ለሙስሊም ወዳጆቻችን ጥያቄዎች የተሰጠ ምላሽ፣ መግቢያ
ከክርስትና ውጪ፣ ሃይማኖቱን በሚሽን/በተልዕኮ በዓለም ላይ ለማስፋፋት ጥረት የሚያደርግ ብቸኛ ሃይማኖት እስልምና ነው፡፡ የእስልምና እምነት አስፋፊዎች የመጨረሻ ግብ ዓለምን በእስልምና መሸፈን መሆኑ ምስጢር አይደለም፡፡ እያንዳንዱ ሙስሊም፣ ሙስሊም ያልሆኑ ሌሎች ሰዎችን ወደ እምነቱ ከመጥራት ሃላፊነት በተጨማሪ የሙሐመድ አስተምህሮዎችንና የሃይማኖቱን መሠረታዊ መመሪያዎች የመፈፀም ግዳጅ አለበት፡፡ ይህ፣ ከሃይማኖቱ ውጪ ያሉ ሰዎችን ወደ እምነቱ የመጋበዝ ሥራ ዳዋ (dawah) በመባል …