የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ምንድን ነው?

ጥያቄ፡– የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ዘፀኤ 31፡3፤ 36፡1፤ ዘዳ 34፡9፤ ሉቃስ 1፡5፥ 41፥ 67፥ 2፡4፤ የሐዋ. 2፡4፤ 4፡8፥ 31፤ 9፡17-20፤ 13፡9-11። ሀ) በእነዚህ ጥቅሶች በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ የተለያዩ ሰዎችን ጥቀስ። ለ) በመንፈስ ቅዱስ መሞላታቸውን የሚያረጋግጥ ምን ነገር አደረጉ? 

በመንፈስ ቅዱስ ስለ መሞላት በምናስብበት ጊዜ ወደ አእምሮአችን የሚመጣው ነገር የሆነ አስደናቂ ነገር ነው። ለምሳሌ በመንፈስ በመሞላትን ስናስብ ታላቅ የፍልስጥኤም ሠራዊትን ያሸነፈውን ሳምሶንን እናስባለን። ወይም ደግሞ በበዓለ ኀምሣ ቀን የታዩትን የእሳት ልሳኖችና በልሳናት መናገርን እናስባለን። ይህ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ምን እንደሚመስል ትክክለኛውን ሥዕል የሚሰጥ ነውን? የብሉይ ኪዳንና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን በአጠቃላይ ከተመለከትን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ያልተለመዱና ልዕለ-ተፈጥሮአዊ የሆኑ ነገሮች ባደረጉ ሰዎች ታሪክ የተሞላ ነው። በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ ነገር ግን ከተላመዱ ነገሮች ያልተለዩ ተግባራት የፈጸሙ ሌሎች ሰዎችም ነበሩ። ቀጥሎ በመጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ሰዎችን መሙላቱን የሚያሳዩ ጥቂት ምሳሌዎችን እናቀርባለን። 

ባስልኤል በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ የመገናኛውን ድንኳን የሚሠራበትን ጥበብ አገኘ (ዘፀአ 3፡3)። 

ኢያሱ በጥበብ መንፈስ በመሞላት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለመምራት ቶላ (ዘዳግ34፡9)። 

መጥምቁ ዮሐንስ ከመወለዱ በፊት ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ነቢይ ተብሎ ተጠራ (ሉቃ. 1፡5)። 

ኤልሳቤጥና ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ትንቢት ተናገሩ (ሉቃ. 1፡41፤ 67)። 

ደቀ መዛሙርት በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት በልሳኖች መናገር ቻሉ (የሐዋ. 2፡4)። 

ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት ለመሪዎች መናገር ቻለ የሐዋ. 4፡8)። 

ደቀ መዛሙርት በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው የእግዚአብሔርን ቃል በግልጥ ተናገሩ የሐዋ. 4፡3)። 

ሰባቱ ዲያቆናት በተለይ ደግሞ እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው የተቸገሩትን የመርዳትና ወንጌልን የመስበክ ስጦታ ነበራቸው (የሐዋ. 6፡3)። 

እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ በሰማይ ያለውን ኢየሱስን ተመለከተ (የሐዋ. 15)። 

ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት ለእግዚአብሔር በድፍረት የሚመሰክር ሆነ (የሐዋ. 9፡17-20)። 

ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት በኤልማስ ላይ የፍርድ መልእክት አስተላለፈ የሐዋ. 13፡9-10። 

በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ የተለያዩ ሰዎችን የሚያሳየው ይህ ዝርዝር ሰው በመንፈስ ቅዱስ በሚሞላበትና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ቁጥጥር ሥር በሚሆንበት ወቅት የሚያደርገው አንድ የተለየ ነገር እንደሌለ በግልጽ ያመላክታል። ለአንዳንዶች ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን አንድ ነገርን ለመገንባት ይሆናል። ለሌሎች ሠራዊትን የመምራትና ጠላትን ድል የማድረግ፥ የመተንበይ፥ ራእይ የማየት ወይም ያለፍርሃት የመመስከር፥ ወዘተ ተግባር ይሆናል። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ውጣዊ መግለጫ የተለያየ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ በተሞላ ሰው ሕይወት ውስጥ የሚፈጸመው ነገር ተመሳሳይ ነው። ከላይ የተመለከትናቸው ሰዎች በሙሉ በተፈጥሮአዊ ብርታታቸው ሊያደርጉ የማይችሉትን ነገሮች ማድረግ ችለዋል። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በተፈጥሮአዊ ችሎታቸው ሊያደርጉት ፈጽሞ የማይችሉትን ነገር እንዲያደርጉና ለእግዚአብሔር ክብር እንዲያመጡ አድርጐአቸዋል። 

ጥያቄ፡- ኤፌ. 5፡18-21 አንብብ። ሀ) የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የተነጻጸረው ከምን ጋር ነው? ለ) አንድ የሰከረ ሰው ሊያሳያቸው የሚችላቸውን የተለያዩ ባሕርያት ግላጽ። እነዚህ ባሕርያት በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር በሆንን ጊዜ ከሚፈጸሙት ነገሮች ጋር የሚመሳሰሉት እንዴት ነው? ሐ) በዚህ ጥቅስ ላይ የሚገኘው ግሥ የተገለጸው በምን ጊዜ ነው? ስለ አንድ ጭብጥ ነው የሚገልጸው? ጥያቄ ነው የሚጠይቀው? ወይስ ትእዛዝ ነው የሚሰጠው? መ) ጳውሎስ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚረጋገጥባቸው መንገዶች ምን ምን ናቸው አለ? 

መንፈስ ቅዱስ በሰው ሕይወት ውስጥ የሚያደርገውን ይህን ተደጋጋሚ ልምምድ ከሁሉ በላቀ ሁኔታ ለመግለጽ አገልግሎት ላይ የዋለው ቃል «የመንፈስ ቅዱስ ሙላት» የሚለው ይሆናል። የእውነተኛ መንፈሳዊነት ሁሉ ምክንያት መንፈስ ቅዱስ ነው። በሕይወታችን የመሥራት፥ ክርስቶስን እንመስል ዘንድ የመለወጥ፥ የክርስቶስን ህልውና በሕይወታችን የመለማመቶችን ብቻ ሳይሆን በተግባራችንም እንደንመስለው ማድረግ የእርሱ ኃላፊነት ነው። ይህ ተግባር እንዳንድ ጊዜ በአስደናቂ ውጫዊ ሁኔታ ሊገለጽ ይችላል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ እስደናቂ ስማይመስል፥ ነገር ግን በፍቅር፥ በደስታ፥ በሰላምና በተስፋ በተሞላ ሕይወት መኖር ነው። 

ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ስለሚኖረን ኅብረት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ግልጽ ትእዛዛት ጥቂት ናቸው። በመንፈስ ቅዱስ እንድንጠመቅ ፈጽሞ አልታዘዝንም። በመንፈስ ቅዱስ እንድንቀባም የተሰጠ ትእዛዝ የላም። ከሁሉ የሚበልጡትን ጠቃሚ መንፈሳዊ ስጦታዎች እንድንፈልግ የተነገረን ቢሆንም እንኳ የመንፈሳዊ ስጦታዎችን ህልውና እንድንፈልግ አልታዘዝንም። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ስላለን ኅብረት የሚገልጹ እነዚህ ነገሮች በሙሉ ከክርስቲያኖች ሁሉ ጋር አብረው ያሉ ናቸው። ወደ መንፈስ ቅዱስ ሙላት ስንመጣ ግን «መንፈስ ቅዱስ እንዲሞላብን») ታዝዘናል (ኤፌ. 5፡18)። መንፈስ ቅዱስን እንዳናሳዝን (ኤፌ. 4፡30)፥ የመንፈስ ቅዱስን እሳት እንዳናጻፍን (1ኛ ተሰ. 5፡19)፥ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንድንራመድ (ገላ. 5፡5) ታዝዘናል። 

በኤፌ. 5፡18 በመንፈስ ቅዱስ «እንሞላ » ዘንድ እግዚአብሔር ያዝዘናል። በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት እንድንችል በቁጥጥር ሥር ከሚያደርግ ሌላ ዓይነት ነገር ማለትም ከስካር ጋር ማነጻጸር አለብን። በአንድ በኩል በእነዚህ ሁለት ዓይነት መሞላቶች መካከል ከፍተኛ ልዩነቶች አሉ። አንድ ሰው በወይን በተሞላ ጊዜ ራሱን ስለማይቆጣጠር ምን እንደሚያደርግ እንኳ አያውቅም። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ አንድን ሰው በሚቆጣጠርበት ጊዜ ስለሚፈጸመው ነገር የተሞላው ሰው በሚገባ ያውቃል። 

እእምሮአቸውን ይቆጣጠራሉ። በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስ በአስደናቂ መንገድ በኃይል እየተጠቀመባቸው እንዳለም ያውቃሉ። 

ስለዚህ በወይን በመስከርና በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት መካከል ያለው ተመሳሳይነት ምንድን ነው? 

1. በወይን ጠጅ የተሞላ ሰው መጠጡ ስለሚቆጣጠረው ከመጠጣቱ በፊት ሊያደርገው የማይችለውን ነገር ማድረግ ይችላል። በተመሳሳይ መንገድ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ማለት በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር መሆንና ተለማምደውት የማያውቁትን ሕይወት መኖር ማለት ነው። ለምሳሌ የሰውዩው ባሕርይ ከቁጣ ወደ ፍቅር ይለወጣል፤ ከላስታምነት ሌሎችን ወደ ማገልገል ይቀየራል። 

2. የመጠጥ ሱሰኛ የሆነ ሰው የሚያጋጥመውን ችግር ለመጋፈጥና ብርታት ለማግኘት በመጠጡ ላይ ይደገፋል። በተመሳሳይ መንገድ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር የሚኖር ሰው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ኑር ለመኖር ኃይል ይሆነው ዘንድ ፊቱን ወደ እግዚአብሔር ይመልሳል።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

3 thoughts on “የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ምንድን ነው?”

  1. Yitbarek Tesfaye

    በቂድሚያ ለዚህ ለከበረውና ሰወችን ሁሉ ለሚያድነው ለህያው ወንገል በእግዝአብሔር ስለተመረጣችሁ ጌታን አመስግነዋለው።
    ሲቀጥል ትምህርቶቹ በጣም ደስ የምልና እንደ ግሌ ብዙ ጥያቀወች ለነበሩኝ ለእኔ መልስ ያገኘሁበት ሆኖ ተገኝቷል ። ነገር ግን አንድ አንድ ጠለቅ ያሉ ቃላቶች ላይ የፊደላት መዘበራረቅ ስለሚታዩ አንባብው ቃላቶችን ለመረዳት ስለሚቸግር ብስተካከል የምል ነው።
    በተረፍ ጌታ አምላክ ቀኙን ይስጣችሁ ተባረኩ ✞☨✞

Leave a Reply

%d bloggers like this: