በልሳናት ስለመናገር ተጨማሪ ጉዳዮች (ክፍል 2) የተለያዩ ዓይነት ልሳናት አሉን?

በካሪዝማቲክና ካሪዝማቲክ ባልሆኑ ክርስቲያኖች መካክልና በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች በራሳቸውም መካከል እንኳ የተለያዩ ዓይነት ልሳናት የመኖራቸው ወይም ያለመኖራቸው ጉዳይ ሌላው አከራካሪ ነጥብ ነው። 

ጥያቄ፡- በአብዛኛዎቹ በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች የሚነገሩት ልሳናት በሐዋርያት ሥራ 2 ላይ በሐዋርያት ከተነገሩት ልሳናት የተለዩ ናቸውን? እንደዚህ ብለህ የምታስበው ለምንድን ነው? 

ክርስቲያኖች እነዚህን ጥያቄዎች የሚመልሱባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ። 

1. በልሳናት መናገር ሁልጊዜ በሰው ቋንቋ መናገር ነው። 

ይህን አመለካከት የሚያንጸባርቁ በአዲስ ኪዳን በልሳናት የሚናገሩ ሁሉ በሰው ቋንቋ እንደተናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ዎች ግልጽ ያደርጋሉ ይላሉ። ልሳን የሚያሰኘው ለሚናገረው ሰው የማይታወቅ ቋንቋ መሆኑ ነው። ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ ቋንቋውን ለሚላዩ ሰዎች የታወቀ ነበር። ወይም ለሚያዳምጡት ሰዎች የታወቀ ባይሆንም እንኳ ሰብዓዊ ቋንቋነቱ የታወቀ ነበር። 

ይህ ዛሬም ለሚነገሩ አንዳንድ ልሳኖች እንኳ የሚሠራ እውነት ነው። በደቡብ አሜሪካ ወንጌልን ሰምተው ያመኑ እጅግ ኋላ ቀር የሆኑ የአንድ ጐሣ አባላት ነበሩ። ትንሽ ቆይተው በአጐራባች ክልላቸው ወደሚገኙና ታሪካዊ ጠላቶቻቸው ወደሆኑ የአንድ ጐሣ አባላት ወንጌላውያንን ለመላክ ወሰኑ። የዚህ ጐሣ አባላት የሚገኙበት ቦታ የበርካታ ቀናት የእግር ጉዞ የሚጠይቅና የሚናገሩት ቋንቋም እነርሱ ከሚያውቁት ፈጽሞ የተለየ ነበር። 

ወንጌላውያኑ ቋንቋውን የማያውቁ ቢሆኑም እንኳ ወደዚያ ስፍራ በደረሱ ጊዜ ወንጌልን ሊያካፍሏቸው በመቻላቸው ብዙዎች አመኑ። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ወንጌላውያኑ አዲሱ ጐሣ ወደሚገኝበት ስፍራ በደረሱ ጊዜ ከዚህ ቀደም ፈጽመው የማያውቁትን ቋንቋቸውን እንዲናገሩ ችሎታ ተሰጣቸው። ስለ ጌታ እየመሰከሩ ሳሉ ያልተላመደ ነገር መፈጸሙን እንኳ አላወቁም ነበር። ሚሲዮናውያን በአንድ ስብሰባ ላይ በተገኙበት ወቅት በልሳናት የሚናገሩ ሰዎች ይሠሩበት የነበረ እካባቢ ቋንቋን የተናገሩበትና እነርሱም በትክክል ቋንቋውን ሰምተው የተረዱበት ሁኔታም አለ። የሚያሳዝነው ግን አንዳንዴ የሚነገረው ነገር እግዚአብሔርን የማያሰከብር ሆኖ ይገኝ ነበር። በእንደዚህ ዓይነት ጊዜያት የልሳናቱ ባለቤት ሰይጣን እንጂ 

መንፈስ ቅዱስ አልነበረም። 

ይህን አመለካከት በአቋምነት የያዙ እመላካከታቸውን ለመደገፍ የሚከተሉትን ምክንያቶች ይሰጣሉ። 

1. በልሳናት የመናገር ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው በሐዋርያት ሥራ 2 ላይ ነው። በልሳናት የተናገሩት የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት በሰው ቋንቋ መናገራቸው ግልጽ ነው። -ከሌላ የዓለም ክፍል የመጡት አይሁዳውያን በራሳቸው ቋንቋ የተነገረውን መረጻታቸው ይህን ያመለክታል። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍም ሆነ በሌላ የአዲስ ኪዳን ክፍሎች በልሳናት መናገር ከሚታወቅ ቋንቋ ወደ ሌላ ነገር መቀየሩን የሚያመለክት አሳብ አናገኝም። 

2. በልሳናት ስለመናገር ለማመልከት ብዙ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለው የግሪክ ቃል «ግሎሳ» የሚለው ነው። በአዲስ ኪዳን በአጠቃላይ በግሪክ ሥነ-ጽሑፎች በሙሉ ስላ ሰብዓዊ ቋንቋ ለመናገር አገልግሎት ላይ የዋለው ቃል ይህ ነው። 

3. በሐዋ 2፡6፥ 8 ላይ የተፈጸመውን ነገር ለመግለጥ አገልጎሎት ላይ የዋለው የግሪክ ቃል ዳይሬክተስ» የሚል ሲሆን ቃሉ ሁልጊዜ ሰብዓዊ ቋንቋን ለመግለጽ አገልግሎት ላይ የሚውል ነው። 

4. በ1ኛ ቆሮ. 12፡10 ላይ ጳውሎስ ስለተለያዩ ልሳናት ይናገራል። «የተለያዩ ዓይነት» የሚለው የግሪክ ቃል የተለያዩ የቋንቋዎች ቤተሰቦችን ወይም ቡድኖችን የሚያሳይ ነው። ለምሳሌ አማርኛ አንድ ቋንቋ ቢሆንም እንኳ የሽዋ፥ የመንዝ፥ የጐንደርና የወሎ ወዘተ… እማርኛ አለ። ወይም በሊማትክ የቋንቋ መደብ ውስጥ ግዕዝ፥ ትግርኛ አማርኛ፥ ዕብራይስጥና ዐረብኛ አሉ። ጳውሎስ በዚህ ቦታ ይህን ቃል የተጠቀመው የተለያዩ ዓይነት ሰብዓዊ ቋንቋዎችን ለማመልከት ነው። 

5. በ1ኛ ቆሮ 14 ጳውሎስ በልሳናት የመናገርን ዓላማ ለመግለጽ ኢሳ. 28፡11-2ን ይጠቅሳል። ከዚህ ጥቅስ በግልጽ እንደምንረዳው ‹ልሳናት› የተባለው የአሶራውያን ቋንቋ ስለሆነ ቋንቋ መሆኑ ግልጽ ነው። 

6. በ1ኛ ቆሮ. 14 ጳውሎስ በጉባኤ የተነገረ ልሳን መተርጐም እንዳለበት ይናገራል። መተርጐም የመቻሉ ነገር ዝም ብሎ የሚመጣ ድምጽ ሳይሆን የሰው ቋንቋ መሆኑን የሚያመለክት እንደሆነ አንዳንዶች ያስባሉ። 

ስለዚህ ይህ አመለካከት ያላቸው ሰዎች እውነተኛው በልሳናት የመናገር ስጦታ አንድ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልቶ የራሱ ባልሆነ፥ አስቀድሞ ባልተማረውና ባላጠናው የሰው ቋንቋ መናገር ነው ይላሉ። 

2. በልሳናት መናገር የሰው ቋንቋ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ብቻ የሚታወቅ ሰማያዊ ቋንቋም ሊሆን ይችላል። 

ሌሎች ክርስቲያኖች ደግሞ በልሳናት መናገርን ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ቋንቋ የመሆኑን ሁኔታ በግልጽ ስለተላማመዱ በልሳናት መናገር አንዳንድ ጊዜ የተለየ ቋንቋ መሆኑን ያምናሉ። በእግዚአብሔር ወይም በመላእክት አገልግሎት ላይ የሚውል ቋንቋ ነው። 

በአዲስ ኪዳን እነዚህን አሳቦች ምናልባት የሚደግፉ በርካታ ጥቅሶች አሉ። የ1ኛ ቆሮ. 13፡1 ጳውሎስ ስለ ሰውና መላእክት ልሳናት ጠቅሷል። ስለዚህ ጳውሉላ በዚህ ቦታ የሚናገረው ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ሆኖ በተለይ ደግሞ በልሳናት የመናገርን ስጦታ ያለ አግባብ በሥራ ላይ ስለ ማዋል ስለነበር በልሳናት መናገር የሰው ባልሆነ የመላእክት ቋንቋ ሊሆን ይችላል ይላሉ። 

የመጀመሪያውን አመለካከት በአቋምነት የያዙ ግን ሊመልሱ ጳውሎስ ሊናገረው የፈለገውን ነገር በግልጽና ክፍተኛ አትኩሮት ሰጥተ ለመናገር በማጋነን የተጠቀመበት ዘይቤያዊ አነጋገር እንጂ ሌላ አይደለም ይላሉ። ይህ ቀጥሎ በተመላከቱት ጥቅሶች የበለጠ ግልጽ ይሆናል። የካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች እንኳ እንድ ሰው በእምነት ስጦታ እየተዘዋወረ ተራሮችን ሲነቃቅል ለማየት አይጠብቁም። 

ልሳናት ሰማያዊ ቋንቋ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚያምኑት 1ኛ ቆሮ. 14፡2ን ይጠቅሳሉ። በዚያ ስፍራ ጳውሎስ ሰው በልሳናት በሚናገርበት ወቅት የሚናገረው ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው እይደለም ይላል። የሚረዳውም እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለም። ስለዚህ ሰው በልሳናት በሚናገርበት ወቅት መንፈሱ ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገራል። ይህ ማለት በልሳናት መናገር ሰማያዊ ቋንቋ መናገር ማለት ነው ይላሉ። 

በልሳናት መናገር ሰብዓዊ ቋንቋ ነው የሚል አቋም ያላቸው ደግሞ ሲመልሱ ቋንቋውን የሚረዳ ማንም ሰው እስከሌለ ድረስ ይህ ጥቅስ ሰብዓዊ ቋንቋን እንዳያመለክት የሚያግድ ምንም ነገር የለም ይላሉ። 

3. በልሳናት መናገር የግድ የሰውም ሆነ የመለኮት ቋንቋ መሆን እያስፈልገውም። የልብን ስሜት የሚገልጥ መቃተት ወይንም ድምጽ ብቻ ሊሆን ይችላል። 

በሮሜ 8፡26 መንፈስ ቅዱስ በማይነገር መቃተት እንደሚማልድልን ተጽፏል። ይህን አቋም የሚያንጸባርቁ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ እኛን ወክሎ ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል ማለት እንደሆነ እምነታቸው ነው። እርሱ ይህን በሚያደርበት ጊዜ ክርስቲያን በጸሎቱ ለመረዳት የማይቻል ድምጽ ያወጣል። እነዚህ ቋንቋዎች ሳይሆኑ ትርጉም የሌላቸው ድምጾች ናቸው። ትርጉም የለሽ የሆኑት ለእኛ ለሰዎች ነውና እንደ ቋንቋ ልንቆጥራቸው ወይም ልንመድባቸው አንችልም። የመንፈስ ቅዱስን አእምሮ የሚያውቀው እግዚአብሔር ቀን የሚነገረውን ነገር ያውቃል። 

ካሪዝማቲክ ያልሆኑና በርካታ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ይህን አቋም ውድቅ ያደርጋሉ። በመጽሐፍ ቅዱሳችን «ግሎሳ» የሚለው ቃል ትርጉም የማይሰጡ ድምጾችን በሚመስል ሁኔታ ፈጽሞ የላም ይላሉ። ሁልጊዜ በጥቅም ላይ የዋለው ሰብዓዊ ወይም መለኮታዊ ቋንቋን ለመግለጽ ነው። እነዚህ ልሳናት መተርጐም አለባቸው የሚለው እውነታ 1ኛ ቆሮ. 1) የሚተረጐም ቋንቋ መኖር እንዳለበት ያሳረጥልናል። 

ይህን ሦስተኛውን አመለካከት የሚያንጸባርቁ ብዙዎች አዳዲስ ክርስቲያኖች ለብቻ ይወስዱና እንዴት በልሳናት መናገር እንዳለባቸው ያስተምራሉ። «ሃሌሉያ። የመሳሰለ ድምፅን ደጋግመው እንዲናገሩ በማድረግ የሚደጋግሙት ቃሎች እስኪደበላለቁ ድረስ እንዲቀጥሉ ያደርጋሉ። በዚያ መካከል በቅጽበት ትርጉም የማይሰጡ ቃሎች ያሉበት ድምፅ ከአፉ ውስጥ ይወጣል። በዚህ ጊዜ ለሰውዬው በመንፈስ ቅዱስ እንደተጠመቀና በልሳናት በዚህ ጊዜ ለሰውዬው በምንም እየተናገረ እንደሆነ ይነግሩታል። ብዙ ጊዜ ይህ በሚፈጸምበት ወቅት አእምሮ መጋበት ወቅት አእምሮ ሥራውን ያቆማል። አእምሮ እንዳይሠራ መዘውሩ ይቆለፍና ለማቅ (መንፈስ) የሚፈልገውን ሁሉ እንዲያደርግ ነህ ይሆናል። 

ይህ ልምምድ በጰንጠቆለጤዎችና በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ዘንድ በዓለም ዙሪያ ሁሉ የተለመደ ቢሆንም ልምምዱ ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በየትም ስፍራ በልሳን እንዴት እንደሚጸልይ ሰው የተማረበት አንድም ማስረጃ የለም። በልሳናት የመናገር ስጦታ በቅጽበት የሚሰጥ ነው። ይህ ዛሬ ብዙዎች በላሳናት መናገር ነው ብለው የሚጠቅሱት ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ልሳን ነው ብሎ ከመደበው – ልምምድ ጋር አብሮ የሚሄድ ያለመሆኑን የሚያመለክት ነገር ነው። 

መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነው ልሳን ካልሆነ ታዲያ ምንድ ነው? ይህ ለመመላስ አስቸጋሪ የሆነ ጥያቄ ሲሆን የተለያዩ ሰዎች ለጥያቄው የሚሰጧቸው መልሶች ይለያያሉ። 

ሀ) ይህ ድምጽ በሙከራና በሥልጠና የተገኘ ከዚያም የመጣ የእንዴት ቃል ነው ብለው አንዳንዶች ያምናሉ። 

ለ) ሌሎች ደግሞ እውነተኛ ልሳን ነው ይላሉ። 

ሐ) ሌሎች ደግሞ በተላይ ስልሳናት መናገርን አበክረው የሚቃወሙ በልሳናት መናገርን ሰው በአጋንንት ሊያዝ ወይም በአጋንንት ቁጥጥር ሥር ሲሆን የሚናገረው ነው ይላሉ። በልሳናት መናገርን በዚህ መንገድ የተማሩ ብዙ ሰዎች እራሳቸውን ለሰይጣን ከፍተው ለሚሰጡ እርሱም ባገኘው ቀዳዳ ወደ ሕይወታቸው ገብቶ ስልሳናት እንዲናገሩ ለማድረግ እንደሚችል አንዳንድ ምልክቶች አሉ። በልሳናት የሚናገሩ ሰዎች ላይ ጥናት ያደረጉ አንድ ምሑር ሲናገሩ ግለሰቡ በልሳናት እንዲናገር የሚያስችለውን ኃይል የሰጠውን መንፈስ በማነጋግርበት ጊዜ መንፈሱ ብዙ ጊዜ ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ለመናገር እንደማይፈቅድ ተገንዝቤያለሁ ብለዋል። ይህ አጋንንት በጉዳዩ እንዳሉበት የሚያመለክት ነው። ምናልባት እኒህ ክርስቲያን የሚሉት የተጋነነ ቢሆንና በልሳናት የሚናገሩ አብዛኛዎቹ ሰዎች የሚናገሩት እውነተኛ ልሳን ቢሆንም እንኳ ልንጠነቀቅና ልናስተውል ይገባል። 

ክርስቲያኖች፥ ብዙ ጊዜ የምናስበው ሰዎች በልሳናት እንዲናገሩ የሚያደርጋቸው መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ነው። በልሳናት መናገር ሰው መንፈሳዊ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት አድርገው የሚቆጥሩትም በዚህ ምክንያት ነው። ሆኖም ግን ሰይጣን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚሠራውን ተአምራት በመሥራት ሰዎችን ጎራ ማጋባት ይወዳል። ሰዎችን ይፈውሳል። ሰዎች የወደፊቱን ጉዳይ እንዲናገሩ ያደርጋል። ሰዎች በልሳናት እንዲናገሩ ይረዳቸዋል። በታሪክ ሁሉ ውስጥ በልሳናት መናገር ሐሰተኛ አምልኮ የሚያካሂዱ መሪዎች ሕይወት አካል ነበር። ለሮም ቤተ መቅደስ የነበሩ ካህናት ብዙ ጊዜ በልሳናት ይናገሩ ነበር። በመካከለኛው ዘመን የነበሩ ጠንቋዮች በልሳናት በመናገራቸው የታወቁ ነበሩ። «ሞርሞን» በመባል የሚታወቅ ታላቅ የሐሰት ትምህርት ጀማሪ የሆነው ጆሴፍ ስሚዝ በልሳናት ይናገር ነበር ተከታዮቹም በልሳናት መናገርን እንዲለማመዱ ያስረታታ ነበር። በአጋንንት የተያዙ ሰዎች በልሳናት መናገራቸው የሚታወቅ ነገር ነው። እንዳንድ የሙስሊም ሃይማኖት መሪዎች እንኳ ስልሳናት ተናግረዋል። ስለዚህ በልሳናት መናገር እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሥራ ላይ ለመሆኑ ማረጋገጥ አይደለም። ከእግዚአብሔር ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ከሰይጣንም ሊሆን ይችላል። 

በድንገት በልሳናት መናገር እስክንችል ድረስ ድምጾችን በመደጋገም በልሳናት መናገርን መማር ስሕተት ነውን? የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ምልክት ነው ወይም በልሳናት የመናገር መንፈሳዊ ስጦታ ነው ብላን እስካላሰብን ድረስ ስሕተት ላይሆን ይችላል። እግዚአብሔርን በዓል አምልኮ ጊዜ ለማምለክ እስከተጠቀምክበት፤ በሕይወትህ የእግዚአብሔርን ህልውና በሆነ መንገድ እንድትረዳ እስካደረገህ፥ ደግሞም በሙላት ታመልከው ዘንድ ለልብህ ነፃነት እስከሰጠህ ድረስ አንዳችም ስሕተት በውስጡ ላይኖር ይችላል። ይህን የግል የአምልኮ ልምምድህን በሌላው ላይ በአስገዳጅነት እንዳትቀንና የማይጠቀሙባቸውን ሰዎች ዝቅ አድርገህ እንዳትመለከት ግን መጠንቀቅ አለብህ። ሌሎች ሰዎች አእምሮአቸውን እየተጠቀሙ በታወቀ ቋንቋ እግዚአብሔርን ማምለክ ይመርጡ ይሆናል። 

ጥያቄ፡- በልሳናት ስለመናገር ከላይ ከተመለከትናቸው ሦስት አመለካከቶች አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች የሚያምኑት የትኛውን ነው? የማታውቅ ከሆነ በተለያዩ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የእምነት ክፍሎች እንደ ሙሉ ወንጌልና መሠረተ ክርስቶስ ውስጥ ያሉ አማኞችን ስለዚህ ጉዳይ ያላቸውን እምነት ጠይቅ። 

በልሳናት ስለመናገር የተሰጡ ትምህርቶች ማጠቃለያ 

በልሳናት ስለመናገር የተመልከትናቸው ትምህርቶች የተለያዩ መልኮች አሉአቸው። ከመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ሙላት ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ ተመልክተናል። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ በልሳናት መናገር አገልግሎት ላይ ስለዋለበት ሁኔታ ተመልከተናል። በመንፈሳዊ ስጦታነት ይዘቱም ተመልክተነዋል። በልሳናት የመናገር ጉዳይ በክርስቲያኖች ሕይወት ስላለው ስፍራ በሊቃውንት መካከል የሚደረገው ክርክር የሚቀጥል መሆኑ አያጠራጥርም። በተለያዩ መንገዶች በልሳናት ስለመናገር ያጠናነውን ጥናት ለማጠቃለል የሚከተሉትን መርሆዎች በዝርዝር አቀርባለሁ። 

1. በልሳናት ስለ መናገር ጉዳይ በየትኛውም አቅጣጫ የከረረ አቋም እንዳይኖርህ ተጠንቀቅ። በልሳናት የመናገር ስጦታ ለ1ኛው ክፍለ ዘመን ክርስቲያኖች ብቻ የተሰጠ ስለነበረ በዚህ ዘመን ያሉት በሙሉ ከሰይጣን ናቸው የሚል ቀኖናዊ አሳብ አይኑርህ። ከ1ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ እግዚአብሔር ይህን ስጦታ ከቤተ ክርስቲያን ስለመውሰዱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኘው ምንጭ (መረጃ ) የላም። መጽሐፍ ቅዱስ ይህ ስጦታ ማክተሙን ያስተምራል ብሎ ለማለት የሚቻለው ስለዚህ ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት በመመርመር ነው። 

በ1ኛ ቆሮ. 14፡39 ላይ ሰዎችን በልሳናት ከመናገር መከልከል እንደሌለብን ተጽፎአል። በልሳናት የመናገር ልምምድን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተዘረዘሩ መመሪያዎች አኳያ የሚለማመዱ ወይም በዚህ ዘመን እንደሚሠራ የሚያምኑ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ምሁር ክርስቲያኖች ዛሬም በመኖራቸው ምንም ከሰይጣን ነው ለማለት አያስደፍርም። 

ክርስቲያኖች ሁሉ በልሳን መናገር አለባቸው፤ በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቅ ብቸኛ ማስረጃ በልሳናት መናገር ነው ከሚል በሌላው ጽንፍ ካላ የከረረ አቋም ቀን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ዎች የሚያመዝኑት መንፈስ ቅዱስ ለክርስቲያኖች ሁሉ የሚሰጥ ስለ መሆኑና በልሳናት የመናገር ችሎታን የሚሰጠው ለሁሉም ሳይሆን ለአንዳንዶች ብቻ መሆኑን፥ በአሁኑም ዘመን በልሳናት የማይናገሩ እግዚአብሔርን የሚፈሩና መንፈሳዊ ብስለታቸው በሕይወታቸው በግልጽ የሚታይ ምሁራን ክርስቲያኖች አሉ። ስለዚህ እነዚህን ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ የላቸውም ወይም በመንፈስ ቅዱስ እልተጠመቁም ማለት ፈጽሞ የማይቻል ነው። 

2. በአዲስ ኪዳን ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስን እንዴት እንደሚያገኝ መማር እንዳለበት ወይም ያገኘው ዘንድ ጥረት ማድረግ እንዳለበት የተሰጠ ማስረጃ ፈጽሞ የለም። በልሳናት መናገርን በመማር መንፈስ ቅዱስን እንደምናገኝ የሚያመለክት ማስረጃ በአዲስ ኪዳን ፈጽሞ የለም። በልሳናት እንዴት መናገር እንደሚቻል ያስተማረ ሰው ስለመኖሩም እንዳችም መረጃ አናገኝም። 

3 በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በልሳናት የመናገር ተቀዳሚ ዓላማ ሆኖ የምናገኘው ይሁዲነትን ከመከተል ይልቅ በኢየሱስ በማመን ወደ እግዚአብሔር የሚመጡት የእግዚአብሔር ሕዝብ ስለመሆናቸውና የአዲስ ኪዳን ተስፋዎች ተጠቃሚ በመሆን ሐሴት እንደሚያደርጉ ማሳየት እንደነበር . ነው። በተጨማሪ ለቤተ ክርስቲያን መልእክት ምላሽ በማይሰጡት ላይ ለመፍረድና በሚተረጐምበት ጊዜ ደግሞ ከእግዚአብሔር መገለጥን ለመቀበል የሚያገለግል መንገድ ነበር። ዛሬ ብዙ ክርስቲያኖች በልሳናት እንዲናገሩ የሚፈልጉበት ተቀዳሚ ምክንያት ይህ ነውን?» ብለን እራሳችንን መጠየቅ ያስፈልገናል። 

4. በልሳናት የመናገር ችሎታ መልካም ስጦታ ስለሆነ ክርስቲያኖች ሁሉ ይህ ስጦታ እንዲኖራቸው ጳውሎስ ይመኝ ነበር። ሆኖም ግን በልሳናት የመናገር ስጦታ ለሁሉም እንደማይሰጥ ይናገራል። ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ለሚፈልገው እንደ ፈቃዱ እንደሚያከፋፍል ያውቅ ነበር፥ 

5. መንፈሳዊ ስጦታዎች በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት መላውን የክርስቶስን አካል ለመገንባት የሚሰጡ ናቸው። ማናቸውንም ለጦታዎች ለግል ጥቅም ማግኛ በስግብግብነት የመፈለግ ዓላማ ከመንፈሳዊ ስጦታዎች ትክክለኛ ዓላማ የራቀ ነው። ስለዚህ ማተኮርና መፈለግ ያለብን ቤተ ክርስቲያን ከሁሉ በላቀ መንገድ የምትጠቀምባቸውን ስጦታዎችን ነው። በልሳን መናገርን ከመፈለጋችን በፊት እራሳችንን «ይህን አነስተኛ ስጦታ ለምንድን ነው አጥብቄ የምፈልገው? መላውን ቤተ ክርስቲያንን የሚጠቅሙ ሌሎች የተሻሉ ስጦታዎችን ለምን የበለጠ አልፈልግም?» ብለን መጠየቅ አለብን። በልሳናት የመናገር ስጦታ ከሌሎች መንፈሳዊ ስጦታዎች ጋር እኩል ከሆነ «ሌሎች ስጦታዎችን ትተን በልሳናት መናገርን ብቻ ለምን እንፈልጋለን?» ብለን እራሳችንን መጠየቅ አለብን። የምሕረት፥ የእርዳታና የመስጠት ስጦታን ለምን እንፈልግም? በልሳናት ለመናገር የተሳሳተ ምክንያት እንዳላን ይህ ያመላክታል? እነዚህን ሌሎች ስጦታዎች በእኩል ፍላጐትና ብርታት የምንፈልጋቸው ለመሆናችን ራሳችንን መጠየቅ ያስፈልጋል። 

6. መንፈሳዊ ስጦታዎች የተሰጡበት ተቀዳሚ ዓላማ ለግል ጥቅምና ለግል አምልኮ አይደለም። በጉባኤ በልሳናት መናገር እስከተተረጐመና በቤተ ክርስቲያን ያሉትን የሚያንጽ እስከሆነ ድረስ የተፈቀደ ነው። የማይተረጐሙ ልሳናት ቀን በቤተ ክርስቲያን ያሉ ሰዎችን ስለማያንጹ የተፈቀዱ አይደሉም። በግል የአምልኮ ጊዜ በልሳናት መናገር ግን ግለሰቡን ሊያንጸው ይችላል። ጳውሎስ በልሳናት መናገርን በዚህ መንገድ ሳይጠቀም እንዳልቀረ የሚያመለክቱ ነገሮች አሉ። ይህ ክርስቲያኖችን ሁሉ ለማነጽ የሆነው የመንፈሳዊ ስጦታዎችን ተቀዳሚ ዓላማ የማሟላት ነገር ሳይሆን ይበልጥ የግል ምርጥ ወይም ዝንባሌ ጉዳይ ነው። 

ጳውሎስ በግል የጸሎት ጊዜ በልሳናት የመጠቀምን ጉዳይ የጠቀሰው እግረ-መንገዱን ብቻ ነው። በልሳናት መናገሩን የጠቀሰ ቢሆንም እንኳ ነገሩን አጠንክሮ አላቀረበውም። ጉዳዩን አጠንክሮ ያላቀረበበት ምክንያት ትኩረት የነበረው በልሳናት የመናገር ስጦታን በኅብረት አምልኮ ስለመጠቀም በመሆኑ ነው። በአዲስ ኪዳን በልሳናት መናገርን በግል ስለመጠቀም የተነገረው በጥቂት ቦታ ነው። ይህም በአማኞች የመንፈሳዊ ብስለት ሂደት ውስጥ ያለው ሚና እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ነው። 

7. እያንዳንዱ ክርስቲያን አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ መንፈሳዊ ስጦታዎች አሉት። መንፈሳዊ ስጦታዎች በሙሉ የመንፈስ ቅዱስ ህልውና መገለጫዎች ወይም ማረጋገጫዎች ናቸው። መንፈሳዊ ስጦታዎች በሙሉ ለቤተ ክርስቲያን አስፈላጊዎች ናቸው። ስለዚህ ሌሎችን ትቶ በአንድ ስጦታ ላይ ማተኮር ስሕተት ነው። በልሳናት መናገር ከሌሎች ለጦታዎች የላቀ አይደለም። ለመንፈስ ቅዱስ ህልውና ከሌሎች ስጦታዎች ይበልጥ ተፈላጊ ወይም የተሻላ ማስረጃ ም አይደለም። በልሳናት መናገር ከሁሉ የላቀ ስጦታ ተደርጐ የታየበት ጊዜ ፈጽሞ የለም። ለመንፈሳዊነት ልዩ መለያ ተደርጐ ፍጹም ተሰጥቶ አይውቅም። 

8. ልሳናትንና ሌሎች መንፈሳዊ ስጦታዎችን የምንጠቀምበት ዝንባሌ ስጦታዎቹን የመለማመድ ያህል እንዲያውም ይበልጥ ተፈላጊ ነው። በልሳናት መናገር መከፋፈልን በሚያመጣ ወይም ስሜቶችን በሚጐዳ ወይም መንፈሳዊ እብሪትን በሚያንፀባርቅ መንገድ ከተደረገ ከፍቅር አመለካከት በተቃራኒ የሚሠራ ስለሆነ ስሕተት ነው። 

9. አንድ ሰው በልሳናት በሚናገርበት ጊዜ ንግግሩ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ አይደለም። በልሳናት የሚናገር ሁሉ በማንኛውም ጊዜ ንግግሩን ስለሚቆጣጠር ተርጓሚ ከሌላም ማቆም ይችል ነበር። 

10. በልሳናት የመናገር ስጦታ አድርጐ በማሳየት ወይም መመሪያ በመስጠት ስለመገኘቱ ምንም ማስረጃ የለንም። በዚህ መንገድ ስለመገኘቱ የተነገረለት አንድም መንፈሳዊ ስጦታ የለም። ይልቁኑ መንፈስ ቅዱስ በሉዓላዊነቱ ስጦታዎችን ይሰጣል። መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለማሳደግ መፈለግ እንችላለን ነገር ግን እንዴት እንደምንጠቀምባቸው በመማር አናገኛቸውም። 

11. በቤተ ክርስቲያን የኅብረት አምልኮ፥ ወይም በቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወይም በትናንሽ ስብሰባዎች በልሳናት ለመናገር ከ1ኛ ቆሮ. 14፡7-28 ያሉት ደንቦች መከበር አለባቸው። ተናጋሪዎች ቢበዛ ሦስት 

· ሆነው በየተራ መናገር አለባቸው። ልሳኖቹም ደግሞ ሁልጊዜ መተርጐም አለባቸው። መንፈስ ቅዱስ በጳውሎስ በኩል ለቤተ ክርስቲያን የሰጣቸውን እነዚህን ደንቦች ለመከተል ያለመፍቀድ ልሳናቱ ከመንፈስ ቅዱስ ላለመሆናቸው ምልክት ነው። 

12. በልሳናት የመናገር ስጦታ ካለህና በሕዝብ መካከል ልትጠቀምበት የምትፈልግ ከሆነ ውጤቱ ክርስቲያኖችን ሁሉ የሚያንጽ ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን። ልሳናትን በግል እምልኮህ ጊዜ እንዳትጠቀም አዲስ ኪዳን የሚከለክለው አንዳችም ነገር የለም። ነገር ግን በግል በልሳናት የመጸለይን አስፈላጊነት አትኩሮት ከመስጠትህ በፊት በተለይ የሰውን መንፈሳዊነት ከሚያሳዩ ሌሎች የአዲስ ኪዳን ትምህርቶች ሲወዳደር በብሉይ ኪዳን ያለውን አነስተኛ ሚና (ለዚያውም አላ ከተባለ) ማን አለብህ (ገላ. 5፡22-23)። ይህን ስጦታ ይፈልጉ ዘንድ ሰዎችን ከማበረታታትህ በፊት ሌሎች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ይፈልጉ ዘንድ ማበረታታህንም አረጋግጥ። 

ጥያቄ፡- ሀ) በኛ ቀን ትምህርት የነበረውን ሁኔታ አልሰ። በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወቅት በልሳን የሚጸልዩትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አኳያ ለመምራት እዚህን መርሆዎች ሙሉ ለሙሉ እንዴት ትጠቀምባቸዋለህ? ለ) በዚህ ዘoመን ከእነዚህ መርሆዎች አብዛኛዎቹን የሚከተሉ ወይም የሚያምኑ ሰዎች የሉም፡ ይህ ለምንድን ነው? ሐ) ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ የማይደግፋቸውን አመለካከቶች መለማመዳቸውና አትኩሮት ማድረጋቸው ትክክል ይመስልሃል? መልስህን አብራራ።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.