ወደ ዕብራውያን

የኢየሱስ ተከታዮች እንደ መሆናችን እንዴት መመላለስ እንዳለብን (ዕብ.13፡1-25)

ጸሐፊው አይሁዳውያን ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን የሚያስከብር ሕይወት ለመኖር ሊያደርጉ የሚገዷቸውን አንዳንድ ነጥቦች በመዘርዘር መልእክቱን ያጠቃልላል። እነዚህ ትምህርቶች ሩጫችንን በሚገባ እንዳንሮጥ የሚከተሉት መሰናክሎች ወይም ኃጢአቶች በመንፈሳዊ ሩጫችን ውስጥ መኖር አለመኖራቸውን ለማረጋገጥ ደግመን ደጋግመን የምንመለከታቸው ነገሮች ናቸው። ሀ) በክርስቶስ ወንድሞቻችሁና እኅቶቻችሁን ውደዱ። ለ) ምንም ያህል ስደት ቢበዛም፥ እማኞችን በእንግድነት ለመቀበል ትጉ። ሐ) በኢየሱስ በማመናቸው ምክንያት የታሰሩትን ወገኖች አትርሷቸው። …

የኢየሱስ ተከታዮች እንደ መሆናችን እንዴት መመላለስ እንዳለብን (ዕብ.13፡1-25) Read More »

እግዚአብሔርን ስላለመታዘዝ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ (ዕብ. 12፡14-29)

ጸሐፊው ስለ መንፈሳዊ ሩጫችን ከገለጸ በኋላ፥ ለሩጫው ብቁ እንዳንሆን የሚያደርጉትን ነገሮች እንደሚከተለው ይዘረዝራል፡- ሀ) ቅድስናችንን ማጣት (ባለማቋረጥ በኃጢአት ውስጥ መኖር)። ይህም እግዚአብሔርን እንዳናይ ይከለክለናል። ለ) በሕይወታችን ውስጥ ባሉት ነገሮች ወይም በጎዱን ሰዎች መማረር፡፡ ሐ) አሁን ሕይወታችንን በምናሻሽልበት ሁኔታ ላይ በማተኮር መንፈሳዊ ውርላችንን መሽጥ። ይህም ኤሳው መንፈሳዊ ብኩርናውን ለምግብ እንደ ሸጠው ማለት ነው። ለሰማያዊ በረከቶች እንደ …

እግዚአብሔርን ስላለመታዘዝ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ (ዕብ. 12፡14-29) Read More »

ክርስቶስን መከተል ማለት በመንፈሳዊ ሩጫችን መጽናት ማለት ነው (ዕብ. 12፡1-13)

አብዛኞቻችን የምንማረው ሌሎች ሰዎችን፥ በተለይም እንደ መልካም ምሳሌዎች የምንጠራቸውን ግለሰቦች በመመልከት ነው። አሠራራቸውን፥ አኗኗራቸውን፥ ልጆቻቸውን የሚያሳድጉበት ሁኔታ፥ ወዘተ.. በመመልከት እኛም ሕይወታችንን እንዴት መምራት እንዳለብን እንረዳለን። ጸሐፊው ዕብራውያን 11ን የጻፈው እንዴት የእምነትን ሕይወት መኖር እንዳለብን ለማሳየት ነው። በመቀጠልም ጸሐፊው እግዚአብሔርን ለሚያስከብር አኗኗር አቻ የሌለውን የክርስቶስ ሕይወት ምሳሌነት ያቀርብልናል። ጸሐፊው ይህንን ሕይወት በስታድዮም ውስጥ የሚካሄደውን የሩጫ ውድድር …

ክርስቶስን መከተል ማለት በመንፈሳዊ ሩጫችን መጽናት ማለት ነው (ዕብ. 12፡1-13) Read More »

ክርስቶስን ለመከተል እምነት ወሳኝ ነው (ዕብ. 11፡1-39)

ብዙውን ጊዜ በክርስቶስ ማመን ምን ማለት እንደሆነ ሰዎች የተሳሳተ አመለካከት አላቸው። ብዙዎቻችን ስለ እውነታው ትክክለኛነት በሚያስረዳው እእምሮአዊ እውቀት ላይ እናተኩራለን። ስለሆነም አንድ ሰው በክርስቶስ እንዲያምን በምንጠይቅበት ጊዜ፥ «ክርስቶስ ለኃጢአትህ እንደ ሞተ እመን» ማለታችን ነው። ነገር ግን በክርስቶስ ማመን እርሱ በሚፈልገው መንገድ መጓዝን እንደሚጠይቅ አንገነዘብም። ከዚህም የተነሣ፥ ብዙ ሰዎች በክርስቶስ እናምናለን ቢሉም፥ ሕይወታቸው ግን አይለወጥም። ብዙ …

ክርስቶስን ለመከተል እምነት ወሳኝ ነው (ዕብ. 11፡1-39) Read More »

እስከ መጨረሻው ጸንቶ ስለ መገኘት የቀረበ ጥሪ (ዕብ. 10፡19–39)

የዕብራውያን ጸሐፊ ይህንን የመጨረሻ ክፍል የሚጀምረው ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንዳለብን፥ ይህ ካልሆነ ግን ከእምነት ርቀን በመቅበዝበዝ የእግዚአብሔርን ፍርድ እንደምንቀበል በማስጠንቀቅ ነው። ሀ. በግላዊ እና በቅርብ ግንኙነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አለብን። የክርስቶስ ሞት ኃጢአተኛ ሰዎችን ከተቀደሰው አምላክ የሚለየውን መጋረጃ ስላስወገደው እና ክርስቶስም አሁን በሰማይ በሊቀ ካህንነት እያገለገለ ስለሆነ፥ በጸሎት እግዚአብሔር ወደሚገኝበት ስፍራ የመቅረብ ድፍረት አለን። እግዚአብሔር …

እስከ መጨረሻው ጸንቶ ስለ መገኘት የቀረበ ጥሪ (ዕብ. 10፡19–39) Read More »

የክርስቶስ መሥዋዕት ከእንስሳት መሥዋዕቶች ይበልጣል (ዕብ. 9፡13-10፡18)

እስከአሁን ጸሐፊው ክርስቶስ የሚሻል ሊቀ ካህናት የእውነተኛ አምልኮ መሪ እንዲሁም ለምትበልጥ ሰማያዊ ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግል መሆኑን ገልጾአል። በመቀጠልም፥ የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ የክርስቶስ መሥዋዕት በምድራዊ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ከቀረቡት መሥዋዕቶች ሁሉ እንደሚበልጥ ያስረዳል። ጸሐፊው አይሁዳውያን ሊቃነ ካህናት ካቀረቧቸው መሥዋዕቶች የክርስቶስ መሥዋዕት ምን ያህል እንደሚበልጥ ለማሳየት የሚከተሉትን እውነቶች ገልጾአል፡ ሀ. ክርስቶስ እራሱን ስለ ሠዋና ሊቃነ ካህናት …

የክርስቶስ መሥዋዕት ከእንስሳት መሥዋዕቶች ይበልጣል (ዕብ. 9፡13-10፡18) Read More »

ክርስቶስ አገልግሎቱን የሚሰጠው ከመገናኛው ድንኳን በምትበልጠው ከሰማይቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ ነው (ዕብ. 9፡1-12)

የብሉይ ኪዳን የአምልኮ ሥርዓት በሚከተሉት ነገሮች ላይ የተመሠረተ ነበር። ሀ) በእግዚአብሔርና በእስራኤል መካከል የተደረገ ብሉይ ኪዳን (ስምምነት)፥ ለ) አምልኮን የሚመራ ሊቀ ካህናት፥ ሐ) ኃጢአትን የሚሸፍኑ የእንስሳት መሥዋዕቶች፥ እና መ) አምልኮ የሚካሄድበት የመገናኛ ድንኳንና በኋላም ቤተ መቅደስ ናቸው። የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ክርስቶስ ከእነዚህ ሁሉ የብሉይ ኪዳን የአምልኮ ነገሮች እንደሚበልጥና እነርሱንም እንደሚተካቸው ያስረዳል። ክርስቶስ ከአሮን የዘር ሐረግ …

ክርስቶስ አገልግሎቱን የሚሰጠው ከመገናኛው ድንኳን በምትበልጠው ከሰማይቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ ነው (ዕብ. 9፡1-12) Read More »

ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት (ዕብ 8፡1-13)

ጸሐፊው መልእክቱን ካቀረበባቸው ልዩ መንገዶች አንዱ አንድን አዲስ አሳብ ካቀረበ በኋላ መለስ ብሎ በዝርዝር ማቅረቡ ነው። ስለ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት በዝርዝር ከመጻፉ በፊት ጸሐፊው በብዙ ምዕራፎች ውስጥ ክርስቶስ ሊቀ ካህናት መሆኑን ገልጾአል (ዕብ. 2፡17-18፤ 4፡14-16)። በዕብራውያን 8፡1-6 ደግሞ ሁለት አዳዲስ አሳቦችን ያቀርብልናል። እነዚህንም ወደ በኋላ ዘርዘር አድርጎ ያብራራቸዋል። ሀ) ክርስቶስ ሊቀ ካህናት እንደ መሆኑ፥ በኢየሩሳሌም …

ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት (ዕብ 8፡1-13) Read More »

የክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ከአሮን ሊቀ ካህንነት ይበልጣል (ዕብ. 7፡1-28)

የዕብራውያን መልእክት የተጻፈው በክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት ትተው ወደ ቀድሞው ኃይማኖታቸው (ይሁዲነት) ለመመለስ ለሚያስቡ ሰዎች ነው። ስደትን ከመፍራታቸው የተነሣ እምነታቸውን ለመካድ በማሰብ ላይ ነበሩ። ምንም እንኳን ቀደም ሲል ስደት የደረሰባቸው ቢሆንም፥ በዚህ ጊዜ በተለይም ከይሁዳውያን ወገኖቻቸው ተጨማሪ ስደት ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም። እንዲሁም እነዚህ አማኞች ክርስቶስ ብቸኛው የድነት (ደኅንነት) መንገድ መሆኑን መጠራጠር ጀምረው ነበር። በብሉይ ኪዳን …

የክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ከአሮን ሊቀ ካህንነት ይበልጣል (ዕብ. 7፡1-28) Read More »

በእምነት ስላለመጽናት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ (ዕብ. 5፡11-6፡20)

ይህ ራስን ለእግዚአብሔር ለማስገዛትና ለመታዘዝ ትምህርት ጸሐፊው እንደገና ቆም ብሎ በክርስቶስ ላይ የነበራቸውን እምነት ለመተው እያሰቡ ላሉት አይሁዳውያን ክርስቲያኖች ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ እንዲሰነዝር ገፋፋው። ይህ በዕብራውያን መልእክት ውስጥ ላሉት የማስጠንቀቂያ ምንባቦች ሁሉ ረጅሙ ሲሆን፥ በአራት ዐበይት ክፍሎች ሊከፈል ይችላል። ሀ) ጸሐፊው በዕብራውያን 5፡11-14 አይሁዳውያን ክርስቲያኖች በእምነታቸው ባለማደጋቸው ማዘኑን ይገልጻል። በክርስትና እምነታቸው የቆዩ በመሆናቸው የክርስትናን መሠረታዊ …

በእምነት ስላለመጽናት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ (ዕብ. 5፡11-6፡20) Read More »