አዘጋጅ
አዳነው ዲሮ ዳባ፣ አዘጋጅ

ኮትኩቶ ያሳደገን ባህል ጥያቄ መጠየቅ ነውር እና ትዕቢት እንደሆነ ነግሮናል። ስለ መንፈሳዊ ነገሮች መጠየቅ መቅሰፍትን ወደ ቤታችን እንደ መጋበዝ፣ በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት እንደመቀነስ በሚቆጥር ማህበረሰብ መካከል ያደገ፣ እውነተን በመፈለግ የነፍሱን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያደርገው ጉዞ ቀላል አይሆንለትም። እውነታው ግን ይህ ነው – እግዚአብሔርን ማመን፣ ከእውቀት ይጀምራል፤ ይህ እውቀት ደግሞ ከእግዚአብሔር ቃል ይመነጫል፣ (ሮሜ 10፡17)። እግዚአብሔር እንድናውቀውና እንድንፈልገው አዞናል (1ዜና 28፡9)፡፡  የእግዚአብሔርን ቃል እንዳንመረምር የሚሞጉቱን ሰዎች የቤሪያ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተመዘገቡ ክርስቲያኖች መሆናቸውን ዘንግተውት ይሆን? ‘‘እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና። ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ (የሐዋርያት ሥራ 17፡11)። እነዚህ ክርስቲያኖች፣ ቃሉን መሙሉ ፈቃድ ከመቀበላቸው በፊት ይመረምሩ ነበር። ‘‘ቃሉን አትመርምር’’ የሚል የእግዚአብሔር ቃል የለም። እንግዳው ኑ አብረን የእግዚአብሔርን ቃል በቅንነት፣ በእምነትና በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እንመርምር፡፡

ምን አገኛለው?

የድነት (የደኅንነት) ትምሕርቶች፣ የደቀ መዝሙር ማሰልጠኛዎች፣ በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ላይ በደራሲው እና አሳታሚው ፈቃድ ለጥናት በሚመች መልክ ተዘጋጅተው የቀረቡ የብሉይ እና አዲስ ኪዳን ማብራሪያ እና ማጥኛዎች፣ በደራሲዎቻቸው ፈቃድ በዌብሳይቱ አዘጋጅ ተተርጉመው የቀረቡ ከ1000 በላይ አጫጭር ትምሕርታዊ ጽሁፎች፣ አማኞችን በጤናማ አስተምሕሮ ላይ የሚመሰርቱ ትምሕርተ ሃማኖት፣ ሙስሊም ወዳጆቻችንን በወንጌል ለመድረስ የሚያግዙ የወንጌል ስርጭት ማቴሪያሎች፣ ወዘተ፡፡ 

በወንጌል በድረገጽ አገልግሎት ተዘጋጅተው የቀረቡ አፖች (Apps)

የመጽሐፍ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ ማስፈንጠርያ (አፕ)

በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ ማስፈንጠርያ (አፕ) Old and New Testaments Study Guide and Commentary Application ስራው ተጠናቆ በፕሌይ ስቶር (play store) ላይ ለአገልግሎት በነጻ ቀርቧል፡፡ አውርደው ይጠቀሙ፡፡

የመንፈሳዊ ጽሁፎች ማስፈንጠሪያ (አፕ)

በሺዎች የሚቆጠሩ መንፈሳዊ ጽሁፎች የሚያገኙበትን ይህን የወንጌል በድረገጽ አገልግሎት 2ኛ አፕ ከፕሌይ ስቶር በነጻ አውርደው እንዲጠቀሙ ተጋብዘዋል! ይህ አፕ፣ የወንጌል በድረገጽ ዌብ ሳይትን ይዘት በአጠቃላይ የያዘ  እና ለእጅ ስልክ አጠቃቀም በሚመች መልክ የተዘጋጀ ነው፡፡