የሕይወት እንጀራ

አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን? 

This entry is part 63 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

አስተምህሮ ምንድን ነው? 

የክርስቶስ አስተምህሮ አስፈላጊነትና ድነት (ደኅንነት) 

የክርስቶስ መለኮታዊነት 

ኢየሱስ ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የሚገዛ ነው

ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነው 

ኢየሱስ በሁሉም ቦታ ይገኛል 

የኢየሱስ ባሕርይ አይለዋወጥም 

ኢየሱስ ሕይወትን ይሰጣል 

ኢየሱስ ተሰግዶለታል

ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ገልጾአል ፤ ኢየሱስ ይቅርታን መስጠት ይችላል 

ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሥልጣን አለው 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ዓይነት ባሕርይ እንዳለው ገለጸ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ተቀብሏል 

የክርስቶስ አምላክነት በቆላስይስ 1፡15-20 

የኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊነት 

ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆኑን እንዴት እናውቃለን? 

የኢየሱስ ሰብአዊ ስሜቶች 

ኃጢአት አልባው የኢየሱስ ሰብአዊነት 

የኢየሱስ ከድንግል መወለድ 

ተሠገዎ በዮሐንስ 1 

ስለ ተሠገዎ በፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2 

ስለ ተሠገዎ በዕብራውያን ምዕራፍ 2 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኢቢዮናውያን 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኖስቲካዊነት

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ሞናርካዊነት ወይም ስባልዮሳዊነት 

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ አርዮሳዊነት 

ተሠገዎ፥ ክፍል 2 

ክርስቶስ «አንድ ባሕርይ» አለው የሚለው አስተምህሮ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ተሠገዎ ያላት ምሥጢረ እምነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ስለ ክርስቶስ ባሕርይና አካል ያላቸው እምነት

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተገለጠባቸው መልኮችና ምሳሌዎች

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የያህዌ መልአክ (ቅድመ- ተሠገዎ የክርስቶስ መገለጥ)

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሲገለጥ (ቅድመ-ተሠገዎ)

በብሉይ ኪዳን የክርስቶስ ተምሳሌቶች

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

መሢሑ ኢየሱስ

መሢሑ እንደ ንጉሥ 

መሢሑ እንደ ካህን 

መሢሑ እንደ ነቢይ 

መሢሑ እንደ መድኅን 

ኢየሱስ የሰው ልጅ 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ በብሉይና በወንጌላት ውስጥ 

የእግዚአብሔር ልጅ መለኮታዊ ነው። 

በጳውሎስና በዮሐንስ መጻሕፍት ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መገለጹ 

ኢየሱስ እንደ ጌታ 

የክርስቶስ መቀባት

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ምሳሌያችን 

ኢየሱስ እና የእግዚአብሔር መንግሥት

የኢየሱስ ሞት 

የክርስቶስ ከፍ ከፍ ማለት (ዕርገት)

የኢየሱስ ዕርገት (ከፍ ከፍ ማለት) 

ኢየሱስ አሁን ያለው ባሕሪና አገልግሎቱ

ክርስቶስ እንደ መካከለኛና እንደ አማላጅ 

የደኅንነት አስፈላጊነት- ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው?

ኃጢአት ከየት መጣ? 

የኃጢአት ውጤት፡- ሞት 

ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት በደልን ወርሰናል

ሁሉም ሰው የኃጢአት ተግባርን ፈጽሟል 

ኃጢአት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ 

ሕፃናት በእርግጥ ኃጢአትን ለመሥራት ከደረሱበት ጊዜ በፊት የኃጢአት በደለኞች ይባላሉ? 

አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን? 

ይቅርታ የማይደረግበት ኃጢአት ምንድን ነው? 

የደኅንነት ትርጉም፡- ከኃጢአትና ከኃጢአት ውጤቶች ሁሉ መዳን 

የእግዚአብሔር ቅዱስነት የኃጢአትን መሥዋዕት ይሻል፡- የብሉይ ኪዳን ምሳሌ 

ኢየሱስ ለኃጢአት ፍጹም የሆነ መሥዋዕት ሆነ፦ የአዲስ ኪዳን መፈጸም

የኢየሱስ ሞት የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቁጣ ለማርካት (ለማብረድ) የቀረበ መሥዋዕት ነው። 

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀን 

ኢየሱስ የራሱ ሰዎች እንድንሆን ከኃጢአት ዋጀን

የኢየሱስ ሞት በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን አስገኝቷል- ክፍል አንድ 

ኢየሱስ በሞቱ በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን ተቀዳጅቷል – ክፍል ሁለት 

ወደ ደኅንነት መድረሻው መንገድ – የእግዚአብሔር ምርጫና የእግዚአብሔር ጥሪ 

እግዚአብሔር ለጥቂቶች ምሕረቱን ሊሰጥ ይመርጣል 

እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ የመረጣቸውን አበክሮ ይጠራቸዋል። 

ስለ እግዚአብሔር ምርጫና ለደኅንነት ስለሚያደርገው ጥሪ ጥያቄዎች 

የመዳኛ መንገድ፡- ንስሐ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ 

ወደ እግዚአብሔር መመለስ ወይም «መለወጥ» 

እምነት ከታዛዥነት ጋር እንዴት ይዛመዳል? 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 1 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 2 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር የመተባበር በረከቶች ምንድን ናቸው? 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ምን ማለት ነው? 

ጽድቅና ይቅርታ፥ ክፍል አንድ 

ጉዲፈቻ (የማደጎ ልጅ) 

ቅድስና 

የደኅንነት በረከቶች – እንከብራለን ሲባል ምን ማለት ነው?  

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫ እና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 1 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 2 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 3 

ደኅንነትን የመቀበል ጥያቄ፣ እምነትና ጥምቀት  

ቅዱስ ቁርባንን መቀበል፥ ደኅንነት ያስገኛል? 

የሚሞቱ ሕፃናት ይድናሉ? 

ለመሆኑ በመጨረሻው ሰዎች ሁሉ ይድናሉ ወይ? 

ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሳይሰሙ ሊድኑ ይችላሉ? 

አንዳንድ ክርስቲያኖች ኃጢአትን የምር መጥፎ የሆኑና እምብዛም መጥፎ ያይደሉ በማለት ይከፋፍሏቸዋል። በዚሁ ሁኔታ አንዳንዶቹ ኃጢአቶች የእግዚአብሔር ካባድ ቅጣት እንደሚያስፈልጋቸው ሌች ደግሞ ይህን ያህል የማያስቀጡ አድርገው ይመለከቷቸዋል። ይህ ብቻ አይደለም፥ አንዳንደ ኃጢአቶች ደኅንነትን የሚያሳጡዋቸው ሆነው ሲታዩዋቸው፥ ሌሎች የኃጢአት ዓይነቶች ደግሞ ደኅንነትን የማያሳጡዋቸው መስለዉ ይታዩዋቸዋል። ይሁንና አንዳንድ ኃጢአቶች ከሌሎቹ ይልቅ የባሱ ናቸው? 

2.1 ኃጢአቶች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እኩል በደለኞች ያደርጉናል። 

ጥያቄ፡– ገላ 3፡10 እና ያዕ. 2፡10 እንብብ። ከትእዛዛቱ መካከል አንዱን እንኳን በማይታዘዙት ላይ ምን ደረሰባቸው? 

መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአቶች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እኩል በደለኞች እንደሚያደርጉን ያስተምረናል። አንድ ኃጢአት ምንም ያህል ትንሽ ቢሆንም የኃጢአትን ቅጣት ያመጣብናል። ገላ. 3፡10 ከሕጎች አንዱን ያፈረሰ ሰው የተረገመ ነው ይላል። ያዕ. 2፡10 ደግሞ ከሕግ ትእዛዛት አንዲቱን ያጎደለ መላውን ያፈረሰ በደለኛ ሆኖ ይቆጠራል ይላል። በዚህ አኳኋን ኃጢአት ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በደለኛ ያደርገናል። 

2.2 አንዳንድ ኃጢአቶች ከሌሎቹ ይልቅ ከእግዚአብሔርና ከሌሎችም ሰዎች ጋር ያሉንን ግንኙነቶች በበለጠ ይጎዱዋቸዋል። 

ጥያቄ፡- ሕዝ 8፡6 አንብብ። እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን ምን ታያለህ አለው?

ጥያቄ፡- ዮሐ 19፡11 አንብብ። ኢየሱስ ለጴንጤናዊው ጲላጦስ አሳልፈው ስለ ሰጡት ምን አለ? 

ጥያቄ፡- ማቴ. 23፡23 አንብብ። ኢየሱስ ፍርድን፥ ምሕረትን እና ታማኝነትን ምን ብሎ ጠራ? 

ጥያቄ፡- ሉቃስ 10፡10 አንብብ። የትኞቹ ከተሞች የከፋ ቅጣትን ይቀበላሉ? ለምን? 

ጥያቄ፡- ሉቃስ 12፡42-48 አንብብ። ሀ) የጌታውን ፈቃድ እያወቀ በማይፈጽም አገልጋይ ላይ ምን ይደርስበታል? ለ) የጌታውን ፈቃድ በሚያውቀውና በሚያደርገው እገልጋይ ላይላ ምን ይደርስበታል? 

ጥያቄ፡- ያዕ. 3፡1 አንብብ። የእግዚአብሔርን ቃል በሚያስተምሩት ላይ ምን ይደርሳል? 

ኃጢአቶች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በደለኛች የሚያደርጉን ሲሆን፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስንመለከት አንዳንድ ኃጢአቶች ከሌሎቹ ብሰው የሚታዩበት ሁኔታ ያለ ይመስላል። እግዚአብሔር ለሕዝቅኤል፥ ካየው የበለጠ እጅግ አስነዋሪ የሆነ ነገር ገና እንደሚያይ ነግሮታል (ሕዝ. 8፡6)። ኢየሱስም ለጴንጤናዊው ጲላጦስ አሳልፈው ስለ ሰጡት ሲናገር፥ አሳልፈው የሰጡት ከጲላጦስ የባለ ኃጢአት እንደሚያደርጉ አስጠንቅቆአቸዋል (ዮሐ 19፡1)። እንዲሁም፥ ከሕግ ውስጥ ፍርድ፥ ምሕረትና ታማኝነት ዋና ቁም ነገሮች ናቸው ብሏል (ማቴ. 23፡23)። በዚህም ኢየሱስ፥ አንዳንድ ኃጢአቶችን ከሌሎች የበለጠ የሚከብዱ መሆናቸውን ሊያስገነዝበን አንዳንዶቹ የሕግ ትእዛዛትም ከሌሎቹ የተለዩ ናቸው። በሉቃስ 10፡10-5 ውስጥ እንደተጻፈው የቅፍርናሆምንና የቤተ ሳይዳን ከተሞች ከሰዶም፥ ከጢሮስና ከሊዶን ከተሞች የበለጠ ቅጣት እንደሚደርስባቸው ኢየሱስ ፈርዶባቸዋል። የበለጠ ቅጣትን የሚቀበሉበትም ምክንያት ከሌሎቹ ከተሞች ይልቅ እነዚህኞቹ በኢየሱስና በሠራቸው ተአምራት ውስጥ እግዚአብሔርን በላቀ መገለጥ ስላዩት ነው። ከእግዚአብሔር ታላቅ መገለጥ ሲመጣ እያዩ ኃጢአት የሚሠሩ ሰዎች በአነስተኛ መገለጥ ውስጥ ሆነው ኃጢአት ከሚሠሩት የበለጠ በደል ይፈጽማሉ። በሉቃስ 12፡42-48 ውስጥ ኢየሱስ በምሳሌ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እያወቁ የማያደርጉት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ካለማወቃቸው የተነሣ ከማያደርጉት የበለጠ ቅጣት እንደሚደርስባቸው ገልጾአል። እያወቁ በድፍረት ኃጢአት የሚሠሩ ሰዎች ምንም እንኳን ኃጢአት እንደ ፈጸሙ ቢገነዘቡም የባሰ ኃጢአት ያደርጋሉ። 

እንደዚሁም አንዳንድ ኃጢአቶች የእግዚአብሔርን ስም የሚያጎድፉ ወይም ራሳችንና ሌሎች አማኞችን ጭምር የሚጎዱ ከሆኑ ከሌሎች ይልቅ ክብደት የሚሰጣቸው ወይም የባሱ ሆነው የሚቆጠሩ ይመስላሉ። 

ጥያቄ፡- አንዳንድ ኃጢአቶች በእግዚአብሔር፥ በራሳችንና በሌሎች ሰዎች ላይ ትልቅ ጉዳትን እንዴት እንደሚያመጡ ምሳሌ ጠቅሳችሁ ጻፉ። 

አንዳንድ የኃጢአት ዓይነቶች ከሌሎች በበለጠ እግዚአብሔርንና ስሙን፥ እኛንና ሌሎችን ይጎዳሉ። ለምሳሌ ያህል፥ አንድ ሰው የጎረቤቱን መኪና ቢመኝ የእርሱ ያልሆነውን ተመኝቷል እና በደለኛ ይሆናል። ነገር ግን ያንን መኪና ቢሰርቅ የባሰ ኃጢአት ይሠራል። ምክንያቱም በእግዚአብሔር ስም ላይ ትልቁ ሐፍረትን በጎረቤቱም ላይ ጉዳትን ያደርሳልና ነው። እንዲሁም አንድ ሰው ሚስቱ ያልሆነችውን ሴት ለግብረ ሥጋ ቢመኛት፥ ኃጢአት ስለሚሆንበት በእግዚአብሔር ዘንድ በደለኛ ይሆናል። ነገር ግን ከሴትዮዋ ጋር የተረጋገጠ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ቢያደርግ፥ የባሰ ኃጢአት ያደርጋል። ምክንያቱም እርስዋን አሳስቶ ኃጢአት እንድትሠራ ከማድረጉም በላይ፥ የእግዚአብሔርንም ስም የሚያረክስ ተግባር ፈጽሟልና ነው። አግብቶ ከሆነ ደግሞ ሚስቱን፥ ልጆቹንና ትዳሩን ይጎዳል። ሴትዮዋም ያገባች ከሆነች ደግሞ ባለቤትዋን፣ ልጆቿንና ጋብቻዋን ትጎዳለች። እርሱም ሆነ ሴትዮዋ ሁለቱም ያላገቡ ከሆኑ ይህ ተግባር የወደፊት የጋብቻ ዕድላቸውን ያበላሻል። ጳውሎስ የግብረ ሥጋ ኃጢአት የሰውን አካል የሚያረክስ ከመሆኑም በላይ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን አንድነት የሚያበላሽ መሆኑን ሰፋ አድርጎ አስተምሯል (1ኛ ቆሮ. 6፡15-18)። ስለዚህ አንዳንዶቹ ኃጢአቶች የእግዚአብሔርን ስም፥ ኃጢአት የሚሠራውን ሰውና ሌሎች ሰዎችንም ስለሚጎዱ ከሌሎች ኃጢአቶች የባሱ ናቸው። 

በተጨማሪም፥ እግዚአብሔር በተለይ ክርስቲያን መሪዎችን በኃጢአታቸው ይጠይቃቸዋል። ያዕቆብ 3፡1 የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምሩ መምህራን የባሰ ፍርድ እንደሚቀበሉ ያስገነዝባል። አንድ ክርስቲያን የሆነ መሪ ኃጢአት በሚሠራበት ጊዜ በተለይ የእግዚአብሔር ስም ይሰደባል። ስለዚህ የክርስቲያን መሪ ኃጢአት ከሌላው ክርስቲያን ኃጢአት የበለጠ ነው። ሁሉም ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት በደለኛ ያደርገናል። ሁሉም ኃጢአት ደግሞ ይቅር ሊባል ይችላል። አንዳንድ ኃጢአቶችን ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚያስጠይቁ እያወቁ ይፈጽሟቸዋል። ስለሆነም አንዳንዶቹ ኃጢአቶች በእግዚአብሔር፥ በራሳችንና በሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳትን ያደርሳሉ። በተለይም በክርስቲያን መሪዎች የሚፈጸሙ ኃጢአቶች በእግዚአብሔር ስም ላይ ኀፍረትን ያመጣሉ። እግዚአብሔር እነዚህን ኃጢአቶች ከሌሎች የባሱ ሆነው ስለሚያያቸው በዚያኑ መጠን የባሰ ቅጣት ይሰጣል።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ሕፃናት በእርግጥ ኃጢአትን ለመሥራት ከደረሱበት ጊዜ በፊት የኃጢአት በደለኞች ይባላሉ?  ይቅርታ የማይደረግበት ኃጢአት ምንድን ነው? 

የጌታ ጸጋ ከእርስዎ ጋር ይሁን፤ ሀሳብዎን ለመስማት ዝግጁ ነን።

Discover more from የሕይወት እንጀራ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading