ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በተከታተልነው ትምህርት ላይ፥ መጽሐፍ ቅዱስ በእውነት ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች ለዘላለም ዋስትናቸው የተጠበቀ መሆኑን እንደሚያስተምር ተገንዝበናል። እግዚአብሔር እነርሱን የማዳኑን ተግባር እነርሱ ከእርሱ ጋር የታረቁ መሆናቸውን በማሳወቅ ጀምሮአል፤ ይህንንም የጀመረውን የማዳን ተግባር በታማኝነት ከግብ ያደርሳል። በዚሁ መሠረት የመጨረሻው የደኅንነታቸው ዋስትና እንዲሆንም የራሱን መንፈስ ቅዱስ ሰጥቶአቸዋል፤ ይህንንም ሲያደርግ ማንም ከፍቅሩ ሊለያቸው እንደማይችል ተስፋውን አክሎ ሰጥቶአቸዋል። እነዚህ አማኞችም የክርስቶስ አካል ክፍል ስለሆኑ፥ ኃጢአት በሚሠሩበት ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ራሱ ይማልድላቸዋል። እነዚህ ሁሉ አስደናቂ የሆኑ እውነታዎች በእርግጥ ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች የደኅንነታቸው ነገር ዋስትና ያለውና የተረጋገጠ መሆኑን ያስገነዝበናል።
ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቲያኖች ደኅንነታቸውን የሚያጡ ዓይነት ትርጉም የያዙ የሚመስሉ ክፍሎች የሉምን? እንደዚሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደኅንነታቸውን ያጡ አማኞች ስለመኖራቸው በምሳሌነት የሚጠቀስባቸው ክፍሎች የሉምን? እንግዲህ በዛሬው ትምህርታችን ውስጥ፥ አማኞች ደኅንነታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ የሚመስሉ ክፍሎች ስለሚሰጡት ትምህርት እንመረምራለን። እነዚህን ክፍሎች ሁልጊዜ ልናስታውሳቸው ከሚገባን ሁለት መንፈሳዊ መመሪያዎች በመነሣት የምናጠና ሲሆን፥ መመሪያዎቹም፡- 1) በክርስቶስ ማመንን ለማመልከት የሚደረግ የሃይማኖት መግለጫ፥ በክርስቶስ ከሚኖረን እውነተኛ እምነት ጋር አንድ አይደለም። 2) እውነተኛ ክርስቲያኖች ኃጢአትን ይሠራሉ፥ ከዚህ በኋላም ዘላለማዊ ደኅንነታቸውን ሳያጡ ስለሠሩት ኃጢአት እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል።
1. በክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት ማሳወቅ፥ በክርስቶስ ላይ ካለን እውነተኛ እምነት ጋር አንድ አይደለም።
ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐ 2፡19 አንብብ። ሰዎች የክርስትና እምነታቸውን ጨርሰው በሚተዉበት ጊዜ ይህ ምንን ያመለክታል?
ጥያቄ፡- ዮሐ 8፡31 አንብብ። ሰዎች በእውነት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ለመሆናቸው ምልክቱ ምንድን ነው?
ጥያቄ፡- ዕብ. 3፡14 አንብብ። ከክርስቶስ ጋር ወራሾች ለመሆናችን ምልክቱ ምንድን ነው?
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከምናገኛቸው እውነታዎች መካከል እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነው፥ በክርስቶስ ማመንን መናገር፥ በክርስቶስ ላይ ካለ እውነተኛ እምነት ጋር አንድ አለመሆኑን በግልጽ የሚያስረዳው ነው። በ16ኛው ትምህርት ውስጥ እንደ ተመለከትነው፥ ሰዎች በክርስቶስ የሚያምኑ መሆናቸውን መግለጣቸው ብቻ ወይም እርሱን በአዳኝነት አምነው የተቀበሉ መሆናቸውን መናገራቸው ብቻ በቂ አለመሆኑን ተገንዝበናል። እንደዚሁ ሁሉ ሰዎች ከልብ ሳይሆን ላይ ላዩን ብቻ ክርስቶስን የተቀበሉ አስመስለው ቢጸልዩ ይህም በቂ አይደለም። ይህ ብቻም አይደለም፥ ሰዎች ሰይጣንን ክደውና ኮንነው ክርስቶስን መቀበላቸውን መናገራቸው ብቻም በቂ አይደለም። ስለዚህ ከልብ ሳይሆን በውጪአዊ ስሜት ላይ ብቻ የተመሠረተ በክርስቶስ ስለማመን የሚደረግ የአፍ መግለጫ ብቻም ማንንም ሊያድን አይችልም። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ከልባቸው አምነው የተቀበሉትን ማዳን የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ኃጢአታቸው ከእግዚአብሔር የለያቸው መሆኑን የሚገነዘቡትና ለደኅንነታቸው በራሳቸው መልካም ሥራ ምንም ተስፋ ሳያደርጉ እርሱን የሚማጠኑትን እግዚአብሔር ያድናቸዋል። በኢየሱስ የሚመኩትንና እርሱን ተገን የሚያደርጉትን ብቻ እግዚአብሔር ያድናል።
እንደዚሁም ሰዎች ክርስቶስን ከልባቸው አምነው በመቀበላቸው ምክንያት፥ ለእርሱ ታማኞች ሆነው እንደሚኖሩ፥ በውጪአዊ ድርጊታቸው በምልክትነት የሚገልጡ መሆናቸውን መጽሐፍ ቅዱስ አክሎ ያስተምረናል። ሰዎች በክርስቶስ የሚያምኑ መሆናቸውን በይፋ ከመግለጥ ቢቆጠቡ ደግሞም ቢያቆሙ ይህ ድርጊት በመጀመሪያ ደረጃ እውነት ዳግም ያልተወለዱ መሆናቸውን የሚያሳይ ምልክት ነው። 1ኛ ዮሐ. 2፡19 ውስጥ ብዙ ሐሰተኞች የሆኑ ክርስቲያኖች የተቀበሉትን እምነትና ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ያላቸውን እንድነት መተቸውን ይገልጻል። ዮሐንስ ሲናገር የተቀበሉትን እምነትና ከሊሎች አማኞች ጋር የነበራቸውን ኅብረት በተዉ ጊዜ፡ ይህ እነታቸውን ከጠበቁት ጋር አንድነት የሌላቸው ለመሆኑ ምልክት ነው ይላል። ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው አላወቁትም፡ ቀድሞውንም ቢሆን እውነተኞች ክርስቲያኖች አልነበሩም። እውነተኞች ክርስቲያኖች ቢሆኑ ኖር፡ ዮሐንስ በእምነታቸው ጸንተው ሰቆዩ እና ከሌሎች አማኞች ጋር የነበራቸው አንድነትም አብሮአቸው በዘለቀ ነበር ብሏል። ምንም እንኳን ሌሎች እንደ እውነተኛ ክርስቲያኖች ቆጥረው ቢቀበሉዋቸውም፥ በመጨረሻው ላይ የተቀበሉትን እምነት መተዋቸው የሚያስረዳው ጌታን በእውነት ያላወቁት መሆናቸውን ነው። ጌታ ኢየሱስ በዮሐንስ 8 ውስጥ ደቀ መዝሙሮቹ መሆናቸውን ሊገልጡለት ለምክሩ ለተሰበሰቡ ብዙ አይሁዳውያን ሲናገር እንመለከታለን። በቁጥር 31 ውስጥ ኢየሱስ በእውነት እነርሱ ደቀ መዛሙርቱ ከሆኑ በቃሉ እንደሚኖሩ አስረዳቸው። በእውነት ዳግም በክርስቶስ የተወለዱ አማኞች እስከ መጨረሻው ድረስ ለኢየሱስ ቃል ታማኞች ሆነው ይኖራሉ። በምንም እኳኋን ክርስቶስን በመጨረሻው ጊዜ ሙሉ በሙሉ አይተዉትም።
ዕብራውያን 3፡14 እምነታችንን እስከ መጨረሻ አጽንተን ብንይዝ ከክርስቶስ ጋር ወራሾች ነን ሊል ይነግረናል። ይህ ጥቅስ የተገለጠበትን የግሥ ጊዜ በጥንቃቄ መመልከቱ እሳቡን ለመገንዘብ ይረዳናል። ቁጥሩ እምነታችንን እስከ መጨረሻው ድረስ አጽንተን ብንይዝ ከክርስቶስ ጋር ወራሾች እንሆናለን አይልም። እንዲህ ቢል ኖር የወደፊቱ ደኅንነታችን እነታችንን አጥብቀን ለመያዝና ለመጽናት በምናደርገው ጥረት ላይ ይመሠረታል የሚል አንድምታ ሰያዘ ነበር። ታዲያ ይህ ጥቅስ ምን ይላል? ጥቅሱ የሚለው እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንይዝ፥ ከክርስቶስ ጋር ወራሾች ለመሆን ችለናል ነው። አስቀድመን በእውነት ድነናል፥ እንዲሁም በእውነት ም ተወልደናል የሚለው አሳብ በክርስትና እምነታችን ውስጥ አንተን ከመቆየታችን አቅጣግ የሚታይ እውነታ ነው። እንዲያው ብቻ በአንደበታቸው ክርስቲያኖች መሆናቸውን የሚለፍፉ ሁሉ፥ እውነተኞች ክርስቲያኖች አይደሉም። በእውነት ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች ብቻ በክርስትና ዴታቸው ጸንተው ባለማወላወል ይዘልቃሉ። እንዲህ ያሉ የልብ ክርስቲያኖች ቀደም ሲል በይፋ የገለጡትን እምነታቸውን በምንም ሁኔታ በመጦረሻው ላይ ተስፋ ቆርጠው አይተዉም።
ጥያቄ፦ ማቴ 7፡21-23 አንብብ። በኢየሱስ ስም ታላቅ ኃይል የታየበት ሥራ በፊልሙ ለቶ ላይ በፍርድ ቀን ምን ብይን ይሰጥባቸዋል?
ጥያቄ፦ ማቴ 10፡1፣4 እንብብ ሀ) ኢየሱስ ለአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት የን ሥልጣንን ሰጣቸው? ለ) ዮሐ 6፡70-71 አንብብ። ይሁዳ ገና ደቀ መዝሙር ሆኖ ጌታን ሊከተል በነበረበት ጊዜ፥ ኢየሱስ ስለ ይሁዳ ምን ተናገረ?
ጥያቄ፦ ዘኁልቁ 24፡15-16 እንብብ። የበለዓም ትንቢት በምን ራእይና ዕውቀት ላይ የተመሠረተ ነበር? ለ) ኢያሱ 13፡22 አንብብ። የበለዓም ሙያ ምን ነበር? ምን እየተባለ ይጠራ ነበር? ሐ) 2ኛ ጴጥ. 2፡1፥5 አንብብ። ሐዋርያው ጴጥሮስ ስለ በለዓም ሊናገር እንዴት ያለ ሰው ነበር አለ?
ብዙ ሰዎች ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖችን እንደሚያውቁና እነዚህም ክርስቲያኖች ኋላ ላይ በክርስቶስ የነበራቸውን እምነት እንዳቋረጡ ይናገራሉ። እነዚህ ይህን የሚሉ ሰዎች፥ እነዚያ ክርስቲያኖች በእንቅስቃሴአቸው መልካም የሆነ የክርስትናን ሕይወት የኖሩ ስለሚመስሉ በእርግጥም ዳግም የተወለዱ እንደሆኑ አድርገው ያውቋቸው ነበር፡ ምናልባትም እነዚህ ሰዎች ኃይለኞች ወንጌላውያን ሆነው ይሆናል ፤ ወይም ታምራትን ይሠሩና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚከናወኑ ተግባራትንም ሲያከናውኑ ይታዩ ነበር። ምናልባትም ታላላቅ ክርስቲያናዊ መሪዎች ነበሩ። ኋላ ግን የክርስትና እምነታቸውንና ሕይወታቸውን ትተዋል። እነዚህ ሰዎች ደኅንነታቸውን ያጡ የእውነተኞች ክርስቲያኖች ምሳሌ ሊመስሉ ይችሉ ይሆናል። በዚሁ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ አማኛች ስለሚመስሉ ሰዎች አያሌ ምሳሌዎችን ያቀርባል። እነዚህ ሰዎች እውነተኞች አማኞች አለመሆናቸውን በመጨረሻው ተግባራቸው ያሳዩ ናቸው። ጌታ ኢየሱስ በማቴዎስ 7፡21-23 ሲናገር ብዙዎች በስሙ ትንቢትን እንደሚናገሩ፥ ተአምራትን እንደሚያደርጉና አጋንንትን እንደሚያወጡ ገልጾአል። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች እርሱ በፍጹም ስለማያውቃቸው፣ በመጨረሻው ቀን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት አይገቡም። ምንም እንኳ እነዚህ ሰዎች በሚያደርጉዋቸው ድንቅ በሆኑ መንፈሳዊ ተግባራት የኢየሱስ ተከታዮች መስለው ቢታዩም፡ በውስጣቸው ግን ዳግም የተወለዱ አማኞች አልነበሩም። ማስተዋል ያለባችሁ ነገር ኢየሱስ አንድ ጊዜ አውቃቸዋለሁ አለማለቱና የእነርሱም ደኅንነትን የማጣት ሁኔታ ነው። ጌታም፣ በፍጹም አላውቃችሁም ነው ያላቸው። በእውነትም፥ የተረጋገጠላቸው በክርስቶስ የሚታመኑ አማኛች አልነበሩም።
ይሁዳ እንዲህ ያለ ሰው ነበር። ማቴዎስ 10፡1 እንደሚነግረን፣ ጌታ ኢየሱስ ለአሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት የመፈወስንና አጋንንትን የማውጣት ሥልጣንን ሰጥቷቸው ነበር። በተለይ ቁጥር 4 እንደሚለው፣ ይሁዳ ከአሥራ ሁለቱ መካከል አንደኛው ነበር። ስለዚህ ይሁዳ በኢየሱስ ሰም አጋንንትን ያወጣና ደግሞም ይፈውስ ነበር። ነገር ግን ይሁዳ በጭራሽ በክርስቶስ የሚያምን እውነተኛ አማኝ አልነበረም። በዮሐንስ 6፡70-71 ውስጥ፥ ይሁዳ በውጢአዊው ሁኔታው የኢየሱስ ተከታይ በነበረበት ጊዜ፥ ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን የመረጠ ቢሆንም፥ እንደኛው (ይሁዳ) ን ዲያብሎስ እንደ ነበረ ተናግሮአል። በዚያን ጊዜ ገና ይሁዳ ሐሰተኛ ደቀ መዝሙር መሆኑን ኢየሱስ አመልክቷል። ቢሆንም ከደቀ መዛሙርቱ መካከል እንጻቸውም እንኳን ይሁዳ ሐሰተኛ ደቀ መዝሙር መሆኑን የጠረጠረ አልነበረም። ኢየሱስና ይሁዳ ራሱ ብቻ ይህን ያውቁ ነበር። ነገር ን በእኛ ዮሐ 219 ውስጥ እንደምናነበው፥ በመጨረሻው ላይ ይሁዳ በልቡ ውስጥ ተሰውሮ የነበረውን ተናገረ፡ በዚህም ክርስቶስን አሳልፎ ሰጠ፥ ደግሞም በይፋ ገልጦት የነበረውን እምነቱን ካደ።
በለዓም የሕያው እግዚአብሔር ተከታይ ይመስል የነበረ ሰው ሌላ ምሳሌ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር የሰጠውን ታላላቅ ቃላት ይናገር ነበር። ኦሪት ዘኁልቁ 24፡15-16 በለዓም እግዚአብሔር በገለጠለት ራእይና እውቀት ላይ የተመሠረተ ትንቢት መናገሩን ይጠቅሳል። ኢያሱ 13፡22 ደግሞ በለዓም የጥንቆላ ተግባር ይፈጽም እንደ ነበረ ያስገነዝባል። ምንም እንኳ በለዓም የእግዚአብሔር ነቢይ መስሎ ቢታይም፥ እንዲሁም እግዚአብሔር በሞዓብ ተራራ ላይ በእርሱ አማካይነት ቢናገርም፥ በለዓም ግን በእርግጥ ጠንቋይ ነበር! ጴጥሮስም ይህ ሰው ሐሰተኛ የሆነ ነቢይ መሆኑን ያረጋግጣል። በ2ኛ ጴጥሮስ ውስጥ ሐዋርያው ስለ ሐሰተኞች ነቢያትና መምህራን በሚያስጠነቅቅበት ጊዜ፥ በለዓምን እንደ አንደኛው ምሳሌ አድርጎ ጠቅሶታል። እንግዲህ በለዓም በእግዚአብሔር እውነተኛ ነቢይ ተመስሎ ቀርቧል፥ እግዚአብሔርም በእርሱ አንደበት አማካይነት የራሱን ቃል ተናግሮአል። ነገር ግን ይህ ሁሉ ሲሆን፥ በለዓም እውነተኛ የእግዚአብሔር ተከታይ አልነበረም። እርሱ ሐሰተኛ የሆነ ነቢይና ጠንቋይም ነበር።
በክርስቶስ ማመንን በቃል ማስታወቅ ብቻ እውነተኛ የሆነ በክርስቶስ የጸና እምነት በልብ ውስጥ መኖሩን አይገልጽም። እውነተኛና በክርስቶስ ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች በምንም አኳኋን በመጨረሻው ጊዜ ለክርስቶስ የገቡትን የእምነት ቃል ኪዳን አፍርሰው ከእርሱ አይለዩም። አንዳንድ እግዚአብሔር የሚገለገልባቸው የሚመስሉ ሰዎች እውነተኞች የልብ ክርስቲያኖች ሊሆኑ የማይችሉበት ጊዜ አለ። ይሁዳ እንዳደረገው ሁሉ፥ በክርስቶስ የነበራቸውን እምነት በሚክዱበት ጊዜ፥ ይህ ድርጊታቸው ቀድሞውኑ ክርስቶስን በእውነት ከልባቸው አያውቁት እንደ ነበረ ይገልጣል።
2. እውነተኞች ክርስቲያኖች ኃጢአት ቢሠሩም ከእግዚአብሔር ዘንድ ግሣጼአቸውን ይቀበሉና ዘላለማዊ ደኅንነታቸውን አያጡም፡፡
ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልንረዳው የሚገባን ሁለተኛውና ጠቃሚ እውነታ፥ እማኞች ኃጢአትን እንደሚሠሩና እግዚአብሔር እንደሚቀጣቸው፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር እጅ ክፉኛ ቢቀጡም ዘላለማዊ ደኅንነታቸውን እንደማያጡ ነው።
ጥያቄ፡- ሉቃስ 22፡31-32 አንብብ። ሀ) ጴጥሮስ ንስሐ ከገባ በኋላ ኢየሱስ ምን አለው? ለ) ሉቃስ 22፡62 አንብብ። ጴጥሮስ ኢየሱስን ከከዳ በኋላ ምን አደረገ?
ጥያቄ፡- ዮሐ 21፡17 አንብብ። ሀ) ኢየሱስ ጴጥሮስን መላልሶ «ትወደኛለህን» ብሎ በጠየቀው ጊዜ የጴጥሮስ መልስ እንዴት ነበር? ለ) ጴጥሮስ መልስ ከሰጠ በኋላ፥ ኢየሱስ ምን አለው?
ጥያቄ፡– 2ኛ ሳሙ 12፡13-14 አንብብ። ሀ) ነቢዩ ናታን ወደ ዳዊት ዘንድ ሄዶ ማመንዘሩንና ኬጢያዊ የነበረውን ኦርዮንን ማለገደሉን፥ በዚህም ኃጢአት መሥራቱን በነገረው ጊዜ ዳዊት ምን ብሎ መለሰ? ለ) እግዚአብሔር ለዳዊት ምን ሲል መለሰለት? ሐ) ዳዊት በሠራው ኃጢአት ምክንያት እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ ቀጣው?
ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 11፡29-30 አንብብ። አንዳንድ የቆርንቶስ አማኞች በምን ምክንያት ታምመው ሞቱ?
ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 3፡12-15 አንብብ። ሀ) አንድ ሰው ሕይወቱን በወርቅ፡ በብርና በከበረ ድንጋይ ቢነሳ ምን ይሆናል (ቁ 14)? ለ) አንድ ሰው ሕይወቱን በእንጦት፥ በገለባና በድርቆሽ ቢገነባ ምን ይሆናል (ቁ 15)?
በኃጢአት ወድቀው በኋላ ኃጢአተኝነታቸው ለለ ተሰማቸው ንስሐ ገብተው ወደ ቀድሞ መልካም ሕይወታቸው በመመለስ እውነተኛ አማኞች መሆናቸውን ያሳዩ፡ በዚህም ተግባራቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የታወቁ አርአያ የሆኑ ሁለት ሰዎች ጴጥሮስና ጳዊት ነበሩ፡ ጴጥርስ ኢየሱስን ሦስት ጊዜ ካደው። ከመካዱም በፊት ተጸጽቶ ንስሐ እንደሚገባ ኢየሱስ ከነገረው በኋላ፥ በሚመለስበት ጊዜ ወንድሞቹን እንዲያጽናናቸው አሳስቦታል። እንደዚሁም ከመክዳቱ በፊት ኢየሱስ ሌሎች ደቀ መዛሙርትን የጥርስ ወንድምች በማለት ጠርቷቸዋል። ጌታ ኢየሱስ ጴጥሮስ በኃጢአት ውስጥ እንደሚወድቅ የሚያውቅ ቢሆንም፥ ጴጥሮስ በውስጡ የነበረውን እውነተኛ እምነት ኢየሱስ ያረጋግጥለት ነበር። ጴጥሮስም በኢየሱስ ላይ የነበረውን እምነት ልባዊ በሆነ ንስሐ ገልጦታል። ኢየሱስም የጴጥሮስን እውነተኛ እምነት፥ እንደሚወደው በነገረው ጊዜና እንዲያገለግለው ባሳሰበው ወቅት መስክሮለታል (ዮሐ 21፡17)። ዳዊት ደግሞ ኃጢአት በመሥራቱ ምክንያት በእግዚአብሔር የተሠጻ ሌላው ሰው ነው። ዳዊት አመንዝሯል፥ ደግሞም ኬጢያዊውን ኦርዮንን አስገድሏል። ነገር ግን ነቢዩ ናታን ወደ እርሱ ዘንድ ቀርቦ ስለፈጸመው ኃጢአት በነገረው ጊዜ፥ ወዲያውኑ ኃጢአቱን በመናዘዝ በእግዚአብሔር የሚያምን እውነተኛ ሰው መሆኑን አሳየ። እግዚአብሔርም በናታን አማካይነት ኃጢአቱ የተሰረየለት መሆኑን አበሠረው። መዝሙር 51 ዳዊት ለእግዚአብሔር ያቀረበው የንስሐ ጸሎት ነው። ይህ የንስሐ ጸሎት ምንም እንኳን ኃጢአት ቢሠራ፥ በኃጢአቱ ተጸጽቶ በእውነት በንስሐ የሚመለስ ሰው መሆኑን መስክሮለታል። እግዚአብሔር ዳዊት፥ ከቤርሳቤህ የወለደው ልጅ እንዲሞት በማድረግ በሠራው ኃጢአት ገሥቱታል 2ኛ ሳሙ. 12፡14-18)። ትዕማር የምትባለው ልጃገረድ ተገድዳ መደፈርዋና አቤሰሎም ያለከተለው ዐመፅ ሁሉ ዳዊት የፈጸመው የግብዝነት ኃጢአት ውጤት ነበር። በእርግጥ ዳዊት በኃጢአቱ ምክንያት ክፉኛ ተሠቃይቷል። ነገር ግን ደኅንነቱን አላጣም፡፡
በቆሮንቶስ በነበረች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኃጢአት የሠሩና ፍርዳቸውን የተቀበሉ የዚህ ምሳሌ የሚሆኑ ብዙ አማኞች ነበሩ። ምንም እንኳን እነዚህ ምእመናን ደኅንነታቸውን በዚህ ምክንያት ባያጡም፥ በኃጢአታቸው ምክንያት የእግዚአብሔርን ተግሣጽ ተቀብለዋል። በ1ኛ ቆሮ. 11፡29-30 ባለው ክፍል ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር፥ ከእነርሱ መካከል አንዳንዶቹ የታመሙት፥ ሌሎች ደግሞ የሞቱት የጌታን ሥጋና ደም ሳይገባቸው ስለተቀበሉ እንደ ነበረ አስጠንቅቋቸዋል። ክርስቶስን በማዕከልነት በመመልከትና ለክርስቲያን ወንድሞቻቸውና እኅቶቻቸው በማሰብ ፈንታ፥ የጌታን ቅዱስ እራት ለራሳቸው ሥጋዊ እርካታና ለስካር አደረጉ። ስለዚህ እግዚአብሔር በበሽታና በሞት ቀጣቸው፡ የን ቀጣቸው እንጂ ደኅንነታቸውን አላሳጣቸውም። በ1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 3 ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ ሕይወታቸውን በወርቅ፥ በብርና በከበረ ድንጋይ የሚሠሩ እማኞች በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት በሚቀርቡበት ጊዜ ስለሚቀበሉት ሽልማት ይናገራል። እነዚህ ሁሉ በክርስቶስ ኃይልና ስለ ክብሩም የሚደረጉ የአገልግሎት ምልክቶች ናቸው። ሌሎች ደግሞ ሕይወታቸውን በእንጨት፥ በገለባና በድርቆሽ ይሠራሉ። እነዚህ ደግሞ በራሳችን ኃይልና ለራሳችን ክብር የሚሠሩ ሥራዎች ምልክቶች ናቸው። ጳውሎስ እነዚህ ለራሳችን የሚከናወኑ ተግባራት በክርስቶስ ዙፋን ፊት ይቃጠላሉ ይላል። ለራሳቸው የሚኖሩ አማኞች፥ በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት `የዘላለም ሕይወት ስለማይኖራቸው ሽልማትንም ሊያገኙ አይችሉም። ነገር ግን አሁንም የመዳን ዕድል አላቸው። ኑርአቸው ኪሳራ ብቻ ይሆናል፣ ነገር ግን ዘላለማዊ ደኅነንታቸውን አያጡም፡፡
3. ክርስቲያንነታቸውን በመናገር በአንጻሩ የእውነተኞች ክርስቲያኖችን ሕይወት የማይኖሩ ሰዎች፥ ዳግም የተወለዱ ወይም ያልተወለዱ መሆናቸውን ሌሎች አማኞች ለይተው ሊያውቁ አይችሉ ይሆናል።
ጥያቄ፡– 2ኛ ቆሮ. 13፡5 አንብብ። ጳውሎስ የቆሮንቶስ ሰዎች እንዲያደርጉ ነገራቸው?
እያንዳንዱ ግለሰብ በእውነት ዳግም የተወለደ ክርስቲያን መሆኑንና አለመሆኑን በእርግጥ ያውቃል። እኛም ብንሆን በክርስቶስ የምናምን ወይም የማናምን መሆናችንን እናውቃለን። እግዚአብሔርም በሰጠው ተስፋ፥ ወልድ ያለው ሕይወት አለው ብሏል (1ኛ ዮሐ 5፡12)። ሆኖም፥ አንድ ክርስቲያንነቱን ያሳወቀ ግን በኃጢአት ውስጥ የሚኖር፥ በዚህም ለክርስቶስ የገባውን ቃል ኪዳን ያፈረሰ ሰው በእውነት ዳግም የተወለደ ይሁን አይሁን መሥፈርታችንን በቀኖና ላይ በማድረግ እንኳ ለማወቅ አንችልም። እንደዚሁም አንድ ሰው ክርስቲያንነቱን ያሳውቅ፥ ግን ዳግም ያልተወለደ ወይም እውነተኛ ክርስቲያን ሆኖ ወደ ኃጢአት ሸርተት ያለ፥ ግን በመጨረሻ ንስሐ ገብቶ የሚመለስ መሆኑን ለይተን በእርግጠኝነት መናገር አንችልም። ከዚህም በስተቀር ወንድም ወይም እኅት በክርስቶስ የነበሩ፥ ኋላ ግን ከጌታ የራቁ፥ በይሁዳ ወይም በጴጥሮስ ደረጃ ይመደቡ ወይ አይመደቡ ፍጹም ልናውቅ አንችልም።
በ2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5 ውስጥ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሲናገር፥ በእምነት ቆመው እንደሆነ ራሳቸውን እንዲመረምሩ ያስጠነቅቃቸዋል። ጳውሉላ በቆርንቶስ ውስጥ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሏል። በግልም በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የነበሩ አብዛኛዎቹን ምእመናን ያውቃቸው ነበር። ሁሉም ራሳቸውን ክርስቲያን አድርገው የሚቆጥሩ መሆናቸውን ያውቅ ነበር። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ ወደ ብዙ ዓይነት ኃጢአት ተንሸራትታ ገብታ ነበር። እነዚህም መከፋፈል፥ የሞራል ውድቀት፥ ስካርና በጸጋ ስጦታዎች አላግባብ መጠቀም ነበሩ። እርሱም ከጎበኛቸውና ሁለት መልእክቶችን ክጻፈላቸው በኋላ፥ በ2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5 ውስጥ ከመካከላቸው እነማን ዳግም እንደ ተወለዱና ማንኛቸውም ራሳቸውን እንደ ክርስቲያን እንደሚቆጥሩ የማያውቅ መሆኑን ይጠቅሳል። ስለዚህ በአጠቃላይ በእውነት ጌታ እንደ መድኅናቸው አድርገው በእውነት ያውቁት እንደሆነ ራሳቸውን በራሳቸው እንዲመረምሩ ያሳስባቸዋል። ጌታ ኢየሱስ በውስጣቸው ስለሚኖር ንስሐ እንዲገቡ ያስጠነቅቃቸዋል። ጳውሎስ ራሱ እንደ እውነቱ ከሆነ፥ ከቆሮንቶስ ምእመናን ውስጥ የትኞቹ በእውነት ዳግም የተወለዱና በአንጻሩ በኃጢአት ውስጥ የሚኖሩ ሐሰተኞች ክርስቲያኖች እንደሆኑ አያውቅም ነበር።
ጥያቄ፡- ቢያንስ አንድ ራሱን እንደ ክርስቲያን የሚጥርና ቀን እንደ እውነተኛ ክርስቲያን የማይኖር የምታውቀውን ሰው ስም ጻፍ። እንዲህ ካለው ሰው ጋር እንዴት አድርገህ ልትወያይ ትችላለህ?
ሐዋርያው ጳውሎስ የቆሮንቶስን ምእመናን ሁኔታ በታዘበ ጊዜ የተሰማው ስሜት፥ ክርስቲያን ነኝ እያለ በኃጢአት ውስጥ የሚኖር ክርስቲያን በሚያጋጥመን ጊዜ እኛንም የሚሰማን ስሜት ነው። ስለዚህ እኛም ራሳቸውን እንዲመረምሩ ልንለምናቸው ይገባል። ስለዚህ እንዲህ እንበላቸው፥ ወንድም (እኅት) ክርስቲያን ነን ትላላችሁ። ነገር ግን እንደ ክርስቲያን አትኖሩም። ራሳችሁን ደህና አድርጋችሁ መርምሩ በእውነት ክርስቲያኖች ከሆናችሁ ጌታ ኢየሱስ በውስጣችሁ እንደሚኖር አታውቁምን? ንስሐ መግባት አለባችሁ፥ በዚህም ራሳችሁን ከእርሱ ጋር ማስታረቅና ሰላማውያን መሆን ይኖርባችኋል። ግን ወንድሜ እኅቴ) በእርግጥ ልትገነዘቡት የሚገባችሁ ቁም ነገር በእውነት ዳግም ተወልዳችሁ እንደሆነ ነው። ስለዚህ ለክርስቲያኖች በተፈቀደው ሁኔታ ስለማትኖሩ፥ ክርስቶስን በእምነት እንደ ቀል መድኃኒታችሁ ተቀብላችሁ የምትኖሩ ስለ መሆናችሁ ራሳችሁን ልትመረምሩና እርግጠኞች ልትሆኑ ይገባል።»
4. እምነታቸውን በይፋ በማሳወቅ፥ ራሳችውን ክርስቲያን ብለው የሚጠሩ፥ በእውነት አማኞች መሆናቸውን እንዲመራምሩ፥ ወይም ክርስቲያኖች በእምነታቸው እንዲጠነክሩ እንጂ ወደ ኃጢአት እንዳይወድቁ፥ ማስጠንቀቂያ የሆነ ትምህርትን የሚሰጡ ጥቅሶች።
4.1 ክርስቲያኖች ደኅንነታቸውን የሚያጡ የሚመስል ትምህርት ለክርስቲያኖች የሚያቀርቡ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍለ ምንባቦች፥ ለክርስቲያኖች ማስጠንቀቂያ የሚሰጡ ናቸው።
ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 9፡27 አንብብ፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በክርስትና አገልግሎቱ ላይ ከውድድር ውጪ እንዳይሆን በሰውነቱ ላይ ምን ማድረግ ነበረበት?
ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 10፡11-13 አንብብ። ሀ) ተረጋግተው የቀሙ የሚመስላቸው አማኞች ምን ዓይነት ስሜት አላቸው? ለ) አማኞች በሚፈተኑበት ጊዜ፥ ፊታቸውን \ ወዴት ይመልሱ?
ጥያቄ፡- ዮሐ 15፡1-8 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር ፍሬ የማያፈሩትን ቅርንጣፎች ምን ያደርጋቸዋል? (ቁጥር 2ና 6) ለ) ደቀ መዛሙርት ፍሬ እንዲያፈሩ ምን ማድረግ አለባቸው? (ቁጥር 4ና 5) ሐ) አንድ አማኝ ፍሬ ማፍራቱ ምንን ይገልጣል? (ቁጥር 8)
ክርስቲያኖች ደኅንነታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ የሚያስተምሩ አንዳንድ ክፍለ–ምንባቦች፡ ክርስቲያኖች የንጽሕናና የቅድስና ሕይወት እንዲኖሩ እንጂ ወደ ኃጢአት እንዳይወድቁ ከዚህም በስተቀር፥ በእምነታቸው እንዲጠነክሩ የሚያስጠነቅቁ ናቸው። እንደዚሁም በሚሠሩት ኃጢአት እግዚአብሔር ክፉኛ ለለግላቸው የሰማይ ሽልማታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ የሚያሳስቡ ናቸው፡፡
በ1ኛ ቆርንቶስ ምዕራፍ 9 ውስጥ ጳውሎስ ስለተጣለበት የኃላፊነት ተግባር ይናገራል፡ እርሱም ምንም እንኳን ብዙ መብቶች ቢኖሩትም፥ በመንግላዊነት ሥራው የበለጠ ውጤታማ ለመሆን በመምረጥ በመብቶቹ ሁሉ መጠቀምን አልፈለገም። በቁጥር 27 ውስጥ፥ እርሱ ኃላፊነትና የአገልግሎት ተግባሩን ከሩግ ተወዳዳሪ ተግባር ጋር አመሳስሉታል። አንድ ሯጭ አካሉን በጠንካራ ሥልጠና ሥር እንደሚያስገዛ ሁሉ፥ ስለ ጌታ የሚያደርገው ምስክርነት ወደፊት ገፍቶ ውጠታማ ይሆንለት ዘንድ፥ ሐዋርያው ራሱን በመቆጣጠር ከሌላው ነገር ሁሉ ሊመላነው ችሏል። በክርስትና ሕይወቱ ውስጥ ራሱን መቆጣጠርና በሥርዓት መያዝ ሲያቅተው ኖሮ፥ ከውጤታማ ወንጌላዊነትና ሐዋርያነት ተግባር ብቃት አጥቶ ከውድድር ውጭ በሆነ ነበር። በዚህ ፈንታ ጳውሎስ አቅሙ የፈቀደለትን በከፍተኛ ደረጃ ለክርስቶስ አገልግሎቱን ለማቅረብ እንዲችል፥ በሕይወቱ ሁሉ ራሱን በሥነ ሥርዓት በመምራት ራሱን ለጌታ አስገዛ።
በ1ኛ ቆሮንቶስ 10፡11-13 ውስጥ፥ ጳውሎስ ክርስቲያኖች በሕይወታቸው ውስጥ ትምክህት እንዳይኖርባቸው አስጠነቀቃቸው። ከቁጥር 1-10 ባለው ጥቅስ እንደተገለጠው እስራኤላውያንን ምሳሌ በማድረግ እነርሱም ቢሆኑ በኃጢአት ውስጥ ወድቀው፥ እንደ እስራኤላውያን ሁሉ፥ የእግዚአብሔር ተግጽ ሊደርስባቸው እንደሚችል አስጠንቅቋቸዋል። እዚህ ላይ ጳውሎስ የቆርንቶስን ሰዎች ባስጠነቀቃቸው ጊዜ፥ እነርሱ በኃጢአት ውስጥ ሲወድቁ ያገኙትን የደኅንነት በረከት የሚያጡ መሆናቸውን አልተናገራቸውም። ነገር ቀን ተሣጽ ሊደርስባቸው እንደሚችል አሳስቦአቸዋል። ሊያስጠነቅቃቸውም በኃጢአት ውስጥ በመውደቅ ፈንታ እግዚአብሔር በሚያዘጋጅላቸው መንገድ ከሚያጋጥማቸው ፈተና ለመውጣት መሞከር እንዳለባቸው አበክሮ ነግሮአቸዋል።
በዮሐንስ ምዕራፍ 15 ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ፍሪ ለማፍራት ቢፈልጉ በእርሱ ጸንተው መኖር እንዳለባቸው አሳስቦአቸዋል። በክርስ፥ለ ጸንቶ መኖር ማለት፥ ቃሉን በማጥናትን በጸሎት ጊዜን ማሳለፍ ማለት ነው ? በምናደርገው ተግባር ሁሉ በእርሱ ላይ መደገፍ፥ ቀኑን ሙሉ ስለ እርሱ ማሰብና ከእርሱ ጋር መነጋገርና ያላማቋረጥም ለእርሱ መታትን ማለት ነው። በዚህ ሁኔታ በኢየሱስ ጸንተው የማይኖሩ ደቀ መዛሙርት ምንም ዓይነት ፍሬ አፍርተው ሊታዩ አይችሉም። በሕይወታቸው ውስጥ የክርስትና ባሕሪ ማለትም እንደ መንፈስ ፍሬ ያለ ተካትቶበት ሊገኝ አይችልም (ገላ. 5፡22-24)። እንዲሁም ለክርስቶስ በሚያደርጉት አገልግሎት ውስጥ የተቃና ውጤት ለማየት አይችሉም። እንዲህ ባሉ አማኞች ላይ ምን ይደርስባቸዋል? ጌታ ኢየሱስ እንደሚለው «ይቆረጣሉ” (ቁጥር 2)፣ ከዚያም ወደ «እሳት» ይጣላሉ (ቁጥር 6)። እዚህ ላይ ጌታ ኢየሱስ እነዚህ ሰዎች ያገኙትን ደኅንነት ያጣሉ፣ ወይም በገሃነም ውስጥ ተጥላው ይቃጠላሉ አላለም። ለለ ወይኑ ንድና ስለ ቅርንጫፎቹ የጀመረውን ትምህርት ይቀጥላል። በንግግሩም ለአገልግሎት ስለማይበጁ በእግዚአብሔር ይሠጳሉ፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ወደ ጎን አድርጎ ያስቀምጣቸውና ከፈለገም ሕይወታቸውን ይወስዳል ነው ያለው። በአንጻሩም፣ ኢየሱስ የተናገረው በእርሱ ጸንተው የሚኖሩና ፍሬ የሚያፈሩ ደቀ መዛሙርት ለሌሎች እውነተኞች ደቀ መዛሙርቱ መሆናቸውን እንደሚያሳዩ ነው (ቁጥር 8)እንዲሁም ለጌታ ኢየሱስ ታማኞች መሆናችን የሚያሳየው ሌላው ነገር እኛ የእርሱ እውነተኞቹ ደቀ መዛሙርት እንደሆንና በዚህም ለአገልግሎት የሚጠቅሙ ብዙ ፍሬዎችን የምናፈራ መሆናችንን ነው። ሆኖም፣ በኢየሱስ ጸንተው የማይኖሩ አማኞች፥ ለእግዚአብሔር የሚጠቅም ምንም ዓይነት ተግባር ሊያከናውኑ አይችሉም። እንዲህ ያሉት ልክ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 3፡12-15 በገለጻቸው እማኞች ይሳላሉ፡ እነዚህ ሰዎች ከጌታ አገልግሎት ተገልለው እንዲቀመጡ ይደረግና ኋላም ተግሣጹውን ይቀበላሉ።
ጥያቄ፡- ክርስቶስን እንደ ል መድኃኒታችሁ ተቀብላችሁት ከሆነ፥ እግዚአብሔር በየትኛው የሕይወታችሁ ክፍል ነው ፈተናን ለመላ የእርሱን ኃይል እንድትች፡ እንዲሁም በመላ አቅማችሁ እንድታገለሉትና በጥንቃቀም በእርሱ ጸንታችሁ እንድትኖሩ የሚያስጠነቅቃችሁ? በዚህ አኳኋን እግዚአብሔር የሚያደርግላችሁን ማስጠንቀቂያ በማስታወሻ ደብተራችሁ ላይ ጻፉ።
4.2 ክርስቲያኖች ደኅንነታቸውን የሚያጡ የሚመስል አሳብ የሚያስተምሩ ክፍለ ምንባቦች ክርስቲያኖች ነን በማለት የሚናገሩ ሰዎች፥ በእርጥ ክርስቶስን እንደ መድኃኒታቸው አድርገው በመቀበል አምነውበት እንደሆነ ራሳቸውን እንዲመረምሩ ለማስጠንቀቅ ነው።
ጥያቄ፡- ዕብ 6፡4-6 አንብብ። ሰዎች የእግዚአብሔርን ኃይልና ቃሉን ቀምሰውና መንፈስ ቅዱስንም ተቀብለው ኋላ ሲወድቁ ምን ይደርስባቸዋል?
ጥያቄ፡- ራእይ 3፡1፣ 5 አንብብ። ሀ) የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን ዘና ምን ነበር? ለ) የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ሁኔታ እንዴት ነበር? እግዚአብሔር አሸናፊ ለሆነው ምንን ይሰጠዋል?
ጥያቄ፡- ራእይ 3፡17፡ 20 አንብብ። ሀ) በሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የነበሩ ምእመናን ስለ ራላቸው ምን ያስቡ ነበር? ለ) ስለ መንፈሳዊ ሁኔታቸው፥ እርጠኛው ነገር ምን ነበር? ሐ) ጌታ ኢየሱስ ልባቸውን ለሚከፍቱለት ምን ያደርላቸዋል?
ክርስቲያኖች ደኅንነታቸውን ሊያጡ ይችላሉ የሚል ትምህርት የሚያስተምሩ የሚመስሉ አንዳንድ ክፍለ ምንባቦች፥ ክርስቲያኖች ነን እያሉ፥ ግን ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው ላላመኑት፥ በእውነትም ማስጠንቀቂያዎች ናቸው። ውድቀታቸው የሚያሳየው፥ ገና ወደ ተሟላና እውነተኛ ወደ ሆነ የደኅንነት ተሞክሮ እንዳልደረሱ ስለሆነ፥ ወደተሟላው የደኅንነት ተሞክር ለመድረስ በጥንቃቄ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ነው።
የዕብራውያን መልእክት አንባቢዎች ራሳቸውን ክርስቲያን ብለው ያሳወቁ አማኞች ነበሩ፧ ጸሐፊውም እንደ አማኞች ቆጥሮ ጽፎላቸዋል። ነገር ግን ካሉበት ደረጃ ቢወድቁ፥ ይህ ቀድሞውንም በክርስቶስ አለማመናቸውን የሚያሳይ ምልክት መሆኑን በመንገር ያስጠነቅቃቸዋል። ስለዚህ በእምነታቸው በመጽናት፥ በእውነት በክርስቶስ መሆናቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። በዕብራውያን 6፡4-6 ስለ እግዚአብሔር እውነትና ኃይል ብዙ ተሞክሮ የነበራቸውና ኋላ ግን ከክርስቶስ ተለይተው የወደቁትን፥ ደግሞም በንስሐ ታድሰው ሊለወጡ ለሚችሉበት ዕድል ልባቸውን ያደነደኑትን ነበር ደራሲው የማስጠንቀቂያ ቃል የተናገረው፥ «ብርሃን ስለ በራላቸው፥ የመንፈስ ቅዱስ ተካፋዮች ስለ ሆኑና ሰማያዊውንም ስጦታ ስለ ቀመሱ፥ እንዲሁም የእግዚአብሔርን መልካም ቃልና የሚመጣውን ዓለም ኃይል ለቀመሱ» ሰዎች ነበር። እዚህ ላይ አንድ ማስተዋል ያለባችሁ ነገር፥ ጸሐፊው ሲናገር እነዚህ ሰዎች አምነዋል፥ ንስሐ ገብተዋል፥ ወይም ወደ እግዚአብሔር ተመልሰዋል አላለም። እነዚህ ሰዎች እውነተኛ ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች ናቸውም አላለም። «መቅመስ» የሚለው ቃል አንድ ምግብን መቅመስ እንጂ መዋጥን አያመለክትም። አንዱን ምግብ መቅመስና መትፋት ሊሆን ይችላል። ጸሐፊው ሰዎች የእግዚአብሔር እውነት ቢቀምሱና ራሳቸውን ከክርስቲያኖች ጋር ከቆጠሩ በኋላ የተማሩትንና የተገነዘቡትን ቢተዉ፥ ልባቸውን ለወንጌል የዘጉ በመሆናቸው ሊቀበሉ አይችሉም ማለቱ ነው። ሰዎች ፈውስን በማግኘት፥ የትንቢትን ቃል በመስማት፥ ወይም መንፈስ ቅዱስ ለንስሐ በልባቸው ውስጥ ሊሠራ እየተሰማቸው ኋላ ችላ ብለው በተዉትና ወደ ውድቀት ቢሄዱ፥ ልባቸውን ያጸኑ በመሆናቸው ንስሐ ሊገቡና ወደ ክርስቶስ ሊመጡ ከቶ አይችሉም። ስለዚህ የዕብራውያን ምዕራፍ 6 ቃል፥ ራሳቸውን ክርስቲያን ብለው የሚጠሩ ሁሉ ከኃጢአታቸው በንስሐ ተመልሰው ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው ለመቀበላቸው እርግጠኞች ሊሆኑ ይገባል።
በራእይ 3፡5 ውስጥ ኢየሱስ ለሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን ጠበቅ አድርጎ ይናገራል። ምንም እንኳን ብዙዎቻቸው ክርስቲያንነታቸውን የሚናገሩ ቢሆኑም (የቤተ ክርስቲያኒቱም አባላት ነበሩ)፥ ኢየሱስ ቀን ብዙዎቻቸው በመንፈስ ሙታን እንደ ነበሩ ነግሮአቸው ነበር። በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የነቁና ዝናን ያተረፉ ይመስሉ ነበር፤ ሐቁ ግን አብዛኛዎቹ በመንፈስ ሙታን ነበሩ። ምንም እንኳን በዚያች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው ያውቁ የነበሩ ጥቂቶች ሰዎች ቢሆኑም (ቁጥር 4)፣ አብዛኛዎቻቸው ድል መንሣት ያስፈለጋቸው፥ ስሞቻቸው ከሕይወት መጽሐፍ እንዳይደመሰሱ ነበር። በራእይ ከምዕራፍ 2-3 ድረስ ባሉት ክፍሎች «ድል የነሡት» የሚለው ቃል በተለይ የሚያመለክተው በእውነት ዳግም ለተወለዱ ክርስቲያኖች ነበር። እንዲያው ብቻ የተለያዩ መንፈሳውያን የክርስቲያን ቡድኖች ለማመልከት ሳይሆን በጥቅም ላይ የዋለው፥ ዓላማው በእውነት ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው አድርገው ላወቁት ክፍሎች ነበር ፣ (ራእይ 2፡7፥ 11፥ 17፥ 26፤ 3፡5፥ 12፥ 21 ተመልከት)። ጌታ ኢየሱስ ድል የነሡ ስሞቻቸው ከሕይወት መጽሐፍ አይደመሰሱም ሲል ምን ማለቱ ነው? ከዳኑና በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ከተጻፉ በኋላ ያንን ደኅንነት ማጣት ይቻላል ማለቱ ነው? ኢየሱስ ከሕይወት መጽሐፍ ላይ ስለ መደምሰስ የሚናገረውን አሳብ ያገኘው ከብሉይ ኪዳን ውስጥ ነው። ይህ ከሕይወት መጽሐፍ ላይ መደምሰስ የሚለው አሳብ፥ አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር አድርገው ነገር ግን በእውነት ከእነርሱ ጋር ያልሆኑትን የሚጠቁም ምሳሌያዊ አሳብ ነው። ዳዊትም በመዝሙር 69፡28 ላይ በውጫዊው ሁኔታዎች የእግዚአብሔር ሰዎች መስለው፥ በውስጣዊ ሕይወታቸው ግን ጨርሶ የእግዚአብሔር ወገኖች ስላልነበሩት ሲገልጽ፥ በተመሳሳይ ምሳሌያዊ ሃሳብ ተጠቅሞአል። በኦሪት ዘጸአት 32፡33 ደግሞ እግዚአብሔር፥ ከእስራኤል ጋር ከግብፅ ወጥተው የመጡና በውጪአቸው የእግዚአብሔር ሰዎች የሚመስሉ፥ በተቃራኒው ግን በውስጣቸው ራሳቸውን የእርሱ ያላደረጉትን ወገኖች ከመጽሐፉ እንደሚደመስሳቸው ለሙሴ ነግሮት ነበር። በተመሳሳይ መንገድ፥ በሰርዴስ ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር ያመሳስሉ የነበሩ፥ ግን የእግዚአብሔር ሰዎች ያልሆኑ ነበሩ። በዚህ በሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን የነበሩ ሰዎች በክርስቶስ አምነው እርሱን እንደ መድኃኒታቸው የተቀበሉ ለመሆናቸው ራሳቸውን እንዲመረምሩ እንጂ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል በመሆን ብቻ ራሳቸውን ከሌሎቹ ምእመናን ጋር በማመሳሰል ብቻ እንዳይኖሩ ያስጠነቅቃቸዋል።
ራእይ 3፡16 ስለ ተመሳሳይ እውነት ያስተምራል። በራእይ 3፡14-22 ውስጥም በአብዛኛው ከሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን ጋር ተመሳሳይ ለሆነችው ለሎዶቂያ ቤተ ክርስቲያንም ኢየሱስ ይናገራል። በሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን የነበሩ ምእመናን በመንፈሳቸው የበለጸጉ ይመስላቸው ነበር። ነገር ግን እውነቱ፥ በመንፈሳቸው ድሆች፥ ዓይነ-ሥውራን እና የተራቆቱ ነበሩ (ቁጥር 17)። በመንፈሳቸው ሙቅ (ጋል ያሉ) ወይም ቀዝቃዛ (አርኪ) አልነበሩም። ያም ሆኖ ትዕቢተኞችና በራሳቸው የሚመኩ ስለነበሩ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምንም ነገር እንደማያስፈልጋቸው አድርገው ያስቡ ነበር። ምንም እንኳን በውጪአቸው ቤተ ክርስቲያን ቢመስሉም፥ በውስጣቸው ግን እውነተኛ ቤተ ክርስቲያን አልነበሩም። ፍላጎታቸውን ብቻ የሚያውቁ፣ ራሳቸውን ክርስቲያኖች ነን የሚሉና ራሳቸውን በትሕትና በጌታ ፊት የሚያቀርቡ፥ ጌታ ኢየሱስንም ወደ ልባቸውና ወደ ሕይወታቸው እንዲገባ የሚጋብዙ ናቸው (3፡20)። ጌታ ኢየሱስን ወደ ልባቸው ባይጠሩትና ድል አድራጊዎች ባይሆኑ ኖሮ፥ ሊድኑ አይችሉምና እግዚአብሔርም ይጥላቸው ነበር።
ጥያቄ፡- እስቲ ትንሽ ቆም ብላችሁ ስለ ራሳችሁም ሕይወት አስቡ። ክርስቶስን በእውነት ተቀብላችሁ፥ አዳኛችሁ አድርጋችሁታል፥ ወይስ ራሳችሁን የቤተ ክርስቲያን አባል በማድረግ ብቻ በማስመሰል ትኖራላችሁ? ክርስቶስን በእውነት አምናችሁ በመቀበል መድኃኒታችሁ አድርጋችሁት ከሆነ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት፥ አወድሱት! በሌላ በኩል በውጫዊው በኩል ክርስቲያን በመምሰል ወደ ቤተ ክርስቲያን የምትመላለሱ ከሆናችሁና በእውነት በክርስቶስ አምናችሁ እንደ አዳኛችሁ በማድረቅ ያልተቀበላችሁት ከሆነ፥ ባለፈው ጊዜ ወደ አጠናችኋቸው አራት ትምህርቶች ተመለሱና አሰላስሉ። በመሆኑም አሁኑኑ ክርስቶስ አዳኛችሁ መሆኑን እመኑ!
4.3 ክርስቲያኖች ደኅንነታቸውን የሚያጡ የሚመስል ትምህርት የሚያቀርቡ አንዳንድ ክፍለ ምንባቦች የሚያስተምሩት ጽናት በእውነት የዳኑ ሰዎች ምልክት መሆኑን ነው።
ጥያቄ፡- ቆላ. 1፡21-23 አንብብ። ሀ) የቆላስይስ ሰዎች ቀድሞ በምን አኳኋን ይኖሩ ነበር? (ቁጥር 2) ለ) እግዚአብሔር ምን አደረገላቸው? (ቁጥር 22) ሐ) የቆላስይስ ሰዎች በእውነት የታረቁ ለመሆናቸው ምስክሩ ምን ነበር? (ቁጥር 23)
ጥያቄ፡- ማቴ 24፡12-13 እንብብ። ሀ) በታላቁ መከራ ጊዜ በብዙዎች ላይ ምን ይደርሳል? ለ) እስከ መጨረሻው ድረስ የሚጸኑ ምን ይሆናሉ?
አንዳንድ ክርስቲያኖች ደኅንነታቸውን እንደሚያጡ ዓይነት የሚያስተምሩ ከፍለ ምንባቦች የሚያስተምሩት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ጽናትና ታማኝነት፥ በእውነት ዳግም የተወለዱትና የዳኑት ምልክት መሆኑን ነው።
በቆላስይስ 1፡21-23 ውስጥ ጳውሎስ፥ የቆላስይስ ሰዎች በአንድ ወቅት ከእግዚአብሔር ተለይተው እንደ ነበሩ ያስታውሳቸዋል። አሁን ግን ስለ ታረቁ በእግዚአብሔር ፊት ቅዱሳንና ጻድቃን ሆነው ቀርበዋል። ሆኖም በእርግጥ የታረቁ ለመሆናቸው እና ቅድስናንና ጽድቅን ለማግኘታቸው ማስረጃው ምንድን ነው? በእምነታቸው ይቀጥላሉ። በክርስትና ሕይወታቸው መጽናታቸው ራሉ ከእግዚአብሔር ጋር የመታረቅ ምልክታቸው ነው። ማስታወስ ያለባችሁ ጳውሎስ በእምነታቸው ቢቀጥሉ ይታረቃሉ አለማለቱን ነው። ሐዋርያው ያለው የቆላስይስ ሰዎች በእምነታቸው ቢቀጥሉ አስቀድመው ድነዋል ነው። ቁጥር 23 ለመዳን በእምነታቸው መቀጠል አለባቸው ሳይሆን የሚለው፣ በእምነት መጽናታቸው፥ እግዚአብሔር ያዳናቸው ለመሆኑ ማስረጃ ነው፡ ነው። በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ጽናት ሰውን አያድነውም፥ በመሠረቱ ጽናት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ አንድ ሰው የመዳኑና በእውነት ዳግም የመወለዱ ምልክት ነው።
በማቴዎስ 24፡12-13 ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ተመሳሳይ አሳብ ያስተምረናል። በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24-25 ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ወደፊት ሊመጣ ስላለው የስራ ጊዜ ይናገራል፡ በሚመጣው የመከራ ጊዜ፥ ብዙ ክርስቲያኖች ነን ሲሉ የነበሩ ሰዎች ከክፋታቸውና የክርስቶስን ፍቅር በማጣታቸው ጌታን አለማወቃቸውን እንደሚገልጹ ጌታ ተናግሯል። ነገር ግን በክርስቶስ ታምነው የጸኑትና እርሱን የሚያውቁት ይድናሉ። በክርስቶስ ታምኖ መኖር ራሱ አንድ ሰው በእውነት የዳነ ለመሆኑ ምስክር ነው።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
