በመንፈስ ቅዱስ መሞላት

«ጌታ ሆይ፥ ሕይወቴ እጅግ ደርቋል። ከአንተ እጅግ እንደራቅሁ ይሰማኛል። እባክህን ድንጋይ ልቤን ለውጥ። የአንተ ህልውና እንዲሰማኝ እድርገኝ። ድምፅህን እንድሰማ እርዳኝ» እያልክ በመጸለይ ላይ ሳለህ ልብህ በድንገት እንግዳ በሆነ ሁኔታ ይሟሟቃል። እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ባለህበት ክፍል እንዳለ ይሰማሃል። ልብህን ደስታ ይሞላውና እግዚአብሔርን ማመስገን ትጀምራለህ። 

«ጌታ ሆይ፥ በሕይወቴ ኃጢአት አለ። የምችለውን ሁሉ ላደርግ ብጥር እንኳ ላሸንፈው አልቻልኩም። እባክህን ይህን ኃጢአት እንዳሽንፍ ኃይልህን ስጠኝ» ብለህ ከጸላይክ ጥቂት ጊዜያት ካለፉ በኋላ የሚያስቸግርህ ኃጢአት ክአንተ መወገዱን ታያለህ። 

«ጌታ ሆይ፥ በቤተ ክርስቲያን እንድሰብክ ተጠይቄአለሁ። ለማጥናትና ራሴን ለማሰናዳት ሞክሬአለሁ ነገር ግን እንደተዘጋጀሁ አይሰማኝም። ምን ብዩ እንደምናገር እንኳ እንደማላውቅ ነው የሚሰማኝ። ጌታ ሆይ፥ ቃላትን ለመደጋገም አልፈልግም። ነገር ግን የአንተን መልእክት ለማስተላለፍ እሻለሁ። ጌታ ሆይ፥ አሁን ለመናገር እቆማለሁ። እባክህን በእኔ ውስጥ ተናገር» ብለህ በመጸለይ በሕዝቡ ፊት ትቆማለህ። በድንገት ፍርሃትህ ይሸሻል። አስተሳሰብህ ግልጽ ይሆናል። ከዚህ ቀደም አስበሃቸው የማታውቃቸው ቃሎች፥ አሳቦችና መግለጫዎች በአእምሮህ ውስጥ ይፈስሳሉ። ቃሎችህ ልባቸውን እየሰነጠቁ ሲገቡ ከአድማጮችህ ፊት ልታነብብ ትችላለህ። ሰዎች ንስሐ ገቡ። ሌሎች ጌታን ለመከተል ወሰኑ። 

ጥያቄ፡- ሀ) እላይ የተጠቀሱትን የሚመስሉ ነገሮች የተለማመድከው (እንዴት ነው? ለ) የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ዘፀአ 33፡18-23፤ መዝ| (42)፡1-2፤ ኤር. 29፡12-13፤ ፊልጵ. 3፡1-11። የእነዚህ ሰዎች ጸሎቶች ወይም ፍላጐቶች ምን ነበሩ? ሐ) እዚህ ጸሎቶች ልንጸልያቸው ከምንችላቸው ታላላቅ ጸሎቶች አንዱ ዓይነት የሚሆኑት ለምንድን ነው? 

ክርስቲያኖች ዛሬ የሚያስፈልጋቸው ብቸኛ ታላቅ ነገር በመንፈስ ቅዱስ መሞላትና በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር የሆነ ሕይወትን መኖር ነው። ሕይወታቸው ኃይል አልባ የሆኑ በርካታ ክርስቲያኖች አሉ። በኃጢአት ተሸንፈው ይኖራሉ። ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት ሰልምድ የሚፈጸም ሥርዓት ብቻ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል መስማት አቁመዋል። ሰልባቸው ህልውናው አይሰማቸውም። በየሳምንቱ የሚሰብኩት ስብከታቸው ግን ኃይል አልባ ስለሆነ የሰዎችን ሕይወት ፈጽሞ መለወጥ የማይችል የሆነባቸው ብዙ መሪዎች አሉ። እነርሱም ወጥ የሆነ፥ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ የሚታይበትና (ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ በጐነት፥ እምነት፥ የዋህነት፥ ቸርነት ትዕግሥት፥ ራስን መግዛት) ሰዎች በሕይወታቸው ያለውን ለውጥ የሚገነዘቡበት ሕይወት እንዲኖራቸው በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ያስፈልጋቸዋል። 

ላለፉት ሁለት ሳምንታት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ስናጠና ቆይተናል። እነዚህ መንፈሳዊ ስጦታዎች አስፈላጊ ቢሆኑም እንኳ በመጨረሻ በየዕለቱ እናንተም ሆናችሁ እኔ እንዴት እንደምንኖር በሕይወታችን ተጽዕኖ የሚያደርግ ከሁሉ የላቀው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ «በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ነው።» እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እንድንኖርና እንድናገለግል የሚያደርገን የመንፈስ ቅዱስ እገልግሎት ይህ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር በምንመላለስበት ወቅት በየዕለቱ በመንፈሳዊ ብስለት እያደግንና ኢየሱስን እየመሰልን እንሄዳለን። በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ሆነን እንደ ኢየሱስ እናስባለን፥ እንደ ኢየሱስ እንኖራለን፥ ለእርሱ ክብር የእርሱን ተግባራት እንፈጽማለን። 

ጥያቄ፡- በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ ክርስቲያኖች በቤተ ክርስቲያኖቻችን ውስጥ መኖራቸው ጠቃሚ የሚሆነው ለምንድን ነው? 

በክርስትና ታሪክ ሁሉ ውስጥ ከማንኛውም ተራ ክርስቲያኖች የተለዩ ክርስቲያኖች ነበሩ። ለእግዚአብሔር ያላቸው ቅናት እጅግ የሚቀጣጠል ከመሆኑ የተነሣ ሕይወታቸው እግዚአብሔርን የበለጠ ለማወቅ የሚያጓጓ ነው። ወይም በእግዚአብሔር ላይ የነበራቸው እምነት ታላቅ ስለሆነ ለእግዚአብሔር አስደናቂ ነገሮችን ለማድረግ የሚችሉ ነበሩ። አንዳንዶቹ እጅግ ልዩ ከመሆናቸው የተነሣ እነርሱ ባሉበት መሆን በእግዚአብሔር ፊት እንደ መገኘት ነበር። እነዚህን ክርስቲያኖች ልዩ ያደረጋቸው ምንድን ነው? ይህ የሕይወት ደረጃ ለተመረጡ ጥቂቶች ብቻ የተሰጠ ነውን? እንደ እነርሱ ለመሆን ምን ማድረግ አለብን? 

የእነዚህን ታላላቅ ክርስቲያኖች ሕይወት ስናጠና ሁላቸውም በሕይወታቸው ሰቆቃ የነበረባቸው ወቅት ነበር። ይህ ጊዜ እግዚአብሔርን በዚያ ሁኔታ ውስጥ እጅግ የፈለጉበትና እግዚአብሔርም በእስደናቂ መንገድ የመለሰላቸው ጊዜ ነበር። እንደዚህ ዓይነቱ ልምምድ ስእነዚህ ትላልቅ ቅዱሳን ሕይወት በተደጋጋሚ በመከሰቱ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የሚታየው እድገት ከአንድ ኮረብታ ወደ ሌላ ከፍተኛ ኮረብታ የመዝለል ያህል ነበር። እነዚህ የቀድሞ ትላልቅ ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ለመግለጽ በተለያዩ ቃላት ተጠቅመዋል። አንዳንዶች በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ብለውታል። ሌሎች በመንፈስ ቅዱስ መቀባት ብለውታል። አሁንም ሌሎች የጠለቀ ሕይወት ወይም ደግሞ በረከት ብለውታል። ወይም በመንፈስ ቅዱስ መሞላት የሚሉም አሉ። ስለ ልምምዶች ምንነት የተሳሳተ መረዳትን ሊሰጡ የሚችሉ ቢሆኑም፥ ልምምዳቸውን ለመግለጽ የተጠቀሙባቸው ቃላት በራሳቸው ጠቃሚ አይደሉም። ዋናው አስፈላጊ ነገር ልምምዳቸው ነው። የእግዚአብሔር ፍላጐት ሁላችንም ይህ ልዩ የሆነ ጥልቅ ግንኙነት ከእርሱ ጋር እንዲኖረን ነው። አጥብቀን ከልባችን ብንፈልግ እንደምናገኘው ተስፋ ሰጥቶናል (ኤር 29፡12-13)። በሕይወታችን የእግዚአብሔርን ክብር ከሁሉ በላቀ መንገድ ለማየት ከፈለግን (ዘፀአ 33፡18-23) እግዚአብሔር እራሱን ይገልጥልናል። እግዚአብሔር በጥልቀት እንድንላማመድ ያላስቻለን ነገር እግዚአብሔር ሌሎች ምርጦች ስላሉትና እኛን በተመሳሳይ መንገድ ሊባርከን ስለማይፈልግ ሳይሆን ነገር ግን የእነርሱን ያህል ጥረት ስለማናደርግ ነው። እግዚአብሔር ማንነቱን በጥልቀት የሚገልጸው በሙሉ ልባቸው ለሚፈልጉት ነው። ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያድግ ኅብረት እንዲለማመዱ በመጀመሪያ ፍላጐት እንዲኖረው ከማድረግ ጀምሮ በመርዳት የሚሠራ መንፈስ ቅዱስ ነው።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.