ኢየሱስ ሕይወትን ይሰጣል 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 5፡21፥ 25 እንዲሁም ዮሐንስ ጥቅሶች ውስጥ ኢየሱስ ምን አደረገ? 

በዮሐንስ 5፡21 ኢየሱስ ራሱን ከእግዚአብሔር አብ ጋር ያነጻጽራል፡ ለሙታን ሕይወት የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር አብ ለሙታን ሕይወትን እንደሚሰጥ ሁሉ፥ እግዚአብሔር ወልድም ለሙታን ሕይወትን ይሰጣል። ስለሆነም ኢየሱስ ሕይወትን በመስጠት ኃይሉ፥ ራሱን ከእግዚአብሔር አብ ጋር እኩል ያደርጋል። ኢየሱስ በዮሐንስ 5፡25 ላይ አካላዊ ሕይወትን መስጠት (ለአልዓዛር እንዳደረገው) ብቻ ሳይሆን 

መንፈሳዊ ሕይወትንም የመስጠት ኃይልና ሥልጣን እንዳለው ይገልጻል እግዚአብሔር ብቻ ነው አካላዊና መንፈሳዊ ሕይወትን ሊሰጥ የሚችል ኢየሱስም አካላዊና መንፈሳዊ ሕይወትን ስለሚሰጥ፥ እርሱ አምላክ ነው። 

ኢየሱስ በዮሐንስ 15፡26 ላይ ለደቀ መዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስ እንደሚልክላቸው ተስፋ ሰጥቷቸዋል። በዮሐንስ 14፡16፥26 እግዚአብሔር እብ መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክ ተናግሯል። ኢየሱስም ደግሞ መንፈ ቅዱስን ይልካል። መንፈስ ቅዱስን የመላክ ብቸኛ ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር ራሱ ነው። ከእግዚአብሔር በታች የሆነ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ሊልክ አይችልም። ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን የመላክ ሥልጣ” ስላለው፥ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር አምላክ መሆኑ ግልጽ ነው። 

ኢየሱስ በሁሉም ስፍራ ይገኛል፤ እርሱ የመፍጠር፥ ሕይወት የመስጠትና መንፈስ ቅዱስን የመላክ ኃይልና ሥልጣን አለው። እርሱ ሁሉ ነገር ያውቃል፤ ደግሞም ፈጽሞ አይለወጥም። በነገው ትምህርት ኢየሱስ ስ 

መለኮታዊነቱ በሚገለጽባቸው ሌሎቹ ሥራዎች ላይ ትኩረት እናደርጋለን ኢየሱስ በግልጽ የእግዚአብሔር ባሕርያት ስላለው እግዚአብሔ የሚያደርገውን ሁሉ ያደርጋል። ኢየሱስ ራሱ አምላክ/ እግዚአብሔር ነው። 

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading