የዮሐንስ ወንጌል

ደቀ መዛሙርቱ ዓሣ በታምር መያዛቸው እና ክርስቶስ ጴጥሮስን ይቅር ማለቱ (ዮሐ. 21፡1-25)

ክርስቶስ ተአምራዊ በሆነ መንገድ ለደቀ መዛሙርቱ ብዙ ዓሣ ሰጠ (ዮሐ 21፡1-14) ሐዋርያው ዮሐንስ መጽሐፉን የደመደመው በዮሐንስ 20፡30-31 ነው። ነገር ግን ስለ ኢየሱስ ታሪክ የጀመረውን ዘገባ ለመቋጨት ሌሎች ሁለት ታሪኮች ቀርተውት ነበር። የመጀመሪያው ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ዓሣን እንዴት በተአምር እንደ ሰጣቸው ነው። ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ አዝዟቸው ነበር (ማቴ. 28፡10)። በገሊላ ሳሉ ድንገት በዚያ …

ደቀ መዛሙርቱ ዓሣ በታምር መያዛቸው እና ክርስቶስ ጴጥሮስን ይቅር ማለቱ (ዮሐ. 21፡1-25) Read More »

የክርስቶስ ስቅለት፣ ቀብር እና ትንሣኤ (ዮሐ. 19፡17-20:31)

የክርስቶስ ስቅለት (ዮሐ 19፡17-37) ዮሐንስ ስለ ክርስቶስ ሞት አያሌ አስገራሚ ዝርዝሮችን አቅርቧል። ሀ. የሃይማኖት መሪዎች በክርስቶስ ላይ ያቀረቡትን ክስ ለመቀየር ፈለጉ። አንድ ሰው በወንጀል ተከስሶ ስቅላት በሚፈረድበት ጊዜ፥ ሮማውያን በአንገቱ ዙሪያ ወንጀሉን የሚገልጽ ጽሑፍ ያንጠለጥሉ ነበር። የክርስቶስ ክስ «የአይሁድ ንጉሥ» የሚል ነበር። የሃይማኖት መሪዎች ክሱ እንዲቀየር ቢጠይቁም፥ ጲላጦስ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ለ. የክርስቶስን ልብስ መከፋፈላቸው፡- …

የክርስቶስ ስቅለት፣ ቀብር እና ትንሣኤ (ዮሐ. 19፡17-20:31) Read More »

የኢየሱስ መታሰር፣ በሐናኒያና በጲላጢስ ፊት መቅረብ (ዮሐ. 18፡1-19፡16)

የወንጌል ማዕከል የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ካላተኮሩ የትኞቹም የወንጌል ታሪኮች ሙሉ ሊሆኑ አይችሉም። በመሆኑም፥ እያንዳንዳቸው ስለ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ከራሳቸው ልዩ ገጽታ አንጻር ተርከዋል። ዮሐንስ ወይም ክርስቶስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር፥ ከሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ይልቅ በእነዚያ የመጨረሻ ቀኖች ስለተፈጸሙት ድርጊቶች ብዙ ጽፎአል። ስለሆነም፥ ዮሐንስ በእነዚያ ጥቂት ሰዓታት በኢየሱስ ላይ ስለተፈጸሙት ነገሮች ከራሱ …

የኢየሱስ መታሰር፣ በሐናኒያና በጲላጢስ ፊት መቅረብ (ዮሐ. 18፡1-19፡16) Read More »

የክርስቶስ የሊቀ ካህንነት ጸሎት (ዮሐ. 17:1-26)

በዕብ 4፡14-16፤ 7፡25 ላይ ክርስቶስ ሊቀ ካህናችን እንደሆነና እንደሚማልድልን ተገልጾአል። እርሱ የሚጸልየው ስለ ምንድን ነው? ለእርሱ አስፈላጊ ነገር ምንድን ነው? እርሱ የሚጸልየው ስለ ሥጋዊ ጤንነታችን፥ ከአደጋ ስለ መትረፋችን፥ ስለ ቁሳዊ በረከት ነው? በዮሐንስ 17 ላይ ክርስቶስ እንደ ሊቀ ካህናችን ስለምን እንደሚጸልይ የሚያሳይ ምሳሌ አለ። ሐዋርያው ዮሐንስ ክርስቶስ ልቡን ከፍቶ የጸለየበትን አጋጣሚ ተገንዝቦአል። የጸለየውም ለራሱ፥ አሥራ …

የክርስቶስ የሊቀ ካህንነት ጸሎት (ዮሐ. 17:1-26) Read More »

ዮሐ. 16:1-33

የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) የመንፈስ ቅዱስ ትልቁ አገልግሎት ምን እንደ ሆነ የኦርቶዶክስ፣ የካቶሊክ፣ የሙሉ ወንጌል፥ የመካነ ኢየሱስና የቃለ ሕይወት ክርስቲያኖችን ጠይቅ። መልሶቻቸውን በወረቀት ላይ ጻፍ። ለ) የመንፈስ ቅዱስ ትልቁ አገልግሎት ምን ይመስልሃል? ሐ) ዮሐ 16፡5-16 አንብብ። በዚህ ክፍል ክርስቶስ የመንፈስ ቅዱለ ትልቁ አገልግሎት ምንድን ነው አለ? መ) አብዛኛቹ ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስ ትልቁ አገልግሎት እንደ ሆነ የሚያስቡት …

ዮሐ. 16:1-33 Read More »

የወይን ግንድና ቅርንጫፎቹ ምሳሌ እና ዓለም የኢየሱስን ደቀ መዛሙርት መጥላት  (ዮሐ. 15፡1-27)

ክርስቶስ የወይን ግንድ ማለትም የተከታዮቹ መንፈሳዊ ሕይወትና ፍሬያማነት ምንጭ ነው (ዮሐ. 15፡1-17) መንፈሳውያን ለመሆናችን ትልቁ መረጃው ምንድን ነው? በልሳን መናገራችን? ሌሎችን መፈወሳችን? ምስክርነት? ወይስ አምልኮ? መንፈሳውያን ለመሆናችን ትልቁ ምልከት ፍቅር መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ገልጾአል። ይህን በሕይወታችን ለመፈጸም ከሁሉም የከበደ መሆኑ ግልጽ ነው። ልንዘምር፥ ልንመሰክር፥ በልሳን ልንናገር እንችላለን። ለሰዎች ሁሉ ከራስ ወዳድነት መንፈስ የጸዳ ፍቅር …

የወይን ግንድና ቅርንጫፎቹ ምሳሌ እና ዓለም የኢየሱስን ደቀ መዛሙርት መጥላት  (ዮሐ. 15፡1-27) Read More »

ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስን ለመስጠት ቃል ገባ (ዮሐ. 14፡15-31)

በዚህ ክፍል ስለ መንፈስ ቅዱስ ዓላማና አገልግሎት ግልጽ አሳብ የሚያስተላልፉ ትምህርቶች ይገኛሉ። ምንም እንኳ አንዳንድ ክርስቲያኖች በልሳን መናገርን በመሳሰሉት አንዳንድ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ብቻ ደስ ቢሰኙም፥ የመንፈስ ቅዱስ መሠረታዊ ዓላማና አገልግሎት ምን እንደ ሆነ ለማወቅ ከፈለግን፥ እነዚህን በክርስቶስ የተነገሩትን እውነቶች መረዳት ይኖርብናል። ሀ. መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብ በክርስቶስ በኩል ይመጣል። ለ. መንፈስ ቅዱስ «ሌላው» አጽናኝ …

ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስን ለመስጠት ቃል ገባ (ዮሐ. 14፡15-31) Read More »

ወደ አብ የሚያደርሰው መንገድ (ዮሐ. 14፡1-14)

ደምሴ ሥራ የሌለው ክርስቲያን ነው፤ እርሱና ቤተሰቡ በልተው የሚያድሩት ምግብ ለመግዛት የሚያስችል በቂ ገንዘብ የሚያገኘው አልፎ አልፎ ነው። የሚረዳው ዘመድ እንኳ አልነበረም። «ለነገ እንዳልጨነቅ እግዚአብሔር ለምን በቂ ገንዘብ አይሰጠኝም?» ሲል ያስባል። «ሥራ የማገኘው እንዴት ነው? ለኑሮ የሚያስፈልገንን ገንዘብ የማገኘው ከየት ነው?» ብታመም የምታክመው በምኔ ነው? በማለት ስለ ወደፊት ኑሮው እጅግ ይጨነቃል። «ብሞትስ፣ ባለቤቴንና ልጆቼን ማን …

ወደ አብ የሚያደርሰው መንገድ (ዮሐ. 14፡1-14) Read More »

ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የፋሲካ ምግብ በላ (ዮሐ. 13:1-38)

ከዮሐንስ 13-17 በኋላ የወንጌሉ ትኩረት ይለወጣል። እስካሁን አጽንኦት የተሰጠው ለኢየሱስ ክርስቶስ ይፋዊ አገልግሎት፥ ላደረጋቸው ምልክቶችና ለሕዝብ ላቀረባቸው ትምህርቶች ነበር። ዮሐንስ በዚህ ይፋዊ አገልግሎት ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ስለሰጠው ቀጥተኛ ትምህርት ብዙም የገለጸው ነገር የለም። አሁን ግን ዮሐንስ ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሳለ በመጨረሻው ምሽት ላይ ለደቀ መዛሙርቱ በሰጣቸው እጅግ ጠቃሚ ትምህርቶች ላይ አተኩሯል። …

ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የፋሲካ ምግብ በላ (ዮሐ. 13:1-38) Read More »

ክርስቶስ ስለ ሞቱ ትንቢት በተናገረ ጊዜ የተለያዩ ሰዎች የሰጡት ምላሽ (ዮሐ.12፡20-50)

ዮሐንስ ስለ ክርስቶስ የመጨረሻ ቀናት ሲናገር ስለ ኢየሱስ ይፋዊ አገልግሎት የጀመረውን ገለጻ የደመደመው በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት የተለያዩ ሰዎች ለኢየሱስ የሰጡትን ምላሽ ምሳሌ አድርጎ በማቅረብ ነው። የእነዚህን ሰዎች ምላሽ የያዘው ልክ በሰርግ ላይ እንደ ተነሣ ፎቶ በዚያን ጊዜ የነበረውንና አሁንም ሰዎች ለኢየሱስ የሚሰጡትን ምላሽ ለማጤን ይረዳሉ። ሀ. ግሪኮች፡- ዮሐንስ የፋሲካን በዓል ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ግሪኮች …

ክርስቶስ ስለ ሞቱ ትንቢት በተናገረ ጊዜ የተለያዩ ሰዎች የሰጡት ምላሽ (ዮሐ.12፡20-50) Read More »