ትናንትና መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው በሚልበት ጊዜ ምን ማለቱ እንደሆነ ማጥናት ጀምረን ነበር። በዚሁ ጊዜም፥ «የእግዚአብሔር ልጅ» የሚለውን መጠሪያ ትርጉም በብሉይ ኪዳንና በወንጌሉች ውስጥ ምን ማለት እንደሆነ ተመልክተናል። ዛሬ ደግሞ «የእግዚአብሔር ልጅ» የሚለው መጠሪያ በጳውሎስና በዮሐንስ መጻሕፍት ውስጥ እንዴት እንደ ተብራራ በመመልከት ጥናታችንን እንቀጥላለን።
3. «የእግዚአብሔር ልጅ» እንደ ጳውሎስ አጻጻፍ
3.3 የእግዚአብሔር ልጅ እኛን ለማዳን መጣ።
ጥያቄ፡- ሮሜ 1፡3-4 አንብቡ። ሀ) የጳውሎስ መልእክት ስለ ምንድን ነው? ለ) ትንሣኤው ስለ ክርስቶስ ምንን ገለጠ?
ጥያቄ፡- ሮሜ 5፡10 አንብቡ። የእግዚአብሔር ልጅ ሞት ምን አደረገልን?
ጥያቄ፡– ሮሜ 8፡3-4፤ ገላትያ 4፡4 አንብቡ። እግዚአብሔር ልጁን በምን ምክንያት ላከ?
ጥያቄ፡- ቆላስይስ 3፡13 አንብቡ። እግዚአብሔር ወደ የትኛው መንግሥት አመጣን? ( 31ኛ ጥያቄ፡- 1ኛ ተሰሎንቄ 1፡10 አንብቡ። ልጁ ከምን ያድነናል?
ሐዋርያው ጳውሎስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ ሲጽፍ፥ የእግዚአብሔር ልጅ ለእኛ ስለሚያደርገው ተጨባጭ መንፈሳዊ ተግባር አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል። ልጁ እኛን የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች ያደርገናል። ብዙ ጊዜ ጳውሎስ ልጁ ስለሚያደርግልን ሁለት ነገሮች ይናገራል። በመጀመሪያም ልጁ እኛን ለማዳን እግዚአብሔር የላከው ስለ መሆኑ ነው። ጳውሎስ የሰበከው ወንጌል ወይም የምሥራች የእግዚአብሔር ልጅ ወንጌል ተብሎ ሊጠቃለል ይችላል (ሮሜ 14)። የክርስቶስ ትንሣኤ ለሁሉም እርሱ አንድ አምላክ የላከው ስለ መሆኑ፥ የእግዚአብሔር ባሕርይ ያለውና ለሰው ልጆች ሁሉ የተዘጋጀ የደኅንነት መንገድ መሆኑን ይገልጻል (ሮሜ 1፡4)። እኛን ሁላችንን ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀን፥ የልጁ ሞት ነው (ሮሜ 5፡10)። ምክንያቱም ሕግ እኛን ሊያድነን ስላልቻለ፥ እግዚአብሔር የሙሴ ሕግ ሊፈጽመው ያልቻለውን ተግባር እንዲፈጽም ልጁን ላከው። እርሱም የኃጢአት መሥዋዕት በመሆን፥ ከኃጢአት ሕግና ከሞት ነፃ ሊያወጣን ተላክ (ሮሜ 8፡3፤ ገላትያ 4፡4)። የእግዚአብሔር ደኅንነት ከጨለማ መንግሥት አውጥቶ ወደ ልጁ መንግሥት ያመጣናል። እንደ ዳንን በልጁ መንግሥት ውስጥ እንሆናለን ማለት ነው (ቆላስይስ 1፡13)። ለወደፊቱም የልጁ ወደዚህ ምድር ዳግም መምጣት እግዚአብሔር በምድር ላይ በሚያፈሰው ቁጣ ያድነናል (1ኛ ተሰሎንቄ 1፡10)።
3.2 የእግዚአብሔር ልጅ ሊቀድሰን መጣ።
ጳውሎስ ለሰዎች ሁሉ ደኅንነትን ያሰፈነ፥ የእግዚአብሔር ልጅ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ትኩረት ሰጥቶ ጽፎአል። እኛን የእግዚአብሔር ልጆች የሚያደርገን ልጁ ነው። ነገር ግን ጳውሎስ ልጁ እኛን እንደሚያድነን ብቻ አያስተምርም። እንደ እግዚአብሔር ሕዝቦች እርሱ የሕይወታችን ማዕከል መሆኑንም በአንክሮ ይናገራል። የሚቀድሰን እርሱ ነው።
ጥያቄ፡- ሮሜ 8፡29 አንብቡ። በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔር ዓላማ ምንድን ነው?
ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡9 እንብቡ። እግዚአብሔር ወደ ምን ጠራን?
ጥያቄ፡- ገላትያ 2፡20 አንብቡ። ጳውሎስ የነበረበትን ሥጋዊ ሕይወት እንዴት ኖረ?
ጥያቄ፡- ኤፌሶን 4፡12-13 አንብቡ። የክርስቶስ አካል ዕድገት ግቡ ምንድን ነው?
የእግዚአብሔር ልጅ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱ እኛን ለማዳን መጥቷል። ቅዱስ እንድንሆንና፥ በክርስቲያናዊ ሕይወታችን እንድናድግ ወደ እኛ የመጣ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር እኛን ያዳነበት ዓላማው እኛ በበለጠ ልጁን እንድንመስል ነው (ሮሜ 8፡29)። እንደዚሁም በልጁ አማካይነት ከእርሱ ጋር አንድነት እንዲኖረን ነው (1ኛ ቆሮንቶስ
1፡9)። እኛ በምንድንበት ጊዜ፥ ከክርስቶስ ጋር እንሰቀላለን፥ የነበረን አርጌውም ሰው ይሞታል። ምንም እንኳን አሮጌው ሰውነት ባይለየንም፥ አዲስ ሕይወትን ለመኖር አዲስ ኃይል እንቀበላለን። ይህም ኃጶላ፥ ያለማቋረጥ በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ካለን እምነት የሚመነጭ ነው። በእዚእብሔር ልጅ ላይ ያለን እምነት፥ አዲስ ዓይነት ሕይወት የምንኖርበትን ኃይል ይሰጠናል (ገላትያ 2፡20)። የክርስቶስ አካል የበለጠ ሲያድግ ከእግዚአብሔር ልጅ ጋር ባለው አንድነትና ስለ እርሱ ባለው እውቀትም ያድጋል (ኤፌሶን 4፡12-13)። የእግዚአብሔር ልጅ እኛ ሕዝቦቹ እርሱ ያዘጋጀልንን አዲስ ሕይወት እንድንኖር ወደ እኛ ዘንድ የመጣ ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
ጥያቄ፡– በመጨረሻ ው አንቀጽ ላይ ወደ አጠናናቸው ክፍሎች መለስ ብላችሁ ተመልከቱ። በክርስቲያናዊ ሕይወታችሁ እያደጋችሁና እየበሰላችሁ በመሄድ ክታዛችሁባቸው መንገዶች ጥቂቶቹ ምንድን ናቸው?
በጥንት ታሪክ አንድ ገዥ ሕዝቡን ለማዳንና ለመንከባከብ ኃይል እንዳለው ለመግለጽ ልጁን ወክሎ መላኩ የተላመደ ነገር ነበር፡፡ በተመሳሳይ መንገድ እግዚአብሔር ልጅ የሆነውን ኢየሱስን ልኮ ሕዝቡን እንዳዳነ፥ ሕዝቡም እንደ እርሱ ይኖሩ ዘንድ ላለያቸውና ኃይላቸው፥ ወደ እግዚአብሔርም የሚያደርስ መንገዳቸው እንደሆነ፥ ሐዋርያው ጳውሎስ አጽንኦት ሰጥቶ ጽፎታል።
4. «የእግዚአብሔር ልጅ» በዮሐንስ ጽሑፍ ውስጥ
ሐዋርያው ዮሐንስ የእግዚአብሔር ልጅ” የሚለውን ስያሜ ከማናቸውም የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ይልቅ ደጋግሞ ይጠቅሰዋል፡ ይህ ስያሜ ኢየሱስን እጅ አዘውትር ከሚገልጽባቸው መንገዶች አንዱ ነው። የሰው ልጅ የሚለውን መጠሪያ ዮሐንስ መጠቀሙ በሌሎች የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ዘንድ የተመለከትናቸውን ብዙዎቹን ጭብጦች ደጋግሞ ያነግልናል። ነገር ግን ዮሐንስ በእግዚአብሔር ልጅና በእግዚአብሔር አብ መካከል ያለውን የቅርብ ግንኙነት በመግለጽ ረገድ ከሁሉም ልቆ ይሄዳል።
4.1 የእግዚአብሔር ልጅ መሢሑ ነው።
ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡49 አንብቡ፡ ኢየሱስ ናትናኤልን ገና በበለሊቱ ዛፍ ሥር በነበረ ጊዜ እንዳየው ከነገረው በኋላ፥ ናትናኤል ስለ ኢየሱስ የግለጻቸው ሁለት ነገሮች ምን ነበሩ?
ጥያቄ፡– ዮሐንስ 1፡27 አንብቡ። ማርታ ስለ ኢየሱስ አምናለሁ ያለቻቸው ሁለት ነገሮች ምን ነበሩ?
ጥያቄ፡– ዮሐንስ 20፡31 አንብቡ። ሀ) ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ማመን የሚያስፈልጉን ሁለት ነገሮች ምንድን ናቸው አለ? ላ) በእዚህ ሁለት ነገሮች ማመን ውብቱ ምንድን ነው?
ዮሐንስ ኢየሱስን «የእግዚአብሔር ልጅ ብሎ ሲጠራው የመጀመሪያውና ሊል የፈለገው ነገር ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን ነው። ኢየሱስ ናትናኤል በበለሲቱ ዛፍ ሥር ተቀምጦ እንዳየው ከተናገረው በኋላ፥ ናትናኤል ኢየሱስ፥ «የእግዚአብሔር ልጅ፥ የእስራኤል ንጉሥ» መሆን አለበት በማለት በአንክሮ ተናገረ፡ የኢየሱስ መለኮታዊ እውቀት፥ ማለትም ርቀት ሳይወስነው የማየቱ ነገር፥ ናትናኤል ኢየሱስ ተስፋ የተሰጠው መሢሕ መሆኑን እንዲያምን ገፋፋው። እርሱም ይህን መሢሕ የእግዚአብሔር ልጅ ሲል ጠርቶታል። ኢየሱስ ለሞቱት ሁሉ ሕይወትን ሊሰጥ እንደሚችል ታምን እንደሆነ ማርታን ሲጠይቃት፥ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንደምታምን መለሰችለት። ማርታ ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅ ስትል የጠራችው እርሱ ሕይወትን ሊሰጥ የሚችል የእግዚአብሔር መሢሕ መሆኑን አምና ነበር፡ ሐዋርያው ዮሐንስ በወንጌሉ መጨረሻ ላይ መጻሕፍቱን የሚያነቡ ሁሉ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ማመን እንዳለባቸው ያሳስባቸዋል። ዮሐንስ የእግዚአብሔር ልጅ ብሎ በሚጠራው በመሢሑ ኢየሱስ ስምናምንበት ጊዜ የዘላለምን ሕይወት እናገኛለን። በእነዚህ በሦስቱ የምንባቡ ክፍሎች ውስጥ፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሚለው ለያሜ፥ መሢሕ ለሚለው ቃል አቻ ወይም ተመሳሳይ ሆኖ ቀርቧል። ነገር ቀን በእያንዳንዱ ሁኔታ፥ የእግዚአብሔር ልጅ ማለትም መሢሑ ማንኛውም ተራ ሰው ሊያደርገው የማይችለውን ነገር ሁሉ ያደርጋል። ጊዜና ቦታ የማይወስነው እውቀት አለው። ሕይወትን መስጠት ይችላል። ታዲያ ዮሐንስ ኢየሱስን የእግዚአብሐር ልጅ ሊለው፥ ሊገልጽ የፈለገው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ መሢሑ መሆኑን ነው።
4.2 የእግዚአብሔር ልጅ ከአባቱ ከአብ ጋር እኩል ነው።
ጥያቄ፡– ዮሐንስ 5፡16-27 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ እግዚአብሔርን አባቴ ብሎ ሲል፥ ስለ ራሱ ምን እንዳለ ነበር ሕዝቡ የገባው? (ቁጥር 18) ለ) በዚህ ምንባብ ውስጥ ላለ አብና ወልድ የተባለውን ነገር በሙሉ በዝርዝር ጻፍ (ቁጥር 19፥ 214 22፡ 3ና 28)።
ጥያቄ፡– ዮሐንስ 17፡1 አንብቡ። ኢየሱስ ሲጸልይ አባትና ልጅ ለእርስ በርስ ምን እንዲያደርጉ ጸለየ?
ጥያቄ፡– ዮሐንስ 19፡7 አንብቡ። አይሁዶች በምን ምክንያት ኢየሱስ መገደል አለበት አሉ?
በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው፥ «የሰው ልጅ» የሚለው መጠሪያ ኢየሱስ መሢሕ ነው ብሎ ብቻ አላቆመም። ኢየሱስ እግዚአብሔርን አባቴ ባለው ጊዜ ሕዝቡ የገባው በእርሱና በእግዚአብሔር መካከል የቅርብ ንኙነት እንደ ነበረ ነው። በዮሐንስ 19፡7 መሠረት ኢየሱስ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ብሎ በመጥራቱ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ነኝ ብሎ ተሳደበ ተባለ። ኢየሱስ ግን ይህን በማሰባቸው አልወቀሳቸውም። በዚህ ፈንታ ይልቅ እርሱ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሆኖ በእግዚአብሔር አብ መካከል ያለውን ቀንኙነት የበለጠ ግልጽ አደረገላቸው። እንደ ልጅ እርሱም አባት የሚፈጽመውን ሁሉ እንደሚፈጽም ነገራቸው። አባት ሙታንን አስነሥቶ ሕይወትን እንደሚሰጣቸው ሁሉ፥ ልጅም ሙታንን አስነሥቶ ሕይወትን እንደሚሰጥ ነገራቸው። ልጅ ከአባቱ እኩል ይከበር ዘንድ አባት ለልጁ ፍርድን ሁሉ ሰጥቶታል። እንዲሁም ማንም ሌላ ሰው ለእግዚአብሔር አብ ሕይወትን እንዳልሰጠ ሁሉና፥ በራሱ ውስጥ ሕይወት እንዳለው፥ ልጅም ስራሱ ሕይወት አለው። አባትና ልጅ አንዱ ለሌላው ክብርን ይሰጣል። በተከታተልናቸው ምንባቦች ሁሉ ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር ልጅነቱ እርሱም እግዚአብሔር የሚያደርገውን እንደሚፈጽምና እግዚአብሔር የነውንም እርሱ እንደሆነ ይናገራል። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የሚለውን ስያሜ በተጠቀመ ጊዜ፥ አይሁዶች በትክክል የገባቸው ኢየሱስ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እንዳስተካከለ ነው።
በዮሐንስ 10፡34-36 ላይ የተጻፈውን በመጥቀስ አንዳንድ ሰዎች አስተያየት ሲሰጡ፥ ኢየሱስ «የእግዚአብሔር ልጅ» የሚለውን በመጠቀሙ፥ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል መሆኑን ክዶታል ይላሉ። ሆኖም ይህን ክፍል በውል ብናጠና፥ እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን እኩልነት ዝቅ እንዳላደረገ እንገነዘባለን፡ ይልቁንም ይህን በማለቱ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን እኩልነት በማጠናከር አረጋግጦታል።
ጥያቄ፡- ዮሐንስ 10፡30-9 እንብቡ፡ ሀ) አይሁዶች በምን ምክንያት ኢየሱስን ለመውገር ድንጋይ አነሡ? ለ) ከቁጥር 34-46 ላይ ኢየሱስ ያደረገውን የማመዛዘን ሁኔታ በራሳችሁ ቃላት ለጹ? ሐ) በቁጥር 38 ላይ ኢየሱስ ምን ድምጻሜ አደረገ? መ) ለለ ድምጻሜው በቁጥር 39 የሕዝቡ ስሜት እንዴት ነበር?
ኢየሱስ አስገራሚ የነበረውን አባባል ማለትም እርሱ ከአብ ጋር አንድ መሆኑን ዮሐንስ 10፡30) በተናገረ ጊዜ፥ ያደምጡት የነበሩ አይሁዶች ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ። ምክንያቱም እርሱ ሰው ሆኖ እያለ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካከለ የሚል ነበር። ኢየሱስ ግን ይህን ለማረጋገጥ ማለትም እርሱ ከአብ ጋር እኩል መሆኑን ሊያብራራላቸው በአንድ ማነጻጸሪያ ተጠቀመ። ለዚህም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ገዥዎችና ፈራጆች ሰንጎ የተናገረው ከመዝሙር 82፡6 ቃል ጠቀሰላቸው። እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ ሲናገር «ኤሎሂም» በተባለው የዕብራይስጥ ቃል ተጠቅሞ ነበር። «ኤሎሂም» የተባለው ይህ ቃል «እግዚአብሔር» ለማለት የሚሆን ቃል ነው። ለታላላቅና ለኃያላን ሰዎችና መላእክትም መጠሪያ ይውል ነበር። ቃሉም አንድ ኃይልና ግርማ ያለው ኑባሬ የሚገለጽበት መንገድ ነበር። ኢየሱስም መጻሕፍት ይህን ቃል ለእግዚአብሔርና ኃያልና ባለግርማ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ እንደሚጠቀሙበት ግልጽ አድርጎ ተናገረ፡ ነገር ግን ኢየሱስ እዚህ ላይ እርሱ ኃያልና ግርማ ያለው ሰው ብቻ መሆኑን አልተናገረም። እርሱ ለማለት የፈለገው፥ እግዚአብሔር ኤሎሂም» የተባለውን ቃል ታላላቅ ሰዎችን ማለትም ሰብአዊ ፍጡር ብቻ የሆኑትን ለመግለጽ ከተጠቀመበት፥ «የእግዚአብሔር ልጅ» የሚለውን መጠሪያ እርሱም መጠቀሙ ተገቢ መሆኑን ለመግለጽ ነው። ምክንያቱም እርሱ ከጥንት ዘላለም ዓለም እግዚአብሔር የለየው የራሱ ያደረገው ወደ ዓለምም የላከው ስለሆነ ይህ መጠሪያ ለእርሱ ተገቢ ነው። በዚህም ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት እንደ ነበረና ከእግዚአብሔር ጋርም ከማንም ሰው የበለጠ ልዩ ግንኙነት እንደ ነበረው አመልክቶአል። እርሱ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን አልካደም፥ ይልቅ ከሰው የበለጠ መሆኑን አረጋገጠ እንጂ። የተናገረው ልጽ መሆኑን ለማረጋገጥ ኢየሱስ ሲናገር እርሱ በአብ ውስጥ አብም በእርሱ ውስጥ እንዳለ ገለጸ። እርሱ ከእግዚአብሔር አብ ጋር ያለው አንድነት በጣም የላቀ ከመሆኑ የተነሣ እርሱና አብ እንደማይነጣጠሉ አስታወቀ። እርሱ መለኮት መሆኑን አመለከተ። እርሱ መለኮት መሆኑን በገለጻ ጊዜ፥ አይሁዶች ነገሩ በግልጽ ስለገባቸው ሊይዙት ቃጡ። ዮሐንስ 10፡30-39 ኢየሱስ ከአብ ጋር እኩል እርሱ ለግድ ኃያልና ግር ግልጽ አድርጎ ትናኤልና ባለግርማ መሆኑን አይክድም። ይልቅ ኢየሱስ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ብሎ ሊጠራ፥ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል መሆኑን መግለጹ እንደሆነ በአጽንኦት ያረጋግጣል።
ስለዚህ ዮሐንስ ለኢየሱስ «የእግዚአብሔር ልጅ» የሚለውን ስም ሲጠቀም፥ እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሆነው መሢሕ መሆኑን መመስከሩ ነበር። ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ስለሆነ በሚገባ እግዚአብሔርን መግለጥ የሚችለው እርሱ ነው።
4.3. የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔርን በተሻለ መንገድ ይገልጻል፥ የዘላለም ሕይወትንም ይሰጣል።
ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡14፥ 18 አንብቡ። ሀ) በእነዚህ ቁጥርች ውስጥ ኢየሱስ ምን ተብሎ ተጠራ? ለ) በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ኢየሱስ ምን አደረገ?
የአማርኛው ምንባብ ዮሐንስ 1፡14፥ 18 ኢየሱስን «አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ” ይላል። ዮሐንስ እዚህ ላይ የተጠቀመባቸው የግሪክ ቃላት፥ ኢየሱስ ማንኛውም ሰው በሚወለድበት ልማድ ከአብ ተወለደ አይሉም። በዚህ ፈንታ ኢየሱስ ከአብ የመጣው እንደ ማንም ሰው አይደለም ነው የሚሉት። ስለዚህ ኢየሱስን «የእግዚአብሔር ልጅ» ብለን በምንጠራበት ጊዜ፥ የኢየሱስን ያህል ሌላ ማንም ሰው እግዚአብሔርን ሊቀርበው አይችልም ማለታችን ነው። ኢየሱስ ከእግዚአብሔር በመጣበት መንገድ ማንም ሌላ ሰው ሊመጣ አይችልም፡ እንደዚሁም ኢየሱስ እግዚአብሔርን እንደ ገለጠው ማንም ሌላ ሰው ሊገልጠው አይችልም። ዮሐንስ የተጠቀመበት የግሪኩ ቃል የሚለው «ከእግዚአብሑር ዘንድ የመጣ አንዱና ብቸኛው» ኢየሱስ መሆኑን ነው። እንዲህ ስለሆነም ኢየሱስ እግዚአብሔርንና ክብሩን ለሰዎች ይገልጣል። እርሱ እግዚአብሔርን ለሰዎች የሚገልጥ ብቸኛው ነው። ዮሐንስም እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ስለሆነ፥ እግዚአብሔርን የሚገልጥም እርሱ ነው ይላል
ኢየሱስ ማንም ሊያደርገው የማይችለውን እግዚአብሔርን የሚገልጥ «የእግዚአብሔር አንዱና ብቸኛው ልጅ» ስለሆነ እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ የሚሰጠውን ሕይወት ማግኘት የሚቻለው በእርሱ በኩል ነው።
ጥያቄ- ዮሐንስ 3፡16-18፥ 36፤ 6፡40 እንብቡ። ሀ) በእግዚአብሔር አንድና ብቸኛ ልጁ በሚያምኑት ላይ ምን ይደርሳል? ለ) በእግዚአብሔር አንድና ብቸኛው ልጅ በማያምኑት ላይ ምን ይደርሳል?
ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐንስ 2፡22-25 አንብቡ። የእግዚአብሔርን ልጅ በሚክድ ላይ ምን ይደርሳል? በልጁ በጊታመን ሰው ላይስ?
ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐንስ 44-5 አንብቡ። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ በሚመሰክር ወይም በሚታመን ሰው ላይ ምን ይደርስበታል?
ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐንስ 5፡10-18 አንብቡ። የእግዚአብሔር ልጅ ያለው ሰው የሚታወቅበት ምንድን ነው?
ኢየሱስ እግዚአብሔርን የሚገልጥ የእግዚአብሔር አንዱና ብቸኛው ልጅ ስለሆነ እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው የዘላለም ሕይወትም ሊገኝ የሚችለው በእርሱ በኩል ብቻ ነው። ዮሐንስ ምዕራፍ 3፥ ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር ልጅ ስለ ማመን ሲናገር፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ በመጣው እርሱንም በሚገልጠው በኢየሱስ የሚያምኑ የዘላለምን ሕይወት ያገኛሉ ማለቱ ነው። ኢየሱስ ከሰማይ መምጣቱንና እግዚአብሔርም በእርሱ እንደሚገለጥ የማያምኑ ይኮነናሉ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡22-25 የሚያስተምረን ማንም ሰው ወደ እግዚአብሔር አብ ለመምጣት ቢሻ በኢየሱስ ማመን እንዳለበት ነው። ማንም ሰው ኢየሱስ ልጁ መሆኑን እርሱ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ከእግዚአብሔርም ዘንድ የመጣና እግዚአብሔርም በእርሱ የሚገለጥ መሆኑን ቢክድ እርሱንም እግዚአብሔር ይክደዋል። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን በሚያምኑ ሁሉ እግዚአብሔር ራሱ በእውነት በውስጣቸው ይኖራል (1ኛ ዮሐንስ 4፡15)፥ የዘላለምንም ሕይወት ይሰጣቸዋል (1ኛ ዮሐንስ 5፡10 13)። እንዲያም ማለት እርሱ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑንና እግዚአብሔርም ራሱ እንዲገለጥበት ኢየሱስን እንደ ላከው ያምናል ማለት ነው።
ዮሐንስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ ያቀረበው ትምህርት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ካሉት ትምህርቶች ሁሉ የተሟላ ትምህርት ነው። ዮሐንስ ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅ ብሎ ሲጠራው ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣው መለኮታዊው መሢሕ ነው። እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሆነ ለእኛ እግዚአብሔርን የሚገልጥ ነው። ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሰን መንገድ መሆኑን ስናምን እግዚአብሔር በውስጣችን ይኖራል፥ የዘላለምንም ሕይወት ይሰጠናል።
ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ ውስጥ ራሳቸውን ክርስቲያኖች ብለው የሚጠሩ ብዙ ሰዎች የሚናገሩትን ሳይገነዘቡ እንዲሁ ብቻ ኢየሱስን «የእግዚአብሔር ልጅ» ብለው ይጠሩታል። ሰዎች ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ ካላቸው የተሳሳቱ አስተሳሰቦች ጥቂቶቹን ጻፉ። ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ የሚሰጠውን ትምህርት፥ ለእነዚህ ሰዎች ለእያንዳንዳቸው ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ የሚረዷቸውን አሳቦች ምን ብላችሁ እንደምትነግሯቸው ጻፉ።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
