መንፈስ ቅዱስ፤ ሦስተኛው የሥላሴ አካል

አንድ ቀን በአውቶብስ ማቆሚያ ስፍራ አውቶቡላ ለጠብቅ «ኢየሱስ ብቻ» በሚባለው ሐሰተኛ ትምህርት ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰው ወደ እኔ ቀረበ። «በሰማይ ስንት ዙፋን አለ?» የሚል ጥያቄ አቀረበልኝ። በሰማይ ያላው አንድ ዙፋን ብቻ ስለሆነ በአንድ አምላክ ውስጥ ሦስት አካላት ሊኖሩ ፈጽሞ የማይቻል እንደሆነ በጥንቃቄ ሊያረጋግጥልኝ ሞከረ። ከመጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ከባድ ትምህርቶች አንዱ የሥላሴ እውነት ማለትም እንደ ክርስቲያን ስም ስት አካል በሚገኝ አንድ አምላክ ማመናችን ነው። ይህ ከሰብዓዊ መረዳታችን በላይ ነው። ላማስረዳትም አስቸጋሪ ነው። ሆኖም ቀን ለአእምሮ የማይቻል በመምሰሉ ነገር ከመረታታችን በፊት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመሄድ ምን እንደሚል ማረጋገጥ አላበን። መጽሐፍ ቅዱስ የሥላሴን ትርጉም ባይሰጥም እንኳ ለመግለጽ አስቸጋሪ በሆነ መንገድ እግዚአብሔር አንድም ሦስትም እንደሆነ ያስተምረናል። 

ጥያቄ፡- ሀ) የሥላሴ ሦስት አካላት እነማን ናቸው? ለ) የሥላሴን ትርጉም በአጭሩ ግለጽ። ሐ) ስለ ሥላሴ አስቀድሞ ሰምቶ ለማያውቅ ክርስቲያን ላልሆነ ሰው ስለ ሥላሴ እንዴት እንደምትገልጽላት በአጭሩ ጻፍ። 

መንፈስ ቅዱስ አካል እንዳለውና በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ያላ ኃይል ወይም ግዑዝ አካል እንዳልሆነ ከተረዳን በኋላ ሌላ ጥያቄ ለመጠየቅ እንገደዳለን። መንፈስ ቅዱስ ማን ነው? እንደ መልአክ በእግዚአብሔር የተፈጠረና በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ያለ መንፈስ ነውን? ወይስ ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ ጋር እኩል የሆነ አምላክ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? 

የክርስትና ታሪክ ክርስቲያኖች በዘመናት ሁሉ ስም ስት አካላት የተገለጠ አንድ አምላክን እንዳመላኩ ያስተምራል። ይህ ስለ እግዚአብሔር ለራሳችን ለመረዳትም ሆነ ለሌሎች ለመግለጽ እጅግ አስቸጋሪ ከሆኑ ትምህርቶች አንዱ ነው። ልንቀበላቸው የማይገቡ ሁላት የከረሩ አቋሞች አሉ። የመጀመሪያው፥ አንዳንዶች በእግዚአብሔር አንድ መሆን ላይ ብቻ ከሚገባ በላይ በማተኮር ኢየሱስም ሆነ መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር እብ ጋር እኩል አምላክ መሆናቸውን ይክዳሉ። ይህ አመለካከት አንዳንዶቹን በብሉይ ኪዳን ዘመን አንዱ አምላክ ይሖዋ በመባል ይጠራ ነበር እያሉ እንዲያስተምሩ አድርጓቸዋል። ይኸው እንድ አምላክ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ተብሏል። በቤተ ክርስቲያን ዘመን ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ተብሏል ይላሉ። በዚህም ስሞች ይቀያየራሉ እንጂ ያለው አንድ አምላክ ብቻ ነው ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ኢየሱስና መንፈስ ቅዱስ እንደ እግዚአብሔር አብ አምላክ አይደሉም። ይልቁኑ አነስ ያሉ አማልክት ናቸው ይላሉ። በታላቁ እምላክ የተፈጠሩ ትናንሽ አምላኮች ናቸው። ልናመልካቸው እንችላለን ነገር ግን እንደ ታላቅ አንድ አምላክ ስላልሆኑ ዘላለማዊና ከእርሱ እኩል የሆኑ ናቸው ማለት የለብንም ይላሉ። 

ጥያቄ፡- በእግዚአብሔር እንድነት ላይ እጅግ በማተኮር በሥላሴ የማያምኑ በኢትዮጵያ የሚገኙ የእምነት ክፍሎችን ዘርዝር። 

በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ቡድኖች ወይም ኑፋቄዎች ስለ እግዚአብሔር ከላይ የተመለከትነውን ዓይነት የተሳሳተ አሳብ ያላቸው አሉ። ሙስሊሞች አንድ አምላክ ብቻ እንዳለ አጥብቀው ይናገራሉ። ለመቀበልም ሆነ ለመረዳት ከሚያስቸግራቸው ትምህርቶች አንዱ የሥላሴ ትምህርት ነው። (ይህ ብዙ ጊዜ የሚሆነው ክርስቲያኖች ሥላሴ ስንል ሦን ማለታችን እንደሆነ ለመግለጽ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር በሚገባ ባለመረዳታችን ነው።) የሐዋርያት እምነት ቤተ ክርስቲያን እንድ አምላክ እንዳለ በተላያዩ የታሪክ ወቅቶችም የተለያዩ ስሞች እንዳሉት ይናገራሉ። የይሖዋ ምስክሮች ኢየሱስ ከእግዚአብሔር የሚያንስ እምላክ እንደሆነ ያስተምራሉ። ራሱን ክርስቲያን አድርጐ የሚቆጥር ነገር ግን ያልሆነ አንድ የሃይማኖት ቡድንን ወይም የሐሰት ትምህርትን ከምንለይባቸው መንገዶች እንዱ ሥላሴን ለማመን ፈቀደኛ አለመሆናቸው ነው። 

በሁለተኛ ደረጃ ልናስወግደው የሚገባ ሌላ የከረረ አቋም አለ። እግዚአብሔር እብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሦስት ፍጹም የተለያዩ አምላኮች ናቸው የሚሉ አስተማሪዎች አሉ። ይህ ሦስት የተለያዩ ሰዎች ቆመው እንደ ማየት ነው። እያንዳንዳቸው የራሳቸው አካል፥ የራሳቸው ፈቃድና የራሳቸው ማንነት አላቸው። በምስት ሰዎች መካከል እንድነት ሊኖር አይችልም። እነዚህ ሰዎች ክርስቲያኖች የላት አማልክትን እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ያመልካሉ ይላሉ። በዚህም ክርስቲያኖች ብዙ አማልክትን ከሚያመልኩ ክሂንዱዎች፥ ከቡድሒስቶች ወይም ከዓረማውያን አይላዩም ይላሉ። 

ሙስሊሞችና ይሁዲዎች ክርስቲያኖችን ሦስት አምላክ ታመልካላችሁ ብለው ይከሱናል። ስለዚህ ክርስቲያኖች ስለ እግዚአብሔር ምን እንደምናምን ለሙስሊሞችና ለይሁዲዎች መግለጽ እንድንችል ግልጽ መረዳት ያስፈልገናል። 

ስለሆነም ክርስቲያኖች የሚያምኑት ምንን ነው? ወይም የተሻለ ጥያቄ የሚሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ሥላሴ ስላሆነው አምላክ ምን ያስተምረናል? 

1. ክርስቲያኖች ሦስት የተለያዩ አማልክትን ሳይሆን አንድ አምላክ ብቻ ያምናሉ። 

ጥያቄ፡– የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አንብብ። ዘዳ 6፡4 5፤ ኢሳ. 45፡5-6፤ ኛ ቆሮ 8፡4-6፤ ያዕ.2፡19። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ምን ያስተምራሉ? 

በብሉይ ኪዳን የነበረው ታላቁ ትኩረት እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል ለማስተማር የፈለገው ዋና እውነት እርሱ ብቻ እግዚአብሔር እንደሆነ ነው። ብዙ አማልክት ሳይሆን አንድ አምላክ ብቻ ነው ያለው ( በግ 6፡4-5) በዚያን ጊዜ የነበረው ዓለም ሁሉ ብዙ አማልክት እንዳሉ ያምን ነበር። ግብጽና ከነዓን የየራሳቸው አማልክት ነበሯቸው። በወንዞች ላይ፥ ከዋክብት ላይ በፀሐይ ላይ አማልክት ነበሩ። እግዚአብሔር እራሱን ለእስራኤል ሲገልጥ በተደጋጋሚ ያስተማራቸው አንድ አምላክ ይሖዋ፥ የእስራኤል አምላክ እርሱ እንደሆነ ነበር። አንዱ አምላክ ዓለምን ፈጠረ ሕዝቡን እስራኤልንም መረጠ። «አማልክት» በመባል የተጠሩት ሌሉቹ ሁሉ ዋጋ የሌላቸው፥ ኃይልም የሌላቸው፥ በሰው ግምት የተፈጠሩ ሰውን የሚመስሉ ደካሞችና በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ጣዖታት ነበሩ። እግዚአብሔር ብቻ ዘላለማዊ፥ ያልተፈጠረ የነገሮች ሁሉ ተቆጣጣሪ ነው (ኢሳ. 45፡5-6)። 

እግዚአብሔር አንድ የመሆኑን እውነታ ኢየሱስ ክርስቶስም ሆነ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች አረጋግጠዋል። ታላቂቱ ትእዛዝ እግዚአብሔር እንድ እንደሆነ ማመንና እርሱንም በሙሉ ልባችን፥ ነፍሳችን፥ አእምሮአችንና ኃይላችን እንድንወደው ኢየሱስ ተናግሯል (ማር. 12፡29)። ጳውሎስ አንድ እምላክ ብቻ አላ ብሏል (1ኛ ቆሮ. 8፡4-6)። ያዕቆብ ሰዎች አንድ እግዚእብሔር ብቻ እንዳለ ማመን እንደሚገባቸው በአጽንኦት ተናግሯል (ያዕ. 2፡19)። 

ምንም ልንረዳው ወይም ልንገልጸው አስቸጋሪ ቢሆንብንም እንኳ እንደ ክርስቲያን አንድ አምላክን ብቻ እንደምናመልክ ማስታወስ አለብን። 

2. ክርስቲያኖች አንዱ እግዚአብሔር ምሥጢራዊ በሆነ መንገድ እራሱን በሦስት አካላት እንደገለጠ ያምናሉ። እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ። 

እሰካሁን ድረስ የተመለከትነው መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን አንደ ተራ ኃይል እግዚአብሔር ዕቅዱን ለመፈጸም የሚጠቀምበት አካል እንደሌለው ኃይል እድርጐ ፈጽሞ እንደማያቀርበው ነው። ይልቁኑ መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን የሚያቀርበው እንደ አካል ነው። ሥጋ እንደለበሰ እካል ሳይሆን ሥጋ እንደሌለው መንፈሳዊ አካል ያቀርበዋል። በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን በአኅዳዊነት እንደሚያቀርበው ማለትም እግዚአብሔር እንድ አምላክ እንደሆነ ተመልክተናል። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማረጋገጫዎችን ልናቀርብላቸው የሚገቡ ሁለት እጅግ ጠቃሚ ጉዳዮች አሉ። የመጀመሪያው እግዚአብሔር በኑባሬ ከአንድ በላይ ነው ወይስ አንድ ብቻ ስለሚለው ነው። ይህ «የኢየሱስ ብቻ» ተከታዮችን ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እምነት የሚለያቸው ዋነኛ ነጥቦች አንዱ ነው። ሁለተኛው ጉዛይ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ አምላክ የመሆኑና በዚህም ከሥላሴ አካላት አንዱ የመሆኑ ጉዳይ ነው። 

መጽሐፍ ቅዱስ አንድ አምላክ ሦስት በአንድ የሆነ አምላክ መሆኑን ያስተምራልን? 

ጥያቄ፡- አንድ የኦርቶዶክስ ክርስቲያንን በተለይ ካህን የሆነውን ሰው በግዕዝ ቋንቋ ሥላሴ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ጠይቀው። ይህ ቃል እግዚአብሔር አንድ እንደሆነና ደግሞም ሦላት እንደሆነ የሚጠቅሱትን አሳቦች እንዴት ያጣምራቸዋል? 

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ ትምህርቶች ከሁሉ የላቀው ከባድ ትምህርት የእግዚአብሔር አንድም ሦ ለትም መሆን ነው። ስለ እግዚአብሔር የሚያስረዳው የዚህ እውነት ሥነ መለኮታዊ አጠራር «ሥላሴ» የሚል ነው። ይህ የሥነ መለኮት ቃል የተመረጠው በመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ሲሆን ትርጉሙም አንድና ሦስት በአንድ ውስጥ ሦስት ማለት ነው። 

እግዚአብሔር አንድና ሦስት መሆኑን የምንረዳበትን ችሎታ የሚሰጠን ሰብዓዊ መረዳት ወይም ልምምድ በእርግጥ ፈጽሞ የለንም። ስለዚህ ሰመጨረሻ ወመቀበል ያለብን ጉዳይ ይህ እውነት ከሰብዓዊ መረዳት ወይም ገለጻ ያለፈ መሆኑን ነው። የምንሰጠው ማናቸውም ዓይነት ማስረጃ በቂ አይደለም። ነገር በኢሳ. 5፡8-9 ላይ እግዚአብሔር አሳቡ ከአሳሳችን የላቀ ስለመሆኑ የተናገረውን በትሕትና ልናስታውሰው ይገባናል። 

ለ2000 ዓመታት ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ በሦስት አካላት እራሱን የገላጠ አንድ አምላክ እንደሚያስተምር ሲያምኑ ኑረዋል። እነዚህም ሦስት አካላት እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ናቸው። ይህ ትምህርት የመጣው ክየት ነበር? መልሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው የሚል ይሆናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚእብሔር ሥላሴን በግልጽ ያብራራበት ቦታ የለም። ሆኖም ግን መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ መንገዶች አንዱ እግዚአብሔር ሦስት ሰአንድ መሆኑን ያስተምረናል። ብሉይ ኪዳን በእግዚአብሔር አንድነት ላይ እንደሚያተኩር አይተናል። ነገር ቀን በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በብዙ ቁጥርም እንደሚታወቅ ጠቋሚ ነገሮች አሉ። 

1. የብሉይ ኪዳን ማረጋገጫ 

ሀ. በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ የተጠራበት ስም፡- በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ የተጠራበት የተለመደ ስሙ «ኤሎሂም» ሲሆን ትርጉሙም እግዚአብሔር ማለት ነው። በዕብራይስጥ ቋንቋ ስሞች አንድ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ነገሮች ለማሳየት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የስሞች ባዕድ መድረሻዎች የተለያዩ ናቸው። ይህ አጠቃቀም የነጠላ ወይም የብዙ ቁጥር ብቻ ካላቸው ከዚህ ያለፈ የተለያየ ክፍፍል ከሌላቸው ከአማርኛና ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈጽሞ የተለየ ነው። ኤሎሂም የተባለው የእግዚአብሔር ለም ክሁላት በላይ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በዕብራይስጥ ቋንቋ የብዙ ቁጥር ግርማዊነትና ታላቅነትን የሚያመለክት ቢሆንም እንኳ በአዲስ ኪዳን ግልጽ ትምህርት አኳያ ይህ ስም ሥላሴን የሚያመላክት ይሆናል። 

ለ. የፍጥረት ታሪክ ቋንቋ 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት፡- ዘፍ 1፡26፤ 3፡22 11፡6፥7 ኢሳ. 6፡8። በእነዚህ ጥቅሶች ሁሉ ከአንድ አካል በላይ የሚጠቁሙ ‘ምን ተውላጠ ስሞች ተግባር ላይ ውለዋል። 

እግዚአብሔር ከአንድ በላይ የመሆኑ አመልካች አሳብ የሚገኘው ከዘፍጥረትና ከኢሳይያስ በምናገኘው ልዩ አገላለጾች ነው። በእነዚህም ጥቅሶች ሁሉ እግዚአብሔር ይናገራል። በዘፍ 1፡26 «ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር» በማለት እግዚእብሔር ይናገራል። ኋላ ደግሞ በዘፍጥ. 3፡22 እግዚአብሔር ሰው ከእኛ እንደ አንዳችን እንዳይሆን ሲል እንመለከተዋለን። በኢሳ. 6፡8 ደግሞ እግዚአብሔር ማን ይሄድልናል?» ብሎ ይጠይቃል። በእያንዳንዱ ሁኔታ እግዚአብሔር ከራሱ ውጭ ለሌላ አካል እንደሚናገር ግልጽ ነው። አንዳንድ ምሁራን እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ የተጠቀመበት መንገድ አንድ መሪ የመንግሥት አቋም ለመግለጽ አሳቦችን የሚያቀርብበትን ዓይነት አነጋገር ነው ይላሉ። ወይም ደግሞ ለመላእክት እየተናገረ ነበር ይላሉ። ነገር ግን ከአዲስ ኪዳን ተጨማሪ ማብራሪያዎች አንጻር እነዚህ ነገሮች የሚያመለክቱት ሥላሴን እንደሆነ ይገመታል። 

2. የአዲስ ኪዳን ማረጋገጫዎች 

ወደ አዲስ ኪዳን ስንመለከት በአንድ መለኮት ውስጥ ሦስት አካላት የመኖራቸው ማረጋገጫዎች ግልጽ እየሆኑ ይመጣሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባልተብራራ ምሥጢራዊ መንገድ እግዚአብሔር እብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ (ሥላሴ) ማለትም እንደ መለኮት በሦስት አካላት የመኖሩ ጉዳይ ግልጽ ሆኖ ይታያል። 

ጥያቄ- ማቴ. 28፡19-20፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡4-6፤ 2ኛ ቆሮ. 13፡14፤ ኤፌ. 3፡14-19፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡2 አንብብ። እነዚህ ጥቅሶች የሥላሴ አካላቱን እኩልነት የሚያሳዩት እንዴት ነው? 

በብሉይ ኪዳን አንዱ አምላክ በአካል ከአንድ በላይ መሆኑን የሚያሳየን ቢሆንም እንኳ አንዱ አምላክ በአካል ሦስት መሆኑን የሚያሳየን አዲስ ኪዳን ነው። ይህን በግልጽ ከሚያሳዩ ጥቅሶች ሁላቱ ማቴ 28፡19ና 2ኛ ቆሮ. 13፡14 ናቸው። በእነዚህ ሁለት ጥቅሶች ሦስቱም የሥላሴ አካላት አንዳቸው ከሌላቸው እንደሚያንሱ ምንም ፍንጭ ሰማይሰጥ መንገድ ጐን ለጐን ተጠቅሰዋል። አዲስ ኪዳን በተጻፈበት የግሪክ ቋንቋ ኢየሱስ ብቻ የሚሉት እማኞች እንደሚሉት ሦስቱ ስሞች ለአንድ አካል የተሰጡ የተለያዩ ስሞች እንዳልሆኑ ግልጽ ሆኖ ቀርቧል። ይልቁኑ ሦስት የተለያዩ አካላትን በግልጽ ያመለክታል። በማቴ. 28፡ 19 ሰዎች የሚጠቀሙበት ስም አንድ ብቻ እንጂ ሦስት ስሞች እንዳልሆኑ ልብ ማለት መልካም ነው። ነገር ግን በዚያ አንድ አምላክ ስም ሦስቱ የሥላሴ አካላት ማለትም እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና መንፈስ ቅዱስ ተካትተዋል። 

የሥላሴን ትምህርት ከዚህ በላይ መግለጥ ከዚህ መጽሐፍ አቅም በላይ ነው። ዓላማችን አንድ አምላክ ሦስት አካላት እንዳሉት በቅድሚያ ማረጋገጥና ከአካላቱ እንዱ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ማሳየት ነው። የአዲስ ኪዳን ተቀዳሚ ትኩረት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ቢሆንም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እንደሆነና ከእግዚአብሔር አብ የተለየ አካል ለመሆኑ በርካታ ማስረጃዎች አሉ። 

ጥያቄ፡- ዮሐ. 1፡1፤ 8፡54-58፤ 20፡28፤ 21፡17፤ ሮሜ 9፡5፤ ዕብ. 1፡6፥8፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡18-19 እንብብ። እነዚህ ጥቅሶች እያንዳንዳቸው ኢየሱስ አምላክ መሆኑን እንዴት ያሳያሉ? 

ሀ. መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ የተለየ አካል ነው፡- ስለ መንፈስ ቅዱስ የተጻፉ ጥቅሶችን በጥንቃቄ ስንመረምር እርሱ ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ የተላየ ፍጹም መለኮት መሆኑን እናረጋግጣለን። ወደ አብ ስለሚማልድ ከአብ የተለየ መሆኑ ግልጽ ነው (ሮሜ 8፡27)። ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን ወደ ደቀመዛሙርት እንደላከው ስንመለከት ከኢየሱስ የተለየ አካል እንዳለው በቀላሉ እንገነዘባለን (ዮሐ 15፡26)። መንፈስ ቅዱስ የራሱ እውቀት ፈቃድ አለው (ዮሐ 14፡26፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡1)። 

ጥያቄ፡– የሚከተሉትን ጥቅሶች አወዳድር። ዘጸ 17፡2-7ና ዕብ 3፡7-9፤ ኢሳ. 6፡8-10ና የሐዋ. 28፡25-27፤ 1ኛ ቆሮ. 3፡16 ና 2ኛ ቆሮ. 6፡16፤ ዮሐ 3፡6ና 1ኛ ዮሐ 5፡4 የሐዋ. 5፡3ና 5፡4 እነዚህ ጥቅሶች የመንፈስ ቅዱስን ላም ከእግዚአብሔር ስም ጋር እየቀያየሩ የሚጠቀሙት እንዴት ነው? 

ለ. መንፈስ ቅዱስ አምላክ ተብሎ ተጠርቷል፡- እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ጥቅሶች ስናጠና በእያንዳንዱ ጥቅስ ላይ መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ስፍራ እየተፈራረቀ ቀርቧል። በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር አብ የተናገረው ነገር በአዲስ ኪዳን ሊጠቀስ መንፈስ ቅዱስ የተናገረው እንደሆነ ተመልክቷል። በአዲስ ኪዳን የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደሆንን የተነገረ ሲሆን ይህም እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል እንደሚያድር የተሰጠው ተስፋ ፍጻሜ እንደሆነ ተጠቅሷል። ከመንፈስ ቅዱስ የተወለደ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ እንደሆነም ተጽፏል። መንፈስ ቅዱስን መዋሸት እግዚአብሔርን መዋሸት ነው። እነዚህ ጥቅሶች አዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር መሆኑን እንደሚያስተምር ከሚያረጋግጡ ጥቅሶች ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው። በሚቀጥለው ክፍል መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር መሆኑን የሚያረጋግጡ ሌሎች ጥቅሶችን እናጠናለን። 

ለማጠቃለል መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል? ብንል በመጀመሪያ፥ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር አንድ መሆኑን ያስተምራል ። እንድ አምላክና አንድ አምላክ ብቻ እለ። በሁለተኛው ደረጃ ፥ መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ አምላክ ውስጥ እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ አካላት መኖራቸውን ያስተምራል። እያንዳንዳቸው እኩልና ምሉዕ እምላክ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ሁለት አካሎች በማጣመር ይህን የማይቻል የሚመስል ነገር እንዴት እንደሆነ ለመግለጽ ጥረት እያደርግም። 

ይህ መሠረታዊ የእምነት ትምህርት (አስተምህሮ) ለመግለጽ ከባድ ነው። ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ተገቢ ባልሆነ መንገድ ስለሚያቀርቡት ሙስሊሞች በተሳሳተ መንገድ ይረዱና በዚህ ትምህርት ይሰናከላሉ። «ኢየሱስ ብቻ » የሚላው እምነት ተከታዮች አንድ አምላክ ብቻ እንዳለ በማስተማር ብዙዎችን ስሕተት ውስጥ ከትተዋል። ትምህርታቸው አዲስ አይደላም። ይልቁኑ የመጀመሪያቱ ቤተ ክርስቲያን ታግላ ተቃውማዋለች። እነዚህ ሰዎች የሚያስተምሩት እግዚአብሔር በተለያዩ ዘመናት እራሱን በተላያየ ቅርጽ (ማንነት) እንዳቀረበ ነው። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ነበር፥ ቀጥሎ እግዚአብሔር ወልድ ሆነ፥ በመጨረሻ ደግሞ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሆነ። ይህ የሥላሴን ትምህርት ለመግለጽ ቀላል ቢመስልም ጨርሶ ሊሆን ግን አይችልም። እግዚአብሔር አብ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደላከ እናነባለን (ዮሐ. 3፡16)። ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር አብ እንደጸለየ ደግሞ እናነባለን (ሉቃስ 22፡41፡42)። ኢየሱስ የጸለየው ወደ ራሱ ነበርን? እግዚአብሔር አብ እራሱን ላከን? ይህ ስሜት የሚሰጥ አይደለም። የሥላሴን ትምህርት መረዳት የማይቻል ቢሆንም የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ግልጽ እንደሚያደርገው እግዚአብሔር ዎ ስት አካላት ያሉት አንድ አምላክ ነው። 

ሦስቱ የሥላሴ አካላት በእንድነት የሠሩበትን ግልጽ የሆነ ማረጋገጫ በማቴ 3፡16-17 ላይ እናገኛለን። ኢየሱላ በዮሐንስ እጅ በተጠመቀ ጊዜ በምድር ላይ ነበር። በዚያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ራስ ላይ ሰርግብ አምሳል ወረደ። በርሃብ አምሳል የተገለጠው መንፈስ ቅዱስና ኢየሱስ በአንድነት ነበሩ። እነርሱ በአንድነት በነበሩ ጊዜ የእግዚአብሔር አብ ድምፅ ከሰማይ ኢየሱስ የሚወደው ልጁ እንደሆነ ሲናገር ተሰማ። ይህ የኢየሱስ ብቻ አስተማሪዎችን ትምህርት በግልጽ ከንቱ ያደርገዋል። ይህ ለማት ሊሰጥ የሚችለው በመለኮት ውስጥ ሦስት አካላት ካሉ ብቻ ነው።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading