መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡1-3)

ጥያቄ፡ ሀ) በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ላይ ባለው የግንዛቤ ልነታት ምክንያት በኢትዮጵያ በሚገኙ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል የተፈጠሩትን ችግሮች ግላጽ። ለ) ክርስቲያኖች በልዩነት የሚከራከሩበት ቁላው ጉዳይ ምንድን ነው? 

«ምነው እንደ እዲስ ኪዳን ቤተ ከርስቲያን ስሆንን ኖሮ! መንፈሳዊ እንሆን ነበር፥ እግዚአብሔርም በአስደናቂ መንገዶች በመካከላችን ሰውራ ነበር። እንደ አዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን እንድንህን መወለላ ያስፈልገናል»። እንደዚህ ዓይነት አባባሎች ሰምተህ ታውቃለህን? ክርስቲያኖች በተለይ ደግሞ ከካሪዝማቲክ ወገን የሆኑት እንደዚህ ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው። ፍላጐታቸው፥ ሕልማቸውና ዓላማቸው ሁሉ እንደ አዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን መሆን ነው። ይህንን ሊሉ የክርስቲያኖች የጠበቀ እንኙነትና ኅብረት+ የመንፈስ ቅዱስን በሙላት መገለጥና የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን መለያ የሆነው ተአምራት መደረጉን መናገራቸው ነው። እነዚህ ሁላችንም በጽኑ ልንፈልጋቸው የሚገቡ መልካም ምኞቶች ናቸው። ነገር ግን የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን የምናስባትን ያህል ንጹሕ ነበረችን? 

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በቤተ ክርስቲያን ምሥረታ የመጀመሪያዎቹን ወቅቶች ስንመለክት አስደናቂ የሆነው የእግዚአብሔር ኃይል የተገለጠበትን ሁኔታ እናያለን። ቢሆንም ስለ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያዎቹ ሠላሳ ዓመታት ዕድሜ የተጻፉትን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍና ሌሎች መልእክቶች በጥንቃቄ ብናጠና ነገርች እንደምናስበው መልካም እንዳልነበሩ እናያለን። ዛሬ ሰብዙዎቻችን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ እንደሚሆነው ግብዝነት ነበር (ለምሳሌ፡- ሐናንያና ሰጲራ) [ሐዋ. 5]። በብሐር ልዩነቶች ምክንያት መከፋፈሉች ነበሩ። (ለምሳሌ ቀሪክ አይሁዳውያን ተገቢውን የምግብ እርዳታ ድርሻ እንዳላገኙ ያስቡ ነበር [የሐዋ. 6])። ክርስቲያኖች ነን የሚሉ ቀን ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የሚያስመስሉ ሰዎች ነበሩ (ለምሳሌ ጠንቋዩ ስምዖን [የሐዋ. 8]። የሥነ ሦግባር ጉድለት ነበር (ለምሳሌ በ1ኛ ቆሮ. 7 የተጠቀሰው ሰው)። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመከፋፈል ነበር (ለምሳሌ በቆርንቶስ ያሉ ክርስቲያኖች [ኛ ቆሮ. 11፥ (ኤድያንና ሌንጠኪን [ፊልጵ. 42። የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ክርስቲያኖች እንደማንኛችንም ዓይነት ነበሩ እንጂ ጨርሶ የተለዩ አልነበሩም። እንደ እኛው ችግር ነበረባቸው። በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንደ እኛው ማደግ የሚሹ ነበሩ። 

የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ትግል ታደርግባቸው ከነበረችባቸው ነገሮች አንዱ የመንፈሳዊ ስጦታዎች ጉዳይ ነበር። መንፈሳዊ ስጦታዎች በተለይ ደግሞ በልሳናት የመናገር ስጦታ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለው ድርሻ በነበረው የአሳብ ልዩነት መከፋፈል ነበር። አንዳንድ ክርስቲያኖች አንድ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ላመሞላቱና መንፈሳዊ ለመሆኑ ዋናው ምልክት በልሳናት መናገር ነው ብለው ሲያስተምሩ የነበሩ ይመስላል። ሌሎች ደግሞ ከቁጥጥር ውጭ የሆነን በልሳናት መናገር በመቃወም አበክረው እንዲቆም ይፈልጉ ነበር። በአምልኮ ጊዜያት የተሳሳተ የልሳን አጠቃቀም ስለነበር የአምልኮ ፕሮራም አገልግሎቶች ረብሻ የሞላባቸውና እግዚአብሔርን የማያስከበሩ ነበሩ። በዚህ ያለመግባባት መካከል በቆሮንቶስ የሚገኙ ክርስቲያኖች በልሳናት የሚናገሩትን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ምክር ለመጠየቅ ላጳውሎስ ጻፉለት። በልሳናት በመናገር ላይ የሚያተኩረው ይህ ክፍል በመንፈሳዊ ስጦታዎች ላይ በአዲስ ኪዳን ከተሰጡት ትምህርቶች ሁሉ በላቀ ሁኔታ ጥልቀት ያለው ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የነበረው ሁኔታ ዛሬ በብዙ አብያተ ክርስቲያናት ካለው ሁኔታ ጋር የሚመሳሰለው ወይም የሚለያየው እንዴት እንደሆነ ለማሳየት አወዳድር። ላ) ዛሬ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ግልጽ የሆነ ግንዛቤ መኖሩ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? 

ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚናገሩትን የመጀመሪያዎቹን ሦስት ክፍሎች ባጠናንበት ወቅት የትምህርቱ አትኩሮት መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለመግለጽ ከመሆኑ ይልቅ ስጦታዎች በክርስቶስ አካል ውስጥ ሊያመጡ የሚገባቸውን አንድነት ማሳየት ነበር። ጸሐፊዎቹ ለክርስቲያኖች አበክረው ለማሳየት የፈለጓቸው ሁለት እውነተች ነበሩ። የመጀመሪያው መንፈሳዊ ስጦታዎችን አጠቃልሎ የያዘ ማንም ስለሌለና እያንዳንዱ ክርስቲያን ስጦታዎች ስላሉት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች በሙሉ አስፈላጊዎችና ጠቃሚዎች ናቸው የሚል ነው። የክርስቶስ አካል ጤነኛ ይሆን ዘንድ ክርስቲያኖች ሁሉ ስጦታዎቻቸውን በመጠቀም በአንድ ላይ መንቀሳቀስና መሥራት አለባቸው። በሁለተኛ ደረጃ ጸሐፊዎቹ ሊያስተምሩን የፈለጉት ነገር ተፈላጊው ስጦታዎቻችንን መጠቀሙ ብቻ ሳይሆን ስንጠቀምበት የሚኖረን ዝንባሌ መሆኑን ነው። ዝንባሌያችን ትክክል ካልሆነ ለጦታዎቻችን አንድነትን የሚገነቡ ከመሆን ይልቅ የጥፋት መሣሪያ ይሆናሉ። 

በዚህ ክፍል ለለ መንፈሳዊ ስጦታዎች በዋናነት የሚያስተምረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል 1ኛ ቆሮ. 12-3 እናጠናለን። ጳውሎላ ለለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ያሉትን እውነቶች በሙሉ ሊያስረጻን የፈለገ ሳይሆን ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ዓላማ፥ በመንፈሳዊ ስጦታዎችን የምንጠቀምባቸው ትክክለኛ ዝንባሌዎችና ከመንፈሳዊ ስጦታዎች አንዳንዶቹን በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዴት እንደምንጠቀምባቸው በርካታ ነገሮችን ለመማር እንችላለን። 

ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 12-14 በፍጥነት አንብብ። ጳውሎስ በዚህ ስፍራ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሰጠውን ትምህርት በእንድ ገጽ አሳጥረህ ጻፍ። 

የ1ኛ ቆሮንቶስ 12-14 መሠረተ አሳብ 

የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ጳውሎስ እራሱ የ1ኛ ቆሮንቶስ መልእክቱን ከመጻፉ አምስት ዓመታት በፊት የመሠረታት ነበረች። ቤተ ክርስቲያኗ በጳውሎስ፥ በአጵሎስና በሌሎች ስጦታ ባላቸው ሰዎች አገልግሎት ያደገች ነበረች፡ ነገር ግን በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት የሐሰት ትምህርት ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሰርጐ መግባት ጀመረ። የተለያዩ ትምህርቶች በቤተ ክርስቲያኒቱ ሲስፋፉ ቤተ ክርስቲያኒቱ መከፋፈል ጀመረች። ከፊሉ ሰው አንድን ነገር ሲያምን ሌላው ደግሞ ሌላ ነገር ያምን ጀመረ። በ1ኛ ቆሮ. 1-6 ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መከፋፈል እንደፈጠሩ ስሰማቸው ጉዳዮች ላይ በቀጥታ እንደጻፈ እንመለከታለን። ቀጥሎ በ1ኛ ቆሮ. 1-5 ጳውሎስ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በጠየቋቸው ጥያቄዎች ላይ ሲጽፍ እንመለከታለን። 

ጳውሎስ መከፋፈል የፈጠሩትን የተለያዩ ነገሮች በማንሣት በዝርዝር ከመጻፍ ይልቅ ምክሩ ያተኮረው ዘመርሆዎች ላይ ነበር። ብዙ ጊዜ መልሱን በሁለት መልክ ይሰጣል። በመጀመሪያ ስለ ክርስትና ነት ክርስቲያኖችን ያሳስባቸዋል። ሕይወታችንን ሰው ሰራሽ በሆኑ ሕጐች መምራት የለብንም። ይልቁኑ መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን በሕይወቱ ያስተማረውን ለማመንና ለመተግበር የሚችልበትን ፃነት መጠበቅ አለብን። ክርስቲያኖች ቅዱሳት መጻሕፍት በግልጽ ለሚያስተምሩት ትምህርት ተገዝተው እለከኖሩ ድረስ ሌሎች ዝርዝር የሕይወት ጉዳዮቻቸውን የሚመሩበት መንገድ የራሳቸው መብት ስለሆነ በዚህ ሌሎች ሊቆጣጠሩአቸው አይገባቸውም። በሁለተኛ ደረጃ የሚያሳስባቸው በክርስቶስ አካል ውስጥ ስላለ የእርስ በርስ ኃላፊነት ነው። ተገቢ የሆነ ዝንባሌ በተለይ አንዱ ለሌላው ማሳየት የሚገባው ፍቅር ልናደርጋቸው ከተፈቀዱልን ነገሮች ሁሉ የበለጠ አስፈላጊ ነው። ሊደረ ያልተከለከላ ማንኛውም ነገር በተሳሳተ ዝንባሌ እስከተደረገ ድረስ ኃጢአት ነው። 

1ኛ ቆሮ. 12-14 የሰፋ ትምህርት አንዱ ክፍል ነው። ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ. 11-5 በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከሚደረግ የአምልኮ ስብሰባ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ነገሮችን ያስተምረናል። በመጀመሪያ፥ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ክርስቲያን እህቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያገኙትን አዲስ የአምልኮ ነነት ያላ አግባብ እየተጠቀሙበት ስለ ነበር ሳይሆን አይቀርም ጳውሎስ በአምልኮ ለብሰባ ውስጥ የሴቶች ድርሻ ምን እንደሆነ ያስተምራል (1ኛ ቆሮ. 1-1-16)። ሁለተኛ፥ የጌታ እራት ሥርዓትን አላአግባብ በመጠቀም ጉዳይ ትምህርት ይሰጣል (1ኛ ቆሮ. 11፡7-34)። ሦስተኛ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በመረዳትና በመጠቀም ስለሚታዩት አግባብ ያልሆኑ ነገሮች በተለይ ደግሞ የአምልኮ ስብሰባዎችን እያወኩ ስለነበሩት እንደ ልሳን ስጦታ ስላሉትም አስተምሯል (1ኛ ቆሮ. 12-14)። በመጨረሻ፥ እሑድ እሑድ የሚሰበከው ወንጌል በተላይ ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት የመነሣቱና ይህም ከትንሣኤ ተስፋችን ጋር እንዴት እንደሚያያዝ የሚገልጸው እውነት ያላመበረዙን ማረጋገጥ ፈልጐ ነበር (1ኛ ቆሮ. 15)። 

በ1ኛ ቆሮ. 12-14 ድረስ ጳውሎስ ሰላ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚችለውን በሙሉ እንዳላስተማረ መረዳት እጅግ ጠቃሚ ነው። ለምሳሌ፥ ጳውሎስ የዘረዘራቸው አብዛኛዎቹ መንፈሳዊ ስጦታዎች ስለ እዚያ ስጦታዎች በትክክል ምን ማለቱ እንደሆነ በምናውቃቸው መንገዶች የተገለጹ እይደሉም። እያንዳንዱ የመንፈሳዊ ስጦታዎች መዘርዝር በቅደም ተከተሉም ሆነ ባካተታቸው ስጦታዎች ምንነት የተለያየ ነው። ስለዚህ ጳውሎስ ለቤተ ከርስቲያን ያሉትን ስጦታዎች በሙሉ ስለመጥቀሱ እንኳን ማረጋገጫ የለም። ለቤተ ክርስቲያን ሌሎችም ይኖራሉ በማለት ነው። ጳውሎስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን የፈረጃቸው በተግባራቸውና በአስፈላጊነታቸው አንጻር ሳይሆን ያለ ምንም ልዩነት ነው የዘረዘራቸው። ይህ የሆነበት ምክንያት ጳውሎስ በሮማ መጽሐፍ ወንጌልን በዓል ያስቀመጠውን ያህል ለለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የተሟላ ትምህርትን ባለ መስጠቱ ነው። ከዚህ ይልቅ የጳውሎስ ዓላማ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ለተፈጠሩት ችግሮች ምክንያት የሆኑ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሚመለከቱ አንዳንድ እውነቶች ላይ ትኩረት መስጠት ነበር። የጳውሎስ ትምህርት ትኩረት መንፈሳዊ ስጦታዎቻችን ምን እንደሆኑ እንድናውቅ ሳይሆን እግዚአብሔርን በመፍራት እግዚአብሔር ያስቻለንን ሁሉ በማድረግ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ እንድንሳተፍ ለማበረታታት ነው። በትሕትና እየተመላለስን እግዚአብሔርንና የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን በትጋት ካገለገልን እግዚአብሔር በሰጠን ስጦታዎች እየተጠቀምን ለመሆኑ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። 

ይህ ትምህርት ዛሬ ብዙ ሰዎች ከሚያስተምሩት ተቃራኒ ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎችን በተለይ ደግሞ በልሳናት መናገር) የማወቅና የመለማመድ ፍላጐት ለቤተ ክርስቲያን ከሁሉ የላቀ የማስተማሪያ ርእስ ሆኗል። አንዳንዶች እንዲህ በማለት ይከራከራሉ። «ስጦታዎቻችንን ብናውቅና ብንለማመዳቸው የቤተ ክርስቲያን ችግርች በሙሉ ይቃለላሉ።» ኢየሱስ ቀን እንዲህ አላ በመጀመሪያ «የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል» (ማቴ. 6፡33)። እዚአብሔር እንደሚፈልግብን በመሆን ላይ ብናተኩር እዚአብሔር እንድንኖር የሚፈልግብንን ብንኖር፥ አንዳችን ሌላችንን ብናገለልና እዚአብሔር እንደሚል ላጠፉት ብንሰብክ መንፈሳዊ ስጦታዎች የቤተ ክርስቲያን ተፈጥሮአዊ አካል ይሆናሉ። አስታውስ፡ ሚዛናዊ የሆኑ ትምህርቶች ላቤተ ክርስቲያን ጤንነት ቁልፍ ናቸው። 

ጥያቄ፡- ሀ) አምልኮን የሚመለከቱ የቤተ ክርስቲያንህን ሰላምና አንድነት የሚነሱ ወይም የሚያውኩ ነገሮች ምንድን ናቸው? ለ) በ1ኛ ቆር. 2-14 ላይ ባለህ መረዳት መሠረት ለታየው ጳውሎስ ለእነዚህ ችግሮች የሚሰጠው መልስ ምን ይሆን ነበር? 

አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት እንደሚያምኑት ጳውሎላ ከ1ኛ ር. 21 ድረስ ባለው ክፍል የሚናገረው ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ሳይሆን መንፈሳዊ ስለመሆን ነው። አንዳንድ የቆርንቶስ ክርስቲያኖች በልሳናት መናገርን በመሳሰለው ውጫዊ ነገር መንፈሳዊ መሆናቸውን ለማረጋግጥ ይጥሩ የነበረ ይመስላል። ጳውሎስ ላላ መንፈሳዊነት ባላቸው አሳብ በተለይ ደሞ በልሳናት በመናገር እንደሚገለጽ በሚያስቡት አስተሳሰብ አልተስማማም ነበር (1ኛ ቆሮ. 4፡6፥ 18-19፥ 3+ + 36-38)። በልሳናት የመናገር ስጦታ ያለአግባብ በሥራ ላይ እየዋለ ነበር። ስለዚህ የመንፈሳዊ ስጦታዎች ላማ ምን እንደሆነ በመናገር ይጀምራል። በልሳናት መናገር ከመንፈሳዊ ስጦታዎች አንዱ ብቻ ነው (1ኛ ቆሮ. 12)። ቀጥሎ ከሁሉም መንፈሳዊ ስጦታዎች ይልቅ የፍቅር አመለካከት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ወደ መናገር ያልፋል (1ኛ ቆሮ 13)። መንፈሳዊ መሆናችንን ወይም ያለ መሆናችንን በትክክል የሚያሳየው መንገድ ይህ ነው። በመጨረሻ በአምልኮ ስብሰባ ውስጥ በልሳናት ስለመናገር ግልጽ የሆኑ ትእዛዛትን ይሰጣል። በልሳናት በሚናገር በእግዚአብሔር መንፈስ የሚነገር የማይታወቅ ቋንቋ) ወይም የትንቢት ንግግር በእግዚአብሔር መንፈስ የሚነገር የሚገባ ንግግር) መካከል ያለውን ልዩነት ይገልጻል (1ኛ ቆሮ. -3)። የአምልኮ ስብሰባ ሁከት የሌለበትና በሥርዓት የሚካሄድ እንዲሆን ትንቢትንና በልሳናት መናገርን በሕዝብ መካከል ስለመጠቀም ግልጽ መመሪያዎችን ይሰጣል (1ኛ ቆሮ. 14፡26-40)። 

1ኛ ቆሮ. 12-14 ለመረዳት ሁለት ነገሮችን ማስታወስ ያስፈልጋል። በመጀመሪያ፥ የጳውሎስ አትኩሮት በሕዝብ መሃል ስለሚደረግ የአምልኮ ስብሰባ እንጂ በቤት በግል ስለሚደረግ አምልኮ አይደለም (1ኛ ር. 14፡2 16፤ 18–19፥ :28፥ 26)። ሁለተኛ፥ የጳውሎስ ትኩረት በልሳናት በመናገር ላይ እንጂ በስጦታዎች ሁሉ ላይ እይደለም። በትምህርቶቹ ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለመክፋፈል ምክንያት የሆነውን ከአግባብ ውጪ የሆነ የልሳን አጠቃቀም ለማስተካከል ወይም” እርምት ለመስጠት ይሞክራል። 

የቆርንቶስ ቤተ ክርስቲያን በልሳናት በመናገር ላይ ሁለት ችግሮች የነበራት ትመስላለች። በመጀመሪያ በልሳናት የመናገር ስጦታ ልዩና መንፈሳዊ ሰው መሆኑ የሚረጋገጥበት መንገድ እንደሆነ አድርገው ያስተምሩ ነበር። ስለዚህ ለሌሎች መንፈሳዊ ስጦታዎች እኩል ዋጋ የማይሰጡ ስለነበሩ ሚዛናዊነት ይጎድላቸው ነበር። ጳውሎስ ለጦታዎች ሁሉ አስፈላጊ መሆናቸውን ላማሳየት ረጅምን ጊዜ የወሰደው ለዚህ ነበር። በሁለተኛ ደረጃ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የልሳን ስጦታ አጠቃቀም ለትክክለኛ አምልኮ አዋኪ ነበር። በአምልኮአቸው እጅግ አፍራሽ ሥርዓት አልበኝነት ሰፍኖ ስለነበር እውነተኛ አምልኮን የሚያደናቅፍና ለማያምኑ ሰዎች መጥፎ ምስክርነት የሚሰጥ ነበር። ስለዚህ ጳውሎላ በልሳናት መናገር በሕዝብ የአምልኮ ስብሰባ እንዴት ተግባር ላይ መዋል እንዳለበት ለየት ያለ ትእዛዝ ሰጠ። 

ጥያቄ፡- ዛሬም በልሳናት መናገር አንዳንድ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከሚያመጣው ችግር ጋር ይህ ተመሳሳይ የሚሆነው እንዴት ነው? 

ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 12፡1-3 እንብብ። ሀ) ጳውሎስ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ባለማወቅ ወይም በቸልታ እንዳያልፉት የሚፈልገው ነገር ምን ነበር? ለ) ከመዳናቸው በፊት የነበራቸውን ሕይወት ግለጽ። ሐ) ከዳኑ በኋላ መንፈስ ቅዱስ እንዲሉ ባለቻላቸው ነገሮችና ከመዳናቸው በፊት ይሉአቸው {የነበሩ ነገሮች መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? 

ሚዛናዊ ያልሆነ ትምህርት የሐሰት ትምህርትን ያህል አደገኛ ነው። ሚዛኑን ያልጠበቀ ትምህርት እንዲያውም የሐሰተኛ ትምህርት ሌላው ቅርጽ ነው። የቆሮንቶስ ከርስቲያኖች አዴጋ ላይ የነበሩት የሐሰት ትምህርት ስላጋጠማቸው ሳይሆን በልሳናት ስለመናገር ሚዛኑን የሳተ ትምህርት ይሰጡ ስለነበር ነው። መሠረታዊው ችግራቸው ቀን ሰው እንዴት መንፈሳዊ እንደሚሆን የተሳሳተ አሳብ ስለነበራቸው ነው። 

ጳውሎስ ትምህርቱን የጀመረው የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ቶላ ማላት እንደሌለባቸው በመናገር ነው። በግሪክ እነዚህን ሁለት ቃላት መረዳት የሚቻልበት ሁለት የተለያዩ መንገዶች አሉ። እዚህ ቃላት የሚሰጡት ትርጉም «መንፈሳዊ ሰው» ማለት ሊሆን ይችላል። ደግሞም ጳውሎስ ያተኩርበት የነበረው ትምህርት ሰው እንዴት መንፈሳዊ እንደሚሆን ነበር። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ ጸሐፊዎች እንደሚሉት የቆሮንቶስ ሰዎች ስለዚህ ችግር ለጳውሎስ በጻፉበት ወቅት በቤተ ክርስቲያን ወስጥ ከነበሩት አንደኛው ቡድን በልሳናት መናገራቸውን ጳውሎስ እንደፍላቸው ይፈልጉ የነበረ ሲሆን ሌላኛው ቡድን ደግሞ በልሳናት የሚናገሩትን እንዲያወግዝላቸው የሚፈልጉ ነበር። ጳውሎላን ይጠይቁት የነበረው ጥያቄ በልሳናት መናገርና ተአምራትን ማድረግ የመሳሰሉ መንፈሳዊ መገለጦች ለሰው መንፈሳዊነት የትክክለኛ ማስረጃ ዎች መሆናቸው እውነት ነውን? ወይስ በልሳናት መናገር ለሰው መንፈሳዊነት ምልክት ነው ብለህ አታስብም አይደል? ማለታቸው ነበር። 

ወይም «መንፈሳዊ ስጦታዎች» የሚለው ሐረግ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን በሕይወቱ የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳለበት ማረጋገጣዎች ይሆኑ ዘንድ የሚሰጡ ልዩ ችሎታዎች ናቸው። ሁለቱም የሚያስክዱ ትርጉሞች ናቸው። የትምህርቶቹ ይዘት መንፈሳዊነት ስለሚያካትታቸው ነገሮች የተሳሳቱ መረዳቶችን ያዘለ ነው። ነገር ግን ጳውሎስ የሚናገረው በልሳን እንደ መናገር ያሉ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሕር ልጆች የሰጣቸውን መንፈሳዊ ስጦታዎችን ሳይሆን አይቀርም። 

ጳውሎስ «መንፈሳዊ» እና «ለጦታዎች» የሚሉትን ቃሎች መንፈስ ቅዱስ የሚገለጥበትን ሁኔታ ለማሳየት አጣምሮ ተጠቀመባቸው። «ስጦታዎች» የሚለው ቃል ጸጋ ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ለአንድ ሰው በእግዚአብሔር ጸጋ ስለተሰጠ ነገር የሚያመለክት ነው። ስለዚህ «የጸጋ ስጦታ» ብለን ልንጠራው እንችላለን። የግሪኩ ቃላ (ካሪዝታ› የሚል ሲሆን ‹ካሪዝማቲክ› የሚለው ቃል የተገኘው ከዚህ ነው። ይህ ቃል በልሳናት መናገርና ተአምራትን ማድረግ የመሳሰሉት ስጦታዎች ለዛሬይቱ ቤተ ክርስቲያንም የእግዚአብሔር ዕቅድ እንደሆነ የሚያምኑ ክርስቲያኖችን የምንጠራበት ነው። ሆኖም ቀን ጳውሎስ ይህን ቃል የሚጠቀመው እንደ ፈውስና በልሳናት መናገር ያሉ ተአምራዊ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለመጥቀስ አይደለም። ይልቁኑ መምከርና መስጠት የመሳሰሉ የተለመዱ የአገልግሎት ችሎታዎች ይካተቱበታል። ቃሉ ከዚህም የሰሩ ትርጉም ያለው ሲሆን እንደ ድነት (ደኅንነት)ና ለማግባት ወይም ሳያገቡ ለመኖር ላላ ችሉታ እንኳ ያገለግላል (1ኛ ቆሮ. 7፡7)። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ካየነው ክርስቲያኖች ሁሉ ካሪዝማቲክ ናቸው። ምክንያቱም ሁሉም እንዳንድ ስጦታዎች ወይም በእግዚአብሔር በነፃ የተሰጡ ችሎታዎች አሏቸው። ሆኖም ግን በ1ኛ ቆሮ. 12 የምናገኘው ጳውሎስ የሚናገርላቸው ልዩ ስጦታዎች በክርስቶስ አካል ውስጥ ያሉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ስጦታዎች ናቸው። 

ነገሮች ሁሉ ወደ እኛ የሚመጡት ስለሚገባን ሳይሆን እግዚአብሔር በነፃ ስላሚሰጠን መሆኑን ስለሚያውቅ ከጳውሎስ ተወዳጅ ቃሎች አንዱ ጸጋ ነው። ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ይህን ማለታወስ የሚገባቸው አስፈላጊ ነገር ነበር። እንደ ተአምራትን ማድረግ ያሉ የሚታዩ አስደናቂ መንፈሳዊ ስጦታዎችም ሆኑ ምሕረትን እንደ ማድረግ ያሉ ተራ ስጦታዎች የሚገኙት በሰው መንፈሳዊነት ምክንያት አይደለም። ይልቁኑ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው እንደሚያስፈልገው በጸጋው የሚሰጠው ነው። 

ጳውሎላ የሚጠቀመው ሁለተኛው ቃል «መንፈሳዊነት» የሚል ነው። ክመንፈስ ቅዱስ የሚመጡ የተለያዩ የማገልገል ችሎታዎች ከሰው ተፈጥሮአዊ ችሎታዎች የሚገኙ ሳይሆኑ ምንባቸው መንፈስ ቅዱስ ነው። ደግሞም በአማኞች መካከል መንፈስ ቅዱስ የመኖሩ ማረጋገጫዎችም ናቸው። 

በ1ኛ ቆሮ. 12፡2-3 ያሉትን ቁጥሮች ለመረዳት እጅግ አስቸጋሪ ነው። ጳውሎስ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚያስተላልፈውን መልእክት የቆሮንቶስ ከርስቲያኖች ክርስቲያን ከመሆናቸው በፊት የነበራቸውን ሕይወትና ክርስቲያን ከሆኑ በኋላ ያላቸውን ሕይወት በማወዳደር ለማሳየት የፈለገ ይመስላል። ጳውሎስ ሁለት መንፈሳዊ ኃይላት እንዳሉ ክርስቲያኖችን ያሳስባቸዋል። የመጀመሪያው ስጦታ ጣዖት በማምለካቸው የተነሣ ከመዳናቸው በፊት የተከተሉት ለሰይጣን ኃይል የሚሠራ ነው። በጣዖት አምልኮ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ባይኖርም እንኳ አጋንንት የሚሰጡት «በልሳናት የመናገር ችሎታ» አለ። ዛሬም ቢሆንም እንኳ በአጋንንት የተያዙ ሰዎችና ጠንቋዮች በልሳናት መናገር እንደሚችሉ የታወቀ ነው።) ክርስቲያን ከሆኑ በኋላ አንዳንዶቹ ስልሳናት ለመናገር የሚችሉ ሲሆኑ በዚህ ጊዜ ግን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካይነት ነው። ስለዚህ አብዛኛዎቹ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እንደሚያስቡት በልሳናት መናገር ብቻ ሰው መንፈሳዊ የመሆኑ ምልክትና የመንፈስ ቅዱስም ውጤት አይደለም።

የአጋንንት ኃይል ውጤት ምን እንደሆነና የመንፈስ ቅዱስ ውጤት ምን እንደሆነ ለመለየት እንድ ተጨማሪ ነገር ያስፈል. ነበር። ልዩነት ማድረቅ የሚቻለው እንዴት ነው? ጳውሎስ እንደሚናገረው ልዩነቱና ቁም ነገሩ ንቃተ ሕሊናን የሚያስለቅቅ ስሜታዊ ንቀር ሳይሆን ሰዎች በአእምሮ ሆነው የሚያምኑትና የሚናገሩት ነገር ይዘት ነው። ማንም ሰው በአጋንንት ተጽዕኖ ሥር ሆኖ በቅንነት «ኢየሱስ ጌታ ነው» ሊል አይችልም። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚናገር ማንም ሰው ደግሞ ኢየሱስን ሊረግም አይችልም። ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚናገር ሰው ሁሉ ንግግሩን የሚጀምረው «ኢየሱስ ጌታ ነው» በሚለው ቃል ነው እላላም። ይልቁኑ ጳውሎላ የሚለው በልሳናት መናገር ብቻ በራሱ ልሳኑ የመጣው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለመሆኑ ማረጋገጥ እንዳልሆነ ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስን በእምልኮ መንፈስ ያለማቋረጥ ከፍ በማድረጉ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ለመገኘቱ እርግጠኞች መሆን እንደምንችል ነው። 

(ማስታወሻ፡- ዛሬ በዘመናችን «ኢየሱስ ጌታ ነው’ የሚሉ ብዙ ክርስቲያን ተብዬዎችን ስንመለከት በ1ኛው ክፍለ ዘመን ለኖሩ ክርስቲያኖች ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለውን ቃል ለማለት ምን ያህል ከባድ እንደ ነበር ለመረዳት ይቸግረናል። ይህ ዛሬ እንደ ሊቢያና ሌሎች የዐረብ አገሮች ባሉ ክርስቲያኖች ላይ ከሚደርስባቸው ጭንቀት ጋር ይመሳሰላል። ላእዚህ አገሮች ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት የሞትን ጽዋ መጋት ነው። በስደቶች ሁሉ ውስጥ ጸንቶ የመቆምና ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ላለን እምነት መሥዋዕት ማድረግ በመንፈስ ቅዱስ ብቻ የሚገኝ ነው። ሰዎች ከሚጠብቁትና ከሚያስቡት በተቃራኒ «ኢየሱስ ጌታ ነው» ብሎ በግልጽ መናገር መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ውስጥ የመሥራቱ ምልክት ነው።) 

ጳውሎስ ያስተምር የነበረው ተአምራታዊ ኃይልና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ለሚያዩ ክርስቲያኖች እነዚህ ነገሮች መንፈስ ቅዱስ በመካከላቸው የመኖሩ እውነተኛ ምልክት ነው ብለው ለማመን እጅግ እንደሚቀላቸው ነው። ሆኖም ቀን መንፈስ ቅዱስ በመካክላቸው እየሠራ ለመሆኑ ለክርስቲያኖች እውነተኛው ማረጋገጥ ኢየሱስን እንደ ጌታ ማክበራቸው ነው። ምንም እንኳ ትክክለኛ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ህልውናና ኃይል መገለፃ ቢሆንም እንኳ ማንኛውም ነገር በልሳናት መናገርም ቢሆን ኢየሱስን እንደ ጌታ ከማክበር ፈቀቅ እያለ የሚሄድ ከሆነ ጣዖትን ማምለክ ዓይነት አደጋ ውስጥ እየገባ ነው ማለት ነው። በጣዖት አምልኮ ሰዎች መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ድርጊቱ ብቻ ስለሚያደስታቸው አንድ የሚታይ አስገራሚ ነገር እንዲፈጸም ይጠብቃሉ። ለክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና በልሳናት መናገር በራሳቸው ዓላማ ከሆኑ ኢየሱስን የማምለኪያ መሣሪያ ከመሆን ይልቅ ሰዎችን ከኢየሱስ እያራቁ ወደ ጣዖት አምልኮ ይመሩአቸዋል። የመንፈስ ቅዱስ ተቀዳሚ ፍላጐት ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ማምጣት ነው። ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከተደረጉ መንፈሳዊ ስጦታዎች በሙሉ ክብርን ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር ያመጣሉ። 

ጥያቄ፡- ሀ) በልሳናት የሚናገሩ ጣዖት አምላኪዎች ወይም ጠንቋዮች እንዳሉ ሰምተህ ታውቃለህን? ለ) የምታውቅ ከሆነ አንዳንድ ክርስቲያኖች በልሳናት በሚናገሩበት ጊዜ የሚያደርጓቸው ነገሮች እዚህ ጠንቋዮች ከሚያደርጓቸው ነገሮች በውዓዊ መልካቸው የሚለዩት በምንድን ነው? ሐ) ብዙ ክርስቲያኖች በልሳናት ለመናገር የሚፈልጉበትና አስደናቂ የፈውስ ልምምድ ወዳሉባቸው ስብሰባዎች መሄድ ደስ የሚያሰኛቸው ምንድን ነው? ብዙ ጊዜ ውስጣዊ ዓላማቸው ምንድን ነው? መ) ውስጣዊ ዓላማቸው መልካም ወይም ስሕተት የሚሆንበት ሁኔታ ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- ሀ) ብዙ ክርስቲያኖች በልሳናት በመናገር ወይም በፈውስ አገልግሎት ኢየሱስ ክርስቶስን ለማክበር ከመነዉ ፍላጐት ሳይሆን አስደናቂ የሆኑ ክስተቶችን ለማየት ከመጓጓት የተነሣ የሚሳቡባቸውን መንገዶች ዘርዝር። ለ) ይህ አደገኛ የሚሆነው ለምንድን ነው? በተአምራቱ በራሱ ወይም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ትኩረት በሚሰጥ መንገድ አንዱ ሁኔታ ሊገለጽ ስለሚችልበት ምሳሌ ስጥ። ልዩነቱ ምንድን ነው?

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.