ጥያቄ፡- ሀ) ራእይ 19፡10 አንብቡ። ሐዋርያው ዮሐንስ ለመልአኩ ሊሰግድ ወ መሬት በተደፋ ጊዜ፥ መልአኩ ምን አደረገ? ሊሰገድለት የሚገባው ብቸኛው ማ ነው አለ? ለ) ዕብራውያን 1፡6 እንብቡ። መላእክት ልጁን ምን እንዲያደርጉ ታዘዙ
ሐ) ፊልጵስዩስ 2፡9-11 አንብቡ። ሰመጨረሻው ላይ ሕዝቦች ሁሉ በኢየሱስ ፊት ምን ያደርጋሉ?
በራእይ 19፡10 ላይ እንደ ተገለጸው ሐዋርያው ዮሐንስ መልአኩን ስላየ በተናገረውም ቃል ስለተሸነፈ፥ ሊሰግድለት እግሮቹ ሥር ወደቀ። ነገር ግን መልአኩ ወዲያውኑ ገሠጸው። ከዚያም ልክ እንደ ሐዋርያው ዮሐንስ እርሱ ከእግዚአብሔር አገልጋዮች መካከል አንዱ መሆኑን አስረዳው። ሊሰገድለት የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
በዕብራውያን 1፡6 ውስጥ መላእክት ለማን መስገድ እንዳለባቸው ነa የተነገረው? መላእክቱ የተነገራቸው ለልጁ እንዲሰግዱ ነው፤ እርሱም ኢየሱ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ በፊልጵስዩስ 2፡9-11 ሰመጨረሻው ጊዜ የሰa ልጆች ሁሉ በፊቱ በጉልበታቸው ተንበርክከው ይሰግዳሉ ይላል። ቅዱሳ’ መላእክት ለኢየሱስ ሰግደውለታል። የሰው ልጆች ሁሉ ይሰግዱለታል እንግዲህ ኢየሱስ እግዚአብሔር አምላክ ለመሆኑ ይህ ግልጽ ማስረጃ ነው፡፡
ጥያቄ፡– በዚህ ሳምንት ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር የምታመልኩትን አንድ መንገድ በጽሑፍ ግለጹ።
ጥያቄ፡- አንድ አማኝ ካልሆነ ወዳጃችሁ ጋር ተዛማጅነት ያለው የኢየሱስ መለኮታዊ ባሕርይ የትኛው ነው? በዚህ ሳምንት ያንን ባሕርይ ለወዳጃችሁ ለማካፈል ዕቅዱን በጽሑፍ ግለጹ።
ጥያቄ፡- ከዚህ ትምህርት ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ባሕርያት እንዳሉትና እግዚአብሔር የሚያደርገውን ሥራ እንደሚሠራ የሚገልጹ ሁለት ጥቅሶችን በቃል እጥኑ።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
