ሀ) የኢየሱስ ደም በሚከተሉት መንገዶች ተገልጿል
– የኢየሱስ ክርስቶስ ደም …1ዮሐ 1፡7
– የመስቀሉ ደም … ቆላ 1፡20
– የጌታ ደም … 1ቆሮ 11፡27
– ንጹሕ ደም … ማቴ 27፡4
– ክቡር ደም … 1ጴጥ 1፡19
– የበጉ ደም … ራዕይ 7፡14፤ 12፡11
ለ) ደም ሳይፈስ ስርየት (የሃጢአት ይቅርታ) የለም …ዕብ 9፡22፤ ዘሌ 17፡11
ሐ) የኢየሱስ ደም ያደረጋቸው ነገሮች
– ቤተ ክርስቲያን በደሙ ተገዛች … ሐዋ 20፡28
– ለእግዚአብሔር ተዋጅተናል … ራዕይ 5፡9
– በደሙ አዲስ ኪዳን ተደርጓል …ማቴ 26፡28፤ ማር 14፡24፤ ሉቃስ 22፡20፤ 1ቆሮ 11፡25
ኪዳኑም ዘላለማዊ ኪዳን ነው … ዕብ 13፡20
– በደሙ ቤዛነትን አግኝተናል … ኤፌ 1፡7፤ ቆላ 1፡14
ከቀድሞ አሮጌ ሕይወት ተዋጅተናል …1ጴጥ 1፡18-19
– በደሙ ጸድቀናል (ተታርቀናል) … ሮሜ 5፡9
– ሕሊናችን ንጽቷል … ዕብ 9፡14
– ወደ እግዚአብሔር አቅርቦናል … ኤፌ 2፡13
በደሙ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላምን አድርገናል …ቆል 1፡20
– የሃጢአት ይቅርታን አግኝተናል … ማቴ 26፡28
ከማንኘውም ሃጢአት ሁሉ ያነጻናል … 1ዮሐ 1፡7
– በደሙ ንጹሃን ነን … ዕብ 13፡12
– በደሙ ሰይጣንን ድል ነስተናል … ራዕይ 12፡11
መ) የኢየሱስ ደም ምሳሌዎች በ ብሉይ ኪዳን
– የፋሲካ በግ ………………………ዘጸ 12፡3-30፤ 1ቆሮ 5፡7
አስቀድሞ የተመረጠ ……….ዘጸ 12፡3፤ 1ጴጥ 2፡4
ከበጎቹ መካከል የተወሰደ ……ዘፀ 12፡5፤ ዕብ 2፡14፣17
ወንድ ……………………ዘፀ 12፡5፣ ኢሳ 9፡6
ያለ ነውር …….. …………ዘፀ 12፡5፤ 1ጴጥ 1፡19
በምሽት የታረደ ……………ዘፀ 12፡6፤ ማር 15፡33-37
ደሙ በበሮቹ መቃንና ጉበን ላይ ተተግብሯል …ዘፀ 12፡7፣ 22፤ ዕብ 9፡13-14፤ 1ጴጥ 1፡2
በበሩ መርገጫ ወለል ላይ አልተገበረም …………ዘፀ 12፡7፤ ዕብ 10፡29
በመራራ ቅጠል የተጠበሰ ሥጋ …………………ዘፀ 12፡8፤ ሮሜ 8፡17
ያለ እርሾ የሆነ ቂጣ …………………………ዘፀ 12፡8፤ 1ቆሮ 5፡7-8
በችኮላ ይበላል (ለመውጣት ዝግጁ በመሆን) ……ዘፀ 12፡11
የደም ምልክት ያለበት ቤት አልተፈረደበትም ……ዘፀ 12፡12-13፤ ሮሜ 5፡9
ግብፅን ለቅቆ የመውጣት ብስራት ………………ዘፀ 12፡17፤ ማቴ 2፡15፤ ዕብ 8፡7-13
መጻተኞች እና እስራኤላውያን ከመብሉ ተካፈሉ ……ዘፀ 12፡19፤ ሮሜ 9፡23-24
እስከ ጠዋት ድረስ በቤት ውስጥ መቆየት ………… ዘፀ 12፡22፤ ሐዋ 13፡43፤ 14፡22፤ ሮሜ 11፡22
– የስርየት ቀን ……………………………. .ዘሌ 16፡1-34፤ 23፡26-32፤ ዕብ 9፡1-10-39
መግባት የሚችለው ሊቀ ካህን ብቻ ነው ……………ዘሌ 16፡2፤ ዕብ 10፡19-22
በ ገዛ ፈቃድ ወደ ውስጥ ለመግባት አይፈቀድም …… ዘሌ 16፡2፤ ዕብ 10፡19-22
ለእራሱ እና ለቤተሰቡ መስዋዕት ያቀርባል …………ዘሌ 16፡6፣11፤ ዕብ 9፡7-10
የበሬና የፍየል ደም ይረጫል …………………… ዘሌ 16፡14-19፤ ዕብ 9፡11-14
የሚለቀቀው ፍየል ወደ በረሃ ይለቀቃል ……………ዘሌ 16፡8-10፣ 20-22 ዮሐ 1፡29
ለሕዝቡ ኃጢአት የሚሰዋ መስዋዕት …………… .. ዘሌ 16፡15፤ 1ቆሮ 3:16
የማደሪያ ድንኳኑ ክፍሎች ስርየት ……………………ዘሌ 16:16፤ 1ቆሮ 6፡19፣ 20
በሬ እና ፍየል ከሰፈሩ ውጭ መቃጠል ……………… ዘሌ 16:27፤ ዕብ 13፡11-13
በዓመት አንድ ጊዜ መደረግ አለበት ………………ዘሌ 16፡34፤ ዕብ 9፡7-10፣ 25-28
የኢዮቤልዩ ዓመት ይጀምራል – ዕዳዎች ይቅር ይባላሉ ……ዘሌ 25፡8-9
በዚህ ድረ ገጽ ውስጥ በአዘጋጁ የተጻፉ እና የተተረጎሙ እንዲሁም በተለያዩ አገልጋዮች የተዘጋጁ የድነት ትምሕርቶች፣ የደቀ መዝሙር ትምሕርቶች፣ የአዲስ ኪዳን እና ብሉይ ኪዳን ማጥኛዎችን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ጽሑፎችን ያገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከኤስ አይ ኤም ጋር በመተባበር የተዘጋጀ በአንድሮይድ ስልክ ላይ የሚጫን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መተግበሪያ (Amharic Bible Commentary App) ያገኛሉ፡፡ የወንጌል በድረ-ገጽ አገልግሎት ዌብ ሣይት (https://ethiopiansite.com/) የፊት ገጽ ግርጌ ላይ በመሄድ፣ በስተቀኝ ባልው ክፍት ሣጥን ውስጥ የኢ-ሜይል አድራሻዎን በመጻፍና “ድረ-ገጹን ይከታተሉ” የሚለውን ቁልፍ በመጫን የዌብ ሣይቱ ተከታይ (follower) እንዲሆኑ ተጋብዘዋል፡፡ ይህን ሲያደርጉ በዌብ ሣይቱ ላይ አዳዲስ ጽሑፎች ሲጫኑ፣ በኢ-ሜይል አድራሻዎ የማስታወሻ መልእክት (notification) የሚያገኙ ይሆናል፡፡