የጳውሎስ የመጨረሻ ቆይታ በሮም (የሐዋ. 27፡1-28፡31)
እግዚአብሔር ጳውሎስ ወንጌልን ወደ ሮም እንደሚያደርስ ተናግሮ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ይህንን ለማድረግ የተጠቀመበት መንገድ ጳውሎስን ጨምር ብዙ ክርስቲያኖችን ሳያስገርም አይቀርም፡፡ ጳውሎስ እንደ ነጻ ሰው ሳይሆን ታስሮ ወደ ሮም ለመሄድ ተገደደ። ይህ እስረኛ ሆኖ የጀመረው ጉዞ ራሱ በችግር የተሞላና የሞት አደጋ ያንዣበበበት ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ጳውሎስን ሮም ለማድረስ ወስኖ ነበር። ስለሆነም፥ ማዕበልና የመስጠም አደጋ …