ተሠገዎ በዮሐንስ 1 

ዛሬ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ተገዎ የሚናገር፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ክፍለ ምንባቦች መካከል አንዱ የሆነውን ዮሐንስ 1፡1–14 ያለውን ጥቅስ በጥንቃቄ እናጠናለን። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ዮሐንስ ደጋግሞ ስለ «ቃል» ይናገራል። ይህን ክፍለ ምንባብ ከማጥናታችን በፊት አስቀድመን መጠየቅ ያለብን፥ «ዮሐንስ ስለ ቃል ሲናገር ምን ማለቱ ነው?» «ቃል» ማለት በግሪኩ ሎጎስ ማለት ነው። በዓለማዊው የግሪክ ፍልስፍና እሳቤ «ሎጎስ» ከዚህ ከሚታየው ፍጥረት በስተኋላ ያለና ሁሉም ነገር በእርሱ ህልውናን የሚያገኝበት መለኮታዊ መንሥዔ ማለት ነው። እንደዚሁም የሰው ነፍስ መሠረት «መነሻ» ወይም «ውስጣዊ እሳቤ» ማለትም ነው። ነገር ግን ለግሪኮች ሉጎስ ግላዊ ወይም ተሠገዎ አልነበረም። 

ጥያቄ፡- ዘፍጥረት 1፡3፥ 6፥ 9፥ 14፥ 20፥ 24፤ መዝሙር 33፡6-9፤ 107፡20፤ ዘዳግም 32፡46-47፤ ኢሳይያስ 55፡11 አንብቡ። በእነዚህ ምንባቦች መሠረት የእግዚአብሔር ቃል ምን ያደርጋል? 

ዕብራውያን ብሉይ ኪዳንን ወደ ግሪክ በተረጎሙ ጊዜ «ሎጎስ» የተባለውን ቃል ተጠቅመውበት ነበር። የእግዚአብሔር ሎጎስ ይፈጥራል (ዘፍጥረት 1፤ መዝሙር 3፡6)፥ ሕይወትን ይሰጣል (ዘዳግም 32፡46-47)፣ ይፈውሳል (መዝሙር 107፡20)፤ የእግዚአብሔርን ድኅነት ይፈጽማል (ኢሳይያስ 55፡ነ0፥ የእግዚአብሔር ቃል እርሱ ኃያልነቱን በፍጥረት ውስጥ የሚያሳይበት ግልጸተ መለኮትና አርነት ነው። 

በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አንድ ውስጥ ዮሐንስም ይህን ጥንታዊ የግሪክና የዕብራውያንን አሳብ በመውሰድና በማዳበር ስለ ኢየሱስ አዲስ ነገር ግንሊያስተምር ችሎአል። 

1. «ቃሉ» ማን ነበር? 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡1-5 አንብቡ። ስለ «ቃል» በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እውነት የሆኑትን ሁሉ ጻፉ። ስድስት ልዩ ልዩ ነገርችን ለማግኘት ሞክሩ። 3ኛ ጥያቄ፡- ዮሐንስ 11 አንብቡ። ዮሐንስ ቃል ከእግዚአብሔር ጋር ስላለው ግንኙነት የተናገረውን ዘርዝሩና እስረዱ። 

በመጀመሪያዎቹ አምስት ቁጥሮች ላይ ዮሐንስ «ስለ ቃል» ስድስት ልዩ ልዩ ነገሮችን ያስረዳል። 

1. በመጀመሪያ ቃል ነበረ። ዮሐንስ፡ «በመጀመሪያ ቃል ነበረ» ሲል ቃል ያልነበረበት ጊዜ በፍጹም አልነበረም ማለቱ ነው። ማንኛውም ነገር ከመጀመሩ በፊት ቃል ነበረ። ቃል ባለፉት እልፍ ዘመናት ለዘላለም ነበር። ለዘላለም የነበረው እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ እንግዲህ ይህ በሌላ ኣባባል ቃል እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። 

2. ቃልም ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበር። ቃል ከእግዚአብሔር ተለይቶ የሚታወቅና ከእግዚአብሔርም ጋር ግንኙነት ወይም አንድነት ያለው ነው። 

3. ቃልም እግዚአብሔር ነው። ሆኖም ቃል ከእግዚአብሔር ጋር ነበር ማለት ብቻ አይበቃም። ቃልም እግዚኣብሔር ነበር። በመጀመሪያው ትምህርታችን ላይ እንደተመለከትነው፥ ኢየሱስ እግዚአብሔር ለመሆኑ ይህ ከግልጽ ማረጋገጫዎች መካከል አንዱ ነው። ዮሐንስ ቃል በእግዚአብሔር ወይም በመለኮት የሚመሰል ነው አላለም። እርሱ የሚለው ቃል ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ነው። ዮሐንስ ቃል ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ይህ ቃልም እግዚኣብሔር ነበረ ሊል እንዴት ቻለ? እንደ ሰው አስተሳሰብ ክሆነ ይህ ስሜት የሚሰጥ አይደለም። ነገር ግን ዮሐንስ የፈለገው ከሰዎች አስተሳሰብ የተለየ ገለጻ ለማቅረብ ነበር። በአንድ መንገድ ቃል እግዚአብሔርም ነው፥ ከእግዚአብሔር የተለየም ነው። ዮሐንስ እንድንገነዘብ የፈለገው የኢየሱስ ቃላትና ተግባራት የእግዚአብሔር የራሱ ቃላትና ተግባራት መሆናቸውን ነው። 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡3 ኣንብቡ። እንደዚህ ጥቅስ ከሆነ፥ ዓለምን የፈጠረው ማን ነው? 

4 ቃል ዓለምን ፈጠረ። የእግዚአብሔር ዓለምን መፍጠር በቃሉ ሆነ (ዘፍጥረት 1-2)። እግዚአብሔር ብቻ ሊፈጥር ስለሚችል፤ ቃል እግዚአብሔር ለመሆኑ ይህ ሌላ ማረጋገጫ ነው። እንደዚሁም ጊዜና ፍጥረት ሲጀመር ቃል ነበር የሚለውንም እንደገና ያጠናክራል። 5ኛ ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡4-5 ኣንብቡ። ሀ) የሕይወት ምንጭ ማን ነው? ለ) ዮሐንስ፥ «ብርሃን» ሲል ምን ማለቱ ይመስላል? ሐ) ብርሃን ምን አደረገ? 

5. ቃሉ ለሰዎች መንፈሳዊ ብርሃንን የሚሰጥ የሕይወት ምንጭ ነው። በራሱ ሕይወት ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ሕይወትን ስለሚሰጣቸው፥ ዕጽዋት፥ እንስሳትና ሰዎች ሕይወት አላቸው። ነገር ግን ይህ ጥቅስ ቃሉ በራሱ ሕይወት አለው ይላል። ማንም ለእርሱ ሕይወትን አልሰጠውም፤ እንዲያውም እርሱ ለሌሎች የሕይወት ምንጭ ነው። ስለሆነም ኢየሱስ እግዚአብሔር ለመሆኑ ይህ ጥቅስ ተጨማሪ ምስክር ነው። ቃሉ የሕይወት ምንጭ እንደ መሆኑ፥ ለሌሎች መንፈሳዊ ብርሃንን ይሰጣል። ዮሐንስ ቃል የሰዎች ብርሃን ነው ሲል ቃሉ ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲያስተውሉት፥ እንዲያዩትና እንዲያውቁት ያደርጋል ማለቱ ነው። ዮሐንስ፥ ኢየሱስ መለኮትና ሰው መሆኑን ማመልከቱን ይጀምራል። ቃል እግዚአብሔር ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔርም ደግሞ ራሱን ለሰዎች የገለጠበት መንገድ ነበር። 

6. የቃሉም ብርሃን በመንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ በራ፥ ነገር ግን በጨለማ የሚኖሩት ሕዝቦች ሊገነዘቡት አልቻሉም ወይም ጨለማው እላሸነፈውም። ቃሉ ከእርሱ በተለዩ እርሱንም ባላወቁ ሰዎች መካከል እግዚኣብሔርን ገለጠ። ነገር ግን ምንም እንኳን ቃሉ እግዚአብሔርን ቢገልጥላቸውም፤ እነርሱ ግን ሙሉ በሙሉ አልተገነዘቡትም፥ ኣላወቁትም። «አላሸነፈውም» የሚለው ቃል በኦሪጅናል ግሪክ ውስጥ ሁለት ትርጉሞች አለው። «አላሸነፈውም» ወይም «አልተገነዘበውም» ማለት ነው። ምናልባት ዮሐንስ ሁለቱንም ትርጉሞች እንድናጤን ፈልጎ ይሆናል። በኢየሱስ ዙሪያ የነበረው መንፈሳዊ ጨለማ አላሸነፈውም፤ ነገር ግን እርሱ ስለ እግዚአብሔር ስለሚገለጠው ነገርም አልተነበበም። 

እነዚህ ጥቅሶች ስለ ተሠገዎ ምሥጢር ጥቂት ጠቃሚ ማብራሪያዎችን ይሰጡናል። ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይነግሩናል። እርሱ ለዘላለም የነበረ፥ ፈጣሪና የሕይወት ምንጭ መሆኑን ይገልጡልናል። ይሁን እንጂ ኢየሱስ እግዚአብሔር ቢሆንም ይህ ለሰው ግንዛቤ አስቸጋሪ ነው። እንደዚሁም እርሱ ከእግዚአብሔር የተለየ ነው። ቃሉ ሰው ሆኖ ለመኖር በምን ምክንያት ወደ ምድር መጣ? ቃሉ ለማያውቁት ሁሉ መንፈሳዊ ብርሃን ሊሰጥና እግዚአብሔርንም ሊገልጥላቸው ወደዚህ ምድር መጣ። ምንም እንኳን ቃልን የተገናኙ ኣብዛኛዎቹ እርሱ ስለ እግዚአብሔር ምንን እንደሚገልጥ ባይገባጵውም፥ እግዚአብሔርን ለዓለም ለመግለጥ የነበረውን ዓላማ ሊሽሩት አልቻሉም። 

ጥያቄ፡- በግላችሁ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እንዴት ገለጠላችሁ? 

ሓዋርያው ዮሐንስ ከቁጥር 6-8 ላይ የመጥምቁ ዮሐንስን ሥራ በአጭሩ ይገልጻል። ሥራው ሰዎችን ወደ ኢየሱስ ማመላከት ነበር። ከዚያም ስለ ኢየሱስ መናገሩን ይቀጥላል። 

2. በቃልና በዓለም መካከል የነበረው ግንኙነት ምን ነበር? 

በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1፡9-13 ባለው ክፍል በቃልና በዓለም መካከል ስላለው ግንኙነት ይገልጻል። ስለዚህ ግንኙነትም ሦስት ነገሮችን ያስረዳል። 

ጥያቄ፡ ዮሐንስ 1፡9-13 አንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ቃልና ዓለም ‘ የሚናገሩትን ጻፉ። ቢያንስ ሦስት ልዩ ልዩ ነጥቦችን ለማግኘት ሞክሩ። 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡9፤ 3፡19-21፤ 8፡12፣ 9፡39-41 አንብቡ። ብርሃኑ ምን ያደርጋል? 

1. ዮሐንስ በምዕራፍ 1፡9 ውስጥ የኢየሱስ መምጣት ለሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን የሚገልጥ ብርሃን እንደሆነ ይናገራል። በተቀረውም የወንጌሉ ክፍል ኢየሱስ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ሲገልጥ እንመለከታለን። ይሁን እንጂ ሰዎች ልባቸውን ከፍተው ኢየሱስ እግዚአብሔርን መግለጡን ሁልጊዜ አይቀበሉም። አንዳንድ ጊዜ ብርሃኑን ችላ ይሉታል። ነገር ግን እርሱ ብርሃን በመሆኑ፥ እግዚአብሔርን እየገለጠ፥ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ውሳኔ እንዲኖራቸው ያደርጋል። ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ለማገናኘት ዓይነተኛው መንገድ ከክርስቶስ ጋር ማገናኘት ነው። 

ጥያቄ፡- ኢየሱስን እንድታምኑ ያደረጋችሁ ምንነቱ ነው? ሌሎች ሰዎች ክርስቶስን እንዲያምኑ፥ የግል ልምምዳችሁን እንዴት ትጠቀሙበታላችሁ? 10ኛ ጥያቄ፡- ዮሐንስ ፡10-11 ኣንብቡ። አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ኢየሱስን እንዴት ተቀበሉት? 

2. ምንም እንኳን ኢየሱስ እግዚአብሔርን ለዓለም ያሳየ ብርሃን ይዞ ቢመጣም፥ የዓለም ሕዝብ ግን እርሱነቱን አላወቁትም ወይም አልተቀበሉትም። የኢየሱስ የራሱ ወገን የነበሩ አይሁዳውያን እንኳን ከእግዚአብሔር እንደ ተላከና፥ እግዚአብሔርንም ለእነርሱ የሚገልጥ መሆኑን አላወቁትም ወይም አልተቀበሉትም። ምንም እንኳን ኢየሱስ እግዚኣብሔርን የሚያንጸባርቅ ብርሃን ቢሆንም፥ ኣብዛኛዎቹ ሰዎች ይገልጥላቸው የነበረውን ሊቀበሉ ፈቃደኞች አልሆኑም። 

ጥያቄ፡- ለምንድን ነው ዛሬ ሰዎች ኢየሱስን ለማወቅም ሆነ ለመቀበል አሻፈረን የሚሉት? ሰዎች እግዚአብሔር ስለ ኢየሱስ ሊገልጥላቸው ለመቀበል እምቢ የሚሉባቸውን እንዳንድ ሁኔታ ጻፉ። 12ኛ ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡12-13 አንብቡ። ሀ) አንዳንድ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ምን ያስባሉ? ለ) ታዲያ የዚህ ዓይነት ስሜት ያላቸው ምን ሆኑ?

3. ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ የዓለም ሕዝቦች ኢየሱስን መቀበል ችላ ቢሉም፥ የተወሰኑ ተቀብለውታል። የተቀበሉትም እግዚኣብሔርን ለእነርሱ በእውነት መግለጡን አምነዋል። እግዚአብሔር በእርሱ አማካይነት የተገለጠላቸው መሆኑን አምነው የተቀበሉት የእግዚአብሔር ልጆች ሆኑ። የእግዚአብሔር ልጅ መሆን፥ ነገር ግን እንደ ሰብኣዊ ሕፃን ሆኖ መወለድ አይደለም። ይህ የሥጋና የደም ልደት አይደለም፥ ወይም አንድ ባል ልጅ ለማግኘት ፈልጎ እንደሚወለድለት ያለ ልጅነትም አይደለም። የእግዚአብሔር ልጆች የሚሆኑት ኃይልን በተሞላ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ተግባር ነው። 

ዮሐንስ 1፡9-13 ውስጥ ወንጌላዊው የተሠገዎ ምሥጢርን ያብራራና ይህ የክርስቶስ ተሠገዎ ለዓለም ስለነበረው , ዓላማና ስላስከተለው ውጤት ይናገራል። ቃል እግዚአብሔርን ሊገልጥ ወደ ዓለም መጣ። በዓለም ያሉ አብዛኛዎቹ ሰዎች ግን ማንነቱን አውቀው አልተቀበሉትም። ሆኖም ጥቂቶቹ ተቀበሉት። የተቀበሉት ሁሉ ግን በእግዚአብሔር በራሱ ሉዓላዊ አሠራር ታላቅ የልጅነት መብትን አገኙ። 

4. ማጠቃለያ፡ – ቃሉ በምን ምክንያት ወደ ዓለም መጣ? 

በዮሐንስ 1፡14 ውስጥ ሐዋርያው ዘላለማዊው ቃል ለምን ወደ ዓለም እንደ መጣ ሲናገር የነበረውንና ያብራራውን ያጠቃልላል። 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡14 አንብቡ። ሀ) በቃሉ ላይ ምን አዲስ ነገር ሆነ? ለ) ቃሉ «በእኛ መካከል ያደረው» ውጤት ምን ነበረ? 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 1፡17-18 አንብቡ። ሀ) ሙሴ ምንን ገለጠ ለ) ኢየሱስ ምንን ገለጠ? ሐ) ሰዎች እግዚአብሔርን ሊያውቁ የሚችሉበት ተመራጭ መንገድ ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡– ዘፀአት 40፡34-35 ኣንብቡ። እስራኤላውያን በምድረ በዳ በነበሩ ጊዜ የእግዚአብሔርን ክብር እንዴት አዩት? 

ሐዋርያው ዮሐንስ በምዕራፍ 1፡14 ውስጥ አዲስ ነገር መፈጸሙን ይነግረናል። ቃል «ሥጋ ሆነ» ይለናል። ዮሐንስ ሲናገር፥ ቃል ራሱን በሥጋ ሸፈነ፥ ወይም ወደ ሰው ኣካል ገባ አላለም። በኣንጻሩ ግልጽ አድርጎ ሥጋ ሆነ ሰውም ሆነ ይላል። በተሠገዎ ኢየሱስ በውስጥ እግዚአብሔር ሲሆን፥ በውጪአዊው ደግሞ ሰው ነበር ብለን ላለማሰባችን ዮሐንስ እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል። እኛ እግዚአብሔር የሆነው ዘላለማዊው ቃል (ዮሐንስ 1፡1-5) ሙሉ በሙሉ ሰው ስለመሆኑ ግንዛቤ መጨበጣችንን ለማረጋገጥ ይፈልጋል። እግዚኣብሔር ቃል፥ ራሱን ለሰው ልጆች ለመገለጥ ብሎ ሰው ሆኖኣል። 

ዮሐንስ አክሎም ቃል ሥጋ ሆነ «በእኛም አደረ» ይላል። «በእኛ አደረ» የሚለው በግሪክ ቃል በቃል ሲፈታ፥ «በመካከላችን ድንኳኑን ተከለ» ማለት ይሆናል። ምናልባት ዮሐንስ «ድንኳኑን ተከለ» ሲል አንባቢዎቹ እስራኤላውያን በምድረ በዳ በነበሩ ጊዜ ያመልኩበት የነበረውን የማደሪያውን ድንኳን እንዲያስታውሱ ለማድረግ ሳይሆን አይቀርም (ዘፀአት 40፡34-35)፡ 

በምድረ በዳ በነበሩ ጊዜ በሲና ተራራ ትይዩ በነበረው ድንኳን ላይ እግዚኣብሔር እንዴት እንደ ወረደ እንዲያስቡም ፈልጎአል። ኣንባቢዎቹ የኢየሱስን በመካከላቸው መገኘት በዚያን ጊዜ በማደሪያው ድንኳን ላይ ያንዣብብ በነበረው የክብር ደመና ውስጥ እግዚእብሔር በሕዝቡ መካከል እንደ መገኘቱ ኣድርገው እንዲረዱት ፈልጓል። 

እግዚአብሔር ቃል ለአጭር ጊዜ በመካከላችን በመቆየቱ ምክንያት፥ እግዚአብሔርን በአዲስና በተለየ መንገድ ልናውቀው ችለናል። የእግዚአብሔርን ክብር አይተናል። የእግዚአብሔርን ጸጋና እውነትም አይተናል። እግዚአብሔርን ከኢየሱስ መምጣት በፊት ይቻል ባልነበረ ሁኔታ ልናየው ችለናል። በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር ይታወቅ የነበረው በሙሴ ሕግ አማካይነት ነበር ( 

ዮሐንስ 1፡17)። ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና እውነት በኢየሱስ በኩል ሊታወቅ ይቻላል። ምንም እንኳን እግዚኣብሔርን አብን ፊት ለፊት ያየው ባይኖርም፥ እግዚአብሔርን ልናውቀው ግን እንችላለን። እንዴት? በኢየሱስ አማካኝነት እናውቀዋለን። ኢየሱስ እግዚአብሔርን ይገልጣል። ኢየሱስ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ በመሆኑ፥ እርሱ ከሁሉ በላይ የሆነ የእግዚአብሔር መግለጫ ነው። 

ዮሐንስ 1፡1-18 ያለው ክፍል ስለ ተሠገዎ ምሥጢር ሃ ስት ጠቃሚ ትምህርቶችን ይሰጠናል፡- ህ ዘላለማዊው ቃል እግዚአብሔር ነበር እና ዘመናት ከመቆጠራቸው በፊትም እንኳ እግዚአብሔር ነበር። 2) በታሪክ ውስጥ በአንድ ወቅት ዘላለማዊው ቃል ሰው ሆነ። 3) ሰዎች እግዚአብሔርን ያውቁት ዘንድ እግዚአብሔር ቃል ሰው ሆነ። ኣብዛኛዎቹ ግን አላወቁትም። ጥቂቶች ግን አውቀው ተቀበሉት። እነዚህ የአወቁትና የተቀበሉት የእግዚአብሔር የራሱ ልጆች ሆኑ። 

ጥያቄ፡– በሕይወታችሁ ውስጥ ኢየሱስን በማየት እግዚአብሔርን ማወቅ ስለሚገባቸው ሰዎች ኣስቡ። ከዚያም ስሞቻቸውን ጻፉ። በዚህ ሳምንት ኢየሱስን ለእነዚህ ሰዎች እንዴት ታቀርባላችሁ? ቃል ሳትናገሩ በድርጊት ብቻ ኢየሱስን ልታሳዩዋቸው የምትችሉባቸውን ሁኔታዎች ኣለቡ። ቀጥሎም ሳታስቀይሟቸው ኢየሱስን ልትገልጹላቸው የምትችሉበትን እነጋገር አስቡ። ኋላም አሳባችሁን ጻፉ። 17ኛ ጥያቄ፡- እናንተስ ኢየሱስን በተሻለ ሁኔታ እንዴት እያወቃችሁት ነው? ከዮሐንስ ወንጌል እንድ ምዕራፍ መርጣችሁ አሁኑኑ አንብቡ። ከዚያም ስለ ኢየሱስ ክፍሉ የሚያስተምራችሁን ጻፉ። ቀኑንም ስታስቡት ዋሉ። ከዚያም ተመልሳችሁ ኢየሱስን በማወቃችሁ እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ እንዴት እንዳወቃችሁት ጻፉ።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading