የሕይወት እንጀራ አገልግሎት

የመጽሐፎችና የስልጠና ማኑዋሎች ማህደር

በዚህ ገጽ ላይ አማኞችን ለተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች የሚያበቁ እና በመንፈሳዊ እውቀት የሚያሳድጉ ጠንካራ የትምህርት ግባቶችን በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት አዘጋጅተን አቅርበናል። ጽሁፎቹ በቀላሉ ዳውንሎድ (Download) ተደርገው ለግል ጥናት፣ ለቡድን ውይይትና ለቤተክርስቲያን ስልጠና እንዲውሉ ታስበው የተሰናዱ ናቸው።

  • የስልጠና ማኑዋሎች (Training Manuals) አማኞች በደቀመዝሙርነት ጉዞ፣ በመሪነት፣ በወንጌል ስርጭት፣ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችና አሰራሮች ዙሪያ፣ ወዘተ ተግባራዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስልጠናን እንዲያገኙ የሚያስችሉ ቅደም ተከተላዊ መመሪያዎች ናቸው። እያንዳንዱ አማኝ ለቤተክርስቲያን ማነጽ መንፈሳዊ ስጦታውን ለሁሉም ጥቅም በታማኝነት ሊጠቀምበት ይገባል (1 ቆሮ 12:7)። እነዚህ ማኑዋሎች ይህንን የአገልግሎት አቅም ለማዳበር ይረዳሉ።

  • የአዲስ ኪዳን መጽሐፎች የጥናት መምሪያና ማብራሪያ (New Testament Books Study Guide and Commentary)፦ ከማቴዎስ ወንጌል እስከ ራእይ ድረስ ያሉትን የእያንዳንዱን መጽሐፍ ዋና ዓላማ፣ ታሪካዊ ዳራ፣ ማዕከላዊ መልእክት እና ቲዮሎጂያዊ አስተምህሮ በግልጽ የሚያብራሩ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ ናቸው። እነዚህ ማብራሪያዎች የክርስቶስን ወንጌል አውድና ጥልቀት በትክክል ተረድታችሁ በዕለት ተዕለት ሕይወታችሁ ተግባራዊ እንድታደርጉ ይረዷችኋል።

  • ጥልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንተናዎች (In-Depth Biblical Analyses) በተለያዩ መለኮታዊና ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ታሪካዊ፣ ቋንቋዊና መንፈሳዊ አውድ በጠበቀ መልኩ የሚተነትኑ ሰፊ ጽሁፎችን ይዟል። አማኞች መልካሙንና ክፉውን ለመለየት ቸውን በማሰልጠን ወደ ጠንካራ መንፈሳዊ ምግብና ብስለት ሊሸጋገሩ ይገባል (ዕብ 5:14)። እነዚህ የትንተና ጽሁፎች ከስህተት ትምህርት ተጠብቃችሁ በጤናማው ትምህርት ጸንታችሁ እንድትቆሙ ያግዟችኋል።

መጽሐፎቹን እንዴት መጠቀም ይችላሉ?

  1. ለግል ጥናት፡ የሚፈልጉትን ርዕስ በመምረጥ የፒዲኤፍ ፋይሉን ወደ ስልክዎ፣ ታብሌትዎ ወይም ኮምፒውተርዎ ዳውንሎድ በማድረግ በጸሎትና በመንፈስ ቅዱስ ምሪት በጥልቀት ያጠኑት።

  2. ለአነስተኛ ቡድኖችና ለሴል አገልግሎት፡ ማኑዋሎቹን በህብረት ጥናቶች፣ በጸሎት ቡድኖችና በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ክፍለ ጊዜያት ለማስተማሪያነት ይጠቀሙባቸው።

  3. ለሌሎች ማካፈል፡ ከእግዚአብሔር ቃል ያገኛችሁትን አደራና እውነት ሌሎች ታማኝና ማስተማር የሚችሉ ሰዎችን ለማብቃት አስተላልፉ (2 ጢሞ 2:2)።

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነውን?

የይሖዋ ምስክሮች ትምህርት

የ"ኢየሱስ ብቻ/Only Jesus" ትምህርት

የአገልጋዮች ማሰልጠኛ ማኑዋል

የእጩ አገልጋዮች ማሰልጠኛ ማኑዋል

ደቀ መዝሙር ማሰልጠኛ (የጥናት ኮርስ)

አማራጭ የደቀ መዝሙር ማሰልጠኛ

የሮሜ መልዕክት ጥልቅ ሥነ-መለኮታዊ ትንታኔ

መሠረታዊ የክርስትና ትምሕርት

የክርስትና መሰረታዊ ትምሕርቶች

የሕግ ትርጉሙ፣ ዓላማውና አተገባበሩ

የሰንበት ቤት ካሪኩለም (ከ9 ዓመት በታች)

የሰንበት ትምህርት ቤት ካሪኩለም (9-12)

የሰንበት ትምህርት ቤት ካሪኩለም (13-18)

የዕቅበተ እምነት (Apologestics) ስልጠና

የማቴዎስ ወንጌል ማጥኛና ማብራሪያ

የማርቆስ ወንጌል ማጥኛና ማብራሪያ

የሉቃስ ወንጌል ማጥኛና ማብራሪያ

የዮሐንስ ወንጌል ማጥኛና ማብራሪያ

የሐዋሪያት ሥራ ማጥኛና ማብራሪያ

የሮሜ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የኤፌሶን መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የፊልጵስዩስ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የቆላስይስ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የ1ኛ ተሰሎንቄ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የ2ኛ ተሰሎንቄ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የ1ኛ ጢሞቴዎስ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የ2ኛ ጢሞቴዎስ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የቲቶ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የፊልሞና መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የዕብራውያን መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የ1ኛ ጴጥሮስ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የ2ኛ ጴጥሮስ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የ1ኛ ዮሐንስ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የ2ኛ ዮሐንስ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የ3ኛ ዮሐንስ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የያዕቆብ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የይሁዳ መልእክት ማጥኛና ማብራሪያ

የዮሐንስ ራዕይ ማጥኛና ማብራሪያ

የመጽሐፈ አስቴር ማጥኛና ማብራሪያ