Site icon

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ምሳሌያችን 

ኢየሱስ ስለ ምን ወደ ምድር መጣ? የእግዚአብሔር ልጅስ ስለ ምን ሰው ሆነ? ለዚህ ጥያቄ ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልሶች አሉ። ለዚህ በጣም ጠቃሚ የሆነው መልስ፥ ኢየሱስ የኃጢአታችንን ቅጣት ለመክፈል መሥዋዕት ሆኖ ሊሞት መጣ (ማር. 10፡45) የሚለው ነው። በዚሁ መጽሐፍ ውስጥ ቆየት ብለን ስለ ኢየሱስ ሞት ስላለው ቁም ነገር በተለያዩ ትምህርቶች ውስጥ እንመለከታለን። እንደዚሁም ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያኑን ለማስተማርና ለመመሥረት መጥቶአል (ማቴ. 16፡18)። ይህች ቤተ ክርስቲያኑም በእርሱ የሚያምኑና እርሱንም ለመከተል የሚፈቅዱ ሁሉ የሚሰበሰቡባት በዓለም ያለች አንዲት የአማኞች ኅብረት ናት። በዚህች የእርሱ አካል በሆነች ቤተ ክርስቲያን አማካይነት ኢየሱስ ዛሬ በዓለም ላይ ሥራውን ይሠራል። ይሁን እንጂ ኢየሱስ ወደ ዓለም የመጣበት ሌላ ምክንያትም አለ። ኢየሱስ ወደ ዓለም የመጣበት ሌላው ምክንያት እንዴት መኖር እንዳለብን ሊያስተምረን ነው። እርሱ ወደ ዓለም የመጣው፥ የእኛ ምሳሌ ለመሆን ነው። አንዳንድ ክርስቲያኖች ይህንን ትልቅ ግምት የሚሰጠው የኢየሱስ የሕይወቱ ክፍል ነው ይላሉ። እነርሱ እንደሚያምኑትም ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣበት መሠረታዊ ምክንያት ለእኛ ምሳሌ ለመሆን ነው። ነገር ግን ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም የመጣስት መሠረታዊው ምክንያት የእኛ ምሳሌ ለመሆን ሳይሆን ለኃጢአታችን ለመሞች ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍት ኢየሱስ በብዙ መንገዶች ምሳሌያችን እንደሆነ በግልጽ ያስረዳሉ። ስለዚህ በእነዚያ መንገዶች የእርሱን ምሳሌ ለመከተል መጣር አለብን። በሁለተኛው ክፍለ ትምህርት ጥናታችን፥ ስለ ኢየሱስ ሰብአዊነት በተመለከትን ጊዜ፥ ኢየሱስ በብዙ መንገዶች ምሳሌያችን እንደሆነ አይተናል። ዛሬ ደግሞ የኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት ምሳሌያችን እንደሆነ፥ ቅዱሳት መጻሕፍት በሌሎች መንገዶች ሲያስተምሩን እንከታተላለን። 

ጥያቄ፡- 2ኛ ቆሮንቶስ ፡18 እንብቡ። ሀ) እማኛች ወደ ምን መልክ መቀየር ይገባቸዋል? ለህ ወደዚህስ መልክ እንዴት እንለወጣለን? 

2ኛ ቆሮንቶስ 3፡18 ከክርስቲያን የሕይወት ግቦች መካከል አንደኛውንና እጅግ በጣም ጥልቅ የሆነውን ይገልጽልናል። የእኛ ግብ ወደ ክርስቶስ መልክ መለወጥ ነው። ስለዚህ እንደ ኢየሱስ መሆን ይገባናል። እንዴት እንደ ኢየሱስ እንሆናለን? ይህ ክፍል እንደሚናገረው የጌታን ክብር ማንጸባረቅ ይኖርብናል። ልክ መስተዋት የሰውን መልክ እንደሚያንጸባርቅ ሁሉ፥ ወደ ጌታ በተመለከትን ቁጥር፥ ለሌሎች የጌታን ክብር እናንጸባርቅላቸዋለን። ወደ ጌታ እንዴት እንመለከታለን? ወደ ጌታ የምንመለከተውማ ከእርሱ ጋር ቃሉን ይዘን በጸሎት ቆይታ ለናደርግ ነው። ወደ ጌታ የምንመለከተው እርሱ ስለፈጸማቸው ሥራዎችና ስለ እርሱ ባሕርይ በማሰላሰል ነው። እንደዚሁም ወደ ጌታ የምንመለከተው፥ በሌሎች ፊት እኛ እርሱን እንዴት አድርገን መምሰላችንን መግለጽ እንደምንችል ስናሰላስል ነው። ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣበት አንዱ ምክንያት፥ የእግዚአብሔር ባሕርይ በሰው አማካይነት ሲንጸባረቅ እንድናይ ነው። ይህ ባሕርይ ልንከተለው የሚገባ ምሳሌ ነው። ስለሆነም ክርስቶስን በሚገባ ልንከተለው እንድንችል፥ የእርሱን ምሳሌ በጥንቃቄ ልናጠናው ይገባናል። 

ጌታን ልንመስል የምንችልባቸው የተለዩ መንገዶች ምን ምንድን ናቸው? 

1. ኢየሱስ ፍትሕን ተነፍጎ ቢሠቃይም ንጹሕና ቅዱስ ሆኖ ጸና 

ጥያቄ፡- 1ኛ ጴጥሮስ 2፡19-23 አንብቡ። ሀ) እንደ ቁጥር 19-20 አባባል፥ ምስጋናን መቀበል ለምን ይበጀናል? ለ) እንደ ቁጥር 21፥ ለክርስቶስ ሥቃይ አንዱ ምክንያት ምን ነበር? ሐ) እንደ ቁጥር 22፥ ክርስቶስ እንዴት ለእኛ ምሳሌ ሊሆን ቻለ? 

1ኛ ጴጥሮስ 2፡19-23፥ ክርስቶስ የእኛ ምሳሌ ስለሆነ እኛ የእርሱን ዱካ መከተል እንዳለብን ያሳስበናል። ይህ ክፍል ለየት አድርጎ ኢየሱስ በሁለት መንገዶች ምሳሌያችን መሆኑን ይነግረናል። በዚህ ጥቅስ ውስጥ እንደተመለከተው ኢየሱስ ለእኛ ምሳሌ የሆነበት አንዱ መንገድ፥ የተሠቃየበት ሁኔታ ነው። በመሠረቱ ኢየሱስ ራሱ በሠራው ኃጢአት ምክንያት አልተሠቃየም። ጽድቅን በማድረጉ ብቻ ኢ-ፍትሐዊ የሆነ ሥቃይ ደረሰበት። ኢየሱስ መልካም ሥራዎችን በማድረጉ ይህ ወንጀል ሆኖበት ያላግባብ ቢሠቃይም፥ አላጉረመረመም፥ አጸፋውን አልመለሰም ወይም አልተበቀለም። ደግሞም ኢየሱስ፥ «የደረሰብኝ በደል አግባብ አይደለም፥ ስለዚህ ትክክለኛ ፍትሕ ሊሰጠኝ ይገባል» አላለም። እንዲሁም ኢየሱስ፡ «እነዚህን ያሠቃዩኝን ሰዎች እበቀላቸዋለሁም» እላለም። ይህን አስመርኩዞ ጴጥሮስ ሲናገር፥ ኢየሱስ ስለ ሥቃዩ ውጤት ራሱን አሳልፎ ለእግዚአብሔር ሰጠ፥ በእርሱም ታመነ ይላል። አንድ ቀን እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ እንደሚያቃናና ፍትሐዊ እንደሚያደርግ ያምን ነበር። ከእርሱ ሥቃይ የተነሣ፥ እግዚአብሔር ለእርሱም ሆነ ለሌሎች ሰዎች መልካሙን ሁሉ እንደሚያመጣ አመነ። በእግዚአብሔር ስለታመነ፥ ያላንዳች ማጉረምረም ኢ-ፍትሐዊ የነበረውንና የደረሰበትን ሥቃይ ሁሉ ሊቋቋምና ሊጸና ችሏል።

ጥያቄ፡– ኢ-ፍትሐዊ የሆነ ሥቃይ መቼ ደረሰባችሁ? ለ) ይህ በደረሰባችሁ ጊዜ ስማታችሁ እንዴት ነበር? በእግዚአብሔር በማመን ያላንዳች ማጉረምረም ሥቃዩን ተቀበላችሁ? ወይስ ያላግባብ ሥቃይ ደረሰብን ብላችሁ ተበላላችሁ? ደግሞስ ለመበቀል አስባችሁ ነበር? 

አንዳንድ ጊዜ ሁላችንም ብንሆን ኢ-ፍትሐዊ የሆነ ሥቃይ ይደርስብናል። ለምሳሌ፥ በትምህርት ቤት ያልጠበቅነውን ዝቅተኛ ነጥብ እናገኝ ይሆናል። የጠበቅነውን ክብርና የደረጃ እድገት ሳናገኝ እንቀራለን። ያለበለዚያም ጨርሶ ባልፈጸምነው ተግባር ተወንጅለን እንከሰስ ይሆናል። ወይም ክርስቲያኖች በመሆናችን ብቻ ተሠቃይተን ሊሆን ይችላል። እዚህ ላይ እንኳ ኢየሱስ በምንሠቃይበት ጊዜ፥ ልናስታውስ የሚገባን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑንና ሁኔታዎችንም በፍጹም እንደሚቆጣጠር ነው። በመጨረሻውም ላይ ሁሉን ነገር ያስተካክልልናል። ለእኛም ሆነ ለሌሎች ሥቃያችንን ወደ መልካም ይለውጠዋል። በዚህ በምድር ላይ ለሚደርስብን ሥቃይ ፍትሕን መሻት ስሕተት የለበትም። ግን ፍትሕን ባናገኝ ማጉረምረምና የበቀል እርምጃ ለመውሰድ መነሣሣት የለብንም። እንደ ኢየሱስ እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ እንደሚቆጣጠር ማመን አለብን። እግዚአብሔርም ለታላቅ ክብሩ ኢልና ለእኛም ጥቅም በማሰብ ሁሉን ነገር ለመልካም ያደርገዋል። ስለዚህ ኢየሱስ ኢ-ፍትሐዊ የሆነ ሥቃይ ሲደርስብን መቋቋም የምንችልበት ምሳሌያችን ሊሆነን ይገባል። 

ሌላው ኢየሱስ ምሳሌያችን ሊሆን የሚችልበት መንገድ በንጽሕናውና በቅድስናው ነው። እርሱ በፍጹም አንድም ጊዜ ኃጢአትን እላደረገም። ቁጥር 22 ይህን በሚገባ ሲገልጽ፥ «በአፉ ተንኮል፥ እልተገኘበትም» ይላል። ያ ማለት፥ ኢየሱስ ሁልጊዜ ፍጹም ታማኝና የማይሸነግል ነበር ማለት ነው። እርሱ ከቶ አንድም ጊዜ ዋሽቶ አያውቅም። ሰዎችንም ለመሸንገል ሞክሮ አያውቅም። 

ጥያቄ፡- ሀ) በሕይወታችሁ ውስጥ ንጽሕና ሳይሰማችሁ የቀረው በምን ዙሪያ ነው? ለ) እንደዚሁም በሕይወታችሁ ውስጥ በየትኛው ሁኔታ ታማኝነታችሁ ማለትም የማትዋሹና የማታጭበረብሩ የመሆናችሁ ነገር የጎደለ፥ ያልተሟላ ሆኖ ተሰምቷችሁ ነበር? 

አማኞች ሕይወታቸው ፍጹም ንጹሕ እንዳይሆን ብዙ ፈተናዎች ይታገሉአቸዋል። ለምሳሌም ያህል፥ አንዳንድ ጊዜ ባለሥልጣናት የምንፈልገውን ጉዳይ ይፈጽሙልን ዘንድ ጉቦ ልንሰጣቸው እንፈተናለን። ጻሩ ግን ኢየሱስ እንዲህ አላደረገም። ስለዚህ ከባለሥልጣናት ጋር የነበረው ግንኙነት ፍጹም ንጽሕናን የተሞላ ነበር። እርሱ ጨርሶ ጉቦ ሰጥቶ አያውቅም። እኛ አንዳንድ ጊዜ በአሳብም ሆነ በተግባር በወሲባዊ ፈተና ተጠምደን ይሆናል። ኢየሱስ ግን በአሳቡም ሆነ በተግባሩ ሴቶችን በሚመለከት ሁኔታ ፍጹም ንጽሕና ያለበት ሕይወት ነበረው። እኛ አንዳንድ ጊዜ ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ላይ ውሸትንና ማታለልን ለመቀላቀል እንፈተናለን። ስለሆነም የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት ብቻ ስንል እንዋሻለን። እንደዚሁም በሌሎች ሰዎች ዓይን የተሻልን ሆነን ለመገኘት ስንል ሙሉ በሙሉ እውነት የሆነ ነገር አንናገርም። ኢየሱስ ምንም ዓይነት የአሳችነት ተግባር አልታየበትም። እርሱ ለሰዎች እውነቱን ከመናገር በስተቀር፥ እነርሱን የሚያስት ቃል ተናግሮ አያውቅም። ስለዚህ የኢየሱስ ንጹሕ ሕይወትና ፍጹም ታማኝነት ለክርስትና ሕይወታችን መልካም ምሳሌያችን ነው። 

1ኛ ጴጥሮስ 2፡19-23 ያለው ክፍል ጌታ ኢየሱስ ለተከታዮቹ ምሳሌ የሆነባቸውን ሁለት መንገዶችን ያመለክተናል። በምንሠራው ጥፋት በኅብረተሰቡ ተወንጅለን እንዳንቀጣ በሕዝብ ፊት ኃጢአት አለመሥራትን ግባችን ልናደርግ ይገባናል። መልካም ምስክርነት ያለበትን ንጹሕ ሕይወት መኖር ይገባናል። ሥቃይ እንኳ ቢደርስብን፥ የሥቃያችን ምክንያት መልካም ተግባራችን መሆን አለበት። ኢ-ፍትሐዊ የሆነ ሥቃይ ብንቀበል በምንም ዓይነት መናደድ ወይም ለመበቀል መነሣሣት የለብንም። በዚህ ፈንታ የንጽሕናና የቅድስና ሕይወትን ለመኖር መሻት አለብን። 

2. ኢየሱስ ራሱን ትሑት አድርጎ ሌሎችን አገለገለ 

ጥያቄ፡- ርሜ 5፡1-3፥5 አንብቡ። ሀ) ሐዋርያው ጳውሎስ በዚህ ክፍል ከቁጥር 1-2፥ ብርቱዎች ምን እንዲያደርጉ ያዛል? ሐዋርያው ትእዛዞቹን በሦስት መንገዶች ይገልጻል፥ እናንተ ደግሞ ፖለቱንም መንገዶች ጻፉአቸው፡፡ ለ) እንደ ቁጥር 2 አማኞች በምን ምክንያት ለዚህ ትእዛዝ መገዛት ይኖርባቸዋል? ሐ) ይህን ትእዛዝ በመቀበል ረገድ የአማኛች ምሳሌ የሆነው ማን ነው? መ) ሮማ 5፡8 አንብቡ። ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ራሱን እንዴት ወሰነ? 

ጥያቄ፡- ፊልጵስዩስ 2፡3-4 አንብቡ። የፊልጵስዩስ ሰዎች ምንን እንዲያደርጉ ነበር ጳውሎስ ያዘዛቸው? ሀ) ከዚያስ ሐዋርያው የፊልጵስዩስ ሰዎች ምን እንዲያደርጉ አዟቸው ነበር? ለ) ፊልጵስዩስ 2፡5 አንብቡ። እነዚህን ትእዛዛት በመፈጸም ለፊልጵስዩስ ሰዎች ምሳሌ የሆነው ማን ነበር? 

ጥያቄ፡– ማርቆስ 10፡43-45 እንብቡ። ሀ) የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የሆነ ሰው በእግዚአብሔር መንግሥት አንድን ነገር ለማድረግ ቢፈልግ እንዲህ ያለው ሰው ምን ተግባር ማከናወን አለበት? ለ) እንደ ቁጥር 45 ከሆነ፥ ይህን ተግባር በመፈጸም \ ለደቀ መዛሙርት ምሳሌ የሆነው ማን ነው? 

ኢየሱስ ለተከታዮቹ ምሳሌ የነበረበት ሌላው መንገድ ሌሎችን ሰዎች በትሕትና ለማገልገል ያሳየው ፈቃደኝነት ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ቢያንስ በሦስት ስፍራዎች እንደምንመለከተው፥ ኢየሱስ ሌሎች ሰዎችን ከራሱ ይልቅ አስቀድሞ መገኘቱን እንገነዘባለን። በዚህ ድርጊቱም እኛ የእርሱን ምሳሌ እንድንከተል ያደርገናል። ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 5፡1-3፥ ለብርቱዎች ክርስቲያኖች የተናገረውን እናነባለን። በርሜ ምዕራፍ 14-15 የተጻፈውን ስንመለከት መሠረተ አሳቡ እንደሚነግረን፥ ብርቱዎች የተባሉት፥ አንዳንድ ክርስቲያኖች ርኩስ ናቸው ብለው የሚያስቧቸውን ምግቦች የሚበሉት ናቸው። ታዲያ ብርቱዎቹ ምግቦች ሁሉ ንጹሕ ናቸው ብለው በማሰብ አንዳንድ ምግቦችን መመገባቸውን ኃጢአት እንደ ሠሩ አይቆጥሩትም ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስ ግን ያለው፥ እንዲህ ያሉት ሰዎች ለሌሎች ክርስቲያኖች እንቅፋት እንዳይሆኑ እነዚያኑ ምግቦች እንዳይበሉ ነበር። ሌሎችን ለመገንባት ሲሉ መብታቸውን ለመተው ፈቃደኞች ይሁኑ ነበር ያለው። በዚህ ረገድ የራሱን ክብርና የራሱን መብት ለሌሎች አሳልፎ የሰጠ ታላቁ ምሳሌያችን ክርስቶስ ብቻ ነው። ስለሆነም ክርስቶስ በምንም ሁኔታ ራሱን ለማስደሰት ያደረገው ምንም ነገር አልነበረም። እንዲያውም ወደ ምድር ሲመጣ፥ ለአይሁድ ሕግ በመታዘዝ ራሱን ውስን አደረገ (ሮሜ 5፡8)። ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ቀድሞ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ለነበሩት አባቶች የተሰጠው የደኅንነት ተስፋ ለሁሉም እንዲዳረስ ለማድረግ ነበር። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ክብሩንና መብቱን ለሌሎች አሳልፎ የሰጠበት ምክንያት እነርሱን ለመገንባትና መልካሙን ሁሉ ለእነርሱ ለመስጠት ሲል ነው። 

ሐዋርያው ጳውሎስም ለፊልጵስዩስ ክርስቲያኖች በላከው መልእክት ተመሳሳይ ትእዛዝን ያስተላልፋል። ይኸውም በራስ ወዳድነት የራሳቸውን ጥቅም ብቻ እንዳይመለከቱ ያስጠነቅቃቸዋል። በዚህ ፈንታ እያንዳንዱ ሰው፥ ባልንጀራው ከእርሱ የተሻለ መሆኑን እንዲያስብ እና በተግባሩም እንዲገልጽ ይናገራል። ስለዚህ የፊልጵስዩስ ሰዎች ትኩረታቸውን በራሳቸው ጥቅምና በግላቸው ምቾት ዙሪያ እንዳያደርጉ ያሳስባቸዋል። በዚህ ፈንታ የሌሎችን ጥቅም ለማንከባከብ ጊዜያቸውን እንዲሠዉ ያሳስባቸዋል። በዚህ ረገድ ሌሎችን ከራሱ አስበልጦ በመመልከትና ጥቅማቸውም ከጥቅሙ አልቆ በማሰብ ጊዜውንም ለእነርሱ እንክብካቤ በማድረግ ያሳለፈ ታላቅ ምሳሌነት የነበረው ማን ነው? ያለ ጥርጥር ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ቀደም ሲል በትምህርታችን በክፍል ሦስት ላይ ያጠናነውና በፊልጵስዩስ 2፡6-11 ስለ ክርስቶስ ተሠገዎ የተጻፈው ቅኔ ክርስቲያኖች ሊያደርጉት የሚገባውን በጎ ምሳሌነት በትክከል አስቀምጦታል። ኢየሱስ ለሰው ልጆች ሁሉ ከራሱ አስበልጦ የተሻለ ስፍራ በመስጠት እንደ እግዚአብሔር የሚገባውን ከብር፥ ምሥጋናና ገናንነት ሁሉ ወደ ጎን በመተው የአገልጋይነትን ቦታ መረጠ። እንዲሁም ከራሱ ምቶት በላይ የሰዎችን ፍላጎት ማሟላትን ዓላማው አደረገ። ስለዚህ ሰው ሆነ፥ ራሱን ዝቅ አድርጎ ጭካኔና ውርደት ለተሞላበት ሞት ራሱን ሰጠ። ኢየሱስ ይህን ታላቅ ተግባር በመፈጸም ሌሎችን ሰዎች ከእኛ የተሻሉ መሆናቸውን ተገንዝበን በትሕትና እንድናገለግላቸው እርሱ ለእኛ ታላቅ ምሳሌያችን ሆኖልናል። 

ጌታ ኢየሱላ ማንም በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ታላቅ ሊሆን ቢሻ፥ አስቀድሞ አገልጋይ መሆን ይገባዋል ሲል ደቀ መዛሙርቱን አስተምሯቸዋል። እዚህ ላይ ኢየሱስ ሲናገር እኛ ለአጭር ጊዜ አገልጋዮች ከሆንን በኋላ፥ ብርቱ ገዢዎች እስከ መሆን ከፍ ከፍ እንላለን ማለቱ 

አይደለም። ነገር ግን «ታላቅ» ሲል እኛ ለእርሱ ታላቅ ቁም ነገር መፈጸም እንደምንችል ሊያሳስበን ነው። ስለዚህ ለዘላለም የሚዘልቅ በጎ ሥራ ለእግዚአብሔር ለማከናወን የሚሹ ሁሉ፥ በመጀመሪያ ሌሎችን ለመርዳት የበታች አገልጋዮቻቸው ሊሆኑ ይገባል። ስለዚህ የደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ምሳሌ ራሱ ኢየሱስ ነው። በመሆኑም እርሱ ሌሎች እንዲያገለግሉት ወደ ምድር አልመጣም። ወደ ምድር የመጣበት የእርሱ ፍጹም ዓላማ ሌሎቹን ለማገልገል ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) እስቲ በቤተ ክርስቲያናችሁ ወይም በኅብረተሰባችሁ ውስጥ አገልግሎትን ስለሚሹ ሰዎች አስቡ። እነዚህን ሰዎች በዚህ ሳምንት ውስጥ ለማገልገል ምን ማድረግ አለባችሁ? ለ) እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናችሁ ወይም በኅብረተሰቡ ውስጥ መብታችሁን አሳልፋችሁ ለመስጠትም ሆነ፥ ራሳችሁን ትሑታን አድርጋችሁ ለማቅረብ ስለምትቸገሩባቸው ሰዎች አስቡ። ታዲያ በዚህ ሳምንት እንዲህ ላሉ ሰዎች እንዴት መብታችሁን አሳልፋችሁ ትሰጣላችሁ? ደግሞስ በፊታቸው ራሳችሁን እንዴት በትሕትና ታቀርባላችሁ? 

እኛ የኢየሱስን ምሳሌ እንከተላለን ካልን የሰዎች ፍላጎት ምንም ዓይነት ይሁን፥ እነርሱን ለማገልገል ዝግጁዎች ልንሆን ይገባል። ይህ ምናልባት አንዳንድ ሰዎችን በሥራቸው ላይ መርዳት ሊሆን ይችላል። ሌሎችን ደግሞ በየቤታቸው ውስጥ ልናግዛቸውም ይገባ ይሆናል። የእኛ አሳብ ከእነርሱ የተሻለ ሆኖ ቢገኝም እንኳን፤ ምናልባት የሌሎችን አሳብ ተቀብለን ማስተናገድ ይጠበቅብን ይሆናል። እንደዚሁም ሌሎችን ሰዎች ማክበርና ከእነርሱ ጋር በሚኖረን ግንኙነት ራሳችን ዝቅ አድርገን በእነርሱ ደረጃ ማቅረብ ሊኖርብን ይችላል። ሁልጊዜም ቢሆን፥ የሌሎችን ፍላጎት ለማሟላትም ሆነ እነርሱን ደስ ለማሰኘት የራሳችንን ክብር መሠዋት፥ እንደዚሁም በፊታቸው ራሳችንን ትሑታን አድርገን ለማቅረብ ፈቃደኞች ሆነን መገኘት አለብን። 

3. ኢየሱስ የእኛን ፍላጎት ለማሟላት ሕይወቱን ሰጠ 

ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐንስ 3፡16-30 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ ለእኛ ፍቅሩን ለመግለጥ ሲል ምን አደረገ? ለ) በቁጥር 16 መሠረት በክርስቶስ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ለሆኑ ሁሉ ሕይወታችንን ለማሳየት ምን ማድረግ አለብን? ሐ) ከቁጥር 17-18 እንደተጻፈው ለሌሉች ያለንን ፍቅር እንዴት ባለ ልዩ ሁኔታ ማሳየት ይገባናል? መ) ከቁጥር 19-20 እንደተጻፈው፥ ሕይወታችንን በዚህ ሁኔታ በምናሳይበት ጊዜ ውጤቱ ምን ይሆናል?

1ኛ ዮሐንስ 3፡16–20 ያለው ክፍል እንደሚነግረን ለሌሎች ፍቅራችንን በመግለጹ ረገድ ኢየሱስ ምሳሌያችን ነው። በተለይም ደግሞ በክርስቶስ ለሚያምኑ ምእመናን ለምናሳየው ፍቅር እርሱ ምሳሌያችን ነው። ታላቁ ) የፍቅር ምሳሌ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለ እኛ መሞቱ ነው። ስለሆነም ክርስቶስ እኛን መውደዱን በቃል ብቻ አልነገረንም፥ ነገር ግን ሕይወቱን ለእኛ አሳልፎ በመስጠት በድርጊት ገለጠው። የእኛን አንገብጋቢ ፍላጎት ለሟሟላት ሲል፥ ፍቅሩን በድርጊት ተረጎመው። ስለዚህ ሐዋርያው ዮሐንስ እኛ ክርስቲያን የሆኑ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችንን እንዴት መውደድ እንዳለብን ክርስቶስ ምሳሌያችን ነው ይለናል። ሌሎች ክርስቲያን አማኞች ችግር እንዳለባቸው እያየን፥ እንዲያው በቃል ብቻ እንወዳችኋለን ብንል አይጠቅማቸውም። ዳሩ ግን ፍቅራችንን በተግባር መግለጥ ይገባናል። ስለዚህ ካለን ቀንሰን ለእነዚህ ሰዎች በመቸር ቁሳዊ ችግራቸውን ማቃለል ይጠበቅብናል። ካለን ከፍለን በመስጠት ፍቅራችንን በምግባር በምንገልጽበት ወቅት፥ በክርስቶስ በእውነት የምናምን መሆናችንን በልባችን ውስጥ ያጸናልናል። ምናልባት ስለ ደኅንነታችን የምንጠራጠር ከሆንን፥ ለሌሎች አማኞች ይህ ያደረግነው ችሮታ፥ በእውነት በክርስቶስ መሆናችንን ሊያረጋግጥልን ይችላል። 

ጥያቄ፡- እስቲ ከአማኞች መካከል ችግር ስላለባቸው ሰዎች አስቡ። ከዚያም በዚህ ሳምንት ውስጥ እነዚህን ሰዎች በምን አኳኋን ልትረዱዋቸው እንደምትችሉ በዝርዝር ጻፉ። በእውነቱ ልንረዳቸው የሚገባ ብዙ አማኞች አሉ። ለምሳሌ ያህል፥ ለሚራቡ ወንድሞችና እኅቶች በምንችለው መጠን ምግብ ወስደን ልንሰጣቸው እንችላለን። እንዲሁም በቂ ልብስ ለሌላቸው ምእመናን ልብስ ልንሰጣቸው ዕድል አለን። ምናልባትም ወደ ሥራ ወይም ወደ ገጠር ወጣ ለሚሉት ክርስቲያኖች ትራንስፖርት ልንረዳቸው እንችላለን። እንደዚሁም ለታመሙት መድኃኒት በመግዛት ብናግዛቸው መልካም ነው። 

አንዳንድ አማኛች ሥራ በመሥራት የገንዘብ ችግራቸውን ሊወጡ ሲችሉ ዘወትር በልመና ችግራቸውን ለማቃለል ይጥራሉ። በ1ኛ ዮሐ 3፡16-20 የተጻፈው ቃል እንዲህ ላሉ ሰዎች ሁልጊዜ ገንዘብ በጠየቁ ቁጥር እንድንመጸውታቸው አይናገርም። እንዲያውም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሌሎች ስፍራዎች እግዚአብሔር ሕዝቡ ጠንክረው ሠርተው ቤተሰባቸውን እንዲያስተዳድሩና እንዲንከባከቡ እንደሚፈልግ በግልጽ ተቀምጧል (ምሳሌ 24፡0-34 2ኛ ተሰ. 3፡10፤ 1ኛ ጢሞ. 5፡8)። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሰዎች ኑሮአቸውን ለመደገፍ የተቻላቸውን ያህል ቢደክሙም ፍላጎታቸውን ሊያሟሉ አይችሉ ይሆናል። በዚህ ወቅት የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል የጎደላቸውን በሟሟላት ልናግዛቸው ይገባል። 4 ኢየሱስ ሁልጊዜም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይፈጽም ነበር። 20ኛ ጥያቄ ዮሐንስ 4፡34 አንብቡ። ሀ) የኢየሱስ ምግብ ምን ነበር? ለ) ዮሐንስ 4፡35 አንብቡ። በተለይ በዚህ ዐውደ ምንባብ መሠረት የአብ ሥራ ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 5፡30 አንብቡ። ሀ) ኢየሱስ የማንን ፈቃድ ለመፈጸም ይሻል? ለ) ዮሐንስ 6፡38 አንብቡ። ኢየሱስ የማንን ፈቃድ ሊፈጽም መጣ? 

ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 10፡32-11፡1 አንብቡ። ሀ) እንደ 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡33 አገላለጽ፥ ጳውሎስ በምን ምክንያት ነው የራሱን ጥቅም ሳያስቀድም የሌሎችን ጥቅም በማስቀደም ሊያስደስታቸው የሞከረው? ለ) በ1ኛ ቆሮንቶስ 1፡1 ላይ እንደተጻፈ፥ ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ሲያደርግ ላለ የማንን ምሳሌነት ተከተለ? 

ኢየሱስ በሕይወቱ ውስጥ ብዙ ጊዜ በግልጽ ሲናገር፥ የሕይወቱ ጥቅል ዓላማ የራሱን ፈቃድ መፈጸም ሳይሆን፥ የአባቱን ፈቃድ መፈጸም እንደሆነ ይጠቅስ ነበር። በዮሐንስ 5፡30 ላይ ኢየሱስ፥ የእርሱ ዓላማ ራሱን ለማስደሰት መሻት እንዳይደለና ግን ወደ ምድር የላከውን ፈቃድ መፈጸምና እርሱንም ደስ ማሰኘት እንደሆነ ለአይሁዶች ነገሮአቸው ነበር። በዮሐንስ 638 ላይ እንዲሁ ለሕዝቡ ሲናገር፥ እርሱ የራሱን ፈቃድ ለማድረግ እንዳልመጣና፥ የመጣው የላከውን የአብን ፈቃድ ለመፈጸም (ቁጥር 40) መሆኑን ገልጾላቸዋል። በዮሐንስ 4፡34 ላይ ደግሞ፥ የእርሱ ምግብ የአብን ፈቃድ ማድረግና ሥራውንም መፈጸም እንደሆነ ለደቀ መዛሙርቱ ነግሮአቸዋል። ደቀ መዛሙርቱ ግን በዓይን የሚታየውን ምግብ እንዲመገብ ይወተውቱት ነበር። ኢየሱስ ግን ከዚህ ከሚታየው ምግብ የበለጠ ሌላ ምግብ መኖሩንና ያም ምግብ የሚያጠግብና የሚያረካ ምግብ መሆኑን ይነግራቸው ነበር። ለእርሱ ከሁሉ የበለጠና አጥጋቢና አርኪ የሆነው ምግብ፥ የአባቱን ፈቃድ ማድረግና ሥራውንም መፈጸም ነው። በሚቀጥለው ቁጥር ዮሐንስ 4፡35 ላይ፥ ኢየሱስ የወቅቱ የአብ ፈቃድ ሥራ ምን እንደ ነበረ ለይቶ ነግሯቸው ነበር። ይህም፥ ንስሐ ለመግባት ዝግጁ ለነበሩት ለሳምራውያን ወንጌሉን ማካፈል ነበር። በዚያኑ ጊዜ «እርሻዎቹ ለመከር ደርሰዋል» ብሎ ሲነግራቸው፥ የወቅቱ የእግዚአብሔር ፈቃድ ለሚቀበሉት ወንጌልን ማዳረስ መሆኑን ሲያስረዳቸው ነበር። 

በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ፥ የራሳቸውን ፍላጎት ለማርካት በመሻት ፈንታ፥ የአብን ፈቃድ ለመፈጸም እንዲችሉ፥ የክርስቶስን ምሳሌ መከተል ይገባቸዋል። 1ኛ ቆሮ. 10፥2-33 ባለው ክፍል ሐዋርያው ጳውሎስ ራሱን ማስደሰት የራሱን ጥቅም በመተው ሌሎችን ወደ ክርስቶስ በማምጣት ላይ ጥረቱንና ትኩረቱን ማድረጉን ይነግረናል። በዚህም የራሱን ክብርና መብት እንዲሁም ደስታ ወደ ጎን ትቶ፥ ሌሎችን ወደ ክርስቶስ ሊያመጣ የሚቻል ሕይወት ኖረ፡፡ በሚቀጥለው በ1ኛ ቆሮንቶስ 11፡1 ላይ አሳቡን ሊያጠቃልል፥ እርሱ እየተከተለ ያለው የክርስቶስን ምሳሌ መሆኑን በማስገንዘብ እኛ ሁላችንም ይህን በማድረግ የእርሱን ምሳሌ መከተል እንዳለብን ያሳስባል። እኛም ይህንኑ ምሳሌ በመከተል፥ ራሳችንን የማስደሰት ምኞታችንን ወደ ጎን ትተን እግዚአብሔርን ደስ እናሰኝ። በግልጽ ለመናገር ራሳችንን ለማስደሰት ከመጣር ይልቅ፥ ቅዱስ ወንጌሉን ለሌሎች ማዳረስን ቀደምት ዓላማችን ማድረግ ይኖርብናል። 

ጥያቄ፡- በየቀኑ ያላችሁን አብዛኛውን የጊዜአችሁን ድርሻ ለምን እንደምታውሉት ቆም ብላችሁ አስቡ? ሀ) በሕይወታችሁ ውስጥ ትልቁን ስፍራ የያዘውና አርኪ የሆነው ነገር ምንድን ነው? ለ) በየቀኑ ከሚያጋጥሙዋችሁ ክርስቶስን እንደ ግል መድኃኒታቸው ያልተቀበሉና የማያውቁ ሰዎች የጥቂቶቹን ስም ጻፉ። ከእነዚህ ሰዎች ከእያንዳንዳቸው ጋር ወንጌልን እንዴት ትካፈላላችሁ? 

አንዳንድ ጊዜ እጅግ ጠቃሚውና አርኪ የሆነው ጉዳይ ራሳችንን መንከባከብ ነው ወደ ማለቱ ልንወሰድ እንችላለን። ከዚህ የተነሣም ጥራት ያለው ትምህርት ለማግኘት፥ የተዋጣለት ሥራ አግኝተን የተቻለውን ያህል ብዙ ገንዘብ ለማፈስ፥ እንዲሁም በወዳጆቻችንና በጓደኞቻችን ዘንድ ተወዳጅና ታዋቂ ለመሆን፥ ወይም የተደላደለ ኑሮና ትልቅ ቤት ለማግኘት በአያሌው እንደክማለን። ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ይህን ሁኔታ በሚመለከት ሲናገር፥ ከሁሉ የበለጠውና አርኪ የሆነው ተግባር፥ የአብን ፈቃድ ማድረግና ሥራውን መፈጸም መሆኑን በግልጽ አስገንዝቧል። የአብ ፈቃድና ሥራም ወንጌልን ለሚያስፈልጋቸው ማዳረስ ነው። እንዲሁም የራሳችንን ጥቅም በማስቀደም ጊዜአችንን ከማሳለፍ ይልቅ፥ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነው ተግባር ወንጌል ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሁሉ ወንጌልን በማዳረስ ጊዜአችንን፥ እውቀታችንና ጉልበታችንን መጠቀም ነው። ሦስተኛ ቀን- የኢየሱስ ትምህርት፡- የእግዚአብሔር መንግሥት አብዛኛው የጌታ ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎት ያተኮረው በማስተማር ተግባር ነው። እናም ኢየሱስ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች ነበር ያስተማረው። ከእነዚህም ሰዎች ተቃዋሚዎች፥ ስለ እርሱ የሚደነቁና ለማወቅም የሚሹ ለአጭር ጊዜ የተከተሉና መላ ሕይወታቸውን ለእርሱ በእውነት የሰጡ ደቀ መዛሙርትም ነበሩ። ታዲያ የኢየሱስ ትምህርት በእነዚህ የተለያዩ ቡድኖች ላይ ያተኮረ ነበር። ሰዎቹ የተለያዩ ይሁኑ እንጂ ኢየሱስ የሰጣቸው ትምህርት ጭብጥ አብዛኛውን ጊዜ ተመሳሳይነት ነበረው። ጌታ ብዙ ጊዜ ያስተምረው የነበረው ርእስ የእግዚአብሔር መንግሥት ነው፡፡ በትምህርት ሰባት ላይ ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የሰጠውን ትርጉም ማጥናት መጀመራችን ይታወሳል። ስለሆነም፥ የዛሬው ትምህርታችን በእግዚአብሔር መንግሥት ላይ ጠለቅ ያለ ጥናት ማድረግ ይሆናል። ኢየሱስ በመጀመሪያ ሲያስተምር እንደሆነው ሁሉ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የሰጠው ትምህርት፥ ለዛሬዎቹ ሕዝቦችም ቢሆን ለሕይወታቸው ሊጠቅማቸው የሚችል ብዙ ቁም ነገሮች አሉት። እናንተም ብትሆኑ ዛሬ የእርሱን ትምህርት ለሚቃወሙት ሲሆን፥ ለጊዜው ወንጌልን ለሚቀበሉትና እንዲሁም በጥልቀት ራሳቸውን ለወንጌል ለሰጡትም ልታስተምሩ ትችላላችሁ።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Exit mobile version