የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

ብሉይ ኪዳን ስለ ክርስቶስ ሕይወትና አገልግሎት በሚያመለክቱ ብዙ ትንቢቶች የተሞላ መጽሐፍ ነው። ስለዚህ ክፍል ውስጥ ከእነዚህ ብዙዎቹን ትንቢቶች እናጠናለን።

ስለ ሰይጣን መሸነፍ የሚናገር ትንቢት 

ጥያቄ፡– ዘፍጥረት 3፡1-5 አንብቡ፡ ሀ) በቁጥር 4 ላይ እግዚአብሔር ለእባቡ ምን ቅጣትን ሰጠ? ለ) በቁጥር ቱ ላይ ደሞ እግዚአብሔር? በእባቡ ላይ ምን ተላፋን ተናገረ? 

ጥያቄ፡– ራእይ 29 አንብቡ። በእርግጥ በአትክልቱ ውስጥ የነበረው እባብ ማን ነበር? 

በዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ላይ ተጽፎ የምናገኘው ስለ ሰው ልጅ የመጀመሪያው ኀጢአት ነው። አዳኞና ሐየን ሰይጣን በእባብ ተመስሎ መጥቶ በፈተናቸው ጊዜ ተሸንፈው ኀጢአትን ሠሩ፡ ይህ ጥቅስ እባቡ አስቀድሞ ምን ይመስል እንደ ነበረ ስለማይነገረን እሮች፥ ክንፎች ወይም ሌላ ነገር ነበረው፥ መልኩም እንዲህ ነው ብለን በግምት መናገር አንችልም። ከዚህም ባሻገር በእባቡና በሰይጣን መካከል ስለነበረውም ንኙነት የተነገረ ሰለሌላ ልጽ አይደለም። ምንም እንኳን ዘፍጥረት 1፥14 ላይ ወደ አዳምና ሔዋን ዘንድ ተራ እባብ መጥቶ እንደ ፈተናቸው ስልጽ የተነገረ ቢሆንም በሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ በተለይም በራእይ 12፡9 ላይ እንደ ተገለጸው፥ ይህ እባብ ተራ እሳብ ብቻ እንዳልነበረ ያመለክታል። ከዚህ እባብ በስተጀርባ የእግዚአብሔር ጠላት የሆነው ሰይጣን እንዳለ ይታያል። ይህም ሲባል ምናልባት ላይጣን በእባቡ ውስጥ እድር ይሆናል። ወይም ሰይጣን ራሱ በእባብ ተመስሉ ቀርቧቸው ይሆናል። ምናልባትም ይህ እባብ ልዩ ጥበብ ኖሮት ይህን ፈተና በማራመድ ረገድ ሰይጣንን ሊረዳ ተስማምተ ሊሆን ይችላል። በሰይጣኑና በእባቡ መካከል ስለነበረው ንኙነት በግልጽ የምናውቀው ባይኖርም፥ በሆነ መንገድ ሰይጣን አዳምና ሔዋንን ለመፈተን በእባቡ መጠቀሙን ግን እናውቃለን። 

ሰይጣን አዳምና ሔዋን ኃጢአት እንዲሠሩ ከፈተነ በኋላ፥ እግዚአብሔር ሦስቱም ለፈጸሙት በደል የቅጣት ፍርፋን ሰጠ። በዚህም እግዚአብሔር በመጀመሪያ የቅጣት ፍርዱን የሰጠው ለተለየው እንስሳ ማለትም ለእሳቡ ነበር። እግዚአብሔር የሰጠው የእርን ፍርድ በፍጥረት ሁሉ ላይ የደረሰ ቢሆንም፥ እባቡ ቀን በከበደ ሁኔታ እርግማኑ ወረደበት (ዘፍጥረት 3፡17) እባብ ይህን ተንኮል ከፈጸሙ በፊት የፈለገው ዓይነት ቅርጽ ይኑረው፥ ዛሬ ግን በሆዱ እየተጥመለመላ አቧራ ይልሳል፡ አቧራ መላስ የመሸነፍ ምልክት ነው። 

ነገር ግን ይህ ቅጣት በቁጥር 5 ላይ ሰፋ ያለ ሆኖ ቀርቧል። ከዚህን ጊዜ ጀምሮ በእባቦችና በሰው ልጆች መካከል ጥላቻ ተመሠረተ። ቀን ጥላቻው በሰዎችና በተራ እባቦች መካከል ካለው ያለፈ ነው፡ ጥላቻውም ከሰዎችና ከእባቡ በስተጀርባ ካለው ሰይጣን ጋር የሚደረገውን ጦርነት ይጨምራል። ሰይጣንና ተከታዮቹ በቻሉት ሁሉ በሰዎች ላይ ጥፋትን ለማድረስ አይቦዝኑም፡ የመጨረሻውም ጦርነት በሰይጣንና በሴቲቱ ዘር መካከል የሚደረገው ይሆናል። ይህ ዘር ከሴቲቱ ተወልዶ የሰይጣንን ራስ ይቀጠቅጣል። እንዲህም ማለት ይህ የሚወለደው፥ ሰይጣንን ድል ማድረግ ብቻ ሳይሆን ያጠፋዋል ማለት ነው። ተራ እባቦች የሰዎችን ተረከዝ እንደሚነድፉ ሁሉ፥ ሰይጣንም የሴቲቱን ዘር ነድፎ ያቆስለዋል። ይሁን እንጂ ሊገድለውና እስከ ወዲያኛው ሊያጠፋው አይችልም ነበር። ከሴቲቱ የተወለደው ዘር በመዉረሻ ድልን ይጎናጸፋል። 

የብሉይ ኪዳን አንባቢዎች አንድ ቀን ከሴቲቱ የሚወለደው ዘር ሰይጣንን ክፉኛ እንደሚያጠቃውና እንደሚያሸንፈውም በዚህ ክፍለ ምንባብ የተስፋ ቃልን አይተውበታል። ይሁንና የእግዚአብሔር ሰዎችም ይህን ትንቢት በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሙሉ በሙሉ እስኪፈጸም ድረስ አልተገነዘቡትም ነበር። 

ጥያቄ፡– ገላትያ 4፡4 አንብቡ። ሐዋርያው ጳውሎስ ኢየሱስ ከእነማን ተወለደ አለ? 

ጥያቄ፡- ቆላስይላ 2፡15 አንብቡ። በመስቀል ላይ ምን ተደረገ? 

በገላትያ 4፡4 ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ፥ ዘፍጥረት ምዕራፍ ሦስትን በሚያስታውስ ቃል ይጠቀማል። ኢየሱስ ከሌቲቱ የተወለደው ነው። ምንም እንኳን በተሰቀለ ጊዜ በሰይጣን የቆሰለ ቢሆን፥ ላቅላቱ ሽንፈት አልነበረም። ይልቅስ ቆላስይስ ምዕራፍ 25፡ በሰይጣን ላይ የተገኘ ድልና ሰይጣንን ያሸነፈ ድርጊት እንደሆነ ይናገራል። ዘፍጥረት 14-5 ያለው ክፍል ሰይጣንን ድል የሚያደር አዳኝ እንደሚመጣና በሰዎች ላይ በኃጢአት ምክንያት የመጣውን መርገም እንደሚያስወግድ የተናገረ የመጀመሪያው ትንቢት ነበር። 

አሁንም ሰይጣን እኛን ወደ ኃጢአት ውስጥ ለማስገባት በልዩ ልዩ ዓይነት የመፈተኛ ዘዴዎች ይጠቀማል። ከእነዚህም አንዱ በዙሪያችን ያለውና እንድንከተለው የሚገፋፋን ዓለም ነው። ሌላው የሰይጣን መፈተኛ መሣሪያ ደሞ ይህ በትዕቢትና በምኞት የተሞላ ሥጋችን ነው (1ኛ ዮሐንስ 2፡5 16)። ሰይጣን አዳምና ሔዋንን ለመፈተን እባብን መሣሪያ አድርጎ እንደ ተጠቀመበት፥ እኛንም በዓለም ቁሳቁሶች ተጠቅሞ ወደ ፈተና ያስገባናል። ሰይጣን በሌላ ጊዜ ደግሞ መልካም የሆነ ነገር ያሳየንና በትክክለኛ መንገድ ሳይሆን በተንኮል እንድናገኘው ይፈትነናል። 

ጥያቄ፡- ሰይጣን ምን የዓለምን ነገሮች ወይም የሥጋን ምኞቶችና ትዕቢቶችን በመጠቀም ነው የሚፈትናችሁ? ታዲያ እነዚህን ፈተናዎች እንዴት ልታሸንፉ ትችላላችሁ? 

አንዳንድ ጊዜ ሰይጣን በገንዘብና በንብረት ተጠቅሞ ይፈትነናል። በሌላ ጊዜ ደግሞ ሥጋዊ ምኞትን በማነሣሣትም ሆነ የምቀኝነትን ስሜት በመቀስቀለ ይፈትነናል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሌሎች ሰዎች ላይ በቂም እንድንነግሣ በማድረግ ይፈትነናል። ሰይጣን በዓለም ወይም በሥጋችን ተጠቅሞ ሲፈትነን፥ የሰይጣንን ራስ በመስቀል ላይ በቀጠቀጠው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ፈተናውን ልናሸንፍ እንችላለን። ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰይጣንን ድል አድርጓልና፥ ተከታዮቹም በሰይጣን ላይ ድልን ይቀዳጃሉ። ጌታ ኢየሱስ ወደ እርሱ ለሚመጡ ሁሉ ፈተናን የሚቋቋሙበት ኃይልን እንደሚሰጣቸው የተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል። እናንተም ለሚያጋጥሟችሁ እነዚህን የመሰሉ ትላልቅ ፈተናዎች ክርስቶስ የአሸናፊነትን ኃይል ይሰጣችሁ ዘንድ አሁኑኑ ጥቂት ደቂቃዎችን በመውሰድ ጸልዩ። 

ሕዝቦች ሁሉ እንደሚባረኩ የተነገረ ትንቢት 

ጥያቄ፡- ዘፍጥረት 12፡3፤ 18፡18፤ 22፡18፤ 26፡4፤ 28፡14 አንብቡ። በእነዚህ ክፍለ ምንባቦች ውስጥ ምን የሚል የተስፋ ቃል ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ተደጋግሞ ተነገረ? 

ጥያቄ፡- ማቴዎስ 12፥ 16 አንብቡ። ኢየሱስ በዘር ሐረጉ በመጀመሪያ ከማን ወገን መጣ? 

ጥያቄ፡- የሐዋ. 3፡5-26፤ ገላትያ 3፡8፥ 16 እንብቡ። እግዚአብሔር ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ እንዴት ተስፋውን ፈጸመላቸው? 

እግዚአብሔር አብርሃምን ቤት ንብረቱን ትቶ እርሱ ወደሚያሳየው አዲስ አገር እንዲሄድ በጠራው ጊዜ ብዙ ተስፋ ሰጥቶት ነበር። በተስፋውም ታላቅ ሕዝብ እንደሚያደርገውና ታዋቂም እንደሚሆን አረጋግጦለታል፡ የሚባርኩትን እንደሚባርክና የሚረግሙትንም እንደሚረግም ተስፋ ገብቶለታል። በእርሱ አማካይነትም የዓለምን ሕዝቦች እንደሚባርክ ተስፋ ሰጥቶታል። እንደዚሁም እግዚአብሔር በዘፍጥረት 18፡18 እና 22፡18 ውስጥ በአብርሃም በኩል የዓለምን ሕዝቦች እንደሚባርክም ቃል ገብቶለታል። እንደዚሁም በዘፍጥረት 26፡4 ላይ ተመሳሳይ ተስፋ ለይስሐቅ ሰጥቶታል። በተጨማሪ በዘፍጥረት 28፡14 ውስጥ ለያዕቆብ ይህንኑ ተስፋ አሳውቆታል። እነዚህ የሃይማኖት አባቶች እግዚአብሔር ይህን የተስፋ ቃል እንዴት ባለ ሁኔታ ከፍጻሜ እንደሚያደርሰው ተገንዝበውታል ብሎ ለመናገር ሙሉ በሙሉ አያስደፍርም። ነገር ግን አዲስ ኪዳን ኢየሱስ በቀጥታ የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ ዘር መሆኑን በግልጽ ያስረዳል (ማቴዎስ 1፡2፥16)። ይህ ተስፋም ሊፈጸም የቻለው በኢየሱስና ለዓለም ሁሉ በሰጠው ደኅንነት አማካይነት ነው (የሐዋ. 3፡25-26፤ ገላ. 3፡8፡ 16)፡፡ 

የንጉሥና የመንግሥት ትንቢት 

ጥያቄ፡- ዘፍጥረት 49፡8-12 አንብቡ። ሀ) በቁጥር 8 ላይ እንደተጠቀሰው፥ የይሁዳ ወንድሞች ከእርሱ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት እንዴት ያለ ይሆናል? ለ) በቁጥር 10 ላይ ለይሁዳ ምን ተስፋ ተሰጠው? ሐ) ይህ ለይሁዳ የተሰጠ ተስፋ እስከ ምን ይዘልቃል? መ) ሕዝቦቹ ምን ያደርጋሉ? 

በዘፍጥረት ምዕራፍ 49 ላይ የተጻፈው ያዕቆብ ለአሥራ ሁለት ልጆቹ የሰጠው የበረከት ቃል ነው። ያዕቆብ ይሁዳን በተለየ ሁኔታ በባረከው ጊዜ፥ ጠላቶቹን ድል እንደሚያደርግና የተቀሩት የእስራኤል ነገዶች በፊቱ ዝቅ ብለው እንደሚሰግዱለት ነግሮት ነበር። ይህ ማለት ይሁዳ ገዥያቸው ይሆናል ማለት ነው። እንደ ያዕቆብ አገላለጽ፥ ይሁዳ የተቀሩትን የእስራኤል ነገዶች እንደሚገዛ የተሰጠው ተስፋ የበትረ መንግሥትና የገዥነት ዘንግ ባለቤትነት የተገባው እስኪመጣ ድረስ ይቀጥላል። ይህ የሚያስረዳን እንደ እግዚአብሔር ዕቅድ የወደፊቱ የእስራኤል ነገሥታት ከይሁዳ ነገድ እንደሚመጡ ነው። ከዚህን ጊዜ ጀምሮ ይሁዳ በእስራኤል ሕዝብ ላይ የሚገባውን የግዛት ሥልጣን ተቀዳጅቶ ይመራል። ይህ ንጉሥ ከይሁዳ ነገድ እንደሚወለድና እግዚአብሔርም ሕዝቡን እንደሚገዛ የገባው ቃል በመጨረሻ በእርሱ በኩል እንደሚፈጸም የተሰጠ ተስፋ ነው። ነገር ግን የሚገዛው የራሱን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን፥ የዓለምን ሕዝቦች ሁሉ በአንድነት ነው። 

ጥያቄ፡- ሩት 4፡12፥ 18-22 አንብቡ። ለይሁዳ የተሰጠው ተስፋ በመጀመሪያ እንዴት ተፈጸመ? 

ጥያቄ፡- ማቴዎስ 1፡3-6፥ 16፤ 21፡9 ለይሁዳ የተነገረው ትንቢት በመጨረሻ ው እንዴት ተሟልቶ ተፈጸመ? 

የትንቢቱ ቃል በንጉሥ ዳዊት አማካይነት መፈጸም ጀመረ። ዳዊት ንግሥናን በማግኘት ረገድ የመጀ መሪያ ከይሁዳ ዘር የመጣ ሰው ነበር። ጻዊት ለእግዚአብሔር ታማኝ ስለነበረ፥ እግዚአብሔር፥ ሥርወ መንግሥቱን ከልጅ ወደ ልጅ እንደሚያስተላልፍለት ተስፋ ሰጠው (2ኛ ሳሙኤል )። በሕጋዊ መንገድ የነገሡ የእስራኤልና የይሁዳ ነገሥታት ሁሉ፥ ከዳዊት ዘር መሥመራቸውን ጠብቀው የመጡ ናቸው። ነገር ግን፥ ዳዊትም ሆነ ኋላም ከቤተሰቡ የተገኙት ነገሥታት፥ አንዳቸውም በመጨረሻ በእስራኤል ላይ ፍጹምና ዘላለማዊ ሥልጣን ተቀዳጅቶ የሚገዛ ንጉሥ ይመጣል የሚለውን ተስፋ አላሟሉም። ይህ ተስፋ የተፈጸመው ጌታ ኢየሱስ የዳዊት ልጅ ሆኖ ሕዝቡን በሙሉ ሥልጣን ለመግዛት በመጣ ጊዜ ነው። ነገር ግን ይህ የኢየሱስ ባለሙሉ ሥልጣን ገዥነት፥ ከእስራኤል ሕዝብ አልፎ ሌሎችንም ሕዝቦች ያጠቃልላል። ይህ የገዥነት ሥልጣን በመላው የዓለም ሕዝብም ላይ ተንሠራፍቷል። ዘፍጥረት 49፡10 እግዚአብሔር በምድር ላይ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ይገዛ ዘንድ መሲሕ ማለትም የተቀባውን እንደሚልክ ያመለከተ የመጀመሪያው ጥቅስ ነው። 

ጥያቄ፡– ዘኁልቁ 24፡17-19 አንብቡ። ሀ) በለዓም ከያዕቆብና ከእስራኤል ማን ይወጣል አለ? ለ) ይህስ ሰው ምን ያደርጋል? 

(ዘኁልቁ ምዕራፍ 22-24 ድረስ ያለው ክፍል በለዓም ስለ እስራኤልና ወደ ፊትም በእስራኤል ዘንድ ስለሚሆነው ትንቢት የተነገረውን ዘገባ ይዟል። በለዓም በሕይወቱ ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ በሐሳዊ ነቢይነት የሚታወቅ ነበር (ዘኁልቁ 31፡8፤ ኢያሱ 3፡22፤ 2ኛ ጴጥሮስ 2፡5፥ ራእይ 2፡14 እንዲሁም 5ኛውን ትምህርት ይመልከቱ)። ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን ሰው በእስትንፋሰ እግዚአብሔር የተሞላ እውነተኛ የእግዚአብሔርን ትንቢታዊ ቃል እንዲናገር ተጠቀመበት። በዘኁልቁ 24፡15-19 ላይ የተጻፈው ደግሞ፥ በለዓም ስለ እስራኤል በረከት የተናገረው አራተኛው ትንቢት ነው። በዚህ ትንቢቱም ላይ ከአይሁድ ሕዝብ መካከል የሚነሣው ገዥ፥ ሕዝቡን ከጠላታቸው እጅ ነፃ እንደሚያወጣቸው ይናገራል። በዘፍጥረት 49 ውስጥ እንዳለው ሁሉ፥ ይህ ትንቢትም በንጉሥ ዳዊት ንግሥና ጊዜ የተፈጸመ ይመስላል። ምክንያቱም ንጉሥ ዳዊት ከሞዓባውያንና ከኤዶማውያን ጋር ተዋግቶ አሸንፎ ነበር። ነገር ግን ጊዜያዊ እፎይታ ቢያስገኝላቸውም፥ እስከ ወዲያኛው ሰላምና ዋስትና የሚያስገኝላቸው ነጻነት የሚሰጥ ድል አላቀዳጃቸውም ነበር። ከዚህ የተነሣ አይሁዳውያን በመጽሐፍ የተነገረለትን ትንቢት በመጨረሻ የሚፈጽም መሢሕ (ንጉሥ) ይጠባበቁ ነበር። በለዓምም ይህ ትንቢት «በኋለኛው ዘመን» ይፈጸማል አለ (ዘኁልቁ 24፡14)። ይህ «በኋለኛው ዘመን» የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ትንቢቶች ሁሉ ተጠቃልለው የሚፈጸሙበትን ወቅት ነው። ይህ ክፍለ ምንባብ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀባው የእስራኤል ንጉሥ እስራኤልን ከጠላቶቻቸው እጅ ሊያድናቸው እንደሚመለስ ተስፋ ሆኖ ይቆያል። 

ጥያቄ፡- 2ኛ ሳሙኤል 7፡10-16 አንብቡ። ሀ) እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል ምን ተስፋ ሰጠ? ለ) በቁጥር 1 ላይ እግዚአብሔር ለዳዊት ምን እንደሚያደርግለት ተስፋ ገባ? ሐይህ ምን ማለት ይመስላችኋል? መ) በቁጥር 12 ላይ እዚእብሔር ለዳዊት ምን እንደሚያደርግለት ተስፋ ሰጠው? ሠ) በቁጥር 16 ላይስ እግዚአብሔር ለዳዊት ምን እንደሚያደርግለት ተስፋ ሰጠው? 

በ2ኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 1 ውስጥ እንደተጻፈው፥ ዳዊት ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለመሥራት ያለውን ምኞት ይናገራል። እግዚአብሔር በነቢዩ ናታን አማካይነት፥ ቤተ መቅደስ የሚሠራለት እርሱ እንደማይሆን ነገረው። ነገር ግን እግዚአብሔር ዳዊት እርሱን ለማክበር ስለ ተመኘ እግዚአብሔርም ተስፋ በመስጠት ምኞቱን አከበረለት። ስለዚህ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ከጠላቶቻቸው ጥቃት በሰላምና በደህንነት ተጠብቆ መኖርን እንደሚሰጣቸው ለጻዊት ነገረው። ከዚያም ለጳዊት የ•ል ተስፋ ( ሰጠው። ጻዊት ለእግዚአብሔር ቤትን ሊሠራ ፈልጎአል። ነገር ቀን እግዚአብሔር ራሱ ለዳዊት ቤት እንደሚሠራለት ተስፋ ይሰጠዋል። እግዚአብሔር በዚህ ተስፋው «ት” ሊላ፥ የዳዊትን በት የዘር ሐረ፥ የወደፊቱ የእስራኤል ነገሥታት መነሻ መሥመር አድርጎ እንደሚያጸናለት ሊናገር ነው፡ ቀጥሎም እግዚአብሔር ዙፋኑን የሚወርስና የእስራኤል ንጉሥ የሚሆን ከዚያም ለእርሱ ቤተ መቅደስ የሚሠራለትን ልጅ እንደሚሰጠው ለዳዊት ተስፋውን ግልጽ ያደርግለታል። ይህ ተለፋም በንጉሥ ሰሎሞን ላይ ይፈጸማል። ምንም እንኳን ኋላ ላይ የዳዊት ልጅ ለእግዚአብሔር ባይታዘዝም፥ እግዚአብሔር በዚህ ዐመፁ ምክንያት ለዳዊት የሰጠውን ተስፋ እንደማያጥፍና የንግሥናውንም መሥመር ከዘር ሐረጉ እንደማይርቅ ቃሉን አጽንቶለታል። ይልቁንም እዚአብሐር በቁጥር 16 ላይ «የዙፋንህ ወራሽ የሚሆን አታጣም” በማለት፥ የዳዊት ቤተሰብ ለዘላለም እንደሚዛ ይናገራል፡፡ 

ዘፍጥረት 49፥ ዘኁልቁ 24 እና 2ኛ ሳሙኤል 7 እግዚአብሔር ከይሁዳ ዘር ከዳዊት ቤተሰብ ሕዝቡን በጥበብ የሚገዛ፥ ከጠላቶቻቸው የሚታደጋቸው፥ እንደዚሁም መላውን የዓለም ሕዝብ የሚገዛ ንጉሥ እንደሚያስነሣላቸው ለእስራኤል ሕዝብ የተገቡ ተስፋዎች የሚገኙባቸው ኮፍሎች ናቸው። በመሆኑም በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ እንደተመለከተው ሁሉ፥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የዚህ ሁሉ ተስፋ ፍጻሜ ነው። 

ጥያቄ፡- የሚመጣው የኢየሱስ አገዛዝ ተስፋ እንዴት ያበረታታችኋል? 

ኢየሱስ ሕዝቡን ለማዳን ሰላምንና ፍትሕን ለዓለም ለመስጠት የሚመጣ ንጉሥ መሆኑ የብሉይ ኪዳን ዘመን አይሁዳውያን ብቻ መበረታቻ አልነበረም። ዛሬም ቢሆን ይህ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ መጽናኛ ነው። ዛሬ ምንም ያህል ፍትሕ ቢጎድልብንና ሥቃይ ቢደርስብን፥ እንድ ቀን ኢየሱስ ከዚህ ሁሉ ሥቃይ አላቅቆ ሁሉንም ነገር እንደሚያስተካክልልን እርግጠኞች ነን። ዛሬ የፈለገውን ዓይነት ጦርነትና አለመግባባት ብናይና ብንሰማም አንድ ቀን ኢየሱስ መንግሥቱን ዘርተ ፍጹም ሰላሙን በዓለም ላይ እንደሚያሰፍን እርግጠኞች ነን። 

ዛሬ ባጠናናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ፥ በብሉይ ኪዳን ትንቢት የተነገረለት ኢየሱስ ለይጣንን የሚያሸንፍ አዳኝ ሆኖ እንደሚጮጣና የሰውን ልጅ ሁሉ ከኃጢአት ነፃ እንደሚያወጣ፥ እንደዚሁም እንደ መድኅን ለመላው ዓለም በረከት እንደሚሆንና በንጉሥነቱ ደግሞ እስራኤልንና መላውን ዓለም እንደሚገባ ተምረናል። ዛሪም ኢየስ የእነዚህ ትንቢቶች ፍጻሜ መሆኑን እንደ ቀጠለ ነው። ከኃጢአት የሚያድነንና ወደ ኃጢአት ከሚስብ ፈተናም ራሳችንን እንድንጠብቅ ኃይል የሚሰጠን እርሱ ነው፡ እርሱ የሰጠውን የደኅንነት ትሩፋት በሦድር ላይ ያሉ ግለሰቦችና ሕዝቦች ሁሉ ሊያገኙ ይችላሉ። ስለዚህ እርሱ የዓለም ሁሉ በረከት ነው። እርሱ የፍጥረታት ሁሉ ንጉሥ እንደ መሆኑ ሁሉ፥ የሕዝቡ ሕይወት ንጉሥ ነው። እርሱ ንጉሥ በመሆኑ ምክንያት፥ የእኛ ፍጹም ታዛዥነት ይገባዋል። በመጨረሻም፥ እርሱ እግዚአብሔር የተገለጠበት ነቢይ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን ለማወቅ ኢየሱስን ማወቅ አለብን።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading