የሕይወት እንጀራ

አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሳይሰሙ ሊድኑ ይችላሉ? 

This entry is part 95 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

እንግዲህ ዛሬ ስለ ደኅንነት ከሚነሡ ከባድ ከሆኑ ጥያቄዎች አንዱን ለመመለስ እንሞክራለን። ስለ ክርስቶስ ስፍጹም ሰምተው የማያውቁ አንዳንድ ሰዎች በእግዚአብሔር በማመናቸው ይድናሉ?  ከአንድ መቶ ዓመት በፊት አካባቢ፥ በደቡብ ኢትዮጵያ ኢሳ የተባለ ነቢይ ተነሥቶ ነበር። ይህ ነቢይ በሕይወቱ ዘመን በአብዛኛው በኢትዮጵያ ደቡባዊው ክፍል እየተዘዋወረ፥ ሰዎች ለርኩስ መናፍስት መስገዳቸውን ትተው አንዱን በሰማይ የሚኖር እውነተኛ አምላክ እንዲያመልኩ ያስተምራቸውና ያሳስባቸው […]

ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሳይሰሙ ሊድኑ ይችላሉ?  Read More »

ለመሆኑ በመጨረሻው ሰዎች ሁሉ ይድናሉ ወይ? 

This entry is part 94 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ሰዎች በክርስቶስ ሥራ ብቻ እንደሚድኑ ተመልክተናል (ትምህርት 13 እና 14)። እንደዚሁም እግዚአብሔር ወደ ራሱ የጠራቸው የሚያምኑና ንስሐ የሚገቡ፥ ኋላም ወደ እግዚአብሔር የሚመለሱ፥ በመጨረሻ የደኅንነትን በረከቶች እንደሚያገኙ ተገንዝበናል (ትምህርት 5 እና 16)። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተረጋገጠው፥ በክርስቶስ ውስጥ እምነታቸው የተረጋገጠላቸው ብቻ ይድናሉ። በተጨማሪም፥ እግዚአብሔር ክርስቶስን ንቀው ሳይቀበሉት የሚቀሩትን ለዘላለም እንደሚቀጣቸው የሚያስተምሩን ብዙ ጥቅሶች አሉ።  ጥያቄ-

ለመሆኑ በመጨረሻው ሰዎች ሁሉ ይድናሉ ወይ?  Read More »

የሚሞቱ ሕፃናት ይድናሉ? 

This entry is part 93 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ሕፃናት በሚሞቱበት ጊዜ የሚድኑ ወይም የማይድኑ ስለመሆናቸው ብዙ ሰዎች ጥያቄዎችን ይሰነዝራሉ። ይህ ጥያቄ ሕፃናት ለሚሞቱባቸው ክርስቲያን ለሆኑ ወላጆች በተለይ ጠቃሚ ነው። ሕፃናት የሚሞቱባቸው ወላጆች በጣም ያዝናሉ። ከዚህም በላይ የሚያስጨንቃቸው ጥያቄ፡- «ልጄን በሰማይ አገኘዋለሁን?» የሚለው ነው።  የሚሞቱ ሕፃናት በቀጥታ ወደ ሰማይ ይሂዱ ወይም ይቅሩ መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ መልስ አይሰጥም። ሆኖም፣ ለዚህ ጥያቄ መልስ እንድናገኝ የሚረዱን ጥቂት

የሚሞቱ ሕፃናት ይድናሉ?  Read More »

ቅዱስ ቁርባንን መቀበል፥ ደኅንነት ያስገኛል? 

This entry is part 92 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ጥያቄ፡- ዮሐ 6፡53-54 እንብብ። ሀ) ጌታ ኢየሱስ፥ አንድ ሰው ሕይወትን ማግኘት ከፈለገ ምን ያድርግ ይላል? ለ) ጌታ ኢየሱስ አንድ ሰው ሥጋውን ቢበላና ደሙን ቢጠጣ ምንን ያገኛል አለ?  ጥያቄ ዮሐ. 6፡35 አንብብ። ጌታ ኢየሱስ አንድ ሰው እንዳይራብ ወይም እንዳይጠማ ምን ያድር አለ?  ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቀብለው ለመዳን ሲሉ ቅዱስ ቁርባንን መቀበል ይፈልጋሉ። ሌሎች ደግሞ ካልቀረቡ

ቅዱስ ቁርባንን መቀበል፥ ደኅንነት ያስገኛል?  Read More »

ደኅንነትን የመቀበል ጥያቄ፣ እምነትና ጥምቀት  

This entry is part 91 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በትምህርት 16 ውስጥ፥ ክርስቶስ በመስቀል ላይና በትንሣኤው የሰጠንን ደኅንነት እንዴት ሰዎች በየግላቸው ሊያገኙ እንደሚችሉ ተምረን ነበር። በዚህም ለደኅንነት መሠረታዊ የሆነ አንድ ዋና ነገር፥ በሦስት የተለያዩ መንገዶች መገለጣቸውን ተመልክተናል። እነዚህም ሦስቱ ንስሐ፥ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ ናቸው። ሰዎች ኃጢአታቸው ከእግዚአብሔር ለይቶአቸው እንደ ነበረ መገንዘብና ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ በራሳቸው ሥራና በሌላም ነገር መታመን እንደሌለባቸው አውቀው፥ በአኳያው በጌታ

ደኅንነትን የመቀበል ጥያቄ፣ እምነትና ጥምቀት   Read More »

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 3 

This entry is part 90 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በተከታተልነው ትምህርት ላይ፥ መጽሐፍ ቅዱስ በእውነት ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች ለዘላለም ዋስትናቸው የተጠበቀ መሆኑን እንደሚያስተምር ተገንዝበናል። እግዚአብሔር እነርሱን የማዳኑን ተግባር እነርሱ ከእርሱ ጋር የታረቁ መሆናቸውን በማሳወቅ ጀምሮአል፤ ይህንንም የጀመረውን የማዳን ተግባር በታማኝነት ከግብ ያደርሳል። በዚሁ መሠረት የመጨረሻው የደኅንነታቸው ዋስትና እንዲሆንም የራሱን መንፈስ ቅዱስ ሰጥቶአቸዋል፤ ይህንንም ሲያደርግ ማንም ከፍቅሩ ሊለያቸው እንደማይችል ተስፋውን አክሎ

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 3  Read More »

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 2 

This entry is part 89 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በትናቱ ዕለት ትምህርታችን ስለ አማኞች ዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጥ ወይም ጥበቃ ማጥናት ጀምረናል። በዚህ ትምህርት ላይም፥ አማኞች በደኅንነታቸው ረገድ ሁኔታው ዋስትና እንዳለውና የተጠበቀላቸው መሆኑን ተመልክተናል። ይህ ሊሆን የቻለበትም ምክንያት፥ ከእግዚአብሔር ጋር በመታረቃቸውና ሰላምንም በመመሥረታቸው ምክንያትና እንደዚሁም እግዚአብሔር ሁልጊዜ የጀመረውን ሥራ ስለሚፈጽም ነው። ከዚህም ጋር መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ በመሆናቸውና ኢየሱስ ራሱ ስለሚጠብቃቸው፥ ከዚህም የተነሣ አዲስ ሰዎች ስለሆኑ

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 2  Read More »

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫ እና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 1 

This entry is part 88 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

በክርስቲያኖች መካከል የሚነግ አንደኛው አስቸጋሪና አከራካሪ የሆነ ርእሰ ጉዳይ፥ እውነተኛና ዳግም የተወለዱ አማኞች ደኅንነታቸውን ይዘውት ይቆያሉ ወይስ ያገኙትን የሚያጡበት ሁኔታ ይኖራል? የሚለው ነው። / ማንኛውም ክርስቲያን በአንድ ወቅት ክርስቶስን አምነው የተቀበሉና ኋላ ግን ይህን እምነታቸውን የተዉ ሰዎችን የሚያውቅ ይመስለኛል። አብዛኛዎቹ እማኞች አንድ ጊዜ መልካም የክርስትና አካሄድ የነበራቸውና ኋላ ላይ በኃጢአት ውስጥ ከመውደቃቸው የተነሣ ያንን የመልካም

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫ እና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 1  Read More »

የደኅንነት በረከቶች – እንከብራለን ሲባል ምን ማለት ነው?  

This entry is part 87 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው አምነው በሚቀበሉበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር አስደናቂና የተትረፈረፉ የደኅነት በረከቶችን በላያቸው ላይ ያፈስሳል። በዚህም አዲስ ሕይወትን ይሰጣቸዋል፥ ከክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራቸው በማድረግ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር ይላቸዋል፣ ከዚያም ከእርሱ ጋር መታረቃቸውን በማሳወቅ፥ የቤተሰቡ አካል ያደርጋቸውና በፊቱ ቅዱሳን ሆነው እንዲገኙ በሕይወታቸው ውስጥ ይሠራል። ሆኖም፣ እያንዳንዱን አማኝ ወደፊት የሚጠብቀው በረከት አለ፣ ይህም የክብር በረከት ነው።

የደኅንነት በረከቶች – እንከብራለን ሲባል ምን ማለት ነው?   Read More »

ቅድስና 

This entry is part 86 of 95 in the series አስተምህሮ ክርስቶስ እና ደኅንነት

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በደኅንነታችን ውስጥ ስለምናገኛቸው በረከተች ስናጠና ነበርን። በዳንንበት ጊዜ ስላገኘናቸው ብዙ የደኅንነት በረከቶች አጥንተናል። ዳግም በዳንንበት ወቅት፣ እግዚአብሔር በዳግም ልደት አዲስ ሕይወትን ሰጥቶናል። በደኅንነታችን ወቅት በውስጣችን ሊኖር ካመጣው ከክርስቶስ ጋር ኅብረት በምናደርግበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር እኛን ከክርስቶስ ጋር አንድ አድርጎ ያየናል። እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር በማለት ደኅንነትን ባገኘንበት ወቅት፣ ወዲያው መጽደቃችንን አስታውቆልናል። እንደ ልጆቹ

ቅድስና  Read More »