“ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” የሚለው መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር ተጽፎ በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ እና በላፕስሊ ብሩክስ ፋውንዴሽን የታተመ ነው፡፡ አስቀድመን ስለ እነዚህ ቅዱሳን ትጋት እና የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን ለማገልገል ለከፈሉት ዋጋ ምስጋናችን እናቀርባለን፡፡ በመቀጠል ጽሁፉን ኮፒ እና ፕሪንት በማድረግ ለግልም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማዋል የተፈቀደ ቢሆንም ያለአሳታሚው ፈቃድ ጽሁፉን መለወጥም ሆነ ለሽያጭ ማዋል ግን ፈጽሞ በሕግ የተከለከለ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ መልካም ጥናት!
መግቢያ
ይህ መጽሐፍ የሥነ-መለኮት ሥልታዊ ትምህርትን ሙሉ በሙሉ ያሟላል በሚል አሳብ የተጻፈ አይደለም። መጠነኛና እጅግ አስፈላጊ በሆኑ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርቶች ላይ በማተኮር፥ ጥልቅ የሆነ የሥነ-መለኮት ትምህርት የሌላቸውን አማኞች ለመርዳት የተጻፈ ነው። “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” የመገለጦች መልህቅ ነው። አስተዋይ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ በአዲስ ኪዳን ጥልቅና መሠረታዊ ትምህርት መደነቁ እርግጥ ነው (ማቴ. 7፡28፤ ዮሐ. 7፡16-17፤ ሐዋ. 2፡42፤ ሮሜ 6፡ 17፤ ኤፌ. 4፡14፤ 1ኛ ጢሞ. 1፡3፤ 4፡6፥ 16፤ 6፡1፤ 2ኛ ጢሞ. 3፡ 10፥ 16፤ 4፡2-3፤ 2ኛ ዮሐ. 9-10)። የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ የእምነት ትምህርት በሚገባ የማይረዳ አማኝ ኤፌሶን 4፡ 14 ውስጥ “እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን..” የሚለውን እውነት ይደርስበታል። ጠንካራ ናቸው የሚባሉ አማኞች በአሁኑ ጊዜ በሀሰት ትምህርት መወሰዳቸው ለዚህ ማረጋገጫ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የመለኮት ዓላማ፥ “ቃሉን ስበክ፤ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፥ ምከርም፤ ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሥበት ዘመን ይመጣልና” በሚለው ቃል መሠረት የጌታ ተከታይ የሆነ ሁሉ ዝግጁ እንዲሆን ነው። በዚህ መጽሐፍ የተካተቱ ምዕራፎች በሙሉ በክብሩና በጸጋው ባለጠጋ ለሆነ ጌታ ክብር ይሆን ዘንድ በጸሎት በመታገዝ ቀርበዋል። የጌታ ልጆች የሆኑ አማኞችም “ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርትን ለመናገር ብቃት እንዲኖራቸው ያግዝ ዘንድም ይህ መጽሐፍ ተዘጋጀ። ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር
የትምሕርቶቹ ዝርዝር
7 እግዚአብሔር ወልድ፡- መለኮታዊነቱና ዘላለማዊነቱ
11 እግዚአብሔር ወልድ፡- ዕርገቱና የክህነት አገልግሎቱ
13 እግዚአብሔር ወልድከቅዱሳኑ ጋር ስለ መምጣቱ
16 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የዳግም ልደት ሥራ
17 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- በሰው ውስጥ ማደሩና ማተሙ
18 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- የማጥመቅ ተግባሩ
19 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- የመሙላት ተግባሩ
38 ቤተ ክርስቲያን፡- አምልኮዋ በጸሎትና በምስጋና
40 ቤተ ክርስቲያን፡- የክርስቶስ አካልና ሙሽራ፥ የሚጠብቃት ሽልማቷ
44 ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቀደም ብለው የሚከናወኑ ሁኔታዎች