Site icon

የኢየሱስ ዕርገት (ከፍ ከፍ ማለት) 

ኢየሱስ ከተነሣ በኋላ፥ ለደቀ መዛሙርቱ በትንሣኤ አካሉ እየተለጠላቸው በምድር ላይ ለአርባ ቀናት አገለገላቸው። ከአርባው ቀናት ፍጻሜ በኋላ (የሐዋ. ሥራ 1፡3)፥ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ዐርጎ በአብ ቀኝ ተቀመጠ። ኢየሱስ በምን ምክንያት ወደ አብ ዐረገ? በምድር ላይ ለምን አልቆየም? ኢየሱስ ባረገ ጊዜ ወዴት ሄደ? የኢየሱስ ዕርገት በማንኛው ሁኔታ እኛን ይመለከታል? ዛሬ ኢየሱስ በምድር ላይ ከነበረው ሕይወቴ ከትንሣኤው በኋላ ወደ ሰማይ ሰላ መመለሱ እናጠናለን። 

1. ኢየሱስ በዐረገ ጊዜ ምን ሆነ? 

ጥያቄ፡- ሉቃስ 24፡50-53 እና የሐዋ. ሥራ 13፥ 6-11 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ ከስንት ጊዜ በኋላ ነበር ዕርገቱ? ለ) ኢየሱስ ባረገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ያዩትን ለጹ። ኢየሱስ በየትኛው አቅጣሳ ሄደ? በመጨረሻ ደቀ መዛሙርቱ ስለ ኢየሱስ ያዩት ምን ነበር? ሐህ ኢየሱስ ወዲያውኑ ካረገ በኋላ ስጀቀ መዛሙርቱ ላይ ምን ደረሰ? 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 16፡10፥ 28 አንብቡ። ኢየሱስ በዐረገ ጊዜ ወዴት ሄደ? 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 20፡17 አንብቡ። ኢየሱስ ወዲያውኑ ከሞት እንደ ተነሣ ማርያም ልትነካው ስትል በምን ምክንያት አትንኪኝ አላት? 

የኢየሱስን ዕርገት የከበቡ፥ ብዙ እኛ ልንገነዘባቸው የማንችል ምሥጢራት እሉ። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ዕርገት በጣም ልጽ የሚያደርጋቸውም ነገሮች አሉ። በመጀመሪያ፥ ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶ ለአርባ ቀናት በቆየ ጊዜ ከዚህ ቁሳዊ ዓለም ጋር የነበረው ግንኙነት በጣም ተለውጦ ነበር። እስከዚያ ጊዜ ድረስ በትንሣኤ አካሉ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ መኖሩንና ማገልገሉን ቀጥሎ ነበር። ነገር ግን ከትንሣኤው በኋላ አርባው ቀን እንደ ተፈጸመ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ከዚያም ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ጫፍ ይዛቸው ሄደ። እዚያም የመጨረሻውን ተልዕኮ ሰጣቸው። ተመልሶ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስለሚመሠርትበት ጊዜ ለማወቅ በማለት እንዳይጨነቁና በዚህ ፈንታ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለመላው ዓለም ስለ እርሱ መመስከር እንደሚገባቸው አሳሰባቸው። ይህን ኃላፊነት ከሰጣቸው በኋላ ኢየሱስ ከምድር ወደ አየር ከፍ ከፍ ይል ጀመር። ደቀ መዛሙርቱም እየተነጠቀ አካሉ ወደ ደመናው እስኪገባ ድረስ ይመለከቱት ነበር። ከዚያ ስኋላ በአካል በምድር ላይ አላዩትም። ወዲያው ሁለት መላእክት መጥተው እዚያ ቆመው ወደ ፀረገው ኢየሱላ መመልከት ብቻ እንደሌለባቸው ነገሩዋቸው። አዎን፥ መላእክቱም አንድ ቀን ኢየሱስ በአካል እንደሚመለስ አረጋገጡላቸው። ይህ በአካል ያውቁት የነበረው ኢየሱስ የተለያቸው ለጊዜው መሆኑንም በመግለጽ አበረታቱአቸው። መላእክቱ ይህንን ሲነግሯቸው በሌላ አባባል ሊሉት የፈለጉት በእርሱና በእነርሱ መካከል አዲስ ግንኙነትና የአገልግሎት ዘመን መጀመሩንና አዲሶቹ የሥራ ኃላፊነቶቻቸውን ከግብ ለማድረስ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ነበር። 

ኢየሱስ በዐረገ ጊዜ ወዴት ሄደ? በዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ 16፡10፥28 እና በሌሎችም ክፍሎች እንደተበሠረው፥ በዐረገ ጊዜ ወደ አባቱ እግዚአብሔር አብ ዘንድ ተመልሷል። ከዘመናዊው ሥነ ከዋክብት እንደምንረዳው ምድር በሞኽዋርዋ ላይ እየተሽከረከረች በፀሐይ ዙሪያ ትዞራለች። እንዲሁም በምድር ዙሪያ በሁሉም አቅጣጫ ሕብረ ክዋክብቶች ወይም የከዋክብት ክምችት ይገኛሉ። እንደሚገባን፥ ኢየሱስ ወደ ላይ መሄዱን አልቀጠለም፤ ምክንያቱም ወደ ላይ መሄድ የሚያደርሰው በአካላዊ ቱኒቨርስ ውስጥ ወደሚገኝ ሌላኛው ኅብረ ክዋክብት ወይም ጋላክሲ ብቻ ነው። በዚህ ፈንታ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ዐይን ከተሠወረ በኋላ በምድርም ይሁን በላይ በከዋክብት ከምናየው ዓለም ለእኛ ወደማይታየን መንፈሳዊ ዓለም ሄዷል። እግዚአብሔር የሚገኝበት ሰማይ፥ የተለየ ስፍራ ነው። ነገር ቀን ይህን ስፍራ በሥነ ፈለክ ቻርት ላይ በክዋክብት መካከል የምናገኘው ስፍራ አይደለም። ይህ ስፍራ በምድራዊ አመለካከትና አካላዊ እሳቤ እዚህ ቦታ ነው ለማለት የማይቻለን፥ መንፈሳዊ እውነታ ነው። ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ዐይን ከተሰወረ በኋላ፥ ወደ ሰማይ ወደዚያ መንፈሳዊ እውነታ ሄዷል። 

አንዳንድ ጊዜ ዮሐንስ 20፡17 የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችን ያደናግራቸዋል። ለመሆኑ ይህ ክፍል ኢየሱስ ከዕርገቱ በፊት ሰማይና ምድር እያፈራረቀ ይመላለስ ነበር የሚል ትርጉም ይሰጣል? ለምንድን ነው ኢየሱስ ገና ወደ አባቱ ያላረገ በመሆኑ ማርያምን አትንኪኝ ያላት? ደግሞስ አካሉ ምትሐታዊ ስለሆነ ማርያም ልትነካው አልቻለችም ማለት ነው? በፍጹም ከዕርገቱ በፊት በኢየሱስ የትንሣኤ አካል ላይ ምንም ዓይነት ምትሐታዊ ባሕርይ አልነበረም። እንዲያውም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው እንዲዳስሱት ከትንሣኤው በኋላ ሲያበረታታቸው ነበር (ሉቃስ 24፡9፤ ዮሐንስ 20፡27)። ኢየሱስ በሞተ ጊዜ ነፍሱ ከአብ ጋር አልነበረችም ማለቱ ነበር? አይደለም በሞተና በተቀበረ ጊዜ ነፍሱ ወዲያውኑ ወደ እግዚአብሔር ዘንድ መሄድዋን ተገንዝበናል (ሉቃስ 23፡43፥46)። ስለዚህ ኢየሱስ ወዲያውኑ ከትንሣኤው በኋላ በነበሩት ሰዓታትና ቀናት ሰማይና ምድር እያፈራረቀ ሲመላለስ ነበር ማለት የሚመስል አይደለም። ኢየሱስ ለማርያም የተናገራት ቃል እንዲህ ተብሎ ሊተረጐም ይችላል፦ «እኔን አጥብቆ መያዝ አስፈላጊ አይደለም። አሁን ወደ አባቴ በማረግ ላይ አይደለሁም።» ኢየሱስ በወቅቱ ለማርያም ሊነግራት የፈለገው ለተወሰነ ጊዜ በምድር ላይ እንደሚቆይና ከእርሱ ጋር ልትሆን የምትችልበት ሌላ ዕድል እንዳላት ሊሆን ይችላል። ይህ ቀንዛቤ ከዐውደ አሳቡ ጋር ይስማማል፥ ምክንያቱም ኢየሱስ ቀጥሉ ለማርያም ያላት፥ «ይልቅስ፥ ወደ አባቴ ልመለስ ስለሆነ፥ በቶሎ ርጠሽ ለወንድሞቼ ንገሪቱ የሚል ነው። ኢየሱስ እንዲህ በማለት ሊነግራት የፈለገው ጊዘው እርሷ አሁን ከእርሱ ጋር የምትቆይበት ሳይሆን በደስታ እየፈነደቀች በሩጫ ሄዳ እርሱ ሕያው መሆኑን ለሌሎች የምትነግርበት መሆኑን ነበር። ከዚህ በኋላ ማርያም ከኢየሱስ ለመለየት ችግር አልነበረባትም። ምክንያቱም ወደ አባቱ መመለስ ቢኖርበትም ወዲያውኑ እንደማይመለስ አውቃለች። 

ዕርገቱ ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ ከአርባ ቀን በኋላ ነበር። ይህም በቁሳዊው ቃድር ከመኖር በመንፈሳዊው ዓለም ማለት አባቱ ባለበት ለመኖር ያደረገው ሽግር ነው። 

2. ኢየሱስ በዐረገበት ጊዜ ምን አደረገ? 

ጥያቄ፡- የሐዋ. 531 ኤፌሶን 1፡19-2፤ ዕብራውያን 1፡3 1ኛ ጴጥሮስ 3፡22 አንብቡ። ኢየሱስ በዐረገበት ጊዜ ምን አደረገ? 18ኛ ጥያቄ፡- ሀ) ዕብራውያን 10፡12 እንብቡ። ኢየሱስ በአባቱ ቀኝ መቀመጡ ምንን ያመለክታል? ላ) ፊልጵስዩስ 2፡9 አንብቡ። እግዚአብሔር ኢየሱስን ከፍ ከፍ ባደረገው ጊዜ ምን ሰጠው? 

ኢየሱስ ከዐረገ በኋላ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ መቀመጡን ብዙ የአዲስ ኪዳን ክፍሎች በግልጽ ያስረዳሉ (የሐዋ. 5፡31፤ ኤፌሶን 1፡19-21፤ ዕብራውያን 1፡3 1ኛ ጴጥሮስ 3፡22)፡፡ ኢየሱስ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ተቀመጠ ሲባል ብዙ ነገር ማለት ሊሆን ይችላል። መጀመሪያ፥ እንዲህ ማለት በምድር ላይ የነበረው ሥራው ተፈጸመ ማለት ነው። ዕብራውያን 10፡12፥ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ ማለት አንዱ ታላቁ ሊቀ ካህን፥ «ለዘላለም የሆነውን አንዱን መሥዋዕት ለኃጢአት አቀረበ» ማለት ነው ይላል። በመሆኑም ከዚህ ሌላ ለኃጢአት መሥዋዕት አላስፈለገም። ኢየሱስ እኛን ከኃጢአት የማዳኑ ተግባር ተፈጽሞአል። ሁለተኛ፥ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ ማለት፥ በዓለም ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖ ወደ መለኮታዊ ሥልጣኑ ተመለሰ ማለት ነው። እንዲሁም ኤፌሶን 1፡19-2# እግዚአብሔር ኢየሱስን ያስቀመጠውም «ከማንኛውም ግዛትና ሥልጣን ከኃይልና ጌትነት በላይ እንዲሁም ከስም ሁሉ በላይ የሆነውን ክቡር ስም በመስጠት ነው» ይላል። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡22 ደግሞ፤ እርሱ አሁን በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ሳለ፥ «መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም ተገዝተውለታል» በማለት ይናገራል። ፊልጵስዩስ 2፡9 እንዲህ ይላል፡ «እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሁሉ በላይ ከፍ ባደረገው ጊዜ ከስምም ሁሉ የሚበልጠውን ስም ሰጠው።» ኢየሱስ ወደ አባቱ ባረገ ጊዜ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ፥ ይኸውም የሥቃይና ራስን ዝቅ የማድረጉ ምድራዊ ተልዕኮው ስላበቃ፥ በፍጥረታት ሁሉ ላይ ሥልጣን ወደ ተሰጠው፥ ወደ ክብር ስፍራም መመለሱን የሚገልጽ ነው። 

ጥያቄ፡- ኢየሱስ ለኃጢአት የመሠቃየቱ ተግባር ማብቃቱንና ከዚያም ወደ ክብርና ሥልጣን ስፍራው መመለሱን ማወቃችሁ ምንኛ ሊያጽናናችሁ ቻለ? 

ኢየሱስ ስለ ኃጢአት የተቀበለው የሥቃይ ተግባርት ተፈጽሞ ወደ ክብርና ሥልጣን ስፍራው መመለሱ ለሕዝቡ ታላቅ መጽናናት ነው። አንዳንድ ሰዎች አከታትለው ለሚሠሩት ኃጢአት በዚያው ልክ አሁንም የኢየሱስ ሥቃይና መሥዋዕት የሚያስፈልግ ይመስላቸዋል። ስለዚህ ኢየሱስ በየጊዜው ለኃጢአታቸው መሠቃየትና መሥዋዕት መሆን ያለበት ወይም ለሚሠሩት ኃጢአት ዋጋውን ራሳቸው መክፈል ያለባቸው አድርገው ያምናሉ። ነገር ግን ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ በተቀመጠ ጊዜ ይህ የሥቃዩ ጊዜ ለማክተሙ ምልክት ነው። ኢየሱስ የኃጢአታችንን ዕዳ ለመክፈል ብሎ ደግሞ አይሠቃይም። እኛም ብንሆን የኃጢአታችንን ዕዳ ለመክፈል ብለን መሠቃየት አይኖርብንም። በተጨማሪ የኢየሱስ ወደ ኃይልና ክብር ስፍራው መመለሱ ለእኛ ትልቅ መጽናናት ነው። ይህ ይዞታው እርሱ በክፉ መናፍስት ሁሉና በምድራዊ መንግሥታትና ኃይላት ላይ ሥልጣን እንዳለው ያረጋግጥልናል። ከዚህ የተነሣ እኛ ልጆቹ የሆንን ሁሉ ማንኛውም ምድራዊ ወይም መንፈሳዊ ኃይል በእኛ ላይ ቁጥጥር ይኖረዋል ብለን ከቶ ልንፈራ አይገባም። ኢየሱስ ሥልጣን ሁሉ አለው። 

3. የኢየሱስ ዕርገትና በአባቱ ቀኝ መቀመጡ ለእኛ ጥቅሙና ክብሩ ምንድን ነው? 

የኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር መመለስና በቀኙ መቀመጥ፥ በምድር ላይ ላሉት ሕዝቦቹ ብዙ ተጨባጭ ጥቅሞችና ቁም ነገሮች አሉት፡ 

ጥያቄ፡– ኤፌሶን 4፡7-10 አንብቡ። ኢየሱስ በዐረገ ጊዜ ምን አደረገ? 

ኤፌሶን 4፡7-10 ላይ ጳውሎስ እንደሚናገረው፥ የኢየሱስ ወደ ሰማይ ማረግ፥ ልክ አንድ ጄኔራል በጦር ሜዳ ድል አድርጎ ወደ ቤቱ እንደሚመለስ የሚቆጠር ነው። ልክ ድል አድራጊው ጄኔራል ፣ በጦር ሜዳ የያዛቸውን ምርኮኞችን እየመራ፥ ለሠራዊቱ ስጦታዎችን እንደሚሰጥ፣ ኢየሱስም በሰማይና በክፉ አጋንንቶች ላይ ድልን ተቀዳጅቶ ከዚያም ለተከታዮቹ ስጦታዎችን አደላቸው። ጳውሎስ ኢየሱስ ለሁላችን ስለሚሰጠን የጸጋ ስጦታዎች ሲናገር፥ ሐዋርያትን፥ ነቢያትን፥ ወንጌላውያንን አስተማሪዎችንና ቤተ ክርስቲያንን እንዲገነቡ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን መጋቢዎች ያጠቃልላል (ኤፌሶን 4፡7፡1) ይላል። ኢየሱስ በመላው ፍጥረታት ላይ ወዳለው ሙሉ ሥልጣኑ በመመለሱ ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች ቤተ ክርስቲያኑን በምድር ላይ እንዲያቋቁሙ እነርሱን መድቧል። | 21ኛ ጥያቄ፡- በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ የሽማግሌነት፥ የወንጌላዊነት ወይም የመጋቢነት ስፍራ ቢኖራችሁ፣ ኢየሱስ ይህን ትልቅ ኃላፊነት የሰጣችሁ መሆኑን ተገንዝባችሁ እንዴት አድርጋችሁ በተግባር ላይ ታውሉታላችሁ? በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ የኃላፊነት ስፍራ ባይኖራችሁ፣ በኃላፊነት ስፍራ ላይ ያሉትን እንዴት ትቀበሉዋቸዋላችሁ? 

ኢየሱስ ለቤተ ክርስቲያኑ ተሰጥኦ ያላቸውን ሰዎች ሰጥቷል። የሰጣቸውም ለዓላማ እንጂ በሌሎች ላይ ሥልጣናቸውን እያሳዩ እንዲገዛቸው አይደለም። ነገር ግን ችሎታቸውንና ያላቸውንም ዕድል ጭምር ለቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ እንዲያውሉት ነው። በኃላፊነት ሥራ ላይ ያሉ ወንጌላውያን፥ ሽማግሌዎች፥ መጋቢያን፥ አስተማሪዎችና ሌሎችም ጭምር ኢየሱስ ከእነርሱ በላይ ሥልጣን ያለው በመሆኑ፥ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲገነቡ የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዴት እንደ ተጠቀሙበት ተጠይቀው የሚመልሱ መሆናቸውን ጨርሰው ሊዘነጉት አይገባም። የቤተ ክርስቲያን አባላትም ቢሆኑ፥ እግዚአብሔር የሰጣቸው መሪዎች ከእርሱ የተሰጡ መሆናቸውን ተገንዝበው፥ የኢየሱስን ቤተ ክርስቲያን በመገንባት ረገድ መሪዎቻቸውን እንዲረዱ ይጠበቅባቸዋል። 

ጥያቄ፡- ሀ) ዮሐንስ 16፡7 አንብቡ። ኢየሱስ እኔ ካልሄድኩ በስተቀር እርሱ አይመጣላችሁም ያለው ማንን ነበር? ለ) የሐዋ. 2፡33 አንብቡ። ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ካለ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ምን አደረገላቸው? 

ኢየሱስ በመጨረሻ ው ለደቀ መዛሙርቱ በሰጣቸው የማጽናኛ መልእክት (ዮሐንስ 14፡16)፥ ደጋግሞ አጽናኙ ማለትም መንፈስ ቅዱስ እንደሚመጣላቸው ተስፋ ሰጥቶአቸው ነበር (ዮሐንስ 14፡16፤ 15፡26)። ነገር ግን በዮሐንስ 16፡7 ውስጥ እርሱ ካልሄደ በስተቀር መንፈስ ቅዱስ እንደማይመጣላቸው የሚያስገነዝብ አስደናቂ የሆነ ነገር ይነግራቸዋል። ሰውም አምላክም የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ትቶአቸው ካልሄደ በስተቀር፥ እርሱ የሚገለጥበት መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዳቸው ሕይወት ውስጥ ሊገኝ አይችልም። ነገሩ እንዲህ የሚሆንበት ምክንያት አይገባንም። እግዚአብሔር ግን በምድር ላይ ሰው በሆነው በልጁ ወይም በመንፈስ ቅዱስ ከሁለቱ በአንዱ አማካይነት ብቻ መኖሩን መግለጥ መርጧል። በጰንጠቆስጤ ቀን፥ የመንፈስ ቅዱስ መውረድ የዚህ የተስፋ ፍጻሜ መሆኑን ጴጥሮስ ተናግሯል። ኢየሱስ በመለኮታዊ ሥልጣኑ እንደገና ወደ አባቱ ቀኝ ከፍ ከፍ ስላለ በሁሉም ላይ አድሮ ኃይልን እንዲሰጣቸው መንፈስ ቅዱስን ላከ። መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ አድሮ የአገልግሎት ችሎታና ሥልጣን የመስጠቱ ውጤት የተገኘው በእግዚአብሔር ቀኝ ወደነበረው ሥልጣኑ ኢየሱስ በመመለሱ ነው። 

ጥያቄ፡- ሮሜ 8፡9 አንብቡ። ሀ) አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ከሌለ ይህ ምንን ያመለክታል? ለ) ዮሐንስ 7፡38-39 አንብቡ። በኢየሱስ የሚያምን ሰው ምንን ይቀበላል? 

በክርስቶስ የሚያምን ሰው ሁሉ በውስጡ እንዲኖር መንፈስ ቅዱስን የሚቀበል መሆኑን እግዚአብሔር ግልጽ አድርጎታል (ዮሐንስ 7፥8-39)። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ በውስጡ የሌለው ሰው እውነተኛ አማኝ ላለመሆኑ ይህ ምልክት ነው (ሮሜ 8፡9)። ሆኖም፥ በክርስቶስ ያሉ ብዙ አማኞች የክርስትና ሕይወትን እንዲኖሩ በውስጣቸው የሚኖረውን የመንፈስ ቅዱስን ኃይል መጠቀም አልጀመሩም። በዚህ ፈንታ የክርስትና ሕይወታቸውን በራሳቸው ፈቃድና መንገድ በኃይላቸውም ለመኖር ይታገላሉ። በዚህም የኤሌክትሪክ መብራት ባለው ቤት ውስጥ የሚኖር፥ ግን በመብራቱ የማይጠቀመውን ሰው ይመስላሉ። በዚህ ፈንታ ለቤቱ በቂ ብርሃን በማይሰጠው በሻማ ወይም በኩራዝ ብርሃን ይጠቀማሉ። ታዲያ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሳይሆን፥ በራሳችን ኃይልና መንገድ የክርስትና ሕይወታችንን መኖር ስንጀምር፥ ስኮረንቲ መብራት በመጠቀም ፈንታ በሻማ መብራት እንጠቀማለን ማለት ነው። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መጠቀም ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ እርሱ መማር ማለት ነው። እንዲሁም ቀኑን ብዙ ጊዜ ወደ እርሱ መጸለይና በሕይወታችን ውስጥ ልዩ ሁኔታ ሲገጥመን እግዚአብሔር ኃይል እንዲሰጠን እርሱን መጠየቅና ችግር ሲያጋጥመን ለመንፈስ ቅዱስ ኃይል አሳልፈን መስጠት ማለት ነው። 

ጥያቄ፡– በሕይወታችሁ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሊሠራ ለማየት የምትፈልጉአቸውን ሦስት ስፍራዎችን ለይታችሁ ጻፉ። ከዚያም በእነዚህ በሕይወታችሁ ውስጥ ባሉ ስፍራዎች ውስጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም እንዲያስችላችሁ እግዚአብሔር መንፈሱን እንዲሰጣችሁ ጸልዩ። በተጨማሪም እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች በሚያጋጥማችሁ ጊዜ ራሳችሁን አሳልፋችሁ ለእግዚአብሔር መንፈስ ኃይል ስጡ። አሁን ደግሞ ወደ ማስታወሻ ደብተራችሁ በመመለለ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል በሕይወታችሁ ውስጥ እንዴት እንዳስተዋላችሁ ጻፉ።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Exit mobile version