ከተስፋቢስነትህ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠሃል?

ብዙ ክርስቲያኖች ራሳቸውን በድንገት በሮሜ 7 ውስጥ በሚገኘው አይነት የሕይወት ልምድ ሲገቡ ቢያገኙም ለምን እንደገቡ ግን መገንዘብ ሲቸግራቸው ይታያል፡፡ በተስፋ እና ድል የተሞላውን የሮሜ 6 ምዕራፍ ካነበቡ በኋላ በፊታቸው በሮሜ 7 ላይ እንደተጠቀሰው አይነት የሕይወት ልምምድ ሊገጥማቸው እንደሚችል ከቶዉኑም አይጠብቁም፡፡ ይህን አስበው ብዙ ሳይቆዩ ራሳቸውን በዚህ ታሪክ ውስጥ ያገኙታል፡፡ ለዚህ ክስተት ማብራሪያው ምንድን ነው?  

በመጀመሪያ፣ በሮሜ 6 ላይ የተገለፀው እና እኛ ከክርስቶስ ጋር የመሞታችን ሃቅ ላለን የኃጢአት ጥያቄዎች ሁሉ በቂ ምላሽ በመሆኑ ላይ ምንም ብዥታ ሊኖረን አይገባም፡፡ ሞታችን እና ከሞታችን ጋር ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች በምዕራፉ በተሟላ ዝርዝር ባለመቅረቡ በምዕራፍ 7 ውስጥ ለቀረበው መንፈሳዊ እውነታ እንግዶች እንድንሆን ሊያደርገን ይችላል፡፡ ሮሜ 7 በሮሜ 6፡14 ውስጥ የተገለጸውን እውነት በጥልቀት እንድንረዳ እና በቂ ግንዛቤ እንድንይዝ የሚረዳን ምዕራፍ ነው፡፡ ጥቅሱ እንዲህ ይነበባል፡- “ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።” እዚህ ላይ ያለው ትልቁ ችግር በርካታ ክርስቲያኖች ከሕግ መፈታት (ሮሜ 7፡6) ወይም አርነት መውጣት ማለት ምን ማለት እንደሆነ አለመገንዘባቸው ነው፡፡ ይህን ለመረዳት አስቀድመን የሕግን ምንንነት ማወቅ ይገባናል፡፡

ጸጋ ማለት እግዚአብሔር ለእኔ የሚያደርገው ነገር ሲሆን ሕግ ደግሞ እኔ ለእግዚአብሔር የማደርገው ነገር ነው። እግዚአብሔር እንድፈጽመው ወይም እንዳደርገው የሚጠይቀኝ ቅዱስና እና ጻድቅ ፍላጎቶች አሉት፤ እርሱም ሕግ ይባላል። ሕግ ማለት እግዚአብሔር እንድፈጽመው ከእኔ የሚጠብቀው ቅዱስ ፍላጎት ከሆነ ከሕግ አርነት ወይም ነጻነት መውጣት ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ይህን ቅዱስ ፍላጎቱን እኔ እንዳሟላ መጠበቅ ትቶ ራሱ አሟልቷል ማለት ነው፡፡ ሕግ እግዚአብሔር ለእርሱ አንድ ነገር እንዳደርግ እንደሚጥብቅ የሚገልጽ ከሆነ፤ ከሕግ ነጻ መውጣት ደግሞ ከእኔ ምንም እንደማይጠብቅ ያመለክታል። እናም በጸጋው እሱ ራሱ ያደርገዋል።  እኔ (ማለትም በሥጋዬ) የሕግን ትዕዛዝ ለመፈጸም ከቶ አልችልም (ሮሜ 7፡14)፡፡ በዚህ በሰረት በሮሜ 7 ላይ ያለው ሰው ችግር በስጋው ለእግዚአብሔር የሕግን ትዕዛዝ ለመፈጸም መታገሉ መሆኑን እንረዳለን። በእንዲህ ሁኔታ (ማለትም በሥጋህ) የሕግን ትዕዛዝ በመፈጸም እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት በምትንቀሳቀስበት ቅስበት ራስህን ከሕግ በታች ታደርጋለ፡፡ ከዛም የሮሜ 7 ሰውዬን የሕይወት ልምምድ መለማመድ ትጀምራለህ፡፡  

እዚህ ላይ አንድ ነገር በጊዜ ግልጽ መሆን አለበት፡፡ ችግሩ እኔ እንጂ ሕጉ አይደለም፡፡ “…ሕጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት” ( ሮም 7:12 )፡፡ በሕጉ ላይ ምንም ችግር የለም፣ ችግሩ እኔ ጋር ነው። የሕግ ፍላጎቶች ጽድቅ ናቸው፤ ነገር ግን እንዲፈጽማቸው የተጠየቀው ሰው ዓመፀኛ ነው። ችግሩ፣ ሕጉ የጠየቀው ጥያቄ ተገቢ አለመሆኑ ሳይሆን ፈጻሚው አካል ሊያደርጋቸው አለመቻሉ ነው፡፡ 

“ከኃጢአት በታች ልሆን የተሸጥሁ” ሰው ነኝ (ሮሜ. 7:14)፡፡ ኃጢአት በእኔ ላይ የበላይ ነው (ይገዛኛል)። ሕግ ከእኔ የሚጠይቀው አንዳች ነገር እስከሌለ ድረስ ጤነኛ መስዬ መኖር እችላለው፤ ሕጉ እንዳደርገው የሚፈልገው ነገር በተገለጠ ጊዜ ግን የእኔም አመጻ (ሃጢአት) አብሮ ይገለጣል፡፡ የተደበቀው ማንነቴ ወደ ብርሃን ይወጣል፡፡

ደንባራ አገልጋይ ቢኖርህና ያለሥራ ተቀምጦ ቢውል ደንባራነቱ ከእርሱ ጋር ቢሆንም ማንነቱ ሳይገለጥ ይቆያል፡፡ ቀኑን ሙሉ ምንም ሳያደርግ ከተቀመጠ ምንም የጠቀመህ ነገር ባኖርም ቢያንስ ግን ሲደናበር ከሚያጠፋው ጥፋት ተጠብቀሃል፡፡ “ጊዜ አታባክን፤ ተነሳና አንድ ነገር አድርግ” ያልከው እለት ወዲያውኑ የተደበቀው ችግር መገለጥ ይጀምራል፡፡ ገና ሲነሳ ከወንበሩ ጋር እግሩ ይላተማል፣ ጥቂት እንደተራመደ በመንገዱ ላይ ካለ ነገር ጋር ይጋጫል፤ ብዙ ሳይቆይ ሲደናበር ውድ እቃህን ከእጁ ላይ ጥሎ ይሰብርብሃል፡፡ እንዲሰራ ሳትጠይቀው ቀርተህ ቢሆን ምንም እንኳ ሊጠቅምህ ባይችልም ይህን ሁሉ ችግር አይፈጸምም፡፡ እንዲያደርግልህ የጠየከው ጥያቄ ከሌለ ደንባራነቱ በጭራሽ አይታወቅም፡፡ ተነስቶ እንዲሰራ መጠየቁ ትክክል ቢሆንም የተጠየቀው ሰው ግን ጥያቄዎን በአግባቡ ለመፈጸም የማያስችል መሰረታዊ ችግር አለበት፡፡ ተቀምጦም ሆነ ሲሰራ ሰውየው ያው ደንባራ ነው፡፡ ነገር ግን ደንባራነቱን የገለጠው ትዕዛዙን ተከትሎ ነው፡፡

ሁላችንም በተፈጥሮ ኃጢአተኞች ነን። እግዚአብሔር ከእኛ ምንም ካልጠየቀ፤ እኛም ሆነ በእኛ ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ጥሩ መስሎ ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእኛ አንዳች ነገር በጠየቀ ጊዜ (ሕግ) ሃጢአተኛ ተፈጥሮአችን ራሱን መግለጥ ይጀምራል፡፡ በሌላ አነጋገር ሕጉ ድካማችንን በግልጽ ያሳያል። ዝም ብለህ እንድቀመጥ ከፈቀድክልኝ፣ ሁሉ ነገር ሰላም ሊመስል ይችላል፡፡ እንድሰራ ባዘዝከኝ ጊዜ ግን፣ ጥፋቴን መመልከት ትጀምራለህ፡፡ ሁለተኛ እድል ብትሰጠኝም ማጥፋቴን አልተውም፡፡ ቅዱሱን የእግዚአብሔርን ሕግ ለመፈጸም ስነሳ የሚፈጠረውm ይኸው ነው፡፡ ሕጉ በውስጤ ያለውን ማንነቴን መግለጥ ይጀምራል፡፡

እግዚአብሔር እኔ ማን እንደሆንኩ ያውቃል፡፡ ከራስ ጸጉሬ እስከ እግሬ ጥፍሬ በኃጢአት የተሞላሁ እንደሆነም  ያውቃል፡፡ ምንም ማድረግ እንደማልችል ለሱ የተሰወረ ሃቅ አይደለም፡፡ ችግሩ እኔ ይህን ሃቅ አለማወቄ ነው። እኔን ጨምሮ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ መሰረታዊ ግንዛቤ ቢኖረኝም ፍጹም ተስፋ ቢስ ሃጢአተኛ መሆኔን ግን በቀላሉ አልገነዘብም፡፡ ለአብነት፣ ራሴን ከአንዳንድ “የከፉ” ሃጢአተኞች ይልቅ የተሻልኩ አድርጌ ልመለከት እችላለው፡፡ በመሆኑም፣ እግዚአብሔር ፍጹም ተስፋ ቢስ እና ደካማ እንደሆንኩ ወደምገነዘብበት ሁኔታ ሊያመጣኝ ይፈልጋል፡፡ የሕግን ትዕዛዝ ከመፈጸም አኳያ ምን ያህል ጎስቋሎች ወይም ደካሞች እንደሆንን የምንለውን ያህል እውነታውን አናውቀውም፡፡  እናም፣ እግዚአብሔር ከዚህ መራር እውነታ ጋር እንድንፋጠጥ እና እንድንቀበል አንድ መሳሪያ አዘጋጅቷል፤ ያም መሳሪያ ሕግ ይባላል፡፡ በሕጉ ባይሆን ኖሮ ምን ያህል ደካሞች እና ተስፋ ቢሶች መሆናችንን ባላወቅን ነበር፡፡ ጳውሎስ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። በሮሜ 7፡7 ላይ፣ “…በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ፦ አትመኝ ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና” በማለት ይህን መረዳቱን ግልጽ ያደርግልናል፡፡ ከሌሎቹ ትዕዛዛት አንጻር ጳውሎስ የነበረው የሕይወት ልምምድ ምን ይምሰል ምን፣ ማንነቱን ያውቅ ዘንድ ፊት ለፊት የተላተመው ከአሥረኛው ትእዛዝ ጋር እንደነበር ተገልጿል፡፡ በዚህ ትዕዛዝ አማካኝነት ጳውሎስ ከድካሙ እና ተስፋቢስነቱ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጠ!

አብዝተን ሕጉን ለመጠበቅ በሞከርን ቁጥር አብዝተን በመውደቅ ሕይወታችን ለሮሜ 7 ልምምድ ቅርብ መሆኑን እየተረዳን እንመጣለን፡፡ የዚህ አላማው፣ በራሳችን የሕጉን ትዕዛዛት ልንፈጽም የማንችል ተስፋ ቢሶችና ደካሞች መሆናችንን ማስገንዘብ ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው እግዚአብሔር ይህን ማንነታችንን ጠንቅቆ ያውቀዋል፤ እኛ ግን አናውቅም፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር እጅግ አስቸጋሪ እና ህመም ባለባቸው ሁኔታዎች ውስጥ እንድናልፍ በመፍቀድ ከዚህ እውነታ ጋር ፊት ለፊት እንድንላተም ብሎም እውነታውን እንድንቀበል ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር ሕግን የሰጠን ወደዚህ እውነት እንድንደርስ ነው።

ስለዚህ በአክብሮት እና በጥንቃቄ እንዲህ ማለት እንችላለን፡- እግዚአብሔር ሕግን እንድንጠብቀው ሳይሆን እንድንጥሰው ነው የሰጠን። ሕጉን መፈጸም እንደማንችል በእርግጥ ያውቃል፡፡ ስረ-መሰረታችን እጅግ የተበላሸና እና ከእኛ አንዳች በጎ ነገር እንደማይገኝ ያውቃል (ሮሜ 7፡18)፡፡ ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ በኩል ሊጸድቅ አይችልም፡፡ ሕግ ሊያጽድቀን የተሰጠ ሳይሆን “በደል እንዲበዛ” የተሰጠ ነውና (ሮሜ 5፡20)፡፡ ሕግ የተሰጠው እንድንፈጽመው ሳይሆን ሕግ ተላላፊዎች መሆናችንን ለማስረዳት ነው፡፡  “…በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ፦ አትመኝ ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና። ኃጢአት ግን ምክንያት አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በትእዛዝ ሠራብኝ፤ ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ነውና። እኔም ዱሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ እኔም ሞትሁ፤” (ሮሜ. 7:7-9)፡፡ ሕግ፣ እውነተኛውን ተፈጥሮአችንን ከተደበቀበት ጎሬ አውጥቶ ወደ አደባባይ ያወጣዋል፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ለራሳችን ያለን ግምት የተጋነነ እና እጅግ ኩሩዎች ስለሆንን እግዚአብሔር ይህን ውሸት ገልጦ ለማሳየት እና ሃጢአተኞች እና ደካሞች መሆናችንን ለማስረዳት ሕግን ይጠቀማል፡፡ 

ሕጉ እንደምንተላላፈው እየታወቀ የተሰጠ እንጂ ይፈጽሙታል በሚል ተስፋ የተሰጠ አይደለም፡፡ ለመጠበቅ በምናደርገው ትግል ውስጥ ተላልፈነው ስናበቃ በውስጣችን ያለውን ማንነት ከገለጠ የሕግ አላማ ተሳካ ማለት ነው፡፡ ሕጉ፣ “በእምነት እንጸድቅ ዘንድ … ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን…” ነው (ገላ. 3፡24)።

አዳነው ዲሮ ዳባ

6 thoughts on “ከተስፋቢስነትህ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠሃል?

 1. ተባርኮ

  On Thu, Nov 11, 2021, 10:40 PM ወንጌል በድረ-ገፅ አገልግሎት wrote:

  > tsegaewnet posted: ” ብዙ ክርስቲያኖች ራሳቸውን በድንገት ወደ በሮሜ 7 ውስጥ በሚገኘው አይነት የሕይወት
  > ልምድ ሲገቡ ቢያገኙም ለምን እንደገቡ ግን መገንዘብ ሲቸግራቸው ይታያል፡፡ በተስፋ እና ድል የተሞላውን የሮሜ 6 ምዕራፍ
  > ካነበቡ በኋላ በፊታቸው በሮሜ 7 ላይ እንደተጠቀሰው አይነት የሕይወት ልምምድ ሊገጥማቸው እንደሚችል ከቶዉኑም
  > አይጠብቁም፡፡ ይህን አስበው ብዙ ሳይቆዩ ራሳቸውን በዚህ ታሪክ ውስጥ ያገኙታል፡፡ ለዚህ ”
  >

  Like

 2. Thank you !
  With blessings

  On Friday, November 12, 2021, ወንጌል በድረ-ገፅ አገልግሎት wrote:

  > tsegaewnet posted: ” ብዙ ክርስቲያኖች ራሳቸውን በድንገት ወደ በሮሜ 7 ውስጥ በሚገኘው አይነት የሕይወት
  > ልምድ ሲገቡ ቢያገኙም ለምን እንደገቡ ግን መገንዘብ ሲቸግራቸው ይታያል፡፡ በተስፋ እና ድል የተሞላውን የሮሜ 6 ምዕራፍ
  > ካነበቡ በኋላ በፊታቸው በሮሜ 7 ላይ እንደተጠቀሰው አይነት የሕይወት ልምምድ ሊገጥማቸው እንደሚችል ከቶዉኑም
  > አይጠብቁም፡፡ ይህን አስበው ብዙ ሳይቆዩ ራሳቸውን በዚህ ታሪክ ውስጥ ያገኙታል፡፡ ለዚህ ”
  >

  Like

 3. በጣም ደስ የሚል ቃል አካፈልከን፡፡ ዉስጤ ሀሴት አደረገ፡፡ እዉነት ለመናገር በሮሜ 6 እና 7 ላይ ያለዉ ቃል ሁል ጊዜ በትክክለኛ መንገድ አልረዳዉም፡፡ ግራ ይገባኛል፡፡ ቤተክርስቲያንም ይህንን ቃል በግልጽ እና በዝርዝር ለምዕመናን አታስረዳም፡፡ ዛሬ ከአንተ የሰማሁት ትምህርት ልቤን መልሶታል፡፡ ደስ ብሎኝል፡፡ ብዥ ያለብኝን በእግዚአብሔር ቃል ፍንትዉ አድርገህ አሳይተህኝል፡፡ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡

  Like

 4. የጌታ ሰላም ለእናንተ ይሁን ! ወደ ጥያቄ ልግባ አገልጋይ ነኝ! መድረክ ላይ ለሎች ስያገለግሉ ውስጤ በቃሉ ይቃጠላል ።
  ከአገልጋዩ የተለየ መገለጥ ይመጣልኛል ። ነገር ግን እነ መድረክ ስወጣ በአገልግሎተ አልረካም ። እቤት መጽሐፍ ቅዱስ
  ሳነብ ሳሰላስል እረካለሁ። ነገር ግን መድረክ ላይ ለሎችን ሳገለግል እርካታውን አጣዋለሁ። ምን ይሁን ምክንያቱ??

  On Thu, Nov 11, 2021, 10:40 PM ወንጌል በድረ-ገፅ አገልግሎት wrote:

  > tsegaewnet posted: ” ብዙ ክርስቲያኖች ራሳቸውን በድንገት ወደ በሮሜ 7 ውስጥ በሚገኘው አይነት የሕይወት
  > ልምድ ሲገቡ ቢያገኙም ለምን እንደገቡ ግን መገንዘብ ሲቸግራቸው ይታያል፡፡ በተስፋ እና ድል የተሞላውን የሮሜ 6 ምዕራፍ
  > ካነበቡ በኋላ በፊታቸው በሮሜ 7 ላይ እንደተጠቀሰው አይነት የሕይወት ልምምድ ሊገጥማቸው እንደሚችል ከቶዉኑም
  > አይጠብቁም፡፡ ይህን አስበው ብዙ ሳይቆዩ ራሳቸውን በዚህ ታሪክ ውስጥ ያገኙታል፡፡ ለዚህ ”
  >

  Like

 5. አገልግሎታችሁ የተባረከ ይሁን

  On Thu, Nov 11, 2021, 10:40 PM ወንጌል በድረ-ገፅ አገልግሎት wrote:

  > tsegaewnet posted: ” ብዙ ክርስቲያኖች ራሳቸውን በድንገት ወደ በሮሜ 7 ውስጥ በሚገኘው አይነት የሕይወት
  > ልምድ ሲገቡ ቢያገኙም ለምን እንደገቡ ግን መገንዘብ ሲቸግራቸው ይታያል፡፡ በተስፋ እና ድል የተሞላውን የሮሜ 6 ምዕራፍ
  > ካነበቡ በኋላ በፊታቸው በሮሜ 7 ላይ እንደተጠቀሰው አይነት የሕይወት ልምምድ ሊገጥማቸው እንደሚችል ከቶዉኑም
  > አይጠብቁም፡፡ ይህን አስበው ብዙ ሳይቆዩ ራሳቸውን በዚህ ታሪክ ውስጥ ያገኙታል፡፡ ለዚህ ”
  >

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.