ክርስቶስ እንደ መካከለኛና እንደ አማላጅ 

ትናንትና ያልተወያየንበት፥ ነገር ግን በጣም ጠቃሚ የሆነ ኢየሱስ አሁን ለእኛ እያከናወነልን ያለው አንድ ሥራ አለ። ይህ ሥራ በኢትዮጵያ ውስጥ ጠቃሚ ስፍራ ያለው ስለሆነ ሙሉ ቀን እንድንወያይበት ፈለግን። ይህም የክርስቶስ የአማላጅነትና የመካከለኝነት ሥራ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ክርስቲያኖችን ከሚከፋፍሏቸው አከራካሪ ጉዳዮች አንዱ አማላጅ ማን ነው? የሚለው ነው። ብዙ የኦርቶዶስ ክርስቲያኖች ለብዙ አማላጆች ይጸልያሉ፣ ያምኑባቸውማል። በአንጻሩ ብዙ ወንጌላውያን ክርስቲያኖች ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛው አማላጅ ነው ይላሉ። በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ለክርስቲያኖች የሚያማልደው ማን ነው? ስለሆነም ዛሬ ስለ ክርስቶስ አማላጅነት እርሱ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ስለመሆኑ እናጠናለን። እንዲሁም በአጭሩ ስለ መንፈስ ቅዱስ የአማላጅነት ሥራ ጠቀስ በማድረግ የእርሱ የማማለድ ተግባር ከክርስቶስ ሥራ ለየት እንደሚልም እናመለክታለን። 

1. ኢየሱስ ክርስቶስና መንፈስ ቅዱስ እንደ አማላጆች 

ጥያቄ፡– ሮሜ 8፡26-27 አንብቡ። ሀ) መንፈስ ቅዱስ በድካማችን፥ በማይነገር መቃተት ምን ያደርግልናል? ለ) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ምን ያደርጋል? 

ጥያቄ፡- ሮማ 8፡34 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ ክርስቶስ ባለፈው ጊዜ ምን እደረገልን? ለ) በአሁኑ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እያደረገልን ነው? ሐ ራእይ 12፡9-10 አንብቡ። አማኞችን የሚከስ ማን ነው? 

ጥያቄ፡- ዕብራውያን 7፡23-24 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ በምን ምክንያት ከብሉይ ኪዳን ካህናት የላቀ ሆነ? ላ) ዕብራውያን 7፡25 አንብቡ። ኢየሱስ በፍጹም ሊያድነን በምን ምክንያት ቻለ? 

አዲስ ኪዳን አማኞች ስለ እነርሱ የሚያማልዱ ሁለት አማላጆች እንዳሉዋቸው ያስተምራል። እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስና መንፈስ ቅዱስ ናቸው። የመንፈስ ቅዱስ የአማላጅነት ሥራ በተለይ የሚታየው ክርስቲያኖች በሥቃይ ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ ነው። ስርሜ 8፡18-27፥ ሐዋርያው ጳውሎስ ሲጽፍ ከሰው ልጅ ኃጢአት የተነሣ ፍጥረታት ሁሉ እስከ ዛሬ ድረስ በምጥ ጭንቀት ተይዞ በመቃተት ላይ መኖሩን እናውቃለንና ይላል። ፍጥረት ከመሠቃየቱ የተነሣ በእውነትም ይቃትታል። ሆኖም ይህ የሚታየው ቁሳዊ ፍጥረት ብቻ አይደለም የሚሠቃየው። በክርስቶስ አማኞች የሆኑትም እንኳ ይሠቃያሉ። የምንሠቃይበትም ምክንያት ደካማ፣ ምዋችና በስባሽ ገላ ስላለንና ይህ ገላም በዚህ ዓለም ላሉ ክፋቶች ሁሉ የተጋለጠ ስለሆነ ነው። በክርስቶስ የሚያምኑ መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው የሚኖርባቸው (ቁጥር 23) ሳይቀሩ በጣም ይሠቃያሉ፤ ስለዚህም በውስጣችን እንቃትታለን። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ድካማችን ላይ የሚረዳን አለ። ይህ የሚረዳንም የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው። እርሱም በድካማችን ጊዜ ይማልድልናል። መንፈስ ቅዱስ ሥቃያችን ስለሚሰማው ከእኛ ጋር አብሮን ይቃትታል። ሊያማልደንም ሥቃያችን እየተሰማው ስለሆነ በቃላት ሊገለጽ በማይችል መቃተት ነው። እንዲህም ማለት መንፈስ ቅዱስ ሲጸልይልን እኛን የሚሰማን ሥቃይ እርሱንም በጥልቀት እየተሰማው ነው ማለት ነው። ሥቃያችንን በቃል አማካይነት ብቻ ለአብ አያቀርብም። ጉዳታችንና ሥቃያችን ይሰማዋል፤ ወደ እግዚአብሔር በሚያቀርበውም ጸሎት የሥቃያችንን ብርታት አብሮ ያቀርባል። ስለሆነም መንፈስ ቅዱስ ስለ እኛ ሰሚጸልይበት ጊዜ የሚጸልየው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ነው። የሚጸልየው ከምናልፍበት ሥቃይ የተነሣ እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥና በሕይወታችን አማካይነት ሊያደርግ የሚፈልገውን ነው። አዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ለሕይወታችን ስላለው ዓላማ ብዙ ምሳሌዎችን ያቀርባል። ይኸውም ከሥቃያችን ውጤት የተነሣ እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ እንድናውቀው (ኤፌሶን 1፡18-19)፥ የበለጠ እንደ ክርስቶስ እንድንሆን፥ የበለጠ ቅዱሳን እንድንሆን (1ኛ ተሰሎንቄ 43) ነው። ሥቃያችን እነዚህን ውጤቶች እንዲያመጣ መንፈስ ቅዱስ ይጸልይልናል። አማኞች በተለይ ስሚሠቃዩበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ይማልድላቸዋል። 

ጥያቄ፡- በምትሠቃዩበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የሚጸልይላችሁ መሆኑን ማወቃችሁ እንዴት ያበረታችኋል? 

ሥቃይ በሚደርስብን ጊዜ ምን እንደሚሰማን በትክክል እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ይህ ደግሞ ያበረታታናል። እግዚአብሔር የልጆቹን ሥቃይና ሕማም የማያዳምጥ የሩቅ ገዥ አይደለም። ይልቁንም እግዚአብሔር መንፈረ ቅዱስ በቀጥታ ከእኛ ጋር በመሆኑ የሚሰማን ሕማም ሁሉ ይሰማዋል፡ እርሱም ሥቃያችንን ለእግዚአብሔር በምልጃው ይገልጽለታል። ደግዋ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በሥቃያችን አማካይነት ወደ ሕይወታች ሊያመጣ የሚፈልገውን ያውቃል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ርቃልካም ፈቃዱ በውስጣችን እንዲፈጽም ይጸልያል። የእኛ ኃላፊነት በሥቃያችን ጊዜ በእግዚአብሔር ማመንና ለእርሱም መታዘዝ፥ እግዚአብሔርም በዚህ ሳቢያ መልካም ነገር እንዲያደርግ መተማመን ነው። የመንፈስ ቅዱስ አማላጅነት የምንሠቃየው ሥቃይ እግዚአብሔርን የሚሰማው መሆኑንና እግዚአብሔር በዚህ ሥቃይ አማካይነት መልካም ነገር እንደሚያደርግ ያረጋግጥልናል። 

ነገር ግን ለአማኞች የሚያማልደው መንፈስ ቅዱስ ብቻ አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱም ለአማኞች ያማልዳል። በሮሜ 8፡31-39 ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር እማኞችን ከእግዚአብሔር ፍቅር የሚለያቸው የለም ይላል። እግዚአብሔር ያጸደቀን ከሆነ እግዚአብሔር ልጁን ለእኛ የሰጠ ከሆነ ማንም አንዳች ክስ ሊያቀርብብን ወይም ሊኮንነን አይችልም። በቁጥር 34 ውስጥ ጳውሎስ በአማኝ ላይ ክስ ሊያስነሣ የሚችል እንደሚኖር ይጠቁማል። ጳውሎስ ይህን ሲል ስለ ሰይጣን እያሰበ ነበር። ሰይጣን ቀንና ሌሊት አማኞችን በእግዚአብሔር ፊት ይከስሳል (ራእይ 12፡10)። ምንም እንኳን ሰይጣን አማኞችን ቢከስስም፣ የሚፈሩት ነገር አይኖርም፥ ምክንያቱም ኢየሱስ በእግዚአብሔር ፊት ያማልዳቸዋል። 

ጥያቄ፡- ኢሳይያስ 53፡12 አንብቡ። በምን ምክንያት ነው የእግዚአብሔር እገልጋይ ለሕግ ተላላፊዎች ያማልድላቸዋል የተባለለት? 

ኢየሱስ በራሱ ደም አማካይነት በእግዚአብሔር ፊት ያማልደናል። በኢሳይያስ 53፡12 ነቢዩ ሲናገር ስለ እኛ ኃጢአት የተሠዋው (ኢሳይያስ 53፡5-6)፥ የእግዚአብሔር ፍጹም አገልጋይ ኃጢአታችንን በመሸከም ያማልድልናል ይላል። እርሱ ራሱ ኃጢአታችንን ስለተሸከመ እነሆ ሰይጣን በኃጢአታችን በሚከስሰን ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ ያማልድልናል። እርሱ የኃጢአታችንን ዋጋ የከፈለልን ስለሆነ፥ ሰይጣን እኛን ሊከዕን ምክንያት አይኖረውም። ለእኛ ይገባን የነበረውን የኃጢአት ቅጣት የከፈለው ኢየሱስ ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ስለሚቆምልን አማኛች በኃጢአታቸው ምክንያት አይኮነኑም። 

ነገር ግን ኢየሱስ ስለ እኛ ኃጢአት ቅጣትን ድሮ የተቀበለ ብቻ ሆኖ በእግዚአብሔር ዘንድ አይኖርም። አሁንም ሊቀ ካህናችን ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት በመቆም ይማልድልናል። ዕብራውያን ምዕራፍ 7 የምድራዊ ካህናትን የእኛ ሊቀ ካህን ከሆነው ከኢየሱስ አገልግሎት ጋር ያወዳድራል። ሰዎች የሆኑ ካህናት አርጅተው በሚሞቱበት ጊዜ በእግራቸው የሚተኩ ሌሎች በርካታ ካህናት ያስፈልጉ ነበር። ኢየሱስ ከእነዚህ የሚለየውና ከእነርሱም በላይ የሚያደርገው አንዱና ዐብዩ ምክንያት እርሱ ለዘላለም ነዋሪ የመሆኑ ነገር ነው። እርሱ የእኛ ዘላለማዊ ሊቀ ካህን ነው። የእኛ ዘላለማዊ ሊቀ ካህን እንደ መሆኑ፥ ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖ ያማልደናል። የብሉይ ኪዳን ካህናት የእነርሱና የሕዝቡ ኃጢአት ይሠረይ ዘንድ መሥዋዕት የሚሆኑ ነገሮችን በማምጣትና መሥዋዕትን በማቅረብ ጊዜያቸውን ያሳልፉ ነበር። ኢየሱስ ግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ደሙን ለኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት አቅርቦአል (ዕብ. 9፡14)። ስለዚህ በኦሁኑ ሰዓት በእግዚአብሔር ዘንድ ቋሚ ሊቀ ካህናችን ሆኖ በመገኘት ስለ እኛ ኃጢአት ይማልድልናል። የእርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ መኖርና መጸለይ፥ የሚያሳስበን ለኃጢአታችን ይቅርታ የእርሱ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መሞት በቂ መሥዋዕት መሆኑን ነው። 

ጥያቄ፡- የክርስቶስ አማላጅነት ምን ያህል መጽናናትን ይሰጣችኋል? 

ብዙ ጊዜ ሰይጣን አማኞችን ስለ ኃጢአታቸው እያስታወሰ ፍርሃትና ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው ያደርጋል። እኛ ክፉ ሰዎች ስለሆንን እግዚአብሔር ይቅር እንደማይለን አድርጎ ይናገራል። አንድ ቀን በኃጢአታችን ምክንያት እንደምንኮነን አድርጎ ያስፈራራናል። ኃጢአታችን ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ብቃት እንደሌለን፥ ከእግዚአብሔርም ጋር በአሁኑ ሰዓት አንድነት ሊኖረን እንደማይችል አድርጎ ይነግረናል። የክርስቶስ አማላጅነት እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ያለን ስለ መሆኑ ለእኛ መጽናኛና ዋስትናም ነው። ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ቅጣቱን ከፍሎአል። ከአሁን ወዲያ የወደፊት ኩነኔን መፍራት አይኖርብንም። ክርስቶስ እንደ ሊቀ ካህናችን ሆኖ እኛን የማማለዱ ተግባር ከእግዚአብሔር ጋር ባለንበት ስፍራ በአሁኑ ሰዓት ግንኙነት እንዲኖረን ያደርጋል። በራሳችን ጽድቅና ቅድስና ተመክተን ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ለማድረግ እንሞክርም። ወደ እግዚአብሔር ፊት መቅረብ የምንችለው ሊቀ ካህናችን በሆነው በኢየሱስ በኩል ሲሆን፥ እርሱም ስለ እኛ ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ይቆማል። ስለዚህ ሰይጣን የሚያመጣብንን ጥርጣሬና ተስፋ አስቆርጦ የማዳከም ሁኔታን ልንቋቋም እንችላለን። ክርስቶስ በአሁኑ ሰዓት ሊቀ ካህናችን ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት ይገኛል። በእግዚአብሔርና በእኛ መካከል ያለው እርሱ ነው። ኢየሱስ አሁን እያደረገ ያለው የማማለድ አገልግሎት ፍጹም ኩነኔ እንደማይደርስብንና አሁኑኑ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነታችን የበረታ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው። ይህንንም መረዳታችን ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው። 

2. ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ መካከለኛ ወይም እንደ አማላጃችን 

ክርስቶስ አማላጃችን ብቻ አይደለም፥ ደግሞም በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ያለም ነው። 

ጥያቄ፡- 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡1-4 አንብቡ። ሀ) ሐ ዋርያው ጳውሎስ ምን እንድናደርግ ያዝዘናል? ለ) እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ የሚፈልገው ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡5 አንብቡ። ሀ) በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ስንት አማላጆች አሉ? ለ) በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ያለው አማላጅ ማን ነው? 

ጥያቄ፡- 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡5 አንብቡ። ክርስቶስ በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል የመሆኑ ጉዳይ መሠረቱ ምንድን ነው? 

በ1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡5 ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚነግረን፥ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ሆኖ የሚያማልደው ወይም የሚያስታርቀው አንድ ነው ይላል። ይህ አንድ አማላጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ያለ አማላጅ መሆኑን የተናገረበትን ምክንያት ለመረዳት ከዚህ ጥቅስ በፊት ያሉትን ጥቅሶች መመልከት ይጠቅማል። አማኞች በእግዚአብሔር ፍርሃት እንዲኖሩ ለሰዎች ሁሉ በተለይም በሥልጣን ላይ ላሉት መጸለይ እንደሚያስፈልግ ሐዋርያው ጳውሎስ በሰጠው ትእዛዝ ላይ አሳስቦአል። 

አማኒያን በጸሎትና በፈሪሃ እግዚአብሔር መኖር ለምን አስፈለጋቸው? ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ስለሚፈልግ ነው። ስለዚህ ማንም ሊድንና ወደ እውነተኛው እውቀት ሊመጣ የሚችለው አንዱ በሆነው አማላጃችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው፡ እናም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ያለው አንዱ መንገድ ኢየሱስ ነው። ስለሆነም ሰዎች ለደኅንነት ወደ እግዚአብሔር የሚመጡበት መንገድ እርሱ ነው። እንዲሁም ሰዎች ስለ እግዚአብሔር እውነተኛውን እውቀት የሚያገኙበት በትኛው መንገድ ነው። ጌታ ኢየሱስ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አማላጅ የመሆኑ መሠረት ራሱን ቤዛ አድርጎ ለሰው ልጆች የመስጠቱ ሁኔታ ነው፡፡ 

የሰው ልጆችን ሁሉ የኃጢአት ዕዳ የከፈለ ስለሆነ፥ ለሰዎች ሁሉ ና ደኅንነት ወደ እግዚአብሔር መምጫው መንገድ በእርሱ ነው፡ በቁጥር አንድ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ አማኞች እንዲጸልዩ ባዘዛቸው ጊዜ ሰዎች በአንዱ መንገድ እርሱም ብቸኛው በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ወደ እርሱ ሊመጡ እንዲችሉ እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ሁኔታ እንዲያዘጋጅላቸው 

እንዲጸልዩ ነበር። 

ጥያቄ፡- እግዚአብሔር ገዢዎችንና የዓለምን ሁኔታዎች በመጠቀም ለምች በኢየሱስ በኩል ወደ እርሱ እንዲመጡ የሚያደርግባቸውን ሦስት የተወሰኑ የጸሎት ርእሶችን ጻፉ፡፡ 

እግዚአብሔር ይህን ዓለም ለወንጌል እንዲያመቻችና እንዲስብ እና ክርስቲያኖች ያለማቋረጥ መጸለይ አለብን። እንደዚሁም ወንጌልን ላልደረሳቸው ሁሉ በማዳረስ ሥራ ላይ የተጠመዱትን ወንጌላውያን እንዲደፏቸውና እንዲያግዙዋቸው እግዚአብሔር የመንግሥትን ባለሥልጣናት ልቦና ይቀሰቅስ ዘንድ መጸለይ ይጠበቅብናል። ወንጌል በሚሰበክበት አካባቢ ያሉ ሰዎችም ለወንጌል ቅን አመለካከት እንዲኖራቸው እግዚአብሔር ያደርግ ዘንድ መጸለይ አለብን። ሰዎች ለወንጌል ጉዳይ የተዘጋጁ ሆነው እንዲገኙ ሁኔታው አመቺ እንዲሆንላቸው ለማድረ እግዚአብሔር የፖለቲካ፥ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ሁኔታዎችን እንደ ፈቃዱ ያስተካክል ዘንድ መጸለይ የሚገባ ነው። እንዲሁም የማያምኑ ሰዎች በራሳቸው መንገድ እውነትን ለማግኘት የሚያደርጉትን ፍለጋ ትተው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስላለው እውነት ልባቸውን የከፈቱ እንዲሆኑ መጸለይ አለብን። በተጨማሪም ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ስላላቸው ችግርና ስላላቸው ጥያቄ ሁሉ መልሱ ኢየሱስ ብቻ መሆኑን ይገነዘቡ ዘንድ መጸለይ ያስፈልገናል። 

ጥያቄ፡- ዕብራውያ 8፡6፤ 9፡15፤ 12፡24 አንብቡ። ኢየሱስ መካከለኛነትና አማላጅነት ለምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- ዕብራውያን 8፡10-12 እንብቡ። አዲስ ኪዳን ከአርጌው በምን ምክንያት የተሻለ ሆነ? 

ጥያቄ፡- ዕብራውያን 9፡13-5 አንብቡ። ሀ) የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ለሕዝቡ ምን ጠቀማቸው? ለ) የክርስቶስ ደም ለሕዝቡ ምን ይጠቅማል? ሐህ በአዲሱ ኪዳን መሠረት የተጠሩት ምን ይቀበላሉ? 

የዕብራውያን መልእክት ኢየሱስ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለ ብቸኛው አማላጅ ስለመሆኑ አንድ ለየት ያለ ትምህርት ይሰጠናል። ይህም እርሱ ለሰው ልጆች የአዲስ ኪዳን አማላጅ ስለመሆኑ ነው። ኢየሱስ ፍጹም በሆነ ሕይወቱ፥ በመስቀል ሞቱና ትንሣኤው በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች መካከል አዲስ ስምምነት እንዲፈጠር አደረገ፡ በዚህ መሠረት አዲሱ ኪዳን ከአሮጌው ኪዳን የተሻለ ሆነ። ዳሩ ግን በአሮጌው ኪዳን ጊዜ ሰዎች ባይታዘዙ ቅጣት ይደርስባቸው ስለነበር ከዚህ ቅጣት ፍራቻና ሥጋት የተነሣ ይታዘዙ ነበር። በአዲሱ ኪዳን ግን እግዚአብሔር ሕጉን በሕዝቡ ልብና አእምሮ ውስጥ ለማስቀመጥ ተስፋ ሰጠ (ዕብራውያን 8፡10)። እንዲህ ማለትም በአዲሱ ኪዳን መሠረት ሊታዘዙት ፍላጎት አላቸው። እግዚአብሔርን በመታዘዝ ደስ ይላቸዋል። ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ደስታ ልናገኝ የቻልንበት ምክንያት ኢየሱስ ለአዲስ ኪዳን መካከለኛና አማላጅ በመሆኑ ነው። በአሮጌው ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሩቅና አስፈሪ ነበር። ከሲና ተራራ ላይ በሚያስፈራና ነጎድጓድ በተቀላቀለው ሁኔታ ይናገራቸው ነበር። ማንም ተራ ሰው በማይገባበት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ይኖር ነበር። በአዲሱ ኪዳን ግን የእግዚአብሔር ሰዎች በቅርበትና በወዳጅነት ሊተዋወቁት ችለዋል (ዕብራውያን 8፡1)። ሁላችንም እግዚአብሔርን ለማወቅ እንችላለን። ምክንያቱም በኢየሱስ አማላጅነት አዲስ ኪዳን ተገኝቶልናልና ነው። በአሮጌው ኪዳን ዘመን የመሥዋዕቱ እንስሳት ደም የሕዝቡን ኃጢአት ለጊዜው በመሸፈን ሥርዓታዊ መንጻትን በእግዚአብሔር ፊት አስገኝቶላቸዋል ምናልባትም ይህ ክንዋኔ እጅግ ጠቃሚ ቁም ነገር ተደርጎ የሚወሰድ ነበር። ነገር ግን በአዲሱ ኪዳን የክርስቶስ ደም ሰዎችን ከኃጢአታቸው ፈጽሞ በእውነት ያነጻቸዋል። አዲሱ ኪዳን ለእግዚአብሔር ሰዎች እውነተኛና ሙሉ የሆነ የኃጢአት ይቅርታን በተስፋው አጽንቶታል (ዕብራውያን 8፡12፤ 9፡14)። ኢየሱስ አዲሱን ኪዳን በማምጣት አማላጅነቱ በአሮጌው ኪዳን ሥር የነበሩት ሰዎች ያላገኙትን የተትረፈረፈ የደኅንነት ባርኮት አጎናጽፎናል። 

ጥያቄ፡- ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚያደርገውን የማማለድ ተግባር እንዴት ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ? ስለዚሁ ነገር ቢያንስ ሦስት መንገዶችን በጽሑፍ ግለጹ? 

አማኞች የአዲሱን ኪዳን የበረከት ትሩፋት ለመጠቀማቸው እርግጠኞች ሊሆኑ ይገባል። እኛስ እንዴት አድርገን በእነዚህ በረከቶች ልንጠቀም እንችላለን? በመጀመሪያ፥ ከእግዚአብሔር ጋር የግል ግንኙነት በማድረ? መጠቀም እንችላለን። ወደ እርሱ ዘንድ አዘውትረን በመቅረብ እርሱን ማነጋገርና ደስታችንንና ጭንቀታችንን መግለጽ እንችላለን። በሩቅ እንዳለ አስፈሪ አምላክ ሳይሆን ልክ እንደ አባት ልንመለከተው እንችላለን። ሁለተኛ፡ እርሱን ባንታዘዘው ይቀጣናል ከሚል ሥጋት ሳይሆን እግዚአብሔርን ለማስደሰት ካለን ፍላጎት ልንታዘዘው እንችላለን። በመሠረቱ እግዚአብሔር ከኃጢአታችን አድኖ ብዙ በረከቶችንና ዕድሎችን ሰጥቶናል። ስለዚህ ለዚህ ሁሉ ወሮታው እርሱን በመታዘዝ ምስጋናችንን ልንገልጽለት ይገባናል። በመጨረሻም፥ በፍርሃትና በጥርጣሬ ከመኖር አልፈን የኃጢአት ይቅርታን ስለማግኘታችን እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን። እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ብቻ አልሸፈነልንም፥ ክርስቶስን መድኃኒታችን አድርገን ያመንበት ከሆነ ክቡር ደሙ ኃጢአታችንን ሙሉ በሙሉ ያጥበዋል፤ ያነጻዋል። እግዚአብሔርም ይህን ኃጢአታችንን ዳግም እንደማያስበው ተስፋ ሰጥቶናል። ስለዚህ ኃጢአታችን የቀረልን መሆኑን በመገንዘብ በልባችን ውስጥ መረጋጋትና ሰላም ሊሰማን ይችላል። 

ኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ሕዝብ መካከለኛና አማላጅም ነው። በዚሁ መሠረት ኢየሱስ ለእኛ ብቸኛው አማላጅ የሆነውን ያክል፥ ቅዱሳን ወይም መላእክት አማላጆች ናቸው ብሎ መጽሐፍ ቅዱስ አያስተምርም። እኛ ኃጢአት በምንሠራበት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ የሚያማልድልን እርሱ ብቻ ነው። በሞቱ ወደ እግዚአብሔር መንገዱን የከፈተውና አዲሱን ኪዳን ያመጣው እርሱ ነው። በኢየሱስ የሚያምኑ ሁሉ ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሰውን መንገድ እንደሚከፍትላቸው ሊተማመኑ ይችላሉ። ስለዚህ በሌላ ሰው በኩል ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ መሞከር የለባቸውም። 

አንዳንዶች ኢየሱስ አማላጅ ነው ብለው ከተናገሩ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር እንዳልሆነ ትርጉም የሚያሰጥ አባባል ሊሆን ይችላል ብለው ይሠጋሉ። ስለሆነም እርሱ አማላጅ ከሆነ ተመላጅ ሊሆን አይችልም ብለው ይፈራሉ። በዚህም አምላክነቱን ይክዳሉ። ምንም እንኳን እውነታው በሰው አስተሳሰብ ሲታይ የሚቃረን መስሎ ቢታይም። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ኢየሱስ አማላጅም ተመላጅም መሆኑን በግልጽ ያስተምረናል (ዕብራውያን 7፡25፥ ሮሜ 8፡34)። 

ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ትናንትና ስንነጋገር ኢየሱስ አሁኑኑ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ሆኖ ሳለ እርሱ ፍጹም አምላክም ፍጹም ሰውም ነው ብለን ነበር። ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ሰብአዊነቱን አልተወውም። እርሱ ፍጹም አምላክ በመሆኑ ተመላጅ ነው። ስለሆነም በዚህ በተመላጅነቱ ‘ ምልጃዎችን ይቀበላል። ደግሞም ፍጹም ሰው በመሆኑ እርሱ የሚያማልድልን አማላጃችን ነው። ይህ እንግዲህ እኛን የማይገባን ትልቅ ምሥጢር ነው። | ይሁንና ኃጢአታችን ይቅር ስለ መባሉ፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ጸሎታችንን አድምጦ መልስ የሚሰጠን መሆኑን አውቀን የምንጽናናበትና ዋስታናም እንዳለን የምንገነዘብበት ብቸኛው መንገድ ነው። ስለሆነም። ኢየሱስ አማላጅም እንዲሁም ተመላጅም ነው።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading