የሕይወት እንጀራ

የደኅንነት አስፈላጊነት – ኃጢአት ምንድን ነው? ክፍል አንድ 

This entry is part 58 of 197 in the series በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች (FAQs)

በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች (FAQs)

አማላጅነት፦ ትርጉሙ፣ የክርስቶስ ዘላለማዊ ምልጃ እና የአማኞች ድርሻ

መጽሐፍ ቅዱስ፦ መለኮታዊ መነሻው፣ መዋቅሩና በአማኝ ሕይወት ውስጥ ያለው ኃይል

ቅዱሳን፦ ትርጉሙ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቱና የቅድስና ሕይወት

ዲያብሎስ፦ ማንነቱ፣ ውድቀቱና በመስቀል ላይ የተሸነፈበት መለኮታዊ ድል

መላእክት፦ ማንነታቸው፣ ተግባራቸውና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርዓታቸው

ኢየሱስ ክርስቶስ፦ ማንነቱ፣ መለኮታዊ ሥራውና የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት

እምነት፦ ትርጉሙ፣ ምንጩና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኃይሉ

አማኑኤል፦ ትርጉሙ፣ ትንቢታዊ መሠረቱና መለኮታዊ ምስጢሩ

ወንጌል፦ ትርጉሙ፣ ማዕከላዊ ሐሳቡና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኃይሉ

እግዚአብሔር፦ ማንነቱ፣ መለኮታዊ ባሕርያቱና የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት

ጸጋ፦ ትርጉሙ፣ መገለጫዎቹና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቱ

ንስሐ፦ መንፈሳዊ ትርጉሙ፣ አስፈላጊነቱና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቱ

ጸሎት፦ መንፈሳዊ ትርጉሙ፣ አስፈላጊነቱና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቱ

ጾም፦ መንፈሳዊ ትርጉሙ፣ ዓላማውና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቱ

ድነት፦ ትርጉሙ፣ አስፈላጊነቱና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቱ

የክርስቶስ ደም፦ ሥነ-መለኮታዊ ትርጉምና የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት

ሰዎች የክርስቶስን መልእክት ሳይሰሙ ሊድኑ ይችላሉ? 

ለመሆኑ በመጨረሻው ሰዎች ሁሉ ይድናሉ ወይ? 

የሚሞቱ ሕፃናት ይድናሉ? 

ቅዱስ ቁርባንን መቀበል፥ ደኅንነት ያስገኛል? 

ደኅንነትን የመቀበል ጥያቄ፣ እምነትና ጥምቀት  

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 3 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 2 

የዘላለማዊ ዋስትና ማረጋገጫ እና የእግዚአብሔር ቅዱሳን ጽናት፥ ክፍል 1 

የደኅንነት በረከቶች – እንከብራለን ሲባል ምን ማለት ነው?  

ቅድስና 

ጉዲፈቻ (የማደጎ ልጅ) 

ጽድቅና ይቅርታ፥ ክፍል አንድ 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር የመተባበር በረከቶች ምንድን ናቸው? 

ከክርስቶስ ጋር መተባበር – ከክርስቶስ ጋር መተባበር ማለት ምን ማለት ነው? 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 2 

ዳግም መወለድ፥ ክፍል 1 

እምነት ከታዛዥነት ጋር እንዴት ይዛመዳል? 

ወደ እግዚአብሔር መመለስ ወይም «መለወጥ» 

እምነት 

የመዳኛ መንገድ፡- ንስሐ እምነትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ 

ስለ እግዚአብሔር ምርጫና ለደኅንነት ስለሚያደርገው ጥሪ ጥያቄዎች 

ይቅርታ የማይደረግበት ኃጢአት ምንድን ነው? 

አንዳንዱ ኃጢአት ከሌላው የባሰ ነውን? 

ሕፃናት በእርግጥ ኃጢአትን ለመሥራት ከደረሱበት ጊዜ በፊት የኃጢአት በደለኞች ይባላሉ? 

የደኅንነት አስፈላጊነት- ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው?

ኃጢአት ከየት መጣ? 

እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ የመረጣቸውን አበክሮ ይጠራቸዋል። 

እግዚአብሔር ለጥቂቶች ምሕረቱን ሊሰጥ ይመርጣል 

ወደ ደኅንነት መድረሻው መንገድ – የእግዚአብሔር ምርጫና የእግዚአብሔር ጥሪ 

ኢየሱስ በሞቱ በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን ተቀዳጅቷል – ክፍል ሁለት 

የኢየሱስ ሞት በሰይጣን ላይ ታላቅ ድልን አስገኝቷል- ክፍል አንድ 

ኢየሱስ የራሱ ሰዎች እንድንሆን ከኃጢአት ዋጀን

ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀን 

የኢየሱስ ሞት የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቁጣ ለማርካት (ለማብረድ) የቀረበ መሥዋዕት ነው። 

ኢየሱስ ለኃጢአት ፍጹም የሆነ መሥዋዕት ሆነ፦ የአዲስ ኪዳን መፈጸም

የእግዚአብሔር ቅዱስነት የኃጢአትን መሥዋዕት ይሻል፡- የብሉይ ኪዳን ምሳሌ 

የደኅንነት ትርጉም፡- ከኃጢአትና ከኃጢአት ውጤቶች ሁሉ መዳን 

ኃጢአት በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ 

ሁሉም ሰው የኃጢአት ተግባርን ፈጽሟል 

ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት በደልን ወርሰናል

የኃጢአት ውጤት፡- ሞት 

የደኅንነት አስፈላጊነት – ኃጢአት ምንድን ነው? ክፍል አንድ 

ክርስቶስ እንደ መካከለኛና እንደ አማላጅ 

ኢየሱስ አሁን ያለው ባሕሪና አገልግሎቱ

የኢየሱስ ዕርገት (ከፍ ከፍ ማለት) 

የክርስቶስ ከፍ ከፍ ማለት (ዕርገት)

የኢየሱስ ሞት 

ኢየሱስ እና የእግዚአብሔር መንግሥት

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ምሳሌያችን 

የክርስቶስ መቀባት

ኢየሱስ እንደ ጌታ 

በጳውሎስና በዮሐንስ መጻሕፍት ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መገለጹ 

የእግዚአብሔር ልጅ መለኮታዊ ነው። 

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ መሆኑ በብሉይና በወንጌላት ውስጥ 

ኢየሱስ የሰው ልጅ 

መሢሑ እንደ መድኅን 

መሢሑ እንደ ነቢይ 

መሢሑ እንደ ካህን 

መሢሑ እንደ ንጉሥ 

መሢሑ ኢየሱስ

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

የሚመጣው መሢሕ ትንቢቶችና ተስፋዎች 

በብሉይ ኪዳን የክርስቶስ ተምሳሌቶች

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሲገለጥ (ቅድመ-ተሠገዎ)

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የያህዌ መልአክ (ቅድመ- ተሠገዎ የክርስቶስ መገለጥ)

ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተገለጠባቸው መልኮችና ምሳሌዎች

በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኢቢዮናውያን 

ስለ ተሠገዎ በዕብራውያን ምዕራፍ 2 

ከተስፋቢስነትህ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ በውትድርና ሙያ ስለሚያገለግል ክርስቲያን ምን ይላል?

የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ክለሳ

የመንፈስ ቅዱስ ሁለተኛ ዋና ተግባሩ፡- ወደ ኢየሱስ ማመልከትና እርሱን እንድንመስል ማድረግ።

የመጀመሪያው የመንፈስ ቅዱስ ዋና ሥራ፡- ዘላለማዊው አምላክ በውስጣችን መኖሩ

በመንፈስ ቅዱስ መሞላትና መንፈሳዊ ብስለት

በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት የሚቀርቡ ቅድመ ሁኔታዎች

በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት ማረጋገጫዎች

ከኤፌ 5፡18-20 በመንፈስ ቅዱስ ስላ መሞላት ምን ልንመለከት እንችላለን?

የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ምንድን ነው?

በመንፈስ ቅዱስ መሞላት

የመንፈሳዊ ስጦታዎች ትምህርት ማጠቃለያ

ስለ ተአምራትና ፈውሶች የሚሰጡ የተሳሳቱ አሳቦች

እግዚአብሔር ፈውስን የሚሰጥባቸው የተለያዩ አሠራሮች

ተአምራትና ፈውሶች በአዲስ ኪዳን

የብሉይ ኪዳን ተአምራትና አዲሱን ዘመን በተስፋ መመልከት

የመፈወስና ተአምራትን የማድረግ ስጦታዎች

የትንቢት ስጦታን ለመጠቀም መመሪያዎቹ ምን ምን ናቸው?

የእውነተኛና ሐሰተኛ ነቢያት ንጽጽር

የትንቢት ስጦታ ምንድን ነው?

ትንቢት ምንድን ነው? ነቢይስ?

በቤተ ክርስቱያን ውስጥ ስለሚመጣው ትንቢት ተጨማሪ አሳቦች

በልሳናት ስለመናገር ተጨማሪ ጉዳዮች (ክፍል 2) የተለያዩ ዓይነት ልሳናት አሉን?

በልሳናት ስለመናገር ተጨማሪ ጉዳዮች (ክፍል 1)

መንፈሳዊ ስጦታዎችና የማያምኑ ሰዎች (1ኛ ቆሮንቶስ 14፡20-40)

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 14፡1-19)

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 13)

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡12-31 )

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡4-11 )

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡1-3)

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ጴጥሮስ 4፡7-11 )

መንፈሳዊ ስጦታ (ኤፌሶን 4፡1-16 )

መንፈሳዊ ስጦታ (ሮሜ 12፡1-8)

መንፈሳዊ ስጦታ ምንድን ነው?

ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች መግቢያ

ሰይጣንን ድል የማድረግ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት

መንፈስ ቅዱስ የክርስቲያኖች ሕይወት ኢየሱስን እንዲመስል የሚሰጠው አገልግሎት

መንፈስ ቅዱስ እንድናመልክ ይረዳናል

የመንፈስ ቅዱስ አማኞችን ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመምራት አገልግሎት

በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ልሳን በመናገር መካከል ያሉ ግንኙነቶች

በክርስቲያኖች መካከል ከፍተኛ ልዩነት የሚፈጥሩ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ክፍሎች (ክፍል 2)

በክርስቲያኖች መካከል ከፍተኛ ልዩነት የሚፈጥሩ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ክፍሎች (ክፍል 1)

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት (ክፍል ሦስት)

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት (ክፍል ሁለት)

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት (ክፍል አንድ)

በካሪዝማቲክ የሥነ መለኮት ትምህርት የሚገኙ ሚዛናዊ ያልሆኑ ነገሮች

ከካሪዝማቲክ ትምህርት ለቤተ ክርስቲያን የተረፉ መልካም ውጤቶች

የጰንጠቆስጤና የአንዳንድ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ዋና ትምህርቶች ምን ምን ናቸው?

የጴንጤቆስጤ ሥነ መለኮት ታሪክ

የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሰው ድነት (ደኅንነት) ውስጥ፤ ክፍል 3

የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሰው ድነት (ደኅንነት) ውስጥ፤ ክፍል 2

የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሰው ድነት (ደኅንነት) ውስጥ፤ ክፍል 1

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 9-28)

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 3-8 )

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 1-2 )

በመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችና በአምልኮ ልምምዶች ውስጥ ያሉ ልዩነቶችን እንዴት መያዝ አለብን?

መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ የተለያዩ መረዳቶች የሚታዩት ለምንድን ነው?

ክርስቲያኖች እንደ መንፈስ ቅዱስ ባሉ መሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮዎች ላይ ባላቸው አመለካከት ልዩነት የሚያሳዩት ለምንድን ነው?

ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ያስተማረው ትምህርት፤ ክፍል 2

ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሰጠው ትምህርት፤ ክፍል 1

መንፈስ ቅዱስ በጌታ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ውስጥ

የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በወንጌላት

የብሉይ ኪዳን ነቢያት መሢሑ የሚመጣበትን ወቅትና የመንፈስ ቅዱስ አገልግሉት የሚለወጥበትን ጊዜ እስቀድመው አመልክተው ነበር

መንፈስ ቅዱስ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንዲጽፉ በመምራት የሰጠው አገልግሎት

የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይመሩ ዘንድ መሪዎችን ብቁ በማድረግ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት

መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን

መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ አምላክ መሆኑን ያሳየናልን?

መንፈስ ቅዱስ፤ ሦስተኛው የሥላሴ አካል

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?

የመንፈስ ቅዱስ ተምሳሌቶች

የመንፈስ ቅዱስ ስሞች

የመንፈስ ቅዱስ ዋና ኃላፊነቶች ምንና ምን ናቸው?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ስፍራ

መንፈስ ቅዱስን ማወቅ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የምንረዳበት ምንጭ

ሥነ መለኮት ምንድን ነው?

ስለ መንፈስ ቅዱስ ለምን እናጠናለን?

መግቢያ

ጌታን እራት ለሚያስፈጽሙ መሪዎች አስተያየት

ክርስቲያኖች በጌታ እራት ላይ ያላቸው የግንዛቤ ልዩነት

አላግባብ የጌታን እራት ስለመውሰድ የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎች

ቅዱስ ቁርባን (የጌታ እራት) ማለት ምን ማለት ነው?

የጌታ እራት ሥረ መሠረት

ስለ ጌታ እራት ኢየሱስ የሰጣቸውን በርካታ መመሪያዎች መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

የጌታ እራት ሥርዓት እንዴት እንደ ተጀመረ?

«ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት»

የቤተ ክርስቲያን ንጥቀት ገለጣ (ዮሐ. 14፡1-3፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡51-57፣ 1ኛ ተሰ. 4፡13-18)

መንግሥተ ሰማያትና የቅጣት ስፍራ

ትንሣኤዎች

የወደፊቱ ፍርድ

የዘመኑ መጨረሻ

የሺህ ዓመት ግዛት

የፍዳው ዘመን [Tribulation]

ስለ ወደፊቱ ጊዜ ያሉ መሠረታዊ አመለካከቶች

ቤተ ክርስቲያን መቼ ተጀመረች?

ዓለም-አቀፋዊት ቤተ ክርስቲያን

ጥምቀት

የጌታ እራት

የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች

አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን

ቤተ ክርስቲያን በሚለው ፅንሰ አሳብ ውስጥ የሚካተተው ምንድነው?

የድነት (የደኅንነት) ቃላት

የአማኙ ዋስትና

በክርስቶስ ሞት የተገኙ አንዳንድ ጥቅሞች

የክርስቶስ ሞት

ምርጫ ምንን ያካትታል?

የሰው ኃጢአት

የሰው ልጅ ውድቀትና የታሪክ መለወጥ (ዘፍጥረት 3)

የሰው ተፈጥሮ፡- የሰው ባሕርይ

ስለ አጋንንት ትምህርት

ስለ ለይጣን ትምህርት

ስለ መላእክት ትምህርት

ባለፉት የመጀመሪያዎቹ አሥር ሳምንታት ትምህርታችን ውስጥ ያጠናነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር። በቀሪዎቹ አሥር ሳምንታት ደግሞ ኢየሱስ ለእኛ ደኅንነትን በማምጣት ስለፈጸመልን ሥራ እናጠናለን። ስለዚህ ኢየሱስ ስለሚሰጠን ደኅንነት አስፈላጊነት በማጥናት ትምህርቱን እንጀምራለን። ሰዎች ኃጢአተኞች ስለሆኑ ኢየሱስ የሚሰጣቸው ደኅንነት ያስፈልጋቸዋል። ኃጢአተኞች ሆነው ከመወለዳቸው በተጨማሪ፥ ሁሉም በሕይወት ዘመናቸው ኃጢአትን ይፈጽማሉ። ኃጢአት ሞትንና ከእግዚአብሔር መለየትን ያመጣል። በዚህና በሚቀጥለው ሳምንት፥ ከኃጢአታችንና ከእግዚአብሔር ከመለየታችን የተነሣ በከፍተኛ ሁኔታ እዳኝ እንደሚያስፈልገን እንማራለን። 

ኃጢአት ምነው? 

ኃጢአት ምን እንደሆነ መገንዘባችን በጣም ጠቃሚ ነው። ስለ ኃጢአት ምንነት የሚኖረን ግንዛቤ፥ ስለ እግዚአብሔር ማንነት፥ ስለ ሰዎችና ስለ ደኅንነት ምንነት ከሚኖረን መረዳት ጋር የተዛመደ ነው። እግዚአብሔርን ሕዝቡም ልክ እንደ እርሱ እንዲሆኑ የሚፈልግ በጣም ንጹሕና ቅዱስ አምላክ አድርገን ካሰብን፥ ሕጉንና ለባሕሪው የሚበጀውን በትንሹ መተላለፍ እንኳን ከባድ ሆኖ ይሰማናል። በአንጻሩ እግዚአብሔር ከእኛ የራቀና ስለ እኛ ሕይወትም ግድ የሌለው አድርገን ከወሰድነው፧ በዚህ አስተሳሰባችን ረገድ ኃጢአት ለእኛ ይህን ያህል ከባድ ነገር ሊሆንብን አይችልም። ሰዎች በመሠረቱ መልካም ናቸው የምንል ከሆነ ኃጢአት ሊያመጣቸው የሚችለውን አባዜ ራሳቸው በራሳቸው ሊወጡት ይችላሉ እንደ ማለት ነው። ሆኖም ሰዎች በመሠረቱ ክፉዎች ከሆኑ ኃጢአት ሊያስከትልባቸው የሚችለውን ፍዳ ለማሸነፍ አዳኝ ይሻሉ። ሰዎች ለሚያደርጉት ተጠያቂዎች መሆን ካለባቸው፥ ኃጢአታቸው በእግዚአብሔር ፊት ከባድ ይሆናል። ሁላችንም ኃጢአት ምን እንደሆነ በሚገባ ካልተገነዘብን በስተቀር ጠንካራ ክርስቲያኖች ሆነን ለማደግና ሌሎችንም ለማገልገል አንችልም። ስለ ኃጢአትና ስለ ደኅንነት ምንነት ለማጥናት ስንነሣ በመጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኃጢአት ምንነት በሚሰጠው ትምህርት መጀመር ይገባል። 

1. ኃጢአት እግዚአብሔር ወደሚፈልገው ደረጃ መድረስ አለመቻል ነው። 

ጥያቄ – ኃጢአት ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ የምታውቃቸው ሰዎች እንዴት ይመልሱታል? 

ስለ ኃጢአት ምንነት ሰዎች የተለያዩ አሳቦች አሉዋቸው። አንዳንድ ሰዎች ኃጢአት የቤተሰባቸውን ወይም የኅብረተሰባቸውን ሰላም የማናጋት ሁኔታ መሥራት ይመስላቸዋል። ይህ አድራጎታቸው በአካባቢያቸው ያሉትን ሰዎች የሚያስቸግር እስከሆነ ድረስ ይህን ያህል ጉዳት የለበትም ብለው ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ ስለ ኃጢአት ምንነት ሲያስረዱ፣ ሌሎች ሰዎች መጥፎ ነው ብለው የሚያስቡትን ሁሉ ማድረግና በዚህም ተግባር ወንጀለኛ ሆኖ መያዝ ኃጢአት ነው ባይ ናቸው። ምንም ነገር ያድርጉ ተግባራቸው በሌሎች ሰዎች ተደርሶበት እስካልተያዙ ኃጢአት እንደ ሠሩ አያምኑም። ከዚህ ለየት የሚሉት ምክንያት አቅራቢዎች ደግሞ፥ ኃጢአት ማለት የእግዚአብሔርን ሕግ የሚጥስ ተግባር መፈጸም ነው ሲሉ ያስባሉ። እንደ እነርሱ እምነትም በውጫዊው ሁኔታዎች የእግዚአብሔርን ሕግ የሚታዘዙ እስከ መሰላቸው ድረስ፥ ኃጢአት ሠርተናል ብለው አያስቡም። የሰዎች አስተሳሰብ ይህ ሲሆን፥ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኃጢአት ምንነት እንዴት ያስተምረናል? 

በዕብራይስጥ ለኃጢአት የተሰጠው ቃል «ኃቻታ» (hachata) የሚል ሲሆን፥ ይህም «ኃጢአት» ከሚለው የአማርኛ ቃል ጋር የተዛመደ ነው። የዚህ ቃል መሠረታዊ ትርጉም፤ «ዒላማን መሣት» (miss the mark) ማለት ነው። የግሪኩ ትርጉም ደግሞ ኃጢአትን «ሐማርቲያ» (hamatia) ይለዋል። የዚህም ትርጉም፥ «ዒላማን መሣት» የሚል ነው። የእነዚህ ቃላት መሠረታዊ ትርጉሞች ለመገንዘብ ቃል በቃል የተጠቀምንባቸውን ሁለት የምንባብ ክፍሎች ቀጥለን እንመለከታለን። 

ጥያቄ፡- መሳፍንት 20፡16 እንብቡ። ሀ) ከቢንያም ነገድ የሆኑ 700 ሰዎች ምን አደረጉ? ለ) ምሳሌ 19፡2 አንብቡ። አንድ ሰው ችኩል ቢሆን ምን ይደርስበታል? 

በመጽሐፈ መሳፍንት 20፡16 እና በምሳሌ 19፡2 ላይ ለኃጢአት በዕብራይስጡ የቃል በቃል አጠቃቀም ተቀምጦ እንመለከታለን። በዚሁ በመጽሐፈ መሳፍንት 20፡16 እንደተጻፈው፥ ከቢንያም ነገድ የሆኑ 70 ሰዎች በወንጭፍ ድንጋይ ሲወረውሩ ሌላው ቀርቶ «ጠጉር የማይስቱ ነበሩ» ይላል። እነዚህ ሰዎች ያነጣጠሩበትን ዓላማ አይስቱም ነበር። በምሳሌ 19፡2 ደግሞ፥ «ጥድፊያም መንገድን ያስታል» ይላል። እነዚህ ጥቅሶች ኃጢአትን መፈጸም ምን እንደሆነ የመጀመሪያውን አሳብ ይሰጡናል። ኃጢአትን ማድረግ ማለት፥ እግዚአብሔር ያስቀመጠውን ዒላማ መሳት ነው። እግዚአብሔር የወሰነልንን ያመለከተንን መንገድ መሣትም ነው። ኃጢአትን መፈጸም ማለት እግዚአብሔር በሚፈልገው ደረጃ ላይ አለመገኘት ማለት አይደለም። 

ኃጢአት ሲባል፥ ዒላማን መሳት ነው ብለን በምናስብበት ጊዜ አንደ ድንጋይ ወንጫፊ ዓላማውን ለመምታት ወርውሮ እንደሚስት ሁሉ፡ እግዚአብሔር ወደሚፈልግብን ደረጃ ለመድረስ ጥረት አድርገን ከደረጃ ወ ሳንደርስ እንደ መቅረት አድርገን ብቻ እንወስደው ይሆናል። ያለጥርጥር ኃጢአት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለመፈጸም ሞክረን ሳይሆንልን መቅረትንም ይጨምራል። ነገር ግን የኃጢአት ትርጉም፥ «ዒላማ ለመምታት ሞክሮ መሳት» ብቻም አይደለም። አንድ ሰው ሆን ብሎ በተሳሳተ ዒላ ላይ በማነጣጠር ዒላማ መሳቱንም ደግሞ ያጠቃልላል። አንድ ሰው ትክክለኛ ያልሆነውን መንገድ በመምረጡ ምክንያት ትክክለኛውን መንገድ ሳተ ማለት ነው። አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ለእኛ ምን እንደሆነ እያወቅን ዳሩ ግን በራሳችን ምርጫ ትእዛዙን እናፈርሳለን። ይህ ኃጢአት ነው። በሌላ ሁኔታ ደግሞ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አናውቅ ይሆናል፥ ነገር ግን አውቀን አለመታዘዝን እንመርጣለን። ይህም ደግሞ ኃጢአት ነው። ኃጢአት ማለት የእግዚአብሔርን ደረጃ ልንደርስበት በምናደርገው ጥረትም ሆነ ፈልገንና አውቀን ዒላማውን ስንስት ነው። 

2. ኃጢአት የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ አለመቻል ነው። 

ኃጢአት በምንፈጽምበት ጊዜ ምን ደረጃ እናጣለን? ኃጢአት የእግዚአብሔርን የሞራል ሕግ ዒላማ በሥራችን፣ ስዝንባሌያችንና በባሕርያችን መምታት ሲያቅተን ነው። 

ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐንስ 3፡4 አንብቡ። እንደ ዮሐንስ አጻጻፍ ኃጢአት ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 2፡12፤ 4፡15 አንብቡ። ሀ) ጳውሎስ «ከሕግ በታች ስላሉት ብሎ ሊል ስለ እነማን መናሩ ይመስላችኋል? ለ) እነዚህ ከሕግ በታች ያሉ ፍርዳቸውን እንዴት ይቀበላሉ? ሐ) ሐዋርያው ጳውሎስ «ሕጉ ላይኖራቸው» ብሎ ሊናገር ስለ እነማን መግለጹ ነው? መ) ታዲያ «ሕግ ሳይኖራቸው» የተባሉት እንዴት ፍርዳቸውን ይቀበላሉ? 

መሠረታዊ የሆነ የኃጢአት ምንነት ትርጉም የሚገኘው በ1ኛ ዮሐንስ 3፡4 ውስጥ ነው። በዚህ ጥቅስ ኃጢአት «ዓመፅ» መሆኑ ተገልጾአል። እንዲህም ማለት ኃጢአት የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ አለመቻል ነው። የእግዚአብሔር ሕግ ሊባል ደግሞ አሥርቱ ትእዛዛት ብቻ ማለትም አይደለም። የእግዚአብሔር ሕግ ማለት የእግዚአብሔር ክቡርና ቅዱስ ምግባር ማለት ነው። ከእነዚህ ደረጃዎች ጥቂቶቹ በአሥርቱ ትእዛዛትና በተቀሩት የብሉይ ኪዳን ሕግጋት ውስጥ ተገልጠዋል። ነገር ግን ይህ የብሉይ ኪዳን ሕግ የእግዚአብሔር ፍጹማዊ የሞራል ሕግ ብቸኛው መገለጫም አይደለም። በመሆኑም አዲስ ኪዳንም ስለ እግዚአብሔር ደረጃዎችና ስለ ሞራል ሕጉ በርካታ ምሳሌዎችን አካትቶአል። 

ሰዎች ሁሉ፥ ብሉይም ይሁን አዲስ ኪዳን ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም፥ ስለ እግዚአብሔር የሞራል ሕግ በልባቸውና በአእምሮአቸው የሚያውቁት ነገር አላቸው። ጳውሎስ በሮሜ ምዕራፍ 2 ላይ አይሁዶችም ሆኑ አሕዛብ ይህን የእግዚአብሔር የሞራል ሕግ እንደ መጠበቃቸው መጠን ፍርዳቸውን ይቀበላሉ ይላል። በሮሜ 2፡12 አይሁዶች «ከሕግ በታች ያሉ» ይላቸዋል። ምክንያቱም እግዚአብሔር የብሉይ ኪዳንን ሕግ ለአይሁዶች ሰጥቷቸዋልና ነው። አሕዛብን ደግሞ «ሕጉ ሳይኖራቸው» በማለት የብሉይ ኪዳን ሕግ እንደ ተሰጣቸው ያብራራል። ሆኖም ጳውሎስ አያይዞ ሁለቱም አይሁድም ሆኑ አሕዛብ የእግዚአብሔርን የሞራል ሕግ በጠበቁበት መጠን ፍርዳቸውን ይቀበላሉ ሲል ይናገራል። አይሁዶች የእግዚአብሔር የሞራል ሕግ መግለፃ ብሉይ ኪዳን ባይኖራቸውም፤ የእግዚአብሔር የሞራል ሕግ በልባቸው አለ። ያልተጻፈ ሕግ በልቦናቸውና በአእምሮአቸው ውስጥ አለ። የእግዚአብሔርን የሞራል ሕግ ሲጥሱ ሕሊናቸው ይወቅሳቸዋል፥ ደግሞም የእግዚአብሔርን የሞራል ሕግ በሚጠብቁበት ጊዜ ደስ እንዲሰኙ ያደርጋል። ስለዚህም አሕዛብ እንኳን ስለ እግዚአብሔር ሕግ መሠረታዊ የሆነ ግንዛቤ አላቸው። በመሆኑም እግዚአብሔር የሞራል ሕጉን በጠበቁበት መጠን ፍርዳቸውን ይሰጣቸዋል። 

አይሁድም ሆኑ ኦሕዛብ የእግዚአብሔርን የሞራል ሕግ ያውቃሉ። ስለዚህ አይሁድ ቢሆንም አሕዛብ የእግዚአብሔርን የሞራል ሕግ ባይጠብቁ ኃጢአት ይፈጽማሉ። 

ሌላው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሕግ ሳይፈጽሙ ስለ መቅረት የሚገልጸው ቃል «መተላለፍ» የተባለው ነው። ይህም ዘርዘር ሲደረግ፥ «ሕጉን መጣስ፥ ደረጃን ማለፍ፥ መግደፍ ማለት ይሆናል»። 

ጥያቄ፡- ሮሜ 4፡5 እንብቡ። ሕግ ከሌለ ሌላ ምን ይጎድላል? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 2፡23 እንብቡ። ምንም እንኳን አይሁድ የእግዚአብሔርን ሕግ ተቀብለናል ብለው ቢመኩም፥ ምን የፈጸሙት ተግባር አለ? 

ጥያቄ፡– ዕብራውያን 2፡2 አንብቡ። «በመላእክት የተነገረውን መልእክት» የጣሱት ምን ሆኑ? 

ሮሜ 4፡15 እንደሚናገረው ሰው ሕግን ሲጥስ ያኔ ሕግን ይተላለፋል። ሕግ ባይኖር ኖሮ ሕግን መተላለፍ ባልኖረም ነበር። ነገር ግን ሕግ ባለበት በዚያ ያንን ሕግ የጣሰ ሁሉ ሕግ ተላላፊ ይሆናል ማለት ነው። በሮሜ 2፡23 ውስጥ ጳውሎስ ሲናገር፥ እግዚአብሔር ይህን ሕግ ስለሰጣቸው አይሁዳውያን ይመኩ ነበር። ነገር ግን፥ ጳውሎስ ሕግ ቢሰጣቸውም እነርሱ ግን እንዳልጠበቁት በመንገር ያስጠነቅቃቸዋል። እናም ለሕጉ ስላልተገዙ በእግዚአብሔር ፊት ሕግ ተላላፊዎች ሆነዋል። ዕብራውያን 22 በመላእክት ስለተነገረ መልእክት ይናገራል። ይህ በመላእክት አማካኝነት ለአይሁድ የተሰጠውን የሙሴ ሕግ ያመለክታል (ዘዳግም 33፡2፤ የሐዋ. 7፡53፥ ገላትያ 3፡19)። ማንም ለዚህ ሕግ የማይታዘዝ ቢኖር ይቀጣ ነበር። 

እግዚአብሔር ቅዱስ ደረጃው ወይም መለኪያው የሆነውን የሞራል ሕግ ለሰው ልጆች ሰጥቶአል። ይህ ሕግም የእርሱን ባሕርይ ቅዱስና ጻድቅ አድርጎ ያንጸባርቃል። መጽሐፍ ቅዱስ ያላቸው የተጻፈ ሕግ አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ የሌላቸው ደግሞ ያልተጻፈው የእግዚአብሔር ሕግ በልባቸውና በአእምሮአቸው ውስጥ አለ። ሰዎች ይህንን ደረጃ በማይጠብቁበት ጊዜ ደረጃውን አለመጠበቃቸውን ማንም ሰው ባያውቅም እንኳ ኃጢአትን ይፈጽማሉ። በማንኛውም ጊዜ ሰዎች ለዚህ ሕግ ባይገዙ አለመታዘዛቸው ባይገለጥባቸውም እንኳ ኃጢአትን ይፈጽማሉ። በማንኛውም ጊዜ ሰዎች እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሳይፈጽሙ ቢቀሩ፥ ምንም እንኳን ሌሎች ሰዎች ይህን መልካም ነገር እንዲፈጽሙ ባይጠብቋቸውም ኃጢአት ሠርተዋል። 

ጥያቄ፡- እናንተ የምታውቋቸው ሰዎች ስለ ኃጢአት ሳላቸው አስተሳሰብና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኃጢአት ባለው አስተሳሰብ መካከል ምን ልዩነት አለ? 

ብዙ ሰዎች ድርጊታቸው በአካባቢአቸው ያሉትን ሰዎች ሲያስቸግር ወይም በኃጢአታቸው ሲያዙ ብቻ ኃጢአት የሠሩ ይመስላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን የሚለው ምንም እንኳን ድርጊታችን ሌሎች ሰዎችን ባያስቸግርም ወይም በኃጢአታችን ባንያዝም የእግዚአብሔርን ፍጹም መለኪያ እስከ ሳትን ድረስ ኃጢአት እየሠራን መሆኑን ነው። ለምሳሌ፥ ውሸት ተናግረን ስናበቃ በውሸታችን ባንጋለጥም ድርጊታችን ኃጢአት ነው። እንዲሁም የራሳችን ያልሆነውን ነገር ብንወስድ ይህን ነገር መውሰዳችንን ሰዎች ባያውቁብንም በድርጊታችን ኃጢአት ሠርተናል። ብዙ ሰዎች ግን በሌሎች ሰዎች ላይ መጥፎ ተግባር ሲፈጽሙና ይህ ተግባራቸው በሌሎች ሰዎች ሲታወቅባቸው ብቻ ኃጢአት የሠሩ ይመስላቸዋል። ምንም እንኳ ማንም ሰው እግዚአብሔር ያዘዘንን መልካም ነገር አለማድረጋችንን ባያውቅም፥ መጽሐፍ ቅዱስ ግን የሚነግረን ያንን ባለማድረጋችን ኃጢአትን መፈጸማችንን ነው። ለምሳሌ ያህል፥ ለሰዎች ቸርነት ማድረግ ሲኖርብን ነገር ግን ሳናደርገው ብንቀር ኃጢአትን እንሠራለን። እንዲሁም ሰዎችን መርዳት እንዳለብን እያወቅን ሳንረዳ ብንቀር ያው ኃጢአት ማድረጋችን ነው። ስለሆነም ኃጢአት ማለት ዒላማን መሳት እንጂ በምንም ዓይነት እስከ እግዚአብሔር ፍጹም ደረጃ ድረስ መድረስ አይደለም። 

3. ኃጢአት ማለት ተግባራችንን ብቻ ሳይሆን ዝንባሌአችንንና ባሕርያችንን ከእግዚአብሔር ደረጃ ጋር አለማመሳሰል ማለት ነው። 

አንዳንድ ሰዎች የእግዚአብሔርን የሞራል ሕግ በድርጊት አለመጠበቃቸው ብቻ ኃጢአት እንደሚሆንባቸው አድርገው ያስባሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚያስረዳው ማንም ሰው የእግዚአብሔርን የሞራል ሕግ በስሜቱ፥ በአስተሳሰቡና በዝንባሌው መጠበቅ ካልቻለ ኃጢአትን ይሠራል። 

ጥያቄ፡- ማቴዎስ 5፡21-22 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ ኃጢአት ነው የሚለው ምንን ነው? ለ) ማቴዎስ 5፡27-28 አንብቡ። ኢየሱስ ኃጢአት ነው የሚለው ምንን ነው? 

ጥያቄ፡- ገላትያ 5፡19-21 ላይ ከተዘረዘሩት የኃጢአት ዓይነቶች ውስጥ የተግባር ሳይሆኑ የዝንባሌ ኃጢአቶች የሆኑትን ዘርዝሩ። 

ኃጢአት የእግዚአብሔርን ሕግ በተግባራችን መተላለፍ ብቻ አይደለም። ነገር ግን በስሜታችንና በዝንባሌአችንም ጭምር ይህን ሕግ መተላለፋችን ነው። በኢየሱስ ዘመን የነበሩ አይሁዶች ኃጢአትን ከውጪአዊው ሁኔታቸው ብቻ መራቅ በቂ ይመስላቸው ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ በተራራ ስብከቱ ላይ በልባቸውና በአሳባቸው ማለትም በዝንባሌአቸው የእግዚአብሔርን ሕግ ከጣሱ ኃጢአት እንደሚሠሩ አስተምሯቸዋል። በማቴዎስ 5፡27-28 ባለው ክፍል ውጫዊው የዝሙት ተግባር ብቻ ላይሆን ውስጣዊው የቁጣ ስሜትም ራሱ ኃጢአት መሆኑን ኢየሱስ አስተምሮአቸው ነበር። በገላትያ 5፡19-21፥ ጳውሎስ ብዙ ኃጢአቶችን ይዘረዝራል። ከእነዚህም ጥቂቶቹ ብቻ ከውጪአዊ ሁኔታ ጋር የተገናኙ ሲሆኑ ብዙዎቹ ግን እንደ ጥላቻ፥ ምቀኝነት፥ ራስ ወዳድነት፥ ቅናት ያሉ በመሠረቱ የልብ ኃጢአቶች ናቸው። እነዚህ ኃጢአቶች ሁልጊዜ በሌሎች ሰዎች ሊታዩ አይችሉም። ሆኖም ግን የእግዚአብሔርን ቅዱስ ትእዛዛት መተላለፍ ናቸው። ስለሆነም ኃጢአት በተግባራችን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መተላለፍ ብቻ አይደለም። ዳሩ ግን በዝንባሌያችን፥ ሰለሜታችንና በአስተያየታችንም የእግዚአብሔርን ሕግ መተላለፍ ነው። 

ከዚህ በተለየ ጠለቅ ባለ መንገድ የእግዚአብሔርን ሕግ የምንጥስበት ሁኔታም አለ። ይህም የእግዚአብሔርን ሕግ በድርጊታችንና በአመለካከታችን መተላለፍ ብቻ አይደለም። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ሕግ በውስጣዊ ባሕርያችንና ዝንባሌያችንም መተላለፍ ነው። 

ጥያቄ፡– ኤፌሶን 2፡3 አንብቡ። ከምን የተነሣ ነበር እኛ የቁጣ ልጆች የነበርነው? 

በኤፌሶን 2፡1-3 ውስጥ ጳውሎስ ሰዎች በክርስቶስ አምነው እንደ አዳኛቸው አድርገው እርሱን በመቀበል ጸጋውን ከማግኘታቸው በፊት እንዴት እንደ ነበሩ ይገልጻል። ከዚሁ ጋር በማያያዝ በዚሁ ማብራሪያው ላይ ሁላችንም ከፍጥረታችን ጀምሮ የቁጣ ልጆች እንደ ነበርን ይናገራል። ጳውሎስ ሲናገር አመለካከታችንና ተግባራችን ብቻ ሳይሆኑ ፍጥረታችንም በኃጢአት የተሞላ መሆኑን ያስረዳል። በሚመጣው ሳምንት በሚኖረን በመጀመሪያው ቀን ትምህርታችን ላይ በኃጢአት ስለተሞላው ተፈጥሮአችን ጉዳይ ሰፋ አድርገን እንወያያለን። እዚህ ላይ ግን ኃጢአት ማለት የእግዚአብሔርን ሕግ በተግባርና በአመለካከት መተላለፍ ብቻ አለመሆኑን መገንዘብ ጠቃሚ ነው። ኃጢአት የእግዚአብሔርን ሕግ ከተፈጥሮአችንና ከስሜታችን ጋር እንዲስማማ ለማድረግ አለመቻላችን ኃጢአት ነው። ውስጣዊው ተፈጥሮአችንና ዝንባሌአችን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ሲቃረን ያ ኃጢአት ይሆንብናል። 

ኃጢአት ምንድን ነው? ኃጢአት የእግዚአብሔርን ሕግ በተግባር፥ በአመለካከት ወይም በተፈጥሮአዊ ባሕርይ መጣስ ወይም መተላለፍ ነው። 

4. ኃጢአት ማንኛውንም ነገር በእግዚአብሔር ቦታ መተካት ነው። 

ኃጢአት ምናልባት የእግዚአብሔር የሞራል ሕግ መስበር ከመሆኑ ባሻገር ጠለቅ አድርገን ስለ ምንነቱ ልንገነዘበው የሚገባን መንገድ ነው። የእግዚአብሔር የሞራል ሕግ እንደ እውነቱ ከሆነ የማንነቱ ተጨማሪ መግለጫ ነው። የእግዚአብሔር የሞራል ሕግ የቅዱስ ባሕርይው ተጨማሪ መገለጫ ነው። ኃጢአት እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ አምላክ እንዲሆን አለመፍቀድ ነው። ኃጢአት በሕይወታችን እጅግ ከፍተኛ የምንለውን ማለትም ለእግዚአብሔር የሚገባውን ስፍራ ተክቶ እንዲይዝ ማድረግ ነው። 

ጥያቄ፡– ዘፀአት 20፡3 አንብቡ። የመጀመሪያው ትእዛዝ ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡– ማርቆስ 12፡30 አንብቡ። ኢየሱስ ከሁሉ የበለጠ ትእዛዝ ነው ብሉ ያለው ምንድን ነው? 

ከአሥርቱ ትእዛዛት መካከል የመጀመሪያው በእውነተኛው አምላክ ፊት ሌላ አምላክ እንዳይኖረን ነው። የዚህ ትእዛዝ ጽንሰ-ሃሳብ ለጣዖታት እንዳንሰግድ ወይም ለአጋንንትና ለመናፍስት መሥዋዕት እንዳናቀርብ ብቻ አይደለም። የዚህ ትእዛዝ የማስጠንቀቂያ አሳብ በሕይወታችን ውስጥ ከእግዚአብሔር በስተቀር ማንንም ከእርሱ አስበልጠን ቦታ እንዳንሰጠው ነው። ይህንንም በተመለከተ ኢየሱስ እውነተኛይቱ ትእዛዝ የትኛይቱ እንደሆነች በገለጸ ጊዜ እንዲህ ብሏል፥ «እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ በፍጹም አሳብህ፥ በፍጹም ኃይልህ ውደድ።» እንግዲህ ፍቅራችን ከእግዚአብሔር ይልቅ ለሌላ ሰው ወይም ነገር የሚበልጥብን ከሆነ ኃጢአት ነው። 

ጥያቄ፡- በሕይወታችሁ ውስጥ ለእግዚአብሔር ይገባው የነበረውን ክብር ለሌላ ሰው ወይም ነገር በመስጠት ከእግዚአብሔር አስበልጣችሁ ለመውደድ ተፈትናችሁ ከሆነ በግልጽና በታማኝነት ቢያንስ ሦስት ምሳሌዎችን ጻፉ። ስለፈጸማችሁት ስሕተትም በእግዚአብሔር ፊት ተናዘዙ። አንዳንድ የክርስትና እምነት ተከታይ ነን የሚሉ ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት ሲሉ ሥዕልንና ቅርጽን በመሳለም፥ ለመናፍስት በመሠዋት ወይም ሌሎች ስጦታዎችን በማቅረብ ሐሰተኞች አማልክትን ለማምለክ ይፈተናሉ። ሆኖም ሐሰተኛ ለሆኑ አማልክት የሚደረገው ስግደት ይህ ብቻ አይደለም። ክርስቲያኖች አብዛኛውን ጊዜ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሌሎች ነገሮችን ያስቀድማሉ፤ ማለትም ትምህርት፥ ሥራ ወይም ሙያ፥ ባል ወይም ሚስት ማግኘት፥ ልጆችን መውለድ፥ በኅብረተሰቡ መካከል ታዋቂና ዝነኛ መሆን፥ ጊዜን በመዝናናት ማሳለፍ፥ እንዲሁም እንደ ቤትና ንብረት ያሉትን ማግኘት የመሳሰሉት ናቸው። እነዚህን የመሳሰሉ ነገሮች በሕይወታችን ውስጥ በጣም ከፍተኛውን ስፍራ በሚይዙበት በማንኛውም ጊዜ ኃጢአትን እናደርጋለን። ስለዚህ ከእግዚአብሔር አስበልጠን አንድን ነገር በምንወድበት ጊዜ ኃጢአትን እንፈጽማለን። በየቀኑ አንድን ነገር ወይም ሰው ከእግዚአብሔር ስለምናስቀድም ሁላችንም ብንሆን በየቀኑ በሕይወታችን ውስጥ ብዙ ጊዜ ኃጢአትን እንሠራለን። የእግዚአብሔርን ሕግ በሥራችን፥ በአሳባችንና በስሜታችን በተፈጥሮአዊ ባሕርያችን የምንጥስ ከመሆናችንም በላይ ሌሎች ነገሮችን ከእግዚአብሔር በላይ አድርገን ስለምንመለከት ከዚህ ኃጢአታችን የሚቤዠንን አዳኝ እንሻለን።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች (FAQs)

የኃጢአት ውጤት፡- ሞት  ክርስቶስ እንደ መካከለኛና እንደ አማላጅ 

የጌታ ጸጋ ከእርስዎ ጋር ይሁን፤ ሀሳብዎን ለመስማት ዝግጁ ነን።

Discover more from የሕይወት እንጀራ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading