በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች (FAQs)
ኃጢአት ከየት መጣ? ለምን ኃጢአትን እናደርጋለን? ደግሞስ ለምን በኃጢአት በተሞላ ዓለም ውስጥ እንኖራለን? ኃጢአትን እንዴት እንደምንከላከል ወይም ለኃጢአት ችግር መፍትሔ የምናገኝበትን መንገድ ከመረዳታችን በፊት ኃጢአት ከየት እንደ መጣ ለማወቅ በመጀመሪያ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሶችን ማግኘታችን ወሳኝ ነው።
ጥያቄ፡- ሀ) እናንተ የምታውቁዋቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች የኃጢአት ዋና ምንጭ ምንድን ነው ይላሉ? ለ) እነዚህ ሰዎች ለኃጢአት ችግር እጅግ ተመራጩ መፍትሔ ምንድን ነው ይላሉ?
አንዳንድ ሰዎች ኃጢአት ከድንቁርና ወይም ከእውቀት ማነስ ይመጣል ይላሉ። ኃጢአት ከዕውቀት ማነስ የሚመጣ ከሆነ እኛን ከኃጢአት የሚያድነን ትልቁ ነገር ትምህርት ነው ማለት ነው። ሌሎች ሰዎች ደግሞ ሰዎች በድህነትና በጭቆና ቀንበር ሥር ከመኖራቸው የተነሣ ኃጢአት በዚህ ምክንያት ይመጣል ይላሉ። እንግዲህ ኃጢአት ከድህነትና ከጭቆና የሚመጣ ሆኖ ከተገኘ፥ እኛን ከኃጢአት የሚያድነን ትልቁ ቁም ነገር ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጥ ነው ማለት ነው። አንዳንዶቹ ደግሞ ሰዎች ከሰዎች ተለይተው ባዕዳን ሲሆኑና ከአካባቢያቸው ኅብረተሰብ ሲገለሉ፥ ያኔ ኃጢአት ይከሰታል ባይ ናቸው። በመሠረቱ ሰዎች ከኅብረተሰብ በመገለላቸው ኃጢአት የሚመጣ ከሆነ በጣም ተገቢ የሚሆነው ተግባር ሰዎች የማኅበረሰባቸው ጠቃሚ አካል እንዲሆኑ ማድረግ ነው። በእነዚህ አስተሳሰቦች ሁሉ ውስጥ ጥቃቅን እውነቶች አሉ። ነገር ግን ማንኛቸውም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኃጢአት ምንጭ ምንነት የሚያስተምረውን ሐቅ አያንጸባርቁም። ስለሆነም፥ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ብቸኛ የኃጢአት እውነተኛ ምንጭ ምን ሊሆን ይችላል።
1. ኃጢአት ሊመጣ የሚችለው ለምኞታችን ከእግዚአብሔር የበለጠ ስፍራ ስንሰጥ ነው።
ጥያቄ፡- ያዕቆብ 1፡3 አንብቡ። ሀ) ሰዎች በሚፈተኑበት ጊዜ ምን አይብሉ? ለ እንደዚህ ጥቅለ አገላለጽ ለእግዚአብሔር የሚሳኑት ሁለት ነገሮች ምንድን ናቸው?
ጥያቄ፡- ያዕቆብ 1፡14-15 አንብቡ። ሀ) የኃጢአት ምክንያት ምንድን ነው? ለ የኃጢአትስ ውጤት ምንድን ነው?
ጥያቄ፡- ዘዳግም 32፡4 አንብቡ። ሀ) የእግዚአብሔር ሥራና መንገድ እንዴላ ተገለጹ? ለ) እግዚአብሔር ራሱ እንዴት ተገለጸ?
ያዕቆብ 1፡13-5 ያለው ክፍል ስለ ፈተናና ብዙ ሰዎች በምን ምክንያ፡ ኃጢአት እንደሚሠሩ ይገልጻል። ከዚህ ክፍል በመጀመሪያ የምንማረግ እግዚአብሔር ማንንም ሰው ኃጢአት እንዲሠራ እንደማይፈትነው ነው ሰዎች በገዛ ምኞታቸው ኃጢአት ሲሠሩ ስሕተታቸውን በእግዚአብሔር ላ ሊያላክኩ አይገባም። እርግጥ ሰዎች በእምነታቸው እንዲያድጉ እግዚአብሔ ሰዎችን የሚፈተንበት ጊዜ ሊኖር ይችላል። ግን እግዚአብሔር በማንም ሰd ላይ ኃጢአትን እንዲሠራ የሚገፋፋ ምኞት አያመጣበትም። እንዲሁና ዘዳግም 32 ላይ የእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ ፍጹም ነው፥ መንገዱም ፍጹ ነው ይላል። እንግዲህ ፍጹም የሆነ አምላክ ኃጢአትን አይሠራም፡ ደግሞ፡ ማንም ሰው ቢሆን በምኞቱ ተፈትኖ ኃጢአት እንዲፈጽም ከቶ አያደርግም ዳሩ ግን አንዳንድ ጊዜ እኛው ራሳችን ስለ ኃጢአታችን እግዚአብሔርን እንድናማርር እንፈተናለን። እንዲህ የሚል አስተሳሰብም ሊቀረጽብን ይችል ይሆናል፥ «እግዚአብሔር እንድፈተን ባያደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሠራሁ ነበር።» አያችሁ ኃጢአት ወይም ኃጢአትን የመሥራት ምኞትና ዝንባሌ የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው ብሎ መናገር ራሱ እግዚአብሔርን መሳደብ ወይም ክብሩን ማዋረድ ነው። በግልጽ መታወቅ ያለበት ነገር እግዚአብሔር ራሱ ኃጢአትን የመፈጸም ምኞት ወይም ዝንባሌ እንደሌለው ሁሉ፥ ማንም ሰው ሲሆን ኃጢአትን የመሥራት ፍላጎት እንዲያድርበት አድርጎም አያውቅም፥ ወደፊትም አያደርግም። ኃጢአት ያለበት ምኞት ወይም ፍላጎት ከእግዚአብሔር ዘንድ አይመጣም። –
እውነቱ ይህ ከሆነ፥ የኃጢአት ፈተናዎች ከየት ይመጣሉ? በቁጥር 14 ውስጥ ካለው ጥቅስ የምንማረው ሁለተኛው ነገር «እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል» የሚለው ቃል ነው። ከጅምሩ አብዛኛዎቹ ምኞቶች ለሰዎች የተሰጡት ከእግዚአብሔር ሲሆን፥ እንደ እርሱ ፈቃድና ፍላጎት ከተፈጸሙ መልካም ናቸው። ሆኖም እነዚህን በእርሱ ፈቃድ የተሰጡንን ምኞቶች በሚገባ በመጠቀም ፈንታ ዓላማቸውን ስተው ወደ ክፉ አቅጣፃ ስበው እንዲወስዱን በመታለል ከፈቀድንላቸው ሕይወታችንን ለጥፋት ይዳርጉታል። በአማርኛ ቋንቋ፡- «አታለለ» የሚለው ቃል በግሪኩ አገላለጽ በዓሣ ወጥመድ ወይም መንጠቆ ጫፍ ላይ የሚደረግ ምግብን ያመለክታል። ዓሣው በወጥመዱ ጫፍ ላይ የተደረገለትን ምግብ ካየ በዚያ ይላብና ለመብላት ይሞክራል። ይህን ጊዜ በመንጠቆው ይያዛል፣ ወይም መረቡ ውስጥ ጥልቅ ይላል። ከዚያም አጥማጁ ከባሕሩ ወይም ከወንዙ ውስጥ ስቦ ይወስደዋል። በተመሳሳይ መንገድ፡ የራሳችንን ምኞቶች በተቻለ መንገድ ሁሉ ለመፈጸም ከአግባብ ያለፈ ስንሯሯጥ በእነዚሁ ምኞቶቻችን ተጠምደን ወደ ኃጢአት እንወሰዳለን። ለመሆኑ ምኞቶቻችን አጥምደውን እንዲወስዱን እንዴት ዕድል እንሰጣቸዋልን? ይህን የምናደርገው ምኞታችን በሕይወታችን ውስጥ ዋናውን ስፍራ ይዞ እንዲንሠራፋ ስንፈቅድለት ነው። በተለይም ምኞታችን ወደ ባሰ ጥፋት የሚያደርሰን ከእግዚአብሔር አምላክ አስበልጠን በሕይወታችን ውስጥ ስፍራ በመስጠት እርሱኑ ለመፈጸም ማንኛውንም አማራጭ መጠቀምን ምርጫችን ስናደርግ ነው። ይኸውም ትክክለኛ ባልሆነ መንገድም እንኳ ቢሆን ይህን ምኞት ለማሳካት እስከምንጠመድ እንወስዳለን ማለት ነው።
ሰዎች ይህን እግዚአብሔር አስቀድሞ ለበጎ ዓላማ የሰጠን ምኞት ለክፉ ተግባር ሊያውሉት ቢመርጡ ቀድሞ መልካም የነበረው ምኞት ይለወጥና ተጣሞ የክፉ መካተቻ ይሆናል።
ለምሳሌ ያህል፥ የምግብ ፍላጎት መልካም ነገር ነው። ለመኖር መብላት አለብን። ነገር ግን ለመብል ያለንን ፍላጎት ለማሟላት ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ብንጠቀምና ከገደብ ውጭ ብንበላ፥ የሆዳምነት ኃጢአት እንፈጽማለን። የእንቅልፍ ፍላጎት ስጎ ነገር ነው። ሁላችንም ብንሆን ለመኖር ዕረፍት ያስፈልገናል። ነገር ግን የእንቅልፍን ዓላማ አጣምመን ሌላ ትርጉም በመስጠት ልንጠቀምበት ብንፈልግ፥ ይህ ምኞት ወደ ስንፍና ኃጢአት ይመራናል። አንድ ሰው ከባለቤቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመፈጸም ያለው ፍላጎት የተፈቀደና ጤናማም ነው። ነገር ግን ከተፈቀደው ውጭ ወጥተን ሕገ-ወጥ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ብንፈጽም፥ ይህ የፍትወተ ሥጋ ምኞት የወሲባዊ ምግባረ ብልሹነትና የዝሙት ኃጢአትን መፈጸም ነው። የራስን ቤተሰብ ለማስተዳደርም ሆነ ድሆችን ለማገዝ ገንዘብ ለማግኘት መመኘት ጥሩ ነው። ግን ብዙ ገንዘብ አግኝቶ ለመበልጸግና የተለያዩ ነገሮችን ለመግዛት ስለ ገንዘብ የሚነሣሣው ምኞት የስስትና ራስን የመውደድ ኃጢአት ነው። እንዲሁም አንድ ሰው የሌላውን ሰው ገንዘብ ወስዶ ለመጠቀም ቢመኝ፥ ይህን የመሰለው ምኞት የሌብነት ኃጢአት ይሆናል። ለእግዚአብሔር ታላላቅ ሥራዎችን የመፈጸም ፍላጎት ድንቅ ነው። ነገር ግን እንዲህ ያሉትን ተደናቂ ሥራዎችን የምንፈጽመው ታዋቂነትን፥ ዝነኛነትን ለማትረፍ ከሆነ፥ የዚህ ፍላጎት ፍጻሜ ትዕቢትና ራስን የመውደድ ከንቱ ምኞት ሆኖ ይቀራል። እንዲሁም ሥራም ሆነ ትምህርትን ለማግኘት መመኘት መልካም ነው። ዳሩ ግን በቃለ መጠይቅ ወይም በምናቀርበው ማመልከቻ በማጭበርበር ሥራ ለማግኘት አልያም ትምህርት ቤት ለመግባት ብንሞክር፥ ይህ የሥራ ወይም የትምህርት ፍላጎታችን የማጭበርበርና የማታለል ኃጢአት ሆኖ ይቆጠርብናል።
የገዛ ምኞታችን መልሶ እንዲቆጣጠረን በምንፈቅድለት ጊዜና በተለይም ይህን ምኞታችንን ከእግዚአብሔር በላይ አድርገን በምንመለከትበት ወቅት ኃጢአትን እንፈጽማለን። ስለሆነም ለምኞታችን ከእግዚአብሔር አስበልጠን ስፍራ ስንሰጠው እርሱኑ መፈጸም በሕይወታችን ውስጥ ዋናውን ስፍራ ይይዛል። ይህን ምኞት ለመተግበር በምናደርገው ሁሉ ሕይወታችን ወጥመድ ውስጥ ይገባል። ከዚህም የተነሣ ምኞታችንን ለመፈጸም ከአግባብ ውጭ የሆኑ መንገዶችን ወደ መጠቀሙ አዝማሚያ እንሳባለን። ከዚያም አንድ ጊዜ ምኞታችን እንዲያጠምደን ካደረግነው ሐዋርያው ያዕቆብ እንዳለው፥ ምኞት ትፀንሳለች ኋላም ያረዝችው ምኞት ኃጢአትን ትወልዳለች።
የኃጢአት ዋጋ ደግሞ ሞት ነው። በሚቀጥለው ትምህርታችን ውስጥ መለስ ብለን የኃጢአት ዋጋ ሞት ስለ መሆኑ እንማራለን።
2. ለእግዚአብሔር ካለን ምኞት ልቀው የሚገኙ ሦስት የኃጢአት ምኞቶች የሚከተሉት ናቸው፡- ተድላ፥ ቁሳቁሶችና ስኬት (ውጤታማነት) ናቸው።
2.1 1ኛ ዮሐንስ 2፡15-16
ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐንስ 2፡5-16 አንብቡ፡ ሐዋርያው ዮሐንስ ሲናገር ከአባት የማይመጡ ነገር ግን ከዓለም የሚመጡ ብሎ የጠቀሳቸው ሦስቱ ነገሮች ምንድን ናቸው?
ሐዋርያው ዮሐንስ በ1ኛ ዮሐንስ 2፡15-16 ባለው መልእክቱ ሦስት የፈተና ምንጮችን ይገልጻል። እነርሱንም፥ «የሥጋ ምኞት፥ የዓይን አምሮትና የኑሮ ትምክህት» (ቁ. 16) ይላቸዋል። እነዚህ ነገሮች እያንዳንዳቸው በመሠረቱ በእግዚአብሔር የተሰጡና በራሱ መልካም የሆነ ነው። ነገር ግን እያንዳንዳቸው እግዚአብሔር በማይፈቅደው መንገድ በተግባር ላይ ሲውሉ ስሕተት ስለሚሆኑ ድርጊቱ ኃጢአትን መሥራት ነው። የሥጋ ምኞቶች ሲባል እኛን ደስ እንዲያሰኙን የተሰጡን ምግብ፥ መጠጥና ግብረ ሥጋን የመሳሰሉት ናቸው።
እነዚህን ምኞቶች የምንፈጽምበት ተገሲና እግዚአብሔርን የሚያስደስት መንገድ አለ። ነገር ግን እነዚህ የሚያስደስቱንን ነገሮች ያለአግባብ በመጠቀም እንዲቆጣጠሩን ወይም እንዲወስዱን ከፈቀድን ከእግዚአብሔር እንዲበልጡብን እናደርጋቸዋለን። እነዚህ ምኞቶች ከእግዚአብሔር በሚበልጡብን ጊዜ በተሳሳተ መንገድ እንጠቀምባቸዋለን ማለት ነው። ያም ኃጢአት ይሆንብናል። በዚህም ሆዳሞች እንሆናለን፥ በፍትወት ምኞት እንቃጠላለን። ከዚያም ከሞራል ውጪ የሆነ ግብረ ሥጋ እንፈጽማለን። የዓይን አምሮት ነገሮችን ለማግኘት የሚኖረን ምኞት ነው። ለእግዚአብሔር ክብርና አገልግሎት የሚጠቅሙ ነገሮችን ብንመኝ ችግር አይደለም። ነገር ግን ነገሮችን ለማግኘት ያለን ምኞት ሁለንተናችንን እንዲወስድ ከፈቀድን ይህ ምኞት ከእግዚአብሔር በላይ ሆኖ በሕይወታችን ውስጥ ስፍራ ይይዛል። እነዚህ ምንቶች ከእግዚአብሔር በልጠው በውስጣችን ሲገኙ እነርሱኑ ለመፈጸም ትክክለኛ ያልሆነ መንገድ መጠቀም ግድ ይሆንብንና ኃጢአት እናደርጋለን። ከዚህም የተነሣ እንዋሻለን፥ እናታልላለን፥ እንሰርቃለን ወይም ነገሮችን ለማግኘት ስንል ሌሎችን ሰዎች እንጎዳቸዋለን። ይህ ብቻ አይደለም የእኛ ስለሆነው ነገር ሁሉ ስስታሞችና ራስ ወዳዶች እንሆናለን።
የቀድሞው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ሦስተኛውን ምኞት «ስለ ገንዘብ መመካት» ይለዋል። ይህ አገላለጽ ግን የግሪኩን ቋንቋ ትርጉም እጅግ የሚያጠብበው ነው። አዲሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሦስተኛውን ምኞት «የኑሮ ትምክህት» ብሎታል። ይህ የበለጠ ትክክለኛ ትርጉም ነው። ! በእርግጥም የኑሮ ትምክህት ሥራን ለመሥራትም ሆነ አንድ ነገርን ለማድረግና የክንዋኔ ውጤትን ለማግኘት ያለው የምኞት ግፊት ነው። ለእግዚአብሔር ክብር የሚከናወን ተግባር እንዲሁም ከሥራችን ውጤት ወይም ገቢ ቤተሰባችንን ለመርዳት የምናደርገው ጥረት ምንም ነቀፈታ የለበትም። ሆኖም፥ ስኬትን ለማምጣት ያለን ምኞት እኛኑ መልሶ | እንዲቆጣጠረንና እንዲወስደን ከፈቀድን ይኸው ምኞት ራሱ ለእግዚአብሔር ‘ መስጠት የነበረብንን ዋና ስፍራ ይይዛል። እነዚህን የመሰሉ ምኞቶች ከእግዚአብሔር የበለጡ መስለው ሲታዩን እነርሱኑ ለማሳካት የተሳሳተ መንገድ እንጠቀማለን። ይህን በማድረጋችን ኃጢአት እንሠራለን። ከዚህ የተነሣ ቀናተኞች፥ ዕቢተኞችና ኩራተኞች፥ እንዲርም ምቀኛችና ራስ ወዳዶች እንሆናለን።
ሰይጣን ምኞታችን ምን እንደሆነ ያውቃል። ከምኞቶቻችን መካከል ይበልጥ የሚስቡንን ያውቃል። እነዚያን ምኞቶች ከእግዚአብሔር ለማስቀደም በቀላሉም እንደምንፈተን ያውቃል። ስለዚህ እነዚህን ምኞቶቻችንን በተሳሳተ መንገድ እንድናሳካ በተደጋጋሚ ይፈትነናል።
ጥያቄ፡- በተሳሳተ መንገድ እንድታላኩአቸው በቀላሉ የምትፈተኑባቸው በልዩ ሁኔታ የሚስቡአችሁ ምኞቶች ምንድን ናቸው? ከእነዚህ መካከል ቢያንስ ሦስቱን ጻፉአቸው።
ሁላችንም ብንሆን ምኞቶቻችንን በማይገባ መንገድ ለማሳካት እንፈተናለን። አንዳንድ ሰዎች በእምነተ ቢስነት ይፈተናሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ በፍትወተ ሥጋ ፍላጎት ወይም ከሞራል ውጭ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ለማድረግ ይፈተናሉ። ሌሎች ደግሞ በስንፍና ይፈተናሉ። እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች ለመታወቅ በሚያድርባቸው ምኞት የተነሣ በኩራት፥ በትዕቢትና በራስ ወዳድነት ይፈተናሉ። ከዚህም በስተቀር አንዳንዶች አንድን ነገር አላግባብ ለማግኘት ስለሚሹ ስስታሞችና እምነተ ቢሶች ለመሆን ይፈተናሉ። አንዳንድ ሰዎች ሕይወት እነርሱ በፈለጉት መንገድ አልሄድ ስትላቸው ቁጡዎችና ብስጩዎች በመሆን ይፈተናሉ። ይሁን እንጂ ሁላችንም ምኞቶች አሉን። ታዲያ ኃጢአት የሚመጣው እነዚህ ምኞቶቻችን ወጥመድ ሆነው ሲጎትቱን ነው። እንዲህ በሚሆንበት ጊዜ ኃጢአትን በማድረግ ምኞቶቻችንን በተሳሳተ መንገድ እናሳካለን።
2.2 ዘፍጥረት 3፡6
የመጀመሪያው ኃጢአት ወደ ሰው ዘር የመጣው ዛሬም የኃጢአት ፈተና ወደ እኛ በሚመጣበት በዚያው መንገድ ነው። የመጀመሪያው ኃጢአት እንዴት ወደ አዳምና ሔዋን እንደ መጣ በምናስብበት ጊዜ እነዚህ ሰዎች ምኞቶቻቸውን ከእግዚአብሔር በማስቀደማቸውና በተሳሳተም መንገድ ለማሳካት ስለ ወደዱ ነው።
ጥያቄ፡– ዘፍጥረት 3፡6 አንብቡ። ሔዋን ፍሬውን ከመብላትዋ በፊት ስለ ፍሬው ምን ሦስት ነገሮችን ተመለከተች?
ሰይጣን ሔዋንን በአትክልቱ ውስጥ በፈተናት ጊዜ ስለ ፍሬው ዎ ስት ነገሮችን አይታለች። ስለ ፍሬው ያየቻቸው ነገሮች ዮሐንስ በመልእክቱ በ1ኛ ዮሐንስ 2፡15-16 የገለጻቸው ሦስቱ ምኞቶች ራሳቸው ነበሩ። በመጀመሪያ ፍሬው ለምግብነት ያማረ እንደ ነበረ ተመለከተች። ይህ እንግዲህ የሥጋ ምኞት ነበር። ይህ የደስታን ስሜት ለማግኘት በነገሮች ለመርካት የመሻት ምኞት ነው። እናም ሔዋን ምግብ መመኘትዋ ወይም መፈለግዋ ስሕተት የለበትም። ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን ምግብ ከልክሎ ነበር። ስለሆነም ሔዋን ሌላ ፍሬ በመብላት የምግብ ፍላጎትዋን ባረካች ነበር። ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሊኖራት ከሚገባት ፍላጎት ይልቅ የምግብ ፍላጎትዋ እንዲበልጥባት ፈቀደች። ሔዋን ለዚህ የተለየ ምግብ የነበራት ፍላጎት እንዲቆጣጠራትና እንዲወስዳት በፈቀደች ጊዜ ኃጢአትን መረጠች። ሁለተኛ፥ ሔዋን ፍሬው ለዓይን የሚያስጎመጅ ሆኖ አገኘችው። ይህ እንግዲህ የዓይን አምሮት የሚባለው ነው። አንድን ነገር ለማግኘት የሚደረግ ፍላጎት ነው።
ፍሬው ለዓይን ያማረ ስለነበረ ሔዋን ልትበላው ጎመጀች። ሔዋን ለዓይን ያማረ ነገር መመኘትዋ ኃጢአት አልነበረም። ነገር ግን እግዚአብሔር በተለይ ይህን ያማረ ነገር ከልክሏል። ሔዋን በዚህን ጊዜ በገነት አትክልት ስፍራ ሞልተው የነበሩ ልዩ ልዩ ፍሬዎችንና አበቦችን በመውሰድ ፍላጎቷን ባረካች ነበር። ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሊኖራት ከሚገባው በላይ ምኞትዋን ለዚህ ለዓይንዋ ላማረው ፍሬ አደረገች። ሔዋን ለዚህ ያማረ ፍሬ የነበራት ምኞት ለእግዚአብሔር ከነበራት ፍላጎት እንዲበልጥ በመፍቀዱ ኃጢአትን መረጠች። ሦስተኛ፥ ሔዋን ፍሬው ለጥበብ መልካም እንደሆነ ተመለከተች። ይህ ወደ አንድ ነገር የመድረስ ወይም አንዳች ነገርን የመፈጸም ፍላጎት ነው። ሔዋን ጥበብን ለማግኘት አሰበች። በመሠረቱ ሔዋን ጥበብን ለማግኘት መመኘትዋ ክፋት የለውም። ነገር ግን ክፉና ደጉን ለማወቅ ከዚያ ፍሬ መመገብ የእግዚአብሔር መንገድ አልነበረም። ሔዋን ይህን በማድረግ ፈንታ፡ ግንኙነትዋን ከእግዚአብሔር ጋር የበለጠ ብታሰፋ ኖሮ በምታገኘው ጥበብ ፍላጎቷ ስረካ ነበር። ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሊኖራት ከሚገባው ፍላጎት በላይ ምኞትዋን መረጠች። ሔዋን ምኞትዋ እንዲቆጣጠራት በፈቀደች ጊዜ ኃጢአት መፈጸምን መረጠች።
ጥያቄ፡– ሮሜ 5፡12 አንብቡ። ሀ) ኃጢአት ወደ ዓለም በማን በኩል ገባ? ለ) አዳም ኃጢአት ስለ ሠራ ምን ደረሰ?
ጥያቄ፦ ዘፍጥረት 3፡4-5 አንብቡ። ሔዋን ፍሬውን ለመብላት እንድትመኝ አንዳንዱን ሁኔታ የመከራት ማን ነበር?
በዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ውስጥ ከተጻፈው የመጀመሪያው ኃጢአት የምንማራቸው ሌሎች ሁለት ትምህርቶች አሉ። የመጀመሪያው፥ የአዳም ኃጢአት ከእርሱ ዘር በተወለዱ ሁሉ ላይ ተጽዕኖ ነበረው። የአዳም ኃጢአት ሁላችንንም ኃጢአተኞች አድርጎናል። ስለዚህም በሁላችንም ላይ የኃጢአት ዋጋ ሞት እንዲፈረድብን አድርጓል። ምኞቶቻችንን ከእግዚአብሔር በማስቀደም በተሳሳተ መንገድ ለማሳካት የምናደርገው ጥረት የሚቀልለን አንደኛው ምክንያት ኃጢአተኞች ሆነን በመወለዳችን ነው። የአዳም ኃጢአት ምንን እንዳስከተለብን በዚህ ሳምንትና በሚመጣው ሳምንት ትምህርታችን ውስጥ መለስ ብለን እናጠናዋለን። ሁለተኛ፥ የኃጢአት ምኞት የሚመጣብን በሰይጣንና በአጋንንቱ ማባበልና ግፊት የተነሣ ነው። በዚህም መንገድ ነው ሰይጣን ሔዋንን ከፍሬው እንድትበላ የገፋፋትና ፍሬውም እንዴት እንደሚያምር አይታ እንድትመኝ ያደረጋት። ሰይጣን ዛሬም ቢሆን ወደ ሁላችን ዘንድ መጥቶ የሚፈትነን ለመደሰት እየነገረ፥ የፈለግነውን ለማግኘት ያቀድነውን ለማከናወን መመኘታችን ከእግዚአብሔር በላይ አስፈላጊ መሆኑን በመንገር ነው። እነዚህን ከእግዚአብሔር በማስቀደም እንድንመለከታቸው በጎድረግ ይፈትነንና በኃጢአተ እንድንወድቅ ያደርገናል። ነገር ግን ኃጢአታችንን በሰይጣን ላይ ልናመካኝ አይገባም። ሰይጣን የሚያደርገው ወደ እኛ ዘንድ መጥቶ ኃጢአት የሚመኙት ነገር መሆኑን ሹክ ማለት ነው። ነገር ግን ይህን ሰምተን ኃጢአትን ማድረግ እንደ ምርግ ስንወስድ፥ ምኞታችንን ከእግዚአብሔር ማስበለጥ የራሳችን ውሳኔ ይሆናል።
ከሰብአዊ ፍላጎት ይልቅ፥ እግዚአብሔርን እጅግ አስፈላጊ ምርጫው ስላደረገው አስደናቂው የኢየሱስ ሕይወት ማየት እንችላለን።
2.3. ሉቃስ 4፡1-13
ጥያቄ፡- ሉቃስ 4፡1-13 እንብቡ። ሀ) ሰይጣን ኢየሱስን የፈተነበትን ቃላቱን መንገዶች ጻፉ? ለ) ኢየሱስ በተፈተነ ጊዜ ለሰይጣን ምላሽ የሰጠባቸውን ሦስቱን መንገዶች ጻፉ?
ሰይጣን ኢየሱስን በምድረ በዳ ሊፈትነው በመጣ ጊዜ የተጠቀመበት ፈተና ቀደም ሲልም በሔዋን ላይ የተጠቀመው ነበር። በ1ኛ ዮሐንስ ምዕራፍ 2 ላይ እንደተጠቀሰው እኛንም ለማጥቃት በዚሁ ዓይነት ፈተና ይጠቀማል። በመጀመሪያ፥ ሰይጣን ኢየሱስ ድንጋዩን ወደ ዳቦ እንዲለውጠው ፈተነው። ሰይጣን ይህን በማድረጉም ኢየሱስን በሥጋ ፍላጎት የሆነ ነገርን አግኝቶ የመደሰት ማለትም ምግብን በመብላት በሚገኘው እርካታ ነበር የፈተነው። በመሠረቱ ኢየሱስ ምግብን መብላቱ ነውር አይደለም። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ላይ ኢየሱስ ታምራዊ ኃይሉን ለራሱ ፍላጎት ብሎ እንዲጠቀምበት ወይም በዚህን ሰዓት ኢየሱስ እንዲበላ የአብ ፈቃድ አልነበረም። በዚህን ወቅት ኢየሱስ ምግብ ለመብላት ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረውም፥ እግዚአብሔርን ከምግብ ማስቀደምና ፈቃዱንም መፈጸም አስፈላጊ መሆኑን ለሰይጣን ነግሮታል።
ሁለተኛ፥ ሰይጣን ወድቆ ሲሰግድለት የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በእጁ እንደሚያስገባለት ኢየሱስን ፈትኖት ነበር። ሰይጣንም ኢየሱስን በዓይን አምሮት ፈተነው። ይህ አንዳች ነገርን ለማግኘት መመኘት ነው። በዚህ ስፍራ ይህ አንድ ነገር የዓለምን መንግሥት መጨበጥ ነበር። በመሠረቱ ለኢየሱስ የዓለም መንግሥታት ገዥ መሆን የሚገባው መብቱ ሲሆን፥ በእርግጥ የእነርሱ ሁሉ ገዢ ለመሆን ቢመኝ ኖሮ ኃጢአትም አልነበረም። ነገር ግን ሰይጣን ያቀረበለትን ፈተና ተቀብሎ ሰግዶለት ቢሆን ኖሮ ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ማስቀደም በሆነበት ነበር። እንግዲህ ኢየሱስ ምኞቱን ተከትሉ አልሄደም። በዚህ ፈንታ ኢየሱስ ማናቸውንም ሌሎች ቁሳዊ ፍላጎቶችን ከመከተል ይልቅ እግዚአብሔርን ማስቀደምና እርሱን ብቻ ማምለክ እንዳለበት ለሰይጣን ነገረው።
ሦስተኛ፥ ሰይጣን ኢየሱስን የእስራኤል መሢሕ መሆንህ ተቀባይነት እንደሚያገኝ ከቤተ መቅደስ ጫፍ ራስህን ቁልቁል ወርውር በማለት ፈተነው። በዚህም ኢየሱስን አንድን ነገር ለማግኘት በሚፈጸም የሕይወት ትምክህተኝነት ሊያጠምደው ነበር። በዚህ ሁኔታ ኢየሱስ እውነተኛ መሢሕ ተብሎ ታዋቂነትን ባገኘ ነበር። ኢየሱስ እውነተኛው መሢሕ ስለነበረ መሢሕ ተብሎ ታዋቂነትን ማግኘቱ ስሕተት አልነበረበትም። ነገር ግን ራሱን ከቤተ መቅደስ ግፍ ቢወረውር፥ ኖር በአንድ በኩል እግዚአብሔርን ተአምር እንዲያደርግ ባስገደደው ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ እግዚአብሔር ለመሢሑ የሰጠውን ተስፋ ሁሉ እስኪፈጽም የታመነ መሆኑን የሚፈትን ሁኔታ ነበር። ኢየሱስ ከመቅደሱ ጫፍ ራሱን ቁልቁል ወርውሮ ቢሆን ኖሮ ለራሱ ታዋቂነትን ለማግኘት ሲል ፍላጎቱን እግዚአብሔር በሕይወቱ ሊያከናውን ካለው ፈቃዱ ባስቀደመ ነበር። መቼና እንዴት መሢሕ ሆኖ ታዋቂነቱን እንደሚያገኝ እግዚአብሔር ካለው የመቆጣጠር ሥልጣን የራሱን ምኞት ባስቀደመ ነበር። እንግዲህ ኢየሱስ ምኞቱን አልተከተለም። እንዲያውም እግዚአብሔር እኛ በፈለግነው መንገድ እና ጊዜ ነገሮችን እንዲያከናውን ልናስገድደው እንደማይገባ ለሰይጣን በብርቱ ነገረው።
ጥያቄ፡- እናንተ ከሰይጣን ጋር ለምታደርጉት ትግል ኢየሱስ የመጣበትን ፈተና ያሸነፈበት ሁኔታ እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል? ኃጢአት ከየት ይመጣል? ኃጢአት የሚመጣው የራሳችንን ምኞት ከእግዚአብሔርና ከእርሱ መንገድ ስናስቀድም ነው። ኢየሱስ ልክ እንደ እኛው ምኞቱን ከእግዚአብሔር ለማስቀደምና በራሱ መንገድ ለመፈጸም ተፈትኖ ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ እግዚአብሔርን በሕይወቱ ውስጥ ከምንም በፊት በማስቀደም የመጣበትን ፈተና አሸንፎአል። የራሱ ምኞት አጥፊው እንዲሆን አልፈቀደለትም። እንደዚሁም ምኞቱ እንዲስበው፥ እንዲያታልለው፥ ወጥመድ እንዲሆንበትና እንዲወስደው አልፈቀደለትም። በዚህ ፈንታ ምኞቱ እግዚአብሔርን የማወቅና ለእርሱም የመታዘዝ ፍላጎት ሕይወቱን እንዲጠቀልል ፈቀደ። ኢየሱስ ለእግዚአብሔር የነበረው ፍላጎት የራሱን ፍላጎት አሸነፈ። እኛ እንዴት አድርገን ፈተናን ማሸነፍ እንደምንችል ኢየሱስ ለእኛ ምሳሌያችን ነው። በምንም ዓይነት ለምኞታችን ትኩረት ሰጥተን እንዲቆጣጠረን ልንፈቅድለት አይገባም። በዚህ ፈንታ ትኩረታችንን በእግዚአብሔር ላይ በማድረግ ምኞታችን ለእርሱ አገልግሎት እንዲውል እንዲጠቀምበት ማድረግ አለብን።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ