ትናንትና ሁሉም ሰው ኃጢአት እንደ ሠራ ተገንዝበን ነበር። ታዲያ ይህ ክርስቲያኖችን ሁሉ ያጠቃልላል? ክርስቲያኖችስ ቢሆኑ ከኃጢአት ነህ ናቸው ወይስ አሁንም ቢሆን ኃጢአት ያለበት ተግባርን እየፈጸሙ ናቸው? ዛሬ በኢየሱስ ክርስቶስ በሚያምኑ ሰዎች ሕይወት ውስጥ ስለሚሆነው ኃጢአት እንማራለን።
1. ክርስቲያኖች ከኃጢአት ተግባር ነፃ አይደሉም።
አንዳንድ ክርስቲያኖች በክርስቶስ የሚያምኑ እውነተኛ ክርስቲያኖች ከእንግዲህ ወዲያ ኃጢአት አይሠሩም ብለው ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ልምምድ ውስጥ ስለሚገቡ በመቀጠል ኃጢአት አይሠሩም ይላሉ። ክርስቲያኖች ከኃጢአት ነፃ ስለ መሆናቸውም ሆነ ነፃ ስላለመሆናቸው ወይም ነፃ ለመሆን ስለ መቻል አለመቻላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐንስ 1፡8፥10 አንብብ። ሀ) ሐዋርያው ኃጢአት አልሠራንም፥ ወይም ኃጢአት የለብንም ስለሚሉት ምን ይላል? ለ) 1ኛ ዮሐንስ 2፡12-14 } 2 5፡13 አንብብ። የዮሐንስ አንባቢያን እማኞች ወይስ የማያምኑ ሰዎች ነበሩ?
ጥያቄ፡– ሮሜ 7፡14-20 አንብብ። ሀ) ጳውሎላ በቁጥር 14 ራሱን እንዴት ይገልጻል? ለ) ይህን ሲል ምን ማለቱ ይመስላችኋል? ሐህ ከቁጥር 5-20 ድረስ ባለው ጳውሎስ ምን ማድረግ እንደ ፈለገ ነው የሚናገረው? መ) ጳውሎስ በእውነት ስለሚያደርገው ነገር ምን አለ? ሠ) ሐዋርያው ላደርገው አልፈልግም ያለው ምንን ነበር? ረ) ጳውሎስ በእርግጥ አላደርገውም ያለው ምን ነበር?
ጥያቄ፡– በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ምሳሌ የሚጠቀሱ ኃጢአት የሠሩ አማኞችን ታስታውሳላችሁ? ቢያንስ ሁለት ምሳሌዎች ጻፉ።
ሐዋርያው በ1ኛ ዮሐንስ መልእክቱን የጻፈው በኢየሱስ ክርስቶስ አማኞች ለሆኑት ነው። በ1ኛ ዮሐንስ 2፡12-14 የጻፈው ኃጢአታቸው ይቅር ለተባለላቸውና አብን ለሚያውቁ ልጆች እንዲሁም አብን ለሚያውቁ አባቶችና ክፉውን ላሸነፉ ወጣት ወንዶች ነው። በ1ኛ ዮሐንስ 3፡2 ደግሞ የእግዚአብሔር ልጆች ለሆኑት እንደ ጻፈ ይናገራል። እንዲሁም በ1ኛ ዮሐንስ 58 ውስጥ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለሚያምኑትና የዘላለምን ሕይወት ላገኙት መጻፉን ይናገራል። የ1ኛ ዮሐንስ መልእክት በግልጽ የተጻፈው ለሚያምኑ ክርስቲያኖች ነበር። በ1ኛ ዮሐንስ 1፡8 ማንኛቸውም ኃጢአት የለብንም ቢሉ ራሳቸውን እንደሚያታልሉና እውነትም እንደሌለባቸው አንባቢዎቹን ያስጠነቅቃቸዋል። ደግሞም በ1ኛ ዮሐንስ 1፡10 አንባቢዎቹ ኃጢአት የለብንም ቢሉ እግዚአብሔርን ውሸታም እንደሚያደርጉት ይገልጻል። እነዚህ ጥቅሶች ክርስቲያኖችም ቢሆኑ ኃጢአት መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ በግልጽ ያመለክታሉ። ስለዚህ ክርስቲያኖችም ጭምር ከኃጢአት ነፃ አይደሉም።
በሳል መንፈሳዊ ክርስቲያኖችም እንኳን ኃጢአትን ለመፈጸም ይፈተናሉ፤ አንዳንዴም ተሸንፈው ኃጢአት የሆኑ ተግባራትን ይፈጽማሉ። በሮሜ 7፡14 20 ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ ራሱ ክርስቲያን ከሆነ በኋላ እንኳን ምን ያህል ከኃጢአት ጋር ይታገል እንደ ነበረ ይገልጻል። (ርማ 77 ውስጥ ጳውሎስ አማኝ ከመሆኑ በፊት የነበረውን ስለ ራሱ ይገልጻል። በቁጥር 14 ደግሞ አማኝ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ይናገራል። በርሜ 14 በየጊዜው ያጋጥመው ከነበረ ኃጢአት ጋር ያደርግ ስለነበረው ብርቱ ትል፥ ጠንካራ በሆኑ ሐረጎች ተጠቅሞ ይገልጻል። እንዲህ ይላል፥ «የኃጢአት ባሪያ ልሆን ተሸጥሁ።» እነዚህ ቃላት እንዲህ ተብለው ሊተረጎሙ ይችላሉ «አሁንም ወደ ኋላ ተመልሼ የኃጢአት ባሪያ ልሆን ራሰን እሸጣለሁ።» ምንም እንኳን እግዚአብሔር ጳውሎስ የኃጢአት ባሪያ እንዳይሆን ቢቤዠውም (ሮሜ 6፡5-23) ኃጢአትን ለመሥራት የተፈተነባቸው ጊዜያት ነበሩ። እንዲያውም ወደ የኃጢአት ባርነት ገበያ የተመለሰበትም ጊዜ ነበር። እናም በሮሜ 7፡5-19 በውስጡ የነበረው የአሮጌው የኃጢአት ተፈጥሮ ፍላጎትና በክርስቶስ ካመነ በኋላ በተለወጠው አዲሱ ሰው ፍላጎት መካከል ስላጋጠመው ጦርነት መግለጹን ይቀጥላል። በክርስቶስም በማመኑ ምክንያት የሚጣላቸው ነገሮች (ቁ15)፥ ማድረግም የማይፈልጋቸው ኃጢአታዊ ነገሮች ነበሩ (ቁ16)፥ ይሁን እንጂ እነዚሁኑ ነገሮች ሲሠራ ራሱን ያገኛል (ቁ15)። በሌላ በኩል እንደ ክርስቶስ ተከታይ በእውነት ሊያደርጋቸው ይፈልግ የነበረ መልካም ነገሮች ነበሩት። ይሁን እንጂ እነዚህንም ለመፈጸም የሚያዳግተው ጊዜም ነበር (ቁ.18-19)። ሥጋው ወይም አሮጌውና ኃጢአታዊው ተፈጥሮው (ቁ17፥20) እየፈተነው በክርስቶስ ያገኛቸውን አዳዲስ ፍላጎቶች መታገሉን ቀጠለ (ቁ17)።
ጳውሎስ ለዘመናት ከኖሩት ጠንካራና ኃይለኛ ከነበሩ አማኞች መካከል አንዱና በሳል አማኝ ነበር። ስለዚህም ለብዙ ዓመታት በክርስትና ሕይወትና በአገልግሎት ተግባር ላይ ከቆየ በኋላ የሮሜን መልእክት ጽፎአል። ሆኖም ግን በዚህን ጊዜም እንኳን ኃጢአትን ለመሥራት ይፈተንና አንዳንድ ጊዜም ኃጢአት ይሠራ ነበር። በሮሜ 7 ውስጥ ያለው የጳውሎስ ገጠመኝ ሁሉም ክርስቲያኖች ኃጢአትን እንደሚሠሩ ለእኛ ጠቃሚ ማስታወሻ ነው።
ከዚህም በስተቀር መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአትን የሠሩ ብዙ አማኞችን በምሳሌነት አካትቶአል። ምናልባትም ጎላ ጎላ ያሉት ምሳሌዎች እነ ዳዊትና ጴጥሮስ ሊሆኑ ይችላሉ። እግዚአብሔር ዳዊትን «እንደ ልቤ የሆነ ሰው» ብሎ ጠርቶት ነበር (1ኛ ሳሙኤል 13፡14)። ነገር ግን የማመንዘርንና ነፍስ የመግደልን ኃጢአት ፈጸመ። ጴጥሮስ ከኢየሱስ ሦስት የቅርብ ደቀ መዛሙርት መካከል አንዱ የነበረና ታዳጊዋን ቤተ ክርስቲያን እንዲጠብቅ ኢየሱስ አደራ የጣለበት ነው (ዮሐንስ 21፡15-17)። ይሁን እንጂ ጰጥርስ ሦስት ጊዜ ካደው። እንዲሁም እጅግ በጣም ጠንካሮችና የበሰሉ አማኞች አልፎ አልፎ በኃጢአት ውስጥ እንደ ወደቁ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንገነዘባለን።
አማኞች ሁሉ በሕይወታቸው ውስጥ አንዳንድ ጊዜ ኃጢአት መሥራታቸው እውነት ከሆነ ደኅንነትን ያጣሉ ማለት ነው? ይህ ካልሆነ አማኞች ኃጢአት በሚያደርጉበት ጊዜ ምን ይደርስባቸዋል?
2. ክርስቲያኖች ኃጢአት በሚሠሩበት ጊዜ ምን ይደርስባቸዋል?
2.1 ክርስቲያኖች ኃጢአትን በሚሠሩበት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ያላቸው ሕጋዊ ደረጃቸው ዝቅ አይልም፥ አይለወጥም። ዘላለማዊ ደኅንነታቸውም አያጡም።
ጥያቄ፡- ሮማ 8፡1 አንብብ፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ለሆኑት የተረጋገጠላቸው ምንድን ነው?
ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐንስ 2፡1 አንብብ። ኃጢአትን የሚሠሩ ክርስቲያኖች በመንግሥተ ሰማይ ምን አላቸው?
ጥያቄ፡- ሮሜ 6፡23 እና ኤፌሶን 2፡8-9 አንብብ። ሀ) ደኅንነት እንዴት ይገለጻል? ለህ ደኅንነት እንዴት ይገኛል?
ወደ ኋላ ላይ በክርስቶስ የሚያምኑ እውነተኛ ክርስቲያኖች ደኅንነትን ያጡ ወይም አያጡ እንደሆነ ስለሚነሣው ጥያቄ እናጠናለን። በዚህ ትምህርት ላይ ግን ኃጢአት አማኞች ደኅንነትን እንዲያጡ ሊያደርግ እንደማይችል ደህና አድርጎ መገንዘብ ይጠቅማል። ሮሜ 6፡3 እና ኤፌሶን 2፡8-9 ደኅንነት በግለሰቦች መልካም ሕይወት ላይ የተመሠረተ አይደለም። እንዲሁም ደኅንነት ኃጢአት መሥራትን ለአቆሙ የሚሰጥ አይደለም። ደኅንነት በክርስቲያኖች ውስጥ ሊቆይ የሚችለው እነርሱ መልካሞች ስለሆኑ ወይም ኃጢአት መሥራት ስለአቆሙም አይደለም። ደኅንነት በክርስቶስ ላይ በሚኖረን እምነት እግዚአብሔር የሚቸረን ነፃ ስጦታ ነው። ሮሜ 8፡1 በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ጳውሎስ በርሜ 7 ላይ እንደገለጸው ከኃጢአት ጋር እየታገሉ ላሉትም ቢሆን እንኳ ኩነኔ የለባቸውም ይላል። በ1ኛ ዮሐንስ 2፡1 ላይ ማንም ኃጢአት ቢሠራ፥ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን ይላል። ክርስቲያኖች ኃጢአት ቢሠሩ ስለ እነርሱ አሁንም የሚሟገት ኢየሱስ አለ። በሕጋዊ መንገድ አሁንም ቢሆን ልጆቹ ናቸው።
በክርስቶስ የሚያምኑ ክርስቲያኖች ኃጢአት በሚፈጽሙበት ጊዜ የእግዚአብሔር ልጆች ሆነው የሚቆዩ ከሆነ ኃጢአታቸው ክብደት የለውም ማለት ነው? እንዲህ አይደለም። ክርስቲያኖች ኃጢአትን በሚሠሩበት ጊዜ ደኅንነትን ባያጡም ከባድ ሁኔታ ያጋጥማቸዋል። ኃጢአት በሚፈጽሙበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይ ምን ይደርሳል?
2.2 ክርስቲያኖች ኃጢአት ሲሠሩ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ይቋረጣል፥ ሕይወታቸው ይበላሻል፥ ወደ ንስሐ እንዲመጡም የእግዚአብሔርን ቅጣት ይቀበላሉ።
ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐ 1፡6 አንብብ። አንድ ሰው በጨለማ ውስጥ ቢሄድ ይህ ጥቅስ ምን ይደርስበታል ሊል ያስተምራል?
ጥያቄ፡- መዝ (38)፡1-4 አንብብ። ጻዊት በሠራው ኃጢአት ስለደረሰበት ሁኔታ ምን አለ?
ጥያቄ፡- ዕብ 12፡6፥9-11 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር ለሚወዳቸውና እንይ ልጆቹም ለሚቆጥራቸው ምን ያደርግላቸዋል? ለ) እግዚአብሔር በምን ምክንያት ይገሥጸናል? ሐ) የእግዚአብሔር ሣጹ ውጤት ምንድን ነው?
ጥያቄ፡- ዮሐ 15፡4 አንብብ። አማኞች በሕይወታቸው ውስጥ ፍሬ ለማፍራት ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?
ጥያቄ፡- ዮሐ 8፡34 አንብብ። ኃጢአትን በሚሠሩ ሁሉ ላይ ምን ይደርሳል?
ኃጢአትን የሚሠሩ አማኞች ደኅንነታቸውን እያጡም። ሆኖም ሌሎች አስቸጋሪና የሚያሠቃዩ ሁኔታዎች ይደርሱባቸዋል። በመጀመሪያ፥ ክርስቲያኖች ኃጢአትን ቢፈጽሙ፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው አንድነትና ግንኙነት ይቋረጣል። እግዚአብሔር ሰዎች ከእርሱ ጋር ግንኙነትና ቅርበት እንዲኖራቸውና በእርሱም ደስ እንዲሰኙ አድርጎ ፈጥሯቸዋል። ባለፈው ሳምንት እንደ ተከታተልነው አዳምና ሔዋን ኃጢአት እንደ ሠሩ ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ደስ የሚል ግንኙነት ተቋረጠ። ሰዎች በክርስቶስ በሚያምኑበት ጊዜ፥ ከእግዚአብሔር ጋር አዲስና አስደናቂ የሆነ ግንኙነት ይጀምራሉ። እግዚአብሔርንም ማወቅና በእርሱም መደሰት ይጀምራሉ። ግን ኃጢአት በሚሠሩበት ጊዜ፥ ያን ግንኙነት ያጣሉ። 1ኛ ዮሐ 1፡6 ሲናገር፥ አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት አለኝ እያለ በጨለማ የሚሄድ ከሆነ ይዋሻል ይላል። «በጨለማ መሄድ» ማለት ኃጢአትን መሥራት ነው። ኃጢአትን የሚሠራ ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት አለኝ ሊል አይችልም። አዳምና ሔዋን በዔድን ገነት በነበሩበት ጊዜ እንደ ደረሰባቸው ሁሉ፥ ኃጢአት አማኛች ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን አንድነት ያሰላሻል። ከእግዚአብሔር ጋር ያለው አንድነት ሲፈርስ ደግሞ፥ በእግዚአብሔርና ኃጢአት በሠሩት በአማኞች መካከል መለያየት ይመጣል። ይሁን እንጂ መለያየቱ ዘላለማዊ አይደለም። ምክንያቱም አማኝ ደኅንነት አላጣምና። ሆኖም መለያየቱ በኃጢአታቸው ምክንያት ከእግዚአብሔር በተለዩ ሁሉ ላይ የሚደርስ የሞት ሽታ ነው። በመሆኑም ኃጢአት ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት በማቋረጥ ከእግዚአብሔር ይለየናል።
ሁለተኛው የኃጢአት ውጤት በአማኙ ሕይወት ውስጥ ብዙ ጊዜ እካላዊና ስሜታዊ ሥቃይን ያመጣል። በመዝ. (38)፡1-4 ከኃጢአቱ የተነሣ የእግዚአብሔር ክንድ በእርሱ ላይ እንደ መጣና የእግዚአብሔር ፍላጻ እንደ ወጋው ዳዊት ይናገራል። በቁጥር 3 ውስጥ ዳዊት የእግዚአብሔር ክንድ በእውን በአካሉ እንደ ተሰማው ይናገራል። በኃጢአቱ ምክንያትም ሰውነቱ እየተሠቃየ ነበር። የዳዊት ኃጢአት ሰውነቱን በቀጥታ እንደ ጎጻው ወይም እግዚአብሔር ለግምጸ ብሎ ሕመም ልኮበት እንደሆነ አናውቅም። ነገር ቀን ዳዊት ከኃጢአቱ የተነሣ ሰውነቱ መሠቃየቱን ይነግረናል። ጻዊት በመንፈሱና በስሜቱም ረገድ ተሠቃይቶ ነበር። በቁጥር 4 ውስጥ፥ በደሉ ከባድ ስለነበረ፥ እንደ ከባድ ሸክም እንደ ተማነው ይናገራል። ስለሆነም ዳዊት በኃጢአቱ ምክንያት በመንፈሱና በስሜቱ ሁሉ ተሠቃይቷል፡፡
ኃጢአት ብዙ ጊዜ አካላዊ ጥፋትን ያስከትላል። እንዴዚሁ ሁሉ አዘውትረው አልኮል የሚጠጡ ወይም የሚያደነዝዙ ሱስ አስያዥ ዕጽዋትን የሚጠቀሙ ሰዎች ሰውነታቸውን ከመጉዳታቸውም የላይ በቀላሉ በበሽታ እንዲጠቃ ያደርጉታል። በዚሁ ረገድ ከጋብቻ ውጪ ቀብረ ሥጋ የሚፈጽሙ ሰዎች ሰውነታቸውን ለኤድስና ለሌሎችም አደገኛ ለሆኑ የአባላዘር በሽታዎች አሳልፈው ይሰጣሉ። ሐኪሞች እንደሚነግሩንሁልጊዜ የሚቆጡና ምሬት የሚያጠቃቸው ሰዎች በቀላሉ የሚታመሙ ሲሆኑ፥ በተለይ የልብ ድካምና የደም ግፊት በሽታ ይይዛቸዋል ይላሉ። ኃጢአት ዘወትር ለአካል ጉዳት ያጋልጣል። ክርስቲያኖች ኃጢአት በሠሩ ቁጥር የራሳቸውን ሰውነት ይጎዳሉ። አንዳንድ ጊዜ ኃጢአት በቀጥታ አካላዊ በሽታ ባያመጣም እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታቸው ለመገሠጽ በሽታ ሊልክባቸው ይችላል። በመዝሙር (38) ውስጥ እንደ ተጻፈው እግዚአብሔር በዳዊት ላይ ያደረገው ይህንኑ ይመስላል። ታዲያ እንዲህ ሲባል ሰው በታመመ ቁጥር ሁሉ እግዚአብሔር የቅጣት በሽታ አመጣበት ማለት አይደለም። የኢዮብ ወዳጆች በሽታ ሁሉ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ቅጣት ይመስላቸው ነበር። ስለዚህ አመለካከታቸውም እግዚአብሔር ገሥጹአቸዋል (ኢዮብ 42፡7)። አብዛኛውን ጊዜ የምንታመመው በሽታው ለቅጣት ስለ መጣብን አይደለም። እግዚአብሔር ኃጢአትን ሁሉ በበሽታ አይቀጣም። ደግሞም በሽታ ሁሉ የእግዚአብሔር የቅጣት ውጤት አይደለም። ነገር ግን ኃጢአት ሠርታችሁ ከዚያ በኋላ ብትታመሙ እግዚአብሔር ኃጢአታችሁ ምንኛ የከፋ መሆኑን ሊያሳስባችሁና ወደ ንስሐም ሊጠራችሁ በሽታውን አምጥቶባችሁ ሊሆን ይችላል።
መዝ (38) ጨምሮ የሚያሳስበን ክርስቲያኖች ኃጢአት በሚሠሩበት ጊዜ የኃጢአታቸው በደል እንደሚሰማቸውና ያ በደልም ከባድ የሕሊና ሸክም እንደሚሆንባቸው ነው ይህ እንግዲህ በሕይወታቸው ውስጥ የሚከሰት ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ግንኙነት የመቋረጡ አንድ ገጽታ ነው። አማኞች ከእግዚአብሔር ጋር በግንኙነት መኖር ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቁት ነው። ግን ይህ ግንኙነታቸው በኃጢአታቸው ምክንያት ሲቋረጥ እጅግ ያዝናሉ፤ የሕሊና ሸክምም ይሆንባቸዋል። ይህን ጊዜ እግዚአብሔር ልጆቹ ወደ እርሱ በንስሐ እንዲመለሱና ግንኙነታቸውን እንዲያድሱ በዚህ የሕሊና ኅዘንና የሕሊና ሸክም ይጠቀማል። ስለሆነም ክርስቲያኖች ኃጢአትን ሲሠሩ በአካል፣ በመንፈስና በስሜት ይሠቃያሉ።
መዝ (38) ደግሞ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ኃጢአት ስለሚያመጣው ሦስተኛው ውጤት ይነግረናል። ይህም የእግዚአብሔር ግሣጼ ነው። የዳዊት ሥቃይ የእግዚአብሔር ግሣጹ አንዱ ክፍል ነው [መዝ. (38)፡፡ እግዚአብሔርም ይህን ያደረገው፥ ዳዊትን በንስሐ ለመመለስ ብሎ ነው። እንዲሁም ዕብራውያን 12 እግዚአብሔር ስለሚወዳቸው ከአባት ጋር በማነጻጸር አፍቃሪ አባትነቱን ያስተምረናል። እናም የሚያፈቅሩ አባቶች ልጆቻቸውን በሚቀጡአቸው ጊዜ በቁጣና በጥላቻ ስሜት አይቀጡአቸውም። ልጆቻቸውን የሚወዱ አባቶች፥ ልጆቻቸው በአእምሮና በአካል እንዲያድጉ ብቻ ላይሆን፥ ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች እንዲሆኑ ይጥራሉ። ስለዚህ ልጆቻቸውን የሚወዱ ወላጆች በሚያጠፉበት ጊዜ ተከታትለው በመቅጣት
መልካም ሆነው እንዲያድጉ ያደርጋሉ። ዕብ. 12፡7-10 እግዚአብሔር እውነተኛ የሆኑ ልጆቹን ይቀጣል ይላል። ይህንንም የሚያደርግበት ምክንያት የእርሱ ቅድስና ተካፋዮች እንዲሆኑ ነው። በመሠረቱ እግዚአብሔር ልጆቹን ይወድዳል፥ ደግሞም የሚበጃቸውን ያውቃል። ለገዛ ደስታቸውና ለዘላለማዊ መጠበቃቸው እጅግ ጠቃሚው በቅድስና እርሱን መምሰላቸው መሆኑን ያውቃል። ስለዚህ እግዚአብሔር አማኞች ኃጢአትን በሚሠሩበት ጊዜ በቅድስና እንዲያድጉና እርሱን የበለጠ እንዲመስሉ ይቀጣቸዋል።
አራተኛ፥ ኃጢአትን የሚያደርጉ ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከማጣታቸውም በላይ በክርስትና ሕይወታቸውም ውስጥ የተሳካላቸው አይሆኑም። በዮሐ 5፡4 ውስጥ ተካታዮቹ በኢየሱስ ባይኖሩ ፍሬ እንደማያፈሩ አረጋግጧል። «በኢየሱስ መኖር» ማለት፥ ለኢየሱስ መታዘዝ፥ እርሱን ማመን፥ ለእርሱም ክብር መኖር ማለት ሲሆን፥ ክርስቲያኖች ይህን በሚያደርጉበት ጊዜ በሕይወታቸው ውስጥ ስኬታማ ውጤትን ያገኛሉ። በሌሎችም ሕይወት ውስጥ ስኬትን ያስገኛሉ። በክርስትና ሕይወታቸውም የበሰሉና የጎለበቱ ሆነው ያድጋሉ። ይህን ጊዜም የማያምኑ ሰዎች ክርስቶስን እንደ ግል መድኃኒታቸው ወደ መቀበል ይመጣሉ። ሌሎች አማኞችም በክርስትና ሕይወታቸው ያድጋሉ። እንግዲህ አማኞች በእርሱ ከኖሩ ፍሬ ያፈራሉ ብሎ ክርስቶስ የተናገረው ይኸው ነው። ነገር ግን በእርሱ ላይ ዐምፀው ሳይታዘዙት ቢቀሩ ምንም ዓይነት ፍሬ ሊያፈሩ አይችሉም። ከዚህም የተነሣ በክርስትና ሕይወታቸው ውስጥ መልካም ውጤት ሊኖር አይችልም። ደግሞ ሌሎችን ለማገልገል በሚያደርጉት ጥረት ውጤት አልባ ይሆናሉ። እነሆ፥ እንግዲህ ኃጢአት በዚህ መንገድ የክርስቲያኖችን ሕይወትና አገልግሎት እያበላሸ ውጤት እንዳያስመዘግቡ መና ያስቀራቸዋል።
በመጨረሻም፥ አማኞች (ወይም ማንም ቢሆን) ኃጢአትን በሚሠሩበት ጊዜ፥ የኃጢአት ባሪያዎች ይሆናሉ። በዮሐ 8፡34 ውስጥ ኃጢአትን የሚያደርጉ ሁሉ የኃጢአት ባሪያዎች ናቸው ሲል ኢየሱስ ይናገራል። ኃጢአትን በምንፈጽምበት ጊዜ ሁሉ በሁለት መንገዶች የኃጢአት ባሪያዎች እንሆናለን። በመጀመሪያ፥ የኃጢአት ባሪያ መሆን ማለት በኃጢአት ወጥመድ ውስጥ ገባን ማለት ነው። ስለዚህ ኃጢአት በሠራን ቁጥር ኃጢአት አመል ይሆንብንና ልንላቀቀው ያዳግተናል። በዋሸን ቁጥር ውሸት ልማዳችን ይሆንና በየጊዜው ደጋግመን በቀላሉ እንዋሻለን። በየጊዜው ስንቆጣ፥ ቁጣው ልምድ ይሆንብንና በየጊዜው ደጋግመን በቀላሉ እንጣለን። የፍትወተ ሥጋን ምኞት በምናስተናግድበት ጊዜ፥ ይህ የዘወትር አመል ይሆንብንና በየጊዜው በቀላሉ በምኞቱ እንጠመዳለን። ስለዚህ ኃጢአት በሠራን ቁጥር ሁሉ ራሳችንን የኃጢአት ባሪያዎች እናደርጋለን። ምክንያቱም ኃጢአትን ባዘወተርነው መጠን፥ በኃጢአት ወጥመድ ውስጥ ስለምንገባ ነው። ሁለተኛ፥ የኃጢአት ባሪያ መሆን ማለት የኃጢአት ቅጣት ከሆነው ሞት አናመልጥም ማለት ነው። ባለፈው ሳምንት እንዳየነው ኃጢአት ምን ጊዜም ሞትን ያመጣብናል። ምንም እንኳን ኃጢአት ወዲያውኑ በአካል እንድንሞት ባያደርግም፥ ብዙ ጊዜ በአካላችን ጉዳትን ያስከትላል። ምንም እንኳን በክርስቶስ የምናምን ብንሆንና በዚህ ምክንያት የምንሠራው ኃጢአት ደኅንነታችንን ባያሳጣንም፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ንኙነት እንዲደናቀፍና ከእርሱ ጋር ያለን የተቀደሰ ክቡር ቀንኙነታችን እንዲቋረጥ ያደርጋል። ኃጢአትን በምንሠራበት ጊዜ ሁሉ ወደ ልማዳዊ ኃጢአት ወጥመድ ውስጥ እንገባለን። በዚህም የኃጢአት ቅጣት የሆነው ሞት ወጥመድ ሆኖ ይይዘናል ማለት ነው።
ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚያደርጉትን ኃጢአት በቀላሉ ሊተዉት የሚችሉ ይመስላቸዋል። ኃጢአት ለመሥራት በሚፈተኑበትም ጊዜ «ይህን ኃጢአት አንድ ጊዜ ብቻ እሠራና ሁለተኛ አይደግመኝም፥ የመጨረሻም ይሆንብኛል” ይላሉ።
ጥያቄ፡– በዚህን ጊዜ ይህን ኃጢአት አሁን ብቻ ላድርና ሌላ ጊዜ ደማ አላደርገውም” በሚል ፈተና ውስጥ የገባችሁበትን ጊዜ አለቡ። በዚህ ጊዜ ያለፋችሁበትን ልምምድ በማለታወሻ ደብተሮቻችሁ ውስጥ ጻፉት። በተጨባጭ የሆነው ምንድን ነው?
ኃጢአት በምንፈጽምበት ጊዜ፡ ራሳችንን የኃጢአት ባሪያዎች እናደርጋለን። ከዚህ የተነሣ ኃጢአቱ ልማድ ይሆንብንና መላቀቅ ያቅተናል። ኃጢአትን በምናደርግበት ጊዜ ሁሉ ከኃጢአት ቅጣት ማለትም ከሞት በሚመጣ አካላዊና መንፈሳዊ ጉዳት እንሠቃያለን።
ጥያቄ፡- በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ጋር ያለ እንኙነት መቋረጥን አካላዊና ስሜታዊ ሥቃይን፥ የእግዚአብሔር ቅጣትን በክርስትና ሕይወታችንም ሆነ በአገልግሎታችን ፍሬ አልባነትንና የኃጢአት ባርነትንም ያስከትልብናል። በሕይወታችሁ ውስጥ የገጠማችሁ ይህን የመሰለ የከፋ የኃጢአት ውጤት ካለ በማለታወሻ ደብተራችሁ ውስጥ እንደ ል ምስክርነት ጻፉት።
3. ክርስቲያኖች ኃጢአትን በሚሠሩበት ጊዜ ምን ያድርጉ?
ጥያቄ፡- መዝ. (32)፡3-5 አንብብ። ሀ) ዳዊት ኃጢአቱን ከመናዘዙ በፊት ምን ተሰማው? ለ) ዳዊት ኃጢአቱን ከተናዘዘ በኋላ ምን ሆነ?
ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐ 1፡9 አንብብ፡፡ እኛስ ኃጢአታችንን በምንናዘዝበት ጊዜ ምን ይሆናል?
ክርስቲያኖች ኃጢአት በሚፈጽሙበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር የተቋረጠባቸውን ግንኙነት የሚጠግኑበት አንድ መንገድ ብቻ አለ። ይህም ኃጢአታቸውን ለእግዚአብሔር መናዘዝ ነው። በመዝሙር 32 ውስጥ ዳዊት ኃጢአቱን ከመናዘዙ በፊት ሰውነቱና መንፈሱ በጣም እንደ ተሠቃየ ይናገራል። ከዚያም ኃጢአቱን ስለ ተናዘዘ፥ እግዚአብሔር ይቅርታን ሰጠው። በ1ኛ ዮሐ 19 ኃጢአታችን ብንናዘዝ እርሱ ሁልጊዜ ታማኝና ይቅር ባይ ስለሆነ ይቅርታን እንደሚሰጠን ተስፋ ገብቶልናል።
ንስሐ ወይም ኑዛዜ ምንድን ነው? ንስሐ ኃጢአት ምንኛ የከፋ መሆኑን ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋር መስማማትና ኃጢአት መሥራታችንን በእርሱ ፊት መናዘዝ ነው። ግን ሰዎች በእውነት ኃጢአት መሥራታቸውንም ሆነ ኃጢአት የራሳቸው ስሕተት ውጤት መሆኑን አምነው አይቀበሉም። እንዲያውም የሠሩት ኃጢአት ይህን ያህል ክብደት የለውም ይላሉ። ለሠሩትም ኃጢአት ሌሎችን ይወቅሳሉ፥ ጥፋቱንም በእነርሱ ላይ ያላክካሉ። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ስለሚሠሩት ኃጢአት እግዚአብሔርን ያማርራሉ። እርሱ ሳይፈቅድ ኖር ኃጢአት ለመሥራት እንደማይፈተኑ አድርገው ያስባሉ። ታዲያ ሰዎች ስለ ኃጢአት እንዲህ ያለ አስተሳሰብ እስካላቸው ድረስ ይቅርታን ሊያገኙ አይችሉም። ስለዚህ ንስሐ ማለት ምን ያህል ኃጢአተኞች እንደሆኑና ኃጢአታችንም እግዚአብሔርን ምን ያህል እንደ ጎዳው ማወቅ፥ ለኃጢአታችንም በደል ኃላፊዎች እኛው ራሳችን መሆናችንን ከእግዚአብሔር ጋር መስማማትና መቀበል የኃጢአታችን አስከፊ ውጤቶች ሁሉ በእኛ ምክንያት መፈጸማቸውን ማመን ነው። ንስሐ ማለት እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችን እንደሚሰማው ሁሉ እኛንም እንዲሰማን ማድረግ ነው።
ኃጢአታችን ምን ያህል የከፋ ስለ መሆኑ ለእግዚአብሔር ከነገርንና ከእርሱም ጋር በእውነት ከተስማማን፥ ንስሐችን መንገዳችንን ለመለወጥ መወሰናችንን ያካተተ ይሆናል። ቀድሞ የሠራነውን ያን ኃጢአት ደግመን ላለመፈጸም ከልብ የሆነ ፍላጎት እናሳያለን። በኃጢአታችን ያሳዘንናቸውን ሁሉ ይቅርታ ለመጠየቅ ለመታረቅና ሰላምን ለማበጀት እንፈልጋለን። እውነተኛና ልባዊ ኑዛዜ ኃጢአታችን እጅግ የከፋ ስለ መሆኑ በእውነት ከእግዚአብሔር ጋር የሚስማማ እውነተኛ ንስሐ ደግሞ ኃጢአት ላለማድረግ ባለን መሻትና ከሌሎችም ጋር እርቅ ለማድረግ ባለን ፈቃደኝነት ይገለጻል።
ጥያቄ፡– በሕይወታችሁ ውስጥ ኃጢአት መሆናቸውን በማመን ያልተናዘዛችኋቸው ኃጢአቶች አሉ? እንዲሁም በሕይወታችሁ ውስጥ የፈጸማችሁትና እንደ ተራ ነገር የቆጠራችሁት ወይም ያንን ኃጢአት ያሠሩዋችሁ ሌሎች ሰዎች ናቸው ብላችሁ እነርሱን የወቀሳችሁበት ምን ኃጢአት አለ? ካለ ጻፉትና አሁኑኑ ለእግዚአብሔር ተናዘዙት።
ኃጢአታችንን ለእርሱ በምንናዘዝበት ጊዜ በደኅንነታችን አማካኝነት ከእርሱ በሚታደስልን ጣፋጭ ግንኙነትና አንድነት በደስታ እንደምንረካ እግዚአብሔር ተስፋ ይሰጠናል። ስለዚህ ንስሐ ይቅርታን የሚያሰጠን ሲሆን ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን ግንኙነትም ያድስልናል።