በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሜትን ከሚስቡ ትምህርቶች አንዱ፥ የጌታ መልአክ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የመገለጡ ሁኔታ ነው። ይህን አስደናቂ ገጸ ባሕሪ በምናጠናበት ጊዜ፥ የጌታ መልአክ እግዚአብሔር ራሱ መሆኑ ግልጽ እየሆነልን ይመጣል። ስለዚህ ይህ በቅርጽና በአካል የሆነው የእግዚአብሔር መገለጥ፥ በእርግጥ ወልድ የእግዚአብሔር መገለጥ ነው። አንዳንድ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ይህን መገለጥ፥ ቅድመ-ተሰገዎ ክርስቶስ ብለው ይጠሩታል።
ዘፍጥረት 16
ጥያቄ፡- ዘፍጥ. 16፡1-13 እንብብ። ሀ) አጋር በምን ምክንያት ቤትዋን ትታ ከአብርሃምና ከሣራ ሸሸች? ለ) አጋር በምድረ በዳ በውኃ ምንጭ ዳር ሳለች ማን አገኛት? ሐ) አጋርን ምን አላት? መ) አጋር የታያትን እንዴት አድርጋ ገለጸችው?
በዘፍጥረት 16 ባለው የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የሚያሳዝን ታሪክ እናነባለን። ሣራ ለአብርሃም ልጅ ልትወልድለት ትመኝ ነበር፥ ነገር ግን ልትወልድለት አልቻለችም። በመሆኑም ለዚህ ችግር መፍትሔ ልታገኝለት ያቀደችው በጊዜው በኅብረተሰቡ ዘንድ የተለመደውን ባሕል በመከተል ነበር። ስለዚህ ለአብርሃም ልጃገረድ አገልጋይዋ የነበረችውን አጋርን ሰጠችው። አብርሃም አጋርን ወስዶ ተገናኛትና ፀነሰች። እርግጥ ነው ይህ ድርጊት እግዚአብሔር የፈቀደው አልነበረም። እግዚአብሔር የፈቀደው አንድ ወንድ ለአንድ ሌት ሆኖ፥ እነርሱም መላ ሕይወታቸውን በፍትወተ ሥጋ በመተማመን እንዲኖሩ ነው። ግራ እግዚአብሔር ለአብርሃም ልጅ እንደሚሰጠው የገባውን ቃል ኪዳን እስከሚፈጽምበት ጊዜ ድረስ በጊዜው የነበረውን የኅብረተሰብ ባሕል ችላ ብላ መቆየት የነበረባት ወቅት ነው። አጋር ከአረገዘች በኋላ፥ ሁኔታዎች እየተባባሱ መጡ። አጋር ልጅ የማርገዝ ዕድል በማግኘቷ ትታበይ ጀመር። ሣራ ልጅ ለማርገዝ ባለመቻልዋ፥ ሁኔታው አጋርን አኩራራትና ከሣራ የተሻለች አስመሰላት። ከዚህ የተነሣ ሣራ በጣም ተቆጥታ ቅናትም ስለ ያዛት፥ አጋርን ትጨቁናትና ታበሳጫት ጀመር። ከዚያም አጋር ወደ ምድረ በዳ ሸሽታ ሄደች።
የጌታ መልአክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ምድረ በዳ ተገለጠ። «ጌታ» የሚለው ቃል በዕብራይስጡ «ያህዌ» ወይም «ጂሆቫ» የተባለው ቃል ነው። ዕብራውያን ጥንት ሲጽፉ በአናባቢ ሆሄያት ስለማይጠቀሙ፥ ይህን የእግዚአብሔር መጠሪያ የሆነ ስም እንዴት ያነቡት እንደ ነበረ እርግጠኞች አይደለንም። ምናልባት እግዚአብሔር የሚለውን ቃል «ያህዌ» ብለው ያነቡት ይሆናል። እንግዲያውስ ይህ የተገለጸው «የያህዌ መልአክ» ተብሎ ይጠራል።
የያህዌ መልአክ ለአጋር በታያት ጊዜ፥ እንደ ዱር አህያ ምድረ በዳን የሚዞርና ዘወትር ከወገኖቹ ጋር የማይስማማ ሞገደኛ ልጅ እንደምትወልድ ትንቢት ነገራት። ከዚያም የያህዌ መልአክ በተለያየ ጊዜ፥ ያነጋገራትን «ኤልሮኢ» አለችው። ትርጉሙም፥ «የሚያየኝ አምላክ» ማለት ነው። ይህን ያለችው በእርግጥ ያነጋገራት እርሱ አምላክ ስለነበረ ነው። በእርግጥም በመከራዋ ጊዜ ታያት። የታያትም እርሷ ደህና አድርጋ ልታየው በምትችልበትና በሚያጽናናት ሁኔታ ነበር።
አጋር የጌታን መልአክ «የሚያየኝ አምላክ» ማለቷ በግልጽ የሚያስረዳን ያ የጌታ መልአክ ተራ መልአክ እንዳልነበረ ነው። በእርግጥም እርሱ በመልአክ መልክና ቅርጽ የተገለጠ እውነተኛው አምላክ ነበር። አገላለጡም ለሰዎች ሊናገር በሚችልበትና እነርሱም ሊያዩት በሚመቻቸው አኳኋን ነበር።
ጥያቄ፡- ዘፀ. 33፡19-20 አንብብ። እግዚአብሔር፥ ሰዎች ፊቱን ቢያዩ ምን ይሆናሉ አለ? 3ኛ ጥያቄ፡- ዮሐ 1፡18 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔርን ማን አየው? ለ) እግዚአብሔር በማን አማካይነት ተገለጠ?
በዘፀ. 33፡20 ውስጥ እግዚአብሔር ለሙሴ፥ ማንም ፊቱን አይቶ በሕይወት ለመኖር እንደማይችል ነግሮት ነበር። ሰው እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ስለማ?ት በሚናገርበት ጊዜ፥ ማንም ሰው አሁን ባለበት ሥጋዊ አካል ሆኖ እግዚአብሔርን በክብሩ፥ በግርማ ሞገሱ ከቶ ሊያየው እንደማይችል መግለጽ ማለት ነው። ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም በአራቱ የትምህርት ክፍሎቻችን እንደ ተገነዘብነው፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እግዚአብሔር ነበር፡ ዮሐ 1፡14 ላይ ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነውን ክብሩን አየን ይላል፡ ነገር ግን ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ክብር ቢገልየም ሙሉ በሙሉ ክብሩንና ሞገሱን አልገለጠውም። ፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2 እንደሚለው፥ «እርሱ የመለኮት ባሕሪ አለው፥ ይሁን እንጂ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሚያደርገውን የመለኮት ባሕርይ እንደ ያዘ መቅረት አልፈለገም። ይልቁንም ያለውን ክብር በዛ ፈቃዱ ትቶ፥ አገልጋይ መሆንን መረጠ፤ በሰው ምሳሌም ተገለጠ» (ፊልጵ. 2፡6-7) ይላል። (አዲሱ ትርጉም)
ዮሐ 1፡18ም እግዚአብሔርን ከቶ ያየው ማንም እንደሌለና አንድ ልጁ ግን እንደ ገለጠው ይናገራል። ዮሐንስ እግዚአብሔርን ማንም አላየውም ሲል፥ በትክክል ስለ እግዚአብሔር አብ መናገሩ ነው። ምክንያቱም በዮሐ
1፡1 ላይ ቀደም ሲል ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ሲል ነግሮናል። ዮሐንስ በምዕራፍ 1፡14 ላይ ቃል የነበረውን እግዚአብሔርን እንዳየነው ነግሮናል። ዮሐንስ እግዚአብሔር በመላ ክብሩ እንደማይታይና በእግዚአብሔር ወልድ አማካይነት ለሰዎች ሁሉ እንደሚገለጥ ይነግረናል። ስለዚህ እግዚአብሔርን ከነሙሉ ክብሩ ሊያየው የሚችል ከቶ ማንም የለም። ነገር ግን እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆኖ ተገለጠ። ሰዎች ሰው ሆኖ የተገለጠውን እግዚአብሔር ወልድን ማየታቸው የእግዚአብሔር አብን ክብርና ሞገስ በተወሰነ ደረጃ እንዲያዩ ያስችላቸዋል።
አጋር እግዚአብሔርን አየች። እግዚአብሔርን ያየችው በሰማያዊ ክብርና ሞገስ ሆኖ ሳይሆን፥ በአካል ተገልጦ ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔርን ያየችው በተወሰነ ክብሩ ሆኖ ነው። በኋላ ሰው ሆኖና ሰብአዊ አካል ለብሶ ወደ ዓለም በመምጣት እግዚአብሔር አብን የገለጠው እግዚአብሔር ወልድ ስለሆነ፥ ለአጋር የተገለጠላትና እርሷም ያየችው እግዚአብሔር ወልድን እንደ ነበር መደምደም እንችላለን። አጋር እግዚአብሔር ወልድን በመልእኮ መልክ በአካል ሆኖ አይታዋለች።
መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ወይም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በአካል ስለ መገለጣቸው በፍጹም ስለማይናገር፥ በሌላ በኩል ግን እግዚአብሔር ወልድ እግዚአብሔር አብን ለመግለጥ በአካል መምጣቱን በግልጽ ስለሚያስረዳ፥ ያ የታየው የጌታ መልአክ ከተሠገዎ በፊት የታየ እግዚአብሔር ወልድ ነው። የያህዌ መልአክ እግዚአብሔር ወልድ ለመሆኑ ሌላው ማረጋገጫ ደግሞ እግዚአብሔር ወልድ ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ምድር ከመጣ በኋላ ይህ የያህዌ መልአክ ዳግም መገለጡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለመጻፉ ነው። የጌታ መልአክ የሚለው ሐረግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚታየው በዘፍጥረት 16 ነው። ነገር ግን በብሉይ ኪዳን ውስጥ የጌታ መልአክ መገለው በተለያዩ ስፍራዎች ተጽፎ ከመገኘቱም በላይ ክፍሎቹ ይህ የጌታ መልአክ እግዚአብሔር መሆኑን በግልጽ ያስረዳሉ።
ዘፍጥረት 22
ጥያቄ፡– ዘፍጥ. 22፡1-10 አንብብ። አብርሃምና ይስሐቅ በምን ምክንያት ወደ ተራራው መጡ?
ጥያቄ፡– ዘፍጥ. 22፡11-18 አንብብ። ሀ) ለአብርሃም ማን ተገለጠለት? ለ) ለአብርሃም ምን አለው? ሐ) አብርሃም ተራራውን ምን ብሉ ጠራው? መ) ለሁለተኛ ጊዜ ለአብርሃም በተገለጠለት ጊዜ በማን ማለለት? ሠ) ምን ተስፋ ሰጠው? ረ) ይህ ሁኔታ ለአብርሃም የተናገረው ማን መሆኑን ምን ይገልጽላችኋል?
ዘፍጥረት 22 አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ስለማቅረቡ የሚያወሳ የታወቀ ታሪክ ነው። እግዚአብሔር አብርሃም ልጁን ይዞ እርሱ ወደሚያሳየው ስፍራ ሄዶ መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርበው አዘዘው። አብርሃምም ታዘዘ። ለሦስት ቀናት እንደ ተጓዙ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተራራውን አሳየው። ተራራውንም ወጡ፥ አብርሃምም መሠዊያ
ሠርቶ ይስሐቅን በማሠር ለመሥዋዕት አዘጋጀው።
ልክ በዚያኑ ጊዜ፥ የያህዌ መልአክ ለአብርሃም ተገልጦለት ልጁን እንዳይሠዋው ነገረው። እግዚአብሔር አብርሃም ልጁን እንዲሠዋው ያዘዘው ሊፈትነው ነበር። አሁን አብርሃም እግዚአብሔርን እንደሚፈራና በእርሱ በፍጹም እንደሚታመን እግዚአብሔር አረጋገጠ። አብርሃም፥ እግዚአብሔርን ከስጦታ ሁሉ በላይ አደረገው፥ ከልጁም በላይ አስበለጠው። እግዚአብሔር ለተስፋው ማስፈጸሚያ የሰጠውን ቢወስድበት እንኳ የገባውን ተስፋ እንደሚፈጽምለት ያምን ነበር። ከዚያም አብርሃም ቀና ሲል በሐረግ የተተበተበ አውራ በግ አየ። ይህም መሥዋዕት የሚሆን እግዚአብሔር ራሱ ያዘጋጀው በግ ነበር። አብርሃም ያንን ቦታ፥ «እግዚአብሔር ያዘጋጃ ል» ብሎ ሰየመው። እንግዲህ ይህ የተገለጠው የያህዌ መልአክ እግዚአብሔር ራሱ ለመሆኑ ይህ የመጀመሪያው ፍንጭ ሊሆነን ይችላል። በጉንም ያዘጋጀው የያህዌ መልአክ ነበር። አብርሃምም፥ ያህዌ ራሱ በጉን አዘጋጀ በማለት ተናግሯል። አብርሃም የያህዌን መልአክ፥ ልክ እንደ ያህዌ እንደ ራሱ አድርጎ ነው የተቀበለው።
እንዲያውም በዚህ ክፍል ውስጥ ያ የተገለጠው የያህዌ መልአክ፥ ያህዌ ራሱ መሆኑን በይበልጥ የሚመሰክር ክፍል አለ። በቁጥር 15 ላይ የያህዌ መልአክ ዳግሞ አብርሃምን ያነጋግረዋል። በዚህን ወቅት መልአኩ በራሱ ይምልና ከዚያም ራሱን ያህዌ ጌታ ብሎ ይጠራል። መልአኩ ራሱ ያህዌ መሆኑን ከገለጠ በኋላ፥ ቀጥሎ ቀደም ሲል ያህዌ ለአብርሃም ሰጥቶ የነበረውን ተስፋ እንደገና ያረጋግጥለታል። በተራራው ላይ ለአብርሃም የታየው የያህዌ መልአክ፥ ያህዌ ራሱ ነበር። ይህም ራሱ እግዚአብሔር ወልድ በብሉይ ኪዳን ውስጥ መገለጡን ግልጽ ያደርገዋል።
መሳፍንት 13
ጥያቄ፡- መሳ. 13፡1-25 አንብብ። ሀ) ለማኑሄ ሚስት የተገለጠላት ማን ነበር? ለ) ምንስ ነገራት? ሐ) በቁጥር 6 ላይ ምን ብላ ገለጻችው? መ) በቁጥር 8 ላይ ማኑሄ ምን ብሎ ጸለየ? ሠ) ከቁጥር 10-11 እንደተጻፈው፥ ለማኑሄ የተገለጠለት ማን መሆኑን ይህ ክፍል እንዴት ያብራራዋል? ረ) የተገለጠው ማን እንደ ነበረ ቁጥር 3 እና 16 እንዴት አድርጎ ያስረዳል? ሰ) በቁጥር 18 ላይ ስሙን ማን ብሎ ጠራ? ሸ) ማኑሄና ሚስቱ የተገለጠላቸው ማን እንደ ነበረ በኋላ ያወቁት መች ነበር? ቀን በቁጥር 22 ላይ እንደ ተጻፈው ማንን አየን እሉ?
መሳፍንት ምዕራፍ 18 ስለ ሳምሶን መወለድ የሚተነብይ ጠቃሚ ክፍል ነው። የያህዌ መልአክ በመጀመሪያ ማኑሄ ለተባለ ሰው ሚስት ተገለጠላትና ልጅ እንደምትወልድ አበሠራት። ይህ ልጅ እንደ ማንኛውም ተራ ልጅ አይሆንም ነበር። ይህ ልጅ ለእግዚአብሔር የተሰጠና፥ የእስራኤልን ሕዝብ ከጠላቶቻቸው ከፍልስጥኤማውያን እጅ የሚያድናቸው ነበር። ለእግዚአብሔር የተሰጠ በመሆኑም የአልኮል መጠጥ አይጠጣም፥ ፀጉሩን አይቆረጥም፥ በድንም አይነካም።
የማኑሄ ሚስት ወደ ባለቤቷ ዘንድ ሄዳ ባገኘችው ጊዜ፥ «የእግዚአብሔርን መልአክ የመሰለ የእግዚአብሔር ሰው» እንዳየች ነገረችው። ይህ ክፍል የያህዌ መልእኮ አንዳንድ ጊዜ በምን አኳኋን ለሰዎች እንደሚታይ ስለሚናገር ጠቃሚ ጥቅስ ነው። በአንዳንድ አኳኋን ይህ መልአክ ሰው ይመስላል። ነገር ግን አካሉ ደግሞ በአንዳንድ ሁኔታው ከምናየው ሰው አካል ይለያል። በዚህ ምክንያት ነው የያህዌ መልአክ እንዳንድ ጊዜ ሰውን ይመስላል በሌላ ጊዜ ደግሞ በመልአክ ይመሰላል የሚባለው።
ማኑሄ፥ ሚስቱ ያየችውን እርሱም አይቶ ለማረጋገጥ ስለ ፈለገ፥ ሚስቱን የጎበኘውን ሰው እርሱም እንዲያየው – እንደገና ይልክለት ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው። እግዚአብሔርም የማኑሄን ጸሎት ሰማና የያህዌ መልአክ ዳግም ለማኑሄ ሚስት ተገለጠላት። በቁጥር 30 እና 11 ላይ የያህዌ መልአክ በሰው መልክ መገለጡ ተነግሮአል። በዚህን ጊዜ የያህዌ መልአክ ጻግሞ ሊገለጥ ክብርና ሞገስ የተላበሰ ቢሆንም፥ ይህ ክብርና ሞገሱ ተሸፍኖ እንደ ማንኛውም ሰው ሆኖ ተገለጠ። አሁንም ቢሆን፥ ማኑሄና ሚስቱ ይህ የተገለጠላቸው የያህዌ መልአክ መሆኑን አላወቁም።
በዚህን ጊዜ ማኑሄ የጌታን መልአክ ስሙ ማን እንደሆነ ሲጠይቀው፥ «ስሜ ድንቅ የሆነ ምሥጢራዊ ነው» (ቁጥር 18) ሲል መለሰለት። የያህዌ መልእክ፥ ያህዌ ራሱ ለመሆኑ ይህ ሌላው ፍንጭ ነው። በመጨረሻም፥ ማኑሄና ሚስቱ መሥዋዕት አምጥተው በመልአኩ ፊት ለእግዚአብሔር ባቀረቡ ጊዜ መልአኩ በነበልባሉ ውስጥ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ። ከዚህ በኋላ ማኑሄና ሚስቱ አብሮአቸው የነበረው የያህዌ መልአክ እንደነበረ አስተዋሉ። መልአኩ፥ የያህዌ መልአክ መሆኑን እንደ ተረዱ፥ ደግሞም እግዚአብሔርን እንዳዩት ተገነዘቡ (ቁጥር 22)። በዚህም የያህዌ መልአክ መገለጥ የእግዚአብሔር መገለጥ መሆኑን ተረዱ።
በዘፍጥረት 16፥ በዘፍጥረት 22 እና በመሳፍንት 13 ላይ እንደምናነበው፥ የጌታ መልአክ፥ ማለትም የያህዌ መልአክ፥ ተራ መልአክ አልነበረም። ይልቅስ የያህዌ መልአክ፥ ያህዌ ራሱ ነው። የያህዌ መልአክ ሰዎች ክብርና ግርማውን ዐይተው እንዳይሞቱ፥ በዐይናቸው ሊያዩት በሚችሉበት አኳኋን ክብሩን ሙሉ በሙሉ ሳያሳይ ይገለጥ ነበር። ይህም ሁኔታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከመምጣቱ በፊት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ብቻ የተፈጸመ ነው። በመሆኑም የያህዌ መልአክ ከተሠገዎ ምሥጢር ስፊት እግዚአብሔር አብን የገለጠው እግዚአብሔር ወልድ መሆኑ ግልጽ ይመስላል።
ብሉይ ኪዳንን በምታነቡበት ጊዜ፥ ስለ ጌታ መልአክ በብዙ ክፍሎች ተጽፎ ታገኛላችሁ። የነገው ትምህርታችን እነዚህን ክፍሎች በዝርዝር ይመለከታቸዋል። በብሉይ ኪዳን ውስጥ «የጌታ መልአክ» የሚለውን ሐረግ በምትመለከቱበት ጊዜ፥ በዕብራይስጡ የያህዌ መልአክ መባሉን ልብ በሉ፡ ይህም የሚያሳየው እግዚአብሔር በሰው አካል ወይም በመልአክ አካል ተመስሎ እንደሚገለጥ ነው። የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች ስለ ሚካኤል ወይም ስለ ገብርኤል ሲጽፉ እነዚህን መላእክት፥ «የጌታ መላእክት» ብለው አልጠሯቸውም። ብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ራሱን ለመጥራት፥ «የጌታ መልአክ» በሚለው ሐረግ ይጠቀማል። በአንጻሩ የብሉይ ኪዳን ክፍሎች ከዚህ የተለዩትን መላእክት «ኪሩብ»፥ ወይም «ሱራፌል» ብለዉ ይጠሯቸዋል። ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የጌታ መልአክ ሲባል፥ ያህግ ራሱ ማለት ነው።
ጥያቄ፡– መለስ ብለህ ስለ ዘፍጥረት 16፥ ዘፍጥረት 22ና መሳፍንት 13 አስብ የጌታ መልአክ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ለሰዎች ሲገለጥ ተልዕኮው ምን ነበር?
በእነዚህ ሦስት ክፍሎች ውስጥ የያህዌ መልአክ ሰዎችን በችግራቸወ ጊዜ ፈጥኖ ደርሶ የሚያድናቸው መልአክ ነበር። በዘፍጥረት 16 ላይ አጋር ተጨንቃ በነበረችበትና ስለ ጭንቅና ችግርዋ ማንም ባልተረዳላት ጊዜ የያህዌ መልአክ ጭንቀቷን አይቶ ደርሶ አጽናናት። ምንም እንኳን ከራሷ ከአብርሃምና ከግራ ኃጢአት የተነሣ ብትሠቃይም፥ የያህዌ መልአክ አጽናንቷታል። ከዘፍጥረት 22 እንደምንረዳው፥ አብርሃም እንድ ልጇ መሥዋዕት ሊያደርገው እንደ ተዘጋጀ፥ የያህዌ መልአክ ምትክ መሥዋዕት ሰጠው። በመሳፍንት 13 ላይ እንደተጻፈው ደግሞ፥ የያህዌ መልአ በፍልስጥኤማውያን ሥር ተጨቁኖ የነበረውን የእስራኤልን ሕዝብ ነ እንዲያወጣ ጀግና አስነሣላቸው። ኢየሱስ ለሚያምኑት ሁሉ ደኅንነትን ሊሰጥ በአዲስ ኪዳን ውስጥ እንደ ተገለጠ ሁሉ፥ በተመሳሳይ መንገድ የያህግ መልአክም በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተገልጦ ሰዎች እርሱን እጅግ በፈለጉት ጊt ደርሶ ደኅንነትን ሰጥቷቸዋል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕዝቡን ዋነኛ ችግር ለማስወገድ የሚገለጥ አምላክ ነው። እናንተም አሁን ምንም ዓይነት ችግ ይኑራችሁ፥ እርሱ ሊፈታላችሁ ይችላል።
ጥያቄ፡- ሀ) እጋር እንደተሠቃየችው በራለህ ወይም በሌሎች ኃጢአት እየተሠቃየህ ነውን? ለ) አብርሃም ለይስሐቅ ምትክ ለማግኘት እግዚእብሔር በጽ እንዳስፈለገው፥ በአሁኑ ሰዓት ለሕይወታችሁ ብርቱ የሆነ ፍላጎት ምንድን ነው? ሐ እስራኤል በሳምሶን ዘመን በፍልስጥኤማውያን እንደ ተጨቆነች፥ በእግዚአብሔ ጠላቶች የተጨቆናችሁት እንዴት ነው? መ) እነዚያን ፍላጎቶቻችሁን ሊፈጽምላችu ኢየሱስ ምን ያህል ችሎታ አለው? ኢየሱስ ፍላጎቶቻችሁን እንደሚፈጽምላችሁ እምነታችሁን በጻሉት ለመግለጽ ጥቂት ጊዜ ውሰዱ።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
