በመንፈስ መመላለስ የሚገኝ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ (ገላ. 5፡16-6፡18)።
ከብሉይና አዲስ ኪዳን አስደናቂ ልዩነቶች አንዱ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሕይወት ውስጥ የሚጫወተው ሚና ነው። በብሉይ ኪዳን፥ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት የተወሰኑ መሪዎች የመሪነትና ጠላቶቻቸውን የማሸነፍ ተግባር እንዲያከናውኑ የሚያስችላቸው የእግዚአብሔር ኃይል ነበር። ስለሆነም፥ መንፈስ ቅዱስ ለጥቂት ሰዎች የሚሰጥ ሲሆን፥ አንዳንድ ጊዜ ከኃጢአት ወይም ከአገልግሎታቸው ፍጻሜ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ይለያቸው ነበር። በአዲስ ኪዳን ግን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለልጆቹ …