መስከረም 1፣ 2011ዓ.ም የሚጀመርና ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ የሚዘልቅ  የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

በኢትዮጵያውያን አዲስ አመት ከመስከረም 1፣ 2011ዓ.ም ጀምሮ አመቱን ሙሉ ሊደረግ በታሰበው መጽሐፍ ቅዱስን ከዳር እስከዳር በጥልቀት የማጥናት መንፈሳዊ ማእድ ላይ ይታደሙ (ማቴ 4:4)፡፡

ወንጌል በድረ-ገጽ አገልግሎት፣ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ መጽሐፍ ድረስ የሚዘልቅና መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ አመት ውስጥ ሙሉ በሙሉ አጥንቶ ለመጨረስ የሚረዳ ማጥኛ አዘጋጅቶ አጠናቋል፡ በየአመቱ ቢያንስ አንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ከዳር እስከዳር የማንበብ ቁርጠኛ ውሳኔ አድርገው ከሆነ በጥናቱ ላይ እንዲሳተፉ ከወዲሁ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስዎን በጥንቃቄ ማንበብዎን የሚመዝኑ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ከመካተታቸው ጎን ለጎን በበርካቶች ዘንድ በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡ አጫጭር ትምሕርታዊ ጽሁፎችም ይቀርባሉ፡፡  የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ ጥያቄዎቹ እና አጫጭር ትምሕርታዊ ጽሁፎቹ ከመስከረም 1፣ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በወንጌል በድረ-ገጽ አገልግሎት ዌብ ሳይት እና የፌስ ቡክ ፔጅ ላይ በየዕለቱ የሚለቀቁ ይሆናል፡፡

እያንዳንዱ ጥያቄ ሁለት እና ከዛ በላይ አማራጭ ያለው ሲሆን ከአጥኚው የሚጠበቀው፣ መልስ ብሎ ያሰበው አማራጭ ላይ ክሊክ (click) ማድረግ ብቻ ይሆናል፡፡ ጥያቄዎቹን ከመስራትዎ በፊት፣ መመሪያውን በጥንቃቄ ማንበብዎን እና በጥያቄዎቹ የፊት ገጽ ላይ የሚጠየቁትን ትክክለኛ የኢ-ሜይል አድራሻዎን መሙላትዎን አይዘንጉ። ትክክለኛ የኢ-ሜይል አድራሻ እንዲሞሉ የተጠየቁበት ምክንያት ውጤትዎ የሚላከው በዚሁ አድራሻ ስለሆነ ነው፡፡ ጥያቄዎቹን ሰርተው ሲያበቁ “submit” የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ። አንዳንድ ጊዜ “Google” ጥያቄዎቹን የሰራው ኮምፒውተር ወይም ሰው መሆኑን ለማጣራት የሴኪውሪቲ ጥያቄዎችን ሊጠይቆት ይችላል። “Submit” የሚለውን ቁልፍ ከተጫኑ በኋላ በሚከፈትሎት አዲስ ፔጅ ላይ “view your score” የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤትዎን እና የተሳሳቱትን ጥያቄ ግብረ መልስ (feedback) ማየት ይችላሉ። ጥያቄዎቹን በድጋሚ ለመስራት የሚሹ ከሆነ ደግሞ “Submit another response” የሚለውን ሊንክ ይጫኑ፡፡

የጥናት ጥያቄዎቹና አጫጭር ትምሕርታዊ ጽሁፎቹ በድረ ገጹ ላይ በሚጫኑበት ጊዜ እንዳያመልጥዎ ወይም ዘግይቶ እንዳይደርስዎ ይረዳዎ ዘንድ የድረ-ገጹ ሆም ፔጅ (https://tsegaewnet.wordpress.com/)  ላይ በመሄድ እና የኢ-ሜይል አድራሻዎን ከድረ-ገጹ የፊት ገጽ ግርጌ ላይ በስተቀኝ በኩል በሚገኘው ሳጥን ውስጥ በማስገባትና “ድረ-ገጹን ይከታተሉ” የሚለውን ቁልፍ በመጫን የድረ-ገጹ ተከታታይ (follower) እንዲሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን። ይህን ሲያደርጉ፣ ጥያቄዎቹና ሌሎች አዳዲስ ጽሁፎች በድረ-ገጹ ላይ በሚጫኑበት ጊዜ ሁሉ በኢ-ሜል አድራሻዎ የማስታወሻ መልዕክት የሚደርስዎ ይሆናል።

የሚያነሱት ሃሳብና ጥያቄ ካለ በሚከተለው የኢ-ሜይል አድራሻ ይላኩልን፤ በተቻለ ፍጥነት ለማስተናገድ ቃል እንገባለን። tsegaewnet@gmail.com

የወንጌል በድረ-ገጽ አገልግሎት አዘጋጅ

ምዕራፍ 11 – የጊዜ አጠቃቀም

ጸሎት፡

‹‹አባት ሆይ፣ መንግስትህን በምድር ላይ ለማስፋት፣ ኃላፊነቶቼን በአግባቡ ለመወጣት፣ ሌሎችን ለማገልገልና አንተን ለማክበር ሰአቶቼንና ቀናቶቼን በተሻለ መንገድ መጠቀም እንድችል አይኖቼን ክፈት፡፡ አንተንና የፈጠርከውን ለማድነቅ የጥሞና እና የእረፍት ጊዜዎችን እሻለሁ፡፡ በሌሎች ጊዜያቶቼ ደግሞ ትጉህ እና ዉጤታማ አድርገኝ! አሜን፡፡››

ስለ ጊዜ አጠቃቀም ማወቅ ለምን ያስፈልጋል?

የትምህርታዊው ጉባኤ መሪ፣ ድራማዊ በሆነ አካሄድ በረጅሙ እየተራመደ ወደ ክፍሉ ገባ፡፡ በእጁ አንድ የወረቀት ከረጢት እና አንድ ጋሎን የሚይዝ የመስታወት ገንቦ ይዟል፡፡ ታዳሚው ሁሉ ምን እንደሚሆን በጉጉት ይጠባበቅ ነበር፡፡

የጉባኤው መሪ ፈገግ ብሎ፣ ‹‹ዛሬ እዚህ የተሰበሰብነው ስለ ጊዜ አጠቃቀም ለመነጋገር ነው፡፡ እናም ይሄ የመስተዋት ገንቦ ዛሬ ለሕይወታችሁ እጅግ ጠቃሚ ትምህርት ያስተምራችኋል፡፡››

አሁን ታዳሚው በሙሉ በፍፁም ጉጉትና መመሰጥ መከታተል ጀምሯል፡፡

“ልብ ብላችሁ ይህን የመስታዋት ገንቦ ተመለከቱ፡፡ ይህ ገንቦ በአየር የተሞላ እንደሆነ ሁላችሁም ታውቃላችሁ ብዬ አስባልሁ። አየሩን ለጌዜው እንተውና፣ ይህ ገንቦ ባዶ ነው ወይስ ሙሉ?” ሲል ጉባኤውን ጠየቀ።

‹‹ባዶ፣›› ሲሉ በርካቶቹ መለሱ፡፡

‹‹ትክክል፡፡ ስለዚህ አሁን መሙላት እንጀምር፡፡›› ከኦትሮንሱ ጀርባ በመሄድ የተለያየ መጠን ያላቸውን ኮረቶች የያዘ ሳጥን አወጣ፡፡ ከዛም ኮረቱን በመስታዋት ገንቦ ውስጥ በጥንቃቄ መጨመር ጀመረ፣ አስተካከለ፣ ደግሞ አስተካከለ፣ እያወጣ ደግሞ አስገባ፡፡ ይህን አድርጎ ሲያበቃ፣ ወደ ታዳሚው ተመልክቶ፣ ‹‹በቃ! አሁን ገንቦው ሞልቷል አይደል?›› ሲል ጠየቀ፡፡

ከ ታዳሚዎቹ መካከል አንዱ፣ ‹‹በትልልቆቹ ኮረቶች መሃል መሰግሰግ የሚችሉ ሌሎች አነስ ያሉ ኮረቶች ካሉህ ገንቦው አሁንም ክፍት ቦታዎች አሉት፡፡›› ሲል መለሰ፡፡

‹‹እጅግ በጣም ጥሩ ነገር ብለሃል!›› ሲል የትምህርታዊው ጉባኤ መሪ ተናገረ፡፡ ከዛም ከአትሮንሱ ስር ያስቀመጠውን አነስ ያሉ ኮረቶች የያዘ ከረጢት አውጥሮ በመስታወት ገንቦ ውስጥ መጨመር ጀመረ፡፡ አነስተኛ ኮረቶቹ መጀመሪያ በገቡት ትልልቅ ኮረቶች መካከል የነበሩትን ክፍት ቦታዎች ሞሉ፡፡

‹‹አሁን ገንቦውን ሞላነው፣ አይደል?›› ሲል ከመናገሩ፣ አንዲት ወጣት ሴት ብድግ ብላ፣ ‹‹ገንቦው አሁንም ጥቂት አሸዋ የሚይዝ ቦታ ይኖረዋል ብዬ አስባለው —›› አለች፡፡

‹‹ጥሩ ሃሳብ ነው!›› የጉባኤው መሪ እንደ ቀድሞው ከአትሮኑስ ስር ያስቀመጠውን ከመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ያነሱ መጠን ያላቸውን ኮረት የያዘ ከረጢት አወጣ፣ የአሁኑ ከረጢትደቃቅ አሸዋ የያዘ ነበር፡፡ አሸዎውን በገንቦው ውስጥ ሲጨምር በኮረቶቹ መካከል የነበረውን ቦታ ያዘ፡፡

‹‹እሺ! አሁን በቃን፤አይደል? ሁሉም ስፍራ በኮረቶች ተይዟል!›› አለ የጉባኤው መሪ ወደ ታዳሚው እየተመለከተ። ‹‹ቆይ አንድ ጊዜ፣ አለ ከታዳሚዎቹ መካከል አንዱ፡፡ ‹‹ጥቂት ውሃ ብንጨምርበትስ?››

‹‹ይህን ሃሳብ ታመጣለህ ብዬ አልገመተኩም ነበር፣›› አለ የጉባኤው መሪ ፈገግ ብሎ፡፡ በጆግ ውሃ ካዘጋጀ በኋላ ቀስ ብሎ በመስተዋቱ ገንቦ ውስጥ መጨመር ጀመረ፡፡ ውሃው ቀስ በቀስ በኮረቶቹ መሃል አልፎ ገንቦው ስር ደረሰ፡፡ በመጨረሻም እስከ አፉ ጢም አለ፡፡

‹‹አሁንስ ልንሞላው የምንችለው ክፍት ቦታ አለ?›› ሲል የጉባኤው መሪ ለታዳሚዎቹ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ማንም ምላሽ አልሰጠም፡፡ ‹‹እንግዳው፣ ከዚህ ገለጻ ስለ ጊዜ አጠቃቀም ምን ተማራችሁ?››

ከታዳሚው መካከል አንድ ሰው ልክ እንደ ተማሪ እጆቹን ወደላይ አውጥቶ በጉጉት፣ ‹‹አጥብቀህ የምታስብ እና ፈጠራ ያለህ ከሆንክ፣ የጊዜ ሰሌዳህ እንደሚይዝልህ ከምታስበው በላይ ሌሎች ልታደርጋቸው የሚገቡህን ነገሮች ሊይዝልህ እንደሚችል ተምሬአልው!›› ሲል መለሰ፡፡

‹‹ፈፅሞ!›› ሲል የጉባኤው መሪ መለሰ፣ ‹‹የዚህ ገለጻ ዋነኛ ነጥብ ይህ አይደለም፡፡ ያልከውን ሃሳብ ከገለጻው መገንዘብ ይቻል ይሆናል ግን ከዚህ የተሻለ ነጥብ አለ፡፡››

ሁሉም በማሰብ ፀጥ አሉ፡፡ በመጨረሻም የጉባኤው መሪ፣ ‹‹የገለጻው ዋና ነጥብ ይህ ነው፡- ‹‹ትልልቁን ኮረት ለመጨመር ከፈለጋችሁ፣ መጨመር ያለባችሁ መጀመሪያ ላይ ነው!››

ይህ ትምህርት በሕይወትህ ያሉ ‹‹ትላልቅ ኮረቶችን›› እንድትለይ እና መጀመሪያ ላይ መግባታቸው እንድታረጋግጥ ይረዳሃል፡፡ ከዛም አነስ ያሉት ጠጠሮች፣ አሸዋውና ውሃው ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዴት እንደሚከተሉ ከገለጻው እንረዳለን።

‹‹ሰአትን በአግባቡ ለመጠቀም መጀመሪያ ማድረግ ያለብህ፣ ጠቃሚ የሆነውን ካልሆነው መለየት ነው፡፡ ልንቀበለው የሚከብደን ነገር ቢሆንም ሁሉን ማድረግ እንደማንችል ማወቅ አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡›› – ሮን ፍራይ

እንዴት ይህ ርዕስ ‹‹ቅዱስ›› ከሆኑት እንደ ጸሎት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ከሚሉት ርዕሶች ተርታ ሊሰለፍ ቻለ? ምላሹ ቀላል ነው፡፡ እንደ ክርስቲያን ከኢየሱስ ጋር መጓዝ ጊዜ እንደሚጠይቅ ሳታስተውል የቀረህ አይመስለኝም፡፡ ኢየሱስን በተቀበልህ ጊዜ፣ በተለያዩ ነገሮች በተጣበበው የጊዜ ሰሌዳህ ውስጥ – ቤተ ክርስቲያን ለመሄድ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ ለመገኘት፣ ለመማር፣ ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ለማድረግ- የሚሆን ተጨማሪ ጊዜ መፈለግ ነበረብህ፡፡ ስለ አንተ ባላውቅም በዚህ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን የሚኖሩ በርካታ ሰዎች የየዕለት የጊዜ ሰሌዳቸው በፕሮግራሞች ተጣቧል፡፡

ዴቪድ ዳውሰን፣ የ ‘Equipping The saints’ አገልግሎት መስራች እንዲህ አለ፡- ‹‹አስቸጋሪው ነገር የጊዜ እጦት ሳይሆን ባለን ጊዜ የምንሰራው ነገር ነው፡፡ ጊዜን ማጠራቀም፣ መግዛት፣ መለዋወጥ ሆነ ወደ ኃላ መመለስ ስለማንችል መቆጣጣር መማር ይኖርብናል፡፡ ጊዜን በአግባቡ ማስተዳደር ካልቻልን ውጤታማ ሕይወት ልንመራ አንችልም፡፡

የሃላፊነት ሹመት (ታማኝ መጋቢነት)

የ ‹‹መጋቢ›› ብያኔ (ትርጉም)፡- በሃላፊነት የተሰጠን ነገር፣ በጥንቃቄና በሃላፊነት መንፈስ ማስተዳደርን ያመለክታል፡፡ 1ቆሮንቶስ 3፡11-15 አንብብ፡፡ ይህ ክፍል ወደፊት ስለሚመጣው ‹‹የክርስቶስ የፍርድ ወንበር›› ትዕይንት ያወራል፡፡ ይህ ጊዜና ቦታ የእግዚአብሔር ወንድና ሴት ልጆች በምድር ላይ ስላደረጉት ሥራና አኗኗራቸው በእግዚአብሔር ፊት የሚጠየቁበት ነው፡፡ በዚህ የፍርድ ወቅት የእያንዳንዱ ‹‹ስራህ›› ዋጋ ‹‹ይፈተናል››፡፡

ማስታወሻ፡- ይህ ስፍራ መንግስተ ሰማይ ወይም ገሃነም ለመግባት ውሳኔ የሚሰጥበት አይደለም፡፡ ይህ ውሳኔ አስቀድሞ ሆኗል፡፡ በክርስቶ ኢየሱስ ላይ ባለህ እምነት ምክንያት የዘላለም ሕይወትን አግኝተሃል፡፡ የዚህ ቀን ፍርድ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግስት ውስጥ የሚኖርህን የሽልማት መጠን፣ መብትና ሃላፊነት ይወስናል፡፡

 1. በ1ቆሮንቶስ 3፡11-15 መሠረት በሕይወትህ ያለው መሠረት ማን ነው?
 2. በዛ መሠረት ላይ፣ ከሁለት የተለያዩ ነገሮች ሥራ ትሰራለህ፡፡ ‹‹ወርቅ፣ ብር እና የከበረ ድንጋይ›› ምን የሚያመለክቱ ይመስልሃል?
 3. ‹‹እንጨት፣ ሣር፣ ወይም አገዳ›› ምን የሚያመለክቱ ይመስልሃል?
 4. የጊዜ አጠቃቀምህን በተመለከተ ራስህን የትኛው ደረጃ ላይ ታስቀምጣል?
 5. ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መካከል በሰአት አስተዳደርህ ውስጥ በጣም አስቸጋሪ የሆነብህ የቱ ነው? [3 ብቻ ምረጥ!]
 • አስቀድሞ ማቀድ
 • ነገሮችን እንደ አስፈላጊነታቸው በቅድመ ተከተል ማስቀመጥ
 • የትኩረት መበታተን
 • በእቅዴ አለመጽናት
 • የትጋት ማነስ
 • ማዘግየት (ማርፈድ)
 • ብኩንነት
 • እግዚአብሔርን ከእቅዴ ማስወጣት
 • ሌሎች? ————————-

ውሱን የሆነ ጊዜ በሃላፊነት (በአደራ) ተሰጥቶሃል፡፡ ይህንን ውሱን ጊዜህን -በወርቅ፣ ብር እና የከበረ ድንጋይ- አልያም -በእንጨት፣ሣር እና አገዳ- መለወጥ አለመለወጥ የአንተ ድርሻ ነው!

‹‹ትላልቆቹ ኮረቶች›› – በሕይወታችን ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ነገሮችን ያመለክታሉ

እነዚህን ትላልቅ ኮረቶች በሕይወትህ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሊደረደሩ እንደሚገባቸው ታምን ይሆናል፤ ነገር ግን ብዙ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ትላልቅ ኮረቶች ምን እንደሆኑ ለማወቅ ግራ ሲጋቡ ይስተዋላል፡፡ እንደ ክርስቲያን የእኛ ቅድሚያዎች በእግዚአብሔር ቅድሚያዎች እንዲዋጡ እንሻለን። በመሆኑም ይህንን ግራ መጋባት ለመፍታት መጀመሪያ የእግዚአብሔር ቅድሚያዎችን ልናውቅ ይገባል፡፡

 • እግዚአብሔር ቅድሚያ እንድትሰጣቸው የሚፈልጋቸው ነገሮች ምን ይመስሉሃል?

የአንተና የእግዚአብሔር ቅድሚያዎች ንፅፅር

የጊዜ አጠቃቀማችንን ከእግዚአብሔር ቅድሚያዎች አንጻር ማየት ተገቢ ነው፡፡ እያንዳንዳችን በሣምንት 168 ሰአቶች ተሰጥተውናል፡፤ እንዴት ነው የምንጠቀማቸው? ሳምንታዊ ተግባሮችህን በመገምገም ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ተግባራት በሣምንት ምን ያህል ሰአት እንደምትፈጅ በመመዝገብ አስላ፡፡

የቅድሚያዎች መገምገሚያ መልመጃ፡

– ለመተኛት

– ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ለመዘጋጀትና ለመሰባሰብ)

– ለመብላት

– የቤት ውስጥ ሥራዎችን ለመስራት

– ለመልበስ፣ ጢም ለመላጨት፣ ለመታጠብ ለመስከታከል፣ ወዘተ

– ከቤተሰብ ጋር ለማሳለፍ

– ከቤት ወደ ሥራ ለመጓዝ

– ሌሎችን ሰዎች ለመጎብኘት

– የክፍል እና የቤት ሥራ ለመስራት

– ለመዝናናት፤ የግል ጊዜ

– የግልና የጋራ ጸሎት ለማድረግ

– ለሰውነት ማጎልመሻ ስፖርት

– ከቅዱሳን ጋር ሕብረት ለማድረግ

– የመስሪያ ቤት ሥራ ለመስራት

– ለማገልገል

– ቤት ለመጠገን፣ ለማስተካከል

– ለማንበብ (መጻሕፍት፣መፅሔቶች)

በሣምንት ውስጥ ያለህ አጠቃላይ ሰአት (168) – የተጠቀምክበት ሰአት (—–) = ‹‹የባከነ ጊዜ›› (————–)

ምዘናውን መስራት፡-

እዚህ ላይ ሁለት ልታጤናቸው የሚገቡ ቁም ነገሮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው – ‹‹የባከኑ ጊዜያቶችህ›› ነው፡፡ ሁለተኛው ነጥብ ደግሞ – ከላይ የዘረዘርካቸውን ተግባራት አስቀድሞ ከዘረዘርካቸው ‹የእግዚአብሔር ቅድሚያዎች ጋር ማነጻጸር ነው፡፡ ምን ያህሎቹ የአንተ ቅድሚያዎች ናቸው ከእግዚአብሔር ቅድሚያዎች ጋር አብረው የሚሄዱት? (በአንዱ ምላሽህ ላይ አክብብ) 0% 10% 20% 30% 40% 50% 60% 70% 80% 90% 100%።

ማንኛውም ክርስቲያን በመጀመሪያ፣ ህጸፅ ከሚበዛበት የቅድሚያ ዝርዝር እንደሚነሳ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለእኛ ከሰጠበት ምክንያቶች አንዱ የእኛ ቅድሚያዎ ከእግዚአብሔር ቅድሚያዎች ጋር በሂደት እንዲገጥሙ ለመረዳት ነው፡፡ ይህ በአንድ ለሊት ሊተገበር የሚችልና ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የምንተባበር ከሆነ ግን መሆኑ በሂደት መሆኑ አይቀርም፡፡

ከዚህ በላይ በተማርናቸው ትምህርቶች መሠረት የሕይወትህ ‹ትላልቆቹ ኮረቶች› ምንድን ናቸው? ወይም ምን መሆን አለባቸው? በማስታወሻ ደብተርህ ላይ፣ ከ5 እስከ 8 የሚሆኑ፣ በሕይወትህ ቀድመው ሊተገበሩ የሚገባቸውና ከፍተኛ ትኩረት ልትሰጣቸው የምትፈልጋቸውን ነገሮች ዘርዝር፡፡

ለውጤታማ የሰአት አጠቃቀም የሚረዱ አምስት ደረጃዎች

በየዕለቱ ባለህ የጊዜ ሰሌዳ ትላልቆቹ ኮረቶች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው በአግባቡ መደርደራቸውን ለማረጋገጥ አምስት ደረጃ ባላቸው ሂደቶች ውስጥ ማለፍህን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡ የሚከተለው ጥናት በእነዚህ አምስት ደረጃዎች ውስጥ እንድታልፍ ይረዳሃል፡፡

ደረጃ 1፡ ቅድሚያዎችህን በተልዕኮ መግለጫ ቅረፅ

የተልዕኮ መግለጫ – በሕይወትህ በአሁኑ ሰአት እየፈጸምክ ያለኸውን ወይም ልትፈፅም የምትሻውን ጉዳይ የሚገልጽ ነው፡፡ ግልፅ የሆነ የተልዕኮ መግለጫ ካለህ ከፊትህ ያሉትን ጊዜያት ለማቀድ ያግዝሃል፡፡ ምክንያቱም የአሁን ጊዜህን ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ለመጠቀም ይህ መግለጫ፣ ተጨባጭ መመዘኛ በመሆን ወደ ሕይወትህ የሚመጡትን አጋጣሚዎች ‹እሺ› ወይም ‹እምቢ› የማለት መሠረት ይጥልልሃልና፡፡ ይህ መግለጫ፣ አንድን ነገር ለመፈጸም የሚያስችል አቅጣጫ ይሰጥሃል። የምትሰራውን ነገር ሁሉ በማካተት እንደ ዣንጥላ ያገለግልሃል። ከዚህ በተጨማሪ ሊለወጥ የማይገባውንና ሙሉ በሙሉ ተከናውኖ ማለፍ የሚገባውን የሕይወት ዘመን ጉዞና ተግባርህን ያመለክታል፡፡

ደረጃ 2፡ የተልዕኮ መግለጫህን እውን ለማድረግ የሚያስችሉህን ዋና ግቦች ለይተህ አስቀምጥ፡፡

እነዚህ ግቦች ቢያንስ ለረጅም ጊዜ የማይለወጡ መሆን ይኖባቸዋል፡፡ እነዚህ ግቦች ሰፊ እና የረጅም ጊዜ ህልሞች (እቅዶች) በመሆናቸው ተግባራዊ ለመሆን ወራት፣ አመታት ወይም አስርት አመታት የሚጠይቁ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ግቦች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁሉንም ወይም የተወሰኑትን የሕይወትህን ክፍሎች ይዳስሳሉ፡፡

 • መንፈሳዊ
 • አካላዊ
 • ግላዊ
 • ስራ ነክ
 • ገንዘብ ነክ
 • ቤተሰብ
 • ማህበራዊ ጉዳዮች
 • ፖለቲካ

ግቦችን ስትቀርፅ ግቦችህ – የተወሰነ፣ የሚለካ፣ ሊደረስበት የሚቻል፣ ተግባራዊ፣ ተጨባጭ መሆናቸውን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡

በመጪዎቹ ሀያ ሰላሳ አመታት ምን ሆነህ ማየት ትፈልጋለህ? ምን ብትሆን ነው በሕይወትህ መጨረሻ ዘመን፣ ‹‹ምንም የምፀፀትበት ነገር የለኝም›› ብለህ ልትናገር የምትችለው? ቤተሰብ ብትመሠርት? የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ብትሆን? ወደ ውጪ አገር ብትሄድ? አንድ ሚሊዮን ብር ብታገኝ? በኦሎምፒክ ውድድር ላይ ብትወዳደር?

በማስታወሻ ደብተርህ ላይ በሕይወትህ ዘመን አጠናቀህ ልታያቸው የምትፈልጋቸውን የመጀመሪዎቹን አምስት ዋና ግቦችህን ፃፍ፡፡ ‹‹ደስተኛ መሆን›› የሚሉ አይነት ግልፅ ያልሆኑ ዐረፍተ ነገሮች እና ‹‹ኃጢአት የሌለበት ፍፁም ሰው መሆኑ›› ወይም ‹‹አንድ ማይል በሦስት ደቂቃ መሮጥ›› የሚሉ አይነት ተጨባጭ ያልሆኑ ዐረፍተ ነገሮችን ከግቦችህ መካከል አስወግድ፡፡

ደረጃ 3፡ ዋነኛ ግቦችህ ላይ ለመድረስ የሚረዱህን መካከለኛ ግቦች ቅርፅ

መካከለኛ ግቦች ወደ ዋነኛው ግብህ የሚያፈናጥሩህ ስፕሪንጎች ናቸው፡፡ በርካታ መካከለኛ ግቦች በአንድ ላይ ሆነው አንድ ዋነኛ ግብ ተግባራዊ እንዲሆን ይረዳሉ፡፡ ለአብነት፡- ከዋነኛ ግቦችኅ መካከል አንዱ ‹‹የአእምሮ ቀዶ ጥገና ባለሞያ መሆን›› ይሆናል፡፡ እናም የመጀመሪያው መካከለኛ ግብህ ‹‹የኮሌጅ ትምህርትህን በ 3.8 አጠቃላይ ውጤት ማጠናቀቅ ይሆናል፡፡ ቀጣዩ ደግሞ፣ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕክምና ትምህርት ቤት ተቀባይነት ማግኘት›› ይሆናል፡፡ ከዛም፣ ‹‹የሕክምና ትምህርቱን ማጠናቀቅ››፣ ወዘተ፡፡

በሌላ ወረቀት ላይ፣ በደረጃ 2 ስር የጻፍካቸውን ዋነኛ ግቦች ከእያንዳንዱ ስር ግማሽ ወረቀት ክፍት ቦታ እየተውክ ጻፋቻ፡፡ ከዛም በእያንዳንዱ ዋነኛ ግቦች ስር ልትዘረዝራቸው የምትችላቸውን ወደዚህ ግብ እንድትደርስ የሚረዱህን መካከለኛ ግቦች ፃፍ፡፡

ከዚህ በታች በተሰጠህ ክፍት ቦታ፣ በሌላ ወረቀት ላይ ከዘረዘርካቸው መካከለኛ ግቦች መካከል ለእያንዳንዱ ዋነኛ ግቦችህ የፃፍከውን የመጀመሪያ መካከለኛ ግብ ፃፍ፡፡

የመጀመሪያ መካከለኛ ግብ፡-

ለዋነኛ ግብ # 1 —- 1. ——————

ለዋነኛ ግብ # 2 —- 2. —————–

ለዋነኛ ግብ # 3 —- 3.——————-

ለዋነኛ ግብ # 4 —- 4. ——————

ለዋነኛ ግብ # 5 —- 5. ——————

ደረጃ 4፡ መካከለኛ ግቦችህ ላይ ሊያደርሱህ የሚችሉ የአጭር ጊዜ ግቦችን ቅረፅ

እዚህ ደረጃ ላይ ራስህ የምትጠይቀው ጥያቄ፣ ‹‹የመጀመሪያውን መካከለኛ ግቤን ተግባራዊ ለማድረግ በአሁን ሰአት መውሰድ ያለብኝ እርምጃ ምንድን ነው? የሚል ነው፡፡ ምላሽህ፣ የአጭር ጊዜ ግቦች ዝርዝር ይሆናል፡፡

ዶክተር ሪቻርድ ፋርማን የቀዶ ጥገና ባለሞያ ለመሆን ኮሌጅ ገብቶ ለመሰልጠን የነበረውን ህልም ለማሳካት የነበረው አጠቃላይ ግብ ውጤታማ የሆነው አንድ ቀን ሌሊት በሰራው የኬሚስትሪ የቤት ስራ ምክንያት እንደነበር ያስታውሳል፡፡ ያችን ሌሊት በስንፍና አሳልፏት ቢሆን ኖሮ፣ ፈተናውን ይወድቅ ነበር፡፡ ፈተናወን ቢወድቅ ኖሮ ደግሞ ኮርሱን አነስተኛ በሆነ ውጤት ያጠናቅቅ ነበር፡፡ ይህ ውጤት አነስተኛ ከሆነ ደግሞ፣ ወደ ሕክምና ኮሌጅ መግባት የማይታሰብ ይሆናል፡፡ የሕክምና ኮሌጅ ካልገባ ደግሞ የቀዶ ጥገና ባለሞያ መሆን የማይታሰብ ይሆናል፡፡ እሱ ግን፣ በዛች ሌሊት በትጋት በመስራት ቆንጆ ውጤት ስላመጣ፣ የቀዶ ጥገና ባለሞያ ለመሆን የሚያደርገው ጉዞ ቀና እና በሮቹም የተከፈቱ ሆኑለት፡፡ ሁሉ ነገር አሁን ያለችሁን ሰአት በአግባቡ በመጠቀም ላይ የተወሰነ ነው፡፡

በደረጃ 3 ላይ የዘረዘርካቸውን አምስቱንም መካከለኛ ግቦች መልሰህ ካጤንክ በኃላ በሌላ ወረቀት ላይ በእያንዳንዱ ስር ያቀድካቸውንና እነዚህን ግቦች ለማሳካት የሚረዱህን የአጭር ግዜ ግቦች ጻፍ፡፡ ከዚህ በታች በተሰጠህ ክፍት ቦታ የመጀመሪያው መካከለኛ ግብህን የሚመለከቱ የአጭር ጊዜ ግቦችህን ፃፍ፡፡

ለመጀመሪያ መካከለኛ ግብ፡-

1ኛ የአጭር ጊዜ ግብ —- 1. ———————

2ኛ የአጭር ጊዜ ግብ —- 2. ——————–

3ኛ የአጭር ጊዜ ግብ —- 3. ———————

4ኛ የአጭር ጊዜ ግብ —- 4. ———————

5ኛ የአጭር ጊዜ ግብ —- 5. ———————

ደረጃ 5፡ የአጭር ጊዜ ግቦችህን የምታጠናቅቅበት የጊዜ ሰሌዳ አውጣ፣ አላስፈላጊ ተግባራትን ለይ።

የዚህ ጉዞ መጨረሻ የሚሆነው፣ የአጭር ጊዜ ግቦችህ በጊዜ ሰሌዳህ ላይ ሰፍረው ሲጠናቀቁ ነው፡፡ እያንዳንዱ የአጭር ጊዜ ግቦች በጊዜ ሰሌዳው መሠረት ሲጠናቀቁ ነገሩ አበቃ ማለት ነው፡፡ ‹‹የተፈጸመች ፈቃድ ሰውነትን ደስ ታሰኛለች!›› (ምሳሌ 13፡19) ፡፡ ፈቃዶችህን በጊዜ ሰሌዳ ላይ አስፍረህ ፍፃሜያቸውን ካልተከታተልክ በቀር ይህንን ደስታ ማጣጣም አስቸጋሪ ነው!

የጊዜ ሰሌዳህን አዘጋጅ፡፡ በደረጃ 4 ስር ያሰፈርካቸውን የአጭር ጊዜ ግቦች አጢናቸው፡፡ በርካቶቹ በጊዜ ገደብ የታጠሩ ናቸው – እነዚህን ግቦች በጊዜህ ሰሌዳህ ላይ አስፍራቸው!

ጊዜህ ቅድሚያ በምትሰጣቸው ነገሮች አስይዘህ ከሆነ፣ አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ‹‹እምቢ›› ስለምትል፣ ሰዎች የአንተን ጊዜዎች በማትፈልጋቸው ነገሮች ሊሞሉ አይችሉም፡፡ ቀናቶችህን የማታቅድባቸው ከሆነ፣ ሌላ ሰው ላንተ ያቅድልሃል – ምናልባትም በዚህ እቅድ አትደሰት ይሆናል!

ብቻህን ከጌታ ጋር በመምከር፣ በገንቦው ውስጥ የትኛቹ ትላልቅ ኮረቶች መጀመሪያ ላይ መግባት እንዳለባቸው፣ ከዛም መቼና እንዴት ጠጠሮቹ፣ አሸዋውና ውሃው መግባት እንዳለበት መወሰን አለብህ፡፡

ተግባራዊ የሰአት አጠቃቀም መርሆዎች

የዚህን ምዕራፍ ጥናት፣ እግዚአብሔር የሰጠህን ጊዜ በኃላፊነት መንፈስ ለመጠቀም የሚያስችልህን ተግባራዊ የሆኑ አምስት አጠቃላይ መርሆዎች በማየት እናጠናቅቃለን፡፡

 1. አስቀድመህ እግዚአብሔርን አማክር

ኢየሱስ ጌታህ እንዲሆን በጠየቅኸው መሰረት እንደዛው ስትመላልስ ሊያይህ ይፈልጋል፡፡ አስቀድመህ ምን ሊያደርግልህ እንደምትፈልግ ልትጠይቀው ይገባሃል፡፡ ይህንን ፓሊሲ የማትከተል ከሆነ የጉዞህ መጨረሻ በውጪያ ወደሌላቸው መንገዶች መጓዝ እና ጊዜ ማጥፋት ይሆናል። ይህ ደግሞ እግዚአብሔር ላንተ ካዘጋጀው አላማ ጋር የሚቃረን ነው፡፡

የሐዋሪያት ሥራ 22፡6-10 አንብብና ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ለተሰበሰቡ ሰዎች የመሰከረውን ምስክርነትን ተመልከት፡፡ ኢየሱስ ለጳውሎስ በተገለጠለት ጊዜ የጳውሎስ የመጀመሪያ ጥያቄ፣ ‹‹ጌታ ሆይ አንተ ማነህ?›› የሚል ነበር፡፡ አንተም ተመሳሳይ ጥያቄ ጠይቀህ ምላሽ አግኝተህ ይሆናል፡፡ የጳውሎስ 2ኛ ጥያቄ ምን ነበር? ይህን ጥያቄ በየቀኑ ደጋግመን ልንጠይቅ ይገባል!

በዮሐንስ 17፡4 የቀረበው ጥቅስ ኢየሱስ ከስቅለቱ በፊት በነበረችው ለሊት የጸለየው ጸሎት ነው፡፡ ኢየሱስ የሦስት አመት የአገልግሎት ጊዜ ብቻ ቢኖረውም በዚህ ጊዜ ውስጥ ስራውን መፈጸም መቻሉን ልብ ልትል ይገባል፡፡ እዚህ ክፍል ልብ ልትለው የሚገባህ ቁልፍ ነጥብ ኢየሱስ ምን አይነት ሥራ እንደሰራ ነው፡፡ በጥቅሱ ውስጥ፣ ኢየሱስ የፈጸመው ስራ ምን አይነት እንደሆነ ነው የተገለጸው?

የምትሰራው ስራ (ማንኛውም ጊዜ የሚወስድ ነገር ሁሉ) ራስህ ለመስራት የወሰንከው ወይም ሰዎች በአንተ ላይ የጫኑት ሳይሆን እግዚአብሔር እንድትሰራው የሰጠህ ስራ መሆኑ የምትለይበት መንገድ ምንድ ነው? – ጥቂቶቹን ግለጽ፡፡

ሕይወትህን በእርሱ ትዕዛዝ ስር ለማስገዛትህ እውቅና እስከሰጠህ ድረስ ጊዜህን በምን ሁኔታ መጠቀም እንዳለብህ በምታደርገው ምርጫ ውስጥ እግዚአብሔር ይረዳሃል፡፡ በሚመራህ መንገድ ለመጓዝ ፈቃደኛነትህን እስከገለፅክ ድረስ በእግዚአብሔር እጅ ጊዜህ አይባክንም፡፡

ዛሬ ላይ ሆነህ ስትመለከት፣ ጥቁር ወይም ሰማያዊ ካልሲ ማድረግ ወይም ወደ መሳሪያ ቤት ለመሄድ ይሄኛውን አልያም ያኛውን መንገድ መምረጥህ እግዚአብሔርን ብዙ የማያሳስበው ጉዳይ እንደሆነ ታስብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ነገሮች በቀላሉ የማይታዩ መሆናቸውን ማወቅ ይኖብሃል፡፡ ለዚህ ነው በማንኛውም ሁኔታ በተገዢነት ልብ ከእግዚአብሔር ጋር መጓዝ የሚኖርብህ፡፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጥቅሶች ጊዜአችንን በመጠቀም ረገድ እግዚአብሔርን ምን ማማከር እንዳለብን ጠቃሚ ነጥቦችን ያሳዩናል፡፡ የተመለከትከውን ሃሳብ ፃፍ፡፡

 • ምሳሌ 3፡5-6
 • ምሳሌ 16፡3
 • ምሳሌ 20፡24
 • ኤርሚያስ 10፡23
 • ኤርሚያስ 29፡11
 1. ለማቀድ ጊዜ ይኑርህ

አንዳንድ ሰዎች ሁሉን ነገር በጥድፊያ ማድረግ ይወዳሉ፡፡ መስራት ያለባቸውን ነገር የሚያውቁት በሩጫ ላያ ሳሉ ነው፡፡ ትኩረት የማጣት ችግር አለባቸው፣ በዚህም ምክንያት በጥቂቱ ብቻ ውጤታማ ይሆናሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አስቀድመን እንድናቅድ በግልጽ ይመክረናል፡፡ ያለህን ግብአቶች፣ ጊዜ፣ እና ከንዘብህን ከግምት ውስጥ በማስገባት ምክንያታዊ እና ሊጨበጥ የሚችል እቅድ ንደፍ፡፡ አስቀድመህ ቀናቶችህን፣ ሳምንታቶችህን፣ ወራቶችህንና አመታቶችህን አቅዳቸው! ወደ እንተ ለሚመጡት ሁኔታዎች ምላሽ እየሰጠህ ከመኖር ይልቅ ሁኔታዎቹ ያንተን እቅዶች እንዲያገለገሉ አድርጋቸው!

 1. ታታሪ ሁን

የዌብስተር መዝገበ ቃላት ‹‹ታታሪ›› የሚለውን ቃል ሲፈታ፣ ‹‹ፅናትን፣ ብርቱ ጥረትን፣ ሀሞተ ኮስታራነትን፣ ስራ ወዳድነትን አጣምሮ የያዘ ማንነትን›› ያመለክታል፡፡ አንድ ሰው የሚፈልገውን እቅድ ሁሉ ሊያወጣ ይችላል ነገር ግን ይህን ለማስፈጸም ታታሪነት ከጎደለው ነገሩ ሁሉ እርባና ቢስ ይሆናል፡፡ በቆላሲያስ 3፡23-24 መሠረት በምንሰራው ስራ ሁሉ ታታሪ መሆን ካለብን ምክንያቶ መካከል አንዱ ምንድን ነው?

‹‹ታማኝነት›› ከ ‹‹ታታሪነት›› ጋር አብሮ ይሄዳል፡፡ በሉቃስ 16፡10 መሠረት እግዚአብሔር በሚሰጠን ጥቂቷ ነገር ሳይቀር ታማኝና ታታሪ የምንሆንበት ምክንያት ምንድን ነው?

ጥቂት ስለዚህ ጉዳይ አስብ፡- እንዴት ነው በአመት ውስጥ 11 ቀን ከግማሽ ያህል የስራ ቀናት በሕይወትህ ላይ መጨመር የምትችለው? ማድረግ የሚኖርብህ ከዚህ በፊት ከምትነሳበት ሰአት 15 ደቂቃ ብቻ ቀደም ብለህ መነሳት ነው! ይህንን ማስላት ትችላለህ፡፡ 30 ደቂቃ ቀደም ብለህ ብትነሳ ደግሞ በአመት ውስጥ ከሦስት ሳምንት በላይ ተጨማሪ የስራ ቀናት ማትረፍ ትችላለህ!

ምሳሌ 21፡5 አንብብና የትጉሃን ሃሳብ ወደ ምን እንደሚያደርስ ተናገር፡፡ ‹‹ችኩሎችስ›› ፍፃሜያቸው ምንድን ነው?

 1. ውጤታማነትን አጥብቀህ ተከታተል

ልብ ልትላቸው የሚገቡ ነጥቦች፡- እንዴት አድርጌ ነው ከዚህ በተሻለ ይህን ነገር የምሰራው? በተሻለ ፍጥነት እንዴት አድርጌ ነው የምሰራው? የተሻለ ውጤት እንዲኖረው ማድረግ የምችለው እንዴት ነው? ሁለት ነገሮችን በአንድ ጊዜ በመስራት ጊዜዬን እንዴት መቆጠብ እችላለሁ? አንዳንድ ነገሮችን ሌሎች እንዲሰሩት በመስጠት ጊዜዬን እንዴት መቆጠብ እችላለሁ?

 • በኤፌሶን 5፡15-16 መሠረት በጊዜዎቻችን በጥንቃቄ መጓዝ ያለብን ምክንያት ምንድን ነው?
 • ‹‹የቀናት ክፋት›› ከዚህ ጉዳይ ጋር ምን ግንኙነት አላቸው?
 • በ1 ቆሮንቶስ 14፡33፣40 መሠረት ነገሮችን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንጂ ስርአት በጎደለው መንገድ መስራት የሌለብን ምክንያት ምንድን ነው?
 1. እስኪዝሉ መስራትን አስወግድ፡- ጥቂት እረፍት አድርግ!

እያንዳንዱን ሰአት ‹‹ውጤታማ›› ለመሆን በማቀድ ከመጠን በላይ ታታሪ መሆን ይቻላል፡፡ ነገር ግን እረፍት በሕይወታችን ልንዘነጋው የማይገባ ትልቅ ጠጠር እንደሆነ እግዚአብሔር ግልጽ አድርጎልናል! የእረፍትን ጠቃሚነት እግዚአብሔር ግልጽ በሆነ መንገድ በአስሩ ትዕዛዛት ውስጥ አስፍሮልናል! ዘጸአት 20፡8-11 አንብብ፡፡ ከትዕዛዛቶቹ ይልቅ ይህ ትዕዛዝ ሰፋ ብሎ መገለጹን ልብ በል፡፡ ይህ ምን ያስገነዝብሃል? የዚህ ትዕዛዝ ዋነኛ አጀንዳ ሰንበትን ‹‹መቀደስ›› ቢሆንም ስለ ስራ ሃሳብም ይናገራል፡፡ ምን እንድናደርግ ነው የሚያዘን?

ማርቆስ 6፡30-31 አንብብ፡፡ ቁጥር 7 ላይ ማንበብ እንደምትችለው – ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሁለት ሁለት አድርጎ እንዲያገለግሉ ላካቸው፡፡ ከአገልግሎታቸው ሲመለሱ ስላደረጉት ነገር ሪፖርት አቀረቡ፤ በቀጣይ ስለሚያገለግሏቸው በርካታ ሰዎችም መደነቅ ይዟቸው ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን ከዚህ የተለየ ሃሳብ ነበረው፡፡ የኢየሱስ ቀጣይ አቅጣጫ ምን ነበር (ቁጥር 31)?

‹‹ወሰን›› አስምር፡፡ ‹‹ወሰን በእኛና በገደቦቻችን መካከል ያለ ክፍተት ነው፡፡ ለመጠባበቂያ እና ላልተጠበቁ ነገሮች የተቀመጠ ጊዜ ልንለው እንችላለን፡፡ በእድገትና ብልጽግና ውስጥ በተሸሸገ የስግብግብነት ባህሪ ምክንያት ይህ ወሰን በብዙ ሰዎች ተጥሷል፡፡ ይህ ክርስቲያኖችንም ይጨምራል። ይህ እረፍት የጎደለው ኑሮ በዚህ ዘመን የሚኖሩ ሰዎችን ጭንቀት፣ ሁከት እና ዝለት ምክንያት ይጠቁመናል! አንዳንድ ጊዜ ነገ ብዙ ለመስራት ዛሬ ጥቂት ነገር ብቻ መስራት ይኖርብህ ይሆናል፡፡

የጊዜ ሰሌዳህን በምታቅድበት ጊዜ ራስህን ዘና የምታደርግበት ጥቂት ጊዜ ማሰብን አትርሳ፡፡ በየቀኑ ለጥቂት ደቂቃዎች ራስህን ዘና አድርግ፡፡ ዊንስተን ቸርችል፣ ቤን ፍራንክሊን፣ ቶማስ ኤድሰን እና የመሳሰሉ በርካታ ውጤታማ ሰዎች ከቀትር በኃላ ጥቂት ጊዜ ለሸለብታ ያጠፋ ነበር፡፡ እሁድን ቀለል አርገህ ለማሳለፍ ሞክር፡፡ በወር አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ገለል ባለ ስፍራ ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ ለማሳለፍ አቅድ፡፡ ከቤተሰቦችህም ጋር አብረህ ዘና የምትልበትን ጊዜ አቅድ፡፡ ከባለቤትህ ጋር ብቻ የምትገናኝበት የቀጠሮ ጊዜ ይኑርህ፡፡ በጫካ ውስጥ የእግር ጉዞ አድርግ፡፡ ቆም ብለህ የአበቦችን ሽታ ለማድነቅ ጊዜ ይኑርህ፡፡ እረፍት ለማድረግ ታታሪ ሁን!

የቃል ጥናት ጥቅስ፡

ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥ ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና። የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና።-ቆላሲያስ 3፡23-24

ማጠቃለያ፡-

‹‹ምርጡ ጊዜህን ለእኔ ትሰጣለህ?›› ሲል ኢየሱስ ይጠይቅሃል፡፡

የደቀ መዝሙር ትምህርቱ ጥናት እዚህ ላይ ያበቃል። የእርስዎ መንፋሳዊ ጉዞ ግን ይቀጥላል። በመቀጠል መጽሐፍ ቅዱስን በርዕስ በጥልቀት እንዲያጠኑ እንጋብዞታለን። ይህንን ጥናት ለማድረግ መጀመሪያ ወደ ድረ ገጹ ዋና ገጽ (Home page) ይመለሱና “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት” በሚለው ርዕስ ስር ያሉትን ይመልከቱ።

ሌሎች ተጨማሪ የደቀ መዝሙር ትምሕርቶችን ለማጥናት ያሚሹ ከሆነ ደግሞ፣ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ጥናትዎን ይቀጥሉ። ግለሰብ ተኮር የደቀ መዝሙር ማሰልጠኛ ማኑዋል

ምዕራፍ 10- መንፈሳዊ ውጊያ

ይህንን ማወቅ ለምን ያስፈልጋል?

‹‹የባሕሩን ነፋሻማ አየር እያጣጣምን በዚህ መርከብ ላይ የምናሳልፈው መልካም የሽርሽር ጊዜ ጊዜ ይታየኛል፣›› አለ ማርቲን ለሚስቱ አብረው የሚያሳልፍቱን ጊዜ በአይነ ህሊናው እየሳለ፡፡

‹‹እውነት ብለሃል፣›› ስትል ሚስቱ ማውዴ መለሰች፡፡ እኔ ደግሞ የናፈቀኝ ያ ምቾት በተላበሰው የመርከቡ ላይ ድግስ መገኘት ነው! መቼም የመርከቡ ካፒቴን በአንዱ የምግብ ሥነ ስርአት ላይ ከእርሱ ጋር በአንድ ጠረጴዛ ላይ እንድንመገብ ይጋብዘናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››

‹‹በእርግጥ ይጋብዘናል እንጂ፣›› ሲል ማርቲን ለባለቤቱ መለሰላት፡፡ ‹‹ከእራት በኋላ ደግሞ በምሽቱ ጨረቃ ማራኪ የዳንስ ጊዜ ማሳለፍ፣ አይደል?››

‹‹ማርቲን፣ አንተ የፍቅር ሰው! ምን አይነት ወርቃማ ጊዜ እንደምናሳልፍ ይታየኛል፣›› አለች በረጅሙ ተንፍሳ፡፡

ከተወሰኑ ቀናት በኃላ የመርከቡን ካፒቴን በዋናው የመርከቡ አዳራሽ ውስጥ አገኙት፡፡ ማርቲን ካፒቴኑን ሰላም ካለው በኋላ ‹‹ካፒቴን፣ ላነጋግርህ እችላለሁ?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ‹‹እንዴታ፣ ስለምን ጉዳይ ነው? ረጅም ጊዜ የማይፈጅ መሆን አለበት፡፡ እንደምታውቁት ሥራ የሚበዛብኝ ሰው ነኝ፡፡››

‹‹እንዳውም ልናነጋግርህ የፈለግንህ ለዚሁ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ መርከብ ላይ የሚገኙ ሰራተኞች በሙሉ ሥራ የበዛባቸው ይመስላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፍላጎቶቻችን ለማሟላት እስካይችሉ ድረስ በስራ የተጠመዱ ይሆናሉ፡፡ እኛ በማናውቀው አንድ ሌላ ጉዳይ የተጠመዱ ናቸው፡፡ እንዳውም አንዳንድ ጊዜ ጥሩ ፊት አያሳዩንም!››

ካፒቴኑ በመገረም ከተመለከተው በኋላ፣ ‹‹ምን እያልክ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም —›› ማውዴ በተራዋ፣ ‹‹ካፒቴን፣ በዚህ መርከብ ላይ ለመውጣት ስንፈርም ከዚህ የተሻለ ምቾት፣ ከዚህ የተሻለ እንክብካቤ ጠብቀን ነበር፡፡ ምቾት የተላበሰው ድግስ ቀርቶ እየተመገብን ያለነው ወጥ ቤቶህ የሚያቀርቡልንን ተራ ምግብ ነው! በመርከቡ ላይ ያቀረብክልን ምቹና ለስላሳ ወንበሮች ሳይሆኑ በአሸዋ የተሞሉ ጆንያዎች ናቸው! ፈፅሞ የገመትነው ነገር አይደለም!››

በርቲን ደግሞ በተራው፣ ‹‹በመርከቡ ላይ የጠበቅነው መዝናኛ የለም። ይህ አልበቃ ብሎ ሰዎችህ መሳሪያዎች እየፈታን እንድንገጥም ሲያደርጉን ነበር፡፡ ለመጀመሪያዎቹ ጥቂት ጊዜያት ምንም አይልም ነበር፡፡ ከ 20 ቀናት በኋላ ግን ደጋግሞ ያንኑ ነገር ማድረግ አሰልቺ ነገር ሆኖብናል።›››

ማዉዴ ብሶቷን ማሰማቷን ቀጥላለች፣ ‹‹ስለጉዞአችን ከእኛ አወንታዊ ሪፖርት የምትጠብቅ ከሆነ ቢያንስ በአከባቢያችን አንድ ፍንዳታ በተሰማ ቁጥር ተከትለው የሚሰሙትን እነዚያን የማስጠንቀቂያ ደውሎችና ፉሽካዎች ዝም ማሰኘት ይኖብሃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሰዎችህ ቀንና ለሊት ሳይለዩ ያለማቋረጥ የሚተኩሷቸውን መድፎች ዝም ልታሰኝልን ብትችል እንደትልቅ እርዳታ እንቆጥረዋለን።››

‹‹እነዚያ የካሚካዝ የጦር አውሮፕላኖችስ?›› አለ ማሪቲን በመሃል ጥልቅ ብሎ፡፡ ‹‹ስልችት ብለውኛል፡፡ እነዚያ ጤና የጎደላቸው አብራሪዎች ሰው ሊጎዱ ይችላሉ እኮ!››

በመጨረሻ፣ ካፒቴኑ ችግሩ ምን እንደሆነ ተረዳ፡፡ ‹‹እናንተ ሰዎች፣ እንዴት ወደዚህ መርከብ ላይ ልትወጡ እንደቻላችሁ ወይም ይህ መርከብ ተራ የመጓጓዣ መርከብ እንደሆነ ልታስቡ እንዴት እንደቻላችሁ አላውቅም፡፡ ይህ መርከብ የጦር መርከብ ነው፣ እኛም በጦነት ውስጥ ነን!››

በርካታ ክርስቲያኖች ልክ እንደ እነዚህ ሰዎች ስላሉበት ቦታ የተሳሳተ መረዳት አላቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የተትረፈረፈ ሕይወት ሊሰጥህ እንደመጣ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንድ አማኝ ሊዘነጋው የማይገባው ሌላ ነገር ቢኖር አሁን የሚኖረው ጦርነት በታወጀበት ቀጠና ውስጥ መሆኑን ነው፡፡ ያ የተትረፈረፈ ሕይወት በዚህ የጦርነት አውድ ውስጥ መታየት ይኖርበታል፡፡ የገባንበት ጦርነት ስለ መሬት ወይም ስለ ፖለቲካ ሳይሆን ዘላለማዊ ስለሆነችው የሰው ነፍስ ነው፡፡ ሃሳብህ፣ አነሳሽ ምክንያቶችህ፣ ቅድሚያ የምትሰጣቸው ነገሮች፣ ንብረትህ፣ ታማኝነትህ እና ሰውነትህ የጦነቱ ሜዳዎች ናቸው፡፡

ራሳችንን ከጠላታችን እንዴት መከላከል እንዳለብን የምናውቅ ከሆነ በደህንነት መኖር እንችላለን፡፡ እንዴት ማጥቃት እንዳለብን የምናውቅ ከሆነ ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግስት እናሰፋለን፣ የጠላትንም ተፅእና እንገፋለን፡፡

ጸሎት፡- ‹‹አባት ሆይ የእኔ ፍላጎት በሁሉም ነገር አንተን ማክበር ነው፡፡ ነገር ግን ይህን ምኞቴን የሚጋፋ ጠላት አለኝ፡፡ አላማው እኔን ማጥፋት ነው፡፡ የአንተ ሃይል ከእርሱ ሃይል በማይቆጠር መጠን እንደሚበልጥ አውቃለሁ! የጨለማውን መንግስት እንድዋጋና ራሴን እንድመክት እንዴት ጦርነት ማድረግ እንደምችል አስተምረኝ፡፡ አሜን፡፡››

“በግዑዙ አለም ላይ ባሉ ሁኔታዎች እየተገለጠ ስላለው መንፈሳዊ ጦርነት ያለን ግንዛቤ ደካማ መሆኑን እኔ በበኩሌ ልቀበል እፈልጋለሁ፡፡ በግልጹ እየታየ ያለው ነገር፣ ክፉ መንፈሳዊያን ሠራዊቶች የክርስቶስን መንግስት ለማጥፋት የሚያደርጉት ጦርነት መሆኑን ልናውቅ ይገባል” – ጀምስ ስቴዎርት፣ ስኮትላንዳዊ የሥነ መለኮት ምሁር።

ጠላታችን ምን ይመስላል?

በ2ቆሮንቶ 2፡11 ሰይጣን፣ ‹‹—በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱ ሃሳብ አንስተውምና፡፡›› ሲል ጳውሎስ ስለ ሰይጣን ይናገራል፡፡ ጳውሎስ የሰይጣንን ሃሳብ እንዳይስት አነበብን፣ ነገር ግን የበሰሉ ክርስቲያኖች ጨምሮ በርካታዎቻችን ይህንን እውነት ሳንገነዘብ እንኖራለን፡፡ የዚህ ጥናት አላማ ጠላትህን እንድትገነዘብ ማድረግና በሴራው ላይ እንድትነቃ መርዳት ነው፡፡

የሰይጣን አጀማመር

በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሕዝቅኤል 28፡12-19 አንብብ፡፡ ሰይጣን በፍጥረቱ መጀመሪያ ላይ ምን ይመስል ነበር? [ቁጥር 12-15፣17 ተመልከት፡፡] ቁጥር 15 ‹‹—በደል እስኪገኝብህ ድረስ—›› ይላል፡፡ ከዛ በኃላ ምን ይመስላል? [ቁጥር 16-18 ተመልከት፡፡]

ስለ ሰይጣን ኃጢአትና አመፅ የበለጠ ለመረዳት በብሉይ ኪዳን የሚገኘውን የኢሳይያስ መጽሐፍ 14፡12-17 ተመልከት፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ደግሞ እግዚአብሔር በሌላ ነቢይ (ኢሳይያስ) አማካኝነት ለሌላ ንጉስ (ለባቢሎን ንጉስ) ተመሳሳይ ጭብጥ ያለው ሃሳብ ያስተላልፋል፡-

 1. ቁጥር 12 በትዕቢቱ ምክንያት ሰይጣን ላይ የደረሰውን ፍርድ ያመለክታል፡፡ አንድ ወቀት ሰይጣን ‹‹አጥቢያ ኮከብ፣›› እና ‹‹የንጋት ልጅ፣›› ነበር፡፡ ቅጣቱ ምንድን ነበር?
 2. ኢየሱስ ክርስቶስ የዚህ ትዕይንት የአይን ምስክር ነበር፡፡ ሉቃስ 10፡18 አንብብና ኢየሱስ ምን እንደተመለከተ ግለጽ፡፡
 3. ተመሳሳይ ትዕይንት በራዕይ 12፡9 ላይ ተገልጿል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ‹‹ታላቁ ዘንዶ›› ወደ ምድር እንደተጣለ እናነባለን፡፡ ከእርሱ ጋር ማን አብሮ ተጣለ?
 4. በኤፌሶን 6፡12 መሠረት ልንጋደለው የሚገባ እውነተኛ ጠላታችን ማን ነው?

ተጨማሪ ምልከታ፡- እግዚአብሔር ሰይጣንና ሌሎች መላዕክቶችን ሁሉ ህጸጽ አልባ አድርጎ ፈጥሯቸው ነበር፡፡ ክፋትን እግዚአብሔር አልፈጠረም፡፡ ሰይጣን የገዛ ነፃ ፈቃዱን በመጠቀም በአመጸ ጊዜ ክክብሩ ተጣለ። ሰዎችንም አሳተ። እግዚአብሔር ግን ገና ከመነሻው ይህን የሰይጣንን አሻጥር በጸጋ፣ በምህረት፣ በእምነት እና የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስን መስዋዕትነት በመጠቀም እንዴት አድርጎ እንደሚገለብጥ አስቀድሞ አቅዶ ነበር፡፡››

ተጨማሪ ምልከታ፡- ሰይጣን፣ አንድ ሶስተኛ የሚሆኑ መላዕክትን ከእርሱ አመፅ ጋር እንዲተባበሩ ለማድረግ ቢችልም የቀሩት ሁለት ሦስተኛ መላዕክት ግን ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆናቸውን ራዕይ 12፡4 ያስነብበናል፡ ያመጹት ጋኔን ሲባሉ የተቀሩት ግን መላዕክት ሆነው ቀሩ፡፡

የሰይጣን አላማዎችና ስልቶች

ከዚህ በታች የቀረቡትን ጥቅሶች ከተመለከትክ በኋላ የሰይጣንን አላማዎች ግለጽ፡፡

 1. ማቴዎስ 4፡1
 2. ማቴዎስ 4፡8-10
 3. ሉቃስ 8፡12
 4. ሉቃስ 13፡16
 5. ዮሐንስ 8፡44
 6. 2ቆሮንቶስ 11፡14-15
 7. 1ጴጥሮስ 5፡8
 8. ራዕይ 12፡9

ተጨማሪ ምልከታ፡- ሰይጣን እግዚአብሔር እንደሚገኝ፣ ‹‹በአንዴ በሁሉ ቦታ›› መገኘት አይችልም፡፡ ውሱን የሆነ ፍጥረት ቢሆንም እርስ በእርሳቸው ስኬታማ በሆነ መንገድ በመረጃ መረብ የተቆራኙ ናቸው፡፡ እንደአማኝ ከሰይጣን የበታቾች ጋር እንጂ ምናልባት በቀጥታ ከራሱ ከሰይጣን ጋር ላትገናኝ ትችላለህ፡፡ ነገር ግን በዚህ ጥናት ውስጥ ቀለል ባለ መንገድ›› ለመጻፍ ይቻል ዘንድ ‹‹ከሰይጣናዊ መንግስቱ›› ጋር የሚኖርህን ግንኙነት ከራሱ ከሰይጣን ጋር እንደምታደርግ አድርገን እናቀርባለን፡፡

የሰይጣን ቀዳሚ ዘዴ – ደጆች እና እድል ፈንታዎች

ሰይጣን እንዴት ሰዎችን ለማጥፋት እንደሚያቅድ ለማወቅ ወደ ዘፍጥረት ተመልሰን መመልከት ይኖርብናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስህን ዘፍጥረት 4፡1-12 ላይ ከፍተህ አንብብ፡፡ ይህ ክፍል የአዳምና ሔዋን የመጀመሪያ ሁለት ልጆችን ማለትም የቃየን እና አቤል ታሪክን ያስነብበናል፡፡ ክፍሉ ከዚህ በተጨማሪ የአላማችንን የመጀመሪያ የግድያ ወንጀልም ያስነብበናል – ይህ በዋናው ገዳይ (ሰይጣን) የተቀነባበረ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ቃየን እና አቤል ለእግዚአብሔር መስዋዕት ቢያቀርቡም በሆነ ምክንያት የቃየን መስዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ለምን እንደሆነ ባናውቅም ምናልባት መስዋዕቱን የሚያቀርብበት የልብ ዝንባሌ ሊሆን ይችላል፡፡ ቃየን በነገሩ በጣም ተበሳጨ፡፡ እግዚአብሔርም የቃየንን ልብ በመመልከት ጠቃሚ ምክር መከረው፡፡ ቃየን ግን ምክሩን ሊቀበል አልወደደም፡፡

 1. በቁጥር 7 ላይ መልካም የሆነውን ነገር ካላደረገ ኃጢአት በደጁ እንደምታደባ እግዚአብሔር ለቃየን ነገረው፡፡ ይህ ‹‹ደጅ›› ምን የሚያመለክት ይመስልሃል?
 2. ለምንድን ነው ኃጢአት በደጅ የሚያደባው? ምን ለማድረግ?
 3. እግዚአብሔር፣ ቃየን ምን እንዲያደርግ መከረው?

በ ኤፌሶን 4፡25-27 መሰረት፣ ቁጣ በራሱ ኃጢአት እንዳልሆነ እና በምንናደድበት ጊዜ የምናደርገው ነገር ኃጢአት ሊሆን እንደሚችል ወይም ቁጣችንን በጊዜ አንድ ነገር ካላደረግነው፣ ኃላ ላይ ኃጢአት ሊሆንብን እንደሚችል ይጠቁመናል፡፡ አሉታዊ ዝንባሌዎች ምላሽ ሳያገኙ በውስጣችን እንዲሰነብቱ ከፈቀድን፣ ለሰይጣን ‹‹ፈንታ›› የመስጠት አደጋ ውስጥ እንሆናለን፡፡

 1. ተራራ ወይም ዛፍ ለመውጣት እግር ለማስገቢያ የምትሆን ትንሽ ሽንቁር ያላትን ጠቀሜታ እላይ ከቀረበው ታሪክ አንጻር እንዴት ታየዋለህ?
 2. እግርህን ለመስቀል የምትረዳህን ሹንቁር ብታገኝ፣ ተራራውን ወይም ዛፉን መውጣት ‹‹ድል መንሳት›› መቻልህን እላይ ከቀረበው ታሪክ አንጻር እንዴት ታየዋለህ?

ሰይጣን በህይወትህ ላይ ተጽእኖ ለመፍጠር በአንድ ጊዜ ሁሉንም ነገር አይቆጣጠርም፡፡ ይህንን ማድረግ ፈፅሞ አይችልም፡፡ ነገር ግን ትንሽ ፈንታ ቢያገኝ፣ ማለትም ትንሿን የሕይወትህን ክፍል እንዲቆጣጠር ብትፈቅድለት፣ በሕይወትህ ትልልቅ ክፍሎች ላይ ድል ለመንሳት ይበልጥ ቅርብ ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር፣ ለሰይጣን የመጀመሪያውን እግር ማስገቢያ እንዳትፈቅድለት ይመክርሃል! አንዴ ይህንን ቦታ ከሰጠኸው መልሰህ ለማግኘት ትቸገራለህና!

በ ሉቃስ 22፡31-34 ላይ ኢየሱስ በይሁዳ ተክዶ፣ ከመያዙና ለፍርድ ቀርቦ ከመሰቀሉ በፊት ባለችው ለሊት ከስምኦን ጋር ሲነጋገር እናነባለን፡፡ ሰይጣን በእግዚአብሔር ፊት ጀብደኛ ጥያቄ ይጠይቃል፡፡

 1. ጥያቄው ምንድን ነበር?
 2. ይህ ምን ማለት ይመስልሃል?

በጴጥሮስ ሕይወት ውስጥ አንድ እክል ነበረ – ምናልባት ያ እክል ትዕቢቱ ሊሆን ይችላል። ይህም ሰይጣን በጴጥሮስ ሕይወት ውስጥ ሕጋዊ መብት እንዲያገኝና በእግዚአብሔር ፊት ቀርቦ የጴጥሮስን ሕይወት እንዲፈትን ፈቃድ ለማግኘት አስችሎታል፡፡ ጴጥሮስ የሰጠውን ደጅ ወይም ፈንታ በመጠቀምም ጥሎታል። ጴጥሮስ በፈተና ውስጥ በነበረበት ጊዜ እግዚአብሔር በሉአላዊ ስልጣኑ ይጠብቀው ነበር፡፡ ውድቀቱንም ለመልካም በመለወጥ ጴጥሮስ የተሻለ ሰው እንዲሆን ተጠቅሞበታል፡፡

የደጆች እና የእድል ፈንታ ሃሳብ ማጠቃለያ

በሕይወትህ ያለ ኃጢአት የሰይጣንን ትኩረት ይስባል፡፡ እርሱና አገልጋይ መናፍስቶቹ ያለማቋረጥ በህይወትህ ውስጥ አመቺ ሁኔታ ይፈልጋሉ፡፡ ምኞት ቢሆን፣ ትዕቢት ቢሆን፣ ቅንአት ቢሆን ወይም የመሳሰሉትን የሃጢአት ዝንባሌዎች ሲመለከት፣ ‹‹እዚህ ቦታ ላይ ዝንባሌ ይታየኛል፡፡ ይሄ ደካማ ጎኑ ነው፡፡ እስቲ ልጠቀምበት፡፡›› ይላል፡፡ ከዛም በበሩ ላይ በማድባት ደጁን ልትከፍትለት የሚያስችለውን አመቺ ሁኔታ ይጠብቃል፡፡ ሰይጣን ጥቃቅን እድሎችን በመጠቀም ሕይወትህን ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር ህልም አለው፡፡

ግልጽ መልዕክት አስተላልፈህለት በሩን በላዩ ላይ ልትዘጋ ወይም ክፍቱን ልትተውለት ትችላለህ፡፡ በርህን ክፍቱን ልትተው ስትፈቅድ እያልክ ያለኸው፣ ‹‹ሰይጣን ሆይ ሃሳብህን ለማስተናገድ ዝግጁ ነኝ፡፡ እንዴት ነው ፍላጎቶቼን የምታሟላው?›› ነው፡፡ እርሱ ደግሞ እቅዱን ያስረዳሃል፣ እናም ሞኝ ከሆንክ ታደምጠዋለህ ምክንያቱም እቅዶቹን አሳማኝ እንዲመስሉ አድርጎ ያቀርብልሃልና፡፡ ከዛም፣ የማታስተውል ከሆነ ያዘጋጀልህ ወጥመድ ውስጥ ትገባለህ፡፡

እግዚአብሔር ግን፣ ‹‹ገና ትንሽ ሳለ ንገስበት››፤ ልረዳህ የምትወድ ከሆነ እረዳሃለው፤ ነገር ግን መንፈሴ ወይም ሰይጣን ማን በሕይወትህ እድል ፈንታ ሊኖረው እንደምትወድ መወሰን ይኖርብሃል፡፡›› ሲል ይመክርሃል፡፡

‹‹በመንፈሳዊ ጦርነት ሙሉ ሙሉ ለመክተት፣ አስቀድመን ለሰይጣንና የእርሱ ለሆነው ሁሉ መራራ ጥላቻ ሊኖረን ይገባል፡፡ የሚያደርገውን መስፋፋት በቸልታ የምንመለከት ከሆነ በስንት ጥረት የተገኙ ግዛቶቹን መልሰን ልናጣቸው እንችላለን፡፡›› – ጎርዳን ቢ. ዋት

በመንፈሳዊ ውጊያ ያለን ስልጣን

ሰይጣንና ጋኔኖቹ እንዴት ያሉ ጨካኝ ጠላቶችህ እንደሆኑ ምናልባት አትረዳ ይሆናል፡፡ ሰይጣን ከዘመናት በፊት በሰው ልጅ ላይ ጦርነት አውጇል፡፡ ታላቅ ኃይል ስላለው በራሳችን ጉልበት ልንገጥመው ብንደፍር ሊያደቀን ይችላል፡፡

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስ አገልጋዮች በመሆናችን ምክንያት ስለተሰጠን ስልጣን ይናገራል፡፡ ለዚህ ስልጣን የግሪኩ አቻ የሚከተለው ነው፡- Exousia: ‹‹መብት፣ ኃይል፣ ስልጣን፣ የመግዛት ስልጣን፣ ስልጣንን የተሸከመ፡፡››

 1. በቆላሲያስ 2፡9-10 መሠረት አለቅነትና ስልጣናትን ሁሉ የያዘው ማን ነው?
 2. በፊልጵስዮስ 2፡9-11 መሠረት የኢየሱስ ስም ከምን ያህል ሰዎች በላይ ነው?
 3. በዚህ ስም የትኞቹ ጉልበቶች ናቸው መንበርከክ ያለባቸው?

ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚበልጥ ስልጣን በዚህ አለም ላይ የለም፡፡ በእርሱ Exousia (ስልጣን) ፊት የትኛውም ንጉስ፣ ፕሬዝደንት፣ ጋኔን መልአክ፣ ሰይጣንን ጨምሮ ሊቆም አይችልም፡፡ እኛ ደግሞ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆንን ከሰይጣን ጋር በሚኖረን ግንኙነት በዚሁ የስልጣን መጠን እንድንጠቀም ፈቃድ አግኝተናል፡፡ በኤፌሶን 2:6-7 መሠረት ከመንፈሳዊ ጠላቶቻችን አሻቅበን ህልቆ ሃይልና ስልጣን ባለበት በሰማይ በመንፈሳዊ ስፍራ በክርስቶስ ጋር ተቀምጠናል!

ነገር ግን በኃጢአትና ባለመታዘዝ ምክንያት ከዚህ መንፈሳዊ ሃይልና ሥልጣን ሸርተት ብንልና በጨለማው መንግስት ስር ራሳችንን ዳግመኛ ብናስገዛ፣ በዚህ መንግስት ላይ ጦርነት ለማወጅ አቅም በማጣት የተወሰነ የሽንፈት መጠን እንቀምሳለን፡፡ ይህ ሁኔታ ፈጥነን በመናዘዝ፣ ንስሃ በመግባትና ዳግመኛ መንፈስ ቅዱስ በመሞላት ሊቀለበስ ይችላል (ምዕራፍ 3 ተመልከት)፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ያልተሞላህ ከሆነ መንፈሳዊ ጦነትን ለማድረግ አትሞክር!

ጠቃሚ ምክሮች

 1. ክርስቲያን መሆን ማለት ምንም ችግር አያጋጥምህም ማለት አይደለም፤ የአፅናፈ አለሙ ብልህ ችግር ፈቺ ባንተ ውስጥ አለ ማለት እንጂ፡፡
 • 1ጴጥሮስ 5፡7-9 አንብብ፡፡ ይህ መልዕክት ለአማኞች የተጻፈ ነው፡፡ ‹‹በመጠን ኑሩ፣ ንቁም›› ይላል፡፡ ለምን?
 • ክርስቲያኖችን በተመለከተ የጠላት የመጨረሻ ግቡ ምንድን ነው (ቁጥር 8)? ለዚህ ማስፈራሪያ ምላሻችን ምን ሊሆን ይገባል (ቁጥር 9) ?
 • የዮሐንስ 16፡33 ጥቅስ ክርስቲያኖችንና የሚገጥማቸውን አስቸጋሪ ሁኔታ በተመለከተ ሁለት ጥቅል ‹‹ተስፋዎችን›› ይናገራል፡- በዓለም ሳለን በእርግጥ ———— አለብን። ነገር ግን ልንፅናና ይገባል ምክንያቱም ————-
 • ለምንድን ነው ሁለቱም እነዚህ እውነታዎች ሊያበረታቱን የሚገባው?
 1. እንደ ክርስቲያን ስትኖር፣ ወደ ሕይወትህ የሚመጡ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ከዚህ በታች በተዘረዘሩ አራቱ ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል –

ሀ. ሞኛ ሞኝ ወይም ኢ – ሞራላዊ የሆኑ ድርጊቶች ስታደርግ

በምስማሩ ፈንታ አውራ ጣትህን ብታስቀምጥ፣ ቅድመ ጥናት ሳታደርግ አክሳሪ በሆነ ካምፓኒ ውስጥ ሙአለ ንዋይን ብታፈስ፣ ሰካራም ብታገባ፣ ያለምንም ፓራሹት ከአስረኛ ፎቅ ላይ ብትዘል፣ የሚገጥምህ ነገር ምን እንደሆነ ብዙ መመራመር አያስፈልግም። በገላቲያ 6፡7 ላይ የተገጸው ሃሳብ ከእነዚህ ሃሳቦች ጋር ምን ግንኙነት አለው?

ለ. የሰይጣን ፈተናዎች

የሰይጣን የቀንና የሌሊት ጥረቱ በእግዚአብሔር ላይ እንድታምጽና የእርሱን መንገድ እንድትከተል ማድረግ ነው፡፡ 1ዮሐንስ 2፡15-16 የሰይጣንን ፈተናዎች ሶስት አቅጣጫዎች ያስነብበናል፡፡ እነዚህን ሦስት የፈተና አቅጣጫዎችን ጻፍና ምሳሌዎችን ፈልግላቸው፡፡

የምታሰላስለው ነጥብ፡- ሰይጣን የፈተና ስልቱን ለዘመናት አልቀየረም፡፡ በእርግጥም፣ መቀየር አላስፈላገውም አሁንም ድረስ ውጤታማ ናቸውና!

ሐ. በኃጢአት ውጤት ምክንያት እግዚአብሔር ሲቀጣን

እግዚአብሔር ልጆቹን ይወዳል፡፡ ማንኛውም ለልጁ ፍቅር ያለው አባት ልጁ ባልተገባ ስፍራ እንዲሆን አይፈቅድም፡፡ ይልቁንም ይህን ባሕሪ እንዲታረም ያደርጋል እንጂ፡፡ ይህን የሚያደርገው ልጁን ለመጉዳት ሳይሆን የተወሰደውን የተሳሳተ ምርጫ ለማረም እንጂ፡፡ የሰማዩ አባታችንም የሚያደርገው ይህንኑ ነው፡፡

ዕብራዉያን 12፡4-11 አንብብ፡፡ ይህ ክፍል እግዚአብሔር ለማረም ሲቀጣን በበጎ ፈቃድ እንድንቀበለው ይመክረናል፡፡ ለምን? (ቁጥር 10-11 ተመልከት)፡፡

መ. ወደ ተሻለ ከፍታ ለማሳደግ በእግዚአብሔር ስንፈተን

አሰልጣኞች አትሌቶቻቸው ወደፊት ለሚገጥማቸው ታላቅ ውድድር ጥንካሬንና ጽናትን እንዲላበሱ በአስቸጋሪ ልምምድ ውስጥ እንዲያልፉ ያደርጓቸዋል፡፡ እግዚአብሔርም ‹‹አትሌቶቹ›› በፊታቸው ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታ መቋቋም እንዲችሉ፣ እዲበስሉና የበለጠ ጠቃሚ እንዲሆኑ ፈታኝ በሆነ ልምምድ ውስጥ ይከታቸዋል፡፡

በ 1ጴጥሮስ 5፡10 መሠረት ፍፁማንና ብርቱ ከመሆናችን በፊት የምናልፍበት ነገር ምንድን ነው?

አትሌቶች በአስቸጋሪ ልምምድ ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ ሁሉ ለመታገስ እንዲችሉ በውድድሩ ግብ (ውጤት/መጨረሻ) ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ክርስቲያኖች ከዚህ ምን ሊቀስሙ ይችላሉ?

 1. መዛራትና ማጨድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ ነው። ያም ሆኖ ከላይ በተገለጹት አራት ምክንያቶች ወደ አማኙ ሕይወት ያሚመጡ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እግዚአብሔር ለመልካም ይለውጣቸዋል።
 • በዚህ ጥናት ውስጥ ገላቲያ 6፡7 አስቀድመን አይተናል (የመዝራትና የማጨድ ጥቅስ) ፤ አሁን ደግሞ ሮሜ 8፡25ን ተመልከት፡፡
 • ምን ያህል ነገሮች ናቸው እግዚአብሔርን ለሚወዱት ለበጎ የሚደረግላቸው?
 • ይህ ‹‹መጥፎ›› ነገሮችንም ጭምር እንደሚያጠቃልል ታስባለህ?
 • ይህ ጥቅስ እያንዳንዱ መንገድና እያንዳንዱ ሁኔታ መልካም እንደሆነ ይናገራል?
 • ይህ ጥቅስ በሕይወትህ ስለሚገጥሙህ አስቸጋሪ፣ የሚጎዱ፣ ፈታኝ፣ እና መጥፎ ሁኔታዎች ምን ይነግርሃል?

‹‹ክርስትና ከአለምና ከችግሮቿ አይለይህም፤ ጠቃሚ በሆነ ሁኔታና በድል በውስጧ እንድትኖር ያመቻችሀል እንጂ፡፡›› ቻርለስ ቴምናልተን

ማጨድ ሁል ጊዜ መዝራትን ይከተላል፡፡ ይህ አለማቀፋዊ መርህ ነው፡፡ እያንዳንዱ ምክንያት ውጤት አለው፡፡ እግዚአብሔር እነዚህን ቁሳዊም ሆኑ መንፈሳዊ ሕጎች የፈጠረው፣ ፍጥረት ያለ እንከን እንዲኖር ነበር፡፡ እነዚህ ሕጎች ለተወሰኑ ሰዎች የተበጁ አይደሉም፡፡ በመሆኑም ማንም ሆንክ ምን ሕጎቹን ብትሰብር እነርሱ መልሰው ይሰብሩሃል፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ሆንክም አልሆንክም ከ 10ኛ ፎቅ ላይ ራስህን ብትጥል፣ ፈጥነህ ወርደህ ትከሰከሳለህ፤ በርካታ አጥንቶችን ታደቃለህ አንተም ለከፍተኛ ሕመም ትዳረጋለህ ወይም ትሞታለህ፡፡ ይህ የምክንያትና ውጤት፣ የድርጊትና ምላሽ እውነታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይህንን አሳዛኝ፣ የስቃይ ‹‹የመዝራትና የማጭድ›› ልምምድ በመውሰድ ለሚወዱትና ከእርሱ ጋር ተባብረው ለሚሰሩት ለመልካም ሊለዉጥላቸው ይችላል፡፡

ለገጠመን አስቸጋሪ ሁኔታም ሆነ ችግር መነሻ ምክንያቱ እግዚአብሔር ነው ብሎ ለመናገር ከባድ ነው፡፡ አንዳንዴ ሊሆን ይችላል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ላይሆን ይችላልና፡፡ በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ልትሆን ትችላለህ፣ ይኸውም – እግዚአብሔር በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ወቅት እንደሚረዳህ፣ ከምትሸከመው በላይ እንዳይሆን እንደሚያደርግ (1ቆሮንቶስ 10፡13)፣ የሚረዳህን ጸጋ እንደሚሰጥህ እና ችግሩን ከፍጹም አላማው ጋር እንደሚያስማማው፡፡

 1. ክርስቲያኖች ከፈተና ሊሸሹና ዲያብሎስን ሊቃወሙት ይገባል፡፡

ክርስቲያኖች ይህን ሃሳብ ገልብጠው፣ ‹‹ከሰይጣን ልንሸሽ›› እና ‹‹ፈተናን ልንቃወም›› ይገባናል ብለው ያስባሉ፡፡ ይህ ግን መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው ተቃራኒ ነው!

 • 2ጢሞቴዎስ 2፡22 የሚመክረን፣ የጎልማሳ ምኞቶቻችንን ቆመን እንድንዋጋቸው ነው ወይስ ቦታችንንና አቅጣጫችንን ፈጥነን በመቀየር በሌሎች ነገሮች እንድንጠመድ?
 • ልክ እንደማይደፈሩ ጠላቶች ከእነዚህ ምኞቶች በመሮጥ ‹‹እንደፈሪ›› አይነት እርምጃ እንድንወስድ የታዘዝነው ለምን ይመስልሃል?

ሰይጣንን ደግሞ ልንሸሸው ሳይሆን ልንቃወመው ይገባል፡፡ ከእርሱ ወይም ከክፉ ስራዊቶቹ ፊት አንሸሽም፣ ጸንተን እንዋጋቸዋለን እንጂ፡፡ ያዕቆብ 4፡7 ልብ አድርገህ ተመልከት፣ የእኛ ድርሻ መቃወም ብቻ ነው፣ መምታት፣ መግረፍ፣ መደብደብ አይደለም፡፡ ይህን ስናደርግ በእግዚአብሔ ቃል ተስፋ መሠረት ከእኛ ይሸሻል!

ኤፌሶን 6፡10-18 አንብብ፡፡ የእግዚአብሔርን ጦር ዕቃ ሁሉ እንድንለብስ መታዘዛችንን ልብ በል፡፡ ለምንድን ነው ሰዎች የጦር መሣሪያን የሚታጠቁት?

‹‹እንድንለብስ›› የታዘዝነውን የጦር መሣሪያ ልብ በል፡፡ ከዛም እያንዳንዱ መሳሪያ ያለውን ጠቀሜታ ወይም ከምን እንደሚከላከለን ጻፍ፡፡

 • የእውነት መታጠቂያ
 • የጽድቅ ጡሩር
 • የሰላም ወንጌል ጫማ
 • የእምነት ጋሻ
 • የመዳን ራስ ቁር
 • የመንፈስ ሰይፍ – የእግዚአብሔር ቃል
 • ዘወትር መጸለይ

ሀ. ዲብሎስን ለመቃወም ጠቃሚ የሆነ አካሄድ

የ ያዕቆብ 4፡7-8 መልእክት፣ ሰይጣንን ለመቃወም ልንጠቀምበት የሚገባንን አካሄድ ያመለክተናል፡፡ ይህን ሃሳብ ንብረት ለመዝረፍ ወደ ቤትህ ከገባ ቤት ሰርሳሪ ጋር ለመጋፈጥ ከምታደርገው ሁኔታ ጋር አዛምደህ ተመልከተው፡፡ በዚህ መሠረት አራት እርምጃዎችን ትወስድ ይሆናል (መመርመር፣ መታጠቅ፣ ማጥመድ፣ መጠናከር)፡፡ እነዚህ አራት ደረጃዎች ጠላታችን በሆነው ዲያብሎስ ላይ የምንወስዳቸው እርምጃዎችም ጭምር ናቸው፡፡

የመጀመሪያ እርምጃ ፡ መመርመር። ‹‹በሰይጣን እንዳንታለል፣ የእርሱን ሃሳብ አንስተውምና፡፡›› -2ቆሮንቶስ 2፡11። ምሳሌ፦ ‹ሰይጣን ኃጢአት እንድሰራ እየፈተነኝ ሳይሆን አይቀርም!››

ሁለተኛ እርምጃ፡ መታጠቅ። ‹‹እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፡፡›› ያዕቆብ 4፡7። ሰይጣንን ለመዋጋት እግዚአብሔር እንዲረዳህ ጸልይ፡፡ በሰማያዊ ስፍራ በክርስቶስ ያለህን ስልጣን መያዝህን አትዘንጋ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ስለመሞላትህ እርግጠኛ ሁን፡፡

በፈተናዎችህ ወቅት የሚከተለውን አይነት ጸሎት መጸለይ ትችላልህ፡- ‹‹አባት ሆይ ባንተ ላይ ኃጢአትን እንድሰራ ሰይጣን እየፈተነኝ ነው፡፡ ስላለሁበት ሁኔታ እንድዋሽ ይፈልጋል፡፡ ልነግስበት እፈልጋለሁ፡፡ እባክህ በመንፈስህ ሙላኝ፡፡ ከስልጣናት፣ ከኃይላት፣ ከገዢቆችና ከክፉ ሃይላት በላይ የሚያደርገኝን በአንተ ቀኝ በመንፈሳዊ ስፍራ ከክርስቶስ ጋር የተቀመጥኩበትን ስፍራ እይዛለሁ፡፡ በአንተ በረከት፣ ጥበቃ እና ኃይል ጠላቴን እንድቃወምና እንዳሸንፈው እንድትረዳኝ እለምንሃለው፡፡››

ልትመክትበት የሚያስችልህ እንደ መሣሪያ ወይም ዱላ ወይም ሌላ ነገር በእጅህ ሳትይዝ ሠርሳሪን መጋፈጥ ሞኝነት እንደሆነ ሁሉ በራሳችን ሃይል የጨለማውን ሃይላት ለመጋፈጥ መሞከር በራስ ላይ ችግር መጋበዝ ነው፡፡

ሦስተኛ እርምጃ፡ ማጥመድ። ‹‹ዲያብሎስን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፡፡›› ያዕቆብ 4፡7። ዋነኛ የጦር መሳሪያህን ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል በመጠቀም ልክ ኢየሱስ በማቴዎስ 4፡1-11 ላይ እንዳደረገው ጠላትህን ፊት ለፊት ግጠመው፡፡

ፊት ለፊት ለመግጠም የምክር ሃሳብ፡- ‹‹አንተ ሰይጣን፣ የነገስታት ንጉስ የጌቶች ጌታ በሆነው እና በደሙ ገዝቶ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ባደረገኝ በኢየሱስ ክርስቶስ ስልጣን እመጣብሃለው፡፡ ኃጢአት እንድሰራ የምታደርገውን ተንኮል አውቄአለሁ፡፡ ይህን በማድረግህ በዘሌዋዊያን 19፡11 ላይ በተጻፈውና ‹‹አትስረቁ፣ አትካዱም፣ ከእናንተም እርስ በእርሳችሁ ሐሰት አትነጋገሩ፡፡›› በሚለው የእግዚአብሔር ቃል ላይ አፊዘሃል፡፡ እንድዋሽ እየሞከርክ በመሆኑ በእግዚአብሔር በተሰጠኝ ስልጣን በኔ ላይ ያነጣጠርከውን ስራ እንድታቆም፣ እንድትተወኝ እና ኢየሱስ ወዳዘዘህ ስፍራ እንድትሄድ አዝሀለው፡፡››

ኢየሱስ በምድረ በዳ ከሰይጣን ጋር ያደረገውን ታላቅ መጋፈጥ የሚተርከውን የማቴዎስ 4፡1-11 ክፍልን አንብብ፡፡ ኢየሱስ ዋነናኛ መሣሪያውን እንዴት እንደተጠቀመ ልብ በል፡፡ እያንዳንዱን የጠላት ፈተና ለመቃወም ሦስት ጊዜ የተጠቀመበት ሃረግ ነበር፡፡ ያ ሀረግ ምንድን ነው? (ቁጥር 4፣7፣10)

እላይ የተዘረዘሩትን መንፈሳዊ የጦር መሣሪያዎች ወደ ኃላ በመሄድ ተመልከት፡፡ ሰባት የተዘረዘሩ መሳሪያዎች ሲኖሩ ከነዚህ መካከል ስድስቱ የመከላከያ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ለማጥቂያ የሚውለው የቀረው አንዱ መሣሪያ ምንድን ነው?

‹‹የድልህ መሠረት የክርስቶስ ሞት ነው፡፡ ይህ ሞት ከኃጢአት ኩነኔ ለይቶ የዘላለም ሕይወት የሚያስገኝህ ሞት ብቻ ሳይሆን ከክፉው ድንገተኛ አደጋም ጭምር የሚሰውርህ ነው፡፡›› ጄለ ዱዋይት ፔንተኮስት

አራተኛ እርምጃ፡ መጠናከር። ‹‹ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል፡፡›› – ያዕቆብ 4፡8። ከጦርነት በኃላ፣ ጥቂት ቆይታ በጸሎት መውሰድ፣ እግዚአብሔርን ማመስገን፣ ማወደስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ፣ ድሉን በማተም ራስህን ማጠናከር ያስፈልጋል።

የቃል ጥናት ጥቅስ፡

‹‹እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።›› ያዕቆብ 4፡7-8

ማጠቃለያ፡

‹‹ከእኔ ጎን በመሆን ትዋጋለህ?›› ሲል ኢየሱስ ጥያቄ ያቀርብልሃል፡፡

ምዕራፍ 11ን ያጥኑ

ምዕራፍ 9 – ምስክርነት

ጸሎት

‹‹አባት ሆይ፣ ይህችን ምድር ዳግመኛ ለመግዛት በምታደርገው ሂደት ውስጥ እንደ እኔ አይነቱን ሰው ለመጠቀም ስላሳየኸው ፍላጎት አመሰግንሃለው፡፡ የሚጠቅም እቃ ሆኜ እንዳገለግልህ ፍቅር፣ እውቀት እና ከቅዱስ መንፈስህ ጋር ጤናማ ሕብረት ስጠኝ፡፡ አሜን፡፡››

ስለምስክርነት ማወቅ ለምን ያስፈልጋል?

ሉጊ ታሪሶ የታሪክ ማህደር ከሚያስታውሳቸው ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በ1792 በጣሊያን ሚላን የተወለደ ሲሆን በመጀመሪያ የአናፂነት ሙያ ሰልጣኝ ተማሪ ነበር፡፡ ታሪሶ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለየት ያሉ ቫዮሊኖችን ለመሰብሰብ ሲል ያላካለለው አገር አልነበረም፡፡ በምርጥ ሞያተኞች የተሰሩ ልዩ ቮዮሊኖችን በማደን ልዩ ተሰጥኦ ነበረው፡፡ እነዚህን ቫዮሊኖች ገዝቶ በጥንቃቄ በመኪናው ጭኖ ካመጣቸው በኃላ በትንሿ መኖርያ ቤቱ ውስጥ ያስቀምጣቸዋል፡፡ የእለት ችግሩን ለመፍታት ከሸጣቸው ጥቂት ቫዮሊኖች በስተቀር የገዛቸው በርካታዎቹ ቫዮሊኖች በመኖሪያ ቤቱ ደብቆ አስቀምጡአቸዋል፡፡ አንዳንድ የአለማችን ታዋቂ ሙዚቀኞች እነዚህን ቫዮሊኖች ለመጎብኘት ወደ ታሪሶ ይመጡ ነበር፡፡ እንዲጫወቱ ግን ፈፅሞ አይፈቅድላቸውም ነበር፡፡

ከቫዮሊኖቹ ሀሉ ለእርሱ ልዩ የነበረው በአንቶኒዮ ስትራዲቫሪ የተበጀው ቫዮሊን ነበር፡፡ ታሪሶ በዚህ ቫዮሊን ውበት በጣም ቢኩራራም በግላጭ አውጥቶ ለማሳየት ግን አይፈቅድም ነበር፡፡ አንድም ጊዜ አውጥቶ አሳይቶት አያውቅም፡፡ ስሙን ‹‹መሲህ›› ብሎ ሰይሞታል ምክንያቱንም ሲገልጽ ‹‹ቫዮሊኑ፣ እንደምንጠብቀው ግን እንደማናየው መሲህ ስለሆነ ነው›› ይላል፡፡

ታሪሶ በ1854 ከዚህ አለም በሞት ሲለይ በቆሻሻ መኖሪያው መሲሁን ጨምሮ 246 የሚደርሱ ውብ ቫዮሊኖች ተቀምጠው ተገኙ፡፡ ለቫዮሊን ካለው ልዩ ፍቅር የተነሳ እነዚህን ውብ የሙዚቃ መሳሪያዎች ከአለም ሸሽጎ ኖረ፣ ባይቆልፍባቸው ኖሮ ሊሰጡ የሚችሉትንም ጥቅም አስቀረ፡፡

በውስጣችን ያለውን መሲህ (ኢየሱስ) ለሌሎች ሳንገልጠው ይህን ታልቅ የምስራች ዜና በእኛ ውስጥ ቆልፈን እንድንኖር እግዚአብሔር አይፈልግም፡፡ ጌታ ኢያሱስ በእኛ ውስጥ ከመኖሩ የተነሳ ሕይወታችን በሚያስደንቅ ሁኔታ ተባርኳል፣ ነገር ግን የእርሱ ምኞት አለሙ ሁሉ ይህን በርከት እንዲካፈል ጭምር ነው፡፡ ይህንን የምስራች ማንም ሊደርስበት በማይችለው የሕይወታችን አፓርትመንት ውስጥ ሸሽገነው እስከመቼ በስስት እንኖራለን?

የካምፓስ ክሩሴድ ለክርስቶስ መስራች የሆነው ቢልብራይት ብዙ ጊዜ እንደሚጠይቀው፣ ‹‹በሕይወትህ ላይ የሆነልህ ታላቅ ነገር ምንድን ነው?›› ተብለን ብንጠየቅ፣ የብዙዎቻችን መልስ፣ ‹‹ክርስቶስን እንደ ግል አዳኜ ማወቄ፣›› ብለን ምላሽ እንሰጥ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም የተቀበልነው ሕይወት ዘላለማዊ ነውና፡፡ የዚህ ሰው የሁል ጊዜ ቀጣይ ጥያቄ፣ ‹‹እናስ፣ ለሌላው ሰው ልታደርግ የምትችለው ታላቅ ነገር ምንድን ነው?›› የሚል ሲሆን፣ ጥያቄው ለአንተ ቀርቦ ቢሆን ምላሽህ ምንድን ነው?

በክርስቶስ ላይ ያለህን እምነት ለሌሎች በማካፈል ሃሳብ ላይ ያለህ ስሜትና አስተሳሰብ ምን ይመስላል? ጉዳዩ በውስጥህ ደስታን ይጭራል ወይስ ፍርሃትን? ድፍረት ይሰማሀል ወይስ አንድ አንድ ጊዜ ሊደርስብህ የሚችለው ተቀባይነት የማጣት ስሜት ያስፈራሃል? በራስ የመተማመን ስሜት ይሰማሀል ወይስ ግር ትሰኛለህ? የግዴታ ስሜት ይሰማሃል ወይስ የፈቃደኝነት?

‹‹በእኔ እምነት በዘመናት ሁሉ የክርስቲያኖች መካከል በስፋት ተሰራጭቶ የሚገኘው የተሳሳተ ግምት፣ ሰዎች እግዚአብሔርን አይሹም – የሚለው ነው፡፡ በተለያዩ አገሮች ስጓዝ ያገኘሁት በቂ ማስረጃ ግን የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በበርካቶች ልብ ውስጥ እግዚአብሔርን የመፈለግ ረሀብን ፈጥሮ ተመልክቻለሁ፡፡›› ቢል ብራይት

ወንጌል ምንድን ነው?

ከዚህ በታች ወንጌልን በአጭሩ የሚገለጹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ቀርበዋል፡፡ ካነበብካቸው በኃላ በውስጣቸው ስለ ወንጌል የያዙትን ፍሬ ሃሳብ ፃፍ፡፡

 1. ዮሐንስ 3፡16
 2. ሉቃስ 24፡46-48
 3. 1ቆሮንቶስ 15፡3-4

ተጨማሪ ምልከታ፡- ‹‹ወንጌል የሚለው ቃል የግሪክ አቻ ቃሉ evangelion ሲሆን ትርጓሜውም ‹‹የምስራች›› ወይም ‹‹አስደሳች ዜና›› ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል ‹‹evangelism›› ለሚለው ቃል ስርወ ቃልም ጭምር ነው፡፡

የወንጌል በአጭሩ፡- ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በኃጢአት ምክንያት በደለኛ ነው፡፡ የኃጢአት ደምዎዝ ሞት (ለዘላለም ከእግዚአብሔር ተለይቶ መኖር) ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ታላቅ ፍቅር የተነሳ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአታችንን ቅጣት ይቀበልልን ዘንድ በመስቀል ላይ ስለኛ እንዲሞት ላከው፡፡ ከሦስት ቀን በኋላ ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነሳ፣ ሕያው ሆኖ ለዘላለም ይኖራል፡፡ አንድ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እና ከዘላለም ሞት ሊያድነው እንደሚችል ቢያምን ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ተደርጎ ይቆጠራል፣ የዘላለም ሕይወትን ይወርሳል፡፡

ምስክርነት ምንድን ነው?

‹‹ምስክርነት፣ የኢየሱስን ወንጌል በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ለሌሎች ለማካፈል መነሳሳት እና ውጤቱን ለእግአዚብሔር መተው ነው፡፡›› ቢል ብራይት

በግርድፉ፣ ምስክርነት የምታውቀውን ነገር መናገር ማለት ነው፡፡ ልክ ጴጥሮስና ዮሐንስ የአይሁድ ባለስልጣናት ስለ ኢየሱስ እንዳይመሰክሩ ባስጠነቀቋቸው ጊዜ እንደመለሱላቸው ማለት ነው – ‹‹እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 4፡20) ፡፡ ስለ ኢየሱስ ምን ሰምተሀል፣ ምንስ አይተሃል? ይህንን እርሱን ለማያውቁ ሌሎች ሰዎች ስታካፍል እየመሰከርክ ነው፡፡

እስቲ በችሎት ውስጥ ያለውን ትእይንት እንመልከት፡፡ በችሎት ያሉ ሰዎች ሁሉ የራሳቸው የሆነ ሚና እና ሃላፊነት አላቸው፡፡ እንደ ‹‹መስካሪ›› የምትጫወታቸው ሚና ምንድን ናቸው?

የከሳሹን ጥፋተኛነት የሚወስኑትን ሰዎች ማሳመን ያንተ (የምስክሩ) ድርሻ ነው? የአንተ ዋነኛ የቤት ስራ እሱ አይደለም፡፡ እንደ አቃቤ – ሕግ መሆን ይኖርብሃል? እንደ ተከላካይ ጠበቃስ? እንደ ዳኛስ? ለሶስቱም ጥያቄዎች መልሱ ፈፅሞ ነው፡፡ እንደ ምስክር ከአንተ የሚጠበቀው ነገር ‹‹ያየኸውንና የሰማኸውን መናገር›› ሲሆን እግዚአብሔር ደግሞ የቀረውን ያከናውናል፡፡

በችሎት ፊት የቀረበ ምስክር የሚጠበቅበት ነገር ‹‹እውነቱን፣ ሁሉንም እውነት፣ እና እውነቱን ብቻ›› መናገር ነው፡፡ እንደ ክርስቶስ ምስክር፣ በሕይወትህ የሆነልህን ነገር አጋነህ ወይም አኮስሰህ በተሳሳተ መንገድ ብትገልጥ ይህ ታማኝነትህን አያሳይም፡፡ እውነትንም መሸሸግ ከዚህ የተለየ ትርጉም አይኖውም፡፡ ማድረግ ያለብህ ነገር የሚሹ ሁሉ ያነቡት ዘንድ ሕይወትህን እንደተገለጠ መጽሐፍ ለሌሎች ማሳየት ነው፡፡ ይህን ካደረግህ በእርግጥ የክርስቶስ ጠቃሚና ውጤታማ ምስክር መሆን ትችላለህ!

በምስክርነት ውስጥ የእግዚአብሔር ድርሻ

‹‹ያየኸውንና የሰማኸውን›› ነገር ለአንድ ሰው ለመመስከር በምትጥርበት ጊዜ እግዚአብሔር ደግሞ ምናልባት አንተም ሆነ የምትመሰክርለት ሰው በማትረዱበት መንገድ ታላቅ ስራን ይሰራል፡፡

ዮሐንስ 16፡7-11 አንብብ፡፡ [በዚህ ክፍል ውስጥ የተገለጸው ‹‹ረዳት›› ወይም ‹‹አጽናኝ›› እግዚአብሔር ከክርስቶስ ትንሳኤ በኋላ የላከው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡] ክፍሉ፣ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሚያደርግ ነው የሚያወራው?

በውጤታማ ምስክርነት ውስጥ የእግዚአብሔር ድርሻ ወሳኝ በመሆኑ፣ በምስክርነት ስልትህ ውስጥ ለጸሎት ቅድሚያ ልትሰጥ ይገባል።

‹‹በወንጌል ስርጭት ወቅት ሁለት ሰአት ከሚፈጅ ንግግር ይልቅ የጥቂት ደቂቃ ጸሎት የበለጠ ስራ ይሰራል፡፡›› ዲ.ኤል.ሙዲ

‹‹ለሰዎች ስለ እግዚአብሔር ከመናገርህ በፊት ስለ ሰዎቹ ለእግዚአብሔር መናገርህን እርግጠኛ ሁን፡፡›› ጆ አልድሪክ

ለምን እመሰክራለሁ?

ከዚህ በታች ለጥያቄው ምላሽ የሚሰጡ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ቀርበውልሃል፡፡ ጥቅሶቹን ካነበብክ በኋላ ያስተዋልከውን ነገር በማስታወሻህ ላይ አስፍር፡፡

 1. ማርቆስ 16፡15
 2. ሉቃስ 19፡10 እና 2ጴጥሮስ 3፡9
 3. ሮሜ 10፡13-14
 4. ዮሐንስ 10፡10
 5. ሉቃስ 9፡26

እንዴት ልመስክር?

ምስክርነት ሁለት በጣም ጠቃሚ ነገሮችን ያካትታል፡፡ በምንኖረው የሕይወት አይነት እንመሰክራለን፤ በተጨማሪም በቃላቶቻችን – በንግግር እንመሰክራለን፡፡ አንዱ ከአንዱ ውጪ ሲሆን በራሱ ሙሉ አይደለም፡፡ ሕይወታችን ክርስቲያን ላልሆኑ ሰዎች የሚናገረው ነገር ይኖረዋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ ሕይወታችን በቃላችን የምናካፍለው መልዕክት አውድና ማረጋገጫ ነው፡፡ ቃላችን ደግሞ የመልዕክታችንን ይዘት ይናገራል። የመልዕክታችንን ሕይወት እየኖርነው በቃላችን ባንናገረው ተመልካቹ ምን ማድረግ እንዳለበት ስለማያውቅ ውሳኔ ማድረግ እንዲቸገር እናደርገዋለን፡፡ የምንናገረውን መልዕክት በአኗኗራችን እየተቃረነው ቃሉን ብቻ ብንናገር ደግሞ ሰሚው በምንናገረው ሕይወት አልባ ቃላት ፍላጎት እንዲያጣ እናደርገዋለን፡፡

በሕይወታችን መመስከር

በርካታ ሰዎች ከሚሰሙት ይልቅ ለሚያዩት ነገር ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡ አንድ ምሽት ወንጀለኞች በሚበዙበት ሰፈር ስታልፍ አንድ ወንበዴ የሚመስል ሰው በከፊል የተጠጣ የአረቄ ጠርሙስ እና ቅቤ የጠገበ ዱላ በእጁ ጨብጦ በአንድ ጠባብ መተላለፊያ ጠርዝ ላይ ቆሞ ብትመለከት ምን ልታስብ ትችላለህ? ‹‹ይቅርታ አድርግልኝ፣ ለአንድ ደቂቃ ወደ እኔ ቀርበህ ልትረዳኝ ትችላለህ? መነፅሬ ወድቆ ጥፍቶብኝ ነው፣›› ቢልህስ፣ ቀድሞ ስለ ሰውየው ታስብ የነበረውን ሃሳብ እንድትለውጥ ያደርግሃል? ሰውየው እንድትረዳው የቀረበበት መንገድ ስነስርአት የሞላው ቢሆንም ከሰውየው የምትመለከተው ነገር ግን አስደሳች ነገር አይደለም፡፡ በመሆኑም፣ ሰውየውን ቀርቦ ለማውራት አትፈቅድም፡፡

በተመሳሳይ መንገድ፣ ክርስቶስን የማያውቁ ሰዎች ሕይወታችንን በወጉ ያጤናሉ። እናም ድርጊቶቻችን ከምናወራው ነገር ጋር አብረው የሚሄዱ ወይም የማይሄዱ ስለመሆን አለመሆናቸው የራሳቸውን ግምገማ ያደርጋሉ።

ድርጊቶቻችን በምስክርነታችን ወቅት ትልቁን ድርሻ እንደሚወስዱ ስንዘነጋ የእግዚአብሔር መንግስት መስፋፋትን እናውካለን፡፡ 1ቆሮንቶስ 15፡34 አንብብ፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ጳውሎስ፣ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች የኃጢአት ድርጊቶቻቸውን ችላ በማለታቸው ምክንያት በአካባቢያቸው በሚኖሩ ኢ -አማኞች ላይ ያሳደሩትን አሉታዊ ተፅእኖ በመጠቆም ይወቅሳቸዋል፡፡ ይህ መልዕክት ዛሬ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ምን የሚያስተላልፍ ይመስልሃል?

‹‹ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደቀረበው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጸንተው ቢሮሩ ኖሮ፣ በአሁኑ ሰአት መላዋ ሕንድ ክርስቲያን በሆነች ነበር፡፡›› -ሞሀንዳስ ኬ. ጋንዲ

በቃላችን መመስከር

የማያምኑ ሰዎች እግዚአብሔር በሕይወታችን ደምቆ ማየታቸው እጅግ መልካም ነገር ነው፡፡ ሌላው ሁሉ ቢቀር ሕይወታችንን ምን እንደዚህ ሊያደርገው እንደቻለ የማወቅ ጉጉት እንዲያድርባቸው ያደርጋልና፡፡ በዚህ ምክንያት ልንነግራቸው ያለውን ነገር ለማድመጥ በሚሹ ግዜ ምን እንበላቸው?

ከዚህ በታች የቀረቡ አራት ቁልፍ ፍሬ ሃሳቦች አንድ አድማጭ በሚገባው መንገድ ከቀረቡ ግለሰቡ ወንጌልን እንዲገነዘብና ክርስቶስን ለመቀበል ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ይረዳዋል፡፡

 1. እግዚአብሔር እያንዳንዱን ሰው ያፈቅራል፡፡ እያንዳንዳችን ከእርሱ ጋር ዘላለማዊ ሕብረት እንዲኖረን አድርጎ ነው የፈጠረን።

‘በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና’ ዮሐንስ 3፡16። በጥቅሱ መሠረት፣ እግዚአብሔር ልጁን ለሰው ልጆች ኃጢአት እንዲሞት የላከበት ዋነና አነሳሽ ምክንያት ምንድን ነው?

 1. ሁሉ ኃጢአትን ሰርቷል፣ ይህም ከእግዚአብሔር ጋር የነበረንን ሕብረት አውኳል፣ ችግሩ ካልተፈታ የዚህ ነገር መጨረሻው ለዘላለም ከእርሱ ተለይቶ መኖር ነው፡፡ ‘ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤’ሮሜ 3፡23
 • በጥቅሱ መሠረት ምን ያህሉ ሰዎች ናቸው ኃጢአትን የሠሩት?
 • እግዚአብሔር በክርስቶስ ያዘጋጀው ድነት የሚያስፈልጋቸው ምን ያህሉ ናቸው?
 1. ከእግዚአብሔር ጋር የነበረን ሕብረት ዳግም ይታደስ ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአታችንን ዋጋ እንዲከፍል፣ እግዚአብሔር ልጁን ላከ፡፡

በ1ጴጥሮስ 3፡18 መሠረት እግዚአብሔር ክርስቶስ ለሰው ልጆች እንዲሞት ወደ ምድር የላከበት ምክንያት ምንድን ነው? ኢየሱስ ከሞተ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ዳግመኛ ሕያው ሆኗል፡፡ ትንሳኤው ሲከተሉት ለነበሩትና የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ለነገራቸው ምን የሚያስረዳው ነገር አለ?

 1. ክርስቶስን በገዛ ፈቃዳችን በእምነት ስንቀበል የኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት ለእያንዳንዳችን ይቆጠርልናል፡፡
 •  ከዚህ በፊት የተገለጹትን ሦስቱን ነጥቦች ብቻ ማወቅ በቂ ነው ወይስ በዮሐንስ 1፡12 ላይ እንደተገለጸው መውሰድ የሚገባን አስፈላጊ እርምጃ ይኖር ይሆን?
 • ካለ ይህ አስፈላጊ የሆነ ድርጊት ምንድን ነው?
 • አንድ ሰው ከክርስቲያን ቤተሰብ በመወለዱ ክርስቲያን ሊሆን ይችላል?

ተጨማሪ ምልከታ፡- በምትመሰክርበት ጊዜ አመቺ በሆነ ጊዜ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቀም፡፡ ለአብነት ያህል የምታስታውሰውን ጥቅስ አካፍል፤ አልያም መጽሐፍ ቅዱስህን በመግለጥ ግለሰቡ ክፍሉን በቃሉ እንዲያነብ ጋብዝ፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ላይ ተመስርቶ ወንጌልን ለሌሎች ማካፈል ወንጌልን የመመስከር አንዱ አካሄድ ሲሆን ስለራስህ መንፈሳዊ ሕይወት ምስክርነት በማቅረብ ወንጌልን መመስከርም በአግባቡ ከተተገበረ ሌላው ውጤታማ አካሄድ ነው።

ከ 3 ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የራስህን ምስክርነት ለማካፈል ዝግጅት አድርግ፡፡ ስለ ራስህ የምትመሰክረው ምስክርነት ብዙውን ጊዜ ሦስት ክፍሎች ይኖሩት፡-

 1. አስቀድሞ – ክርስቶስን ከመቀበልህ በፊት ሕይወትህ ምን እንደሚመስል
 2. እንዴት – እንዴት ክርስቶን ለመቀበል እንደወሰንክ
 3. በኃላ – ክርስቶስን ከተቀበልክ በኃላ ሕይወትህ ምን እንደሚመስል

ስለ ራስህ ሕይወት በምትመሰክርበት ጊዜ የወንጌሉን መልዕክት ማካተትህ በጣም ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም ምስክርነትህን በምታጠናቅቅበት ጊዜ አድማጩ ክርስቶስ እንደሚያስፈልገውና እንዴት ክርስቲያን መሆን እንደሚችል መረጃ ይሰጠዋልና፡፡

የሐዋሪያት ሥራ 26፡1-23 አንብብ፡፡ ጳውሎስ በአይሁድ ቁጥጥር በመሆን እስር ቤት ከገባ በኃላ በንጉሥ አግሪጳ ፊት እንዲቀርብ ተደረገ፡፡ ለጳውሎስ የራሱን ምስክርነት ለማካፈል ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነበር! የጳውሎስን ምስክርነት ከዚህ በታች በቀረቡት አራት ክፍሎች ስር መድበህ አስፍር፡-

 1. የጳውሎ ሕይወት አስቀድሞ ቁጥር 1-11
 2. ጳውሎስ እንዴት እንደ ዳነ ቁጥር 12-18
 3. የጳዉሎስ ሕይወት ከዳነ በኃላ  ቁጥር 19-23
 4. ስለ ወንጌል የሚናገሩ ጥቅሶች

ሰዎች ምስክርነቴን ቢቃወሙስ?

አንዳንድ ሰዎች ወንጌልን መስማት ላይፈልጉ ይችላሉ፡፡ በዚህ ጊዜ የሚቃወሙት አንተን እንዳልሆነ ልታስታውስ ይገባሃል፡፡ እነዚህ ሰዎች የሚቃወሙት ወይም የማይቀበሉት አዳኝ እንደሚያስፈልጋቸው የሚሞግታቸውን መንፈስ ቅዱስን ነው፡፡ ስለዚህ አንተን እንደተቃወሙህ አድርገህ አትቁጠር፡፡

ሌላው ልታስታውሰው የሚገባህ ነጥብ – ከምስክርነት በኋላ ሁል ጊዜ የሚታይ ውጤት መጠበቅ የለብህም፡፡ በመሠከርከው መጠን የሚለወጡ ሰዎች አሉ ብለህ አትደምድም! በእርግጥ ምስክርነት በሂደት ውጤትን ሊወልድ ይችላል፡፡ በርካቶቹ ክርስቲያኖች (በተለይም ጎልማሶች) ጌታን ለመቀበል ውሳኔ ላይ ከመድረሳቸው በፊት ሰይጣን ለዘመናት በሕይወታቸው ውስጥ የዘራውን ለመንቀልና ጥራጣሬያቸውን ለማጥፋት ጊዜ ያስፈልጋቸው ይሆናል፡፡ በሌላ አነጋገር አንድ ሰው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ከአምስት ወይም አስር የተለያዩ ምንጮች የምስራቹን ዜና እየሰማ ጥቂት በጥቂት ወደ ወንጌሉ መቅረብ ያስፈልገው ይሆናል፡፡ ወንጌል ለአንድ ሰው በነገርህ ቁጥር ይህን ሰው ለጌታ ይበልጥ ቅርብ እያደረከው ነው፡፡

 1. 1ቆሮንቶስ 3፡5-10 አንብብ፡፡ በመስካሪዎች መካከል ያለውን የጋራ ሥራ አስተዋልክ? (አጵሎስ እንደ ጳውሎስ ያለ ወንጌላዊ ነበር) ፡፡ ‹‹እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስም አጠጣ—›› (ቁጥር 9 ) የሚለው አረፍተ ነገር ምን ማለት ይመስልሃል?
 2. ጳውሎስ፣ በቁጥር 7 ላይ ‹‹—የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም፡፡›› ሲል ምን ማስተላለፍ ፈልጎ ይመስልሃል?

ጥያቄአቸውን መመለስ ቢያቅተኝስ?

ሰዎች ስለ ክርስትና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጥያቄዎችን ያነሱ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ጥያቄዎች በእምነታቸው ፊት የተጋረጡ እንቅፋቶች ሊሆኑ ይችላሉ፤ ሌላ ጊዜ ግን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው ላለመቀበል የሚደነቅሯቸው ሰበቦች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የገጠመህ ሰው የትኛው እንደሆነ እንዲገልጽልህ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ታመን፡፡

ወንጌልን በምትመሠክርበት ጊዜ የምስክርነትህን መስመር የሚያስለቅቅ ጥያቄ ቢነሳብህ፣ ‹‹ጥሩ ጥያቄ ነው፤ ትያቄው ምላሽ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን አሁን ወደ ጀመርነው ነጥብ እንመለስና በዚህ ሂደት ውስጥ ጥያቄው ካልተመለሰ፣ በኃላ እንደገና ጥያቄውን ልታነሳ ትችላለህ፡፡›› በማለት አላማህ ግቡን እንዲመታ ጣር፡፡

ተገቢ ጥያቄ ተጠይቀህ መልሱን የማታውቀው ከሆነ ደግሞ፣ ‹‹መልሱን አላውቅም፤ ነገር ግን በሌላ ጊዜ ለጥያቄው ምላሽ እንድታገኝ አደርጋለው፡፡›› በማለት መልስ፡፡ ከዛ በኃላ ምላሹን ለማግኘት ጥረት አድርግ!

 • በ 2ጢሞቴዎስ 2፡16፣ 2-26 ላይ ጳውሎስ ለወጣት ደቀመዝሙሩ፣ ጢሞቴዎስ ምን አይነት ምክር መከረው?

የምስክርነት ውይይት እንዴት አድርጌ ልጀምር?

ውይይትን በጥያቄ መጀመር የተሻለ መንገድ ነው፡፡ የሐዋሪያት ሥራ 8፡26 አንብብ፡፡ ፊሊጶስ ለኢትዮጵያዊው ሰው በሚመሰክርበት ጊዜ እንዴት አድርጎ ጀመረ?

ውይይት ለመጀመር የሚረዱ ጥቂት ነጥቦች እነሆ፡-

 • ስለ መንፈሳዊ ነገሮች (ወይም ስለ እግዚአብሔር፣ ከሞት በኃላ ስላለ ሕይወት) አስበህ ታውቃለህ?
 • መንፈሳዊ ሕይወትህ ምን ይመስላል?
 • ወደ ቤተ ክርስቲያን ትሄዳለህ? ለምን? በቤተ ክርስቲያናችሁ ስለ ምንድን ነው የምትማሩት?
 • ከእግዚአብሔር ጋር ባለህ ሕብረት ረክተሃል ወይስ አንድ የሚጎድል ነገር እንዳለ ይሰማሃል?
 • ያደረከውን መስቀል ተመልክቼዋለሁ፣ ክርስቲያን ነህ? [ካለሆነ፡-] ይህ መስቀል የሚወክለውን ነገር ለማወቅ ፈቃደኛ ነህ?
 • ስለ አራቱ መንፈሳዊ ሕጎች ሰምተህ ታውቃለህ?
 • ስለ ክርስቲያናዊ ሥነ ስርአት አንስተህ፡- ስለዚህ ነገር ምን ታስባለህ? ትርጉም ይሰጥሃል? ተጨማሪ ነገር መስማት ትፈልጋለህ?
 • ለምታውቀው ሰው፡- ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት ሕብረት እንደጀመርኩ ነግሬህ አውቃለሁ?

ከሕይወትህ ጋር ማዛመድ

ልትጸልይላቸው የሚገባህን የ 10 ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎችን ስም ዝርዝር ፃፍ፡-

 • ለእነዚህ ሰዎች ያለማቋረጥ ለመጸለይ ቁርጠኛ ውሳኔ አድርግ፡፡
 • ከእነዚህ ሰዎች ጋር እንድታሳልፍ እግዚአብሔር የሚያዘጋጅልህን ‹‹መለኮታዊ ቀጠሮ›› ንቁ ሆነህ ተጠባበቅ፡፡

ለተጨማሪ ምልከታ፡- ለማያምኑ ወዳጆችህ ልትጸልይላቸው የምትችለው የጸሎት አይነት በኤፌሶን 1፡17-19 ላይ ሰፍሮ ታገኛለህ፡፡

ማጠቃለያ

‹‹ስለ እኔ ለሌሎች ሰዎች ልትነግር ትፈቅዳለህ?›› ሲል ኢየሱስ ጥያቄ ያቀርብልሃል፡፡

የቃል ጥናት ጥቅስ

‹‹በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።›› ሮሜ 1፡16

ምዕራፍ 10ን ያጥኑ

ምዕራፍ 8 – ጸሎት

ስለጸሎት ማወቅ ለምን ያስፈልጋል?

‹‹ጎሽ፣ ይህች ልዩ ሴት መጣችልኝ፡፡ አብራኝ ስትሆን እጅግ ደስተኛ እሆናለሁ!›› ሲል አሰብ ብራየን በውስ፡፡

ብሪየን፣ የአስር አመት ልጅ ሲሆን በከፍተኛ የኦቲዝም በሽታ ይሰቃያል፡፡ ጥቁር ቡኒ ፀጉር፣ ሰማያዊ የአይን ብሌን ያለው መልከ መልካም ልጅ ነው፡፡ በአእምሮው ላይ ያለው ችግር እስረኛ ባየሰደርገው ኖሮ በመልኩ ብቻ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ታዋቂ ልጅ ይሆን ነበር፡፡

እናቱ ሞኒካ ብራየንን ልጇን ከወለሉ ላይ አንስታ የእርሱ ብቸኛ አለም ወደ ሆነችው ክፍሉ ውስጥ ወደ ምትገኘው ጠረጴዛው ወሰደችው፡፡ ምሳ አቀረበችለት፡፡ ምሳው ሁል ጊዜ እንደሚበላው የተጠበሰ አይብ ሳንዲዊች፣ በአራት እኩል ቦታ የተቆራረጠ ግማሽ ፓም፣ ሦስት የስኒከር ዱድል ብስኩቶች እና አንድ ብርጭቆ ወተት ነበር፡፡

‹‹እንደገና ሰራችልኝ አይደል! ምርጥ ነው! ልክ እንደምወደው!›› አለ ብራየን ከፊቱ ላይ ማንም ሊያነበው ባይችልም በውስ እጅግ ደስ እየተሰኘ፡፡ “የምትገርም ሴት ናት! ከእሷ ውጭ እንዴት መኖር እንደምችል አላውቅም››፣ አለ በልቡ።

ሞኒካ ልጇ ምግቡን በስርዐት ሲመገብ እየተመለከተች፣ ጮክ ብላ ‹‹እወድሃለው ብራየን›› አለችው፡፡ ‹‹ምኞቴ ምን ያህል እንደማፈቅርህ እንድታውቅልኝ ነው፡፡›› ብላ ማጅራቱን በፍቅር አበስ አበስ አደረገችለት፡፡

ብራየን ስቅጥጥ አለው፡፡ በመደናገጥ ‹‹ምንድን ነው ይሄ? ‹‹በምበላበት ጊዜ በማጅራቴ አካባቢ እንዲህ አይነት ስሜት እንዲሰማኝ አልፈልግም፡፡ ለምንድን ነው እንዲህ እንዲሰማኝ የምታደርገኝ? የማልረዳላት አንድ ነገር ቢኖር ይሄን ብቻ ነው፡፡ ምግቤን ከሰጠችኝ በኋላ በዚህ መንገድ ለምን ታስፈራራኛለች? በሄደች!›› ሲል አሰበ፡፡

‹‹ምን ሆንክ፣ ብራየን?›› ስትል ሞኒካ ጠየቀችው፡፡ ‹‹እባክህ ንገረኝ የኔ ፍቅር፡፡ ምን አለበት ልትነግረኝ ብትችል! በጭንቅላትህ ውስጥ የሚመላለሰውን ሃሳብ መረዳት ብችል ምንኛ በወደድኩ! ማውራት ብንችል ምንኛ ደስ ባለኝ፡፡ ላወራህና ካንተ ልሰማቸው የምፈልጋቸው በርካታ ነገሮች ነበሩኝ!›› ስትል አወራችው፡፡

‹‹የምፈልገውን ነገር ጠንቅቃ ታውቃለች፣ አንዳንድ ጊዜ ግን ቅድም እንዳደረገችው አይነት ነገር ስታደርግ ስለ እኔ ደንታ ያላት አትመስልም፡፡›› አለ ብራየን በውስጡ፡፡ ብራየን ማለዳ በሰውነቱ ላይ በነበረው የመደንዘዝ ስሜት ተበሳጫጭቷል፡፡ ሰውነቱ አንዳች ስሜት እንዲሰማው በመፈለግ የአቲዝም በሽተኞች አንዳንድ ጊዜ እንደሚያደርጉት ራሱን ከግድግዳ ጋር በኋይል ማጋጨት ጀመረ፡፡ ሞኒካ ሮጣ በመምጣት መጋጨት መፈለጉን እስኪተው ድረሰስ እቅፍ አድርጋ ያዘችው፡፡ ‹‹ለምንድን ነው እንዲህ የምታደርገኝ? ደስ የሚያሰኝ ነገር ነበር እኮ፣ ለምንድ ነው እንድተው የምትከለክለኝ? በጣም ነው የሚያስጠላው፡፡›› ሲል በውስጡ ለራሱ ተናገረ፡፡

ሞኒካ ከብራየን አጠገብ በርከክ ብላ አይን አይኑን ለማየት ጥረት ብታደርግም እርሱ ግን በምላሹ ሊመለከታት ፈፅሞ አልፈለገም፡፡ ከእርሷ አይን በተቃራኒው ዘወር በማለት አሻግሮ ማየት ጀመረ፡፡ ሞኒካ በለሆሳስ ‹‹ባንተ ተስፋ አልቆርጥም፡፡›› አለችው፡፡ ‹‹ባታወራኝም፣ እቅፍ ባታደርገኝም፣ ችላ ብትለኝም፣ ሁል ጊዜ ከጎንህ ነኝ››፣ አለችው አይን አይኑን በፍቅር እየተመለከተችው።

አሁን ብራየን በማጅራቱ መነካት የተሰማውን ስሜት ዘንግቷል፡፡ “ለምን እነዚያን ድምፆች ከአንደበቷ እንደምታወጣ ይገርመኛል፡ በጣም እንደምወዳት ግን እርግጠኛ ነኝ! ይህን እንድታውቅልኝ የማደርግበት መንገድ ቢኖር ምንኛ በወደድኩ! እህ —፣ ይሁና፡፡ ያን ማድረግ ብችልም ለእርሷ ምንም ማለት ላይሆን ይችላል”፣ አለ በውስጡ።

ለአንዳንድ ክርስቲያኖች ከእግዘኢብሔር ጋር ማውራት ልክ ብራየን ከእናቱ ጋር የነበረውን አይነት ነው፡፡ እግዚብሔር እንደሞኒካ ሳይሆን የውስጣችንን ሃሳብ ሁሉ ያውቃል፡፡ ያም ሆኖ ግን ሃሳቻችንን እንድንገልጽለትና ለእኛ ያለውን ሃሳብ ደግሞ እንድናደምጥለት በብርቱ ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን በርካታ ክርስቲያኖች በገዛ ፈቃዳቸው በመጣ የመንፈሳዊ ኦቲዝም በሽታ ተጠቅተዋል፡፡ ከኦቲዝም በሽታ የሚያገግሙ ሕፃናት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ክርስቲያን ከዚህ መንፈሳዊ ኦቲዝም ፈፅሞ ሊገላገል ወይም ሊያገግም ይችላል፡፡ ጉዳዩ፣ የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡

ጸሎት፡- ‹‹አባት ሆይ ስለ አንተ ማወቁ ብቻ አያረካኝም፣ አንተን ራስህን ማወቅ እፈልጋለሁ! በመስጠትና መቀበል እውነተኛ ልምምድ ውስጥ ልገናኝህ እፈልጋለሁ፡፡ ካንተ ጋር ማውራት፣ አንተን ማምለክ፣ አስተምረኝ፡፡ የቤተኝነት ስሜት እንድለማመድ እና በእውነተኛ የአባት-ልጅ ግንኙነት እንዳድግ እርዳኝ፡፡ አሜን፡፡››

ስለ ጸሎት ማወቅ የሚገባህ አስር እውነታዎች

በመሠረቱ ጸሎት ከእግዚአበሔር ጋር ማውራት ማለት ነው፡፡ ከዚህ ያለፈ እንዲሆን ማድረግም ሆነ መደረግ ያለበት ቢሆንም ይህ አባባለ፤ በበቂ ሁኔታ ጸሎትን ይገልጸዋል፡፡ እግዚአብሔር ከተራ ወዳጅ በእጅጉ የላቀና አእምሮአችን ሊረዳው ከሚችለው በላይ ወዳጃችን ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ከሰው ጋር እንደምናደርገው ሁሉ ከእርሱ ጋር እንድናወራ ይጠይቀናል፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር ማውራት ልክ ከሌሎች ሰዎች ጋር እንደምናወራው አይነት አይደለም፡፡ ይህ ግንኙነት-ጥበብ፣ ክህሎት የተጠና ባህሪን እና ስነ ስርአትን የሚጠይቅ ግንኙነት ነው፡፡ በሕይወታቸው ዘመናቸው በሞላ በአይሁድ ስርዕት በማደጋቸው ብዙም ለጸሎት እንግዳ ያልነበሩት እነዚያ 12ቱ የኢሱስ ደቀመዛሙርት ኢየሱስን በሉቃስ 11፡1 ላይ፣ ‹‹—እንጸልይ ዘንድ አስተምረን—›› ካሉት፣ እኔ እና አንተማ እንዴት ስለ ርዕሰ ጉዳዩ እውቀት አያስፈልገን ይሆን!

‹‹እግዚአብሔር ከሰጠን መብቶች ሁሉ ታላቁ በማንኛውም ሰአት ወደ እርሱ እንድትቀርብ ማድረጉ ነው፡፡ ከእርሱ ጋር እንድታወራ ብቻ አይደለም መብት የተሰጠህ፣ ተጋብዘሀል፡፡ ፈቃድ ብቻ አይደለም የተሰጠህ፣ እንድታደርገው ይጠብቅሃል፡፡ እግዚአብሔር እስክታወራው በጉጉት ይጠብቅሃል፡፡›› ዌስሊ ኤል. ዱዌል

 1. በማንኛውም ቦታ እና ሰአት በምትፈልገው በማንኛውም ጉዳይ ላይ መጸለይ ትችላለህ፡፡

ከዚህ በታች ያሉትን ነገሮች አስበህ ታውቃለህ?

 •  እግዚአብሔር በውጥረት ውስጥ ስላለ ለፍላጎቶቼ ትኩረት አይሰጥም፡፡
 •  የእኔ ፍላጎቶች በእግዚአብሔር አይን እዚህ ግባ የማይባሉና ችላ የሚባሉ ናቸው፡፡
 •  ፍላጎቶቼን ለማስታወቅ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የጽድቅ ድፍረት የለኝም፡፡
 •  በቂ እምነት ስለሌለኝ እግዚአብሔር ጥያቄዎቼን አይቀበላቸውም፡፡
 •  ሌላ አሉታዊ አሳቦች ካሉህ በማስታወሻህ ላይ አስፍራቸው።

እግዚአብሔር መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው፣ በሁሉ ስፍራ የሚገኝ እና ሁሉን ማድረግ የሚችል መሆኑን ማወቅህ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጸሎቶችን እየሰማ ምላሽ በሚሰጥበት ሁኔታ ውስጥ ያንተንም ጸሎት ሰምቶ ለመመለስ ስላለው ችሎታ ምን ያስገነዝብሃል?

ከዚህ በታች በቀረቡት ጥቅሶች ውስጥ ስለምን እንደተጸለየ በመለየት እግዚአብሔር እኛንም በምን ጉዳዮች ላይ እንድንጸልይ እንደሚያበረታታን አመልክት፡፡

 • 1ዜና 4፡10
 • መዝሙር 18፡1
 • መዝሙር 22፡1-2
 • መዝሙር 143፡9
 • ማቴዎስ 6፡11
 • ፊሊጵሲዮስ 4፡6-7
 1. አራት አይነት መሠረታዊ የጸሎት አይነቶች አሉ፡፡

ጸሎት በእግዚአብሔር ፊት ቃላትን ከ‹‹መድገም›› የዘለለ ሊሆን ይገባል፡፡ ልመናችንን ማድመጥ ቢወድም፣ ከዚህም ያለፈ ነገር ከእኛ ይጠብቃል፡፡ የጸሎት ሕይወት ከዚህ በታች ያሉትን አራት መሠረታዊ የጸሎት አይነቶ ማካተቱን ልብ በል፡፡

ውዳሴ – በአምልኮ እና አድናቆት ፍቅርህን ለእግዚአብሔር መግለጥ።

 • ባልና ሚስት ለምን ‹‹አፈቅርሀለው/አፈቅርሻለው›› መባባል ያለባቸው ይመስልሃል?
 • ‹‹ተናገሪው›› ከእዚህ ምን ይጠቀማል?
 • የሚነገረውስ ሰው ከእዚህ ምን ይጠቀማል?

አፈቅርሃለው ብለህ ስትነግረው በታላቁ አምላክ ላይ ተመሳሳይ ነገር እየፈጸምክ መሆንህን ትረዳለህ? ልጆቹ ለእርሱ ያላቸውን ፍቅር ሲገልጹ መስማት እግዚአብሔርን እጅግ ደስ ያሰኘዋል፤ ይባርከዋልም! ካደረገልን በረካታ ነገሮች በኋላ ይህንን በረከት ከእርሱ ማስቀረት ጭካኔ አይሆንም? ሁል ጊዜ እንደምታፈቅረው ንገረው፡፡ ይህን ስታደርግ ግን ስለጠየቀህ ወይም ልታስታውሰው ስለሚገባህ ሳይሆን የሚገባው እንደሆነ በመረዳት ይሁን! ውለታ ካለበትና ከሚያፈቅር ልብ የሚወጣ ጤናማ ምላሽ ይህ ነውና!

ኑዛዜ – ኃጢአት ባደረከው ነገር ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት።

 • መዝሙር 66፡18 አንብብ፡፡ ያልተናዘዝከው ኃጢአት በጸሎትህ ላይ የሚያደርሰው ነገር ምንድን ነው?
 • 1ዮሐንስ 1፡9 አንብብ፡፡ የኑዛዜ ጸሎት ኃጢአትህን ምን ያደርጋል?

‹‹ኑዛዜ›› ለሚለው ቃል የግሪክ አቻ ቃሉ ‹‹homologeo›› ሲሆን የቃል በቃል ትርጓሜው ‹‹ያንኑ መናገር›› ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት እግዚአብሔር በሕይወታችን ላይ ኃጢአትን ሲመለከት ስለ ኃጢአቱ ሃጢአትነት ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት ማለት ነው፡፡ ራሳችንን ከኃጢአት ለማጥራት የምንሰራው ከባድ ነገር የለም፤ የሰራነው ስራ ትክክል ስላለመሆኑ ከእርሱ ጋር እንድንስማማ ይነግረንና ይህን ስናደርግ ራሱ ያነፃዋል፡፡ በአንድ ጊዜ ከኃጢአት የጸዳ ሕይወት እንድንመራ በእያንዳንዱ የሕይወታችን ሽንቁር ውስጥ የተሸሸጉትን “ጥቃቅን” ኃጢአቶቻችንን ጭምር በራሳችን እየመረመርን እንድናገኝና በነሱም ላይ ንስሃ እንድንገባ እግዚአብሔር አይጠብቅብንም። እርሱ ራሱ በመንፈሱ ላለንበት መነፈሳዊ አቅም የሚመጥንና ምላሽ እንድንሰጥባቸው የሚፈልገውን የተወሰኑ ጊዚያዊ ጉዳዮችን በመምረጥ ያመለክተናል፡፡ ይህን የመንፈስ ቅዱስ ወቀሳ ታዘን ትክክለኛ ምልሽ እንድንሰጥም ይጠብቅብናል።

ምስጋና – ስለሰራው ነገር እግዚአብሔርን ማመስገን

ሮሜ 1፡18-32 እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ለምን ለሃሳባቸው ከንቱነት አሳልፎ እንደሰጣቸው ይናገራል፡፡

 • ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ሆኖ ሳለ በሃሳባቸው ከንቱ ሆኑ፣ የሚያስተውለውም ልባቸው ጨለመ፡፡ ይህ የሆነው እግዚአብሔርን ስላላመሰገኑትና ምን ስላላሉት ነው?
 • ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን ግንኙነት መካከል ምስጋናን ስናስቀር፣ ከአሮጌው ወይስ ከአዲሱ ተፈጥሯችን ጉድጓድ ነው መቅዳት የጀመርነው?

ማስታወሻ፡- የ ‹‹አሮጌው ጉድጓድ/አዲሱ ጉድጓድ  ማብራሪያ በምዕራፍ 4 ላይ ቀርቧል። አሮጌው ተፈጥሮህን እንቢ በማለት ለእግዚአብሔር ያልተቋረጠ ምስጋና አምጣ!

ልመና – እግዚአብሔርን መጠየቅ

እግዚአብሔር ልመናህን ወደ እርሱ ማምጣት እንደምትችል ብቻ ሳይሆን እንድታመጣ እንደሚፈልግም ጭምር እንድታውቅ ይፈልጋል! ልጅ በመሆንህ ለአንተ የሰጠው መብት ነው!

 1. እግዚአብሔር በእርግጥ ጸሎትህን ያደምጣል፡፡

ጸሎት ስነልቦናዊ ልምምድ ወይም ስነስርአት አይደለም፡፡ ለራሳችን ጥቅም ለማግኘት ስንል የምንመስጥበት የተመሰጦ አይነትም አይደለም፡፡ ጸሎት እውነተኛ ውይይት ነው፡፡ አንተ ታወራለህ፣ እግዚአብሔር ደግሞ ያደምጥሃል፡፡ ከዛም እርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ በኩል፣ ወይም በሁኔታዎች ወይም በቀጥታ በልብህ ይናገርሃል፡፡

መዝሙር 94፡9 አንብብ፡፡ ይህ ጥቅስ ምን ጭብጭ ይዟል?

 1. በጸሎት ውስጥ እምነት ወሳኝ ነገር ነው፡፡

በርካታ ክርስቲያኖች ወደ እግዚአብሔር እምነት በሌለው ዝንባሌ ይቀርባሉ፡፡ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ለመመለስ ያለውን ፈቃድና ችሎታ ይጠራጠራሉ፡፡ እና እግዚአብሔር ለጸሎታቸው ምላሽን ባይሰጥ የሚያስገርም ነው? ‹‹በአንተ ውስጥ እንድሰራ እኔ ላደርገው እንደምችል እመን፣›› ሲል እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ዳር እስከ ዳር ይጠይቅሃል፡፡ ለጸሎትህ አስደናቂ ምላሽ ይሰጥ ዘንድ እምነት፣ እግዚአብሔር በአንተ ውስ ሊያሳድገው ከሚፈልጋቸው ነገሮች መካከል ዋነናው ነው!

ማቴዎስ 13፡54-58 አንብብ፡፡ ለምንድን ነው ኢየሱስ በገዛ አጋሩ ሊያደርግ ከነበረው አስደናቂ ተአምራት የተስተጓጎለው?

 1. እግዚአብሔር በአራት መንገዶች ጸሎትን ይመልሳል፡፡

እግዚአብሔርን በጸሎት አንድን ነገር መጠየቃችን በራሱ አፋጣኝ ምላሽ ለመቀበል ዋስትና አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ጠቢብ ነው፡፡ ከምንጠይቃቸው ነገሮች ከፊሎቹ ለእኛ መልካም ነገሮች እንደሆኑ፣ ከፊሎቹ ደግሞ እንደሚጎዱን፣ ከፊሎቹ ደግሞ ዘግይተው ወደ ሕይወታችን ቢመጡ የተሸለ እንደሆነ፣ ከፊሎቹ ደግሞ የተወሰኑ ቅድመ ሁኑታዎች ከተሟሉ በኋላ ወደ ሕይወታችን ቢመጡ የተሻሉ መሆናቸውን ያውቃል፡፡ ለዚህም ነው ወደ እርሱ የምንጸልያቸውን ጸሎቶች “እሺ”፣ “አይሆንም”፣ “ጠብቅ”፣ “አስቅድሞ ይህ ይሁንና” ብሎ የሚመልሰው፡፡ እንደ ልጆቹ፣ እግዚአብሔር በጸሎታችን ላይ ባደረገው ውሳኔ ስምምነታችንን ያለማንጎራጎር ልንገልጽ ይገባል፡፡ በታላቅ ጥበቡ እንታመናለንና፡፡

ድክ ድክ የምትል ልጄ በቆንጆ አንጸባራቂ ቢላ ለመጫወት ብትጠይቀኝ እና ብፈቅድላት በጣም ክፉ አባት ነኝ፡፡ በዚህ ወቅት ስለነገሩ ጎጂነት የፈለኩትን ያህል ላብራራላት ብሞክርም ላትረዳኝ ትችላለች፡፡ በማልቀስና በመለማመጥ ሃሳቤን እንድቀይር ልትሞግተኝ ትሞክር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ስለምወዳት በአቋሜ ጸንቼ እቆያለሁ፡፡ ከተወሰኑ ጊዜያት በኃላ፣ ማለትም ቢላን በአግባቡ ለመጠቀም በምትደርስበት እድሜ ግን ቢላውን ልሰጣት እችላለሁ፡፡

የ እሺ፣ አይሆንም፣ ጠብቅ፣ ይህ ይሁንና ምሳሌዎች

ከዚህ በታች ያሉትን ጥቅሶች ካነበብክ በኋላ እሺ፣ አይሆንም፣ ጠብቅ፣ ይህ ይሁንና ከሚሉት አማራጪች ተስማሚውን በመምረጥ ከጥቅሶቹ ፊት ጻፍ፡፡ (ለእያንዳንዱ አማራጭ ሁለት ሁለት ጥቅሶች ቀርበዋል፡፡)

 • 1ሳሙኤል 1፡11፣19-20 __________________
 • ማቴዎስ 26፡36-45 __________________
 • ዘፍጥረት 15፡2-6፤21፡1-7 __________________
 • [በቤተ መቅደሱ ምረቃ ወቅት የሰሎሞን ጸሎት፡፡] 2ዜና 6፡36-39 እና 7፡14 __________________
 • 2 ነገሥት 6፡15-20 __________________
 • 2 ቆሮንቶስ 12፡7-10 __________________
 • ዘጸአት 2፡23-25 እና መዝሙር 105፡26-38 __________________
 • ዘኁልቁ 21፡4-9 __________________

ምናባዊ ሃሳብ፡- አንድ ሰው ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፡- ‹‹ጌታ ሆይ ግራ በመጋባት ውስጥ ነን! አዲስ ለተወለደው ልጃችን፣ ለቤት ኪራይ እና ለመኪና እዳ ክፍያ የሚሆን ተጨማሪ ገቢ ያስፈልገናል፡፡ በመስራ ቤቴ ያለውን አዲስ የሰራ ማስታወቂያ ከተጨማሪ የደመወዝ ክፍያ ጋር እንዳገኘው እርዳኝ?›› እግዚአብሔር ለዚህ ጥያቄ ‹‹አይሆንም›› ወይም ‹‹ጠብቅ›› ሊል የሚችልበትን ሃሳባዊ ምክንያቶች ፃፍ፡፡

አይሆንም፡፡ —————-

ጠብቅ፡፡ ——————–

 1. ‹‹እሺ›› የሚሉ ምላሾች ቅድመ ሁኔታዎች አሏቸው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ሳይንስ መሠረት ከአንድ ጥቅስ ተነስተህ ዶክትሪን መስራት አትችልም፡፡ ርዕስ ጉዳዩን አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ጠቅላላ ሃሳብ ማጤን ይኖርብሃል፡፡ አለበለዚህ የዝሆንን የተወሰነ የሰውነት ክፍል ከዳሰሱ በኃላ ስለዝሆን መግለጫ ለመስጠት እንደሞከሩ ሦስት ማየት የተሳናቸው ሰዎችን መምሰልህ ነው፡፡ አንዱ የዝሆኑን ሰፋ ያለ የሰውነት ክፍል ከነካ በኃላ እንደ መኖሪያ ቤት ትልቅና ጠፍጣፋ ይመስላል አለ፡፡ አንዱ ደግሞ ኩንቢውን ከነካ በኃላ እባብ ይመስላል አለ፡፡ ሌላው ደግሞ እግሮቹን ከነካ በኃላ ዛፍ ይመስላል አለ፡፡ ምሳሌው ለጸሎታችን ‹‹እሺ›› የሚል ምላሽን ለማግኘት ከምናደርገው ምርመራ ጋር የሚመሳሰልበት ነገር አለው፡፡ ይህም፣ ከእሺታ ምላሾች ጋር አብረው የሚመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች ከአጠቃላዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ አንጻር  መፈተሽ ይኖርብናልን እና ነው። እዚህ ማጠቃለያ ላይ ለመድረስ ይረዳን ዘንድ እስቲ ከዚህ በታች ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚያስተላልፉትን ቅድመ ሁኔታዎች እናጢን።

ከዚህ በታች አስር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ቀርበዋል፡፡ እያንዳንዱ ለጸሎቶቻችን አወንታዊ ምላሽ ለማግኘት መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ያሳያሉ፡፡ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች በክፍት ቦታው ላይ ፃፍ፡፡

 • ቴዎስ 17፡20 ________________
 • ማርቆስ 11፡24 ________________
 • ማርቆስ 11፡25 ________________
 • ሉቃስ 18፡1-8 አንብብ ________________
 • ሉቃስ 18፡9-14 አንብብ ________________
 • ዮሐንስ 14፡13 [በዚህ ጥቅስ ውስጥ 2 ቅድመ ሁኔታዎች አሉ] ________________
 • ዮሐንስ 15፡7 ________________
 • ያዕቆብ 4፡2 ________________
 • ያዕቆብ 4፡3 ________________
 • 1ዮሐንስ 5፡14-15 ________________
 1. በ ‹‹ኢየሱስ ስም›› በሚድረግ ጸሎት ውስጥ ታላቅ ስልጣን አለ

በማሕበር በሚደረጉ ጸሎቶች ላይ በጸሎቱ ማብቂያ ላይ ‹‹በኢየሱስ ስም፣ አሜን›› ሲባል ሰምተህ ይሆናል፡፡ ይህን ማድረግ ተገቢ ቢሆንም በኢየሱስ ስም መጸለይ የጸሎታችን መደምደሚያ በማድረግ የእግዚአብሔርን የማረጋገጫ ማህተም ከመጠባበቅ የላቀ ነው፡፡

‹‹በኢየሱስ ስም›› መጸለይ ምን ማለት ነው? ይህ ማለት የኢየሱስ ክርስቶስን ሕጋዊ ውክልና ይዘህ በክርስቶስ ፍጽምና በአብ ፊት በመታየት ጸሎትህን ማቅረብ ማለት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ፣ በር ካንኳኳ በኃላ የሕግ ማዘዣ በማሳየት ‹‹በሩን ይክፈቱልኝ!›› የሚልን ፖሊስ ይመስላል፡፡ ይህ ሰው በሩን ክፈቱልኝ ስላለ ብቻ ይከፈትልኛል ብ አይጠብቅም፤ በሩ እንደሚከፈትለት የሚጠብቀው በሕግ ስም ሕጉን ወክሎ መምጣቱ ብቻ ነው፡፡

‹‹ሰይጣን በጥረታችን ላይ ሊሳለቅ ይችል ይሆናል፣ በጥበባችን ላይም ሊዘባበት ይችላል፣ ነገር ግን፣ ደካማ አማኝ እንኳን ሳይቀር በጉልበቱ ሲንበረከክ ሲያይ ይርበደበዳል፡፡›› – ያልታወቀ ምንጭ

ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ኢየሱስ ለተከታዮቹ ጸሎታቸውን በቀጥታ ወደ አብ ማድረስ እንደሚችሉ ነግሯቸዋል፡፡ ምክንያቱም አሁን በራሳቸው ሳይሆን በእርሱ ስም ወደ አብ ይቀርባሉና፡፡ ኢየሱስ ስልጣኑንና ፍፅምናውን ለእኛ ሰጥቷል በመሆኑም ለልመና በአብ ፊት ስንሆን ፈጣሪያችን እኛን ሳይሆን በእርሱ ደስ የሚሰኝበትንና ጸሎቱን ሊሰማ የሚወደውን ኢየሱስን ይመለከታል!

በስካር ሆኜ ከነጉድፌ በመሆን እና ልቤ በሃሰት ተሞልቶ በፊቱ ብቀርብና ‹‹እርሱን በመወከል በልጁህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በፊትህ መጥቻለሁ፣›› ብል አብ እንዴት የሚመልስልኝ ይመስልሃል?

አብ ልባችንን ያውቃል፡፡ እኛም ሆንን እርሱ ከእኛ ኃጢአት የለሽ ፍፁም ሕይወት የማይጠበቅ ቢሆንም፣ ለመንፈስ ቅዱስ የእርምት ጥረት ተገቢ ምላሽ መስጠት አለመስጠታችንን ያውቃል፡፡ ‹‹በኢየሱስ ስም›› የሚጸልይ ሰው አንዳንድ ባህሪያት ምን ሊመስል ይገባል ትላለህ?

 1. ለ እሺ መልስ፣ በፅናት መቆም

በእግዚአብሔር ፊት ልመናን አንዴ ካስታወቁ በኋላ በድጋሜ ጉዳዩን ሳያስቡ ወይም ሳያሳስቡ ምላሹ እስኪመጣ በትዕግስት መጠባበቅ የምክንያታዊነት፣ የትህትና እና የታላቅ እምነት መገለጫ እንደሆነ ይታሰብ ይሆናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የእግዚአብሔር ልጅ ያለውን መመልከት ጠቃሚ ነው፡፡

ሉቃስ 11፡5-13 አውጥተህ አንብብ፡፡ በቁጥር 9 እና 10 ላይ ያለው መልዕክት የግሪኩ ሃሳብ የተሻለ ትርጓሜ፣ ‹‹ሳታቋርጡ ለምኑ — ሳታቋርጡ ፈልጉ — ሳታቋርጡ አንኳኩ —›› የሚለው ነው፡፡ ኪዚህ ጥቅስ በጸሎታችን በፅናት ስለመሆን ምን ትማራለህ?

ሳታቋርጥ እንድንለምን፣ ሳናቋርጥ እንድንፈልግ፣ ሳናቋርጥ እንድናንኳኳ የሚፈልገው ለምን ይመስልሃል?

 1. ችላ ያልናቸው ኃጢአቶች የ‹‹እሺ›› መልሶቻችን እንቅፋቶች ናቸው፡፡

ለምንድን ነው እግዚአብሔር ኃጢአትህን ችላ የማይለው?

ዴኒስ የጓደኛውን የቤት እቃ ለማጓጓዝ መኪናውን እንዲያውሰው ለመጠየቅ ወደ ማይክ ሄደ፡፡ ስለ ጉዳዩ በሚያወሩበት ጊዜ ማይክ የዴኒስ እጅጌ ላይ ደም ተመለከተ፡፡

‹‹ዴኒስ እየደማህ መሆኑ ተመልክተሀል?››

‹‹አዎ፣ ምንም ችግር የለውም፡፡ ይቆማል፡፡ አሁን ስለመኪናህ እናውራ፡፡ ልዋስው እችላለሁ? ነዳጁን ሞልቼ እመልስልሃለው፡፡››

ደሙ እየበዛ ሄደ ወለሉ ላይ መንጠባጠብ ጀመረ፡፡

‹‹ፈጥነን ወደ ሆስፒታል መሄድ ይኖርብናል፣ ዴኒስ፡፡ አርተሪህ ሳይቆረጥ አይቀርም!››

ዴኒስ በመታወክ፣ ‹‹ማይክ፣ ስለደሜ ጉዳይ ልታልፈው ትችላለህ? አሁን የማወራው ስለ መኪናህ ነው! የማወራው ነገር ግድ አይልህም? ርዕሱን እቀያየርክ ትቀጥላለህ ወይስ የመኪናውን ቁልፍ ሄደህ ታመጣልኛለህ?››

ማይክም እንደዛው በመታወክ፣ ‹‹ወደ ሆስፒታል ሄደን ይህን ቁስልህን እስካላሰፋነው ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ ስለመኪናው አዲት ቃል አልተነፍስም – አለበለዚያ መኪናዬን ለመጠቀም በሕይወት የምትቆይ አይመስለኝም!››

ዴኒስ ጓደኛው ቤት ለመቀየር የሚያደርገውን ስራ ለማገዝ ያደረገው ተነሳሽነት አስደናቂ ነው፡፡ ማይክ ግን ከዚህ ይልቅ አስቸኳይ ነገር በዴንስ ሕይወት ላይ ተመልክቷል፡፡ እኛም ወደ እግዚአብሔር በርካታ አስደናቂ ጥያቄዎችን ይዘን ልንመጣ እንችላለን ነገር ግን ኃጢአት ሕይወታችንን በስለት ሲቆራርጥ እየተመለከተ እነዚሕን ጥያቄዎች ከቁብ ሊቆጥራቸው አይችልም፡፡

 1. ማድመጥ መዘንጋት የለብህም፡፡

እስካከሁን ስለ ጸሎት በጣም ጠቃሚ ነጥቦን ተገንዝበሃል፡፡ ሮዝላንድ ሪንኮር እንዳለው፣ ‹‹ጸሎት በሁለት ወዳጆች መካከል የሚደረግ ውይይት፣›› ከሆነ እግዚአብሔር ሊናገርህ የሚፈልገውን ነገር ለማድመጥ የተወሰነ ጊዜ ልትሰጥ ይገባሃል፡፡

ይህን ለማድረግ መጽሐፍ ቅዱስህን ከፍተህ በዝምታ ልትጠብቅ ትችላለህ፣ አልያም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እያሰላሰልክ ከእግዚአብሔር አንዳች ነገር በመጠባበቅ መቆየት ትችላለህ፡፡ ሊናገር የሚፈልገው ነገር ካለ እንዲናገርህ ጠይቀው፡፡ ከዛም ጠብቅና ስማ፡፡

በ 1ሳሙኤል 3፡10 ላይ ሳሙኤል እንዲህ አለ፣ ‹‹ባሪያህ ይሰማልና ተናገር፡፡›› ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ጸሎቶቻችን ከዚህ በተቃራኒው፣ ‹‹ባሪያህ ይናገራልና አድምጥ!›› የሚሉ ናቸው፡፡ ኢሳይያስ 55፡2 እና 3 አንብብና እግዚአብሔር ምን እንድናደርግ እንደሚፈልግ ጻፍ፡፡

‹‹ጸሎት በመጀመሪያ ደረጃ እግዚአብሔርን ማድመጥ ነው፡፡ እግዚብሔር ሁልጊዜ ይገራል፤ ሁል ጊዜ አንድ ነገር ያደርጋል፡፡ ጸሎት ወደዚህ ተግባር መግባት ማለት ነው፡፡›› – ሄነሪ ኖወን

‹‹መንፈሳዊ ጦርነቶች በድል የሚጠናቀቁት ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጡትን መገለጦች በመከተል ነው፡፡ ልጅ በአባቱ ላይ እንዳለው አይነት ጥገኝነት በእግዚአብሔር ላይ ጥገኛ ሆነን ብንሰማው፣ በድል ጎዳና ይመራናል፡፡›› – ጆን ዳውሰን

ለማን ልጸልይ?

ከዚህ በታች በጸሎት ጊዜህ ሊረዳህ የሚችል ምቹ የምስል ማብራሪያ ቀርቦልሃል፡፡ ለማን መጸለይ እንዳለብህ ለማስታወስ እጅህን ማየት ብቻ ነው፡፡

 • አውራ ጣትህ ላንተ ቅርብህ ነው፣ ስለዚህ ጸሎትህን ላንተ ያቅርብ ከሆኑ ሰዎች ጀምር፡- ለባለቤትህ፣ ለልጆችህ፣ ለወላጆችህ፣ ለወንድሞችህና እህቶችህ፣ ለሌሎች ዘመዶችህ፣ ጓደኞችህ እና ጎረቤቶችህ፡፡
 • አመልካች ጣትህ የሚያስተምሩ ሰዎችን ማለትም መጋቢዎችን፣ ሚሽነሪዎችን እና መምህሮችን ያስታውስሃል፡፡ ሌሎችን በትክክለኛ አቅጣጫ እንዲመሩ ድጋፍና ጥበብ ያሻቸዋል፡፡
 • የመሃል ጣትህ ትልቁ ጣትህ ነው በመሆኑም ለመሪዎች እንድትጸልይ ያስታውስሃል፡- ለፕሬዝደንቶች፣ በንግዱ አለም ላሉ ዎኖች፣ ለትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች፣ ለአለቃህ፣ ወዘተ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከተሞቻችንን፣ ክልሎቻችንን እና አገራችንን የሚቀርጹ ስለሆኑ የእግዚአብሔር ምሪት ያሻቸዋል፡፡
 • የቀለበት ጣትህ ደካማው ጣትህ ነው ይህም ለደካሞች በችግር ውስጥ ላሉትና በህመም ላሉ እንድትጸልይ ያስታውስሃል፡፡ እነዚህ ሰዎች ቀንና ለሊት ጸሎትህን ይሻሉ፡፡
 • ትንሿ ጣትህ ከጣቶችህ ሁሉ ትንሿ ናት። ይህም ከእግዚአብሔርና ከሌሎች አንጻር ራስህን ዝቅ አድርገህ እንድትመለከት ያስታውስሃል፡፡ ስለ ፍላጎቶህ፣ ስለደስታህ፣ ስለ ችግሮችህ፣ ስለ እቅድህና ህልሞችህ ጸልይ፡

የጸሎት ማስታወሻ

ከዚህ ቀጥሎ የጸሎት ሕይወትህን የሚያነቃቃና እምነትህን የሚያሳድግ ሃሳብ ቀርቦልሃል፡፡ ሦስት ቀለሞች ያሉት በርካታ ወረቀት አዘጋጅ፡፡ የቀለሞቹንም ርዕስ ‹‹ቀን›› ፣ ‹‹ልመና›› ፣ እና ‹‹መልስ›› ብለህ ሰይም፡፡ ስለ አንድ ጉዳይ እንድትጸልይ በተሰማህ ጊዜ ሁሉ፣ የልመናውን ርዕሰ ጉዳይ ፅፈህ ቀኑን አኑር፡፡ ከዛም እግዚአብሔር ከአራቱ የመልስ አይነቶች በአንዱ ምላሽ ሲሰጥህ፣ ምላሹን በሦስተኛው ኮለም ላይ ፃፍ፡፡ ከቆይታ በኃላ ይህን የጸሎት ማስታወሻ ስትመለከት እግዚአብሔር ለጸሎትህ በሰጠህ ምላሾች ትደነቃለህ!

ከሕይወትህ ጋር ማዛመድ

በሚከተሉት ሦስት ጉዳዮች (የግል ወይም ለሌሎች ሊሆን ይችላል) ላይ አሁኑኑ መጸለይ እጀምራለሁ፡፡ ተጨባጭ ምላሽ ከእግዚአብሔር እስካገኝ ድረስ ጸሎቴን አላቋርጥም፡፡ ጸንቼ እጸልያለሁ!

 1. _________________________________
 2. _________________________________
 3. _________________________________

የቃል ጥናት ጥቅስ፡-

እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ።-ዮሐንስ 16፡24

ማጠቃለያ

‹‹ልታወራኝ፣ ወደ እኔ ልትመጣ ትወዳለህ? ሲል ኢየሱስ ጥያቄ ያቀርብልሃል

ምዕራፍ 9ን ያጥኑ

ምዕራፍ 1 – የእግዚአብሔር ቃል

ጸሎት፡-

‹‹አባት ሆይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ነገሮች እመለከት ዘንድ አይኖቼን ክፈታቸው! ቃልህን ከእለት ምግቤ ይልቅ አስፈላጊዬ እንደሆነ አድርጌ እመለከት ዘንድ እርዳኝ፡፡ አሜን፡፡››

እግዚአብሔርን ማወቅ

ስለ እንግሊዝ ንግስት ለማወቅ ብትፈልግ ምንድን ነው የምታደርገው? ወደ ስፍራው በአውሮፕላን በመብረር የስብሰባ ጊዜ እንዲመቻችልህ በመጠየቅ፣ የምትፈልገውን ሁሉ ጥያቄ መጠየቅ አንዱ አማራጭ ነው፡፡ ሆኖም ብዙዎቻችን በረራው የሚጠይቀውን ዋጋ መክፈል አንችልም ወይም ከእርሷ ጋር ተገናኝቶ ማውራት ከቶ የማይቻል ይሆንብናል፡፡ በዚህ ምክንያት የሚቀረው አማራጭ ስለ እርሷ የተፃፉ መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ ይሆናል፡፡ የትኛውን መጽሐፍ ማንበብ እንዳለብህስ በምን ታውቃለህ? አንዳንዶቹ ምንጮች ስለ ንግስቲቱ ትክክለኛ መረጃ የያዙ ሊሆኑ ቢችሉም ሌሎች ደግሞ በሃሰተኛ ጻሃፍት የተጻፉ የንግስቲቱን ክብር የሚያጎድሉ የሃሰት ሃሜቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

በመጀመሪያ የደራሲዎችን ተአማኒነት ማረጋገጥ ይኖርብሃል፡፡ ስለ ንግስቲቱ ታሪክ በጥልቀት ባጠኑ ደራሲያን የተጻፉ መጻሕፍትን ማጤን፣ በይበልጥ ደግሞ ንግስቲቱን በቅርበት በሚያውቃትና ከእርሷ ጋር በርካታ ሰአታት ባሳለፈ ሰው የተፃፈ መጽሐፍ ማጤኑ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ‹‹ይህ መጽሐፍ በወዳጄ የተጻፈ ነው፣ በውስጡ ባለው ነገር ሁሉ እስማማለሁ፡፡›› የሚል የንግስቲቱ ማረጋገጫ የሰፈረበት መጽሐፍ ቢሆን ደግሞ ለማንበብና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ይበልጥ የተሻለ ይሆናል፡፡

ስለ እግዚአብሔር ማወቅ ስትፈልግስ? በቀጥታ እርሱን አግኝተህ ማነጋገር ስለማትችል የመጽሐፍ ማስረጃዎችን ለመመርመር ፊትህን ማቅናትህ አይቀሬ ይሆናል፡፡ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ላንሳልህ? የትኛውን መጽሐፍ ለማንበብ ትወስናለህ?

እኛ ይህን እንመክርሃለን፡፡ ለዘመናት ስለ እግዚአብሔር ለተፃፉ መፃሕፍት ሁሉ ምንጭ እንደሆነ ወደተመሠከረለት መጽሐፍ – ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ዘወር እንድትል እንመክርሃለን፡፡ በእርግጥ በዚህ ጉዳይ ላይ ሙስሊሞች፣ ቡዲሂስቶች፣ ሂንዱዎችና የሌሎች እምነት ተከታዮች ላይስማሙን ይችላሉ፡፡ በክርስትና አንጻር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የእውነተኛ መረጃ ምንጭ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ለእግዚአብሔር ቅርብ በነበሩ ሰዎች የተጻፈ ነው። 2ጢሞቴዎስ 3፡16፣ እያንዳንዱ ጸሐፊ በቀጥታ በእግዚአብሔር ተመርቶ እንደጻፈ ይናገራል፡፡ በመሆኑም ስለ እግዚአብሔር ማወቅ ከፈለግህ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደተገለጠው መጽሐፍ ጎራ ማለት ይኖርብሃል፡፡

‹‹አንድ ቀን እምነት እንደ መብረቅ ካላይ መጥቶ በእኔ ላይ እንዲወርድ ስለ እምነት ጸለይኩ፡፡ የጠበኩት አልሆነም፡፡ አንድ ዕለት እንዲህ የሚለውን የሮሜ 10 መልዕክትን አነበብኩ፣ ‹እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው›፡፡ አስቀድሜ መጽሐፍ ቅዱሴን ከድኜ ስለ እምነት ጸለይኩ፡፡ አሁን መጽሐፍ ቅዱሴን ገልጬ ማጥናት ስጀምር ግን እምነት በውስጤ ማደግ ጀመረ፡፡›› -ዱዋይት ኤል. ሙዲ

የእግዚአብሔርን ቃል መመገብ

ባለፉት ምዕራፎች ውስጥ ማንነትህ ከሰውነት፣ ከነፍስና መንፈስ የተዋቀረ ባለ ሦስት ገጽ ፍጥረት እንደሆንክ ተረድተሃል፡፡ ሁላችንም ስጋችን መመገብ እንዳለበት እናውቃለን፣ ይህንንም በውስጣችን ባለው የረሃብ ስሜት እንረዳለን፡፡ ነፍሳችንና መንፈሳችንም ጭምር መመገብ እንዳለባቸው የምንረዳ ግን ጥቂቶች ነን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የመንፈስህ ምግብ ነው፡፡ ለአብነት ኢየሱስ በማቴዎስ 4፡4 ላይ፣ ‹‹ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም…›› ሲል ተናግሯል፡፡ ጴጥሮስ ደግሞ በ 1ጴጥሮስ 2፡2 ላይ እንዲህ ሲል ገልጿል፣ ‹‹…ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።››፡፡

የእግዚአብሔርን ቃል በመደበኛነት የማይመገብ ክርስቲያን መንፈስ የመነመነ፣ ደካማና በሽተኛ ይሆናል፡፡ ምናልባት በ 2ኛ የአለም ጦርነት ፍፃሜ ወቅት ከናዚ የጦር ካምፖች ነፃ የወጡ ሰዎችን ፎቶግራፍ ተመልክተህ ይሆናል፡፡ የአንዳንድ ክርስቲያኖችን መንፈስ ፎቶ ማንሳት ብንችል፣ ለረጅም ጊዜ እንግልት የደረሰባቸውን የእነዚህን ሰዎች አካላዊ ሁኔታ ይመስል ይሆናል፡፡ ይህ እንዲሆንብህ አትፍቀድ! የእግዚአብሔርን ምግብ እየተመገብክ ስለመሆንህ እርግጠኛ መሆን ይኖርብሃል!

መጽሐፍ ቅዱስ ምንድን ነው?

በግርድፉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የታሪክ መጽሐፍ ነው ማለት እንችላለን፡፡ በእርግጥ ከታሪክ በላይ የሆነ ነገር የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡ ግጥም፣ መዝሙሮች፣ ድራማ፣ ምሳሌዎች፣ ደብዳቤዎች፣ ትንቢቶች፣ ትዕዛዞች፣ ቀልድ፣ አሳዛኝ ነገር፣ ምስጢር፣ የፍቅር ታሪኮች፣ አስደንጋጭ ነገር፣ የሕግ ስምምነቶች፣ ፍልስፍና፣ የሕዝብ ቆጠራ ዳታ፣ የህይወት ታሪክ፣ ግለ ታሪክ እና ሌሎችንም ጉዳዮች በውስጡ ታገኝለህ፡፡ ጠቅለል አድርገን ስንወስደው የታሪክ መጽሐፍ ልንለው እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር ራሱን በሰዎች ታሪክ ውስጥ ያደረገበትና ከሰዎች ጋር ያደረገው ግንኙነት ትረካ መጽሐፍ ነው፡፡

ሰዎች፣ ‹‹እግዚአብሔር ራሱን ቢገልጥልን ኖሮ ማመን አይከብደንም ነበር፣›› ይላሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ፍላጎት ሞልቷል፡፡ እግዚአብሔር ራሱን የገለጠላቸው የአይን ምስክሮች እግዚአብሔር ምን እንደሚመስል፣ ምን ደስ እንደማያሰኘው፣ ከየት እንደመጣን፣ ወዴት እንደምንሄድ ለእኛ የቱ ጥሩ እንደሆነና የቱ ደግሞ መጥፎ እንደሆነ፣ ወዘተ ነግረውናል፡፡ እግዚአብሔር በዘመናት መካከል አስደናቂ ነገሮችን አድርጓል፡፡ ሰዎች ደግሞ እነዚህን ነገሮች እንዳንዘነጋ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መዝግበውልናል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈው? መቼ ተጻፈ?

‹‹ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። ›› -2ጴጥሮስ 1፡20-21

 1. በጥቅሱ መሠረት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ትንቢቶችን ምን አይነት ሰዎች ጻፏቸው?
 2. የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት ምንጭ ማን ነው?
 3. ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።›› -2ጢሞቴዎስ 3፡16 በጥቅሱ መሠረት፣ ‹‹በእግዚአብሔር እስትንፋስ›› ማለት ምን ማለት ይመስልሃል?

የሰው ደራሲያን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ 66 መጻሕፍትን አካቷል፡፡ 39ኙ በብሉይ ኪዳን የሚገኙ ሲሆኑ ቀሪዎቹ 27 ደግሞ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ይገኛሉ፡፡ መጻሕፍ ቅዱስ ቢያንስ 40 በሚሆኑ ጸሃፍት ተጽፏል፡፡ እያንዳንዱ በመንፈስ ቅዱስ እየተነዱ ነበር የጻፉት፡፡ እነዚህ ጸሐፊዎች የተለያየ መነሻና የሕይወት ታሪክ ያላቸው ነገስታት፣ ነቢያት፣ ፈላስፎች፣ ወታደሮች፣ ገበሬዎች፣ አሳ አጥማጆች፣ ሃኪም፣ ጠጅ አሳላፊ፣ ቀራጭ፣ አይሁድ መምህርና ሌሎች ናቸው፡፡ የኢዮብ መጽሐፍ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1850 ዓ.ዓ. የተፃፈና ከቅዱሳት መጻሕፍቱ ሁሉ ረጅም እድሜን ያስቆጠረ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በርካቶቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከ1500 ዓ.ዓ. በፊት የተፃፉ ናቸው፡፡ አምስቱ የሙሴ መጻሕፍት (ዘፍጥረት፣ ዘጻአት፣ ዘሌዋዊያን እና ዘዳግም) በ 400 ዓ.ዓ. ገደማ ተፅፈዋል፡፡ ሁሉም የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ደግሞ በ57 ዓ.ም. እና በ96 ዓ.ም. መካከል ተፅፈዋል፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት በሦስት የተለያዩ ቋንቋዎች ተፅፈዋል፡፡ እብራይስጥ የአይሁድ ቋንቋ ሲሆን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ዋነኛ ቋንቋ ነው፡፡ ግሪክኛ በክርስቶስ ዘመን ልክ እንደዛሬው እንግሊዘኛ ቋንቋ አለማቀፋዊ ቋንቋ የነበረ ሲሆን አብዛኛው የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ የተጻፉትም በዚሁ ቋንቋ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ሁሉ የአራማይክ (አራማዊ) ቋንቋ ጥቅም ላይ የነበረ ቢሆንም ጥቂት የብሉይና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ብቻ ናቸው በዚህ ቋንቋ የተጻፉት፡፡

ጸሐፊዎቹ ከኢሲያ፣ አፍሪካና አውሮፓ አህጉሮች የተዉጣጡ ናቸው። ከጸሃፊዎቹ መካከል አንዳንዶቹ ጥልቅ ትምህርት የነበራቸው ምሁራን ሲሆኑ ሌሎች አልነበሩም፡፡ አንዳንዶቹ በተሰበረ ልብ ሲጽፉ ሌሎች ደግሞ በደስታ ጽፈውታል፡፡ አንዳንዶቹ በተድላ ይኖሩ የነበሩ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በታላቅ ድህነትና ስደት ውስጥ ነበሩ፡፡ ከነዚህ መካከል አንዳንዶቹ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ እግዚአብሔር እየፈሩ የኖሩ ሲሆኑ ሉሎቹ ደግሞ ዘግይተው በጉልምስናቸው ለእግዚአብሔር እጅ የሰጡ ነበሩ፡፡

‹‹መጽሐፍ ቅዱስ የሁለት ወገኖች ድርሰት ሲሆን የሰው ልጅ ሁለተኛ ደረጃ ደራሲ ብቻ ነው፡፡ ዋነኛው ደራሲ እነዚህን ሰዎች ያነሳሳው፣ የመራው ያበራላቸውና የተቆጣጠራቸው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡›› – ጄ.አይ. ፓከር

የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት አስደናቂ አንድነት

መጽሐፍ ቅዱስ ምንም እንኳ በተለያዩ ደራሲያን የተፃፈና በመጽሐፎቹ መካከልም የረጅም ጊዜ ልዩነት ቢኖርም፣ በቅዱሳት መጻሕፍቱ መካከል የሃሳብ፣ የርዕስ ጉዳይ፣ የእይታ፣ የፍልስፍና እና የአላማ አንድነት አለ፡፡ ሦስት የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ፣ ከሶስት የተለያዩ ክፍለ አለማት የመጡ፣ 40 የተለያዩ አርክቴክቶች ለ 2000 አመታት ያህል የኋይት ሃውስን ሕንፃ ሲገነቡ በአይነ ህሊናህ ለመሳል ሞክር፡፡ ምን አይነት ቀውስ ሊፈጠር እንደሚችል አስብክ? መጽሐፍ ቅዱስ ግን አንድነቱን የጠበቀ መልዕክት የሚያቀርብ መጽሐፍ ነው፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ መነሻው እግዚአብሔር መሆኑ ነው፡፡ ኤፌ.ኤፌ. ብሩስ እንደገለጸው፣ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ ደራሲያን ስራዎች መድብል አይደለም፡፡ በውስጡ መጽሐፍቱን አንድ አድርጎ የሚያስተሳስረ ውህደት አለ፡፡ መድብል መጻሕፍት ሊዋቀር ይችላል፣ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ፈፅሞ፡፡››

የመጽሐፍ ቅዱስ መዋቅር

የመጽሐፍ ቅዱስህን ማውጫ ከፍተህ ተመልከት፡፡ 66ቱ መጻሕፍት በሁለት አብይ ክፍሎች ተከፍለው ትመለከታለህ፡፡ ምን ይባላሉ?

 1. ————
 2. ————

ብሉይ ኪዳን ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የነበረና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የነበረውን አሮጌ ‹‹ኪዳን›› ወይም ‹‹ስምምነት›› የሚያመለክት ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን ማዕከላዊ ነገር ለመልካም ማሕበራዊ ሕይወት ቀጣይነት የሚበጁ እና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል እንዲኖር ለሚፈለግ መልካም ግንኙነት የሚጠቅሙ ‹‹ሕጎች›› ናቸው፡፡ ሕጎቹን ይታዘዙ የነበሩ በምድር ላይ በረከትን ከማግኘት በተጨማሪ በዘላለም ሕይወት የሽልማት ባለቤቶች ይሆኑ ነበር፡፡

ከብሉይ ኪዳን ሕዝቅኤል 18፡4-9 አንብብ፡፡ ይህ ክፍል በብሉይ ኪዳን ‹‹ጻድቅ›› ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ጻድቅ ሰው ምን እንደሚገጥመው ነው የሚናገረው? ቁጥር 9 ላይ ‹‹— ፈፅሞ በሕይወት ይኖራል፡፡›› ይላል፡፡ በዚህ ጥቅስ ውስጥ አንድ ሰው ይህንን ‹‹ህይወት›› ይወርስ ዘንድ እንዲገልፅ የሚጠበቅበትን አምስት ወይም ስድስት ባሕሪያት ግለጽ፡፡

የብሉይ ኪዳን ሕጎችን በመታዘዝ መንግስተ ሰማይን ለመውረስ የምንችል ይመስልሃል? እስቲ ያዕቆብ 2፡10 አንብብና ምላሹን ፈልግ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህ ሃሳብ ጋር ይስማማል?

 1.  አንድ ሰው ሁሉንም ሕጎች ካልታዘዘ፣ የዘላለም ሕይወት አይኖረውም፡፡ በመጀመሪያው ጥቅስ መሠረት ኃጢአትን የሚሰራ ምን ይሆናል?
 2. በሁለተኛውና በሶስተኛውም ጥቅስ መሠረት ምን ያህል ሰው ኃጢአትን ሰርቷል?
 3. ይህ ቁጥር አንተን ይጨምራል?

የእግዚአብሔር የምሕረት እቅድ

እግዚአብሔር የሰው ልጅ በእርሱ የጽድቅ መለኪያ መጠን (መለኪያው ፍፁምነት እንደሆነ ልብ በል) ሊኖር እንደማይችል ስላየ የኃጥዑን ኃጢአት ‹‹የሚሸፍን›› የንፁ እንስሳ ደም እንዲሰዋ ስርዐትን አደረገ፡፡ ለብዙዎች ሁኔታው አሰቃቂ ሊመስላቸው ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ሁኔታ በፈጣሪያችን ላይ የሰራነው ኃጢአት አሰቃቂነትና ሰው ለሰራው ኃጢአት ሊከፍለው የሚገባውን የኃጢአት ዋጋ ግምትን ያስረዳል፡፡ የሰው ልጅ እነዚህን የሞራል ሕጎች መጠበቅ አቅቶት ሲተላለፍ ለበደሉ ሽፋን ለማግኘት መስዋዕት ያቀርብና በእርሱና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ሕብረት ይታደስ ነበር፡፡ በብሉይ ኪዳን ሳይቀር ሰውየውን የሚያድነው ኃጢአትን ይቅር ሊል በሚወድ በእግዚአብሔር ላይ ያለው መታመን (እምነት) መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡

በኤርሚያስ 31፡31-34 ላይ እንደተገለፀው እግዚአብሔር አዲስ ኪዳንን ለማድረግ አስቀድሞ አቅዶ ነበር፡፡ ይህን ክፍል መጽሐፍ ቅዱስህን ክፈትና አንብበው፡፡ በቁጥር 33 መሰረት ሕጌን የት አኖርዋለሁ ነው የሚለው?

እዚህ እቅድ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ ምን ይመስልሃል?

‹‹አዲስ ኪዳን በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተካቷል፣ ብሉይ ኪዳን ደግሞ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ተብራርቷል፡፡›› – ሜሪል ኤፍ. አንገር

አዲስ ኪዳን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞተና ከተነሳ በኋላ የተፃፈ ነው፡፡ የኢየሱስ ሞት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል አዲስ ስምምነትን በመፍጠሩ ምክንያት አዲስ ኪዳን ሊሰኝ በቅቷል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ፍፁምና ንፁህ መስዋዕት ነው፡፡ የእንስሳት መስዋዕት ኃጢአትን ከእግዚአብሔር አይን ይሸፍን የነበረ ሲሆን የኢየሱስ ደም ግን ኃጢአትን ያስወግዳል፤ እርሱ የኃጢአታችንን ዋጋ ከፍሏል፡፡ በዚህ አዲስ ስምምነት መሠረት አሁን ሙሉ በሙሉ ልንታዘዛቸው ከሚገቡን እነዚያ ሕጎች በታች መሆናችን ቀርቷል፡፡ አሁን በዚህ ፈንታ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በእኛ ውስጥ በማደር መልካምን እንድናደርግ ይረዳናል፡፡ አሁን በእግዚአብሔር ፊት ፃድቅ የሚያደርገን ሕግን ለመፈጸም የምናደርገው ጥረት ሳይሆን በክርስቶስ ላያ ያለን እምነት ነው፡፡

 1.  ሮሜ 8፡1-4 አንብብ፡፡ በክርስቶስ ነህ? ክርስቶስን ተቀብለህ ከሆነ በክርስቶስ ነህ፡፡ በክርስቶስ ከሆንህ ቁጥር 1 ምን የለብህም ይላል?
 2. በ ቁጥር 2 መሠረት፣ ምንድነው ‹‹ከኃጢአትና ሞት ሕግ›› ነፃ ያወጣህ?
 3. በ ቁጥር 3 ላይ ከሥጋ የተነሣ የብሉይ ኪዳን ሕግ ‹‹ደካማ›› እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው?
 4. በ ቁጥር 4 መሠረት፣ ምን ስናደርግ ነው የሕግ ትእዛዝ የሚፈጸመው?

የብሉይ ኪዳን መዋቅር

ብሉይ ኪዳን ከ ‹‹ሕግና ትዕዛዛት›› ያለፈ ዛሬም ድረስ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን በርካታ ነገሮች ይዟል፡፡ ከብሉይ ኪዳን ስለ እግዚአብሔር ማንነትና ባሕሪይ፣ ከሕዝቡ ምን እንደሚጠብቅ፣ ለወደፊት ምን እንዳሰበልን፣ እና እንዴት ልናመልከው እንደምንችል ልንማር እንችላለን፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫህን ዳግመኛ ተመልከት፡፡ የብሉይ ኪዳንን 39 መጻሐፍ የመከፋፈያ በርካታ መንገዶች ቢኖሩም አንድ የተለመደ አከፋፈል አለ፡፡ ምን አልባት ይህን አከፋፈል በመጽሐፍ ቅዱስህ ማውጫ ላይ ልታኖረው ትችላለህ፡፡

የታሪክ መጻሐፍት

ዘፍጥረት፣ ዘጻአት፣ ዘሌዋዊያን፣ ዘኁልቁ፣ ዘዳግም፣ ኢያሱ፣ መሳፍንት፣ ሩት፣ 1ኛ እና 2ኛ ሳሙኤል፣ 1ኛ እና 2ኛ ነገስት፣ 1ኛ እና 2ኛ ዜና፣ ዕዝራ፣ ነህምያ፣ እና አስቴር

የግጥም መጻሐፍት 

ኢዮብ፣ መዝሙረ ዳዊት፣ ምሳሌ፣ መክብብ፣ እና ማኃልየ ማኅልየ ዘሰለሞን

የትንቢት መጻሐፍት

ኢሳይያስ፣ ኤርሚያስ፣ ሰቆቃው ኤርሚያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ዳንኤል፣ ሆሴዕ፣ ኢዩኤል፣ አሞጽ፣ አብድዩ፣ ዮናስ፣ ሚኪያስ፣ ናሆም፣ ዕንባቆም፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ዘካርያስ፣ እና ሚልክያስ

የታሪክ መጻሕፍቱ ሰለ ሰነ ፍጥረት፣ ሰለ ሰው ልጅ በምድር ገጽ ላይ መበተን እና ስለ የጥፋት ውሃ ይተርኩና የትኩረት አቅጣጫውን በአንድ አብርሃም በተባለ ታማኝ ሰው ላይ ያነጣጥራሉ፡፡ በመቀጠልም እነዚህ መጻሐፍት በደቡብ ባቢሎን (በአሁኑ ሰአት ኢራቅ እየተባለ) ከሚጠራው ስፍራ የአብርሃም ትንሽ ቤተሰብ ተነስቶ ለብዙ ዘመናት በግብጽ ባርነት መሰንበቱን፣ በሙሴ አማካኝነት በድንቅና ተአምራት ከግብጽ መውጣታቸውን፣ በኢያሱ አማካኝነት የፍልስጤም ምድርን መውረሳቸውን እና በመጨረሻም በንጉሥ ዳዊት አማካኝነት በምድር ላይ ታላቅ መንግስት በመሆን መጽናታቸውን ያወሳሉ፡፡ በመቀጠልም መሪዎቿ አምልኮተ እግዚአብሔርን ትተው እንግዳ አማልዕክት በማምለካቸው እና የገዛ ፈቃዳቸውን በመከተላቸው እስራኤል ጥቂት መቶ አመታት በእግዚአብሔር ፍርድ ስር እንደ ወደቀች እናነባለን፡፡

የግጥም መጻሕፍቱ በዋናነት በእስራኤል ‹‹ወርቃማ ዘመን›› የተፃፉ ሲሆኑ እግዚብሔርን በቅርበት የሚያውቁት ሰዎች ጥልቅ ጥበብ ነጸብራቅ ነው፡፤ አብዛኞቹ እነዚህ መጻሕፍትን በእግዚብሔር ዘንድ ‹‹እንደልቤ የሆነ ሰው›› (ሐዋሪያት ሥራ 13፡22) በተባለው ንጉሥ ዳዊት እና መጽሐፍ ቅዱስ፣ ‹‹ከሰውም ሁሉ ይልቅ…ጥበበኛ ነበር›› (1ነገሥት 4፡31) ባለው በዳዊት ልጅ በሰለሞን የተጻፉ ናቸው፡፡

የትንቢት መጻሕፍቱ በእስራኤል ‹‹የጨለማ ዘመን›› ማለትም የእስራኤል መንግስት በሰለሞን ልጅ በሮብአም ንግስና ወቅት ለሁለት በተከፈለችበት ዘመን የተፃፉ ናቸው፡፡ መንግስታቱም እስራኤልና ይሁዳ ተባሉ፡፡ ነቢያቱ ለእስራኤልና ለተቀረው አለም በቅርብና በሩቅ የሚፈጸሙ ትንቢቶችን ገለጡ፡፡ የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ በመቀጠላቸው በእስራኤል መንግስት ይኖሩ የነበሩ አስሩ ነገዶች በአሶራዊያን ግዞት ስር በመውደቅ በዙሪያቸው ያለው ሕዝብ ባህል ሰለባዎች ሆኑ፡፡ በይሁዳ መንግስት የነበሩ ሁለቱ ነገዶች ደግሞ ኃላ ላይ በባቢሎን ቅኝ ስር በመውደቅ ልግዞትና ባርነት ወደ ባቢሎን ተጋዙ፡፡ አንዳንዶቹ የትንቢት መጻሐፍት ከግዞት በፊት ጥቂቶቹ ደግሞ በግዞቱ ወቅት ሌሎቹ ደግሞ ከ 70 አመት ግዞት በኃላ የተጻፉ ናቸው፡፡

የአዲስ ኪዳን መዋቅር

27ቱን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍ ለመከፋፈል ብዙ አማራጮች አሉ፡፡ የሚከተለው አከፋፈል በስፋት የሚታወቀው ነው፡፤ እነዚህ መጻሐፍት ታሪኮችን፣ ደብዳቤዎችንና ስለመጨረሻው ዘመን ሰፊ ዘገባን ያካትታሉ፡፡ እያንዳንዱ መጽሐፍ ስለ ክርስቶስና ስለ ዘላለማዊ መንግስቱ ያወሳሉ፡፡

 1. የታሪክ መጻሕፍት

ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ዮሐንስ፣ የሐዋሪያት ሥራ

 1. መልዕክቶች (ደብዳቤዎች)

ሮሜ፣ 1 እና 2ኛ ቆሮንቶስ፣ ገላቲያ፣ ኤፌሶን፣ ፊሊፕሲዮስ፣ ቆላሲያስ፣ 1ኛ እና 2ኛ ተሰሎንቄ፣ ዕብራዊያን፣ 1ኛ እና 2ኛ ጢሞቴዎስ፣ ቲቶ፣ ፊሊሞና፣ ያዕቆብ፣ 1ኛ እና 2ኛ ጴጥሮስ፣ 1ኛ፣2ኛ እና 3ኛ ዮሐንስ፣ ይሁዳ

 1. ራዕይ

የታሪክ መጻሕፍቱ ከኢየሱስ ጋር አብረው በነበሩ ሰዎች የተፃፈ ሲሆን ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅትና ከትንሳኤው በኋላ በነበሩ አመታቶች የሆነውን ሁኔታ ይተርካሉ፡፡ ማቴዎስ ከኢየሱስ 12 ደቀ መዛሙርት መካከል አንዱ ሲሆን ቀራጭ ነበር፡፡ ማርቆስና ጴጥሮስ ለብዙ አመታት የቅርብ ወዳጆች ስለነበሩ የማርቆስ ወንጌል፣ ጴጥሮስ ለማርቆስ በቃል ያጻፈው ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡ ማርቆስ የበርናባስ የአጎት ልጅ ሲሆን በጳውሎስ የመጨረሻ የአገልግሎት ዘመን ወቅት አብሮት የሚያገለግል ሰው ነበር፡፡

ሉቃስ ሃኪም ሲሆን ከጳውሎስ ጋር አብሮ ያገለገለ እና የማርቆስ የልብ ወዳጅ ነበር፡፡ መጽሐፉን ሲፅፍ በጥንቃቄ ሁሉን ከመረመረና በርካታ የአይን ምስክሮችን ከጠየቀ በኋላ ነበር (ሉቃስ 1፡1-4)፡፡ ሉቃስ ከዚህ በተጨማሪ ስለ ቀደመቺቱ ቤተ ክርስቲያን ግብር (ሰራ) የሚያትተውን የሐዋሪያት ሥራን ፅፏል፡፡ ዮሐንስም ከ 12ቱ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መካከል አንዱ ነበር፡፡ ‹‹ኢየሱስ ይወደው የነበረው›› ደቀ መዝሙር ነበር፡፡ ይህ አባባል በመካከላቸው የነበረውን ቅርበት ይገልፃል፡፡

መልዕክቶች በቤተ ክርስቲያን ‹‹አእማዳት›› የተፃፉ ደብዳቤዎ ናቸው፡፡ እነዚህ ደብዳቤዎች ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ ፍጥነት በምታድግበት ወቅት፣ እነዚህ በመንፈስ ቅዱስ የሚነዱ መሪዎች ከክርስቶስ ተከታዮች ጋር ለመነጋገር የተጠቀሙባቸውን ጠቃሚ መረጃዎችን ይዘዋል – የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ኢ-ሜይል ልንላቸው እንችላለን፡፡ ጳውሎስ አክራሪ ፈሪሳዊ ነበር፡፡ ፈሪሳዊያን ክርስትናን ከ ‹‹ውጉዝ ዶክትሪኑ››ጋር ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ምለው የተገዘቱ አይሁድ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከሞት የተነሳውን ኢየሱስ ፊት ለፊት ከተገናኘው በኋላ ታላቅ ተፅእኖ የሚፈጥር የኢየሱስ ተከታይ ሆኖ አረፈው፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሁለቱ የኢየሱስ የቅርብ ደቀ መዛሙርት ሲሆኑ ያዕቆብና ይሁዳ ደግሞ የማርያምና የዮሴፍ ልጆች የኢየሱስ ግማሽ ወንድሞች ናቸው፡፡

The Apocalypse፣ በአንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሶች ላይ ‹‹የቅዱስ ዮሐንስ ዘመለኮት ራዕይ›› ወይም በሌሎች ‹‹የኢየሱስ ክርስቶ ራዕይ›› እየተባለ የሚጠራው መጽሐፍ በክፍፍሉ እራሱን የቻለ ስፍራ ይይዛል፡፡ ራዕይ ምናባዊ በሆነ ከባድ መልዕክቶች የተሞላ ምስጢራዊ መጽሐፍ ነው፡፡ ሰለ ምን የተፃፈ እንደሆነ በርካታ አስተያየቶች ቢሮሩም ስለ መጨረሻው ዘመንና ክርስቶስ በምድር ላይ ስለ ሚነግስበት ጊዜ በርካታ ትንቢት ምልከታዎችን መያዙ እርግጥ ነው፡፡ እነዚህ ትንቢቶች በሕዝቅኤል፣ ዳንኤል እና በሌሎች በርካታ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እንዲሁም ኢየሱስ ራሱ በቃሉ በማቴዎስ 24 እና 25 ላይ ከተናገራቸው ትንቢቶች ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው፡፡ በሦስቱም የአዲስ ኪዳን ክፍፍል ስር ያሉ መጻሐፍቶችን ዮሐንስ መጻፉን ልብ ይሉዋል፡፡

ኢየሱስ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍቱ የተናገረውን ከ ማቴዎስ 22፡29፣ ሉቃስ 24፡25 እና ዮሐንስ 5፡39 ካነበብክ በኃላ በራስህ አባባል ግለጽ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ጠቀሜታ

የሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብና በሕይወት ላይ ተግባራዊ የማድረግ ጠቀሜታዎችን ይገልፃሉ፡፡ ከጥቅሶቹ የተገነዘብከውን አብራራ፡፡

 1. ኢያሱ 1፡8
 2. መዝሙር 19፡7-8
 3. መዝሙር 37፡31
 4. ዮሐንስ 15፡3፤17፡17
 5. 2 ጢሞቴዎስ 3፡16-17
 6. 1 ጴጥሮስ 2፡2-3
 1. መስማት

ሉቃስ 6፡45-49 አንብብ፡፡

 • በዚህ ክፍል ላይ ኢየሱስ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል መስማት እንዳለበት አመልክቷል፡፡ ከመስማት በተጨማሪ ምን የተቀመጠ ነገር አለ?
 • እነዚህን ትዕዛዛት የሚተላለፍን ሰው ኢየሱስ ከምን ጋር ነው ያመሳሰለው?
 • በቋሚነት የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት እርግጠኛ የምትሆንባቸው መንገዶች ምንድን ናቸው?
 1. ማንበብ

ዘዳግም 17፡18-20 አንብብ፡፡

 •  በእስራኤል ላይ የሚነግሱ ነገስታት ሊከተሉት የሚገባቸው ሕግ ነው፡፡ ንጉሱ ይህን ሕግ (የመጀመሪያዎቹ 5ቱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፎች) ምን ያህል ጊዜ እንዲያነብ ነው የሚናገረው?
 • ይህን ማድረጉ በንጉሡ ላይ ምን ያመጣል?
 • የእግዚአብሔርን ቃል ሳታቋርጥ ማንበብ በአንተ ሕይወት ላይ ምን አይነት ለውጥ የሚያመጣ ይመስልሃል?
 • መጽሐፍ ቅዱስን ሳታቋርጥ ለማንበብ ምን ማድረግ ያልብህ ይመስልሃል?
 1. ማጥናት

መጽሐፍ ቅዱስን ‹‹ማጥናት›› ከማንበብ የበለጠ ልዩ ትኩረትን የሚጠይቅ ድርጊት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል በሕይወትህ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዱህ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ የማጥኛ ዘዴዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ከዚህ በታች ለመነሻ የሚሆንህ አንድ ዘዴ ቀርቧል፡፡ ይህ የማጥኛ አቀራረብ ያስገረመኝ፣ የወደድኩት፣ የማደርገው፣ የምጠይቀው በመባል ይታወቃል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንድ ክፍል መርጠህ ካነበብክ በኋላ እነዚህን አራት ነገሮች ራስህን ጠይቅ፡-

 1. ያስገረመኝ! – በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያስደነቀኝ ነገር፡-
 2. የወደድኩት – በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የወደድኩት ጥቅስ፡-
 3. የማደርገው – ምዕራፉን ካነበብኩ በኋላ ልተገብረው የሚገባኝ ነገር፡-
 4. የምጠይቀው – ምዕራፉን ሳነብ ወደ አእምሮዬ የመጣ ጥያቄ፡-

መዝሙር 1 አንብብና ያስገረመኝ/የወደድኩት/የማደርገው/የምጠይቀው/ አጠና አቀራረብን ተግባራዊ አድርግ፡፡

 1. በቃል መያዝ

የምዘና ባለሙያዎች ምርምር እንደሚያሳየው፣ አንድ ሰው ከ 24 ሰአት በኋላ የሚያስታውሰው ነገር ከሰማው 5%፣ ካጠናው 35% ገደማ ሲሆን በቃል ከያዘው ውስጥ ግን 100% ነው፡፡ ካነበብከው የእግዚአብሔ ቃል ውስጥ የተወሰነውን ክፍል በቃል ይዘህ ‹‹በልብህ ስለ መሸሸግ ›› ይህ ምርምር ምን ያስተምርሃል?

መዝሙር 119:11 አንብብና የተገነዘበከውን አብራራ “አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።”

 1. ማሰላሰል

መጽሐፍ ቅዱሳዊው ማሰላሰል፣ ‹‹በግል ጊዜ በመውሰድ የተወሰኑ መንፈሳዊ እውነታዎች ወይም ምስጢሮችን በጥልቀት ማሰብ፣ በውስጥ መጸለይና በወደፊት ባህሪና ድርጊት ላይ ለውጥ ለማምጣት ፈቃድን የማስገዛት ውሳኔ ውስጥ መግባትን የሚያካትት አምልኮ ነው፡፡›› (አንገር የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት)፡፡

አውራ ጣታችን ከቀሪዎቹ አራት ጣቶቻችን ጋር እርስ በእርስ እንደተያያዘ ሁሉ የምንሰማውን፣ የምናነበውን፣ የምናጠናውን እና በቃል የምንይዘውን የእግዚአብሔር ቃል ማሰላሰል ይኖርብናል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በወንፊት ውስጥ እንደሚያልፍ ውኃ በእኛ ውስ እንዲልፍ መፍቀድ የለብንም! የእግዚብሔርን ቃል ስናሰላስል እንይዘዋለን፣ ከተለያዩ አቅጣጫዎች እንመረምረዋለን፣ በጥልቀት እናስበዋለን። ይህም መንፈስ ቅዱስ ቃሉን በሕይወታችን ተግባራዊ እንዲያደርግ ሁኔታዎችን ያመቻችለታል፡፡

ከሕይወት ጋር ማዛመድ፡-

ከዛሬ ——– ቀን ጀምሮ፣ ለመጪዎቹ ———– ሣምንታት ያህል መጽሐፍ ቅዱስን በሣምንት ለ ————— ቀናት ያህል ከ ———— ደቂቃ ላላነሰ ጊዜ ለማጥናት ራሴን አዘጋጃለሁ፡፡ እንዲያበረታታኝና የሚረኖሩኝን ጥያቄዎች በመመለስ እንዲያግዘኝ ——— (እከሌን) እጠይቀዋለሁ፡፡

የቃል ጥናት ጥቅስ፡-

የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። –2 ጢሞቴዎስ 3፡16-17

ማጠቃለያ፡-

‹‹ቃሌን ትመገባለህ?›› ሲል ኢየሱስ ጥያቄ ያቀርብልሃል፡፡

ምዕራፍ 8ትን ያጥኑ

ምዕራፍ 6 – ሕብረት

ጸሎት

‹‹አባት ሆይ በዘላለማዊው ቤተሰዎችህ ውስጥ ሰለጨመርከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በዚህ ቤተሰብ ውስጥ እንዴት በሰመረ ሁኔታ መኖር እንዳለብኝ፣ እንዴት ወንድሞቼንና እህቶቼን መርዳት እንዳለብኝ እና እንዴት በእነሱ መረዳት እንዳለብኝ እንዳውቅ እርዳኝ፡፡ አሜን፡፡››

ስለ ሕብረት ጠቀሜታ ማወቅ ለምን ያስፈልጋል?

ወደ ሰሜን ካሊፎርኒያ ሄደህ በተለያዩ ፓርኮች ውስጥ ያሉትን አስደናቂ የሬድውድ ዛፎችን ጎብኝተህ ታውቃለህ? እነዚህ ዛፎች በምድራችን ላይ ካሉ ረጃጅምና ግዙፍ ዛፎች መካከሉ የሚመደቡ ናቸው፡፡ በርካቶቹ ቁመታቸው ከ 350 ጫማ በላይ ሲሆኑ እድሚያቸው ደግሞ እስከ 4000 አመታት ያዘልቃል፡፡ በዝምታ ቀናት፣ በእነዚህ እጅብ ባሉ ዛፎች መካከል መገኘት በጥንታዊያን ቅዱሳት ካቴድራሎች ውስጥ የመገኘት ያህል ይሰማል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ዛፎች አፍ አውጥተው ከአብርሃም፣ ይስሃቅና ያዕቆብ ዘመን ጀምሮ መኖር ምን እንደሚመስል እንዲነግሩህ መጠየቅ ያሰኝሃል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጸሃይ ወራትን አሳልፎ አሁንም ድረስ በጥንካሬ፣ በብቃትና፣ በፅናት ግዙፍነትን ጠብቆ መዝለቅ ምንኛ አስደናቂ ነገር ይሆን!

አሁን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ፡- ለመሆኑ የሬድውድ ዛፍ ብቻውን በእርሻ መካከል በቅሎ አይተህ ታውቃለህ? ምናልባት አካበቢው የነበሩትን መሰል ጓደኞቹን ሰው ጨፍጭፎ እርሱ ብቻ ቀርቶ አግኝተኸው ከላሆነ በቀር መልሱ፣ ‹‹ፈፅሞ!›› የሚል ይሆናል፡፡ በዚህ ሁኔታ ብቻውን የተገኘ የሬድውድ ዛፍ ቢኖርም እንኳ እድሜው ረጅም አይሆንም፡፡ እግዚአብሔር የእነዚህን ዛፎች ድብቅ ታሪክ ስለሚያውቅ በአጀብ (በሕብረት) ብቻ እንዲገኙ ወስኗል፡፡ የእነዚህ ዛፎች ደካማ ጎን ሥሮቻቸው አጫጭሮች መሆናቸው ነው፡፡

የሬድ ውድ ዛፎች እንደሌሎች በርካታ ዛፎች ስሮቻቸው ወደ ምድር ውስጥ የዘለቀና የጠለቀ ሳይሆን ድንጋያማ በሆነው አካባቢያቸው የሚዘንበውን ዝናብ በበቂ ሁኔታ ለመቀራመት ይረዳቸው ዘንድ ስሮቻቸው ወደታች ጥልቅ ከመሆን ይልቅ ወደጎን ሰፊ ቦታን በመሸፈን ይበቅላሉ፡፡ እነዚህ ዛፎች በከባድ ነፋስ ተገፍተው እንዳይወድቁ ስሮቸው ምድር ለምድር ለረጅም ርቀት እርስ በእርሳቸው የተቆላለፉ ናቸው፡፡ በአካባቢያቸው ጠንካራ ንፋስ በሚነፍስበት ወቅት በስሮቻቸው እርስ በእርስ የተያያዙ ስለሆኑ ለንፋሱ አይበገሩም!

ይህ ምሳሌ የክርስቲያኑ ማህበረሰብ እንዴት መኖር እንዳለበት አስደናቂ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ በዚህ አለም ውስጥ መኖር በየዕለቱ አስቸጋሪ እየሆነ ነው፡፡ ይህንን አስቸጋሪ ሁኔታ ‹‹ብቻውን›› ለመወጣት የሚሞክር ክርስቲያን ለአደጋው ተጋላጭ ነው፡፡ ብቻውን ሊቋቋመው ከሚችለው በላይ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ብዙ ሳይቆይ ያጋጥመዋልም፡፡ በአስቸጋሪ ወቅቶቻችን ወቅት ‹‹ስሮቻችንን›› አቆላልፈን አንዳችን በአንዳችን ሕይወት ውስጥ በመሳተፍ የመኖር አስፈላጊነትን ከዚህ እንማራለን። የክርስቲያኖች ሕብረት ፍሬ ነገር ይሄ ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ በመመሪያዎች፣ በሕጎች እና ትዕዛዛት የተሞላ ነው፡፡ በእውኑ እግዚአብሔር ሕይወታችንን እስከሞት ድረስ ጠፍንጎ የሚገዛ የደስታችን ጠር አምላክ ነውን? ፈፅሞ፡፡ እርሱ ለሕይወታችን የትኞቹ ነገሮች መልካም፣ የትኞቹ ደግሞ አጥፊዎቻችን እንደሆኑ እንድንገነዘብ በመርዳት የሚንከባከበን ድንቅ አባት እንጂ፡፡ የሕጎቹም አላማ ይኸው ነበር፡፡

እንዴት ነው ታዲያ እነዚህን ሁሉ ህጎች ማስታወስ የሚቻለው? እንዴትስ ነው መታዘዝ የሚቻለው? ኢየሱስ ይህንን ጉዳይ ቀሊል አድርጎልናል፡፡ በሙሉ ልባችን ሁለት ሕጎችን ብቻ ብንታዘዝ የተቀሩትን በሞላ ልንታዘዛቸው እንደምንችል ነግሮናል፡፡

ማቴዎስ 22፡37-40 ካነበብክ በኃላ እነዚህን ሁለት ህጎች ፃፍ፡-

 1. __________
 2. __________

እስቲ ጥቂት ጥያቄዎች ራሳችንን እንጠይቅ። መጪውን የዘላለማዊ ሕይወታችንን ዘመን ከእርሱ ጋር በመንግስቱ ስለምናሳልፍ፣ አሁን በሕይወታችን ውስጥ ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች እርሱ ከሚሰጣቸው ነገሮች ጋር መግጠም የለባቸውምን? እኛስ ለተፈጠርንለት አላማ መኖር የለብንምን? እርሱ ዋጋ በሚሰጣቸው ነገሮች ላይ እኛም ቅድሚያ በመስጠት የተካንን መሆንስ የለብንምን?

ለእነዚህ ጥያቄዎች ምልሽህ አወንታዊ ከሆነ፣ እንግዳው እግዚአብሔርንና አብረውህ ያሉትን (ክርስቲኖችና ክርስቲያን ያልሆኑትን) በሞላ በመውደድ የተካንክ ልትሆን ይገባሃል፡፡ የዚህ ጥናት አላማ ክርስቲያን ወንድሞችህንና እህቶችህን በማፍቀር እንድታድግ መረዳት ሲሆን ምዕራፍ 9 ላይ ‹‹ምስክርነት›› በሚለው ርዕስ ስር ደግሞ ክርስቶስን ያላወቁትን እንዴት በዚህ ፍቅር መቅረብ እንደምትችል የሚያግዝህ መረጃ ይቀርብልሃል፡፡

የፍቅርን ብያኔን እንመልከት፡-

‹‹ፍቅር›› ለሚለው ቃል ሦስት የግሪክ አቻ ቃላት አሉ፡-

ኤሮስ፡- ለማግኘት የሚወድ ራስወዳድ ፍቅር፤ ወሲባዊ ፍቅር፡፡

ፊሊዬ፡- ወንድማዊ ፍቅር፤ በደምሳሳው የሆነ ፍቅር

አጋፔ፡- እግዚአብሔራዊ፣ ራስወዳድ ያልሆነ ፍቅር – ክርስቲያኖች ሊኖራቸው የሚገባ ፍቅር

‹‹እውነተኛዎቹ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ብዙ የሚያውቁቱ ሳይሆኑ ብዙ የሚያፈቅሩቱ ናቸው፡፡›› -ፍሬድሪክ ስፓንሄይም

በክርስቲያኖች ሕብረት ውስጥ የፍቅር የበላይነት

 1. በዮሐንስ 13፡34-35 መሠረት የኢየሱስ ተከታዮች እውነተኛ የእርሱ ደቀ መዛሙርት መሆናቸው የሚታወቅበት መታወቂያ ምንድን ነው?
 2. እርሱ እንደ ወደደን፣ እርስ በእርሳችን መዋደድ እንዳለብን ኢየሱስ ተናግሯል፡፡ ይህን ሲል ምን ማለቱ ይመስልሃል? ኢየሱስ ለእኛ ያለውን ፍቅር ከገለጠበት መንገዶች መካከል ጥቂቶቹ ግለጽ?

ከዚህ በታች በቀረቡት ጥቅሶች ውስጥ ስለ ክርስቲያን ፍቅር ያስተዋልከውን ቁም ነገር ፃፍ፡-

 1. ‹‹ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፣ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።›› -1ቆሮንቶስ 13፡2
 2. ‹‹ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።››-1ጴጥሮስ 4፡8 
 3. ‹‹ልጆቼ ሆይ፣ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።››-1ዮሐንስ 3፡18 
 4. ‹‹ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?››-1ዮሐንስ 4፡20

‹‹ሌላውን ማዕከል›› ያደረገ የክርስቲያኖች ሕብረት

ከእርስ በእርስ ግንኙነት ጋር በተገናኘ ክርስቲያኖች እንዲያደርጉ የሚጠበቅባቸውን ነገሮች ለመረዳት፣ ከርዕሱ ጋር በተያያዘ ‹‹እርስ በርሳችሁ›› የሚሉ ሃረጋትን ያካተቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን መመርመር ያስፈልጋል፡፡ በአወንታዊ መንገድ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተገለጹ እንደ እነዚህ አይነት 31 ጥቅሶች እናገኛለን፡፡ ከዚህ በታች ለአብነት ስድስቱ ቀርበዋል፡፡ እያንዳንዱን በመጽሐፍ ቅዱስህ ላይ ካነበብክ በኃላ ምን እንድናደርግ እንደሚያመለክቱን ግለጽ፡፡

 1. ዮሐንስ 15፡12______________
 2. ሮሜ 12፡10________________
 3. ሮሜ 12፡10________________
 4. ኤፌሶን 4፡2________________
 5. ኤፌሶን 4፡32_______________
 6. ዕብራዊያን 10፡25___________
 7. ከላይ ከተገለፁት የ ‹‹እርስ በርሳችሁ›› ጥቅሶች መካከል ለማድረግ የሚያስቸግርህ የቱ ነው? ለምን?
 8. ይህ ጉዳይ ወደፊት በሕይወትህ ውስጥ አስቸጋሪ ሆኖ እንዳይቀጥል ምን ለማድረግ አቅደሀል?

‹‹እግዚአብሔር እኛን ለመስራት ሁሉንም ነገር ይጠቀማል፡፡ ከሁሉ በላይ ግን አንዳንችንን በሌላው በመጠቀም ያበጀናል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ለሌላው መስታዋት ነው፤ ወይም የክርስቶስን ሕይወት በ ‹‹መሸከም›› ለሌላው የሚያሳይ ነው፡፡ ክርስቶስን ለሌላው ሰው ሊያስተዋውቁት የሚችሉት የሚያቁቱ ሰዎች ናቸው፡፡ ለዚህ ነው የክርስቲያኖች እርስ በእርስ መተያየት አስፈላጊ የሚሆነው፡፡›› -ሲ.ኤስ. ሊዊስ

‹‹እውነተኛ ሕብረት›› ምን ማሟላት ይገባዋል?

በሚከተሉት ጥቅሶች መሠረት ክርስቲያኖች ሕብረት ሲያደርጉ ምን መፈጠር አለበት?

 1. ‹‹ብረት ብረትን ይስለዋል፣ ሰውም ባልንጀራውን ይስላል።››-ምሳሌ 27፡17 
 2. ‹‹አንዱም አንዱን ቢያሸንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆማሉ፤ በሦስትም የተገመደ ገመድ ፈጥኖ አይበጠስም።››-መክብብ 4፡12 
 3. ‹‹በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።››-የሐዋሪያት ሥራ 2፡42 
 4. ‹‹በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።››-ሮሜ 15፡1 
 5. ‹‹በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤››-ኤፌሶን 5፡19 
 6. ‹‹ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤››-ዕብራዊያን 10፡24 

ከላይ የተገለፁት ድርጊቶች ሁሉ ክርስቲያኖች ሕብረት ባደረጉ ቁጥር እንዲኖሩ አንጠብቅም፣ ነገር ግን የተለመዱና አዘውትረው የሚስተዋሉ መሆን አለባቸው፡፡ በዚህ መሰረት፣ ከዚህ በታች የቀረቡት ሁኔታዎች እውነተኛ የክርስቲያኖችን ሕብረት ይገልፅ ይሆን?

 1. ሦስት ክርስቲያኖች ለምሳ ተገናኝተው ስለ እግር ኳስ ቡድናቸው የወደፊት እጣ ፈንታ፣ ስለ ተሻሻሉ ኮምፒውተሮች እና ስለ አየሩ ሁኔታ ቢያወሩ፡፡
  • አዎ
  • ፈፅሞ
 2. ሦስት ሴቶች ከምሳ በኃላ ተገናኝተው ካርታ እየተጫወቱና ሻይ እየጠጡ ስለዘመናዊና ስለተሻሻሉ የልብስ ዲዛይኖች ጉዳይ ቢጨዋወቱ፡፡
  • አዎ
  • ፈፅሞ
 3. ሁለት ክርስቲያን ጥንዶች በሚያምር የበጋ ወር ተገናኝተው ስለ ስፖርት ውድድር ቢያወጉ፡፡
  • አዎ
  • ፈፅሞ

በሁሉም አንፃር ‹‹ፈፅሞ›› የሚል ከመረጥክ፣ እንዚህን ሁኔታዎች አበረታች ወደ ሆነ እውነተኛ የክርስቲያኖች ሕብረት ለመቀየር በእያንዳንዱን ዐረፍተ ነገሮች ላይ ምን መጨመር አለበት ትላልህ?

 1. ______________
 2. ______________
 3. ______________

ማህበራዊ ግንኙነታቸው፣ ‹‹እውነተኛ›› የክርስቲያን ሕብረትን ሃሳብ ካላሟላ በቀር፣ ክርስቲኖች እርስ በእርስ ተገናኝተው መልካም ጊዜ ማሳለፍ አይችሉምን?

ሕብረት መደረግ ያለበት የት ነው?

ለዚህ ጥያቄ ወደ አእምሮህ የሚመጣው የመጀመሪያ ምላሽ ‹ቤተ ክርስቲያን› የሚለው ሊሆን ይችላል! ይህ ስፍራ በእርግጥ እርስ በእርስ ለመበረታታትና በሌሎች የክርስቶስ አካል ብልቶች ለመጠቀም፣ የእግዚአብሔርን ቃል ለመመገብ፣ በህብረት እግዚአብሔርን ለማምለክ፣ በአንድነት ለመጸለይ፣ እና እንደ ሬድውድ ዛፎቹ ‹‹እርስ በእርስ እንያያዝ›› ዘንድ በጥልቀት ለመተዋወቅ አማኞች ዘወትር የምንገናኝበት ልዩ ስፍራ ነው፡፡ ‹‹ቤተ ክርስቲያን›› የሚለው ቃል ሁል ጊዜ የአማኞች ስብስብን የሚያመለክት ሲሆን አባላቱና የሚገናኙበት ስፍራ ግን የተለያየ ነው፡፡ ከዚህ በታች የቀረቡትን ጥያቄዎች መልስ፡፡ የሚከተሊትን ጥቅሶች ካነበብክ በኋላ የተስመሩባቸው ሃረጋት የሚገልጡትን ሃሳብ አሰላስል።

 1. ‹‹በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፣ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፤››– 1ቆሮንቶስ 1፡2
 1. ‹‹የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ በቤታቸው ካለች ቤተ ክርስቲያን ጋር በጌታ እጅግ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።››-1ቆሮንቶስ 16፡19
 1. ‹‹(ጳውሎስ ስለራሱ ሲናገር እንዲህ ይላል) እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና፣ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ፤››-1ቆሮንቶስ 15፡9

‹‹የምንመስለው አካባቢያችንን ነው፡፡ ጓደኞችህን አሳየኝና ከአስር አመት በኋላ የምትሆነውን አሳይሀለው፡፡›› -ኸርብ ኢቫንስ።  በተጨማሪ 1ቆሮንቶስ 15፡33 ተመልከት

ማብራሪያ፡- ቤተ ክርስቲያን – በነጭ ቀለም የተቀባች፣ ጉልላት ያላት እና በጉልህ በሚታይ አንድ ቦታ ላይ መስቀል የተከለች ቋሚ ሕንፃ መሆን አለባትን? በአሁኑ ሰአት ያሉ ቤተ ክርስቲያናት ብዙ ጊዜ ይህን ይመስላሉ፤ ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በኋላ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ግን በሰዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ፣ በአይሁድ ምኩራቦች ውስጥ እና አንዳንዴ ደግሞ በገላጣ ስፍራ ትሰባሰብ ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያን የስደት ዘመናት ደግሞ በዋሻዎች ውስጥ፣ በዛፎች ስርና በመቃብር ስፍራዎች ሳይቀር ይሰበሰቡ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶች በተሰሩ በተዋቡ ሕንፃዎች ውስጥ የመገናኘት እድል ገጥሞናል፡፡ ነገር ግን ከዚህ በተለየ መንገድ ቤተ ክርስቲያን በቤቶች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በመጋዘኖች በእስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ በመስሪያ ቤቶች፣ በጂምናዚየሞች እና ሬስቶራንቶች ውስጥ ልትገናኝ ትችላለች፡፡ ዛሬም ክርስቲያኖች በስደት ውስጥ ባሉባቸው ስፍራዎች፣ ቤተ ክርስቲያን ከአሳዳጆቿ አይን በምትሰወርበት ማናቸውም ስፍራዎች ትሰባሰባለች፡፡ አስተውል፡- ቤተ ክርስቲያን ሕዝቦቹ እነጂ ሕንፃው አይደለም!

ሌሎች የሕብረት አውዶች

ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለሆነው ሕብረት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት መሰረታዊውን ሃሳብ የሚሰጡን ቢሆንም፣ (አንተም ደግሞ በእነዚህ ስፍራዎች ለመጠቀም ስትል ንቁ ተሳትፎ የሚጠበቅብህ ቢሆንም)፣ ሕብረት በተለያዩ ስፍራዎች ሊደረግ ይችላል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ልትሰባሰብ የሚገባት የግድ አራት ግድግዳ ባለበት ስፍራ ወይም በተወሰነ ጊዜ ብቻ አይደለም፡፡ ከዚህ በታች በቀረበው ባዶ ቦታ ከተለመደው የቤተ ክርስቲያን ስፍራ በሰባሰቢያ ስፍራ ውጪ፣ የተሳካ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሕብረት ልታደርግባቸው የምትችልባቸውን አራት ስፍራዎች ፃፍ፡፡

 1. ___________________
 2. ___________________
 3. ___________________
 4. ___________________

የበሰለ የሕብረት አድራጊ ሰው ባሕሪያት

መጽሐፍ ቅዱሳችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነውን ሕብረት በብስለት በተረዳ ሰው ውስጥ የሚስተዋሉ ቢያንስ ሃያ ድስት ባሕሪያትን ይገልፅልናል፡፡ እነዚህ ባሕሪያት በእሁድ ማለዳ ብቻ ሳይሆን ሁል ጊዜ አንድ ግለሰብ ከሌሎች ጋር የሚያደርገውን ሕብረት የሚገልጹ ባህሪያት ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡

የሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከእነዚህ 26 መካከል አስሩን ባሕሪያት ይገልጻሉ፡፡ አንዳንዶቹ ስፍራ ላይ ጥቅሶቹ የቀረቡ ሲሆን ሌሎቹን ግን ራስህ ከመጽሐፍ ቅዱስህ ላይ ፈልገህ ማንበብ ይጠበቅብሃል፡፡ እያንዳንዱን ጥቅሶች ካነበብክ በኃላ በጥቅሶቹ ውስጥ ያገኘኸውን የበሰለ ሕብረት አድራጊ ባሕሪይ (ባሕሪያት) ፃፍ፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ

 1. ‹‹እንግዲያስ ሰላም የሚቆምበትን እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን እንከተል።›› ሮሜ 1419   
 2. ‹‹የጌታምባሪያ ለሰው ሁሉ ገር ለማስተማርም የሚበቃ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም።›› -2ጢሞቴዎስ 224
 3. ‹‹በወንድማማችመዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤›› ሮሜ 1210
 4. ‹‹ለጸሎትምበቆማችሁ ጊዜ፣ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፣ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።›› ማርቆስ 1125 1ጴጥሮስ 55-6
 5. ‹‹ስለዚህ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤››ያዕቆብ 119-20ማቴዎስ 543-48
 6. ‹‹ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።›› ሮሜ 1213
 7. ‹‹ደስከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፣ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።›› ሮሜ 1215  

በሕብረት ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን መፍታት

አንድ ሰው እንዲህ አለ፡ ‹‹ፍፁም ቤተ ክርስቲያን ካጋጠመህ፣ ሕብረት አታድርግ- ታበላሸዋለህና!›› ቤተ ክርስቲያንን የመሠረታት ኢየሱስ ክርስቶስ ቢሆንም፣ እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን በቀላሉ ሊሳሳቱ በሚችሉ ሰዎች የተሞላ መሆኑም መዘንጋት የለብህም፡፡ እነዚህ ሰዎች እንደ ክርስቲያን በእግዚአብሔር የተወደዱ፣ ምህረት ያገኙ፣ ከጠላት እጅ የተዋጁ እና ወደ መንግስተ ሰማይ ጉዞ የጀመሩ ቢሆኑም ሊስቱ የሚችሉ ሰዎች ደግሞ ናቸው፡፡ ከክርስቶስ ጋር በዘላለማዊ የክብር መንግስት ውስጥ አብረን እስክንሆን ድረስ ማናችንም ብንሆን ፍፁም ልንሆን አንችልም፡፡ ይህ አንተንም ያካትታል!

በዚህ ጉዞ መካከል አልፎ አልፎ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር የሚከሰቱ ችግሮችን ልትጠብቅ ይገባል፡፡ ኢየሱስ በማቴዎስ 9፡12 ላይ እንደ ገለጸልን፣ ‹‹ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፡፡›› ከታላቁ ሃኪም ውጪ ጤነኛ መሆናቸው የሚሰማቸው ሰዎች ወደ እርሱ አይመጡም፡፡ የሚያስፈልጋቸውን እና ጉድለታቸውን የተረዱ ግን አንድ በሽተኛ እርዳታ ፍለጋ ወደ ሃኪም እንደሚሄድ ሁሉ እርሱን ይፈልጉታል! ስለዚህ ያለህበት ቤተ ክርስቲያን የታመሙ ሰዎች ያሉባት እንደሆነች ልታውቅ ይገባል! ምቾት የማይሰጥ ነጥብ ቢመስልም ጉዳዩን ልትረዳ ይገባል፡፡ ክርስቲያኖች ፍፁማን አይደሉም፤ ነገር ግን እየተሻሉ ለማደግ ጉዞ ጀምረዋል፤ (ቢያንስ ወደ ሆስፒታሉ መጥተዋል!)፡፡ ራስህን ከሌሎች ክርስቲኖች ጋር በማይመች ሁኔታ ውስጥ ስታገኝ አንተንም ሆነ እነሱን በሚጠቅም መልክ ችግሩን ለመፍታት የሚረዱህ ጥቂት መርሆዎች እነሆ፡፡

 1. በሌሎች ላይ አትፍረድ፡፡

በሌሎች ላይ መፍረድ ከሌለብን ምክንያቶች አንዱ ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት የተሟላ መረጃ የሌለን በመሆኑ ነው! ይህን ሊያደርግ የሚችል አንድ ብቻ ነው – እርሱም እግዚአብሔር ነው፣ እኛ ደግሞ እርሱን አይደለንም! በሌላው ሰው አነሳሽ ምክንያቶች፣ ባሕሪያት፣ ምኞቶች፣ ቃሎች እና ድርጊቶች ላይ ማጠቃለያ ላይ ስንደርስ፣ ይህንን የምናደርገው በእውነታው ቅንጣቢ እውቀት ላይ ተመስርተን በመሆኑ ስህተት ለመስራት ቅርብ እንሆናለን፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ልብ ይመለከታል፤ ሰው ግን ይህን ማድረግ አይችልም፡፡ ስለዚህ ፍርዱን ለእግዚአብሔር ስጥ- የአንተ ዋነኛ ስራ ማፍቀር ነው!

‹‹እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፣ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።›› -ማቴዎስ 7፡1-2

በሌሎች ላይ የመፍረድ ተቃራኒው ምንድን ነው?

 1. መጀመሪያ የራስህን አይን አጥራ፡፡

‹‹በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፣ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም? ወይም ወንድምህን። ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፣ በዓይንህ ምሰሶ አለ። አንተ ግብዝ፣ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፣ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።›› -ማቴዎስ 7፡3-5

ብዙ ጊዜ፣ ሰዎች በራሳቸው ላይ ቀለል ብለው በሌላው ሰው ላይ ግን ጠንካራ ሂስ የማድረግ ዝንባሌ ይታይባቸዋል፡፡ በአብዛኛው የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ሌሎችን ዝቅ በምናደርግበት ጊዜ የበላይ የመሆን ስሜት ስለሚሰማን ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ያለውን ሰይጣናዊ ሃሳብ አስተዋልክ አይደል? ከዚህ ይልቅ ሁኔታውን የተገላቢጦሽ እናድርገው፡- ለራስህ ጉድለቶች ጠንካራ ሂስ በመስጠት በሌሎች ላይ ቀላል በል፡፡ መንፈሳዊው የብረት መጋዝህ በአይንህ ውስጥ ባለው ዛፍ ላይ ካነጣጠረ በኋላ የ‹‹ምንጣሮ ለክርስቶስ›› ክለብ አባል መሆን ትችላለህ!

ከአይንህ ሊወገድ የሚገባ ምን ግንድ አለብህ? በመጀመሪያ የቱን ልታስወግድ አቀድክ?

‹‹የክርስቲያን ማህበረሰብ እኛ ወደ ክርስቶስ መልክ የምንቀየርበት የሥራ ስፍራ ነው፤ በመሆኑም በዚህ የሥራ ስፍራ ንጽሕናን ልንጠብቅ አይገባም፡፡›› -ስቴቭ ኦቨርማን

 1. ‹‹ለትልቁ ጉዳይ›› ትኩረት ስጥ፡፡

በአንድ ወይም በሁለት ዋና ጉዳዮች ላይ ከሌላ ክርስቲያን ጋር አለመግባባት ላይ ልትደርስ ትችላለህ፡፡ ነገር ግን ይህ አለመግባባት ጓደኝነታችሁን እንዲያቋርጥ ፈፅሞ አትፍቀድ! በአማኞች ሕይወት ውስጥ በጣም ወሳኙ ነገር ምንድን ነው? ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ሕብረትና ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸው አስተያየት አይደለምን? በእዚህ ጉዳይ ላይ የምትስማሙ ከሆነ የቀረው ነገር ሁሉ ኢምንት ሊሆን ይገባል፡፡ ጥቃቅን በሆኑ የልዩነት ነጥቦቻችሁ ላይ ሳይሆን ዋና በሆኑ የስምምነት ነጥቦቻችሁ ላይ ትኩረት አድርግ፡፡

‹‹አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ አንድነት፣ አጠያያቂ በሆኑቱ ደግሞ የመምረጥ ነፃነት፣ ነገር ግን በሁሉ ነገር ፍቅር ይኑርህ፡፡››-ሩፓርተስ ሜልዴኑስ

 1. ፋታ ስጥ፡፡

‹‹በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤›› -ኤፌሶን 4፡2። ጥቅሱ እንደሚያዘው፣ ለምን ትሑት፣ የዋህና ትዕግስተኛ መሆን ያስፈልገኛል? ምክንያቱማ፣ አንተም እንደማንኛውም ሰው ታጠፋልህ፡፡ ከዛም ሰዎች ‹‹እንዲያልፉህ›› የምትፈልግበት ወቅቶ ይኖራልና ነው፡፡ ከሌሎች ጋር ያለህን የሕብረት መልክ ራስህ ልትወስን ትችላለህ፡፡ ስህተት ፈላጊ ከሆንክ ምናልባት ሰዎችም ባንተ ላይ ይህንኑ ያደርጉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ዝንባሌህ፡- ‹‹አብረን ማደግ አለብን፤ እርስ በእርሳችን እንረዳዳ፣›› የሚል ከሆነ፣ ሕብረታችሁ ጥልቅና ጠንካራ እየሆነ ይሄዳል፡፡ በወንድምህ ወይም እህትህ ላይ የምታየውን የተገለጠ አጥፊ ኃጢአት ችላ በማለት ማበረታታት እንደሌለብህ ሁሉ በእያንዳንዱ ስህተቶቻቸው ላይ እጅ ማንሳትም አይገባህም፡፡

ማን ፋታ እንዲሰጥህ ትፈልጋለህ? በምን መንገድ?

 1. ምቹ በሚሆንበት ጊዜ፣ በፍቅር አርም፡፡

‹‹የተገለጠ ዘለፋ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል። የወዳጅ ማቍሰል የታመነ ነው፤ የጠላት መሳም ግን የበዛ ነው።››– -ምሳሌ 27፡5-6። አስቀድሞ የተገለጹትን- አለመፍረድ፣ በራስህ አይን ውስጥ ያለውን ማጥራትና የሌሎችን ሰዎች ስህተቶች ማለፍ- ከግምት ውስጥ አስገብተህ ለአማኙ ድነት ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ላለ ሕብረት ሲባል አንዳንድ ጉዳዮችን ለመፍታት በፍቅር እርምጃዎችን ልትወስድ ትችላለህ፡፡ ያን ሰው የምትወድ ከሆነ በእርግጥ እርምጃ ትወስዳለህ፡፡ ነገር ግን ድርጊትህ በፍቅርና ትህትና ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይገባል፡፡ እርምጃውን ስትወስድ ውስጥህ እንዲህ ሊል ይገባል፡- ‹‹ይህን ሳደርግ ካንተ የተሻልኩ ነኝ እያልኩ አይደለም፤ መፍትሄ እየጠቆምኩ ያለሁ፣ ነገር ግን እኔም ብሆን ችግር ያለብኝ ሰው ነኝ፡፡ ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ላናግርህ እወዳለሁ…››

 1. አነሳሽ ምክንያትህንና ስልቶችህን መርምር፡፡

‹‹እንደሚዋጋ ሰይፍ የሚለፈልፍ ሰው አለ፤ የጠቢባን ምላስ ግን ጤና ነው።›› –ምሳሌ 12፡18። በሌላው ወንድምህ ወይም እህትህ ውስጥ ስላየኸው ነገር መነጋገር እንዳለብህ ሲሰማ፣ ከማናገርህ በፊት ራስህን ይህን ጥያቄ ጠይቅ፡- ‹‹አላማዬ፣ ማረድ ወይስ ቀዶ ጥገና ማድረግ?›› ከምክርህ በኋላ ሰዎቹ በመንፈስ እና በፍቅር ከተቀመመው ትሁት ምክርህ የተነሳ ይበረታታሉ ወይስ በደረሰባቸው ውጊያ ቆስለው ይደማሉ?

የጤናማ ቤተ ክርስቲያን ምልክቶች

 • መጋቢው ለመጽሐፍ ቅዱስ ክብር ይሰጣል፣ እሱንም ያስተምራል
 • ጸሎትና አምልኮ በግላጭ ይታያሉ፡፡
 • ወንጌል በግልጽ ይቀርባል፡፡
 • ሰዎችን ለክርስቶስ ደቀ መዝሙር በማድረግ፣ ለታላቁ ተልዕኮ ትኩረት ይሰጣል፡፡
 • አማኞች፣ እርስ በእርሳቸውና ለጎብኚዎች ምቹ ናቸው፡፡
 • ሁሉም አማኝ በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት ውስጥ የራሱን ድርሻ ይወጣል፡፡
 • ለተቸገሩ ለጋሶች ናቸው፡፡
 • በእግዚአብሔ ላይ ያለ እምነት ለሁሉም ውሳኔዎች መሠረት ነው፡፡

ከሕይወትህ ጋር ማዛመድ፡-

 1. በሣምንት ምን ያህል ጊዜ በክርስቲያኖች ሕብረት ውስጥ ትካፈላለህ? (ይህ ሕብረት፣ ቤተ ክርስቲያን በመካፈል፣ መጽሐፍ ቅዱስ በማጥናት፣ የጸሎት ስብሰባዎች ላይ በመካፈል፣ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በተለየ መንገድ አብሮ ጊዜ በማሳለፍ የሚገለጽ ሊሆን ይችላል)
 2. ይህንን በበቂ ደረጃ እያደረክ ያለህ ይመስልሃል?
 3. ለውጥ ለማድረግ የምታቅድ ከሆነ ምን አይነት ለውጦች ታደርጋለህ? በምን ያህል ፍጥነት?

የቃል ጥናት ጥቅስ፡-

‹‹ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፣ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፣ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤›› -ዕብራዊያን 3፡13

ማጠቃለያ፡- ‹‹ከመንጋዎቼ ጋር አብረህ ትሆናለህ ወይ?›› ሲል ኢየሱስ ይጠይቅሀል፡፡

ምዕራፍ 7ትን ያጥኑ