ትናንትና ለደኅንነት አስፈላጊ ስለሆኑት ነገርች ጥናታችንን ጀምረን ነበር። በመሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ደኅንነት አንድ አስፈላጊ የሆነ ነገር ብቻ ይሰጠናል። ይህንንም አንድ አስፈላጊ የሆነ ነገር በሦስት የተለያዩ መንገዶች ይገልጻቸዋል። አንዳንድ ጊዜም መጽሐፍ ቅዱስ ለደኅንነት አስፈላጊ የሆነውን ነገር እንደ «ንስሐ» አድርጎ ያቀርበዋል። በሌላ ጊዜም መጽሐፍ ቅዱስ ለደኅንነት ተፈላጊውን ነገር ሲጠቅስ፥ «እምነት» መሆኑን ይናገራል። እንደዚሁም መጽሐፍ ቅዱስ ለደኅንነት አስፈላጊ ሆኖ የሚያቀርበው ነገር «ወደ እግዚአብሔር መመለስን» ነው። ስለሆነም እንግዲህ ንስሐ፥ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ እነዚህ ሦስቱ ለደኅንነት አስፈላጊ የሆነውን አንዱን ነገር በሦስት መንገዶች መግለጽ ነው። ትናንትና አዲስ ኪዳን ለደኅንነት አስፈላጊ ስለሆነው ነገር የተናገረውን ፍሬ ነገር ተምረን ነበር። ዛሬ ደግሞ አዲስ ኪዳን እምነት ለደኅንነት አስፈላጊ መሆኑን ሲያብራራ እንማራለን። በነገው ክፍለ ጊዜ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ለደኅንነት ያለውን ጠቃሚነት አዲስ ኪዳን የሚሰጠውን ትምህርት እናጠናለን።
1. እግዚአብሔር በክርስቶስ ለሚታመኑት ደኅንነትን ይሰጣል።
ጥያቄ፡ ዮሐንስ 3፡16 እንብቡ። ) እንድ ሰው የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት ምን ማድረግ አለበት? ለ) ዮሐንስ 20፡21 እንብቡ። አንድ ሰው ሕይወት እንዲኖረው ምን ማድረግ አለበት?
ጥያቄ፡- ሉቃስ 7፡36-50፥ በተለይም ቁጥር 50ን እንብቡ። ኃጢአተኛዋ ሴት ደኅንነትንና የኃጢአት ይቅርታን እንድታገኝ ያደረጋት ምን ነበር?
ጥያቄ፡- የሐዋርያት 16፡31 እንብቡ። ጳውሎስ የፊልጵስዩስ ወኅኒ ቤት ጠባቂ ለመዳን ምን እንዲያደርግ ነገረው?
ጥያቄ፡ 1ኛ ዮሐንስ 5፡13 አንብቡ። የዘላለም ሕይወት እንዳላቸው እነማን እርግጠኞች ሊሆኑ ይችላሉ?
ለደኅንነት አንዱ አስፈላጊ የሆነው ነገር በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን መሆኑን አዲስ ኪዳን በግልጽ ይናገራል። በዮሐንስ 3፡16 ላይ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ በልጁ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለው ነግሮት ነበር። እንዲሁም በዮሐንስ 20፡21 ዮሐንስ እንደሚነግረን ወንጌሉን የጻፈው አንባቢዎቹ ኢየሱስ በእግዚአብሔር የተመረጠ መሢሕ መሆኑን እንዲረዱ፥ ከዚያም በእርሱ በሚያምኑበት ጊዜ በስሙ የዘላለም ሕይወትን ሊያገኙ እንደሚችሉ እንዲያውቁ ነው። ያቺ ኃጢአተኛ ሴት ወደ ፈሪሳዊው ስምዖን ቤት በመጣች ጊዜ ኢየሱስ ኃጢአትዋ እንደ ተሰረየላት አስታወቃት። እርስዋም በእምነትዋ ምክንያት ደኅንነትን እንዳገኘች ነገራት። የፊልጵስዩስ ወኅኒ ቤት ዘበኛ ለመዳን ምን ማድረግ እንዳለበት ጳውሎስን በጠየቀው ጊዜ ጳውሎስ መልሶ፣ «በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እመን» አለው። በ1ኛ ዮሐንስ 5፡13 ደግሞ ዮሐንስ እንደሚነግረን፥ በእግዚአብሔር ልጅ ስም የሚያምኑ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዳላቸው በእርግጥ ያውቃሉ ይላል።
በእነዚህ ሁኔታዎች ሁሉ እምነት ብቸኛውና አስፈላጊው ነገር መሆኑን ማስተዋል ይገባል። ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኝ ብዙ መልካም ሥራዎችን መፈጸም እንዳለበት አልነገረውም። እንደዚሁም ኢየሱስ ሰሉቃስ 7 ላይ ያቺን ኃጢአተኛ ሴትዮ እምነትና ሌላ ተጨማሪ ተግባር አጻናት አላለም። ጳውሎስም ለፊልጵስዩስ ወኅኒ ቤት ጠባቂ ለመዳን ኃጢአት መሥራቱን አቁሞ በኢየሱስ እንዲያምን አልነገረውም። ዮሐንስም ለአንባቢዎቹ ሲጽፍ ኃጢአት መሥራትን አቁመው መልካም ሥራ ቢሠሩና በእግዚአብሔር ልጅ ቢያምኑ የዘላለምን ሕይወት እንደሚያገኙ አልነገራቸውም። ስለሆነም እምነት ራሱ ብቻ ለደኅንነት አንድ አስፈላጊ ነገር ነው። 2. እምነት በኢየሱስ ላይ ብቻ መደገፍ ማለት ሲሆን፥ በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛች አድርጎ ያቀርበናል።
ነገር ግን እምነት ምንድን ነው? ትናንት እንደ ተረዳነው፥ አዳኝ የሆነ እምነት ንስሐንም ይጨምራል። ነገሩ ስለ ኃጢአት፥ ስለ ደኅንነትና ስለ ኢየሱስ ያለንን አስተሳሰብ መለወጥ ነው። እንደዚሁም ኃጢአት አሰቃቂና አስከፊ ድርጊት በመሆኑ ከእግዚአብሔር የለየን መሆኑን መገንዘብ ነው። ከዚህም በተጨማሪ እኛ ራሳችንን ለማዳን የምናደርገው ጥረት ሁሉ ፋይዳ ቢስ መሆኑን ማስተዋል ነው። ስለዚህ በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ ሊያደርገን የሚችል በኢየሱስ፥ በሞቱና በትንሣኤው ላይ መደገፍ ብቻ ነው።
ብዙ የአዲስ ኪዳን ክፍሎች በግልጽ እንደሚያረጋግጡልን አዳኝ የሆነ እምነት፥ ራሳችንን ለማዳን በመልካም ሥራችንና በጽድቃችን ላይ መመርኮዝ እንደሌለብን ነው።
ጥያቄ፡– ኤፈሶን 3፡4-6፥ 7፣9 አንብቡ። ሀ) ማንም ሰው በመልካም ሥራውና በመንፈሳዊ ውርሱ የሚድን ሲሆን ኖሮ፥ ጳውሎስ ማን ይድን ነበር አለ (ቁጥር 4-6)? ለ) ታዲያ የጳ ውሎስ መልካም ተግባርና መንፈሳዊ ውርስ ምን አደረገለት? (ቁጥር ) ሐ) ምን ዓይነት ጽድቅ ክርስቶስንና ደኅንነትን ለማምጣት ይሳነዋል? መ) ምን ዓይነት ጽድቅ ክርስቶስንና ደኅንነትን ሊያመጣ ይችላል?
ጥያቄ፡– ኤፌሶን 2፡8-9 አንብቡ። ሀ) እኛ እንዴት ጻንን? ለህ እንዴት አልዳንንም? ሐ) እግዚአብሔር በዚህ መንገድ ለምን አላዳነንም?
ጥያቄ፡- ሉቃስ 18፡9-14 አንብቡ። ሀ) ከሁለቱ ሰዎች መካከል የትኛው በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ ሆነ? ለ) ይህ ሰው በቤተ መቅደስ ውስጥ በነበረ ጊዜ ምን አደረገ? ምንስ ተናገረ? ሐህ እንደ ቁጥር 14፥ ኢየሱስ በምን ምክንያት ይህ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ ሆነ አለ?
ጥያቄ፡– ሮሜ 3፡20-22 አንብቡ። ሀ) የሙሴን ሕግ በመጸም ስንቶች በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይባላሉ? ለ) የሕጉ እውነተኛ ዓላማ ምንድን ነው? ሐህ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ጻድቃን ሊባሉ ይችላሉ? መ) ሮሜ 3፡26 እግዚአብሔር ጻድቅ ነው ብሎ የሚናገርለት ማን ነው?
ጥያቄ፡- ሮሜ 4፡1-8 አንብቡ። ሀ) በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉና ጳውሎስ ስማቸውን እዚህ የጠቀሳቸው ሁለት ሰዎች እነማን ናቸው? ለ) አብርሃም በሥራው ቢጻድቅ ኖሮ ምን ባደረገ ነበር? (ቁጥር 2) ሐ) መጽሐፍ ቅዱስ አብርሃም እንዴት ባለ ሁኔታ በእግዚአብሔር ፊት ጸደቀ ይላል? (ቁጥር 3) መ) አንድ ሰው ሥራ ሠርቶ ለሥራው ክፍያ ገንዘብ ቢያገኝ ይህ ገንዘብ ደመወዙ ነው ወይስ በነፃ የተሰጠው ገንዘብ ነው? (ቁጥር 4) ሠ) እንደ ቁጥር 5 አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጽድቅ ለመሆን ምን ማድረግ አለበት? ምንስ ማድረግ የለበትም? ረ) ከቁጥር 6-8 ዳዊት የተባረከ ነው ብሎ ያለው ማንን ነበር?
ጥያቄ፡- ሮሜ 4፡20-25 አንብቡ። ጳውሎስ የአብርሃም ታሪክ እንዴት ባለ ሁኔታ እኛንም ይመለከተናል አለ?
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እምነት የሚናገረው አሳብ ክርስቶስ ብቻ እኛን የሚያድነን ሊሆን፥ ከእርሱ ሌላ ለለ ደኅንነታችን በሌላ መታመን እንደሌለብን ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ክፍሎች የደኅንነት እምነት እንዲኖረን ከፈለን ራሳችንን ለማዳን እኛ ብቁዎች አለመሆናችንን እንድንገነዘብ፥ እንዲሁም በመልካም ሥራችን እንዳንመካ ያስጠነቅቀናል። በፊልጵስዩስ 3፡4-6 ውስጥ ጳውሎስ በመልካም ሥራቸውና በመንፈሳዊ ‘ ውርሳቸው በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቁ ካሉ እኔ በሆንኩ ነበር ሊል ይነግረናል። ነገር ገን በፊልጵስዩስ 3፡9 ውስጥ ሕግን በመጠበቅ ክርስቶስን ሊያገኝና ጻድቅ ለመሆን በብቃቱ እንደማይችል ያረጋግጣል። እርሱ በእግዚአብሖር ጻድቅ ሊሆን የሚችለው መልካም ሥራውንና መንፈሳዊ ውርሱን እንደ ካንቱ ነገር አድርጎ ሲመለከተውና ለደኅንነቱ በክርስቶስ ብቻ ሲተማመን ነው (ፊልጵ 3፡7)። በኤፈሶን 2፡8-9 ላይም ሐዋርያው ሲነግረን ደኅንነታችን በእምነት የምናገኘው የእግዚአብሔር የጸጋው ነፃ ስጦታ ነው ይላል። በእምነት የምናገኘው ማለት በመልካም ሥራችን የምናገኘው ነው ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በመልካም ሥራችን በኩል ደኅንነትን ለእኛ የማይሰጥበት ምክንያት ደኅንነታችንን በመልካም ሥራችን አገኘን ብለን እንዳንመካ ነው። ነገር ን ማንም ሰው ቢሆን ደኅንነቱን በራሱ ጥረት ሊያገኝ አይችልም፡ ደግሞም ማንም ሰው ቢሆን ለመዳን ብቁ አይደለም። ማንኛውም ሰው ሊድን የሚችለው ደኅንነቱን በበጎ ሥራው ማግኘት እንደማይችል ተረድቶ የእግዚአብሔርን ነህ ስጦታ ሊቀበል ብቻ ነው።
ደኅንነትን የሚያሰጠን እምነት ምን ማለት እንደሆነ ስለ ፈሪሳዊውና ስለ ቀራጩ የቀረበው ምሳሌ ቀንዛቤን የሚያስጨብጠን ትምህርት ነው። ፈሪሳዊው ሊጸልይ ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ ስሜቱ መልካም ሥራው በእግዚአብሔር ፊት እንዳጸደቀው ሆኖ ነበር። የመዝረፍንና የማመንዘርን ኃጢአት አልሠራም ቁጥር ነህ። በየቀኑ ይቆማል፥ ካለው አሥራት በታማነት ለእግዚአብሔር ይሰጣል። ብዙ ሰዎች ይህ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ እንደሆነ ያህል ይቆጥሩ ይሆናል። ምክንያቱም የጻድቅ ሕይወትን የኖረ ስለነበረ፡ በቁጥር 14 ውስጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ እንዳልነበረ ኢየሱስ ይናገራል። ይህ ሰው ጻድቅ አልነበረም። ምክንያቱም ስለ ጽድቁና ላለ ትክክለኛነቱ በራሱ ጽድቅ ላይ የተደገፈ ስለነበረ ነው። በሌላ በኩል ቀራጭ ወደ እግዚአብሔር ሊጸልይ ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዘ በእዚእብሔር ፊት ጻድቅ ሊያደርገው የሚችል ነገር ጨርሶ በስሜቱ ውስጥ አልነበረም። ስለዚህ በእግዚአብሔር ፊት ብቁ አድርጎ የሚያቆመው ምን ነገር እንደሌለና እርሱ ኃጢአተኛ እንደሆነ ለእግዚአብሔር ተናገረ እንዲያውም እርሱ ደኅንነትን ለማግኘት ብቃት ያለው አለመሆኑን በመረዳት እግዚአብሔር በቸርነቱ ምሕረቱን እንዲያድለው ተማፀነ፡ ለብዙ ሰዎች ይነ ሰውዩ ትክክለኛ ሆኖ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚታይ መሆኑ አይገባቸውም ቀብር ሰብሳቢ እንደ መሆኑ ከራሱ ሕዝብ ሰርቋል። በዚህም የአይሁዶች ጠላት ለሆኑት ሮማውያን ከመጻፉ በላይ ራሱን አላግባብ አበልጽጓል። ነገር ግ ኢየሱስ በእርግጥ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቁ ሰው ይህ ነው ይላል በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖአል፥ ምክንያቱም ኃጢአት ላለመሥራ፡ ቃል ገብቷልና ነው። በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው ሰው ሊሆ ችሏል። ምክንያቱም በእግዚአብሔር ምሕረት ብቻ ተማምኗልና ነው በቁጥር 3 ውስጥ ስለ ምሕረት የተነገረው ቃል በስርየት ቀን የእስራኤል ሕዝብ ኃጢአት ለመሸፈን ይደረግ ከነበረው መሥዋዕት ከሚለው ቃል ጋ አንድ ነው። ቀራጩም በመስቀል ላይ ራስ ኃጢአቱን ለመሸፈን ፈስ በነበረው ደም አማካይነት በእግዚአብሔር ምሕረት ያምን ነበር በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ አድርጎ በሚያቀርበው በእግዚአብሔር ቃል በእግዚአብሔር ተስፋ ይተማመን ነበር። ራሱን ለእግዚአብሔር ጻድቅ አድር የሚቀርብ ብቃት እንደሌለው ገባው። ስለዚህ እግዚአብሔር ባዘዘጋጀው መሥዋዕት ለሚያምኑት ሁሉ ምሕረትን ሊሰጥ በገባው ቃል አመነ። የዚያ ፈሪሳዊና የቀራጩ ሰው ታሪክ እዳኝ የሆነ እምነት፡- 1) እኛ በመልካም ምግባራችን ራሳችንን ትክክለኛ አድርገን በእግዚአብሔር ፊት ማቅረብ እንደማንችል መቀበልን፤ እና 2) እግዚአብሔር የሚሰጠንን የምሕረት መንገድ በእርሱ አምነን መወሰድ እንዳለብን ያስተምረናል።
ምናልባት እምነት ማለት በበጎ ሥራችን መተማመን እንዳልሆነ ደህና አድርጎ የሚያቀርብልን ክፍል ሮሜ 3-4 ነው። በሮሜ 3፡20 ውስጥ ደግሞ ጳውሎስ በሮሜ 1፡18-3፡19 ውስጥ የተናገረውን አካትቶ ያቀርባል። ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ ስለሆነ ሕግን በመጠበቅ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን አይችልም። እንደ እውነቱ ከሆነ የሕግ ዓላማ የደኅንነትን መንገድ መስጠት ሳይሆን፣ እኛ ምን ያህል ኃጢአተኞች እንደሆንን ማሳየት ነው። የእግዚአብሔርን ሕግ ታላቅና ቅዱስነት ደረጃ ስንመለከት ይህን ደረጃ ማሟላት እንደማንችል እናረጋግጣለን። እንዲሁም ሁላችን ኃጢአተኞች መሆናችንን እንረዳለን። በተጨማሪ ሕጉ እግዚአብሔር ደኅንነትን እንዲሰጠን እርሱ ምን ያህል አስፈላጊአችን መሆኑን ያሳየናል። በሕጉ አማካይነት በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛች ሆነን በመታየት ፈንታ እግዚአብሔር ከዚህ የተለየ መንገድ ገልጾልናል። ሮሜ 3፡21 አሁን በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ሆነን ልንቀርብ እንችላለን። ይህን ስናደርግ በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኞች ያደርጉናል የምንለውን በሕግ ላይ መመካትን ትተን በእግዚአብሔር ፊት በሚያጸድቀን በኢየሱስ ክርስቶስ እንታመናለን (ሮሜ 3፡22)። በእምነት በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን እንሆናለን እምነት ማለትም በሕግ መተማመን ማለት አይደለም። ስለሆነም እምነት ማለት መልካም ሥራችን ወይም ጽድቃችን በእግዚአብሔር ፊት ያቆመናል ማለትም አይደለም። በራሳቸው ሳይሆን በኢየሱስ ብቻ የሚያምኑ በእግዚአብሔር ዘንድ ጻድቃን ይባላሉ (ሮሜ 3፡26)።
በሮሜ 4 ውስጥም ጳውሎስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ሆኖ መገኘት የሚቻለው በእምነት ብቻ መሆኑን ይገልጻል። ስለሆነም ይህ ክፍል ስለ እምነት ግልጽ አድርጎ በማስረዳት ረገድ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከሚገኙ እጅግ ጠቃሚ ከሆኑ ክፍሎች መካከል አንዱ ነው። ስለዚህ ሐዋርያው እንዲህ ብሎ በመጀመር ይጠይቃል፥ «የአብርሃምን ሕይወት በማጥናት ምን ልንማር እንችላለን? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት የጽድቅን ስፍራ አገኘ?» ይላል። አብርሃም በመልካም ሥራው ጸደቀ ሲባል ኖሮ፥ በፈጸመው ተግባር በተመካ ነበር። ነገር ገን ጳውሎስ ሲናገር፣ አብርሃም በእግዚአብሔር ፊት ሊመካ አይገባውም ነበር፥ ምክንያቱም በበጎ ሥራው አልጸደቀምና ነው። ታዲያ እንዴት ጻድቅ ሊባል ቻለ?
ይህን ለመመለስ ጳውሎስ ዘፍጥረት 15፡6 ይጠቅሳል። በኦሪት ዘፍጥረት 12 ውስጥ እግዚአብሔር ለአብርሃም የከነዓንን ምድር እንደሚሰጠውና ዘሩንም እንደሚያበዛለት ተስፋ ሰጥቶት ነበር። ግን በምዕራፍ 15 ላይ እንደተጻፈው፥ አብርሃም ገና ልጅ አላገኘም ነበር። በዘፍጥረት 15፡1 ውስጥ እግዚአብሔር አብርሃምን እንደሚጠብቀውና ታላቅ በረከትም እንደሚሰጠው ቃል ገባለት። ግን አብርሃም፦ «አሁንም ድረስ ልጅ የለኝም» ሲል ለእግዚአብሔር መለሰለት (ዘፍጥረት 15፡2-3)። እንዲሁም፥ «የምትሰጠኝ በረክት ምን ያደርግልኛል? ሀብቴን የሚወርሰው ይኸው ከአገልጋዮቼ አንዱ የሆነው ነው አለ»። እግዚአብሔርም ለአብርሃም በተስፋ ቃል መለሰለት። ከዚያም እንደ ሰማይ ክዋክብት ለቁጥር የሚታክቱ ልጆች እንደሚሰጠው ተስፋ ገባለት። አብርሃም ይህን የተስፋ ቃል ሲሰማ ምን ተሰማው? እግዚአብሔር ተስፋውን እንደሚፈጽም አመነ። አገልጋዩ ንብረቱን ሁሉ እንደሚወርስ በእርሱ መተማመኑን እርግፍ አድርጎ ትቶ ሲያበቃ እግዚአብሔር የሀብትና ንብረቱ ሁሉ ወራሽ የሆነ ልጅ እንደሚሰጠው አመነ። እንግዲህ እግዚአብሔር ለአብርሃም ጽድቅ አድርጎ የቆጠረለት፥ ይህን እምነትና ይህን መታመን ነበር። ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 15 እንደሚያስተምረን አብርሃም ባከናወነው መልካም ሥራው ብቃት ጻድቅነቱ አልታወቀለትም። በአጭሩ አብርሃም ጻድቅ መሆኑ የተነገረለት፥ እግዚአብሔር ቃሉን ጠባቂ መሆኑን ስለ አመነ ብቻ ነበር።
ጳውሎስ ኦሪት ዘፍጥረት 15፡16ን ጠቅሶ አብርሃም እግዚአብሔርን ባመነ ጊዜ እግዚአብሔርም ጽድቅ አድርጎ እንደ ቆጠረለት ይናገራል። በእንግሊዝኛው (credit) በአማርኛው ደግሞ መቁጠር ማሰብ የተባለው ቃል ለሂሳብ አያያዝ መዝገብ የሚውል ቃል ነው። ምናልባት ገንዘብ ከባንክ ወይም ከአለቃችሁ ያም ባይሆን ከሌላ ሰው ተበድራችሁ ይሆናል። ይህ የምትበደሩት ገንዘብ ልክ ብድር ተብሎ በመዝገቡ ውስጥ ይጻፋል። ታዲያ ያን ገንዘብ መክፈል ይኖርባችኋል። ይህን የተበደራችሁትን ገንዘብ መልሳችሁ እስከ ከፈላችሁ ደረስ ዕዳው አለባችሁ ማለት ነው። ግን ዕዳውን ከፍላችሁ ስታበቁ ቆዳው ይሰረዝላችኋል፥ ከዕዳውም ነፃ ትሆናላችሁ። ዕዳውም ሊሰረዝላችሁ የሰው ገንዘብ ሊኖርባችሁ አይችልም። እግዚአብሔር ስለ አብርሃም ሕይወት የሚናገረውን መዝገብ በከፈተ ጊዜ አብርሃም የሚከፍለው ዕዳ እንደ ነበረበት ተመለከተ። ይህ ዕዳ የኃጢአቱ ዕዳ ነበር። ነገር ግን ያኔ እግዚአብሔር ወደ አብርሃም እምነት ተመለከተ። አብርሃም በተስፋው ስላመነ እግዚአብሔር የአብርሃም የሕይወት ዕዳ በተጻፈበት መዝገብ ውስጥ በነፃና በቸርነቱ «ጻድቅ» ሲል በዚህ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ጻፈለት። ከአብርሃም እምነት የተነሣ እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የነበረውን የኃጢአት ዕዳ ለረዘለት። እንዲሁም አብርሃም ስላመነ እግዚአብሔር ጻድቅ መሆኑን አሳወቀለት። ታዲያ እግዚእብሔር የአብርሃምን የኃጢአት ዕዳ የሰረዘለት አብርሃም መልካም ሰው ስለነበረ ወይም እንዳች የጽድቅ ተግባር ስለፈጸመ አልነበረም። እግዚአብሔር የአብርሃምን ዕዳ የሰረዘበት ምክንያት በአጭሩ በእግዚአብሔር ተስፋውን እንደሚፈጽም ስላመነበት ነው።
ሮሜ 4፡3 (ኦሪት ዘፍጥረት 15፡6 የሚጠቅስ ነው) አብርሃም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን የቻለው በእምነቱ እንጂ በመልካም ሥራው አለመሆኑን በግልጽ ያስረዳል። አንድ ሰው ሥራ ሠርቶ የሚገባውን ደመወዝ እንደሚያገኝ ሁላችንም እናውቃለን። ይህ ክፍያ ለሰውየው በነፃ የተሰጠው ስጦታ አይደለም። ይህን ሰው ሲያሠራው የነበረ ሰውዬ ለዚህ ሰው ሊከፍለው የሚገባ ዕዳ ነበረበት። በሽፍጥረት ፡ ውስጥ ግን፥ ምንም የሥራ ጉዳይ አልተጠቀሰም። በዚህ ክፍል አብርሃም ሥራ ሠርቶ ነበር ተብሎ ቢጻፍ ኖር ጽድቁ እንደ ሥራ ክፍያ ከእግዚአብሔር የተሰጠው ሆኖ በታሰበ ነበር። ስለሆነም እግዚአብሔር አብርሃምን ጻድቅ ሊያደርገው ግዴታ በኖረበት ነበር። ግን የተጻፈው ክፍል ስለ ሥራ ምንም አያነሣም። በዚህ ፈንታ እምነቱን ብቻ ጠቅሷል። ስለዚህ አብርሃም በእግዚአብሔር ፈቃድ ፍላጎት በጸጋው መጠን በእምነቱ የተነሣ ጻድቅ መሆኑ ተረጋገጠለት።
በቁጥር 5 አብርሃም እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ እንደ ሆነና እግዚአብሔር እንዴት ሁልጊዜ ሰዎችን እንደሚያጸድቅ የሚናገር የጳውሎስ ማጠቃለያ ነው። ክፍሉ በቃል ለመያዝም ጠቃሚ ከመሆኑም በላይ ለወዳጅም ምስክርነት ሊሰጥበት የሚችል ነው። ምክንያቱም ሊደረጉ የሚገባቸውን ነጥቦች በሚከተለው ሁኔታ ያብራራልናል፡
1) ሰው በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው ሆኖ ለመገኘት ምን ማድረግ እንዳለበት ይናገራል፥ ማለትም በእግዚአብሔር ማመን እንዳለበት ያስረዳል።
2) አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው ሆኖ ለመቅረብ ምን ማድረግ እንደማይኖርበት፣ ይህም በራሱ በጎ ሥራ መታመንና ደኅንነትን እንደሚያስገኝለት ማመን እንደሌለበት ነው።
እዚህ ላይ ትምህርታችሁን ቆም አድርጋችሁ ሮሜ 4፡5ን በቃል ለማጥናት ሞክሩ።
እምነት ማለት ደኅንነትን ለማግኘት በኢየሱስ ብቻ ማመን ማለት ነው። ይህም በመልካም ሥራችን ታምነናል፣ ወይም ኃጢአት ጨርሶ አልሠራንም፣ እንዲሁም አንዳንድ ኃጢአትን ከማድረግ ተቆጥበናል ማለት አይዴለም። እምነት ማለት ኃጢአታችን ከእግዚአብሔር የለየን ስለሆነ በራሳችን ብቃት ጻድቃን ሆነን በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ እንደማንችል ማወቅ ነው። በሮሜ 4፡5 ውስጥ «ኃጢአተኛ» ተብሎ የተጻፈው ቃል በተጻፈበት የመጀመሪያ ቋንቋ መሠረት በጣም ጠንካራ የሆነ ቃል ነው። ትርጉሙም እጅግ እኩይ፥ እጅግ ክፉ የሆኑ ሰዎች ማለት ነው። በአንጻሩ ጳውሎስ እግዚአብሔር በምድር ላይ እጅግ በጣም ክፉና ጨካኝ የሆኑ ሰዎችን ጻድቃን ብሎ እንደሚጠራቸው ያስተምረናል። ታዲያ እዚአብሐር እንዲህ ያሉትን ሰዎች ለዚህ ታላቅ ስያሜ የሚያበቃቸው ኃጢአታቸው የከፋ መሆኑን በመገንዘብ በራሳቸው መልካም ሥራና ብቃት ወደ እግዚአብሔር ፊት ሊቀርቡ የማይችሉ መሆናቸውን የሚረዱና እግዚአብሔር እነርሱን ለማዳን ብሎ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እንዲሞት ማድረጉን የሚያምኑትን ብቻ ነው። በእግዚአብሔር ፊት ሰውን ፍጹም አድርጎ የሚያቀርበው መልካም ሥራው ወይም ኃጢአት አለመሥራቱ አይደለም። በክርስቶስ የሚኖራቸው እምነት ብቻ እግዚአብሔር ጻድቅ አድርጎ እንዲቀበላቸው ያስችላቸዋል። ማንኛውም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው በክርስቶስ ብቻ ማመንና በሚፈጽመው መልካም ሥራ አለኝታ ማድረግን መተው ይጠበቅበታል።
አብርሃም በሠራው መልካም ሥራ ሳይሆን እንዲሁ ጻድቅ ተብሎ በመጠራቱ ጳውሎስ የብሉይ ኪዳን ዐቢይ ምሳሌ አድርጎ አቅርቦታል። ነገር ቀን ሌሎች ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎችም ነበሩ። ከእነዚህም አንዱን ጳውሎስ ይጠቅሳል። ይህም የዳዊት ምሳሌነት ነው። ዳዊት በመዝሙር 32 ውስጥ ከእግዚአብሔር ስለ ተቀበለው የነፃ ይቅርታ ምስክርነቱን አቅርቧል። ኃጢአት ሠርቶ ነበር፥ ስለዚህ ኃጢአቱንም ለእግዚአብሔር ተናዝቧል። እግዚአብሔርም ኑዛዜውን ተቀብሎ በክብር ይቅር ብሎታል። ጳውሎስ ለማስታወስ የፈለገው በመዝሙር 32 ውስጥ እንደተጻፈው ዳዊት ይቅርታን ያገኘው በበጎ ሥራው ምክንያት አለመሆኑን ነው። በዚህን ጊዜ ዳዊት ያደረገው ነገር በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአቱን መናዘዝና ከእግዚአብሔር በሚሰጠው ይቅርታ ማመን ነበር። በመሆኑም እግዚአብሔርም በነፃ ይቅር አለው። ይህ እንግዲህ እግዚአብሔር ኃጢአትን ይቅር እንደሚልና ሰዎችን እንደሚያጸድቅ ሌላው ማረጋገግ ሊሆን ይችላል። ሰዎች ይህን ይቅርታ አግኝተው ሊጸድቁ የሚችሉት በሠሩት በጎ ሥራ ወይም ኃጢአት ማድረግን ስላቆሙ ሳይሆን በእግዚአብሔር ስላመኑ ነው።
ጳውሎስ በሮሜ 4፡22-25 ውስጥ ነገሩን ሲያጠቃልል፥ አብርሃም እግዚአብሔር ልጅ እንደሚሰጠው ማመኑ ይህ ለእኛ የእምነት ምሳሌ ነው ይላል። ስለዚህ አብርሃም እግዚአብሔር ልጅ እንደሚሰጠው የሰጠውን ተስፋ በእምነት እንደ ተቀበለ ሁሉ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በፊቱ ብቁዎች አድርጎ እንደሚቀበለን በሰጠን ተስፋ ማመን አለብን።
እምነት እግዚአብሔር እንደ ተስፋ ቃሉ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያድነን ማመን እንጂ በሌላ በማንም መታመን አይደለም። አዳኝ የሆነ እምነት ማለት ምን እንደሆነ የሚያብራራልን አንድ ትምህርታዊ ምሳሌ እነሆ። በአንድ ትልቅ ከተማ ውስጥ ይገኝ የነበረ አንድ ረጅም ሕንፃ በእሳት ተያያዘ። ይህ ሕንፃ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን የመጨረሻ ረጅሙን ሕንፃ ያህል ርዝማኔ ነበረው። በእሳት መያዙ እንደ ታወቀ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ መኪናዎች ውኃ ተሸክመው እሳቱን ሊያጠፉ መጡ። ነገር ቀን እሳቱ ስለ ተስፋፋና ወላፈኑ ኃይለኛ ስለሆነ የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞች እስከ ሕንፃው ላይኛው ክፍል ድረስ ሊወጡ አልቻሉም። ስለዚህ ከታች በእሳት የተያያዙትን ክፍሎች እንዲጠፋ ሲያደርጉ የላይኛዎቹን ክፍሎች እሳት ላያጠፉ ቀሩ። የላይኛዎቹ ክፍሎች እየነደዱ ሳሉ፣ ድንገት ከአንደኛው ክፍል ውስጥ አንዲት ልጅ በመስኮት ብቅ አለች። ይህች ልጅ ከመጨረሻዎቹ የላይኛው ክፍሎች ውስጥ በአንዱ የምትኖር ነበረች። ቀን እሳቱ ሲጀምር ብቻየን ነበረች። ምን ያደርጋል እሳቱ በየስፍራው ተያይዞ እየነደደ ስለሆነ ልጅትዋ ወደ ታች በመምጣት ከእሳቱ ለመዳን አልቻለችም። ስለዚህ ልጅትዋ እርዳታ ለማግኘት ታለቅስ ጀመር፡፡ የእሳት አደጋ ሠራተኞችም ይህን እንደ ተመለከቱ ልጅትዋ ከላይ ወደ ታች ዘልላ ወርጻ ከእሳት አደጋው ልታመልጥ የምትችልበትን መረብ አምጥተው ዘረጉላት ? ከዚያም ልጅትዋ ቁልቁል ወደ መረቡ እንድትዘል በነገሩአት ጊዜ እምቢ ፡ አለች። ልጅትዋ ከእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች መካከል አንዱን እንኳን ስለማታውቅ ዘልላ ለመውረድ ፈራች። ቁልቁል በምትዘልበት ጊዜ መረቡ ተቀብሎ ከአደጋ እንደሚያድናትም አልተማመነችበትም ነበር። ስለዚህ ከፍርሃትዋና ከጥርጣሬዋ የተነሣ እየተቃጠለ ባለው ሕንፃ ውስጥ ቆየች፡፡ ታዲያ ይህን ጊዜ የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች ምን ሊያደርጉ ይችሉ ነበር? እሳቱ እየተቀጣጠለ ልጅትዋ ወዳለችበት ክፍል እየቀረበ ነው። ሠራተኞቹ ወደ ላይ ወጥተው ልጅትዋን እንዳያተርፉ፣ እሳቱ እነርሱንም አቃጥሎ ሊገድላቸው ነው። ልጅትዋ ዘልላ ካልወረደች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቃጥላ ልትሞት ነው።
ልክ በዚህን የጭንቅ ጊዜ የልጅትዋ አባት እየተቃጠለ ወደ አለው ሕንፃ መጣ። ሕንፃው በእሳት በተያያዘ ጊዜ እርሱ በመሥሪያ ቤቱ በሥራ ላይ ነበርና ወሬውን እንደ ሰማ እየተጣፈደ መጣ። እንደ ደረሰም አሻቅቦ ሲመለከት ሴት ልጁ ቁልቁል ወደ መረቡ መዝለል ፈርታ ስትጨነቅ ተመለከተ። ከዚያም ተጣራና እርሱ ከእሳት አደጋ ሠራተኞች ጋር መሆኑንና እነርሱም መረብ መያዛቸውን ነገራት። ከዚያም ወደ መረቡ ዘልላ ብትወርድ ከእሳቱ እንደምታመልጥ አረጋገጠላት። ልጅትዋም አባትዋ በሰጣት የመዳን ተስፋ አምና ቁልቁል ወደ መቀበያው መረብ ዘለለች። የእሳት አደጋ ሠራተኞችም በመረባቸው ተቀበሉዋትና ከሞት ተረፈች።
ታዲያ ይህ ታሪክ እንዴት እምነትን ሥዕላዊ በሆነ ይዘት ሊያቀርበው ይችላል? እግዚአብሔር እኛ በኢየሱስ ብናምን ደኅንነትን እንደሚሰጠን ተስፋ እንደ ሰጠን ሁሉ፥ የዚያች ልጅ አባትም ደፍራ ቁልቁል ወደ መረቡ ብትዘል ከቃጠሎው እንደምትተርፍ ተስፋ ሰጣት። ነገር ግን ልጅትዋ ከአባትዋ ተስፋ ይልቅ በሌላ ነገር ልትታመን ትችል ነበር። እሳቱ ወደ እርሷ እንደማይደርስ ልታምን ትችል ነበር። ወይም የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኛች እርሷ እስካለችበት ድረስ ሄደው ሊያወርዷት እንደሚችሉ ባመነችም ነበር። እንዲሁም ራሷ በእሳቱ ውስጥ ወርዳ እንደምታመልጥ ባመነች ነበር። ይሁን እንጂ፣ በእነዚህ ሌሉች መንገዶች ብትተማመን ኖሮ፣ ከእሳቱ ቃጠሎ ባልዳነችም ነበር። ስለሆነም ከአደጋው ለመትረፍ በሌሎች ሁኔታዎች መታመንን ትታ በአባትዋ ተስፋ ብቻ መታመን ነበረባት። አዳኝ እምነት ማለት እግዚአብሔር በኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ እንደሚያድነን በሰጠን ተስፋ ብቻ መታመን ማለት ነው።
ጥያቄ፡- ሀ) በአካባቢአችሁ ከሚኖሩት ሰዎች እምነት ውጪ እግዚአብሔር አብዛኛዎቹን ክፉዎች ሰዎችን በክርስቶስ በሚኖራቸው እምነት እነርሱን የማዳኑ ነገር እንዴት ይታያል? አብዛኛዎቹ የቤተ ክርስቲያን አባላት ከሚኖራቸውስ እምነት እንዴት ይለያል?
ዛሬ አብዛኛዎቹ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኞች ሆነው ለመገኘት ኃጢአት መሥራትን ማቆም ያለባቸው መስሎ ይታያቸዋል። ከዚህም ሌላ ብዙ መልካም ሥራዎችን ማከናወን እንዳለባቸውም ይታያቸዋል። እነዚህም ኦም፡ ጸሎት፡ ምጽዋት መስጠት፥ አዘውትር ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድን የመሳሰሉት ናቸው። በዚህም በእግዚአብሔር ፊት መልካም ሆነው የሚቀርቡ ይሙላላቸዋል። በዚህ ፈንታ በእግዚአብሔር ፊት ትክከለኞች አድርጎ በሚያቀርባቸው ስኢየሱስ፥ በእርሱ ሞትና ትንሣኤ ብቻ አይተማመኑም። እነዚህ ሰዎች ኢየሱስ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 18 ውስጥ ጠቅሶ ምሳሌ ያደረገውንና በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ ያልነበረውን ፈሪሳዊ ይመስላሉ። ምክንያቱም በራሱ ጽድቅ የተኩራራ ስለነበረ ነው። ሁላችንም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን የምንሆነው በኢየሱስ፥ በሞቱና በትንሣኤው ብቻ ስንታመን ነው።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
