ የነቢያቱ ትኩረት መሢሑና መንፈስ ቅዱስ ለእይሁድ በሚያመጡት በረከት ላይ ነበር። ኢየሱስ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ የአይሁድ ምድር በነበረችው ፍልስጥኤም እንደ እንድ አይሁድ ኖረ። ደቀመዛሙርቱም አይሁዳውያን ነበሩ። 

ሆኖም ግን ወደ መንግሥተ ሰማያት ከመመለሱ በፊት ለደቀ መዛሙርት ወንጌል በአይሁዶች መካከል ብቻ መቅረት እንደሌለበት ተናገረ። ይልቁኑ ደቀ መዛሙርት በዚያን ጊዜ ከነበሩበት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ፤ የአይሁዶች አገር ወደሆነችው ይሁዳ፥ ሰማርያና ወደ ዓለም ሁሉ መስፋፋት ነበረበት። 

(የሐዋ. 1፡8 አንብብ።) 

ቤተ ክርስቲያን በጴንጠቆስጤ ዕለት መጀመሪያ የተቆረቆረችው በአይሁድ መካከል ነበር። መንፈስ ቅዱስ በአይሁዶች ላይ ወረደ። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ ስምንት ምዕራፎች መንፈስ ቅዱስ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ በአይሁዶች መካከል ስላሠራው ሥራ የሚናገሩ ናቸው። ቀጥሎ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሰማርያና ወደ አሕዛብ እንዴት እንደተስፋፋች እናነባለን። እንድ አዲስ ማኅበረ ሰብ ወደ ክርስቶስ በመጣ ቁጥር ይህ ሕዝብ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጨመሩንና ከአይሁድ ክርስቲያኖች እኩል መሆኑን ለማረጋገጥ መንፈስ ቅዱስ በልዩ መንገድ ይሰጥ እንደነበር እንመለከታለን። ጥናታችንን መንፈስ ቅዱስ በአይሁድ ላይ እንዴት እንደወረደ በመመልከት እንጀምር። 

ጥያቄ፡- የሐዋርያት ሥራ 2፡1-13 እንደገና እንብብ። ሀ) መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ በወረደ ጊዜ ደቀ መዛሙርት የት ነበሩ? ለ) የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ምልክት የሆኑት ሁላት ውጫዊ ምልክቶች ምንና ምን ነበሩ? ሐ) የመንፈስ ቅዱስ መውረድ በደቀ መዛሙርት ሕይወት የተረጋገጠው እንዴት ነበር? መ) ስንት ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ? እነዚህ ደቀ መዛሙርት የተናገሩባቸውን ልሳናት ግለጽ። በዛሬ ዘመን ሰዎች ከሚለማመዱዋቸው ልሳናት ሁኔታ ጋር አወዳድር። ተመሳሳይ ወይም ልዩ የሆነው እንዴት ነው? 

ከዚህ መንፈስ ቅዱስ በደቀ መዛሙርት ላይ ከወረደበት የመጀመሪያ ልምምድ ከምንማራቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ቀጥለው ተዘርዝረዋል። 

1. መቶ ሃያዎቹ ደቀመዛሙርት በኢየሱስ ያመኑ ቢሆኑም እንኳ ሁለቱን ተፈላጊ የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች እልተለማመዱም ነበር። የመጀመሪያው የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ወደ ልባቸው ያስገባና የክርስቶስ እካል በሆነችው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያጣበቃቸውን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ለአገልግሎት ኃይል የሚሰጠውን የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን አልተቀበሉም ነበር። 

በብሉይ ኪዳን ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የታወቀ አገልግሎት ነበር። አንዳንድ የብሉይ ኪዳን እማኞች ይህን ሙላት የተለማመዱት ቢሆንም፥ ጥቅሱን ስንመለከተው ግን አገልግሎቱ ለእንዳንድ አማኞች ብቻ ለተወሰነ ጊዜ የሚሰጥ ነበር። ነገር ግን አማኞች የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የመሆናቸውና በማናቸውም ጊዜ በመንፈስ ሊሞሉ የመቻላቸው ጽንሰ-አሳብ አዲስ ነው። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትም በብሉይ ኪዳን ያልነበረ አዲስ አገልግሎት ነበር። ይህ ትርጉም የሚሰጠን በክርስቶስ አካል ውስጥ የሚያጣብቀን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መሆኑንና የክርስቶስ አካል ብሎ ነገር ደግሞ በብሉይ ኪዳን አለመኖሩን ስናገናዝብ ነው። ደቀመዛሙርት እዲስ ከተመሠረተችውና የክርስቶስ አካል ከሆነችው ቤተ ክርስቲያን የሚያጣብቃቸውን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በሚለማመዱበት በዚያው ጊዜ መንፈስ ለሁላቸውም የሙላት አገልግሎትንም ያበረክት ነበር። 

እነዚህ ሁለት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች በጰንጠቆስጤ ዕለት ተጀመሩ። በብሉይ ኪዳን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ቋሚ ህልውና የማይታወቅ ስለነበረ መንፈስ ቅዱስ በአንድ ጊዜ ሁለቱን አገልግሎቶች በኢየሱስ ባመኑ እማኞች ሕይወት መጀመር አስፈለገው። መንፈስ ቅዱስ በመቶ ሃያዎቹ ደቀመዛሙርት ላይ ከተለወጡ በኋላ መውረድ ያስፈለገው ለዚህ ነው። ይህ መንፈስ ቅዱስ የአዲስ ኪዳን አገልግሎቱን የጀመረበት ሁኔታ ነበር። ቤተ ክርስቲያን የተጀመረችው በዚህ መንገድ ነበር። ደቀመዛሙርት በዚህ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ስለነበር ለአገልግሎት ኃይልን ላብሰው ነበር። 

2. በመካከላቸው መገኘቱ እንዲታወቅ መንፈስ ቅዱስ በደቀመዛሙርት ላይ የወረደው በታላላቅ ምልክቶች በመታጀብ ነበር። ታላቅ የሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ነበር። ይህ ምናልባት መንፈሱን በደቀመዛሙርት ላይ የላከውን የታላቁን የእግዚአብሔርን ኃይል የሚያመለክት ነበር። በብዙ ነበልባል እየተከፋፈለ በእያንዳንዱ ደቀመዝሙር ላይ የተቀመጠ እሳትም ታይቶ ነበር። እሳት ብዙ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን የሚወክል ነው (ዘፀአ 3፡2፤ 13፡21)። ስለዚህ እሳቱ የሚያመላክተው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በመካከላቸው መሆኑን ነው። እሳቱ የተከፋፈለ መሆኑ የሚያሳየው አንዱ መንፈስ በዚያ ክፍል ውስጥ ለነበሩት ለሁሉም በእኩል ደረጃ እንደመጣላቸው ነው። ለእንዱ ሰው ብቻ የተሰጠ አልነበረም። ደግሞም ከአንዱ ይልቅ ለሌላው ሰብልጫ የተሰጠም አልነበረም። 

3. መንፈስ ቅዱስን በተቀበሉትና ባልተቀበሉት መካከል ልዩነት ወይም መከፋፈል አልነበረም። ኢየሱስን ይከተሉ የነበሩ አንድ መቶ ሃያ ሰዎች በክፍሉ ውስጥ ነበሩ። መንፈስ ቅዱስ በአንዳንዳቸው ላይ መጥቶ በሌሎቹ ላይ ሳይመጣ አልቀረም። ይልቁኑ እያንዳንዳቸው በመንፈስ ቅዱስ ይሞሉ ዘንድ በሁሉ ላይ ነው የወረደው። 

4. መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ ሁሉ ላይ የምንመለከተው ውጫዊ ምልክት አንድ ዓይነት ነበር። ይህም ሁሉም በልሳን መናገራቸው ነው። ይህ በልሳናት የመናገር ስጦታ የተጠቀሰበት የመጀመሪያ ስፍራ ነው። ይህ ልዩ ነገር ነበር። ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን የመንፈስ ቅዱስ ህልውና የሚታይበት ዋና መንገድ «ሰትንቢት ስጦታ» ነበር (ዘኍ. 11፡25)። ኢዩኤልም ሲናገር የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ይቀበሉታል ያላው ስጦታ ትንቢትን መናገር ነበር (ኢዩ. 2፡28-32)። እግዚአብሔር ለደቀ መዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስን ለመስጠቱ ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ «ስልሳናት መናገርን» ለምን እንደ መረጠ አናውቅም። ምናልባት ሊሰበክ ያለው ወንጌል ልክ የተናገሯቸው ልሳናት በወቅቱ በነበረው ዓለም ከሚነገሩት ቋንቋዎች የተውጣጡ እንደ ነበር፥ የነበረውን ዓለም አቀፋዊ ይዘት እግዚአብሔር ሊያሳያቸው ስለፈለገ ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር ይህንን የበዓል ቀን ለአይሁድ መንፈስ ቅዱስን ለመስጠት የመረጠበት ምክንያት በዓለም ዙሪያ የነበሩ በሺህ የሚቆጠሩ አይሁድ ለሰዓሉ መጥተው ስለነበር ነው። በኢየሩሳሌም ይነገር በነበረው፥ ነገር ግን ለብዙዎቻቸው ባዕድ በሆነው አራማይክ ቋንቋ ሳይሆን፥ ባደጉበት አካባቢ በግል ቋንቋቸው ወንጌልን እንዲሰሙ እግዚአብሔር ሆን ብሎ አቀነባበረላቸው። 

5. በልሳናት የመናገር ስጦታዎች የታወቁ፥ ለመረዳት የሚቻሉ ቋንቋዎች እንጂ የማይታወቁ ልሳናት አልነበሩም። በኢየሩሳሌም የነበሩ አይሁዶች በአካባቢያቸው በሚነገሩ ቋንቋዎች የተነገረውን መልእክት ተገነዘቡ። ይህ ዛሬ ከሚናገሩት ልሳኖች የተለየ ይመስላል። በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች የሚነገሩ ልሳኖች አብዛኛዎቹ የሰው ቋንቋ አይደሉም። ነገር ግን አንዳንዶች የመላእክት ቋንቋ እንደሆነ የሚናገሩለት የማይታወቅ ቋንቋ ነው። የመጀመሪያ የልሳን ስጦታ ግን የመላእክት ቋንቋ ሳይሆን የሰው ቋንቋ ነበር። 

6. አንዳንድ ሊቃውንት የተለያዩ ቋንቋዎች በሚደመጡበት ወቅት ሌላ ተአምራትም ተፈጽሟል ይላሉ። የሐዋ. 2፡6 አሳብ እያንዳንዱ ደቀመዝሙር በልሳናት በሚናገርበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሕዝቡ ወደሚሰሙባቸው ቋንቋዎች ተርጉሞላቸው ይሆናል ማለት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ይኸኛው አመለካከት የሚያስገነዝበን ደቀ መዛሙርት በሙሉ የተለያዩ ቋንቋዎች እንደተናገሩ ሳይሆን፥ ይልቅ ሁላቸውም ሰአንድ ቋንቋ እንደተጠቀሙ፥ ቃሎቻቸውን ደግሞ ለሚሰሙአቸው አይሁድ መንፈስ ቅዱስ በቋንቋቸው ይተረጉምላቸው እንደ ነበር ነው። 

7. የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የእግዚአብሔርን ቃል በድፍረት ወደ መናገር አመራ። ጴጥሮስ በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል በድፍረት የተናገረውና ብዙዎችም በኢየሱስ ያመኑት ለዚህ ነበር። 

8. የመንፈስ ቅዱስ በደቀመዛሙርት ላይ መውረድ በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ በልዩ መንገድ፥ ጾታ፥ ዕድሜና የኑሮ ደረጃን ሳይለይ በሁሉም ሰው ላይ የሚወርድበት አዲስ ዘመን እንደሚመጣ የተነገረው ትንቢት ፍጻሜ ነው። ሆኖም ግን ጴጥሮስ ከኢዩ. 2፡28-32 የወሰደውን ጥቅስ ከተፈጸመው ነገር ጋር ብናወዳድረው የጴንጠቆስጤ ዕለት ትንቢቱ በከፊል እንጂ በሙላት 

186 

የተፈጸመበት ዕለት አይደለም። መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በትንቢት እንደተናገረው ዕድሜ ወይም የኑሮ ደረጃ በማይወስነው መንገድ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መውረዱ እርግጥ ነው። 

ሆኖም ግን እግዚአብሔር የዘላለም መንግሥቱ ከመጀመሩ በፊት የሚገለጹት የእግዚአብሔር ፍርድ ምልክቶች ማለትም ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃ ወደ ደም ወዘተ… የመለወጣቸው ነገር እዚህ ላይ አልታዩም። ይህ የሆነበት ምክንያት «የመጨረሻው ዘመን» በሁለት የተለያዩ ደረጃዎች የሚፈጸም ስለሆነ ነው። አንደኛ፥ የእግዚአብሔር መንፈሳዊ መንግሥት በቤተ ክርስቲያን መመሥረት መጀመር ነበረበት። ይህ መንፈሳዊ መንግሥት በእግዚአብሔር ላይ የዓመፅ ተግባር በሚፈጸምበት በቀድሞው ዘመን መከሳት ነበረበት። መንፈስ ቅዱስ በመንግሥቱ ውስጥ የሚጫወተው ከፍተኛ ሚና ነበረው። በሁለተኛ ደረጃ፥ የእግዚአብሔር ዕቅዶች ፍጻሜ የሚያገኙበት ቀን መምጣት ነበረበት። ይህ የሚታየው አሁን ያሉት ሰማይና ምድር ተደምስሰው እግዚአብሔር በዚያ ምትክ አዲስ ሰማይና ምድር ሲሠራ ነው (ራእይ 21፡1)። ይህ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃሎች ሙሉ በሙሉ ወደመፈጸም ያመጣቸዋል። መንፈሳዊ መንግሥት ከተመሠረተ ሁላት ሺህ ያህል ዓመት ያለፈ ሲሆን የመጨረሻው መንግሥት ግን ገና አልተጀመረም። የአዲሱ መንገሥት ዋና ምልክት የሆነው መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ልጆች ተሰጥቷል። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በታላቅና ልዩ መንገድ የሚወርድበት ሌላ የሚጠበቅ ጊዜ ያለ ይመስላል። 

9. ኢየሱስ ለደቀመዛሙርት የገባውን የተስፋ ቃል ፈጽሟል። ከእግዚአብሔር አብ እጅ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ፥ ለደቀ መዛሙርት እንዲሁም በኢየሱስ ላመኑ ሁሉ ሰጥቷቸዋል። 

10. ጴጥሮስ ለአይሁድ ሕዝብ ሲናገር መንፈስ ቅዱስ ንስሐ ገብተው በኢየሱስ አምነው ለተጠመቁ ሁሉ እንዲሁ በነፃ እንደ ተሰጠ ገለጸ። (አስታውሱ እዲስ ኪዳን ሁልጊዜ የአማኞችን ጥምቀት የሚያቀርበው ሰዎች በኢየሱስ ካመኑ በኋላ እንደሚፈጸም የተለየ ክንውን ሳይሆን ንስሐ መግባትንና እምነትን ተከትሎ ወዲያው እንደሚደረግ ድርጊት ነው።) ጥምቀት አንድ ስው እራሱን ለኢየሱስ ክርስቶስ የመስጠቱና እራሱን የክርስቶስ የማድረጉ ውጫዊ ምልክት ነው። መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል የተሰጠ አንዳችም መመዘኛ እልነበረም። ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል እንዲሹ፥ ወይም ለራሱ ለመንፈስ ቅዱስ እንዲጸልዩ፥ ወይም እንዲጾሙ፥ ወይም ሌላ ምንም ነገር እንዲያደርጉ አልነገራቸውም። መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ሲጸልዩ ወይም እጅ ሲጭኑ እንመለከትም። ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያ በደቀ መዛሙርት ላይ ከወረደ በኋላ በተከታይ በሚወርድበት ጊዜ የሚታወቅበት የተለየ መንገድ ስለመኖሩም እልተናገረም። በደቀ መዛሙርት እንደሆነው መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ ሁሉ በልሳናት ይናገራሉ አላላም። እንዲያውም ከዚህ በኋላ መንፈስ ቅዱስን የሚቀበል የአይሁድ ክርስቲያን እንደ መጀመሪያዎቹ የአይሁድ ክርስቲያኖች በልሳን ስለመናገሩ የምናነበው ነገር ምንም የለም። ይህ ታሪክ ያመኑት ሦስት ሺህ ሰዎች በሙሉ መንፈስ ቅዱስን መቀበላቸውን ያመለክታል እንጂ በልሳናት ለለመናገራቸው ምንም አይገልጽም። 

ጥያቄ፡- ከዚህኛው ለቀደመው ጥያቄ የሰጠኸውን መልሶች ከልስ። በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ላይ በተሰጠው ትንተና መሠረት ከመልሶችህ አንዳንዶቹን የምትለውጠው እንዴት ነው? 

2. መንፈስ ቅዱስ በሰማርያ ሰዎች ላይ ወረደ (የሐዋ. 8፡2-25) 

ጥያቄ፡- የሐዋ. 8፡2-5 አንብብ። ሀ) ፊልጶስ ወንጌልን የሰበከው የት ነበር? ለ) ስለ ሳምራውያን ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ላይ አንብብ። በአይሁዳውያንና በሳምራውያን መካከል ያለውን ግንኙነት ግላጽ። ሐ) ሳምራውያን አማኞችን ለመመርመር የመጣው ማን ነበር? ይህ አስፈላጊ የነበረው ለምን ይመስልሃል? መ) ለእነዚህ ሳምራውያን ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደተሰጠ ግለጽ። ሀ) ሳምራውያን ባመኑበት እና መንፈስ ቅዱስን በተቀበሉበት ጊዜ መካከል ያለው ልዩነት የተፈጠረው ለምን ይመስልሃል? ረ) በሳምራውያን ክርስቲያኖች ላይ መንፈስ ቅዱስ የመውረዱ ማረጋገጫ ምን ነበር? ሰ) መንፈስ ቅዱስ ላይ ስላለ የተሳሳተ አመለካከት ከጠንቋዩ ስምዖን ድርጊት ምን እንማራለን? 

ስደት ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ዓላማውን የሚፈጽምበት መሣሪያ ነው። ይህ በቀድሞ ቤተ ክርስቲያን ዘንድም የታወቀ ነበር። ለብዙ ዓመታት ወንጌል በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ቆየ። ኢየሱስ ለደቀመዛሙርት ወንጌልን ወደ ሰማርያ እንዲያደርሱ ያዘዛቸው ቢሆንም ይህን አላደረጉትም። ስለዚህ እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ላይ ስደትን አስነሥቶ ክርስቲያኖች እንዲበተኑ አደረገ። በሄዱበት ስፍራ ሁሉ ስለ ኢየሱስ መሰከሩ። በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን መሪ ይሆኑ ዘንድ ከተመረጡ ዲያቆናት አንዱ የነበረው ፊልጶስ ወንጌልን ወደ ሰበከበት ወደ ሰማርያ ተሰደደ። እግዚአብሔር በእርሱ ውስጥ በመሥራቱ ብዙ ሳምራውያን በኢየሱስ አመኑ። 

አይሁዳውያን ለሳምራውያን የነበራቸውን ጥላቻ መረዳት ለእኛ ከባድ ነው። ዛሬ በዓለማችን እንዳሉ ለዘር ጥላቻ በምሳሌነት እንደሚቀርቡ እንደ ሩዋንዳና ዩጐዝላቪያ ዓይነት ሊሆን ይችላል። የጥላቻው መንስዔዎች በርካታ ነገሮች ናቸው። በመጀመሪያ፥ ሳምራውያን የአይሁድና የአሕዛብ ቅይጦች ነበሩ። ንጹሕ አይሁድ አልነበሩም። በሁለተኛ ደረጃ ፥ ሳምራውያን የራሳቸውን የአምልኮ ሥርዓት አበጅተው ነበር። ይህም በኢየሩሳሌም ካለው የአምልኮ ሥርዓት የሚቃረን ነበር። የራሳቸው ቤተመቅደስ፥ የራሳቸው ካህናት የነበራቸው ሲሆን የሙሴን ሕግጋት (ከዘፍጥረት – ዘዳግም) ብቻ እንጂ የቀሩትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ወይም አይሁዳውያን የሚያጣብቁትን ባሕል አይቀበሉም ነበር። ሦስተኛ፥ በአይሁዳውያንና በሳምራውያን መካከል የረጅም ዘመን የጦርነትና ጭካኔ ታሪክ ነበር። ይህ ከመሆኑ ጥቂት ዓመታት ቀደም ብሎ እንኳ በሁለት ሕዝቦች መካከል ከፍተኛ ጦርነት ተደርጐ አይሁዳውያን ብዙ ሳምራውያንን ገድለው ነበር። አራተኛ፥ አይሁዳውያን ሳምራውያንን ይገዙ ነበር። 

ጥላቻው ከፍተኛ ስለነበር ማንኛውም አይሁድ አንድም ሳምራዊን አያናገርም ነበር። ድንገተኛ ችግር ካልተፈጠረ በስተቀር በሰማርያ በኩል እንኳ አያልፉም ነበር። በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የነበረውን ይህን ጠላትነት መረዳት መንፈስ ቅዱስ ልዩ በሆነ መንገድ በሳምራውያን ላይ ለምን እንደወረደ እንድንገነዘብ ያግዘን ይሆናል። በታሪኩ ውስጥ ከሚገኙ ዋና እውነቶች አንዳንዶቹን እንመልከት። 

1) ሳምራውያን አዲስ የሆነ የአማኞች መደብ ነበሩ። እስከዚህ ጊዜ ድረስ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችው ሙሉ በሙሉ በእይሁዶች ነበር። በዚህ ጊዜ ግን ወንጌል ወደ አዲስ የዘር ክልል ደረሰ። እግዚአብሔር ለሰማርያ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስን መስጠት ያዘገየበት ምክንያት ከሐዋርያት አንዳንዶቹ ለሚከተሉት ምክንያቶች እስኪመጡ ድረስ ነበር። 

ሀ. ሐዋርያት የሳምራውያንን እምነት መርምረው ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ ነበረባቸው። 

ለ ሳምራውያን መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ልክ የአይሁድ ሰዎች በተቀበሉበት ዓይነት መንገድ ስለነበር ከአይሁድ ጋር እኩል መሆናቸውን ለሁሉም ለማሳየት በመንፈስ ቅዱስ አሰጣጥ ሁኔታ ላይ ሐዋርያት መሳተፍ ነበረባቸው። እግዚአብሔር ለሳምራውያን ባመኑ ጊዜ ወዲያውኑ መንፈስ ቅዱስን ያልሰጠበት ምክንያት የአይሁድ ክርስቲያኖች ሳምራውያን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክእነርሱ እኩል መሆናቸውን እንዲነዘቡ ለማድረግ ይመስላል። 

ሒ ቤተ ክርስቲያን የአይሁድ ቤተ ክርስቲያንና የሳምራውያን ቤተ ክርስቲያን በመባል እንዳትከፋፈልም ለመጠበቅ ነበር። የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን በተለይ ደግሞ ሐዋርያት የሳምራውያንን እምነት የሚያረጋግጡ የእግዚአብሔር መሣሪያ እንዲሆኑ መፈቀዱና ለሳምራውያን መንፈስ ቅዱስ መስጠቱ፥ ሳምራውያን በመንፈሳዊ ጉዳዮች ከሐዋርያትና ከኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ሥር መሆናቸውን የሚያሳያቸው ነበር። የራሳቸውን ቤተ መቅደስ እንዳቋቋሙ ሁሉ የራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን መመሥረት አይችሉም ነበር። 

መንፈስ ቅዱስ ወደ ሳምራውያን ክርስቲያኖች ሕይወት መውረዱንም ሆነ መጠመቃቸውን እግዚአብሔር ያዘገየው በሳምራውያንና በአይሁድ ቤተ ክርስቲያኖች መካከል መከፋፈል እንዳይፈጠር ነበር። አይሁዳውያንም ሆኑ ሳምራውያን በክርስቶስ አንድ በመሆናቸው ላይ አትኩሮት በመስጠት ሳምራውያን ክርስቲያኖች ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ኅብረት እንዲመጡ ተደረገ። 

2. ሳምራውያን የሚያድን እምነትን ተቀብላው ነበር። በትክክል ማመናቸውን ፊልጶስ ባያረጋግጥ ኖሮ እንዲጠመቁ ባልፈቀደ ነበር። ለሳምራውያን መንፈስ ቅዱስ የወረደው ወዲያውኑ እንዳመኑ ሳይሆን ካመኑ በኋላ ነበር። ጴጥሮስ እስኪመጣ ድረስ የዘገየው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ብቻ አልነበረም። የመንፈስ ቅዱስ ህልውና ጭምር ነበር። መንፈስ ቅዱስን ሊቀበሉ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነበር እንጂ ሁለተኛ በረከት መቀበላቸው አልነበረም። (ማስታወሻ፡—አንዳንድ ካሪዝማቲኮች መንፈስ ቅዱስ አንድ ሰው በሚያምንበት ጊዜ ወደ ሕይወቱ ሊመጣ ይችላል ነገር ግን ሁላተኛ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ያስፈልገዋል እንደሚሉት አይደለም። አመለካከታቸውን ለመደገፍ ይህን ጥቅስ ሊጠቀሙበት አይገባም። ምክንያቱም የሰማርያ ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስን ህልውና እንኳ ገና አላገኙም ነበርና።) 

3. የሳምራውያንን እምነት ለማረጋገጥ እናት ቤተ ክርስቲያን የነበረችው የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ሁለቱን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ማለትም ጴጥሮስና ዮሐንስን የሰማርያ ክርስቲያኖችን ይመረምሩ ዘንድ ላከቻቸው። የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ሐዋርያት እስኪመጡ ድረስ ዘገየ። በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ የነበረውና ወደ ክርስቶስ የመራቸው የፊልጶስ መኖር እንኳ (የሐዋ. 6፡3-5፤ 8፡3–13) ለእነዚህ እማኞች መንፈስ ቅዱስን ሊያስገኝላቸው አልቻለም። 

4. እግዚአብሔር በደቀ መዛሙርቱ ላይ መንፈስ ቅዱስን ለማምጣት ጴጥሮስንና ዮሐንስን መሣሪያ አድርጐ ተጠቀመ። በመጀመሪያ ጸላዩላቸው፤ ቀጥሎም እጆቻቸውን በደቀ መዛሙርት ላይ ጫኑባቸው። እጅን መጫን በአይሁድ ባሕል በረከትን የማስተላለፊያ መንገድ ነው። እንድ አባት ልጁን ሲባርክ እጁን ይጭንበት ነበር። አንድ ካህን ማንኛውንም ሰው በሚባርክበት ወቅት እጁን ይጭንባቸው ነበር። እጅን መጫን መንፈስ ቅዱስ የሚሰጥበት ብቸኛ መንገድ አድርጐ ክመቁጠር ይልቅ የተቀበሉትን በረከት ለሌላ የሚያስተላልፉበት አይሁዳዊ ባሕል መሆኑን ማየት ይቀላል። ይህ ጴጥሮስና ዮሐንስ መንፈስ ቅዱስን ለሌሎች ለማስተላለፍ የተጠቀሙበት መንገድ ነበር። መንፈስ ቅዱስ የሚሰጥበት ብቸኛ መንገድ ለመሆኑ ምንም ማስረጃ የለንም። ለሳምራውያን ክርስቲያኖች በድጋሚ ሊደረግም ፈጽሞ እናይም። 

5. የሰማርያ ክርስቲያኖች በሙሉ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለዋል። መንፈስ ቅዱስን አንዳንዶች ብቻ እንደተቀበሉ የሚያመለክት እንዳችም ፍንጭ የለም። 

6. መንፈስ ቅዱስ የመኖሩና ያለመኖሩ ምልክት እንዴት እንደሆነ አልተጻፈልንም። የሰማርያ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉ በልሳን ስለመናገራቸው ወይም ሌላ ተአምራት ስለመደረጉ የተጠቀሰ ነገር የለም። 

7. መንፈስ ቅዱስ በሰማርያ ክርስቲያኖች ላይ የወረደው በታላቅ ሁኔታ በመገለጽ ነበር። ምክንያቱም ጠንቋዩ ስምዖን ይህንን በመመልከቱ ነው ለፈለገው ሁሉ መስጠት እንዲችል በመንፈስ ቅዱስ ላይ የማዘዝ «ኃይል»ን ለመቀበል የፈለገው። መንፈስ ቅዱስ እንዳሻን የምናዘው አይደለም። እጆችን በመጫንም ሆነ በሌላ ውጫዊ ዘዴ ቁጥጥር ሥር አይሆንም። በአንድ ወገን ሉዓላዊና የሰጠውን የሚያደርግ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ለሚያምኑ ሁሉ በነፃ የሚሰጥ ነው። 

በመንፈስ ቅዱስ የመጀመሪያ መምጣትና ሁለተኛ መምጣት መካከል የተደረገ ንጽጽር 

1. መንፈስ ቅዱስ በአይሁድ ላይ በወረደ ጊዜ እግዚአብሔር ምንም ሰብዓዊ መሣሪያ አልተጠቀመም። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለአይሁድ ክርስቲያኖች በቀጥታ ላከ። ላሰማርያ ክርስቲያኖች ግን ጴጥሮስንና ዮሐንስን እንደ ሰብዓዊ መሣሪያ አድርጐ ተጠቀመባቸው። 

2. መንፈስ ቅዱስ በአይሁዳውያን ላይ በወረደ ጊዜ እጅ መጣንም ሆነ መንፈስ ቅዱስ ይወርድ ዘንድ ጸሎት አልነበረም። ለሳምራውያን ክርስቲያኖች ግን ጸሎትም እጅ መንም ተደርጐላቸው ነበር። 

3. መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያዎቹ የአይሁድ ደቀ መዛሙርት ላይ በወረደ ጊዜ ህልውናው በምን እንደተረጋገጠ አልተጠቀሰም። ምልከቱ በልሳን መናገር ነበር ብላን በእርግጠኛነት መናገር አንችልም። ትንቢት፥ ታላቅ ደስታ ወይም ሌላ ምልክት ሊሆን ይችላል። 

4 አይሁድም ሆኑ ሳምራውያን መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ በወረደ ጊዜ ይህን ለማግኘት ፈልገው እንደነበር፥ ጾመው እንደነበር ወይም ሌላ ሙከራ አድርገው እንደነበር አልተጻፈም። አነሣሹ እግዚአብሔር ወይም ሐዋርያት እንጂ ተቀባዮቹ አልነበሩም። 

5. መንፈስ ቅዱስ በአይሁድም ሆነ በሳምራውያን ላይ በወረደ ጊዜ በአንድ ጊዜ በሁሉም ላይ ነው የወረደው። በጣም መንፈሳዊ በሆኑት ላይ መጀመሪያ መጥቶ ሌሎቹ ላይ ደግሞ በርትተው እስኪጸልዩ ወይም አንድ ልዩ ነገር እስኪያደርጉ ድረስ አልዘገየም። አመጣጡ ቅጽበታዊና ደግሞም በሁሉም ላይ ነበር። 

6. ለእይሁድም ሆነ ለሳምራውያን ካመኑበት ጊዜ ውጭ ክዚህ ጊዜ ሰኋላ መንፈስ ቅዱስ እንደወረደባቸው የተነገረበት ቦታ የለም። ለእነዚህ ሁላት ቡድኖች ከዚህ ጊዜ ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ በመጸለያቸው ወይም እጅን በመጫን እንደተቀበሉ የተጠቀሰበት ቦታ ፈጽሞ የለም። መንፈስ ቅዱስን ለመቀበላቸው በልሳናት መናገር ምልክት የሆነበት ቦታም የለም። 

ጥያቄ፡- ሀ) በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከዚህ በፊት የሰጠኸውን መልስ ከልስ። ከመልሶችህ አንዳንዶቹን የምትቀይረው እንዴት ነው? ላ) ከላይ የተመለከትነው ትምህርት አንዳንድ ክርስቲያኖች ስለ ክፍሉ ከሚሰጡት ትምህርት የተለየ የሆነው እንዴት ነው? ሐ) ከዚህ አስተሳሰብ ጋር ተስማማህ ወይስ እትስማማም? መልስህን አብራራ።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Exit mobile version