ባለፈው ሳምንት፥ ክርስቶስ በሕይወቱም ስሞቱም ስለፈጸማቸው አገልግሎት አጥንተን ነበር። እነዚህ አንዳንድ ጊዜ የክርስቶስ የውርደት አገልግሎቶች ተብለው ይጠራሉ። በዚህ ሳምንት ደግሞ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ፥ እርገትና በዚህ ዘመን ስለሚፈጽማቸው አገልግሎቶች እናጠናለን። እነዚህ ከክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር መምጣት ጋር ተያይዘው የክርስቶስ የከፍታ እገልግሎቶች ይባላሉ።
የኢየሱስ ትንሣኤ
የክርስትና እምነታችን የማዕዘን ድንጋይ ከሆኑ ታላላቅ ድርጊቶች አንዱ የክርስቶስ ትንሣኤ ነው። ስለዚህ የክርስቲያን እምነት የሚነሣውም የሚወድቀውም በክርስቶስ ትንሣኤ ላይ ነው። በመሆኑም እያንዳንዱ አማኝ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤና በትንሣኤውም በምን ምክንያት እንደሚያምን መግለጽ መቻል አለበት።
ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮንቶስ 5፡14፥17-18 አንብቡ። ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስ ከሞት ባይነሣ ኖሮ፥ ምን እውነት በሆነ ነበር አለ?
ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ ውስጥ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስፈላጊነት ይነግረናል። በዚህ ክፍል ሐዋርያው፥ ክርስቶስ ባይነሣ ኖሮ የእርሱ ስብከት ከንቱ በሆነ፥ የቆሮንቶስ ሰዎችም እምነት እንዲሁ ከንቱ በሆነ፥ አማኞችም ሁሉ በኃጢአታቸው በጠፉ ነበር ይላል። ክርስቶስ ከሞት ባይነሣ ኖሮ፥ በክርስቶስ አማኝ የነበሩና የሞቱ ሰዎች ተስፋቸው ከንቱ በሆነ ነበር፤ እንዲሁም የክርስቲያን ሕይወት በከንቱ የቀረ ሕይወት የመሆን ዕጣ ይደርስበት ነበር። ስለዚህ ያለ ትንሣኤ የክርስትና እምነት ሊኖር አይችልም። በመሆኑም ስለ ትንሣኤ ያለውን እውነትና ቁም ነገር፥ ዋጋውንም በሚገባ መገንዘብ አለብን። ይህ ሲሆን ትንሣኤው ለእምነታችንም ሆነ ለሌሎችም በምናደርገው አገልግሎት ሁሉ ሊጠቅመን ይችላል።
እዚህ ላይ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ ልንመልሳቸው የሚገቡን በርከት ያሉ ጥያቄዎች አሉ። ስለ እነዚህ ቀጥለን ተራ በተራ እንመለከታለን።
1. በእርግጥ ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶአል?
ኢየሱስ ከሞት ተነሣ የሚለውን ትምህርት ሲሰሙ ብዙ የተማሩ ሰዎች በአባባሉ ላይ ያፌዛሉ። አንዳንዶቹ በኢየሱስ አካል ላይ ስለተፈጸመው ሁኔታ የራሳቸው የሆነ ተለዋጭ አሳብ ይሰነዝራሉ። በእርግጥ አንዳንዶቹ ኢየሱስ በመስቀል ላይ አልሞተም፥ ብዙ ደም ስለፈሰሰው ራሱን ስቶ ስለነበር ነፍሱ ፍጹም ስላልወጣች ኋላ በመቃብር ውስጥ ሆኖ ሕይወት ዘራ ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ የኢየሱስን አካል ሰርቀውት ነበር ይላሉ። የተቀሩት ተከራካሪዎች ደግሞ ወደ መቃብር ሄደው የነበሩት ሴቶች ወደ ተሳሳተ መቃብር ስለ ሄዱ አጡት እንጂ፥ ኢየሱስ ግን እንደ ሞተ በዚያው በራሱ መቃብር ውስጥ ነበር ይላሉ።
ጥያቄ፡- ዮሐንስ 19፡31-37 አንብቡ። ኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞቱን ማን አረጋገጠ? እንዴት አረጋገጡ?
ጥያቄ፡- ማቴዎስ 28፡11-15 አንብቡ። የኢየሱስን አካል ደቀ መዛሙርቱ ሰረቁት ብለው በመጀመሪያ የሐሰት ወሬ የነዙት እነማን ነበሩ?
ጥያቄ፡- የሐዋ. ሥራ 5፡40 አንብቡ። ደቀ መዛሙርቱ ስለ ትንሣኤ በመስበካቸው ምን ደረሰባቸው?
ስለ ኢየሱስ ትንሣኤ የተሠነዘሩ የተለያዩ ማመካኛዎች እያንዳንዳቸው ቀላል መልስ አላቸው። በመስቀል ላይ ተሰቅለው የነበሩ የሦስቱን ሰዎች ሞት ለማፍጠን ሊል ጲላጦስ ጭናቸው እንዲሰበር አዘዘ፡፡ ይህ የተደረገበት ምክንያት ከእንግዲህ ወዲያ በመስቀል ላይ ሆነው ለመተንፈላ ሊሉ ሰውነታቸውን በእግሮቻቸው ወደ ላይ መግፋት እንዳይችሉ ለማድረግ ነበር። እንዲህ ባለ ሁኔታ ሰዎቹ አየር በማጣት ቶሎ እንዲሞቱ ነበር። ነገር ግን ወታደሮቹ የኢየሱስን ጭን ለመስበር በመጡ ጊዜ ሞቶ አገኙት። ሆኖም ለ ለመሞቱ እርግጠኛች ሊሆኑ ስለ ፈለጉ ጎኑን በጦር ወጉት። በዚያን ጊዜም ከጎኑ የፈሰሰው ደምና ውኃ፥ በወቅቱ ክርስቶስ ራሱን የሳተ ሳይሆን የሞተ መሆኑን የሚያረጋግጥ ትክክለኛ ምልክት ነበር።
ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሰረቁት የሚለው ሐሰተኛ ወሬ፥ ስለ ጌታ ትንሣኤ ቀደም ብሎ በመጀመሪያ የተነሣ ሐሰተኛ ወሬ ነበር። ይህን የሐሰት ወሬ እንዲነዙ፥ የአይሁድ ሊቀ ካህናት መቃብሩን ይጠብቁ ለነበሩ ወታደሮች ጉቦ ከፍለዋቸው ነበር። ነገር ግን ይህ የፈጠራ ወሬ በብዙ ምክንያቶች መሠረተ ቢስ ነው። በመጀመሪያ ነገር፥ ወታደሮቹ ተኝተው ከሆኑ በኢየሱስ ሥጋ ላይ ስለ ደረሰው ሁኔታ ሊያውቁ አይችሉም። ሁለተኛ፥ ሐሙስ ሌሊት ፈርተው የሸሹ ደቀ መዛሙርት (ማቴ. 26፡56)፥ እሑድ ማለዳ በታጠቁ ወታደሮች ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ነበራቸው ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ሦስተኛ ነገር፥ ሁሉም ደቀ መዛሙርት የተሰደዱት ስለ ትንሣኤ ይሰብኩ ስለነበረ ነው። የቤተ ክርስቲያን ታሪክም እንደሚነግረን፥ ከደቀ መዛሙርቱ አብዛኛዎቹ በዚህ ምክንያት ተገድለዋል። ደቀ መዛሙርቱ የኢየሱስን ሥጋ ሰርቀውት ቢሆን ኖር፣ ስለ ጉዳዩ የሚዋሹት ለአጭር ጊዜ ብቻ በሆነ ነበር። ነገር ግን ለውሸት ብለው ስደትንና ሞትን ባልተቀበሉ ነበር።
ሴቶች ወደ ሌላ መቃብር ሄዱ የሚለውም መላ የሞኝነት አነጋገር ነው። ይህ ቢሆን ኖርማ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶአል እያሉ ገና መስበክ እንደ ጀመሩ፥ የአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች ትክክል ነው ወደሚሉት መቃብር ሄደው ለሰው ሁሉ የኢየሱስን አስከሬን ባሳዩ ነበር። ይህ ራሱ ብቻ የደቀ መዛሙርቱን ስብከት እዚያው ባለበት ባስቀረው ነበር። እንደ እውነቱ ከሆነ ኢየሱስ ከሞት መነሣቱን ለማስተባበል የተነዛው የሐሰት ወሬ ሁሉ ከሽፎአል። ስለዚህ ኢየሱስ ከሞት የመነሣቱ እውነት በግልጽ በማስረጃ ተረጋግጦአል።
2. ከሞት የተነሣው የኢየሱስ አካል ምን ይመስል ነበር?
ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 5፡20 አንብቡ። ሀ) ከትንሣኤው የተነሣ ክርስቶስ እንዴት ተብሎ ተብራራ? ለ) 1ኛ ቆሮ. 15፡37 እንብቡ። ሐዋርያው ጳውሎስ የአሁኑን አካላችንን፥ ክሚነሣው አካል ጋር ለማነጻጻር ስምን ምሳሌ ተጠቀመ? ሐ) 1ኛ ቆሮ.
5፡42-44 አንብቡ። የትንሣኤ አካል በእንዴት ዓይነት መንገድ ተብራራ? በዚህ ላይ ቢያንስ አራት ገለጻዎችን አቅርቡ።
ጥያቄ፡- ዮሐ 20፡10-16 አንብቡ። ሀ) መግደላዊት ማርያም ኢየሱስን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስታወሰችው መቼ ነው? ለ) ሉቃስ 24፡13-16፥ 28=31 አንብቡ። ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ በኤማሁስ መንገድ ላይ ሲሄዱ በነበሩበት ጊዜ፥ ኢየሱስን በመጀመሪያ ያስታወሱት መች ነው? ሐ) ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስን እንዳስታወሱ ምን ሆነ?
ጥያቄ፦ ሀ) ዮሐንስ 20፡19-20 አንብቡ። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የተገለጠበት ሁኔታ እንግዳ ሰለ መሆኑ ይህ ክፍል ምን ይላል? ለ) ከተገለጠላቸው በኋላ ምን አሳያቸው? ሐ) ሉቃስ 24፡36-43 አንብቡ። ኢየሱስ መንፈስ ብቻ ሳይሆን ሥጋና አጥንት ስለመሆኑ ምን ማረጋገጫ ሰጣቸው? መ) ኢየሱስ በቁጥር 39 ላይ ሥጋና አጥንት እንዳለው እንዴት ገለጸላቸው? ሀ) ማቴዎስ 28፡8-9 አንብቡ። ለተቹ ኢየሱስን ከትንሣኤው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳገኙት ምን አደረጉ?
እንሞቱት የመነግት የመሬት ሰዎች ሞቷል። እዚህም አልጋ
ኢየሱስ ከሞት በተነሣ ጊዜ፥ ከመሞቱ በፊት ከነበረው የተለየ አካል ለብሶ መነሣቱ የሚያጠራጥር አይመስልም። በ1ኛ ቆሮንቶስ 5፡20 ላይ «ክርስቶስ ለሞቱት የመነሣት የመጀመሪያው ምሳሌ ሆኖ በእርግጥ ከሞት ተነሥቶአል» ይላል። ከኢየሱስ በፊት ሰዎች ሞተው አካላቸው ሕይወት ዘርቶ መነሣታቸውን ቅዱስ መጽሐፍ በግልጽ ያስረዳል። ለዚህም አልዓዛር ( ዮሐንስ 11፡44) እና የኢያኢሮስ ሴት ልጅ (ሉቃስ 8፡55) እንደ ምሳሌ የሚቀርቡ ናቸው። ሆኖም እነዚህ ሰዎች ሕይወት በዘሩ ጊዜ ልዩ አካል ለብሰው አልተነሡም። ግን ነፍሳቸው እንዲሁ ወደ ቀድሞው አካላቸው ተመለሰች። በመሆኑም በቀድሞ እካላቸው ውስጥ የነበሩት ልባቸው፥ ላምባቸው፥ አንጎላቸው እንደገና መሥራት ጀመሩ። ነገር ግን ኢየሱስ ከሞት በተነሣ ጊዜ፥ ፍጹም የተለየ አካል ለብሶ ተነሣ። የለበሰው አካል በአቋሙ ሥጋዊ አካል ይምሰል እንጂ ነገር ግን ከመሞቱ በፊት ከነበረው አካልና እኛም አሁን ካለን አካል የተለየ ነበር። ኢየሱስ የለበሰው አካል የማያረጅና የማይሞት አካል ነበር። የከበረና ከፍ ያለ አካል ነበር። ስለዚህ ነው ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ እርሱ «ለሞቱት ከሞት የመነሣት የመጀመሪያው ምሳሌ» ብሎ የተናገረው። ሐዋርያው ጳውሎስ የሚነግረን ኢየሱስ ከተነግ በኋላ የነበረው አካል በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ ከሙታን ሲነሡ የሚለብሱት ዓይነት አካል መሆኑን ነው። ከሞት በተነሣ ጊዜ አካሉ ልዩ ወደ ሆነ የትንሣኤ አካል የተለመጠለት የመጀመሪያው ኢየሱስ ነው። ከሞት በመነሣትና የትንሣኤ አካል በመልበስ በእውን እርሱ የመጀመሪያው ነው።
የኢየሱስ የትንሣኤ አካል ምን ይመስል ነበር? የእኛስ የትንሣኤ አካል ምን ይመስል ይሆን? ሐዋርያው ጳውሎስ በሚሞት በእሮጌው አካላችንና ለወደፊት በምንለብሰው የትንሣኤ አካላችን መካከል ያለውን ልዩነት ለመግለጽ የዘርንና የተክልን ምሳሌ ተጠቅሞአል። በስንዴ ዘርና ሙሉ እድገት ላይ በደረሰው የስንዴ ተክል መካከል መመሳሰል ይታያል። ሆኖም አንዳንድ ልዩነቶችም አሉ። በዚሁ መሠረት በኢየሱስ አሮጌው አካልና፥ ሞቶ በተነሣው አካሉ መካከል አንዳንድ ተመሳሳይነቶች ነበሩ። እነዚህ ተመሳሳይነቶችና ልዩነቶች ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ በኋላ ታይተውበታል። በመሆኑም በኢየሱስ ገጽታ ላይ ለየት ያለ ሁኔታ ይታይ እንደ ነበረ ግልጽ ነው። ስለዚህ መግደላዊት ማርያም ወዲያው እንዳየችው በአንድ ጊዜ ልታስታውሰው አልቻለችም። እንደዚሁም ወደ ኤማሁስ ይጓዙ የነበሩ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት በአንድ ጊዜ ሊያውቁት አልቻሉም። በዮሐንስ 21 ውስጥ በሊላ ባሕር አጠገብ ኢየሱስ ለሰባቱ ደቀ መዛሙርቱ ተገለጠ። በዚያን ጊዜ በኢየሱስ ገጽታ ላይ ለየት ያለ ሁኔታ ይታይ ስለነበረ፥ ብዙ ዓሣ እንዲይዙ ባደረገው ተአምር ሳቢያ ኢየሱስ መሆኑን ቢያውቁትም፥ ቁጥር 12 እንደሚያስረዳን «ከደቀ መዛሙርቱ አንድ እንኳ ‹አንተ ማን ነህ) ብሉ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም»። ታዲያ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ መሆኑን አውቀዋል፥ ነገር ግን ስለ ማንነቱ በአእምሮአቸው ውስጥ እንዳች ጥርጣሬ እንደነበረም ይህ ጥቅስ የሚጠቁም ይመስላል። ያም ሆኖ በኋላ ኢየሱስ በታያቸው ዘንድ ሁሉ ይታወቅ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት ሰነበረው መልክና ኋላም ከትንሣኤው በኋላ በተጎናጸፈው ገጽታ መካከል መመሳሰልም ልዩነትም ነበር።
ጳውሎስ ኢየሱስ ከትንሣኤው በኋላ የለበሰውን አካል የማይበላሽ ይለዋል (ይህም የማያረጅ ወይም የማይሞት ማለት ነው)። ይህ አካል ክቡር፥ ኃያልና መንፈሳዊ አካል ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን አካል መንፈሳዊ አካል ነው ሲል፥ ምንም ዓይነት ሥጋና አጥንት የሌለበት አካል ነው ማለቱ አይደለም። ከሞት የተነሣው ኢየሱስ አካል ሥጋና አጥንት ነበረው። ኢየሱስ በመጀመሪያ በላይኛው ክፍል ለደቀ መዛሙርቱ በታየ ጊዜ፥ ገና ሲያዩት የኢየሱስ መንፈስ የተገለጠላቸው መስሎአቸው ነበር። ኢየሱስም ሥጋና አጥንት መሆኑን ሊያስገነዝባቸው ሲል፥ መጥተው እንዲዳስሱት አበረታታቸው (ሉቃ. 24፡39)፣ በፈታቸውም ትንሽ ዓሣ በላ (ሉቃስ 24፡42 43)። ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ በኋላ በመንገዱ ላይ ያገኙት ለቶች ባዩት ጊዜ በእግርቼ ሥር ወድቀው ሰገዱለት። ኢየሱስ ያለ ጥርጥር ለቶች ሊጨብጡ የቻሉት አካል ነበረው። እንደዚሁም ኢየሱስ በሚስማር ተቸንክረው የነበሩ እጆቹንና በጦር ተወግቶ የነበረ የጎኑን ጠባሳዎች ለደቀ መዛሙርቱ አሳያቸው (ዮሐ 20፡19-20)። ከሞት የተነሣው አካሉ በአንዳንድ ሁኔታ ከመሞቱ በፊት ከነበረው አካሉ ጋር ተመሳሳይነት ነበረው። ይሁንም እንጃ ለየት ያለ አካል እንደ ነበረ ግልጽ ነው። ኢየሱስ በመጀመሪያ በላይኛው ክፍል ለደቀ መዛሙርቱ በታየ ጊዜ፥ በተዘጋ ክፍል ውስጥ በድንገት ገብቶ ነበር የታያቸው። ኢየሱስ በሆነ መንገድ በተዘጋው ክፍል ውስጥ ሰተት ብሎ ተራምዶ ገብቶ ይሆናል። ወይም ወደ ክፍሉ ውስጥ መጀመሪያ በገባ ጊዘ እንደዚሁም ኋላ ያለ ጥርቅም ቶች ባዩት ለደቀ መዛሙርቱ አልታያቸው ይሆናል። በኤማሁስ መንገድ ላይ ይጓዙ ለነበሩ ደቀ መዛሙርት ከታያቸውና ካወቁት በኋላ ወዲያው ተሰወረባቸው። ከሞት የተነሣው የኢየሱስ አካል፥ ከመሞቱ በፊት ከነበረው አካሉ ጋር በአንዳንድ መንገዶች ተቀራራቢ የሆነ፥ ነገር ግን ደግሞ ልዩነት የነበረው ነበር። ያሁኑ አካሉ ግን የካበረ፥ የማይበላሽና አዲስ ኃይል ያለው አካል ነው።
አንዳንድ የትምህርተ መለኮት ተማሪዎች ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 5፡20 ላይ፥ «ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም» ያለውን ይጠቅሱና፥ ኢየሱስ የትንሣኤው አካል «ሥጋና አጥንት» አለው ሲሉ ይናገራሉ (ሉቃስ 24፡9)። በመቀጠልም ምናልባት የኢየሱስ የትንሣኤ አካል ቆዳና አጥንት ሊኖረው ይችል ይሆናል፥ ደም ግን አይኖረውም በማለት ግምታቸውን ይሰጣሉ፤ እንዲሁም የተነሣው አካሉ አሁን ከምናየው ከእኛ አካል የተለየ አካላዊ ሥርዓተ ተቋም ነበረው ይላሉ። በመጨረሻም በዚህ ግምታዊ አነጋገራቸው ወደፊት የሚኖረን የትንሣኤ አካላችንም እንደዚሁ የተለየ አካላዊ ሥርዓተ ተቋም ይኖረዋል ሲሉ አሳባቸውን ደምድመዋል። ይሁንና ቅዱስ መጽሐፍ ስለ ትንሣኤ አካል እንዲህ ጠለቅ አድርጎ አልነገረንም ለማለት ይቻላል። ጳውሎስ በ1ኛ ቆርንቶስ 5፡50 ውስጥ ምናልባት ሊናገር የፈለገው አሁን ያለንበት ሟች ሥጋችን በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ አሁን በያዘው አካላዊ ሥርዓተ ተቋም ለዘላለም ሊኖር እለመቻሉን ነው። ስለዚህ አካላችን ተለውጦ ሌላ ሆኖ ይሠራል። ኢየሱስ ከሞት በተነሣ ጊዜ እንዲሁ ብቻ ወደ ሕይወት ተመልሶ አልመጣም። ነገር ግን አካሉ ወደ አዲስ አካል ተለውጦ አዲስ አካላዊ ሥርዓተ ተቋም ይዞ ተነሥቷል ብለን ልንደመድም እንችላለን። ሆኖም ስለ ክርስቶስ የትንሣኤ አካል ይዘትና አቋም ለመተንተን ብንሻ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከመጠን በላይ የሆነ ዝርዝር ማብራሪያ ለማግኘት እንደምንሞክር ያህል ይቆጠራል። በጥቅሱ ትንሣኤው የኢየሱስን አካል ወደማይበላሽ፥ ክብርን ወደ ተጎናጸፈ አካል ለውጦታል ብለን ልንደመድም እንችላለን።
3 ትንሣኤው ለእኛ የሚሰጠን ጥቅምና ቁም ነገር ምንድን ነው?
ትንሣኤው በሁለት ምክንያቶች ለአማኛች ጠቀሜታ ያለው ቁም ነገር ይዟል። በመጀመሪያ፣ በክርስቶስ ትንሣኤ አዲስ ኃይል የተሞላን አዲስ ሰዎች ሆነናል። ሁለተኛ የክርስቶስ ትንሣኤ ደኅንነታችንና የወደፊት ትንሣኤያችንን አረጋግጦልናል።
ጥያቄ፡- ኤፈሶን 2፡4፥ ቆላስይስ 3፡1 እና ሮማ 8፡4 አንብቡ። እግዚአብሔር ክርስቶስን ባስነሣ ጊዜ እነማንን ሕያዋን አደረገ?
ጥያቄ፡– ኤፌሶን 19-20 እንዳውም ፊልጵስዩስ 3፡10 አንብቡ። ሐዋርያው አውሎስ ምን ኃይል እንድናውቅ ይፈልጋል?
ትንሣኤ ከብዙ ምክንያቶች የተነሣ ለክርስቲያኖች በጣም አስፈላጊ ነው። በመጀመሪያ፥ አንድ አማኝ ክርስቶስን እንደ ግል መድኃኒቱ አድርጎ ሲቀበለው፥ እርሱ የነበረበት አሮጌው ሰው ይሞታል። አዲሱ ሰው ሕያው ሆኖ ይነሣል። ልክ አሮጌው ሰው በመስቀል ላይ ከክርስቶስ ጋር እንደ ሞተ ሁሉ፥ በክርስቶስ ትንሣኤ እዲሱ ሰው ሕያው ሆኖ ይነሣል። ኤፌ 2፡4 እና ቆላስይስ 3፡1፥ አማኞች በክርስቶስ ባመኑ ጊዜ፥ «ከክርስቶስ ጋር ከሞት ተነሡ» ይላል። ይህን የመሰለውን ሁኔታ አንዳንድ ጊዜ «አዲስ ልደት» እንለዋለን። አንድ ሰው ክርስቶስን እንደ አዳኙ ተቀብሎ ሲያምንበት፥ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከላይ ይወለድና አዲስ ሰው ይሆናል። በዚህ ሁኔታ አማኞች አዲስ ሰዎች ሆነው ከክርስቶስ ጋር ከሙታን ስለ ተነሡ በአዲስ ሕይወት ለመኖር የሚያስችላቸውንና የሚያስፈልጋቸውን ኃይል ትንሣኤው ይሰጣቸዋል። ሮሜ 6፡4፥ ከክርስቶስ ጋር ስለ ተነሣን፥ አዲስ ሕይወት እንኖራለን ይላል። እንዲሁም በኤፌሶን 1፡19-20 ባለው ክፍል፥ ሐዋርያውም ጳውሎስ፥ የኤፌሶን አማኞች የእግዚአብሔርን ኃይል፥ ይኸውም ክርስቶስን ከሞት ያስነሣውን እንዲያውቁ እንደሚጸልይ ይነግራቸዋል። እንዲሁም በፊልጵስዩስ 3፡10 ላይ ሐዋርያው፥ በሕይወቱ አንደኛውና ታላቁ ግብ የክርስቶስን የትንሣኤ ኃይል ማወቅ እንደሆነ ያስረዳል። ስለሆነም በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ በክርስቶስ ከማመናቸው በፊት፥ ይኖሩ ወደ ነበሩበት ሕይወት እስከሚመለሱ ድጋፍ ያጡ አይደሉም። እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር አስነሥቶ ፍጹም የሆነ አዲስ ሕይወት ሰጥቷቸዋል። ከዚህም ሕይወት ጋር በእግዚአብሔር የትንሣኤ ኃይል አዲስ ሕይወትን የሚለማመዱበት ዕድል አብሮ ይመጣል።
ጥያቄ፡- አንድ ወደ እናንተ የመጣ የኃጢአት ፈተናን ለመቋቋም የሚያስችል የእግዚአብሔር የትንሣኤ ኃይል በሕይወታችሁ ሲሠራ ለማየት የፈለጋችሁበትን ሁኔታ አስቡ። እግዚአብሔር ይህን ፈተና የምታሸንፉበትን የራሱን ኃይል እንዲሰጣችሁ የምታቀርቡለትን የጸሎት ርእስ ጻፉ።
እኛ አዲስ ሕይወትን እንድንኖር እግዚአብሔር ኃይሉን ይሰጠናል። ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን ኃይል በሕይወታችን ውስጥ እንዲገልጣቸውና፥ ፈተናም ሲደርስብን ፈተናውን ለማሸነፍ እንድንችል እርሱን በመለመን ልንጠቀምበት ይገባል። የሌላውን ሰው ንብረት የመመኘት ፈተና ሊያጋጥመን፥ እግዚአብሔር ልባችንና አእምሮአችንን በእርካታ እንዲሞላልኝ መጸለይና እርሱን መማጠን አለብን። ከዚያም እግዚአብሔር በቸርነቱ ስለ ሰጠን ትሩፋት ሁሉ ሆን ብለን ማሰላሰል ይገባናል። ይህን ስናደርግ ሰሰው ንብረት ምክንያት በሚቀሰቀስብን ፈተና ላይ የእግዚአብሔርን የአሸናፊነት ኃይል እንለማመዳለን። የቁጡነት ፈተና በሚደርስብን ጊዜ፥ እግዚአብሔር አባታችን አእምሮአችንን በሰላም እንዲሞላው ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ይጠበቅብናል። ከዚያም ቁጣችንን ሆን ብለን በመቃጣጠር፥ እግዚአብሔር መፍትሔ እንዲሰጠን ሁኔታውን ለእርሱ አሳልፈን መስጠት አለብን። ይህን በማድረጋችን ለቁጣ በሚገፋፋን ሁኔታ ላይ የእግዚአብሔርን ኃይል ድል አድራጊነት እንለማመዳለን። እንደዚሁም የፍትወተ ሥጋ ምኞት ሊመጣብን እግዚአብሔር አእምሮአችንን በንጹሕ አላቦች እንዲሞላው በጸሎት ልንጠነው ይገባናል። በመቀጠልም እነዚህ ንጹሕ አሳቦች አእምሮአችንን እንዲቆጣጠሩ ሆን ብለን ጊዜ ወስደን የምናሰላስልበት ጊዜ፥ ይህን በመሰለው ምኞት ላይ የእግዚአብሔርን ኃይል ድል አድራጊነት እንለማመዳለን። የክርስቶስ ትንሣኤ በአካባቢአችን ካሉ ከማያምኑ ሰዎች የተለየ ሕይወትን እንድንኖር ኃይልን ይሰጠናል። ይህም የሚሆነው በሚገባ ስንጠቀምበት ነው።
ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡14 እና 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡4 አንብቡ። የክርስቶስ ትንሣኤ ምንን ያረጋግጥልናል?
ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 5፡20-28 አንብቡ። በዚህ ክፍል ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ የክርስቶስን ትንሣኤ ከእኛ ጋር እንዴት አድርጎ ያገናኘዋል?
የክርስቶስ ትንሣኤ ለአማኛች ጠቃሚ የሆነበት ሁለተኛ ምክንያት ፥ ትንሣኤ ለእኛ ዋስትና ስለሆነ ነው። 1ኛ ቆሮ. 6፡14 እና 2ኛ ቆሮ. 4፡14 ሁለቱም ኢየሱስ ከሙታን ስለተነሣ፥ እኛም ከሙታን እንደምንነሣ ያረጋግጡልናል። በተለይ በክርስቶስ ትንሣኤና በእኛ ትንሣኤ መካከል ያለውን ግንኙነት ደህና አድርጎ የሚያስረዳው ክፍል 1ኛ ቆሮንቶስ 15 ከቁጥር 20 እስከ 28 ያለው ነው። ቀደም ሲል እንደተመለከትነው በዚህ ክፍል ክርስቶስ ለሞቱት «የመጀመሪያው ምሳሌ ሆነ» ይላል። የመጀመሪያው ፍሬ አዲስ ለሚገባው አዝመራ ዋስትናና ምሳሌ እንደሚሆን ሁሉ፥ የክርስቶስ ትንሣኤ፥ በእርሱ የሞቱት ሁሉ ልክ እንደ እርሱ እንደሚነ የሚያመለክት ዋስትና ነው። እንደዚሁም የክርስቶስ ትንሣኤ፥ በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ እነርሱም አንድ ቀን እንደ እርሱ የክብር አካል፥ ለብሰው ከሙታን እንደሚነሡ ዋስትና ይሆናቸዋል።
ጥያቄ፡- በክርስቶስ አማኝ ስለ ነበረና በሞት ስለ ተለያችሁ ወዳጃችሁ ወይም የቤተሰብ አባል መለስ ብላችሁ አስቡ። እዚህ ላይ በክርስቶስ የሚያምኑ የእውነተኞች አማኞች የትንሣኤ ዋስትና ምን ያህል ያጽናናችኋል?
ዛሬ ብዙ ሰዎች ተስፋ ስቆረጠ አቋም ሞትን ይጋፈጡታል። የሞተ ሰው ለዘላለም የት እንደሚኖርም እርግጠኞች አይደሉም። ከእነርሱ ጋር ተመልሰው እንደሚሆኑም አያውቁም። ይወዷቸው ስለነበሩት ዘመዶቻቸው የወደፊት ዕጣ ፍርሃትና ተስፋ ቢስነት ይሰማቸዋል። ከዚህ የተነሣም ላለ ራሳቸው የወደፊት ሁኔታ ይፈራሉ። ደግሞም ተስፋ ይቆርጣሉ። ነገር ግን በክርስቶስ የሚያምኑት በሚሞቱበት ጊዜ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ሊያድርብን አይገባም። አንድ ቀን እንደ ክርስቶስ፥ እነርሱም በከበረ አካል ከሙታን እንደሚነሡ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። እኛም በክርስቶስ የምናምን ከሆንን ከእርሱና ከእነርሱም ጋር አብረን እንደምንነሣ እርግጠኞች ነን። ስለዚህ መቃብርን መፍራት የለብንም። ስለሞቱት ወዳጆቻችን ተስፋ መቁረጥ አይገባንም። የክርስቶስ ትንሣኤ እንደሚያረጋግጥልን፥ እኛም አንድ ቀን እንነግለን።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
