የሕይወት እንጀራ

የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሰው ድነት (ደኅንነት) ውስጥ፤ ክፍል 3

የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ

መግቢያ

ስለ መንፈስ ቅዱስ ለምን እናጠናለን?

ሥነ መለኮት ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የምንረዳበት ምንጭ

መንፈስ ቅዱስን ማወቅ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ስፍራ

የመንፈስ ቅዱስ ዋና ኃላፊነቶች ምንና ምን ናቸው?

የመንፈስ ቅዱስ ስሞች

የመንፈስ ቅዱስ ተምሳሌቶች

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?

መንፈስ ቅዱስ፤ ሦስተኛው የሥላሴ አካል

መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ አምላክ መሆኑን ያሳየናልን?

መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን

የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይመሩ ዘንድ መሪዎችን ብቁ በማድረግ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት

መንፈስ ቅዱስ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንዲጽፉ በመምራት የሰጠው አገልግሎት

የብሉይ ኪዳን ነቢያት መሢሑ የሚመጣበትን ወቅትና የመንፈስ ቅዱስ አገልግሉት የሚለወጥበትን ጊዜ እስቀድመው አመልክተው ነበር

የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በወንጌላት

መንፈስ ቅዱስ በጌታ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ውስጥ

ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሰጠው ትምህርት፤ ክፍል 1

ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ያስተማረው ትምህርት፤ ክፍል 2

ክርስቲያኖች እንደ መንፈስ ቅዱስ ባሉ መሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮዎች ላይ ባላቸው አመለካከት ልዩነት የሚያሳዩት ለምንድን ነው?

መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ የተለያዩ መረዳቶች የሚታዩት ለምንድን ነው?

በመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችና በአምልኮ ልምምዶች ውስጥ ያሉ ልዩነቶችን እንዴት መያዝ አለብን?

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 1-2 )

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 3-8 )

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 9-28)

የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሰው ድነት (ደኅንነት) ውስጥ፤ ክፍል 1

የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሰው ድነት (ደኅንነት) ውስጥ፤ ክፍል 2

የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሰው ድነት (ደኅንነት) ውስጥ፤ ክፍል 3

የጴንጤቆስጤ ሥነ መለኮት ታሪክ

የጰንጠቆስጤና የአንዳንድ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ዋና ትምህርቶች ምን ምን ናቸው?

ከካሪዝማቲክ ትምህርት ለቤተ ክርስቲያን የተረፉ መልካም ውጤቶች

በካሪዝማቲክ የሥነ መለኮት ትምህርት የሚገኙ ሚዛናዊ ያልሆኑ ነገሮች

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት (ክፍል አንድ)

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት (ክፍል ሁለት)

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት (ክፍል ሦስት)

በክርስቲያኖች መካከል ከፍተኛ ልዩነት የሚፈጥሩ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ክፍሎች (ክፍል 1)

በክርስቲያኖች መካከል ከፍተኛ ልዩነት የሚፈጥሩ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ክፍሎች (ክፍል 2)

በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ልሳን በመናገር መካከል ያሉ ግንኙነቶች

የመንፈስ ቅዱስ አማኞችን ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመምራት አገልግሎት

መንፈስ ቅዱስ እንድናመልክ ይረዳናል

መንፈስ ቅዱስ የክርስቲያኖች ሕይወት ኢየሱስን እንዲመስል የሚሰጠው አገልግሎት

ሰይጣንን ድል የማድረግ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት

ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች መግቢያ

መንፈሳዊ ስጦታ ምንድን ነው?

መንፈሳዊ ስጦታ (ሮሜ 12፡1-8)

መንፈሳዊ ስጦታ (ኤፌሶን 4፡1-16 )

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ጴጥሮስ 4፡7-11 )

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡1-3)

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡4-11 )

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡12-31 )

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 13)

መንፈሳዊ ስጦታ (1ኛ ቆሮንቶስ 14፡1-19)

መንፈሳዊ ስጦታዎችና የማያምኑ ሰዎች (1ኛ ቆሮንቶስ 14፡20-40)

በልሳናት ስለመናገር ተጨማሪ ጉዳዮች (ክፍል 1)

በልሳናት ስለመናገር ተጨማሪ ጉዳዮች (ክፍል 2) የተለያዩ ዓይነት ልሳናት አሉን?

በቤተ ክርስቱያን ውስጥ ስለሚመጣው ትንቢት ተጨማሪ አሳቦች

ትንቢት ምንድን ነው? ነቢይስ?

የትንቢት ስጦታ ምንድን ነው?

የእውነተኛና ሐሰተኛ ነቢያት ንጽጽር

የትንቢት ስጦታን ለመጠቀም መመሪያዎቹ ምን ምን ናቸው?

የመፈወስና ተአምራትን የማድረግ ስጦታዎች

የብሉይ ኪዳን ተአምራትና አዲሱን ዘመን በተስፋ መመልከት

ተአምራትና ፈውሶች በአዲስ ኪዳን

እግዚአብሔር ፈውስን የሚሰጥባቸው የተለያዩ አሠራሮች

ስለ ተአምራትና ፈውሶች የሚሰጡ የተሳሳቱ አሳቦች

የመንፈሳዊ ስጦታዎች ትምህርት ማጠቃለያ

በመንፈስ ቅዱስ መሞላት

የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ምንድን ነው?

ከኤፌ 5፡18-20 በመንፈስ ቅዱስ ስላ መሞላት ምን ልንመለከት እንችላለን?

በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት ማረጋገጫዎች

በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት የሚቀርቡ ቅድመ ሁኔታዎች

በመንፈስ ቅዱስ መሞላትና መንፈሳዊ ብስለት

የመጀመሪያው የመንፈስ ቅዱስ ዋና ሥራ፡- ዘላለማዊው አምላክ በውስጣችን መኖሩ

የመንፈስ ቅዱስ ሁለተኛ ዋና ተግባሩ፡- ወደ ኢየሱስ ማመልከትና እርሱን እንድንመስል ማድረግ።

የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ክለሳ

በኤፌ. 1፡3–14 ጳውሎስ እግዚአብሔር በሰማያዊ ስፍራ ባለ መንፈሳዊ በረከት ሁሉ ክርስቲያኖችን ስለባረከን ያመሰግናል። ባለፉት ሁለት ቀናት ትምህርት በዳንንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በርካታ በረከቶችን ሕይወትን የሚለውጡ በረከተችን፥ ተአምራዊ በረከቶችን እንደሰጠን እይተናል። ስለሆነም እግዚአብሔር እንድናመሰግነው መፈለጉ የሚያስገርም አይሆንም። ወደ ክርስቶስ በእምነት ስተመለስንበት ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ስለሰጠን በረከቶች በሙሉ አብረን እግዚአብሔርን ከማመስገን ሌላ ምንም ማለት አንችልም። 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። 2ኛ ቆሮ. 1፡22፤ 5፡5፤ ኤፌ. 1፡13፤ 4፡30፤ ዮሐ 1፡12፤ ሮሜ 8፡13-17፤ ገላ. 4፡5-7፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡13። ሀ) አንድ ሰው ገና በሚድንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያን በሆነው ሰው ውስጥ ስለሚሠራቸው ሥራዎች እነዚህ ጥቅሶች የሚሰጡትን እውነቶች ዘርዝር። ለህ እያንዳንዱ በረከት ስለያዛቸው ነገሮች አጭር መግለጫ ጻፍ። 

1. የመንፈስ ቅዱስ ማኅተምና መያዣ (2ኛ ቆሮ. 1፡22፤ 5፡5፤ ኤፌ. 1፡13፤ 4፡30)። በጥንት ጊዜና ዛሬም በኢትዮጵያ ማኅተም በጣም ጠቃሚ ምልክት ነው። የባለቤትነት ምልክት ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፥ አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ ማኅተም ሊያደርግ የዚያ ነገር ባለቤት መሆኑን ያሳያል። (መጻሕፍት ላይ ስማችንን ስንጽፍ የእኛ መሆናቸውን እንደምናመለክተው ዓይነት ማለት ነው።) ደግሞም አንድ ድርጅት ለመንግሥት ወይም ለሌላ ድርጅት በሚልከው ማንኛውም ኦፊሴላዊ ደብዳቤ ላይ እንደሚጠቀምበት ሁሉ፥ ማኅተም የሕጋዊ ሰነዶችን ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ ነው። ደብዳቤው ሳይከፈት እንዲደርስ በፓስታው እፍ ማኅተም እንደምናሳርፍ ሁሉ፥ አንድ ሰነድ ያልተለወጠና ሕጋዊ ስለመሆኑ ማኅተም በምልክትነት ያገለግላል። መያዣ ደግሞ የመጨረሻው ክፍያ በሚካሄድበት ጊዜ ሙሉ ባለቤትነት ላይ እንደሚደረስ ዋስትና የሚሰጥ ነገር ነው። 

በአዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ማኅተም እንደሆነ ወይም በአማኙ ላይ ማኅተም የሚያደርግ እንደሆነ ተነግሮናል። ማኅተም የሚደረግበት አማኙ ነው። ማኅተም አድራጊው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በመጠቀም በሆነ መንገድ እያንዳንዱን ልጁን ያትምበታል። በእግዚአብሔር ማኅተም የሚደረግበት ማን ነው? በአዲስ ኪዳን ውስጥ ክርስቲያኖች ማኅተም እንደተደረገባቸው በተጻፈባቸው ቦታዎች ሁሉ ማኅተሙ የተደረገባቸው ክርስቲያኖች በሙሉ ናቸው። አንዳንድ ክርስቲያኖች ብቻ ማኅተም እንደተደረገባቸው የሚያመለክት ነገር የለም። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እንኳ ያ ሁሉ ችግር በቤተ ክርስቲያናቸው እያላ በእግዚአብሔር እንደታተሙ ተጽፎአል። በተጨማሪ ክርስቲያን ይታተምበት ዘንድ እንዲያደርገው የተጠየቀው አንዳችም ትእዛዝ የለም። ለምሣሌ፡- ይታተም ዘንድ መጸለይ የለበትም። ስለዚህ አንድ ሰው በኢየሱስ በሚያምንበት ወቅት ወዲያውኑ መንፈስ ቅዱስ እንደሚያትመው ማሰብ እንችላለን። መንፈስ ቅዱስ በተጨማሪ አሁን በከፊል ሐሴት ለምናደርግባቸውና ወደ መንግሥተ ሰማያት ስንደርስ በሙላት የእኛ ስለሚሆኑት በረከቶች የሚያረጋግጥልን መያዣችን በመሆንም ይሠራል። 

አዲስ ኪዳን በመንፈስ ቅዱላ ታትመናል፤ እርሱ ዋስትናችን ነው፤ ሊል ምን ማለቱ ነው? በዚህ የመንፈስ ቅዱስ ተግባር ውስጥ ሦስት ድርጊቶች የተጠቃለሉ ይመስላል። 

በመጀመሪያ፥ የባለቤትነት አሳብ አለበት። ማኅተሙ የእግዚአብሔር መሆናችን ማረጋገጥ ነው። 

በሁለተኛ ደረጃ ፥ የሥልጣን አሳብ አለው። እንድ ማኅተም ያለው ደብዳቤ ማኅተም ያደረገበትን አካል ሥልጣን የያዘ እንደሆነ፥ ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ማኅተም በእኛ ላይ መኖሩ የንጉሥ ልጆች ከመሆናችን የተነሣ የእግዚአብሔር ሥልጣን እንዳለን የሚያሳይ ምልክት ነው። 

በሦስተኛ ደረጃ ፥ የእግዚአብሔርን ተስፋዎች በሙሉ እንደምንቀበል ማኅተሙ ዋስትና ነው። የእግዚአብሔር ንብረቶች እንደምንሆን ዋስትና የሚሰጥ ነው። በእግዚአብሔር ተስፋ የተገባልንን በረከቶች በሙሉ በተለይም ደግሞ የዘላለም ድነት (ደኅንነት) ተስፋ እንደምንቀበል የሚያረጋግጥ ነው። ብዙ ክርስቲያኖች እንደሚያምኑት ወደ መንግሥተ ሰማይ እስክንደርስ እግዚአብሔር እንደሚጠብቀን ከእውነተኛ እምነት ተሳስተን እንዳንወድቅ እንደሚከልለን የሚያረጋግጥ ዋስትና ነው። እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስን ማኅተም አንድ ጊዜ ካደረገብን በኋላ ወድቀን ደኅንነታችንን እንድናጣና ከዘላላም ሽልማታችንም እንድንቀር የሚያደርገን እንዳችም ነገር የለም። 

ጥያቄ፡– መንፈስ ቅዱስ የሚያትመን የመሆኑ እውነት ዛሬ እንዴት ሊያበረታታን ይገባል? 

2. መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ የልጅነት መብት ሰጥቶናል (ዮሐ 1፡12፤ ሮሜ 8፡13-17፤ ገላ. 4፡5-7)። ከአዲስ ኪዳን አስደናቂ እውነቶች አንዱ በዳንንበት ወቅት እግዚአብሔር ጠላቶቹ የነበርነውን እኛን ልጆቹ ማድረጉ ነው። ይህ ሂደት ማደጎነት ወይም ልጅነትን መቀናጀት ይባላል። በጥንት ጊዜ ሮማውያንና ግሪኮች ልጅ ያልወለዱ ወላጆች የሌላን ሰው ልጅ ወይም የባሪያን ልጅ እንኳ ሰመውሰድ በሕግ የራሳቸው ልጅ ያደርጉ ነበር። ወደ ቤተሰቡ የተጨመረው የማደጎ ልጅ ወዲያውኑ በሥጋ እንደተወለደ እንደማንኛውም ልጅ ሕጋዊ መብቶችን በሙሉ ያገኛል። 

ምንም ልዩነት አይደረግበትም። እነዚህ ወላጆች በሥጋ የወለዱት ልጅ ቢኖራቸው የመውረስ ሙሉ መብት እንዳለው ሁሉ ይህም ልጅ ይኖረዋል። 

በዳንንበት ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ እኛን ወስዶ በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ያስቀምጠናል። የእግዚአብሔር ልጅ በመሆን የሚገኝ መብት፥ ደረጃ ግዴታዎች በሙሉ ይሰጡናል። ይህ የልጅነት ስፍራችን ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነቶች ሙሉ በሙሉ ይለውጣል። ክዚህ ቀደም በፍርሃት ከእግዚአብሔር ርቀን እንዳልነበርን አሁን ግን በሙሉ ልብ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለን። መንፈስ ቅዱስ ያለማቋረጥ የእግዚአብሔር ተወዳጅ ልጆች መሆናችንን ያሳስበናል። ትንሽ ልጅ ምድራዊ አባቱን «አባዩ» ብሎ እንደሚጠራ ከእግዚአብሔር ጋር እጅግ በቀረበ መንገድ እንድንነጋገር ያስችለናል። በልጅነታችን በእግዚአብሔር ተስፋ የተገቡልንን ዘላለማዊ በረከቶች በሙሉ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንደምንወርስ ቃል ገብቶልናል። ነገር ግን ይህ መብት ከግዴታዎች ጋር አብሮ የሚመጣ ነው። እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መንገድ በመኖር የቤተሰቡን ስም እንዳናጎድፍ መጠንቀቅ አለብን። ልጅ ወላጆቹን እንደሚታዘዝ ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ የመታዘዝ ግዴታ አለብን። 

ጥያቄ፡– እውነተኛ አማኝ ከሆንክ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ። ሀ) እግዚአብሔርን እንደ አባት ብትቆጥርና እንደ ፈጣሪ ብቻ ብትቆጥር ከእርሱ ጋር የሚኖርህ ግንኙነት የሚለወጠው በምን በምን መንገድ እንደሆነ በዝርዝር ግለጽ። ለ) እግዚአብሔር አባትህን ምን ያህል እንደምትወደው ለመግለጽ ጊዜ ውሰድ። 

3. የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት (1ኛ ቆሮ. 12፡13)። ይህን የጥናት መጽሐፍ በጻፈው ሰው አመለካከት መንፈስ ቅዱስ አንድን ሰው የማጥመቅ ሥራው የሚፈጸመው ሰውዬው በዳነ ጊዜ ከመቅጽበት ነው። አዲሱን አማኝ የክርስቶስ አካል በሆነችው ጽንፈ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የመጨመር ተግባር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው። ከየትኛውም ነገድ ይምጣ ምንም ዓይነት ፆታ ይኑረው ምንም ዓይነት ማኅበረሰባዊ አቋም ይኑረው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የዳነውን ሰው ወስዶ በክርስቶስ አካል ውስጥ እኩል ደረጃ ያለው አባል ያደርገዋል። በክርስቲያኖች መካከል ውዝግብ ከሚያስነሡ ጉዳዮች እንዱ ይህ በመሆኑ ወደፊት ባሉ ትምህርቶች በጥልቀት እንመለከተዋለን። 

ጥያቄ፡- ከ 1ኛ እስከ 4ኛ ቀን ያሉ ትምህርቶችን ከልስ። ሠንጠረዥ አብጅ። በመጀመሪያው ክፍል ውስጥ አንድ ሰው ክርስቲያን በሚሆንበት ወቅት መንፈስ ቅዱስ የሚፈጽማቸውን ተግባራት በሙሉ ዘርዝር። በሁለተኛው ክፍል ይህ በረከት ምን ማለት እንደሆነ አጭር ገለጻ ጻፍ። በሦስተኛው ክፍል ውስጥ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ልጅነትህ ይህ በረከት ለምን ለአንተ ጠቃሚ እንደሆነ ግላጽ። 

አንድ ሰው በሚድንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የሚፈጽማቸውን አገልግሎቶች የዘረዘርን ቢሆንም እንኳ ከእነዚህ አብዛኛዎቹ አገልግሎቶች ተወራራሽ መሆናቸውን ማስታወስ ይገባናል። እንዲያውም አንዳንድ የሥነ መለኮት ሊቃውንት እነዚህ ሁሉ የዘረዘርናቸው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች በጥቅሉ የሚያመለክቱት አንድን ሁኔታ ነው ብለው ያምናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው አንድ ሰው በሚድንበት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ ልዩ ስጦታ ይቀበላል ብለው ያምናሉ። ይህ ስጦታ የመንፈስ ቅዱስ በሰው ልብ ውስጥ መኖር ወይም ማደር ነው። የዚህ የመንፈስ ቅዱስ ማደር ወይም መኖር በተለያዩ መንገዶች ይገለጻል። እነዚህም «የመንፈስ ቅዱስ ተለፋ»፥ «የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ»፥ «የመንፈስ ቅዱስ ዘር»፥ «የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት»፥ በመንፈስ ቅዱላ ልጅ የመሆን ሂደት»፥ ወዘተ… ናቸው። እነዚህ ሁሉ ነገሮች ግን አንድ ናቸው። ስለዚህ በእነዚህ አገልግሎቶች መካከል ከፍተኛ ልዩነት እንዳንፈጥር መጠንቀቅ አለብን። ከሁሉ የሚሻለው አመለካከት ይህ እያንዳንዱ አገልግሎት የአንዱ የመንፈስ ቅዱስ ህልውና የተለያየ ገጽታ መሆኑን መቀበል ነው። 

ከመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ትምህርት በስተቀር ክርስቲያኖች ሁሉ እነዚህ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች በአዲሱ አማኝ ሕይወት ውስጥ የሚፈጸሙ እንደሆኑ ይስማማሉ። የሚያሳዝነው ነገር ግን ትኩረት የምናደርገው በአንድ ወይም በሁለት አገልግሎቶች ላይ ብቻ መሆኑ ነው። ሰመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ወይም በተወሰኑ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ላይ ማተኮር በሥነ መለኮት ትምህርታችን ሚዛናዊነትን ያሳጣናል። መንፈስ ቅዱስ ስለሚያከናውናቸው ስጦታዎች እንደ በልሳን መናገር፥ ፈውስ፥ ተአምራትና መገለጥ ያላችሁ እምነት ምንም ይሁን፥ ነገር ግን ከተእምራት ሁሉ የበላይ በሆነው ማለትም የአዲስ ልደት ተአምር ላይ እንድታተኩሩ አበረታታችኋለሁ። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ጠላት የሆነውን ሰው ወስዶ ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ሊለውጠው ክማየት የላቀ አስደሳችና ተአምራዊ ድርጊት የላም። ሁላችንም የበለጠውን ትኩረታችንን በዚህ ተአምር ላይ ብናደርግ በሌሎች የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች ላይ በክርስቲያኖች መካከል የሚነሡ አለመግባባቶች የደበዘዙ ይሆናሉ። በአብያተ ክርስቲያናት መካከልና በአማኞች መካከል ያለው አንድነት እንደገና ይታደሳል።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ

የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሰው ድነት (ደኅንነት) ውስጥ፤ ክፍል 2 የጴንጤቆስጤ ሥነ መለኮት ታሪክ

የጌታ ጸጋ ከእርስዎ ጋር ይሁን፤ ሀሳብዎን ለመስማት ዝግጁ ነን።

Discover more from የሕይወት እንጀራ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading