ትንቢተ ሶፎንያስ

የትንቢተ ሶፎንያስ ዓላማ እና ዐብይ ትምሕርት

የትንቢተ ሶፎንያስ ዓላማ ከይሁዳ ውድቀት በፊት እግዚአብሔር የመጨረሻ መልእክተኞች ካደረጋቸው ቃል አቀባዮቹ አንዱ ሶፎንያስ ነበር። ሶፎንያስ በእግዚአብሔር የተላከው በክፋታቸው ምክንያት በቅርብ ጊዜ ስለሚፈጸምባቸው ፍርድ በመናገር የይሁዳን ሕዝብ ለማስጠንቀቅ ነበር። ሕዝቡ ንስሐ ካልገቡና አኗኗራቸውን ካልለወጡ ሊመጣባቸው ስላለው ፍርድ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ለማቅረብ እግዚአብሔር ተጠቀመበት። በመሆኑም ሊመጣ ስላለው «የጌታ ቀን» ተናገረ። ይህ ቀን አብዛኛው ሕዝብ እንደሚጠብቀው የደስታና የበረከት […]

የትንቢተ ሶፎንያስ ዓላማ እና ዐብይ ትምሕርት Read More »

ትንቢተ ሶፎንያስ መግቢያ

የውይይት ጥያቄ፥ ሶፎንያስ 1፡12 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር እቀጣለሁ ያለው ምን ዓይነት ሰዎችን ነበር? ለ) ሰዎች ስለ እግዚአብሔር የነበራቸው የተሳሳተ አመለካከት ምን ነበር? ለእግዚአብሔር ሕዝብ እጅግ አደገኛ ከሆኑ ነገሮች ዋናው በእግዚአብሔር ላይ በግልጽ ማመፅ አይደለም። ወደ ሐሰት ትምህርቶች ወይም ሃይማኖቶች መለወጥም አይደለም። የእግዚአብሔር ሰዎች በራሳቸው መርካታቸው እንጂ። ሶፎንያስ ባገለገለበት ዘመን በይሁዳ ላይ ችግር ከፈጠሩት ኃጢአቶች አንዱ

ትንቢተ ሶፎንያስ መግቢያ Read More »