ትንቢተ ናሆም

የትንቢተ ናሆም ዓላማ እና ዋና ዋና ትምርቶች

የትንቢተ ናሆም ዓላማ ናሆም ብቸኛ ዓላማው የነነዌን ውድቀት ማመልከት ነበር። እንደ ዮናስ ወደ ነነዌ በመሄድ መልእክቱን አላቀረበም። መልእክቱን ያቀረበው በይሁዳ ሆኖ ነበር። የናሆም መልእክት አሦርን ስለሚመጣባት ሽንፈት ለማስጠንቀቅ የተሰጠ አልነበረም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ ለነበሩት ለአይሁድ የተሰጠ የማበረታቻ መልእክት ነበር። ለብዙ ዓመታት በአሦር መንግሥት ቁጥጥር ሥር ነበሩ። አሁን ግን ነነዌ የምትደመሰስበት ጊዜ እንደደረሰ እግዚአብሔር ይነግራቸዋል። […]

የትንቢተ ናሆም ዓላማ እና ዋና ዋና ትምርቶች Read More »

ትንቢተ ናሆም መግቢያ

የእግዚአብሔር ፍትሐዊ ወፍጮ የሚፈጨው በዝግታ ቢሆንም ጥሩ አድርጎ ይፈፃል የሚል አባባል አለ። ይህ ማለት በሰብአአዊ አመለካከት የእግዚአብሔር ፍትሕ በምድር ላይ የሚሠራ አይመስልም ማለት ነው። በሁሉም ስፍራ ጦርነት፥ ድኅነት፣ ፍትሕ-አልበኝነትና ክፋት አለ። ኃጢአተኞች እንዲሳካላቸውና ኑሮ እንዲሰምርላቸው ጉቦን፥ ዛቻንና ሰውን ማሠቃየትን ይጠቀማሉ። ብዙውን ጊዜ የእግዚአብሔርን ሕግጋት በግልጽ ከሚጥሱ ሰዎች ይልቅ ጻድቃን የበለጠ ሥቃይ የሚቀበሉ ይመስላሉ። እንዲህ ባሉ

ትንቢተ ናሆም መግቢያ Read More »