ትናንትና ስለ ኢየሱስ ተሠገዎ የሚያስተምር በጣም ጠቃሚ ከሆኑ ጥቅሶች መካከል አንዱ የሆነውን ዮሐንስ ምዕራፍ አንድን አብረን አጥንተናል። ዛሬ ደግሞ ሌላ በጣም ጠቃሚ የሆነና ስለ ተሠገዎ ምሥጢር የሚያስረዳውን ከፊልጵስዩስ 2፡5-ህ ያለውን ክፍል እንማራለን።
ጥያቄ፡- ፊልጵስዩስ 25 አንብቡ። ክርስቲያኖች ሊኖራቸው ይገባል?
ፊልጵስዩስ 2፡6-11 የቀድሞ ክርስቲያኖች ስለ ኢየሱስ የዘመሩትን መዝሙር ይመስላል? ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ አመራርና ግፊት ዘላለማዊው የእግዚአብሔር ልጅ ሰው በሆነ ጊዜ ምን እንደ ተደረገ ሊያመለክተን ይህን መዝሙር ጽፎታል። ነገር ግን ሐዋርያው ይህን የጻፈበት ዋነኛው ምክንያት ክርስቲያኖች ልክ ኢየሱስ የነበረውን ዓይነት የትሕትናና ራስን ዝቅ የማድረግ ልብ እንዲኖራቸው ለማበረታታት ነው። ይህ መዝሙር ኢየሱስ አምላክ ሆኖ ሳለ እንዴት በፈቃዱ ሰው ሆኖ ለእኛ ሲል ሊሞት ወደዚህ ዓለም መምጣቱን ይገልጽልናል። ኢየሱስ ለትሕትና እጅግ በጣም ጥሩ ምሳሌያችን ነው። ላለዚህ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ትሕትና የሕይወታቸው ምሳሌ አድርገው ሊወስዱት ይገባል።
1. ኢየሱስ ወደ ዓለም ከመምጣቱ በፊት ምን ይመስል ነበር?
ጥያቄ፡- ፊልጵስዩስ 2፡6 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት ምን ይመስል ነበር? ለ) ኢየሱስ ወደዚህ ምድር ሰው ሆኖ ከመምጣቱ በፊት፥ ስለ መለኮታዊ ተፈጥሮ የነበረው አመለካከት ምን ነበር?
ስለ ኢየሱስ ትሕትና ለመገንዘብ በመጀመሪያ ወደዚህ ምድር ከመምጣቱ በፊት የነበረውን የክብር ስፍራ ልናስተውል ይገባል። ጳውሎስ ኢየሱስ ከመወለዱ በፊትም እንደነበረ የምናውቅ እድርጎ ይገምታል። ታዲያ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት ምን ይመስል ነበር። (የቀድሞው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም «በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ» ይላል። በእንግሊዝኛው «ቅርጽ» የሚለውን ቃል በግሪኩ ትርጉም ሲታይ ውጪአዊውን መልክ ብቻ የሚመለከት አይደለም። በአንጻሩ ቃሉ ውጪአዊውን መልክና ውስጣዊውንም ተፈጥሮ ሁለቱንም ይመለከታል። ቃሉ በጥቅም ላይ ሲውል፥ የውጫውን መልክና ከበስተኋላው ያለውንም ባሕርይ ይገልጻል። እንዲህ ማለት ታዲያ ኢየሱስ ውጫዊ የእግዚአብሔር መልክና ውስጣዊ የእግዚአብሔር ባሕርይም አለው ማለት ነው፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው እናም የእግዚአብሔር ክብር፥ ሞገስና ኃይል አለው። አዲሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፥ «የመለኮት ባሕርይ አለው» ሲል ይህንኑ ያመለክታል። ለምሳሌ፥ ከልጆቼ ጋር በመንገድ ላይ ሳለሁ ብታገኙኝና ልጆቼን ስንከባከብ ብታዩ፥ «እስጢፋኖስ፥ ዛሬ በእርግጥ እባት ትመስላለህ?» ትሉኝ ይሆናል። እኔ አባት መምሰሌን መግለጻችሁ ብቻ ሳይሆን አባት አለመሆኔንም ነው። በዚህ ፈንታ እስጢፋኖስ፥ «አባት ነህ፥ በእውነት አባት ትመስላለህ?» ልትሉ ትችላላችሁ። ጳውሎስ ኢየሱስ ከተሠገዎ በፊትም እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ስለ እርሱ የሆነው ሁሉ የእርሱን አምላክነት እንደሚገልጽ ይናገራል። እርሱ የእግዚአብሔር ኃይል ነበረው። ይህ ኃይል በተናገረው ቃል ፍጥረተ ዓለምን (ዩኒቨርስን) የመሠረተ ነበር። የእግዚአብሔር ጥበብ ነበረው። በኃላፊ ጊዜያት ስለተከናወኑት፥ ኣሁንና ወደፊትም ስለሚከናወኑት ሁሉ ፍጹም እውቀት አለው። እርሱ የእግዚአብሔር ክብርና ሞገስ ነበረው። ይህም በእልፍ አእላፋት መላእክት ውዳሴ የተከበበ አንጸባራቂ የሰማይ ፀዳል፥ ፍጹም ብርሃንና ክብር ነበር። እርሱ የእግዚአብሔር ፍጹም ባሕርያት የሆኑ፥ ቅድስና፥ መልካምነትና ንጽሕና ነበረው። ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን በሰማይ የነበረው ክብሩ ገልጾታል።
ጥያቄ፡- ሀ) ኢየሱስ እግዚአብሔር ለመሆኑ የሚያመለክቱ ሌሎች ባሕርያቱ የትኞቹ ናቸው? ለህ እናንተ ከእርሱ ጋር ላላችሁ ግንኙነት እነዚህ እያንዳንዳቸው ለምን ጠቃሚዎች ሆኑ?
ኢየሱስ እግዚአብሔር የመሆን ክብሩን በመብትነት መያዝን አልፈለገም። በዚህ ፈንታ በገዛ ፈቃዱ የእግዚአብሔርነትን ክብርና ግርማ አሳልፎ ለመስጠት ወደደ። በግሪኩ ቋንቋ፥ «ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም» የሚለው አገላለጽ፥ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን እንደ ራሱ መልካም ዕድል አድርጎ ሊጠቀምበት አልፈለገም የሚል ነው። ምንም እንኳን ክርስቶስ እግዚአብሔር ቢሆንም፥ የመለኮቱን ኃይልና ክብር ለጥቅሙ ሊያውል አልፈለገም። እግዚአብሔር የመሆኑን ክብር ለራሱ ጥቅም ሊያውለው አልፈቀደም። በዚህ ፈንታ ኢየሱስ መለኮትነቱን እንዴት ተጠቀመበት?
2. ኢየሱስ ወደ ዓለም በመጣ ጊዜ ምን ይመስል ነበር?
ጥያቄ፡- ፊልጵስዩስ 2፡7-8 ኣንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ኢየሱስ ስለ አከናወናቸው አምስት ነገሮች ምን ይላሉ?
ኢየሱስ መለኮትነቱን ለግል ጥቅሙ በማዋል ፈንታ፥ አራት ነገሮችን አድርጓል።
1) በቀድሞው የአማርኛ ትርጉም «ራሱን ባዶ አደረገ» የሚለው ሐረግ፥ የጥቅሱ የመጀመሪያው ሐረግ ባይሆንም በግሪኩ የጥቅሱ የመጀመሪያው ሐረግ ነው። በአዲሱ የአማርኛ ትርጉም ላይም የመጀመሪያው ሐረግ ሆኖ ተጽፎአል። «ራሱን ባዶ አደረገ» የሚለው የአማርኛው የቀድሞ ትርጉም፥ የግሪኩን ሐረግ ቃል በቃል ተርጉሞታል። እንዲህ ማለት ምን ማለት ነው? እንዲህ ማለት ኢየሱስ ወደ ምድር ሲመጣ የመለኮትነቱን ባሕርይ ትቶ ገዶውን መጣ ማለት ነው? ደግሞስ ወደ ምድር ሲመጣ አምላክነቱ አበቃ ማለት ነው? አይደለም። ይህ ሐረግ ኢየሱስ የፈጸመውን ተግባር ጠቅለል ኣድርጎ ያቀረበበት የጳውሎስ ልማዳዊ አገላለጽ ነው። የሚቀጥሉት ሦስት ሐረጎች ምን ማለቱ እንደሆነ ዘርዘር አድርገው ይገልጻሉ። ሐረጉ ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ትቷል አይልም። ሐረጉ የሚለው ኢየሱስ ግዚአብሔር መሆኑ እንዳለ ሆኖ፥ ሌላ ነገር ሆነ ነው። በነበረው መለኮታዊ ሕርይ ላይ ሌላ ባሕርይ ጨመረ።
2) ጌታ ኢየሱስ የባሪያን መልክ ወሰደ። በድሮው የአማርኛው የመጽሐፍ ዱስ ትርጉም «መልክ» የሚለው ቃል በቁጥር ስድስት ከሚገኘው ጋር ንድ ነው። የባሪያን መልክ ወሰደ ማለት ኢየሱስ ሁለቱንም፥ የባሪያን ውነተኛ ውስጣዊ ባሕሪና ውጪኣዊ መልክ ያዘ ማለት ነው። እርሱም ባሪያ ነ፥ በእውነትም የባሪያን መልክ ወሰደ። ከተሠገዎ በፊት ኢየሱስ እግዚአብሔር ነበር። በእግዚአብሔርነትም ተገልጦአል። ከተሠገዎ በኋላ ባሪያ ሆነ፥ እንደ ባሪያም ተገለጠ። የጥንት ዓለም ሰዎች ስለ ባርነት ደህና አድርገው ያውቁ ነበሩ። ባሪያዎችን በየቀኑ ይመለከቱ ነበር። ባሪያዎች ጨርሶ መብት ያልነበራቸው ሰዎች ነበሩ። ታዲያ ኢየሱስ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ በገዛ ፈቃዱ ክብሩንና ታላቅነቱን በመተው በሰዎች ዘንድ ባሪያ መስሎ ተገኘ።
(3) ኢየሱስ የሰውን መልክና ምሳሌ ወሰደ። የግሪኩ ቃል «መምሰል» የሚለው በትክክል እንደ አንድ ነገር መሆን ሊሆን ይችላል። እርሱ እንደሚለው ክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ከሰው ዘር ጋር ተመሳስሏል። ኢየሱስ ወደ ምድር መጥቶ ራሱን ባዶ በማድረግ የተቀሩት የሰው ልጆች እንደሚኖሩት ኖረ። «መልክ» የሚለውን የግሪኩ ቃል «በስሜት ሕዋሳት የሚታወቅ አቀራረብ፥ ቅርጽ ወይም አበጃጀት» ይለዋል። እንዲህ ማለት ኢየሱስ እውነተኛ ሰው አይደለም ማለትም አይደለም። በአንጻሩ ይህ አገላለጽ ሁሉም ሰው እርሱ ሰው መሆኑን ያውቅ ነበር ማለት ነው። እርሱ እንደ ሰው ተገለጠ፤ በአካባቢው የነበሩ ሰዎችም ግንዛቤ እርሱ ሰው እንደሆነ ነበር። ይህ በአጽንኦት የሚያመለክተው ምንም እንኳን ኢየሱስ የአምላክነቱን ባሕርይ እንደ ያዘ ቢሆንም፥ የተገለጠው በሰው መልክ መሆኑን ነው። ኢየሱስ እንደ ማንኛውም ሰው ከሰዎች ጋር በመኖር ራሱን ባዶ አድርጓል። አብሮአቸው የኖረው ሰዎች የተመለከቱት እንደ እግዚአብሔር አድርገው ሳይሆን ልክ እንደ እነርሱ ሰው አድርገው ነበር። እነዚህ ቃላት በአንድነት የሚገልጹት ኢየሱስ በሰዎች መካከል ሰው ሆኖ በመኖር ራሱን ባዶ እንዳደረገ ነው። እርሱ እውነተኛ ሰው ሆኖ ኖሯል።
ጥያቄ፡– ሀ) ዘዳግም 21፡23 ኣንብቡ። በአይሁዶች እስተሳሰብ በተለይ የተረገመ ማን ነበር? ለ) ገላትያ 3፡13 አንብቡ። ኢየሱስ ለእኛ ምን ሆነ?
4) ኢየሱስ ጭካኔና ሥቃይ ስሞላበት ሁኔታ ተሰቅሎ ሞተ። ኢየሱስ በመጨረሻው ላይ ራሱን ባዶ ያደረገውና የነበረውን ክብር አሳልፎ የሰጠው ለሞት ራሱን ባስገዛ ጊዜ ነበር። ኢየሱስ ሰው ለመሆን መፍቀዱ ብቻ ሳይሆን፥ ራሱን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ራሱን ትሑት አድርጎአል። የኢየሱስ ሕይወት ሙሉ በሙሉ የአባቱን ፈቃድ በመታዘዝ ላይ የተመሠረተ ነበር (ዮሐንስ 5፡30፤ 6፡38)። ነገር ግን በተለይ ራሱን ለስቅላት አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ለአባቱ ፈቃድ ታዛዥነቱን አሳይቷል። ለቅላት በጥንቱ ዓለም ከባድ ጭካኔ ያለበት የውርደት ሞት ነበር። ሥቃይና መከራ ያለበት የአሟሟት ዘዴ ስለነበረ ቅጣቱ በሮም መንግሥት ላይ ላመፁ ክፉ ወንጀለኛች የተመደበ ነበር። በተለይም ስቅላት ለአንድ አይሁድ በጣም የከፋ ዮርጊት ነበር። በኦሪት ዘዳግም 21፡23 ላይ፥ «በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነው» ይላል። እንዲህ ማለት በዚህ ሁኔታ የሚሞቱ ሰዎች ከእግዚአብሔር የበረከት ኪዳን ውጭ ስለሚሆኑ፥ የመዳን ተስፋ የላቸውም ማለት ነው። በእውነቱ ኢየሱስ ለእኛ ይገባ የነበረውን የኃጢአት መርገም ተሸከመ (ገላትያ 3፡13)። ራሱንም አሳልፎ እስከ መስቀል ሞት በመስጠት የነበረውን መብትና ክብር በፈቃዱ ተወ። ሙሉ ለሙሉ ራሱን ባዶ አደረገ።
ፊልጵስዩስ 2፡6-8 ስለ ተሠገዎ ከፍተኛ አጽንኦት የተሰጠበት ክፍል ነው። በእነዚህ ጥቅሶች ኢየሱስ ከተሠገዎ በፊት ለእግዚኣብሔርነት በተገባ ክብርና ሞገስ ፍጹም የተላበሰ አምላክ ነበር። ነገር ገን በዚህ ሁሉ ክብሩ መጠቀም ሲችል ትቶታል። ይህን ሁሉ ክብሩን የተወው ወደ ምድር በመምጣት፥ እንደ ማንኛውም ሰው በመኖርና እውነተኛ ባሪያ በመሆን ነበር። እንደ እግዚአብሔርነቱ የነበረውን ትሩፋት (ልዩ መብት) ሁሉ ትቶ ለስቅላት ፈቅዶ ራሱን ሰጠ።
3. ኢየሱስ ዓለምን ትቶ ከሄደ በኋላ ምን ሆነ? ወደፊትስ ምን ይሆናል?
ጥያቄ፡- ፊልጵስዩስ 2፡9-11 አንብቡ፡ ሀ) ኢየሱስ ትሑት በመሆኑ፥ እግዚኣብሔር ምን አደረገላት? ለ) ወደፊትስ ፍጥረታት ሁሉ ለኢየሱስ እንዴት ያለ ምላሽ ይለጣሉ?
በፊልጵስዩስ 2፡6-11 ያለው መዝሙር እግዚአብሔር ለኢየሱስ ትሕትና በሰጠው ምላሽ ይደመደማል። ጌታ ኢየሱስ ክብሩን ሁሉ ትቶ በፈቃዱ ትሑት ስለሆነና ራሱንም ዝቅ ስላደረገ እግዚአብሔር ከፍጥረታት ሁሉ
በላይ ከፍ ወደ ኣለው ክብሩ መለሰው። ነገር ግን እግዚአብሔር ኢየሱስን ወደ ቀድሞ ክብሩ ከመመለስ የላቀ አድርጓል። ወደፊት ፍጥረቱ የሆኑ የሰው ልጆችና መላእክት ሳይቀሩ ኢየሱስ ሥልጣን ሁሉ ያለውና የፍጥረተ ዓለም ሁሉ ገዥ መሆኑን ተረድተው ያከብሩታል፥ ያመልኩታልም። ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ሥጋ ከለበሰ በኋላ ቀድሞ በአምላክነቱ በሰማይ ሠራዊት ይደረግለት የነበረውን ክብርና ሞገስ በፈቃዱ ተወይሁን እንጂ ወደፊት ገና እንደ አምላክነቱ ክብር ያልሰጡት ጭምር የሚገባውን አምልኮና ክብር ይሰጡታል።
ነገር ግን አስተውሉ፥ እግዚአብሔር በተለይ ኢየሱስ ለተባለው ስም ሥልጣንና ገዥነትን ሰጥቶታል። «ኢየሱስ» የሚለው ስያሜ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ወደ ዓለም ሲመጣ የተሰጠው ሰብኣዊ መጠሪያ ነበር። ኢየሱስ ወደዚህ ምድር ሰው ሆኖ መጥቶ በሰውነቱ ስለአከናወናቸው ተግባራት፥ እግዚአብሔር ከፍ አድርጎ ከሥልጣን ሁሉ በላይ ሥልጣን ሰጠው። «ኢየሱስ» ማለት አዳኝ ማለት ነው። ኢየሱስ ሰው እስከ መሆን ደረጃ ራሱን ዝቅ በማድረጉና ዓለምን ከኃጢአቱ ለማዳን ሲል የከፋ ሞት ለመሞት ስመፍቀዱ፥ ምክንያት እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገው፡፡ የኢየሱስ ፍጥረተ ዓለም (የዩኒቨርስ) ገዥ እንዲሆን ከፍ ከፍ የመደረጉ ሁኔታ ሰውም አምላክም በመሆኑ ላይ የተመሠረተ ነው። ምክንያቱም ኢየሱስ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ የቀድሞ ክብሩን ትቶ የተናቀና የተዋረደ ሰው ሆኖ በመኖሩ፥ ከተሠገዎ በፊት እንደ አምላክነቱ ክብር ያልሰጡት እንኳ አንድ ቀን ክብርና ምስጋናን ያቀርቡለታል።
ኢየሱስ ሰው ሆኖ ሳለ አምላክነቱን ትቷል ብሎ ፊልጵስዩስ 2 ያስተምራል? እንዲህ ብሎ አያስተምርም። ይህ ክፍል የሚያስተምረው፥ እርሱ የአምላክነት ክብሩና ሞገሱን ተወ ብሎ ነው። ለእግዚአብሔር የተገባውን መብትና ክብር ሁሉ ተወ ነው የሚለው። ያላንዳች ክብርና መብት በመሆን የባሪያን ስፍራ ወሰደ ነው የሚለው። እንደ ሰው ሆኖ ኖረ፥ ሰዎችም ሰው አድርገው ተቀብለው አብረውት ኖሩ ነው የሚለው። ይህ ክፍል ለእግዚአብሔር አብ እስከ መስቀል ሞት ድረስ በትሕትና መታዘዙን ያስተምራል። እግዚአብሔር እግዚአብሔርነቱን አይተውም፥ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሌሎች ክፍለ ምንባቦችንም እንደ ተመለከትን ኢየሱስ በምድር ሳለ እንኳን አምላክ ነበር። ፊልጵስዩስ 2፡5-11 ኢየሱስ የአምላክነቱን ክብርና ሞገስ በፈቃዱ ተወ ብሎ ቢያስተምርም፥ አምላክ ኣልነበረም ብሎ አያስተምርም።
ጥያቄ፡- ፊልጵስዩስ 2፡3-4 አንብቡ። ሀ) መብታችሁንና ክብራችሁን አሳልፋችሁ መስጠት የሚከብዳችሁ መቼ ነው? ለ) የሌሉችን ጥቅም ከራሳችሁ ጥቅም ለማስቀደም አስቸጋሪ ሆኖ የምታገኙት መቼ ነው? ሐ) በዚህ ሳምንት የራሳችሁን መብት ትታችሁ የሌሎችን ጥቅም ለማስቀደም የምትችሉበትን ቢያንስ ሦስት መንገዶችን ጻፉ።
ፊልጵስዩስ 2፡5-1 ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ባሕርይ ብቻ የሚያስተምረን አለመሆኑን መርሳት የለብንም። በመሠረቱ ይህ ክፍል የተጻፈው እንዴት እንደምንኖር ሊያስተምረን ነው። ኢየሱስ ክብሩንና መብቱን እንደ ተወ ሁሉ እኛም የራሳችንን መብትና ጥቅም ከሌሎች ማስቀደም ትተን በዙሪያችን ያሉ የሌሎች ፍላጎት ለማሟላት ተጠርተናል። አንዳንዴ ሌሎችን ለመርዳት ጊዜያችንን አሳልፈን መስጠት ይኖርብን ይሆናል። አንዳንድ ጊዜም ሌሎችን ለመርዳት የእኛን ደረጃ ትተን ዝቅ ማለት ይገባናል። አንዳንዴም ለሌሎች ለየት ያለ አገልግሎት መስጠት ይኖርብን ይሆናል። አንዳንድ ጊዜም የማንስማማበት አሳብ ቢሆንም እንኳ፥ ሌሎች ውሳኔ እንዲሰጡ የምንፈቅድበት ጊዜ አለ። በምናደርገው ሁሉ ኢየሱስን ጥሩ ምሳሌያችን በማድረግ እርሱን እናስቀድም። ራስን አሳልፎ ለሌሎች በመስጠት፥ በትሕትና፥ ከጥቅማችን ሌሎችን በማስቀደም ረገድ ኢየሱስ ቋሚ ምሳሌያችን ነው።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
