የሉቃስ ወንጌል

የኢየሱስ ትንሣኤና ዕርገት (ሉቃስ 24፡1-53)

የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) የኢየሱስ ትንሣኤ ወሳኝ እንደሆነ የምታስበው ለምንድን ነው? ለ) 1ኛ ቆሮ. 5፡12-32 አንብብ። ጳውሎስ ትንሣኤ አስፈላጊ ነው የሚለው ለምንድን ነው? ሠ) በትንሣኤው ላይ ብዙ ትኩረት እየሰጠን ትንሣኤውን እምብዛም የማናነሣው ለምንድን ነው? ከታሪክ ምሑሩ አመለካከት አንጻር፣ የኢየሱስ ትንሣኤ በታሪክ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ቀደም ሲል ሰዎች በመስቀል ላይ ሲሞቱ ኖረዋል። ከእነዚህም አንዳንዶቹ የእግዚአብሔር …

የኢየሱስ ትንሣኤና ዕርገት (ሉቃስ 24፡1-53) Read More »

ሉቃስ 22፡39-23፡56

እግዚአብሔር ከመስቀሉ እንዲያድነው ኢየሱስ ጸለየ (ሉቃስ 22፡39-46) ሉቃስ ብዙውን ጊዜ የኢየሱስን ፍጹም ሰው መሆን አጉልቶ ያሳያል። ኢየሱስ መስቀሉን የተሸከመው ኃይሉን ሁሉ እንደተላበሰ አምላክ ሳይሆን፤ በሁላችንም ላይ በሚያንዣብብ የፍርሃት ስሜት ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርት በዘመናት ሁሉ በኢየሱስ በማመናቸው ምክንያት ለሞት በሚዳረጉበት ጊዜ ሁሉ ሲያስጨንቃቸው ይኖራል። ስለሆነም ፍርሃት ተፈጥሯዊ የሰው ልጆች ስሜት ነው። ዋናው ነገር ፍርሃትን የምንቋቋምበት መንገድ …

ሉቃስ 22፡39-23፡56 Read More »

ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የፋሲካ ምግብን በላ (ሉቃስ 22፡1-38)

ሀ. ሰይጣን ኢየሱስን አሳልፎ በሚሰጠው በይሁዳ ልብ ውስጥ ሰርጎ ገባ (ሉቃስ 22፡1-6)። ሉቃስ የእግዚአብሔር መንፈስ እንዴት መልካሙን ተግባር ለመፈጸም በሰዎች ሕይወት ውስጥ እንደሚሠራ ገልጾአል። ነገር ግን ሌላም ኃይል አለ። ይህም ክፋትን በመሥራት በእግዚአብሔር ላይ በደልን እንድንፈጽም የሚያነሣሣን ሰይጣን ነው። ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ ሕይወቱን እንዲቆጣጠርለት አልፈቀደም ነበር፡፡ ምክንያቱን ባናውቀውም፣ ሕይወቱ ከእውነት ርቆ እንዲቅበዘበዝ አድርጓል። የግብዝነት ሕይወት …

ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የፋሲካ ምግብን በላ (ሉቃስ 22፡1-38) Read More »

ሉቃስ 21፡1-38

ትንቢቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ከሚረዷቸው የሥነ ጽሑፍ ዐይነቶች መካከል የሚመደቡ ናቸው። ትንቢት የተሰጠው ወደፊት ስለሚፈጸሙት ክስተቶች ዝርዝር መረጃዎችን እንድናገኝ ነውን? እንደዚያ ከሆነ፣ የእያንዳንዱን ትንቢት ትርጉም አስመልክቶ የተለያዩ አመለካከቶች የሚንጸባረቁት ለምንድን ነው? ምንም እንኳ ብዙዎቻችን ነቢይ ወደፊት የሚከሰተውን አስቀድሞ የሚተነብይ አገልጋይ እንደሆነ ብናስብም፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነቢይ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት የተቀበለ ሰው ነው። …

ሉቃስ 21፡1-38 Read More »

ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ከተለያዩ ቡድኖች ጋር ተከራከረ (ሉቃስ 20፡1-47)

ሀ. ኢየሱስ ሥልጣኑን አስመልክቶ ከካህናት ጋር ተከራከረ (ሉቃስ 20፡1-19)። ሥልጣን አስፈላጊ ነገር ነው። አንድ ሰው ወደ አንተ መጥቶ ወደ ጦር ሜዳ መሄድ እንዳለብህ ቢነግርህ፣ የመጀመሪያው ጥያቄህ ሰውዬው ማን ነው? የሚል ይሆናል። ይህን ያለህ የመንግሥት ሥልጣን የሌለው ተራ ሰው ከሆነ፣ የሚነግርህን ችላ ብለህ ልትተው ትችላለህ። ነገር ግን ሌላ ሁለተኛ ሰው መጥቶ ቢናገርህ ሰውዩው የመንግሥት ባለሥልጣን ከሆነ፣ …

ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ከተለያዩ ቡድኖች ጋር ተከራከረ (ሉቃስ 20፡1-47) Read More »

ሉቃስ 19፡11-48

የአሥሩ ምናን (ብር) ምሳሌ (ሉቃስ 19፡11-27) የውይይት ጥያቄ፡- 2ኛ ተሰሎ. 2፡1-12 አንብብ። ሰዎች ኢየሱስ ስለሚመለስበት ጊዜ ምን ያስባሉ? አይሁዶችና የቀድሞ ክርስቲያኖች ከሚጠብቋቸው ነገሮች መካከል አንዱ፥ ኢየሱስ በፍጥነት ተመልሶ መሢሑ በዓለም ሁሉ የሚገዛበትን ምድራዊ መንግሥት መመሥረቱ ነበር። ምናልባትም ወደ ኢየሩሳሌም እየቀረበ ሲመጣ፣ አይሁዶች አሁን የመሢሑን አገዛዝ በጳለስቲና እንደሚጀምር በማሰብ ሳይደሰቱ አልቀሩም። ስለሆነም ኢየሱስ ለአይሁዶች ምድራዊ መንግሥቱን …

ሉቃስ 19፡11-48 Read More »

ቀራጩ ዘኬዎስ ደኅንነት አገኘ (ሉቃስ 19፡1-10)

ሉቃስ ታሪኩን የተናገረው፥ ኢየሱስ አንድን ሰው በሚነካበት ጊዜ በሕይወቱ ውስጥ ምን እንደሚከሰት ለማብራራት መሆኑ ግልጽ ነው። ወጣቱ ገዥ ሕይወቱን የተቆጣጠረውን ገንዘብ ትቶ፥ ኢየሱስን ለመከተል አልፈለገም ኃጢአተኛውና የተናቀው ቀራጭ ግን ገንዘቡን ትቶ ከኢየሱስ ኋላ ለመሮጥ ፈቅዷል። የእግዚአብሔር መንገድ ከእኛ የተለየ ነው። በጥሩ ሕይወታቸው፤ ችሎታቸውና ገንዘባቸው በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሊኖሩ የሚገባቸው ሰዎች ሳይገቡ ይቀራሉ፡፡ ነገር ግን እኛ …

ቀራጩ ዘኬዎስ ደኅንነት አገኘ (ሉቃስ 19፡1-10) Read More »

ሉቃስ 18፡1-43

ሙላቱ የአንዲት ፍሬያማ ቤተ ክርስቲያን መሪ ነበር። ለብዙ ዓመታት ክርስቲያን ሆኖ ስለኖረ ከመዳኑ በፊት፡ ኃጢአት በሕይወቱ ውስጥ የነበረውን ኃይል ዘንግቷል። ስለሆነም ክርስቲያኖች በኃጢአት በሚወድቁበት ጊዜ ትዕግሥት በማጣት በብርቱ ቃላት ይገሥጻቸዋል። ገና ከኃጢአት እስራት ላልወጡት ዓለማውያንም ትዕግሥት የለውም። «ሁሉም ሰው ለምን እንደ እኔ አይሆንም? የጽድቅ ኑሮን የማይኖሩት ለምንድን ነው? እኔ በቤተ ክርስቲያኔ ውስጥ ካሉት አብዛኞቹ ሰዎች …

ሉቃስ 18፡1-43 Read More »

ሉቃስ 17፡1-37

እንደ ኢየሱስ ተከታዮች እንዴት መኖርና ማሰብ እንደሚገባ የሚያሳዩ ትምህርቶች (ሉቃስ 17፡1-10) ሀ. ደቀ መዛሙርት የማሰናከያ ዓለት ሆነው ሰዎችን ለኃጢአት እንዳይዳርጉ መጠንቀቅ አለባቸው። የኢየሱስ ተከታዮች ኃጢአት መሥራታቸው የማይቀር ጉዳይ ነው። ኃጢአትን እንድናደርግ የሚፈትኑን ብዙ ፈተናዎች አሉ። ይህ ግን አንድ ሰው በተለይም የቤተ ክርስቲያን መሪ በግድየለሽነት እንዲኖርና ሌላውን ሰው ወደ ኃጢአት እንዲመራ ወይም ሌላውን ሰው በኃጢአት እንዲፈትን …

ሉቃስ 17፡1-37 Read More »

ሉቃስ 16፡16-31

ኢየሱስ በብሉይ ኪዳንና በፈሪሳያውን መካከል ስላለው ግንኙነት ያቀረበው ትምህርት (ሉቃስ 16፡16-18) እዚህ ላይ ሉቃስ ኢየሱስ በተለያዩ ጊዜያት ያስተማራቸውን እውነቶች ጠቅለል አድርጎ የሚያቀርብ ይመስላል። አጠር ብለው ከመቅረባቸው የተነሣ አንዳንዶቹን ለመረዳት አስቸጋሪ ነው። ሀ. ከሙሴ ዘመን ጀምሮ እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ አይሁዶች ዘወትር ብሉይ ኪዳንን ሲማሩ ቆይተዋል። አሁን ኢየሱስ በመካከላቸው ተገኝቶ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች እየነገራቸው ነበር። ነገር …

ሉቃስ 16፡16-31 Read More »