በቤተ ክርስቱያን ውስጥ ስለሚመጣው ትንቢት ተጨማሪ አሳቦች

ዮሐንስ ጐላ ያላ ድምፅ ማውጣት የሚችል ወጣት ሰው ነበር። አንድ ቀን የጸሎት ስብሰባ ተካፈለ። መሪው ሰዎችን ለበለጠ ጸሎት ያነሣሣል ብሎ በማሰብ የመሰብሰቢያ ክፍሉን መብራት አጠፋው። ወዲያውኑ ሰዎች በከፍተኛ ድምፅ መጸለይ ጀመሩ። አንዳንዶቹ በልሳናት ይጸልዩ ነበር። በድንገት በቡድኑ ውስጥ ከነበሩት ሰዎች አንዱ ወደ ዮሐንስ «መጣና እግዚአብሔር ለአንቺ የሚሆን መልእክት ሰጥቶኛል» አለው። «ማሕፀንሽ አሁን ተስፍቶአልና ልጅ ይኖርሻል» አለው። ዮሐንስ ቀን መለሰና እኔ እኮ ወንድ ነኝ አለው። ሰውዬውም መልሶ «እግዚአብሔር በውስጥህ ያለውን ከፉ መንፈስ ይገስጸው» አለው። 

ትንቢት መናገርና የጌታን ቃል እንደተናገሩ መቁጠር። ከላይ የተመለከትነው ታሪክ መንፈሳዊ ስጦታ ያለአግባብ ሥራ ላይ የዋለበትን አንድ ሁኔታ ብቻ የሚያሳየን ነው። ያ ቃል የማን ነበር! የእግዚአብሔር ቃል እንዳልነበረ ግልጽ ነው። ስለዚህ የሌላ አካል ማለትም የሰው ወይም የክፉ መንፈስ ነው። ይህ የጌታ ቃል አለኝ በማለት የሚናገርን ሰው ሳንመዝነው እንዲናገር የመፍቀድን አደገኛነት የሚያሳየንና የሚያስጠነቅቀን ይሆናል። በዚህ ዘመን በአብያተ ክርስቲያናት አካባቢ የሐሰት ትምህርቶችና ልምምዶች በታላቅ ፍጥነት እያደጉ የመጡበት አንድ ምክንያት የሰማናቸውን መልእክቶች ለመመዘን ባለመቻላችን ነው። ቢሆንም እግዚአብሔር አሁንም መናገሩን አይተውም። ከተዘረዘሩት መንፈሳዊ ስጦታዎች አንዱ የትንቢት ስጦታ ነው። ዛሬ ይህን ስጦታ በመመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ስጦታ የሚያስተምረውን እንመለከታለን። 

ጥያቄ፡- ሀ) አንድ ሰው ከእግዚአብሔር የተሰጠ መልእክት አለኝ ያለበትን ሁኔታ ግለጽ። ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠ ቃል ይመስልሃልን? ከእግዚአብሔር መሆኑንና ያለመሆኑን እንዴት ታውቃለህ? ለ) አንድ ሌላ ሰው ደግሞ ከእግዚአብሔር መልእክት አለኝ ብሉ የመጣበትንና አንተ ደግሞ መልእክቱ ከእግዚአብሔር መሆኑን የተጠራጠርክበትን ሌላ ሁኔታ ግላጽ፡ ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ ለምን አሰብክ? 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። 1ኛ ተሰ. 5፡20፤ 1ኛ ቆሮ. 145 12፡8-14፤ ሮማ 12፡6፤ ኤፌ. 2፡20፤ 4፡11፣ 1ኛ ጢሞ. 18፤ 4፡14። በእነዚህ ጥቅሶች ስለ ትንቢት የተነገሩ የተለያዩ እውነቶችን ዘርዝር። 

በጳውሎስ መልእክቶች ከተዘረዘሩት መንፈሳዊ ስጦታዎች በሙሉ በተደጋጋሚ የተጠቀሰው የትንቢት ስጦታ ነው። ነቢያት በቀደምቷ ቤተ ክርስቲያን እጅግ አስፈላጊዎች ስላነበሩ እንደ ዋና የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሆነው ተመዝግበዋል። ቀደምታ ቤተ ክርስቲያን የተገነባችበት መሠረት አካል ነበሩ (ኤፌ. 2፡20)። ስለዚህ ነቢያትም ሆኑ የትንቢት ስጦቃዎች በቀደምቷ ቤተ ክርስቲያን ዋና ክፍል ነበሩ። 

በልሳናት መናገር መንፈሳዊ ስጦታ እንደሆነው ሁሉ የትንቢት ስጦታም ዛሬ በክርስቲያኖች መካከል አከራካሪ ጉዳይ ነው። ይህ መንፈሳዊ ስጦታና (እግዚአብሔር ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጥ ከልጆቹ ጋር የሚያደርገው ቀጥተኛ ግንኙነት በሙሉ) ከአዲስ ኪዳን መጻፍ በኋላ ቆሟልን? ብዙ ክርስቲያኖች በተለይ ደግሞ በልሳናት የመናገር ስጦታ በዚህም ዘመን መሥራቱን የማይቀበሉ ሁሉ የሚሉት ይህንን ነው። ወይስ የትንቢት ስጦታ ዛሬም ቢሆን የሚሠራ ነው? እግዚአብሔር ዛሬም ቢሆን በሕልም፥ በራእይ፡ በድምፅ፥ ወዘተ… ይናገረናልን? ይህ ከሆነ ይህ ስጦታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? የትንቢት ቃሎች በአዲስና በብሉይ ኪዳን ካሉ ቃሎች ጋር እኩል ሥልጣን አላቸው? 

ጥያቄ፡– ሀ) ስለትንቢት ምንነት የምታምነውን ጻፍ። ላ) ነቢይ ምንድን ነው? ሐ) የእግዚአብሔርን ቃል በጻፈ የብሉይ ኪዳን ነቢይና በዚህ ዘመን የትንቢት መንፈሳዊ ስጦታ አለኝ በሚል ሰው መካከል ልዩነት ያላ ይመስልሃልን? ካለስ ልዩነቱ ምንድን ነው? 

በትንቢት ምንነትና በነቢይ ማንነት ርእሰ ጉዳይ ላይ በዚህ ዘመን ባለች ቤተ ክርስቲያን ብዙ ውዥንብር አላ። በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ሰዎች ይቆሙና ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበሉት የትንቢት ቃል እንዳላቸው ይናገራሉ። የሚያመጡት መልእክት ግን ለእግዚአብሔር ሕዝብ ምንም ወይም አነስተኛ ዋጋ ብቻ ያለው ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ከሚያስተምረው ጋር እንኳ የሚቃረን ይሆናል። አንዳንድ ሰዎችን የትንቢት ቃል ያመጡ ዘንድ እነርሱን የመጠባበቅ ዝንባሌ እየጨመረ መጥቷል። እግዚአብሔር ተናገረኝ ስንል ምን ማለታችን እንደሆነና የትንቢትን ምንነት በሚገባ ካላወቅን እንስታለን።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.