“ኢየሱስ አልተሰቀልም፡፡”

ሙስሊሞች የአዲስ ኪዳንን ትምህርት ላለመቀበል እንደ ምክንያት ከሚያነሷቸው ነገሮች መካከል በቀዳሚ ሥፍራ ላይ የሚቀመጠው የኢየሱስ የስቅለት ታሪክ ነው፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የመሞቱን እውነታ ለመቀበል ግትርነት ይታይባቸዋል፤ ስለ ስቅለቱ የሚነገርው ታሪክ ሁሉ፣ ክርስቲያኖችን ለማታለል ሆን ተብሎ የተነዛ የሃሰት ወሬ ነው ሲሉም ይደመጣሉ፡፡ በርካታዎቹ ሙስሊሞች ከዚህ አልፈው በመሄድ፣ ቁርአን ከተገለጠበት ምክንያቶች አንዱ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሞቷል የሚለውን የሃሰት ትምህርት ለማረም ነው የሚል ሙግት ያቀርባሉ፡፡

የስቅላቱ ታረክ ‹‹ማታለያ›› ከሆነ፣ እና ቁርአን ደግሞ ይህንን ‹‹የተሳሳተ›› ትምህርተ- ሃይማኖት ለማረም የመጣ ከሆነ፣ በውስጡ ስለ ሙታን ትንሳኤ እና ስለ ፍርድ ቀን በርካታ ጥቅሶችን እንዲያካትት መጠበቅና እንዲሁም ‹‹ኢየሱስ በመስቀል ላይ አልሞተም፣›› የሚሉ በርካታ ጥቅሶችን በውስጡ አካቶ እንዲይዝ መጠበቅ ምክንያታዊንት ነው! እውነታው ግን ይህ አይደለም፡፡ ቁርአን በውስጡ 6000 ጥቅሶችን አካቶ ይዟል፡፡ የመጣበት አላማ ይህን ‹‹የተሳሳተ›› የተባለለትን ትምህርት ለማረም ከሆነ ‹‹ኢየሱስ በመስቀል ላይ አልሞተም››፣ የሚለው አሳብ ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ቢያንስ 5 እጁን (ፐርሰንት) ያህል ሊሸፍን አይገባ ይሆን? 5 እጁ በዛ ከተባለ ደግሞ 4 እጅ ያህል ጥቅሶች ሊያካትት በተገባ ነበር፡፡ ይህ ማለት 60 ጥቅሶች ብቻ ማለት ነው፡፡ ወይም ከ 6000 ጥቅሶች ውስጥ ‹‹ኢየሱስ በመስቀል ላይ አልሞተም፣›› የሚል ቢያንስ 10 ጥቅሶች መጠበቅ አይገባን ይሆን? በተግባር ይህ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ይህንን ብዥታ በታደገው ነበር፡፡

ነገር ግን በሚያስገርም ሁኔታ! ከእነዚህ 6000 የቁርአን ጥቅሶች ውስጥ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስላለመሞቱ ወይም ኢየሱስ ስላለመሰቀሉ የሚናገር አንድም ጥቅስ የለም፡፡ አንድም የለም!  ስለ ስቅለቱ የሚያወራ ግን አንድ ክፍል በቁርአን ውስጥ እናገኛለን፤ እርሱም እንደ ሚከተለው ይነበባል፡-

  • እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን [የማሪያምን] ልጅ አልመሲሕ [መሲህ] ዒሳን [ኢየሱስን] ገደልን በማለታቸዉም (ረገምናቸው)፤ አልገደሉትም፤ አልሰቀሉትምም፤ ግን ለነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፤ እነዚያም በርሱ ነገር የተለያዩት ከርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸዉ፤ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፤ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡

ሱረቱ አል-ኒሳእ (4)፡157

That they (the Jews) said (in boast) “We killed Christ Jesus, the son of Mary, the Apostle of God”-But they killed him not, nor crucified him, but so it was made to appear to them, and those who differ therein are full of doubts, with no (certain) knowledge, but only conjecture to follow, for of a surety they killed him not. Nay, God raised him up unto Himself; and God is exalted in power, Wise.

ይህንን ክፍል ልብ ይበሉ፡፡ የክፍሉ ርዕሰ-ጉዳይ (subject) ኢየሱስ ሳይሆን አይሁድ ናቸው፡፡ ክፍሉ በግልጽ የሚናገረው አይሁድ ኢየሱስን ስላለመግደላቸው ወይም ስላለመስቀላቸው ነው፡፡ ይህ ክፍል አይሁድ ኢየሱስን አልገደሉትም ይላል እንጂ ኢየሱስ በመስቀል ላይ አልሞተም አይልም፡፡ ልብ ይበሉ፣ በቁርአን ውስጥ ስለ ስቅለቱ የሚያወራው ክፍል ይህ ብቻ ነው፡፡

‹‹(የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ›› የሚለው ዐረፍተ ነገር ግልጽ አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ አሳብ አመንጪዎች ይህን አሳብ በመውሰድ ‹‹ኢየሱስ ከስቅለት የዳነበትን መንገድ›› እንዲመራመሩ መንገድ ከፍቶላቸዋል፡፡ አንዱና በሰፊው ተቀባይነት ያገኘው ተመራጭ ወግ፣ እግዚአብሔር የከሃዲዉ ይሁዳን መልክ ቀይሮ ኢየሱስን እንዲመስል አደረገው፤ ስለዚህም በመስቀል ላይ የተቸነከረው ይሁዳ እንጂ ኢየሱስ አልነበርም የሚል ነው፡፡ ነገር ግን ይህንን ታሪክ የሚያስረዳ በቁርአን ውስጥ የሚገኝ ምንም ጥቅስ የለም፡፡ ይህ አይነቱ ታሪክ የመነጨው ታላላቅ ከሆኑ ታሪክ ተናጋሪዎች (ተራኪዎች) ህሊና ውስጥ ብቻ ነው!

ይህ ክፍል በሚከተለው መንገድ ሊብራራ ይችላል፡፡ አይሁድ በኢየሱስ ላይ አሴሩ፤ ለሕይወቱ ፍጻሜ ያበጁለት መስሏቸው ተኩራሩ፡፡ ሴራቸው ተሳክቶ የኢየሱስ አገልግሎት እስከ ወዲያኛው ያከተመለትም መሰለ፡፡ ነገር ግን ጉዳዩ በእግዚአብሔር ዘንድ አስቀድሞ የታሰበበት ነበርና ኢየሱስ ቢሞትም እርሱ መሲሁ እንደሆነ ለአይሁድ ያረጋግጥላቸው ዘንድ አስነሳው፡፡ እርሱ በዓለም ላይ አዳኝና ገዢ እንዲሆን በእግዚአብሑር የተቀባ ነውና፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር፣ ኢየሱስ በመስቀል ላይ መከራን የተቀበለው በእግዚአብሔር ፈቃድና አጀንዳ መሠረት ነበር፡፡ የኢየሱስ ሞት፣ በሰው ልጅ ያልተቋረጠ አመፅና ኃጢአት ምክንያት የተሰቃየውን የእግዚአብሔርን ፍቅር ይገልጻል፡፡ የኢየሱስ ሞት ምላሌው የነበሩትን የእንስሳት መሥዋዕትነት አቁሟል፤ እርሱ የዚህ ስርዐት ፍፃሜ ነውና፡፡ ለዚህ ነው ኢየሱስ ‹‹የእግዚአብሔር በግ፣›› የተባለው፡፡ ራሱን ካሳ አድርጎ በመስቀል ላይ የከፈለው ሞት የኃጢአት ይቅርታንና ቤዛነትን አስገኝቶልናል፡፡ ይህም ወደ እግዚአብሔር መገኘት እንድንደርስ አድርጎናል፡፡ የሰውን ዘር ወደ እግዚአብሔር መገኘት ሊያመራ የሚችለው አራት እግር ባላቸው የእንስሳት መሥዋዕት ሳይሆን በኢየሱስ መስዋእትነት ነው! የእንስሳት መሥዋዕት፣ ከእነርሱ ይልቅ ንፁ ለሆነውና ሊመጣ ላለው፣ እግዚአብሔር ላዘጋጀው እዉነተኛ መሥዋዕት ምሳሌ ነበር፡፡

እንግዲህ ይህ ሁሉ የአይሁድ እቅድ ሳይሆን የእግዚአብሔር አጀንዳ ነበር፡፡ ኢየሱስን በመስቀል ላይ ያኖሩት አይሁድ አይደሉም፣ እግዚአብሔር እንጂ፤ ይህም ለሰዎች ሁሉ የገለጠውን የድኅነት/የመዳን መንገድ ያስታውቅ ዘንድ ነው፡፡ መስቀሉ የሰይጣንን ሴራ ለመሻር ፈጣሪያችን የተጠቀመበት አጀንዳ እንደ ነበር ዓለም ሁሉ ያውቅ ዘንድ እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን መካከል አስነሳው፣ ወደ ሰማይም አረገ፣ በዙፋኑም ቀኝ አስቀመጠው!

ቁርአን የኢየሱስን ሞት እንዲህ ሲል ይገልጣል፡-

  • ሰላምም በኔ ላይ ነው በተወለድሁ ቀን በምሞትበትም ቀን ሕያው ሆኜ በምቀሰቀስበትም ቀን፤

ሱረቱ መርየም (19)፡33

So peace is on me the day I was born, the day that I die, and the day that I shall be raised up to life (again).

በርካታ ሙስሊሞች የኢየሱስን ልደትና ወደ ሰማይ ማረግ ይቀበላሉ፡፡ ነገር ግን በነዚህ በሁለቱ መካከል ያለውን የስቅላቱንና ሞቱን ጉዳይ መቀበል አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል፡፡ በቀረበው ጥቅስ አንጻር ሲታይ የኢየሱስን ሞት ማመን ሊከብድ የማይገባ ነገር ቢሆንም አሁንም ድረስ አስቸጋሪ ርዕሰ ጉዳይ መሆኑ ቀጥሏል፡፡ ይህ ጥቅስ በመጽሐፍ ቅዱስ ከቀረበው የኢየሱስ መወለድ፣ መሞትና መነሳት፣ ወደ ሰማይም ማረግ ትምህርት ጋር በእርግጥ ይስማማል፡፡ ነገር ግን፣ በሚያሳዝን ሁኔታ ቁርአን ኢየሱስ በምን አይነት ሁኔታ እንደ ሞተ አይተርክም፡፡ እርግጥ ነው ይህ ጉዳይ ትልቅ ጥያቄ እንዲነሳ ይጋብዛል፤ እንዲህ አይነቱን ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ ሲገጥም ደግሞ ቁርአኑ የሚከተለውን መመሪያ ይሰጣል፡-

  • ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን [ክርስቲያኖችን] ጠይቅ፤ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፤ ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን፡፡

ሱረቱ ዩኑስ (10)፡94

If thou wert in doubt as to what We have revealed unto thee, then ask those who have been reading the Book from before thee (ask the people of the Book).

የመጽሐፉ ሰዎች/ክርስቲያኖች ስለ ኢየሱስ አሟሟት ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ምክንቱም መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ጉዳይ በግልጽ ያስቀምጣልና፡፡ የሚከተሉት ጥቅሶች በጠያቂው ጭንቅላት ውስጥ ላሉት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ፡-

  • ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሊወጣ ሳለ፣ በመንገድ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ብቻቸውን ወደ እርሱ አቅርቦ፡- እነሆ፣ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፣ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፣ ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፣ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል አላቸው። 

ማቴዎስ 20፡17-19 

  • የእሥራኤል ሰዎች ሆይ፣ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤ እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት። እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፣ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና። 

የሐዋሪያት ሥራ 2፡22-24

  • ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ከአብ ተቀብሎ ይህን እናንተ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው። 

የሐዋሪያት ሥራ 2፡32፣33

Leave a Reply

%d bloggers like this: