መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡12-31 )

ዮሐንስና ጸጋዬ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ሁላት መሪዎች ነበሩ። ጻሩ ቀን በጣም የተለያዩ ስጦታዎች ነበሯቸው። ዮሐንስ ብዙ ሰዎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለሱ ዘንድ እግዚአብሔር የሚጠቀምበት ወንጌላዊ ነበር። ጸጋዩ ሰዎችን የእግዚአብሔርን ቃል ጥልቀት ባለው መንገድ ለማስረዳት የሚችል አስተማሪ ነበር። ነገር ግን ጸጋዬ በዮሐንስ ይቀና ነበር። ምክንያቱም ዮሐንስ ብዙ ሰዎችን ለክርስቶስ የማረከና በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሰዎች የሚያመሰኑት ስለ ነበር ነው። ስለዚህ ጸጋዬ በዮሐንስ ላይ በማሴር የቤተ ክርስቲያንን ሽማግሌዎች በእርሱ ላይ እንዲነሡ ለማድረግ ጣረ። በመጨረሻ ቤተ ክርስቲያን ዮሐንስን አባራ ጻጋዩን በወንጌላዊነት ቀጠረች። 

ጥያቄ፡- ሀ) ይህ ታሪክ ስለ ክርስቶስ አካልና እግዚአብሔር መንፈሳዊ [ስጦታን እንዴት እንደሚሰጥ ትክክለኛ ግንዛቤ ማጣትን እንዴት ያሳያል? ላ) የዮሐንስና ጸጋዬ አብረው ቢሠሩ ኖሮ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ጠንካራ ትሆን ነበር? ሐ) የወንጌላዊነት ስጦታ ያልነበረው ጸጋዩ እንደ ወንጌላዊ ሆኖ ለመሥራት በመሞከሩ ቤተ ክርስቲያን የምትክመው በምን ዓይነት መንገድ ነበር? መ) ይህ ታሪክ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለ አገልግሎት ያለውን የተሳሳተ አመለካከት እንዴት ያሳየናል? ሀ) እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች በቤተ ክርስቲያንህ እንዴት እንደተከሰቱ ምሳሌዎችን ስጥ። 

ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 12፡12-31 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር አካልን የሠራበት መንገድ በልዩነቶች ውስጥ ያላ አንድነት መሆኑን የአካል ብልቶች ንጽጽር እንዴት አድርጐ ያሳያል? ለ) የክርስቶስ አካል የሆነቸው ቤተ ክርስቲያን ከሰው አካል ጋር ያላት ተመሳሳይነት እንዴት ነው? ሐ) መንፈስ ቅዱስ እንዴት መንፈሳዊ ስጦታዎችን እንደሚሰጥና ስጦታዎችን ሁሉ በአንድነት እንደሚሠሩ ዋና ዋና መርሆዎችን ዘርዝር። መ) ዮሐንስና ጸጋዬ ይህን እውነት በሚገባ ተገንዝበው ቢሆን ኖር እንዴት ይረጻቸው ነበር? ሠ) በሠንጠረዥ ላይ አዳዲሶችን መንፈሳዊ ስጦታዎችና ትርጉማቸውን መሙላትህን ቀጥል። 

የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች አንድነት ይኖር ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ በአንድ መንገድ መሥራት አለበት በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ውስጥ ነበሩ። ለእያንዳንዱ ክርስቲያን ተመሳሳይ ስጦታን በተለይ ደግሞ በልሳናት የመናገር ስጦታን መስጠት አለበት ይሉ ነበር። የሰውነት አካል እንዴት እንደሚሠራ አልገባቸውም ነበር። ጳውሎስ የሚያስተምረው ሥጋዊ አካል ይሠራ ዘንድ በአንድነት ውስጥ ያሉ ልዩነቶች መኖር እንዳለባቸው ነው። የክርስቶስ አካል ይሠራ ዘንድ በመንፈሳዊ ስጦታዎችና በአጠቃቀማችን ልዩነት መኖር አለበት። 

ቤተ ክርስቲያን እማኞች የሚሰበሰቡበት ሕንፃ አይደለም። እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን አካል ናት። ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን የክርስቶስ አካል ብሎ ይጠራታል። ስለ ቤተ ክርስቲያን በሚናገርበት ጊዜ እንኳ ቤተ ክርስቲያንን ክርስቶስ ብሎ ይጠራታል (1ኛ ቆሮ. 12፡12)። ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን በሚያሳድድበት ጊዜ ኢየሱስ ጳውሎስን ስለምን ታሳድደኛለህ በማላት ወቅሶት እንደነበር ታስታውሳለህ (የሐዋ. 9፡4)። እግዚአብሔር የአማኞች አካል በአንድ ቦታ እንደተሰበሰቡ በሚመለከትበት ጊዜ የሚያመለክተው የሆኑ የተለያዩ ግለሰቦችን አይደለም። ነገር ግን «አካልን» ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስን በምድር ላይ የምትወክል መሆኗን ነው የሚመለከተው። 

የአንድ አጥቢያ ክርስቲያኖችን በቡድን አካል የሚያደርጋቸው ምንድን ነው? መንፈስ ቅዱስ ነው። የልዩነታቸውና የአንድነታቸው ምንጭ ነው። የአንድነታቸው መነሻ ሁላቸውም በመንፈስ ቅዱስ መጠመቃቸው ነው። እያንዳንዱ ክርስቲያን በዳነ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሏል። በዚያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አማኞችን ወደ አንድ የክርስቶስ አካል ልምሮአቸዋል። የተለያዩ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በአንድ አካል ውስጥ የሚሰጥ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የልዩነቶቻቸው ምንጭ ስለሆነ ነው። 

ጳውሎስ በዚያን ዘመን የነበረችው ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ዘመን ካሉት ጋር የምትመሳሰልበት ሁኔታ በቀጥታ አላ ባይልም እንኳ በልሳናት የመናገር ስጦታዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጡ የተላያዩ ሁኔታዎች ይከሰታሉ። ብዙ ጊዜ በልሳናት መናገር የሚጀምሩት እራሳቸውን እንደ መንፈሳዊ ሰዎች ይመለከታሉ። የተመረጡና መንፈስ ቅዱስ ያላቸው እነርሱ ` ብቻ ይመስላቸዋል። እነዚህ ውስጣዊ ወገኖች አካሎቻቸው በተለይ ደግሞ በተግባራቸው ለቀሪው ጉባኤ እኛ ከእናንተ እንሻላለን፥ መንፈስ ቅዱስ አለን። ለዚህ ማረጋገጥ በልሳናት እንናገራለን። እናንተ ስለማትናገሩ እንደ እኛ መንፈሳዊ አይደላችሁም የሚል ገጽታ አላቸው። ወዲያውኑ መከፋፈል ይሆንና ቡድኖች መፈጠር ይጀምራሉ። 

ቀጥሎ ሦስት ነገሮች ይሆናሉ። ብዙዎች መንፈሳዊ ለመሆን በመፈለግ ማስመሰል ይጀምራሉ። ለሌሎች መንፈሳዊ መለለው መታየት ስለሚፈልጉ በልሳናት የሚናገሩ ያላመስላሉ። ሃሌሉያ እያሉ ይጮኻሉ፡ እዞቻቸውን ያነሣሉ። በሌሎች ፊት መንፈሳውያን ለመምሰል ይወዛወዛሉ። ይህ የግብዝነት ኃጢአት ነው። 

ሁለተኛ፣ አንዳንድ ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያኖቻቸውን በመልቀቅ ወደ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ይገባሉ። ወይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለቡድኑ ወገናዊነት የማይሰማቸው እጅግ ዝምተኞች ይሆናሉ። እንደ ሌሎች መንፈሳውያን ለምን እንዳልሆኑ በማሰብ ይደነቃሉ። 

ሦስተኛ፣ አንዳንዶች የመጀመሪያውን ቡድን አጥብቀው የሚቃወሙ ይሆናሉ። እነርሱ እራሳቸውን የበለጠ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አድርገው ስለሚያስቡ ይታበያሉ። እነዚህ ስሜታውያን ብቻ ናቸው ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ስለማያውቁ እውነተኛ ክርስቲያኖች እንደሚያደርጉት አይለማመዱትም ሰማላት ይሳለቁባቸዋል። የእነዚህም ትዕቢት የመጀመሪያዎቹን ያህል ክፉ ነው። 

ጥያቄ፡– ይህስ ነገር በቤተ ክርስቲያን ሲፈጸም እንዴት እንዳየህ ግለጥልን። 

የሚያሳዝነው ግን እነዚህ ቡድኖች የተሳሳቱ መሆናቸው ነው። ሁላቸውም ጳውሎስ ለክርስቶስ አካል ያስተማረውን ዘንግተዋል። ለዚህ ነው ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን የሰጠው የስጦታዎች ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ የአካል እንድነት አስፈላጊ ስለመሆኑ እነዚህን ሦስት ቡድኖች እያንዳንዳቸውን ለማስተማር የጻፈው። 

1ኛ ቆሮ. 12፡12-31 ላይ ሰብዓዊ አካልን ከመንፈሳዊ አካል ጋር ከሚያነጻጽረው ክፍል የሚከተሉትን ነገሮች እንማራለን። 

1. የክርስቶስ አካል እርስ በርሱ የተሳሰረ አንድ ቅንጣት ነው። እንደ አንድ አብሮ ለመሥራት የተቀናጀ ነው። በሌሎች ቦታዎች ክርስቲያኖች በአእምሮና በመንፈስ አንድ እንዲሆኑ ጳውሎስ ይለምናቸዋል (ፊልጵ. 2፡1-4)። 

2. የክርስቶስ አካል የተለያዩ ክፍሎች ወይም የተላያዩ ስጦታዎች ያሉት ነው። በዚህ ልዩነት ውስጥ እንድነት አለ። 

3. የክርስቶስ አካል የተለያዩ ክፍሎች ወይም ሰዎች ሁሉ ከመንፈሳዊ ስጦታዎች ጋር በክርስቶስ አካል ውስጥ ይፈለጋሉ። ድንቀኛ ስጦታ የሌለው ማንኛውም ግለሰብ እንኳ ላመለየት መብት የለውም። ሌላ ማንኛውም ሰው ደግሞ ይህንን ሰው አንተ የአካሉ ክፍላ አይደለህም የማለት መብት የለውም። እያንዳንዱን ሰው በክርስቶስ አካል ውስጥ ያስቀመጣው መንፈስ ቅዱስ ከሆነ እያንዳንዱ ሰው ለዚያ አካል ጤንነትና ተግባር ተፈላጊ መሆኑን መገንዘብ አለብን። 

በልሳናት በመናገር ስጦታዎች የሚመኩ ሰዎች ሌሎች እንደ እነርሱ እንዲሆኑ ለማስገደድ ወይም ኅብረቱን ትተው እንዲሄዱ እንዳይገፉ መጠንቀቅ አለባቸው። በልሳናት የማይናገሩት ደግሞ በልሳናት የሚናገሩትን እንደ እነርሱ ለማድረግ እንዳያስገድዱ መጠንቀቅ አለባቸው። በልሳናት ባለመናገራቸው ምክንያት መንፈሳውያን እንዳልሆኑ የሚመስላቸው፥ በልሳን የሚናገሩት እግዚአብሔርን እንደሚያከብሩበት ያለ የተለየ ስጦታ በመንፈስ ቅዱስ ለእነርሱም እንደተሰጠ ማስታወስ አለባቸው። ስለዚህ በልሳናት የማይናገርና የመምከር ስጦታ ብቻ ያለው ሰው በልሳናት በሚናገረው ሰው ምክንያት ስጋት ሊሰማው አይገባም። 

4. የቤተ ክርስቲያን ንነት የሚገኘው እያንዳንዱ አካል በተገቢው ሁኔታ ተግባሩን ሲፈጽም ነው። ዓይናችንና ጆሮአችን፥ በተናጠልና በተደጋጋፊነት መሥራት አለባቸው። ስለዚህ ደግሞ በአካሉ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ሰው የራሱን ስጦታ መጠቀም አለበት። ይህን በማድረጉ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ጥንካሬ ያጐላብታል። 

5. ማንኛውም ዓይነት ስጦታ ከሁሉም የላቀ እንደሆነ በሚታሰብበት ጊዜ አካሉ ሚዛን ያጣ ይሆናል። ለአካሉ ስትክክል መሥራት እያንዳንዱ ሰው መንፈሳዊ ስጦታውን መጠቀም አለበት። አንዱ ስጦታ በሌላው ስጦታ ላይ ጥገኛና ደግሞም የሌሎችን ስጦታዎች ሚዛን የሚጠብቅ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ስጦታዎችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ለመጠበቅ መቻል አለባት። ሰዎች ድንቀኛ በሆኑት በልሳናት መናገርና ፈውስና ሌሎችም ላይ ከሚገባው በላይ ካተኮሩ አካል እንድ ትልቅ ዓይን ብቻ መስሎ አስቀያሚ መልክ ይይዛል። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በሙሉ ሊከበሩና ተግባር ላይ ሲውሉ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር በቀደሳት መንገድ ሚዛናዊና ውብ መሆን ትችላለች። 

6. ድንቀኛ ያልሆኑ መንፈሳዊ ስጦታዎች ለቤተ ክርስቲያን ተግባር እጅግ ጠቃሚ የሆኑና እንዳንድ ጊዜ ድንቀኛ ከሚሆኑት ስጦታዎች እንኳ የበለጠ ሊከበሩ የተገቡ ናቸው። በልሳናት የሚናገሩት ክርስቲያኖች በማይናገሩት ላይ የበላይነት ከተሰማቸውና ካሪዝማቲክ ያልሆኑ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዳይኖሩ የሚመኙ ከሆኑ ጥንቃቄ ቢያደርጉ ይሻላቸዋል። በዚህ መንገድ ሊመጻደቁና በልሳናት በመናገር ላይ የማያተኩሩትን ሊያባርሩ መብት የላቸውም። ካሪዝማቲክ ያልሆኑት ክርስቲያኖች በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ላይ ስለሚኖራቸው አመለካከት ተመሳሳይ ነገር ማለት ይቻላል። 

መንፈሳዊ የሆንን እኛ በተለይ እግዚአብሔር በጣም የሚታይ ስጦታ የሰጠን ድንቀኛ ስጦታ የሌላቸውን ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን በጣም የሚፈለጉትን ሰዎች የምናከብርበትን መንገድ እንድንፈልግ ታዝዘናል። የመምከር ስጦታ፥ ያላቸው ሰዎች ስጦታዎቻቸውን ባይጠቀሙበት ብዙ ሳይቆይ የቤተ ክርስቲያን አባላት ተስፋ በመቁረጥ እርስ በርስ ይጋጫሉ። ሁላችንም ብንሆን ከእኛ የተለዩ ሰዎችን ማድነቅን መማር አለብን። ወንዶች የሴቶችን ከእነርሱ መለየት ማድነቅና ልዩ ክብር ላሌቶች መስጠትን መማር አለባቸው። ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ተፈላጊ መሆናቸው ንዛቤ ውስጥ መግባት አለበት። ከፍተኛ ቁጥር ካለው ብሒር የተገኙ ክርስቲያኖች ከአናሳ ብሔር የመጡ ክርስቲያኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የዓወቱት ሚና እኩል መሆኑን ተነዝበው ክብር መስጠት ይገባቸዋል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ ዘሮች መካከል ማኅበራዊ ደረጃዎች፥ ጾታዎችና ገደቦች ተወግደዋል (ገላ. 3፡26-29)። 

7. ሁላችንም የአንድ አካል ክፍሎች መሆናችንን ከተረጻን እያንዳንዳችን ስላለን ስጦታ ሳይሆን ስለ አካሉ ማሰብ አለብን። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለ አንድ ሰው ሲጐዳ አማኞች ሁሉ ለእርሱ እንደሚገጻቸው ተቆርቋሪነታቸውን ማሳየት አለባቸው። የበለጠ የሚታይ ለጦታ ያለው ሰው ሲከበር ከመቅናት ይልቅ ሁሉም ሰው በአንድነት ሐሴት ሊያደርግ ይገባል። ማንም ክርስቲያን በአካሉ አንድነት ላይ ሊያተኩር እንጂ በላሰባዊነት አቅጣት ሊያስብ አይገባም። ይህ አመለካከት ካለን እግዚእብሔር ለአንድ ሰው በልሳናት የመናገር ስጦታን ሲሰጥ ሁላችንም ፍስ እንሰኛለን። እግዚአብሔር ለሌላው ሰው የእርዳታንና የመስጠትን ስጦታ ሲሰጥ ሁሉም ደስ ይሰኛሉ። ይህ ዓይነት ስለ እካል የሚኖረን አመላካከት መንፈሳዊ ስጦታዎቻችንን ከሌሎች ጋር በማወዳደር ሊፈጠር ሚችለውን መንፈሳዊ ትዕቢት ለማሸነፍ ይረዳናል። በተጣማሪ ብርቱ መንፈሳውያን ተብሎ የሚጠራና ደካማ መንፈሳውያን የሚባሉ ቡድኖች ከመፍጠር አዝማሚያ ይጠብቀናል። በአንዳንድ ስጦታዎች ላይ ሚዛን ያጣ ትኩረት ከማድረሳ በምንታቀብበት ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ልዩ ልዩ ስጦታዎች የከበርንና እግዚአብሔር እንደሚፈልግብን እንደ አንድ አካል የምንሠራ መሆን እንችላለን። 

ጥያቄ፡- ሀ) ከላይ ከተመለከትነው ክፍል ዋና ትምህርታችን ከልስ። ለ) በመንፈሳዊነትና በመንፈሳዊ ስጦታዎች ላይ ባለ የተሳሳተ አመለካከት አብያተ ክርስቲያናት መካከልና ደግሞ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መከፋፈል እንዴት እንደተፈጠረ የተመለከትከውን ግለጽ። ሐህ ይህን ጉዳይ በግልጽ መረዳት በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ወይም በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ የአማኞች ቡድኖች መካከል የተፈጠረን ውጥረት ለማርገብና ላማጥፋት እንዴት ይረዳል? 

1ኛ ቆሮ. 12፡12-31 በልሳናት ለሚናገሩም ሆነ ለማይናገሩ ማስጠንቀቂያ ነው። አንዳችን ሌላችንን ከቤተ ክርስቲያን ወይም ካለንበት ኅብረት ገፍተን እንዳናስወጣ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። ይልቁኑ አንዳችን የሌላችንን ስጦታዎች ልብ በማለት ስጦታዎቹ አካሉን እንዲያጠናክሩ መርዳት አለብን። 

በተጨማሪ ማንኛውም ቡድን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የዘር፥ የገንዘብ አቋም ወይም ́ የጾታ ልዩነት መሠረት በማድረግ እራሱን ከሌሎች የተሻለ አድርጐ እንዳይቆጥርና ለሌሎች ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አነስተኛ ስፍራ እንዳይሰጥ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ነው። ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የትኞቹም ቢሆኑ ለአንድ ጾታየዕድሜ ክልል ብሔር ወይም የኑሮ ደረጃ ክልል ለመሰጠቱ አመልካች ነገር የለም። እያንዳንዳቸው ቤተ ክርስቲያኖቻችን መንፈስ ቅዱስ ስእዚህ ልዩነቶች መካከል ስጦታዎችን ለዚህ ሁሉ የኅብረተሰብ ክፍል ያለ አድልዎ የመስጠቱን እውነታና እዚህ ስጦታዎችም ለቤተ ክርስቲያን የሚያስገኙትን አንድነት ማንፀባረቅ አለባቸው። 

በ1ኛ ቆሮ. 12፡27-31 ጳውሎስ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ በሙሉ ያተኮረባቸውን ነገሮች ጠቅለል አድርጎ ያቀርባል። የቆርንቶስ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ስትሆን እያንዳንዱ አካል ስጦታው ምንም ያህል ትልቅም ይሁን ትንሽ የዚያ አካል ብልት ነው። ሰዎች የሚቀበሉት መንፈሳዊ ስጦታ ምን መሆን እንዳለበት ራሳቸው መወሰን አይችሉም። ይልቁኑ እዚአብሔር እርሱ እንደ ፍላጐቱ ወይም እንደ ዓላማው መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለቤተ ክርስቲያን አባላት ይሰጣል። 

በክርስቶስ አካል ውስጥ ባሉት የመንፈሳዊ ስጦታዎች ልዩነት ላይ በማተኮር ጳውሉላ እንደገና አንዳንድ የመንፈሳዊ ስጦታዎችን ምሳሌዎችን ይዘረዝራል። በዚህ ዝርዝር ውስጥ ተአምራትን ማድረ፥ ፈውስና በልሳናት መናገር ብቻ በቀድሞው ዝርዝር ውስጥ ካሉት ጋር እንደሚመሳሰሉ መመልከት በጣም አስገራሚ ነገር ነው። እነዚህ ስጦታዎች በአራት ክፍል ይመደባሉ። 

በመጀመሪያ፥ ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያን መሪነት ደረጃ በቅደም ተከተል የሚያስቀምጣቸውን መንፈሳዊ ስጦታ ያላቸውን ሰዎች ያቀርባል (ሐዋርያት፥ ነቢያት፥ አስተማሪዎች። ሐዋርያት ለእያንዳንዱ ጉባኤ የተሰጡ ከመሆን ይልቅ እግዚአብሔር ለድፍን ቤተ ክርስቲያን የሰጣቸው ናቸው። በመጀመሪያ የተጠቀሱት እንደ ጳውሎስ አመለካከት የቤተ ክርስቲያን መሥራች በመሆናቸው ነው። የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን እንድትመሠረትና በዘመኑ በታወቀው ዓለም ሁሉ እንድትስፋፋ እግዚአብሔር የተጠቀመባቸው ሰዎች ናቸው። ነቢያት ቀጥለው ተጠቅሰዋል። ይህ ደግሞ የትንቢትን መልእክት ለማምጣት የሚችሉ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎችን የሚያመላክት ቢሆንም እንኳ እንደ እጋበለ ያሉ የሐዋ. 1፡27-28) በነቢይነት የተጠሩና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ያመጡ ሰዎችን ለማመልከት የተጠቀሰ ሳይሆን አይቀርም። ጳውሎስ ሰምስተኛ ደረጃ ሕዝቡን የእግዚአብሔርን ቃል ለማስተማር የተላየ እገልግሎት የተሰጣቸውን አስተማሪዎች ይጠቅሳል። 

በሁለተኛ ደረጃ፥ ሁለት ተአምራታዊ ስጦታዎችን ይጠቅሳል። ተአምራትን ማድረግና ፈውስ። ጳውሎስ እነዚህን የሚያቀርብበት ቅደም ተከተል በ1ኛ ቆሮ. 12፡8–10 ከተሰጠው በተገላቢጦሽ ነው። እነዚያ በአለፈላጊነታቸው ቀደም ብለው ከተጠቀሱት ሦስት የመሪነት ስጦታዎች ቀጥለው የሚመጡ ለመሆናቸው ምንም ዓይነት ፍንጭ የለም። ይልቁኑ የቅደም ተከተሉ መገልበጥ የሚያሳየው እዚህ ስጦታዎች በቤተ ክርስቲያን ያሉ መሆናቸውንና መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ለቤተ ክርስቲያን ከሚሰጥባቸው የተለያዩ መንገዶች አንዳንዶቹ መሆናቸውን ጳውሎስ እንደሚናገር ብቻ ነው። 

ሦስተኛ ደረጃ፣ ጳውሎስ ሁለት የአገልግሎት ስጦታዎችን ይጠቅሳል። ሌሎችን መርዳትና አስተዳደር። እነዚህ ስጦታዎች በመጽሐፍ ቅዱስ በሌላ ስፍራ ያልተጠቀሱና እኛም መንፈሳዊ ስጦታዎች ከሚባሉት በቀላሉ የማንደራቸው ናቸው። ጳውሎስ ሊያተኩርበት የፈለገው ነገር መንፈሳዊ ለጦታዎች ልዩ ልዩ ቅርጽ እንዳላቸውና አንጸንድ ጊዜ የተላዩ ከመምሰል ይልቅ የተለመዱ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው። ሌሎችን የመርዳት ስጦታ ከመስጠት፥ ለሌላው እንክብካቤ ከማድረግና በርማ 23 ከተጠቀሰው ምሕረትን ከማድረግ ስጦታ ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ግልጽ ነው። በቤተ ክርስቲያንና በማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ ሰዎችን መንፈሳዊና ሥጋዊ ፍላጐት የመርሳት ችሎታ ነው። የአስተዳደር ወይም የአመራር ስጦታ ትኩረቶች ለቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለግለሰቦች ብልህነት የተላበት ምክርና ምሪት ወመስጠት ነው። 

በአራተኛ ደረጃ ፥ ጳውሎስ በቆርንቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ውዝግብ በፈጠረው በልሳናት በመናገር ስጦታ ያጠቃልላል። በላሳናት የመናገር ስጦታ ለሁለተኛ ጊዜ በስጦታዎች ዝርዝር የመጨረሻው ሆኖ ቀርቧል። አንዳንድ ሰዎች ጳውሎስ በልሳናት የመናገር ስጦታን የመጨረሻ ስፍራ መለጠቱ ነው ይላሉ። ጳውሎስ ይህን ስጦታ በመጨረሻ ማቅረቡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያሳስብ ነገር የፈጠረውና ሚዛናዊነት የጐደለው ነገር የተመለከተበት ስጦታ ይህ ስለሆነ ለማስተካከል በመፈለጉ ሳይሆን እንደማይቀር ማሰብ የሚያስኬድ ነው። 

መንፈሳዊ ስጦታዎች የተለያዩ ስለመሆናቸውና ለሁሉም እንደማይሰጡ አጉልቶ ለማሳየት በ1ኛ ቆሮ. 12፡29-30 ላይ ጳውሎስ የተለያዩ ጥያቄዎችን ይጠይቃል። ለእያንዳንዱ ጥያቄ የሚጠበቀው መልስ አይደለም የሚል ነው። ጳውሎላ ሊያስተላልፈው የፈለገው መልእክት ጉዳዩ እንዲህ ከሆነና እዚአብሔር ተመሳሳይ ስጦታዎችን ለሁሉ ሰው የማይሰጥ ከሆነ የቆርንቶስ ክርስቲያኖች በአንድ ስጦታ ላይ ያተኮሩበትና ሰዎች ሁሉ በልሳናት እንዲናገሩ የጠበቁበት ምክንያት ምንድን ነው? ልሳናት የተፈቀች ቢሆኑም ሁሉም ቀን በልሳን መናገር የላባቸውም። ጳውሎስ የሚፈልገው በልሳናት መናገር ከስጦታዎች አንዱ ብቻ መሆኑን አውቀው ለልሳን የሚሰጡትን አትኩሮት ሚዛናዊ እንዲያደርጉት ነው። 

ጥያቄ፡- ይህ የጳውሉላ አመለካከት በልሳናት የመናገር ስጦታን ከሌሎች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ሁሉ ላይተው አትኩርት ለሚያደርጉበት የዘመናችን በርካታ ክርስቲያኖች ማስጠንቀቂያ የሚሆነው በምን ዓይነት መንገድ ነው? 

በ1ኛ ቆሮ. 12፡31 ላይ ለጦታዎችን ሰብርቱ መፈለግ እንደሚያስፈልግ ጥብቅ ምክር ሲሰጥ እንመለከታለን። በዚህ ትርጉም ላይ ብዙ ክርክር አለ። አንዳንድ ሰዎች በስጦታዎች መካከል የደረጃ ልዩነት አላ፥ አንዳንዶች እጅግ አስፈላጊዎች ሊሆኑ ሌሎች ደግሞ አስፈላጊነታቸው አነስተኛ ነው ይላሉ። ለምሳሌ የሐዋርያነት ስጦታ በጣም አስፈላጊ ሲሆን በልሳናት የመናገር ስጦታ •ን ከሁሉ ስጦታ በአነስተኛ ደረጃ የሚፈለግ ነው ይላሉ። ጳውሎስ በ1ኛ 3. 14 ላይ የትንቢት ስጦታ በልሳናት ከመናገር ስጦታ እንደሚበልጥ ተናግሯል። ለዚህ ምክንያቱ ስጦታዎቹ እርስ በርስ መበላለጣቸው ሳይሆን መንፈሳዊ ስጦታዎቹ የሚሰጡት «ለጋራ ጥቅም» ስላሆነና የትንቢት ስጦታ ደሞ ሰው በሚገባው ቋንቋ ስለሚናገር ጥቅሙ ለቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰብ በሙሉና በስብሰባው መካከል ለተገኝ የማያምን ሰው ጭምር በመሆኑ ነው። በልሳናት መናገር ሌሎች የማይረዱት ስለሆነ በአምልኮ ስብሰባ ላይ ለአካሉ ጥቅም አይሰጥም። 

ሌሎች ደግሞ የሚረዱት ጳውሎስ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ዝንባሌ ምን ያህል የተሳሳተ መሆኑን ለማሳየት በምሬት እንደሚናገር ነው። «እናንተ ትልቁ ስጦታ ብላችሁ የምታስቡትን በልሳናት የመናገር ስጦታ ትፈልጋላችሁ። መንፈሳዊ የመሆናችሁ ማረጋገጫ ይህ ይመስላችኋል። እኔ ገን የተሻለ መንገድ አሳያችኋለሁ። እርሱም እናንተ ከሁሉ ይሻላል ብላችሁ ከምታስቡት መንፈሳዊ ስጦታ የላቀ ነው።» ጳውሎስ ከዚህ በኋላ የፍቅርን መንገድ ያሳያቸዋል። 

ጳውሎስ ከዚህ በኋላ በሕዝብ የአምልኮ ለብሰባ ላይ ከሁሉ የላቀ ጠቃሚ የሆኑትን ላጦታዎችን መጥቀሱ ሳይሆን አይቀርም። እንደ ትንቢትና ማስተማር ያሉ ስጦታዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎችን በሙሉ የሚደርሱና ቤተ ክርስቲያንንም በልሳናት ከመናገር በተሻለ ሁኔታ የሚጠቅሙ ናቸው። በሕዝቡ የአምልኮ ሰብሰባ ላይ ሰው ሁሉ ሊረዳቸው በሚችል መልኩ የሚቀርቡ ስጦታዎች ከሁሉ የላቁ ናቸው። ምክንያቱም በልሳናት መናገር ሊያንጹ ከሚችሉት በላይ ክርስቲያኖች ስለሚያንጹአቸው . ነው። ስለዚህ በልሳን የመናገር ስጦታ የበለጠ የሚታይና የሚደነቅ ቢመስልም እንኳ ለሰዎች የሚሰጠው አገልግሎት አነስተኛ በመሆኑ የክርስቶስን አካል ( በሙላት በሚነካ ላጦታ ላይ አትኩረት ማድረግ አለባቸው። 

ጳውሎስ ትንቢት እንደሚበልጥ ማስተማር ከመጀመሩ በፊት መንፈሳዊ ለጦታዎች ሁሉ እገልግሎት ላይ ሲውሉ መሠረት ሊሆናቸው ስለሚገባ ተገቢና ትክክለኛ ዝንባሌ አስፈላጊነት ላይ ያተኩራል። ፍቅር ከማንኛውም ድንቀኛ ስጦታ ይበልጣል። ያላ ፍቅር ማንኛውም መንፈሳዊ ስጦታ ዋጋ ቢስ ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) ዮሐንስና ጸጋዩ እርስ በርስ ከቀመጣላት ይልቅ አንዱ {የሌላውን ስጦታ በማድነቅና በማክበር ሊኖሩ የሚችሉባቸውን የመንፈሳዊ ስጦታዎችን መርሆዎች ዘርዝር። ላ) እነዚህ መርሆዎች ካሪዝማቲክ የሆኑና ያልሆኑ ክርስቲያኖችን የሚረዱት እንዴት ነው?

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.