ሕፃናት በሚሞቱበት ጊዜ የሚድኑ ወይም የማይድኑ ስለመሆናቸው ብዙ ሰዎች ጥያቄዎችን ይሰነዝራሉ። ይህ ጥያቄ ሕፃናት ለሚሞቱባቸው ክርስቲያን ለሆኑ ወላጆች በተለይ ጠቃሚ ነው። ሕፃናት የሚሞቱባቸው ወላጆች በጣም ያዝናሉ። ከዚህም በላይ የሚያስጨንቃቸው ጥያቄ፡- «ልጄን በሰማይ አገኘዋለሁን?» የሚለው ነው።
የሚሞቱ ሕፃናት በቀጥታ ወደ ሰማይ ይሂዱ ወይም ይቅሩ መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ መልስ አይሰጥም። ሆኖም፣ ለዚህ ጥያቄ መልስ እንድናገኝ የሚረዱን ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አሉ።
ጥያቄ፡- ሀ) 2ኛ ሳሙ. 12፡22-23 አንብብ። ሀ) ዳዊት ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ምን ማጽናኛ አገኘ? ለ) መዝሙር 23፡6 አንብብ። ጻዊት ለዘላለም የት እንደሚኖር ይገነዘብ ነበር?
ጥያቄ፡- ማር. 10፡13-16 እንብብ። ሀ) ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግሥት የማን ነው አለ? ለ) ሕፃናትን ወደ ኢየሱስ ባመጡ ጊዜ ምን አደረገላቸው?
ጥያቄ፡- ማቴ. 18፡1-4 እንብብ። ሀ) በእግዚአብሔር መንግሥት ታላቁ ማን ነው? ለ) ማቴዎስ 18፡10-14 አንብብ። እነዚህ ትንንሽ ልጆች በሰማይ ምን ያገኛሉ? (ቁጥር 1) ሐህ እግዚአብሔር ስለ ትንንሽ ልጆች ያለው ስሜት እንዴት ነው (ቁጥር 14)?
በ2ኛ ሳሙ. ምዕራፍ 12 ውስጥ ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር በማመንዘርና ኦርዮንን በማስገደል፥ ስለ ሠራው የከፋ ኃጢአት ነቢዩ ናታን ወደ እርሱ ዘንድ ቀርቦ ነገረው። ጳዊትም ወዲያው ጥፋቱን በኑዛዜ አስታወቀ (ቁጥር 13)። ሆኖም ናታን ዳዊት ለፈጸመው ኃጢአት ተግሣጽ ይሆን ዘንድ ከቤርሳቤህ የተወለደው ሕፃን እንደሚሞት አረዳው። ዳዊትም እግዚአብሔር ምሕረት አድርጎለት ልጁን ከሞት እንዲያተርፍለት በማሰብ በጾምና በጸሎት ራሱን አስ። ግን በሰባተኛው ቀን ሕፃኑ ሞተ። ዳዊትም ሕፃኑ መሞቱን እንደ ሰማ፥ ኦሙን አቆመና ፊቱን ታጠበ፥ ልብሱንም ቀየረ፥ ከዚያም ለእግዚአብሔር ሰዶ ምግቡን በላ። ዳዊት ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ይህን ሁሉ ነገር በማድረጉ አገልጋዮቹ ሁሉ ተገረሙ። በምን ምክንያት ነው ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ኀዘኑን ያልቀጠለው? ዳዊት በጊዜው የሰጠው መልስ፥ እግዚአብሔር ልጁን ከሞት እንዲያድንለት ተስፋ በማድረግ ኦሞና ጸልዮ እንደ ነበረ ነው። አሁን ግን ልጁ ሞቶአል። ስለዚህ ሊያደርገው የሚችለው ነገር አይኖርም። ጾምና ጸሎቱን ቀጥሎ ቢሆንም፥ ሕፃኑን ከሞት ወደ ሕይወት መልሶ ሊያመጣው አይችልም ነበር። ነገር ግን ዳዊት በመጨረሻ፥ በሚሞትበት ጊዜ ከሕፃኑ ጋር ሊሆን ወደ እርሱ ዘንድ ይሄዳል። ዳዊት ለዘላለም በእግዚአብሔር ቤት እንደሚኖር እርግጠኛ ነበር። በ2ኛ ሳሙኤል 12 ውስጥ ዳዊት ሲናገር፥ አንድ ቀን ሄዶ በሚኖርበት ስፍራ ሕፃኑ የዘላለም ሕይወትን አግኝቶ በእግዚአብሔር ቤት መኖር መጀመሩን ዳዊት ያመነ መሆኑ ይገመታል። ጳዊት በንግሩ ሕፃኑ እንደ ሞተ ሁሉ እርሱም የሚሞት መሆኑን ብቻ ሊናገር አይችልም ነበር? የተናገረው ይህን አይመስልም። ለእግዚአብሔር ሰቶአል፥ እንደዚሁም ራሱን በማጽናናት ላይ ነበር (ቁጥር 22-23)። ጻዊት *ከሕኑ ሞት በኋላ ለእግዚአብሔር መስገድና ከዚያም መጽናናቱ እርሱም አንድ ቀን ሟች መሆኑን ብቻ አሳሰበው ብሎ መገመት ያዳግታል። በቁጥር 3 እንደምናነበው፥ ዳዊት አንድ ቀን ከሕፃኑ ጋር እንደሚሆን ተስፋ ያደረገ ይመስላል። ስለዚህ በ2ኛ ሳሙ. 12፡22-23 የተጻፈው ቃል የሚሞቱ ሕፃናት በእግዚአብሔር ዘንድ ሆነው የዘላለምን ሕይወት እንደሚኖሩ ያመለክታል።
ኢየሱስ በወንጌል ውስጥ ብዙ ጊዜ ስለ ትንንሽ ልጆች ይናገራል። በማርቆስ 10፡13-16 ኢየሱስ እንዲዳስሳቸው ሰዎች ልጆችን ወደ ኢየሱስ ዘንድ እንዳመጡ ተጽፎአል። ደቀ መዛሙርቱ ግን እነዚህ ትንንሽ ልጆች ኢያሱስን ስቶሩታል ብለው ጉ። ን ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በዚህ ጉዳይ ገሠጻቸው። ለኢየሱስ ልጆች ናቸው። ኢየሱስ ሕፃናትን ተቀብሎ ጠቃሚ የሆነ መንፈሳዊ ትምህርት ያስተምራቸው ነበር። አብረውት ለነበሩት ሰዎች የእግዚአብሔር መንግሥት እነዚህን ሕፃናት ለመሰሉት ነው ሲል ነገራቸው። ኢየሱስ ዘንድ ይመጡ የነበሩ ልጆች ትንንሾች እንደ ነበሩ ግልጽ ነው። ምክንያቱም ቁጥር 16 እንደሚለው አንሥቶም በክንዱ አቀፋቸው ይላል። ምንም እንኳን ልጆቹ ገና የተወለዱ ሕፃናት ባይሆኑም፣ ኢየሱስ በቀላሉ እንሥቶ ሊያቅፋቸው የሚችላቸው ዓይነት ነበሩ። እነዚህ ልጆች ኢየሱስ አዳኛቸው ለመሆኑ እምነታቸውን በሚገልጹበት ዕድሜ ላይ አልነበሩም። ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደዚህ ላሉት ነው ሲል ተናገረ። እዚህ ላይ ይህን ቃል የመናገሩ ሁኔታ፥ መልካም ሥራቸውን ይዘው ሳይሆን፥ ደካሞች፥ አነስተኞችና በማንም ዘንድ ጎልተው የማይታዩ መሆናቸውን ተገንዝበው ወደ እርሱ ዘንድ የሚመጡ እነርሱ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንደሚገቡ ሲያሳስብ ነው። ኢየሱስ በዚህ ንግግሩ ምናልባት እነዚህ ሁለት ወይም እራት ዓመት የሚሆናቸው ልጆች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባሉ ብሎ በግልጽ አልተናገረም። ግን የንግግሩ አንድምታ ወይም አቅጣጫው ይህንኑ የሚጠቁም ነው። በተለይ በማርቆስ 10፡13-16 ያለው ቃል፥ የሚሞቱ ትንንሽ ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር ሆነው የዘላለምን ሕይወት እንደሚኖሩ በጥብቅ የሚያመለክት ክፍል ነው።
በማቴዎስ 18፡1-14 ያለውም ተመሳሳይ ቃል ነው። በዚህ ክፍል የጌታ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስን በእግዚአብሔር መንግሥት ታላቁ ማን ነው? ሲሉ ጠየቁት። ኢየሱስም ትንሽ ልጅ በመጥራትና በመካከላቸው በማቆም መልሱን ሰጣቸው። ተጠርቶ የቆመው ልጅ መቆም የሚችል ነበር፥ ግን ጥቅሱ ትንሽ ልጅ ያደርገዋል። እንደዚሁም ኢየሱስ ሲናገር፥ በመንግሥተ ሰማይ ከሁሉም ታላቅ የሚሆኑት ወደ እርሱ ዘንድ የዚህን ልጅ ትሕትና ተላብሰው የሚመጡ መሆናቸውን አስገንዝቧል። በኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚታየው በኢየሱስም ጊዜ የልጆች ድርሻ በጸጥታ በዕድሜ የገፉትን ማገልገል ነበር። ስለዚህ ልጆች ትሑት፥ ራሳቸውን ያስገዙና ታዛዦች መሆን ይጠበቅባቸው ነበር። ስለ ራሳቸው ትልቅነት ስለማያስቡ፥ ሁልጊዜ ጥገኝነትና ጎልቶ ያለመታየት ሁኔታ ይታይባቸዋል። ስለዚህ ኢየሱስ ወደ እርሱ ለሚመጡት ሰዎች ሁሉ እንደዚህ ያሉ ልጆችን በምሳሌነት በማቅረብ እነርሱ ወደ እርሱ ሊመጡ የሚችሉበትን ሁኔታ ይገልጥላቸው ነበር። ይህም በትሕትናና በእርሱ ላይ በመመርኮዝ፥ ኢየሱላ የሚሰጣቸውን ለመቀበል ብቁ አለመሆናቸውን በመገንዘብ ወደ እርሱ እንዴት እንደሚቀርቡ ምሳሌ ሆኖ የሚገልጽላቸው ነበር።
ነገር ገን ኢየሱስ ነገሩን ከፍ አድርጎ በማጉላት፥ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደዚህ ሕፃን ናት አለ። በቁጥር 10 ውስጥ ክሎ ሲናገር፥ ለእነዚህ ታናናሾቹ «በሰማይ መላእክት አሉዋቸው አለው። ኢየሱስ ይህን ሲናገር አባባሉ ትንንሽ ልጆች በሰማይ አብረዋቸው ሆነው የሚጠብቋቸው መላእክት አሉ ማለቱ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር ሰዎች የሚጠብቁዋቸው መላእክት እንዳሉዋቸው የሚጠቁሙ ክፍሎች አሉ (መዝ 34፡7፤ 91፡11)። እንግዲህ እንዲህ ከሆነ፣ የኢየሱስ አነጋገር ትንንሽ ልጆች ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር የሚቆጠሩ መሆናቸውን ያመለክታል። እንዲያውም በቁጥር 14 ውስጥ አባቴ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዳቸውም እንዲጠፉ አይፈልግም በማለት ግልጽ ያደርገዋል። ይህ ጥቅስ እግዚአብሔር ለልጆቹ በጣም ትልቅ ግምት እንደሚሰጥ ይገልጻል። ነገር ቀን ከዚህ የበለጠ የሚናገር ይመስላል፥ ይህም ለማቴዎስ 18፡14 ትንንሽ ልጆች አይጠፉም የሚለው ነው።
በዚህ ክፍል እንደተገለጸው፥ እግዚአብሔር የሚሞቱትን ትንንሽ ልጆች ወደ እርሱ ዘንድ አምጥቶ የዘላለም ሕይወትን የሚሰጣቸው ስለመሆኑ ግንዛቤ ይፈነጥቃል። ሆኖም እነዚህ ሕፃናት ከሞቱ በኋላ ወደ ሰማይ የሚገቡት በልዩ ተሰጥኦዋቸው ወይም ከኃጢአት ነፃ ስለሆኑ አይደለም። በ1ኛውና በ12ኛው ትምህርት ውስጥ እንደ ተከታተልነው፥ ሰዎች ሁሉ በኃጢአት መወለዳቸው የታወቀ ነው። ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ ሕፃናት ደኅንነትን ስለሚያገኙበት መንገድ ባይገልጽም፥ ክርስቶስ በሞቱና በትንሣኤው የሰጠውን ደኅንነት፥ እምነትን በተግባር ለመግለጽ ላልደረሱ ሕፃናት እግዚአብሔር ሰጥቶአቸዋል።
እንዲሁም እግዚአብሔር ሕፃናት ስለተጠመቁ እንደማያድናቸው፥ ደግሞም ስላልተጠመቁ እንደማይኮንናቸው እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን። እንደተመለከትነው ሁሉ፥ ጥምቀት ደኅንነትን አያመጣም። ነገር ግን ጥምቀት ለሰዎች የማዳን እምነታቸው ምልክትና ማኅተም ነው። ሕፃናትን የማጥመቅ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የተነሣበት አንዱ ምክንያት፥ ክርስቲያኖች በሚሞቱበት ጊዜ ወደ ሰማይ የሚሄዱ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ነበር። ነገር ግን ሕፃናትና ትንንሽ ልጆች በጥምቀት ምክንያት እግዚአብሔር ያድናቸዋል የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ አሳብ የለም። የእግዚአብሔር ሕፃናትን የማዳን ነገር፥ እርሱ በክርስቶስ ሞት ትሩፋት ተጠቅሞ እምነታቸውን ለመግለጽ ለማይችሉ ሕፃናትና ትንንሽ ልጆች የሚሰጠው ሉዓላዊ የሆነ ምሥጢራዊ ሥራው ነው።
ጥያቄ፦ ልጆቻቸውን በሞት ላጡ ወላጆች ማጽናኛነት በእነዚህ ጥቅሶች እንዴት ትጠቀማላችሁ?
ወላጆች ልጆቻቸውን በሞት በሚያጡበት ጊዜ፥ ከባድ የሆነ የትምህርተ መለኮት የማጽናኛ ቃል አያስፈልጋቸውም። ይህን በመሰለ ከባድ ወቅት ከእነርሱ ጎን ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስን አብሮ ማንበብና እብሮ መጸለይ ያሻል። መጽሐፍ ቅዱስን በምታነቡበት ጊዜ፥ አሁን ያጠናናቸውን ክፍሎች ብታነቡ የተሻለ ነው። እነዚህ ክፍለ ምንባቦች እግዚአብሔር ለልጆቻቸው ስላለው ፍቅር በመግለጽ ያጽናናቸዋል።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ