መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ጴጥሮስ 4፡7-11 )

ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ስንነጋገር ልናስታውሳቸው ከሚገቡን እጅግ ጠቃሚ ነገሮች አንዱ ለግለሰቦች ብቻ የታቀዱ ያለመሆናቸውን ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎች በመንፈስ ቅዱስ የተሰጡት ለዓላማ ነው። ለታላቅ ዓላማ ማላትም የክርስቶስን አካል ለመገንባት የተሰጡን መሣሪያዎች ናቸው። መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለሌሎች አገልግሎት ላይ የሚውሉት እንዴት እንደሆነ ከማሰብ ይልቅ በስጦታነታቸው ላይ ስናተኩር ችግሮች መፈጠር ይጀምራሉ። መንፈሳዊ ትዕቢት ተሽሎክልኮ ይገባል። ቅናቶች ይነሣሉ። መከፋፈል ይመጣል። በአዲስ ኪዳን ስጦታዎች በተጠቀሱባቸው ስፍራዎች – ሁሉ የተገላጺት ሌሎችን በማገልገል መንፈስ ነው። ለእኛ ሊያደርጉልን ስለሚችሉት ነገር በሚናገር መልኩ የተጠቀሱበት ቦታ ፈጽሞ የለም። የአዲስ ኪዳን ደራሲ በሆነው በመንፈስ ቅዱስ በተደጋጋሚ የሚነገረን ለጦታዎቻችንን የምንጠቀምበት ዝንባሌ ስጦታዎቹን ራሳቸውን ከመለማመድ በላቀ ሁኔታ ተፈላጊ ስለመሆኑ ነው። ተራርችን ከስፍራቸው ከሚያንቀሳቅላና ተአምራትን ከሚያደርግ እምነት ይልቅ ፍቅር ይበልጣል። ሰጦታዩን እኔ በምፈልገው መንገድ ለመጠቀም ካለኝ ችሎታ ይልቅ አንድነት ይበልጣል። ላእግዚአብሔር ክብርን ማምጣት የሁሉም ተቀዳሚ ዓላማ ስለሆነ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች በምንነጋገርበት ወቅት ዋናው አትኩሮት የሚሰጥበት ጉዳይ የእዚአብሔር ክብር መሆን አለበት። በእያንዳንዱ ስጦታ ምንነትና በቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደምንጠቀምበት በዝርዝር እንመለክት ልንለያይ ብንችልም ጸሎቴ እነዚህን መመሪያዎች እንዳንዘነጋ ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) መንፈሳዊ ስጦታን በተሳሳተ መንገድ መጠቀም እንዳት እንደሚሠራ ወይም በምን ዝንባሌ እንደሚሠራ) ለእዚአብሐር ክብርን መንፈጉን ያየህበትን ሁኔታ ቀላጽ። ለ) ከላይ የተመለከትናቸው መመሪያዎች በዚህ ሁኔታ ለእግዚአብሔር ክብርን በሚመጣ መንገድ መንፈሳዊ ላጦታዎችን መጠቀሙ እንዴት ሊረዳ ይችል እንደነበር ልጽ። 

ጥያቄ፡ 1ኛ ጴጥ 4፡7-11 አንብብ። ሀ) በመንፈሳዊ ስጦታዎች ላይ ውይይት የተካሄደበትን ክፍል ዋና አሳብ አድርገህ ተናዢ። ላ) የታ መምጣት በቀረበ ቁጥር ባሕርያችን ምን መሆን እንዳለበት የሰላም የተለያዩ ነገሮችን ዘርዝር። ሐ) መንፈሳዊ ስጦታ ያለው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ስጦታው ምን ማድረሳ አለበት? ) ቀደም ሲል በጀመርከው ሠንጠረዥ ላይ የተጠቀሱትን የተለያዩ ስጦታዎች በመዘርዘር ስለ እያንዳንዱ ስጦታ ገለጻ ስጥ። ሠ) ከእያንዳንዱ ስጦታ ጋር አብሮ መሄድ ያለበት አመለካከት ምንድን ነው? ረ) ስጦታችንን በሚገባ መጠቀም የዘለቄታ ዓላማ ምንድን ነው? ሰ) ከዚህ ክፍል ስለ መንፈሳዩ ስጦታዎች እና ላላ አጠቃቀማቸው የተጠቀሱ መመሪያዎችን ዘርዝር። 

የ1ኛ ጴጥ. 4፡7-11 መሠረተ አሳብ (ዳራ) 

ጴጥሮስ በትንሹ እላያ ለተበተኑት ክርስቲያኖች ሲጽፍ እዚኦብሔርን በሚያከብር መንገድ እንዲኖሩ ሊያበረታታቸው ፈለገ፡ ክርስቲያኖች ሰማያምኑ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰደዱ ነበር። ከዚህ ለደታ ለገላዋ ሲሉ እንደ ዓላማውያን ለመኖር እስኪፈተኑ ይደርሱ ነበር። ሆኖም ቀን ጴጥሮስ ክርስቲያኖች የተለዩ መሆናቸውን ያሳለባቸዋል። የእግዚአብሔር ስለሆኑ እግዚአብሔርን በመታተዝ መኖር አለባቸው። የዘመን ፍጻ እንደደረሰና ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ የሚመጣበት ጊዜ በደች እንደሆነ አበክሮ ነገራቸው። ኢየሱስ የሚመላለበትን ጊዜ በትዕሥት ሲጠባበቁ በጥንቃቄ እርሱን በሚያስከብር መንገድ መኖር ነበረባቸው፡ ኢየሱስን ክበር ምን ምንን ይዉምራል? ጴጥሮስ በምናጠናው በዚህ ክፍል እንዳንዶቹን ይገልጻል። 

1ኛ ጴጥሮስ 4፡7-9 

ክርስቲያኖች ብዙ ጊዜ ስደት የሚደርስባቸው አናሳ የኅብረተሰብ ክፍሎች ስለሆኑ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ብዙ ተጽዕኖዎች ይመጣሉ። ከውጭ ላደት ከውስጥ ደግሞ የሐሰት ትምህርቶችና መከፋፈል ይከሰታሉ። ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሁሉ ውስጥ ማለፍ እንዴት ትችላለች? ጴጥሮስ ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ሊኖራቸው ስለሚገባ ሦስት አመለካከቶች ይናገራል። 

1. በመጀመሪያ ንጹሕ አእምሮ ያላቸውና የሚዝ መሆን ይገባቸዋል። ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታ እንዳላወቀ ወይም 1ድ እንደ ሌለው ከመሆን ይልቅ ከርስቲያኖች ልጽ አስተሳሰብ ሊኖራቸው እንደሚገባ ይናገራል። የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ዕቅድና የኢየሱስን መመለስ መርሳት የለባቸውም። የሚያጋጥሙአቸውን የተለያዩ ትምህርቶችና ችግሮች በጥንቃቄ በመመርመር እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እንዴት ማስተናገድ እንዳላባቸው ማሰብ አለባቸው። በመንፈስ ቅዱስና በእግዚአብሔር ቃል ሥልጣን ሥር በመኖር እእምሮአቸውንዝንባሌያቸውንና ተግባራቸውን መቆጣጠር ነበረባቸው። ይህ ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ ይጸልዩ ዘንድ እንዲረዳቸው ነበር። 

2. እርስ በርስ በመዋደድ ላይ ማተኮር ነበረባቸው። አንድ ክርስቲያን ሌላውን ክርስቲያን ሊጐዳ የሚችል ነገር የሚያደርግባቸው ጊዜያት እንደሚኖሩ ጥርስ ያውቅ ነበር። በዚህ ጊዜ የሚሆነው ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ ያለ እባብ መፍረድና ለመበቀል መሞከር ነው። ፍቅር ቀን አንድነትን ይጠብቃል። በመካክላቸው የነበረ ኃጢአት ያመጣውን መቆሳሰል ይሸፍንላቸው ነበር። 

3. አንዱ ለሌላው መልካም አቀባበልን ማድረግ ነበረበት። ይህ ትእዛዝ በዚህ ሰፍራ መቅረብ ያለበት አይመስልም። መልካም አቀባበል ቀን የፍቅር ተቀጥላ ነው። በጳጥርስ ዘመን አንድ ሰው አማኝ በሚሆንበት ጊዜ በአብዛኛው ሁኔታ ከቤቱ ይባረር ነበር። ሌላ ቤት እስኪያገኝና ኑሮውን እስኪያደራጅ ድረስ ሌላውን ጠለላ ማድረጎ ዴታው ነበር። ባሪያ ወይም እገልጋይ የነበረ ከሆነ ደሞ ለሕይወት የሚያስፈልገውን ነገር በሚያገኝበት ሁኔታ ላይ ወድን መንግድ አጻሪ ይሆን ነበር። ይህ ሁኔታ ሴት በነበራቸው ሰዎች ላይ ተደራራቢ ሸከም ይጨምራል። በመንግሥት ዘንድ በጥርጣሬ ይታዩ የነበሩትን ክርስቲያኖች በማስጠጋት ሕይወታቸውና ቤታቸው የባሰ አደጋ ላይ ይወድቅ ነበር። ቤትና ሥራ ላላቸው ክርስቲያኖች የረመዷቸው፥ የሚያለብሏቸውና ሌሎች እንክብካቤዎች የሚያደርጉላቸውን ሰዎች መጨመር በከፍተኛ የማይመች ነገርን ይፈጥርባቸው ነበር። በርካታ ሃብታም የህኑ ክርስቲያኖች ኑርአቶውንና ቤታቸውን ከአደጋ ለመከላከል ሲሉ የተጣሉትንና የተገፉትን ላለማስጠጋትና ላለመቀበል ይፈተኑ ነበር። ጴጥሮስ ቀን የሚያሳስባቸው አንድነቱ ይቀጥል ዘንድ መልካም የእን አቀባበል ልምድ መቀጠል እንደነበረበት ነው። •ልካም የእንግዳ አቀባበል ደግሞ ማጉተምተም ሳይሆን በትክክለኛ ዝንባሌ ማለትም በደስታ መደረግ ነበረበት። 

ጥያቄ፡- ሀ) እነዚህ ሦስት ባሕርያት በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ የሚያስፈልጉት እንዴት ነው? ላ) በቤተ ክርስቲያንህ በእነዚህ ባሕርያት ሕይወቱ የተመሰከረለትና የምታውቀውን አንድ ሰው በምሳሌነት ጥቀለ። ውጤቱ ምንድን ነው? 

1ኛ ጴጥ. 4፡10-11 

ጴጥሮለ በስደት ጊዜ ለአንድነት መሠረት ከሚሆኑት ከእነዚህ ባሕርያት መለስ ይልና ይህን አንድነት ጠብቆ ለማቆየት በመርዳት መንፈሳዊ ስጦታዎች ስላላቸው ስፍራ ያውሳል። የሚከተሉትን እውነተች አስተውል፡- 

1. እያንዳንዱ ሰው መንፈሳዊ ስጦታዎች አላው። መንፈሳዊ ስጦታዎች ላአንዳንዶች ተሰጥተው ላሌሎች የተከለከሉ አይደሉም። 

2. የስጦታው ዓላማ «ሌሎችን ማገልገል» ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚሰጡበት ተቀዳሚ ዓላማ ለራስ ጥቅም አይደለም። በአገልግሎት ላይ መዋል የሚገባቸው ሌላውን ለማገልገል ነው። 

3. እያንዳንዱ ክርስቲያን መንፈሳዊ ስጦታውን የመጠቀም ኃላፊነት አለበት። ሌሎችን ለመገንባት እንዴት እንደሚጠቀም ታማኝ መሆን አለበት። ይህ ማለት ለመጠቀም ቸል ከማለት ወይም በተሳሳተ መንገድ ከመጠቀም መጠበቅ አለበት ማለት ነው። ታማኝ መሆን ማለት መንፈሳዊ ስጦታዎቻችንን ከትክክለኛ ዝንባሌ በመነሣት ለትክክለኛ ዓላማ ልንጠቀምባቸው ይገባል ማለት ነው። 

4. መንፈሳዊ ስጦታዎች በእግዚአብሔር ጸጋ የሚሰጡ ናቸው። ለለ መንፈሳዊ ታላቅነታችን ወይም ስላደረግነው ማንኛውም ነገር የሚሰጥ አይደለም። በምንም ነገር ላይ ካልተመሠረተ ልዩ ችርታ የሚመነጭ ህ ስጦታ ነው። 

5. መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚመጡት በተለያዩ መልኮች ነው። መንፈሳዊ ስጦታዎች ብዙ ዓይነት እንጂ አንድ ዓይነት እይደሉም። በእርግጥ በአዲስ ኪዳን ከተዘረዘሩ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚኖሩን እንዳንዶች ብቻ ሳይሆኑ አይቀሩም። ክርስቲያኖች በክርስቶስ አካል ውስጥ የሚያደርጓቸው በርካታ ሌሎች ነገሮችም እንደ ስጦታዎች ሊመደቡ ይችላሉ። 

ጴጥሮስ ቀጥሎ ለጦታዎች ናቸው ብለን ፈጽሞ የማናስባቸውን ተራና የተላመዱ ሁለት ስጦታዎችን ይጠቅሳል። 

1 መናገር፡- ይህ ስጦታ ከሌሎች ስጦታዎች ጋር ተጣምሮ የሚቀርብ ሳይሆን አይቀርም። የነቢይነት የማስተማር፣ የመምከር፡ በልሳናት የመናገርና በልሳናት የተነገሩትን የመተርጐም ስጦታዎች በሙሉ በመናገር ላይ የተመሠረቱ ናቸው። 

2 ማገልገል፡- ይህ ስጦታ በሮሜ 12፡7 ላይ የተጠቀሰ ሲሆን ‹ዲያቆን› ከሚለው ጋር አንድ ዓይነት ቃልን ይጠቀማል። የሌሎችን ፍላጐት ለማሟላት የማገልገልን ጉዳይ ያመለክታል። ይህ የክርስቶስን አካል ተግባራዊ በሆኑ መንገዶች የማገልገል ስጦታ ነው። 

የጴጥሮስ አትኩሮት አንድ ሰው ለጦታውን መለማመዱ ወይም አላመለማመዱ ላይ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ስጦታውን በሚጠቀምበት ወቅት ባለው ዝንባሌ ላይም ጭምር ነበር። ከላይ በተመለከቱት በሁለቱም ስጦታዎች ጴጥሮስ ክርስቲያኖችን የሚያስታውሰው ስጦታዎቻቸውን ስለ ሚጠቀሙበት መንገድ ነው። 

1. የሚናገር ሰው የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚናገር ይናገር። ይህ ዐረፍተ ነገር ሁለት ጐኖች አሉት። የመጀመሪያው ጐኑ በድፍረት የመናገር ጉዳይን ያመለክታል። ትክክለኛው ነገር ይህ ይመስለኛል እያሉ በጥርጣሬ መንፈስ ከመናገር እርግጠኛ ሆነን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ለማለት መቻል አለብን። ሌላው ጐኑ ግን የተጠያቂነት ጉዳይ ነው። በቤተ ክርስቲያን የምንናገረው ነገር የራሳችን አስተሳሰብ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል ለመሆኑ በእርግጠኛነት እናደርገው ዘንድ የምንናገረው ቃል በእግዚአብሔር ቃል ላይ በትክክል መገኘቱን እርግጠኛ እስክንሆን ድረስ የእግዚአብሔርን ቃል የማጥናት ኃላፊነት አለብን። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን ወክሎ የሚናገር (ሰባኪ ወይም አስተማሪ) የእግዚአብሔርን ቃል ሳያጠናና የሚናገረውንም ቃል በትክክል ሳይተረጉምና ሳይገልጽ ከመቅረት የበለጠ አደገኛ ነገር የለም። 

2. የሚያገለግልም ቢሆን እግዚአብሔር በሚሰጠው ኃይል ያገልግል። አንዳንዶች ለማገልገል ብዙ ኃይል አላቸው። ሌሎች ደግሞ አነስተኛ ኃይል አላቸው። ነገር ግን ውድድር ሊኖር አይገባም፡ ብርታትና ኃይልን የሚሰጥ እግዚአብሔር ስለሆነ የእኛ ኃላፊነት ብርታታችንን ሌሎችን ለማገልገል መጠቀማችን ላይ ነው። ከእኛ የሚያንሱ ወይም የሚበልጡ ከሚመስሉን ጋር ማወዳደር የለብንም። 

ጴጥሮስ የስጦታዎች ተቀዳሚ ዓላማቸው የክርስቶስን አካል ማገልገል እንደሆነ ቢናገርም መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን የሚሰጥበት የላቀ ዓላማ አለ። ስጦታዎቻችን የክርስቶስን አካል ላማሳደግና በትክክለኛ ዝንባሌ ስንጠቀምበት እግዚአብሔር ይመሰገናል። መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ወዳለው ዓላማ እንደገና እንመለሳለን። ልናደርጋቸው የሚገቡ በርካታ ነገሮች አሉ። ነገር ግን ለምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ መሠረታዊ ዓላማችን ለእግዚአብሔር ክብርን ማምጣት መሆን አለበት። እግዚአብሔር የሰጠንን ስጦታዎች እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ፥ በትክክለኛ አመለካከት ስንጠቀምባቸው እግዚአብሔር የሚገባውን ክብርና ምስጋና ያገኛል። 

ጥያቄ፡- ሀ) መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለእግዚአብሔር ክብር በማያመጣ መንገድ ልንጠቀም የምንችልባቸውን መንገዶች በምሳሌነት ጥቀለ። ላ) ከላይ የተሰጠውን ያንኑ ስጦታ ለእግዚአብሔር ክብር በሚያመጣ መንገድ ከመጠቀም እንዴት ይለያል? 

አምስተኛ ቀን፡- የዚህን ሳምንት ትምህርት ከልስና ለሳምንታዊ ስብሰባ ዝግጅት ይረዳህ ዘንድ የውይይት ጥያቄዎችን ተመልከት።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.