የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይመሩ ዘንድ መሪዎችን ብቁ በማድረግ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት

ጥያቄ፡- ሀ) በቤተ ክርስቲያን መሪ ሆኖ ማገልገል በጣም ከባድ የሚሆነው ለምንድን ነው? ለ) የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እጅግ የቀረበ ግንኙነት እንደሚያስፈልጋቸው ይህ ምን ያሳየናል? 

ምናልባት በምድር ላይ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከመምራት የበለጠ እጅግ እስቸጋሪ ተግባር አይኖርም። ጳውሎስ ለወንጌል ብሉ ከተቀበላቸው መከራዎች ሁሉ በላይ ለአብያተ ክርስቲያናት ያለበት ኃላፊነት በጣም አስቸጋሪ እንደነበር ተናግሯል (2ኛ ቆር. 11፡23-29 ተመልከት)። የእግዚአብሔርን ሕዝብ የመምራት ኃላፊነታቸውን በቀላሉ የሚያዩ በርካታ መሪዎች አሉ። ሥልጣናቸውን ለራሳቸው ጥቅም ይገለገሉበታል። ከሕዝቡ ገንዘብ ይወስዱና ትላልቅ ቤቶችን ለራሳቸው ይሠራሉ። በሚገባ ለመምራትና ለእግዚአብሔር መንጋ መልካም እረኛ መሆን ግን እጅግ ከባድ ሥራ ነው። ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ይህንን ሥራ (ተግባር) ማከናወን የማይቻል ነው። 

ትናንት እንዳነበብነው መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን በሥራ የተጠመደ ነበር። በብሉይ ኪዳን ታሪክ ተቀዳሚው ትኩረት የተሰጠው እርሱ ባይሆንም ሕይወትን በመፍጠርና በማቆየት ሥራ ምን ያህል ተካፋይ እንደሆነ ተመልክተናል። አንዳንድ ሰዎች ለእግዚአብሔር አንድ ተግባርን እንዲፈጽሙ ልዩ ችሎታዎችን በመስጠት ተሳታፊ ነበር። በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረው የመንፈስ ቅዱስ ዋና ተግባር ሕዝቡን በሚገባ ይመሩ ዘንድ መሪዎችን ብቁ ማድረግ ነበር። 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ዘፍ 41፡38-40፤ ዘኁል. 11፡16-18፥ 24-29፤ 27፡18-19፤ ዘዳ 34፡9፤ መሳፍ 3፡9-10፤ 6፡34፤ 11፡29፤ 13፡24-25፤ 14፡6፤ 1ኛ ሳሙ. 10፡9-10፤ 11፡6፤ 16፡13፤ 19፡20-23፤ ዳን 4፡8፤ 5፡11-14 2ኛ ነገ 2፡9-14። ሀ) የእግዚአብሔር መንፈስ በላያቸው ላይ እንደነበር የተነገረላቸውን የተለያዩ ሰዎች ዘርዝር። ለ) መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ይሠሩ ዘንድ እነኚህን ሰዎች ምን እንዳስቻላቸው ግለጽ? 

መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመንና እጅግ በብዛት የተጠቀሰበት ሁኔታ መሪዎች ለእግዚአብሔር ክብርን የሚያመጣ ተግባር ይፈጽሙ ዘንድ ብቁ ማድረጉ ነው። ዮሴፍ የነበረው ህልሞችን የመተርጐም ጥበብ በውስጡ ካለው የእግዚአብሔር መንፈስ ጋር የተያያዘ ነበር። መንፈስ ቅዱስ በመሪዎች ላይ የመውረዱ ጉዳይ በቅድሚያ የታየው በዘኁል. 1 ላይ ነበር። እስራኤላውያን በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ እግዚአብሔር በሚያስደንቅ ተአምራት ህልውናውን ቢያሳያቸውም ያላማቋረጥ በእርሱ ላይ ዐመፁ። ∫አንድ ቀን እግዚአብሔር እየመጎባቸው ከነበረው ከመና ይልቅ ሌላ ሥጋን ይሰጣቸው ዘንድ ሙሴን ጠየቁት። ሙሴ እጅግ ከመናደዱ የተነሣ መሪ መሆኑን ለመተው ፈለገ፤ እንዲያውም እግዚአብሔር እንዲገድለው ጠየቀ። የእግዚአብሔር መልስ ምን ነበር? እግዚእብሔር ለሙሴ አመራር እገዛ እንዲያደርጉ 70 ሽማግሌዎችን ለየ። እግዚአብሔር ለሙሴ ሲናገር በእንተ ላይ ያደረግሁትን ይህን መንፈስ በ70 ዎቹም ላይ እደርጋለሁ። ስለዚህ የሕዝቡን ሸክም ለብቻህ አትከምም አለው። እነዚህ 70 ሰዎች የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳለባቸው ማረጋገማው ምን ነበር? የእግዚአብሔርን መንፈስ እንደተቀበሉ ትንቢት ተናገሩ። ግን አንድ ጊዜ ብቻ ተናገሩ እንጂ ከዚያ በኋላ አልደገሙትም። መንፈስ ቅዱስ የተሰጣቸው ነቢያት እንዲሆኑ አልነበረም። ለሕዝቡ የእግዚአብሔር አፈ ጉባኤ ሆኖ የሚናገር ሙሴ ነበር። ነገር ግን እነዚህ 70 ሰዎች በእግዚአብሔር እንደተመረጡና ላመሪነታቸው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንደተሞሉ ለሕዝቡ ለማሳየት የመተንበይ ችሎታ እግዚአብሔር ለአጭር ጊዜ ሰጣቸው። መንፈስ ቅዱስ ከእነርሱ ጋር በመቆየት ይመሩ ዘንድ እገዛቸው እንጂ ከእነርሱ ጋር ለመሆኑ ማረጋገጥ ድጋሚ ትንቢት እንዲናገሩ አላደረገም። 

የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ከ70 ዎቹ ጋር ባልነበሩት በሁለቱም ሰዎች ላይ መርዶ እንደ ነበር መመልከት እስደናቂ ነው (ዘኁል. 11፡26)። እግዚአብሔር ይህን ለምን እንዳደረገ አናውቅም። ይህን ያደረገው ምናልባት የእግዚአብሔር መንፈስ በሰው ቁጥጥር ሥር የሚሆንና እንዴት እንደሚሠራ የሚወስንለት እንዳልሆነ ለማሳየት ይሆናል። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለፈለገው ሁሉ በፈለገው ጊዜ የመስጠት መብቱ ሁልጊዜ እንደተጠበቀ ነው። የሙሴ ምላሽ ግን ሁላችንም ልናስታውሰው የተገባ ነው። የሙሴ ረዳት የነበረው ኢያሱ ሙሴ የእግዚአብሔርን መንፈስ እንዲቆጣጠር ፈለገ። ኢያሱ ቀናተኛ ነበር፤ ሙሴ ግን ኃይሉን ለመከላከል እልቃጣም። የእግዚአብሔር ሰዎች በሙሉ መንፈስ ቅዱስን ቢለማመዱና ለመተንበይ ቢችሉ ምኞቱ እንደሆነ ለኢያሱ ነገረው። ስሉዓላዊነቱ መንፈሱን እንደ ፈቃዱ የሚያድል እግዚአብሔር ስለሆነ፥ ሙሴ እግዚአብሔርን መቆጣጠር የተገባው አልነበረም። 16ኛ ጥያቄ፡- ብዙ ክርስቲያን መሪዎች ሌሎችን ሰዎች ከእነርሱ በተሻለ መንገድ እግዚአብሔር ሲጠቀምባቸው ሲያዩ ያላቸው አመለካከት ሙሴ ከነበረው በጣም የሚለየው እንዴት ነው? 

የብሉይ ኪዳን ታሪክ እንደሚናገረው (በግልጽ እንዳስቀመጠው) ይህ መሪዎችን ብቁ የማድረግ ተግባር ሊቀጥል እንመለከታለን። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ለሁላም መሪዎች የተሰጠ አልነበረም። ኢያሱ ከሙሴ የተላለፈበት የጥበብ መንፈስ እንደነበረው እናነባለን። መንፈስ ቅዱስን የማስተላላፍ ተግባር በሙሴ የግል ውሳኔ የሆነ ቢመስልም እግዚአብሔር ለሙሴ አስቀድሞ እርሱን የሚተካው መሪ ኢያሱ እንደሚሆን ነግሮት ነበር (ዘጻ 1፡38)። ኢያሱ በእግዚአብሔር የተመረጠ መሪ መሆኑን ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ለማሳየት ሙሴ በኢያሱ ላይ እጆቹን በመጫን በሾመው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከሙሴ ወደ ኢያሱ በግልጽ አለፈ። 

ጥያቄ፡– መሳ. 13–16 አንብብ። መንፈስ ቅዱስ የተጠቀሰባቸውን የተለያዩ ጊዜያትና በሳምሶን ሕይወት ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ምን ምን መማር እንደምትችል ዘርዝር። 

በመሳፍንት ዘመን የነበሩ መሪዎች መሳፍንት በመባል የሚታወቁ ነበሩ። እነዚህ በመሠረቱ ወታደራዊ መሪዎች ሲሆኑ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ጊዜያዊ አርነትን እንዲያስገኙ በእግዚአብሔር የሚሾሙ ነበሩ። ብዙዎቹ መንፈስ ቅዱስ እንደወረደባቸው ይነገራል። ከዋና ዋናዎቹ አትናጐልቶ ጌዴዎን ዮፍታሔና ሳምሶን ይገኙበታል። መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ስለ ሠራው ሥራ ታላቅ ምሳሌ የሚሆን መስፍን ሳምሶን ነበር። እግዚአብሔር ሳምሶንን የእስራኤል መሪ እድርጐ የመረጠው በእናቱ ማኅፀን ሳለ ነበር። ለእግዚአብሔር አገልግሎት ለመለየቱ ውጫዊ ምልክት (መለያ) ይሆን ዘንድ የሚያሰክር መጠጥ እንዳይጠጣ፥ በድን እንዳይነካና ፀጉሩን እንዳይቆረጥ እግዚአብሔር እዝዞ ነበር። ወጣቶች ሳለን እንደተነገረን የጌታ መንፈስ ሳምሶንን ያነቃቃው ጀመረ (መሳ. 23፡25)። መንፈስ ቅዱስ በሳምሶን ላይ መሆኑ ኲመንፈሳዊ ሕይወቱ ጋር ምንም ቀንኙነት እልነበረውም። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በግልጽ ጥሶ ከአሕዛብ ሌት አገባ። ሴተኛ አዳሪዎች ቤት ይሄድ ነበር። ሳምሶን የተገባለትን ቃል ኪዳን እንኳ ጥሶ በድን አንበሳ ነክቷል። ወይን ጠጅም ጠጥቷል። ነገር ግን በተዴጋጋሚ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል እንደወረደ እናነባለን (መሳ. 14፡6፥ 19፣ 5፡14)። በእርግጥ ሳምሶን ከእግዚአብሔር እጅግ በመራቁና የመጨረሻውን ቃል ኪዳን ጥሶ ፀጉሩን በመላቱ መንፈስ ቅዱስ ተላየው። ይህ ሁሉ ሲሆን ሳምሶን እግዚአብሔር እንደተወው አላወቀም ነበር (መሳ. 16፡20)። ከዚህ የምንመለከተው በብሉይ ኪዳን ዘመን አንድ መሪ ልዩ የሆነ ተግባር መፈጸም እንዲችል መንፈስ ቅዱስ ይወርድበት እንደነበር ነው። ሆኖም ይህ የተለየ ተግባር ሲፈጸም መንፈስ ቅዱስ ከሰውዬው ተለይቶ ይሄድ ነበር። ሳምሶን እግዚአብሔር የሚፈልገውን ይፈጽም ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በተደጋጋሚ ተሰጥቶት ነበር። ሳምሶን ካለመታዘዝ ይልቅ እግዚአብሔርን በመታዘዝ ቢኖር ኖሮ ለእግዚአብሔር ምን ባደረገ ነበር! 

መንፈስ ቅዱስ በውስጡ መንፈሳዊነት በሌለው ሰው እንኳ እንደሚጠቀም ሳምሶን ጥሩ ምሳሌ ነው። ይህን የሚያደርገው የእግዚአብሔር መንፈስ ሰዎች በፈለጉት መንገድ የሚሄድ ሳይሆን በአንድ ሰው ሕይወት ወይም አገልግሎት ውስጥ አንድ ታላቅ ነገር ሲፈጸም ኃይሉ የመንፈስ ቅዱስ እንጂ የዚያ ሰው እንዳልሆነ ለማሳየት ነው። ሆኖም ግን ብዙውን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሥጋዊ ክርስቲያንን ኃይልን በሚገልጥ መንገድ አይጠቀምም። 

ጥያቄ፡- ህ) ሰዎች ለእግዚአብሔር በማይኖሩበት ጊዜ እንኳ መንፈስ ቅዱስ እነርሱን በኃይል መጠቀሙን እንዴት ትመለከታለህ? ለ) በመጨረሻ በእነዚህ ሰዎች ላይ ምን ይሆናል? ሐ) ከሳምሶን ሕይወት ምን ማስጠንቀቂያ መውሰድ ይገባናል? 

በነገሥታት የመጀመሪያ ዓመታትም መንፈስ ቅዱስ ለአመራር በተመረጡ በአንዳንዶች ላይ ይወርድ እንደነበር ተጽፏ። ሳኦል ንጉሥ ይሆን ዘንድ በሳሙኤል ከተቀባ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ወረደበት። አዲስ ንጉሥ በእስራኤል በሚነግሥስት ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ህልውና በእርሱ ላይ የሚረጋገጠው በተለያዩ መንገዶች ነበር። በሙሴ ዘመን የነበሩት 70 ዎቹ ሽማግሌዎች መንፈስ ቅዱስ በወረደባቸው ጊዜ ትንቢትን እንደተናገሩ ሳኦልም መንፈስ ቅዱስ በወረደበት ጊዜ ትንቢት ተናገረ። ነገር ግን በሳኦል ላይ ሌላም ለውጥ ታየ («እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትላወጣለህ» 1ኛ ሳሙ. 10፡6)። ሳኦል ድፍረትና ጠላቶችን በጦር ሜዳ የሚያሸንፍበት ኃይል ተሰጠው። ሳኦል በተላይ ለጦርነት በሚዘጋጅበት ጊዜ በተደጋጋሚ መንፈስ ቅዱስ ይወርድበት እንደነበር እናነባለን (1ኛ ሳሙ. 11፡6)። ነገር ቀን ሳኦል ኃጢአትን በሠራና እግዚአብሔርም የእስራኤል ንጉሥ እንዳይሆን በናቀው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ተወሰደበት 1ኛ ሳሙ. 15፡10፥22-23)። መንፈስ ቅዱስ በሳኦል ላይ እንደገና በድንገት መምጣቱ የሚያስደንቅ ነው። በ1ኛ ሳሙ. 19፡18-24 ሳኦል ዳዊትን ለመግደል የሞከረበትን የሕይወቱን ክፍለ ገጽታ ስናይ ጻዊትን ለመያዝ ሦስት ቡድን ጦር ላከበት። ሦስቱንም ጊዜ ጦሩ ሳሙኤልንና ዳዊትን ለመያዝ ቢቀርብም እንኳ መንፈስ ቅዱስ በወታደሮቹ ላይ በመውረድ ቶትን እንዳይማርኩ አገጻቸው። እንዲያውም ትንቢት መናገር ጀመሩ። በሕይወቱ ለሁለተኛ ጊዜ በመጨረሻ ሳኦል እራሱ ሄደ። ምንም እንኳ በእግዚአብሐር የተናቀና ጳዊትን ለመግደል እየሞከረ ቢሆንም መንፈስ ቅዱስ ወረደበትና ትንቢት ተናገረ። በሳኦል ላይ የመጣው መንፈስ ቅዱስ በኃይል ስለ ነበር ሳኦል ለአንድ ቀንና ሌሊት እንደ በድን ሆነ። 

ሳሙኤል ዳዊትን በቀባው ጊዜ በእርሱም ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ። ዳዊት ከሳኦልም ሆነ ከሌሎች መሪዎች የተለየ ነበር። ምክንያቱም በሌሎች የወረደው መንፈስ ቅዱስ ጊዜያዊ የነበረ ቢሆንም፥ በዳዊት ላይ ከወረደበት ቀን ጀምሮ ከእርሱ ጋር ነበር (1ኛ ሳሙ. 16፡13)። ጻዊት የማመንዘርና የነፍስ መግደል ኃጢአት በሠራ ጊዜም እንኳ መንፈስ ቅዱስ ትቶት እንደሄደ አናነብም። ታላቁ ፍርሃቱ ይህ ነበርና በመዝ. 50፡11 ላይ እግዚአብሔር ቅዱስ መንፈሱን እንዳይወስድባት ለመነ። ዳዊት እንደ ሳኦል በእግዚአብሔር መናቅ አልፈለገም ነበር። 

እግዚአብሔር ለጊዜው መንፈሱን የላከላቸው ሌሎችም አሉ። ከዳዊት ዋና መሪ ጀኔራሎች መካከል አንዱ በሆነው በዓማሣይ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ነበር (1ኛ ዜና 12፡18)። መንፈስ ቅዱስ በሌሎች በርካታ ሰዎች ላይ በመውረዱ የእስራኤል ና የይሁዳ ነገሥታት ለእግዚአብሔር ባልታዘዙበት ጊዜ ትንቢት ተናግረውባቸዋል (2ኛ ዜና 5፡1፤ 20፡14፤ 24፡20)። 

በብሉይ ኪዳን ዘመን ስለ መንፈስ ቅዱስ የምናያቸው ጠቃሚ ነጥቦች ቀጥሎ ተዘርዝረዋል። 

መንፈስ ቅዱስ ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ ይሰጥ ነበር። ለእግዚአብሔር ሰዎች በሙሉ አልተሰጠም ነበር። አንዳንድ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ መውረድ በመሪዎች ውስጥ ይሆን ነበር (ሰኢያሱ ወይም በዳንኤል እንደሆነው)፤ ብዙ ጊዜ ግን መንፈስ ቅዱስ በመሪዎች ላይ የሚወርደው እግዚአብሔር ሕዝቡን በአንድ የተለየ ሁኔታ ውስጥ እንዲመሩ ለማስቻል በሚፈልግበት ጊዜ ነበር። (በብሉይ ኪዳን ዘመን በነበረው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎትና በአዲስ ኪዳን ዘመን ባለው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት መካከል ከፍተኛ ልዩነት ከሚታይባቸው ነጥቦች እንዱ ይህ መሆኑን ወደፊት እንመለከታለን።) 

መንፈስ ቅዱስ ለሰዎች የሚሰጠው በእግዚአብሔር ፈቃድና ውሳኔ ነበር እንጂ በሰው ፈቃድ የሚሰጥ ወይም በሰው ቁጥጥር ሥር የሚሆን አልነበረም። 

የመንፈስ ቅዱስ ህልውና አንዳንድ ጊዜ በተአምራዊ ምልክቶች የታይ ቢሆንም ይህ ግን ሁልጊዜ የሚሆን አልነበረም። የእስራኤል ሽማግሌዎች በመጀመሪያ የትንቢት ስጦታ ነበራቸው። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእመራራቸው ውስጥ የነበረው ህልውና የቀጠለ ሲሆንም የመተንበይ ስጦታቸው ግን አልዘለቀም። በብሉይ ኪዳን የነበሩና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የታጠቁ አብዛኛዎቹ መሪዎች ተአምራዊ ምልክት (እንደ ትንቢት ያላ) አብሮአቸው እንደነበር የሚጠቁም ምንም ማስረጃ የለንም። 

መንፈስ ቅዱስ ለአንዳንድ ሰዎች የሚሰጥበት ምክንያት የእግዚአብሔር ሕዝብ ጠላቶቻቸውን ማሸነፍ እንዲችሉ ለመምራት ነበር። 

የመንፈስ ቅዱስ ህልውና በመሪዎች ሕይወት ውስጥ ጊዜያዊ እንጂ ቋሚ አልነበረም። ለምሳሌ በሳምሶን ሕይወት መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ በርካታ ጊዜ እንደወረደ እናነባለን። 

መንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ሕይወት መኖሩ በሰውዬው የሕይወት ንጽሕና ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ባለው የቀረበ አካሄድ የተወሰነ አልነበረም። ሳምሶን እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ ሲኖርም እንኳ መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ ይወርድ ነበር። ክፉ መንፈስ ያለማቋረጥ ያሰበው በነበረበትና ጻዊትንም ለመግደል በፈለገበት ጊዜ እንኳ መንፈስ ቅዱስ በሳኦል ላይ ይወርድ ነበር። ጳዊት አመንዝራና ነፍሰ ገዳይ በሆነበት ጊዜ እንኳ መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ጋር ነበረ። 

እግዚአብሔር መንፈሱን ከአንድ መሪ ይወስድ የነበረው የመሪው አገልግሎት ሲፈጸም ወይም እግዚአብሔር መንፈሱ በመሪው ውስጥ እንዲቆይ እስከማይታገሥ ድረስ በኃጢአቱ ሲቀጥል ነበር። ሳምሶን ፀጉሩን በተላጨ ጊዜ ያለመታዘዙ መጠን ከፍተኛ ደረጃ ስለደረሰ እግዚአብሔር መንፈሱን (የኃይሉ ምንጭ የነበረውን) ከሳምሶን ወሰደ። እግዚአብሔር መንፈሱን የመለሰው ሳምሶን የቤተ መቅደሱን ምሶሶዎች በመናድ በርካታ ፍልስጥኤማውያንን ለመግደል ያስቻለውን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ብቻ ነበር። ከንጉሥ ሳኦል የእግዚአብሔር መንፈስ የተወሰደበት እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ አካሄዱ እጅግ ተጠናክሮ በቀጠለበት ጊዜ ነበር። 

ጥያቄ፡- መንፈስ ቅዱስና የብሉይ ኪዳን አመራርን አስመልክቶ የተጠናቀሩ አንኳር እውነቶችን በመከለስ ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ከሚጠቀምበት አሠራር የሚመሳሰሉና የሚለያዩ እነዚህ እነዚህ ናቸው ብለህ የምታምናቸውን ነጥቦች ዘርዝር።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

1 thought on “የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይመሩ ዘንድ መሪዎችን ብቁ በማድረግ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት”

  1. ጌታ ኢየሱስ ይባርክ ደስ ብሎኛል

    በቀን 23/12/2013 የሙስሊም ወንጌል መስበክ እንዳለብን ለነገ ስልጠና አስፈላጊ መረጃ ላክልኝ ? በተለ ወንጌል እንዴት እንዲረስ?

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading