Site icon የሕይወት እንጀራ

ሕፃናት በእርግጥ ኃጢአትን ለመሥራት ከደረሱበት ጊዜ በፊት የኃጢአት በደለኞች ይባላሉ? 

This entry is part 62 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ምንድን ነው? 

የክርስቶስ አስተምህሮ አስፈላጊነትና ድነት (ደኅንነት) 

የክርስቶስ መለኮታዊነት 

ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የሚገዛ ነው

ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነው 

ኢየሱስ በሁሉም ቦታ ይገኛል 

የኢየሱስ ባሕርይ አይለዋወጥም 

ኢየሱስ ሕይወትን ይሰጣል 

ኢየሱስ ተሰግዶለታል

ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ገልጾአል ፤ ኢየሱስ ይቅርታን መስጠት ይችላል 

ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሥልጣን አለው 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ዓይነት ባሕርይ እንዳለው ገለጸ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተቀብሏል 

የክርስቶስ አምላክነት በቆላስይስ 1፡15-20 

የኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊነት 

ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆኑን እንዴት እናውቃለን? 

የኢየሱስ ሰብአዊ ስሜቶች 

ኃጢአት አልባው የኢየሱስ ሰብአዊነት 

የኢየሱስ ከድንግል መወለድ 

ተሠገዎ በዮሐንስ 1 

ስለ ተሠገዎ በፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2 

ስለ ተሠገዎ በዕብራውያን ምዕራፍ 2 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኢቢዮናውያን 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኖስቲካዊነት

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ሞናርካዊነት ወይም ስባልዮሳዊነት 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ አርዮሳዊነት 

ተሠገዎ፥ ክፍል 2 

ክርስቶስ «አንድ ባሕርይ» አለው የሚለው አስተምህሮ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ተሠገዎ ያላት ምሥጢረ እምነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ስለ ክርስቶስ ባሕርይና አካል ያላቸው እምነት

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተገለጠባቸው መልኮችና ምሳሌዎች

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የያህዌ መልአክ (ቅድመ- ተሠገዎ የክርስቶስ መገለጥ)

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሲገለጥ (ቅድመ-ተሠገዎ)

በብሉይ ኪዳን የክርስቶስ ተምሳሌቶች

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

መሢሑ ኢየሱስ

መሢሑ እንደ ንጉሥ 

መሢሑ እንደ ካህን 

መሢሑ እንደ ነቢይ 

መሢሑ እንደ መድኅን 

ኢየሱስ የሰው ልጅ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ በብሉይና በወንጌላት ውስጥ 

የእግዚአብሔር ልጅ መለኮታዊ ነው። 

በጳውሎስና በዮሐንስ መጻሕፍት ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መገለጹ 

ኢየሱስ እንደ ጌታ 

የክርስቶስ መቀባት

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ምሳሌያችን 

ኢየሱስ እና የእግዚአብሔር መንግሥት

የኢየሱስ ሞት 

የክርስቶስ ከፍ ከፍ ማለት (ዕርገት)

የኢየሱስ ዕርገት (ከፍ ከፍ ማለት) 

ኢየሱስ አሁን ያለው ባሕሪና አገልግሎቱ

ክርስቶስ እንደ መካከለኛና እንደ አማላጅ 

የደኅንነት አስፈላጊነት- ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው?

ኃጢአት ከየት መጣ? 

የኃጢአት ውጤት፡- ሞት 

ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት በደልን ወርሰናል

ሁሉም ሰው የኃጢአት ተግባርን ፈጽሟል 

ኃጢአት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ 

ሕፃናት በእርግጥ ኃጢአትን ለመሥራት ከደረሱበት ጊዜ በፊት የኃጢአት በደለኞች ይባላሉ? 

አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን? 

ይቅርታ የማይደረግበት ኃጢአት ምንድን ነው? 

የደኅንነት ትርጉም፡- ከኃጢአትና ከኃጢአት ውጤቶች ሁሉ መዳን 

የእግዚአብሔር ቅዱስነት የኃጢአትን መሥዋዕት ይሻል፡- የብሉይ ኪዳን ምሳሌ 

ኢየሱስ ለኃጢአት ፍጹም የሆነ መሥዋዕት ሆነ፦ የአዲስ ኪዳን መፈጸም

የኢየሱስ ሞት የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቁጣ ለማርካት (ለማብረድ) የቀረበ መሥዋዕት ነው። 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀን 

ኢየሱስ የራሱ ሰዎች እንድንሆን ከኃጢአት ዋጀን

የኢየሱስ ሞት በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን አስገኝቷል- ክፍል አንድ 

ኢየሱስ በሞቱ በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን ተቀዳጅቷል – ክፍል ሁለት 

ወደ ደኅንነት መድረሻው መንገድ – የእግዚአብሔር ምርጫና የእግዚአብሔር ጥሪ 

እግዚአብሔር ለጥቂቶች ምሕረቱን ሊሰጥ ይመርጣል 

እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ የመረጣቸውን አበክሮ ይጠራቸዋል። 

ስለ እግዚአብሔር ምርጫና ለደኅንነት ስለሚያደርገው ጥሪ ጥያቄዎች 

የመዳኛ መንገድ፡- ንስሐ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ 

ወደ እግዚአብሔር መመለስ ወይም «መለወጥ» 

እምነት ከታዛዥነት ጋር እንዴት ይዛመዳል? 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 1 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 2 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር የመተባበር በረከቶች ምንድን ናቸው? 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ምን ማለት ነው? 

ጽድቅና ይቅርታ፥ ክፍል አንድ 

ጉዲፈቻ (የማደጎ ልጅ) 

ቅድስና 

የደኅንነት በረከቶች – እንከብራለን ሲባል ምን ማለት ነው?  

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫ እና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 1 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 2 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 3 

ደኅንነትን የመቀበል ጥያቄ፣ እምነትና ጥምቀት  

ቅዱስ ቁርባንን መቀበል፥ ደኅንነት ያስገኛል? 

የሚሞቱ ሕፃናት ይድናሉ? 

ለመሆኑ በመጨረሻው ሰዎች ሁሉ ይድናሉ ወይ? 

ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሳይሰሙ ሊድኑ ይችላሉ? 

የተወሰኑ ሰዎች ልጆች ኃጢአትን ለመሥራት እስካልደረሱ ድረስ የኃጢአት በደል አለባቸው አይባልም ይላሉ። ግን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ልጆች የኃጢአት በደል ምን ይላል? 

ጥያቄ፡- መዝ (51)፡5 አንብቡ። ሀ) ዳዊት ከመቼ ጀምሮ ኃጢአተኛ ተባለ? ላ) መዝ. (58)፡3 አንብብ። ለ) ክፉዎች ከመቼ ጀምረው ይሳሳታሉ? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 5፡14 አንብብ። ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባላፈረሱት ላይ ሳይቀር ምን ነግሦ ነበር?

\ጥያቄ፡- 1ኛ ሳሙ 12፡23 አንብብ። ጳዊት ከቤርሳቤሕ የወለደው ልጅ መች ሞተ? በዚያን ጊዜ ዳዊት የት እንደሚያገኘው ተናገረ? 

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተማርናቸው ትምህርቶች ውስጥ እንደተከታተልነው ሰዎች ሁሉ በኃጢአት ስለ ተወለዱ፥ በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች ናቸው። ዳዊትም ገና በእናቱ ማኅፀን ውስጥ እያለ ኃጢአተኛ እንደ ነበረ ይናገራል። እንዲሁም ክፉዎች ተለዩ፣ ደግሞም ከማኅፀን ጀምር ሳቱ ይላል። እንዲህም ማለት እግዚአብሔር ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ ኃጢአተኞች አድርጎ ይመለከታቸዋል ማለት ነው። በሮሜ ምዕራፍ 5 ውስጥ ከአዳም የተነሣ፥ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች እንደሆኑና የኃጢአት ቅጣት የሆነው ሞት እንደ ተበየነባቸው ያስረዳል። ሮሜ 5፡14 እንደ አዳም ሕግን በመተላለፍ ኃጢአት ያልሠሩት እንኳ ሳይቀሩ ክአዳም እስከ ሙሴ ባሉት ዘመናት የነበሩ ብዙ ሰዎች ሞተዋል ይላል። በአዳም ኃጢአት ምክንያት እነርሱም በደለኞች ስለሆኑ ሞቱ። አንዳንድ ሕፃናትም ስለሚሞቱ እነርሱም ቢሆኑ የአዳም ውርስ ኃጢአት ቅጣት እየተቀበሉ እንደሆነ መደምደም እንችላለን። ምንም እንኳን በእርግጥ ኃጢአት የፈጸሙ ሳይሆኑም፥ ከኃጢአት ጋር ስለ ተወለዱና ይህም በደል ስለሆነ ይሞታሉ። ምንም እንኳን ሕፃናት ኃጢአትን ለመሥራት ከመድረሳቸው በፊት በአዳም ምክንያት ኃጢአት አለባቸው ቢባልም፣ የሚሞቱ ሕፃናት ወደ ሲኦል ወይም ገሃነም ይወርዳሉ ማለትም አይደለም። ከቤርሳቤሕ የወለደው ልጁ በሞተ ጊዜ ዳዊት ተመልሶ ወደ ሕይወት እንደማይመጣና ከሞት በኋላ እንደሚያገኘው ገልቆአል (2ኛ ሳሙ. 12፡23)። ዳዊት ይህን ማለቱ አንድ ቀን እንደሚሞትና ወደ ሙታን ስፍራ እንደሚሄድ አይደለም። ነገር ን፥ “እኔም ወደ እርሱ ዘንድ እሄዳለሁ» አለ። ዳዊት ልጁን በእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚገናኘው ተስፋ ነበረው። ከዚህ በሕፃንነታቸው የሚሞቱ የአማኞች ልጆች ወደ መንግሥተ ሰማይ እንደሚሄዱ አሳብ ልናገኝ እንችላለን። ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ ሕፃናት ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ ይሄዳሉ ብሎ በግልጽ ባይነግረንም፥ ሕፃናት ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገቡ ይመስላል። ሆኖም ግን፣ ከአዳም በደል የተነሣ ሕፃናት ከኃጢአት ጋር ይወለዳሉ። ሕፃናት ሲሞቱ እግዚአብሔር የክርስቶስን ደም የማዳን ኃይል በመጠቀም ከበደላቸው አንጽቶ ከኃጢአት ዕዳ ይቤዣቸዋል። ሕፃናቱ ስለ ተጠመቁ ወይም ስለ ተገረዙ እግዚአብሔር አያድናቸውም። እንዲሁም ወላጆቻቸው መልካም ሥራ ስላደረጉ እግዚአብሔር አያድናቸውም። እግዚአብሔር የሚያድናቸው ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ለኃጢአታቸው ቤዛ ስለሆናቸውና በምሕረቱና በጸጋውም ነው።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ኃጢአት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ  አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን? 
Exit mobile version