በትናንትናው ትምህርታችን ኢየሱስ በደላችንንና የኃጢአታችንን ቅጣት የተሸከመ ፍጹም ቤዛ መሥዋዕት መሆኑን ተገንዝበናል። አዲስ ኪዳን የኢየሱስ መሥዋዕትነት ኃጢአታችንንና የከፋ ውጤቶቹን እንዴት እንዳስወገደ ለመግለጽ በሌሎች ሥዕሎችና አሳቦች ይጠቀማል። ዛሬና በሚቀጥለው ሳምንት ከእነዚህ ምስሎችና አሳቦች አራቱን እናጠናለን። ለዛሬው የኢየሱስ መሥዋዕትነት እግዚአብሔር በኃጢአት ላይ የነበረውን ቅዱስ ቁጣ እንዴት እንዳበረደው እንመለከታለን።
ጥያቄ፡– ኤር. 2፡12 አንብቡ። እግዚአብሔር ፍትሕ በማይኖርበት ጊዜ ምን አደርጋለሁ አለ?
ጥያቄ፡ ሕዝ. 24፡13 አንብቡ። እስራኤላውያን ራሳቸውን ከርኩሰታቸው ባለማንጻታቸው ምክንያት ምን ደረሰባቸው?
ጥያቄ፡– 2ኛ ነገ 23፡26 እንብቡ። ከምናሴ ኃጢአት የተነሣ የእግዚአብሔር ምላሽ ላይሁዳ ምን ነበር?
ጥያቄ፡ ሰአ. ኤር. 3፡42-43፡- እግዚአብሔር እስራኤልን ለምን ወደ ምርኮኝነት ላካቸው?
የሰዎች ኃጢአት የእግዚአብሔርን የጽድቅ ቁጣ እንደሚቀሰቅስ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል። በኤር. 21፡12 ውስጥ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ሲያስጠነቅቅ ክፋት ከቀጠለ፥ ለተበዘበዙትም ፍትሕ ካልሰፈነ ቁጣው እንደ እሳት እንደሚቀጣጠል ይነግራቸዋል። በሕዝቅኤል 24፡18 ውስጥ በርኩሰታቸው ስለ ቀጠሉ መዓቱን እንደሚያመጣ እግዚአብሔር ለእስራኤል ተናግሯል። ምንም እንኳን ንጉሥ ኢዮስያስ የይሁዳ መልካም ንጉሥ ቢሆንም፥ በ2ኛ ነገ. 23፡26 ውስጥ በቀድሞው ንጉሥ በምናሴ ኃጢአት ሳቢያ እግዚአብሔር ሕዝቡን በጽድቅ ቁጣው የተቆጣው መሆኑን ለእስራኤል ተናግሮ ነበር። በሰቆ. ኤር. 3፡42-43 እንደተገለጸው እግዚአብሔር እስራኤልን ወደ ምርኮ የላከው በኃጢአታቸው ላይ የጽድቅ ቁጣ ስለ ነሐደ ነበር። ትናንትና በሮሜ 1፡18 በክፉዎችና በዐመፀኞች፥ ነገር ። የእግዚአብሔርን እውነት እያወቁ ቸል በሚሉትና በማይታዘዙት ላይ የእግዚአብሔር ቅዱስ ቁጣ እንደሚወርድ ተገንዝበናል። ሰዎች ኃጢአትን በሚሠሩበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር በቅዱስ ቁጣው በኃጢአታቸው ላይ ይቆጣል።
የእግዚአብሔር ቁጣ ሲባል እግዚአብሔር ራሱን ስቶ ወይም ግንፍል ብሎት ይቆጣል ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ቁጣ፥ እግዚአብሔር ኃጢአትን የሚሠሩ ሰዎችን ስለ ጠላ ይወርድባቸዋል ማለትም አይደለም። የእግዚአብሔር ቁጣ፥ እግዚአብሔር በኃጢአት ላይ የሚሰጠው የጽድቅ ምላሽ ነው። ይህን የሚያደርገው ኃጢአት የከፋና አጥፊ መሆኑን ስለሚነዘብ ነው። ብዙ ጊዜ ግን እኛ የሰው ልጆች የምንቆጣው ሰዎች ወይም ሁኔታዎች የሚያደርሱብንን ድርጊት በራስ ወዳድነትና በክፉ አስተሳሰብ ስለምንመለከተው ነው። ሰዎች የእኛ ሊሆን የሚገባውን ዕቃ በሚወለዱብን ጊዜ እንቆጣለን። እንዲሁም ሰዎች የምንፈልገውን ነገር ስላልሰጡን፥ ወይም የምንሻውን ስላላደረጉልን እንቆጣለን። እግዚአብሔር ግን ራሱን ወዳድ ስላልሆነ እንዲህ ባሉት ነገሮች አይቆጣም። እግዚአብሔር የሚቆጣው ለእኛ እጅግ የሚጠቅመንን ነገር ኃጢአት ሲያበላሽብን ሲያይ ነው። እግዚአብሔር ስለሚወደን የእኛ ኃጢአት ሌሎች ሰዎችን፥ ካሌሎችና ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት፥ ፍጥረትንና ራሳችንን ሲጎዳ ያዝናል። ስለሆነም እግዚአብሔር በኃጢአትና ኃጢአት በሚያስከትለው ጥፋትና ውጤቶቹ ላይ ይቆጣል።
አንዳንድ ጊዜ እኛም ብንሆን እግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣውን እንደሚቆጣ ሁሉ፥ እኛም ትንሽ ትንሽ የእርሱን የመሰለ ቅዱስ ቁጣ የምንቆጣበት ጊዜ አለ። እኔም አንድ ጎልማሳ ታዳጊዋን ልጃ ገረድ አስገድዶ ሕግዋን መግሰሱን በሰማሁ ጊዜ ይህን የመሰለ ቁጣ ተሰምቶኛል። ሰውዬውን ወይም ልጃገረዲቱን አላውቃቸውም ነበር። ነገር ግን በጣም ተናድጄ ነበር። የተቆጣሁበትም ምክንያት ይህ ሰው የታዳጊዋን ልጃገረድ ሕይወት ስላበላሸባት ነው። በዚህም ሰውዬው ንጽሕናዋን አጉድፎታል። በቀረው ዕድሜዋ በአካልና በስሜት ጎድቷታል። ስለዚህ የሰውዬው ኃጢአት አናደደኝ። ይህ ሰው በወንጀሉ ተከሶ ወደ ፍርድ ቤት ቢቀርብና ዳኛው፥ «ይህን ወንጀል በይቅርታ ስላለፍኩት ሰውዬው ያለቅጣት ነፃ ይለቀቅ» ብሎ ቢለቀው ኖሮ ምን ይሰማኝ ነበር? በጣም ይነደኝና ፍትሕም መጓደሉን አስብ ነበር። የከፋ ኃጢአት መቀጣት ይኖርበታል። አንድ ወንጀለኛ ኃጢአቱ ከመቀጣቱ በፊት፡ ነፃ ሊለቀቅ አይገባም። የጽድቅ ቁጣን ለማስታገስ ኃጢአትን መቅጣት ያሻል። በዚሁ መንገድ እግዚአብሔር በኃጢአታችን ላይ የጽድቅ ቁጣን ይቆጣል። ይህ ከመፈጸሙ በፊት እንዲህ በቀላሉ ይቅር አይለንም። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቁጣ ለማብረድ ኃጢአት መቀጣት አለበት።
ጥያቄ፡- ዕብራውያን 9፡5 አንብቡ። በብሉይ ኪዳን የማደሪያው ድንኳን ውስጥ ካታቦቱ በላይ የነበሩ መላእክት ምንን ሸፍነው ነበር?
ጥያቄ፡- ሉቃስ 18፡18 አንብቡ። ቀራጩ በጸሎት ላይ ምን አለ?
በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ይቅርታ እንደ ሰጣቸው፥ እግዚአብሔር በኃጢአት ምክንያት የሚያወርደው ቅዱስ ቁጣ መታገስ እንዳለበት ያውቁ ነበር። በድንኳኑ ውስጥ በነበረው ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ይገኝ በነበረው በኪዳኑ ታቦት ላይ መክደኛ ነበር። ከኪዳኑ ታቦት በላይ የነበሩ መላእክት ይህንን መክደኛ ይጋርዱ ነበር። የዚህ መክደኛ ስም «የስርየት መክደኛ» (ማስተላለፊያ) ነው። ስፍራው የስርየት መክደኛ ቃል በቃል ሊተረጎም፥ ምሕረት የሚሰጥበት ቦታ ማለት ነው። ይህም የእግዚአብሔር ቁጣ የሚበርድበት ቦታ ነው። በየዓመቱ በስርየት ቀን (ዘሌዋ. 16)፥ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገብቶ በዚህ «በስርየት መክደኛ» ላይ ደም ይረጫል። ከዚህ ከመሥዋዕቱ ደም የተነሣ በሕዝቡ ኃጢአት ላይ የነበረው የእግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣ ለአንድ ሌላ ዓመት ይበርዳል። በዚህ ምክንያት ሕዝቡም የእግዚአብሔርን ምሕረት ያገኝ ነበር። የስርየቱ መክደኛ የምሕረቱ መቀመጫ ነው። ምክንያቱም የእግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣ ማስታገሻ ስፍራ ስለነበረ ነው። በሉቃስ 18፡13 ውስጥ ኢየሱስ ስለ ፈሪሳዊውና ስለ ቀራጩ ታሪክ ተናግሮ ነበር። ቀራጩ በጸለየ ጊዜ ኃጢአቱ ይሰማው ስለ ነበረ በትሕትና መንፈስ ጸለየ። እንዲህ አለ፥ «እግዚአብሔር እኔን ኃጢአተኛውን ይቅር በለኝ።» ይህ ቃል በአማርኛው ለየት ያለ ቢሆንም በመጀመሪያው ግሪክ «ይቅር በለኝ» የሚለው ቃል «የምሕረት መክደኛ» ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው። ቀረጥ ሰብሳቢው የጸለየው «በምሕረት መቀመጫው ላይ ያለው ደም በኃጢአቴ ላይ የተቃጣውን የጽድቅ ቁጣህን ያስታግስልኝ» በማለት ነበር። ቀራጩ እግዚአብሔር በእርሰ ኃጢአት ላይ የጽድቅ ቁጣ እንደሚቆጣ ገብቶታል። እግዚአብሔር የራሱን ቁጣ ለማስታገስ በምሕረት መቀመጫው ላይ ባለው ራሱ ባዘጋጀው ደም አማካይነት የኃጢአት ይቅርታ እንደሚያገኝ ያምን ነበር።
ነገር ግን፥ በብሉይ ኪዳን ጊዜ በሚደረገው መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ ይፈስ የነበረው ደም ኃጢአትን በጊዜያዊነት የሚሸፍን ብቻ ነበር እግዚአብሔር በኃጢአት ላይ ያለው የጽድቅ ቁጣ እስከ መጨረሻው ድረ በእንስሳ ደም ረክቶ ሊበርድ አይችልም ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔt በኃጢአት ላይ ያለውን ቁጣ ለመጨረሻው ለማቆም፥ ፍጹምና ዘላቂ የሆ መሥዋዕት ይሻ ነበር።
ጥያቄ፡- 1ኛ ዮሐ 2፡2 አንብቡ። ) ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ም ሆነ? ለ) 1ኛ ዮሐ 4፡10 አንብቡ። እግዚአብሔር ልጁ ስለ እኛ ኃጢአት ም እንዲሆን ላከው?
ጥያቄ፦ ዕብ 2፡17 አንብቡ። በምን ምክንያት ኢየሱስ ምሕረት የተሞላ ታማኝ ሊቀ ካህን ሆነ?
ጥያቄ፡- ሮሜ 3፡25-26 አንብቡ። ሀ) እግዚአብሔር ምን አድርጎ አቆመው ለ) ይህ ምንን ፈጸመ?
ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔርን በኃጢአት ሁሉ ላይ ለሁልጊዜ፡ የነበረውን የጽድቅ ቁጣ በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ያበረደ የእግዚአብሖ ፍጹም መሥዋዕት ነው። በ1ኛ ዮሐ. 2፡2 ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶ የኃጢአታችን ማስተሰሪያ ነው ይላል። 1ኛ ዮሐ 4፡10 ውስጥ እግዚአብሖ ልጁን የላከው የኃጢአታችን ማስተሰሪያ እንዲሆን ነው ይላል። ቀደም ሲ እንደተመለከትነው ይህ «የስርየት መሥዋዕት» የሚለው አገላለ የሚያስገነዝበው፥ የመሥዋዕቶቹ ደም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ቁ የሚመልሰውን የታቦቱን የምሕረት ማስቀመጫ ያመለክታል። እዚህ ላይ ዮሐንስ የሚነግረን አሁን ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚመልስ ፍጹምና የመጨረሻው መሥዋዕት መሆኑን ነው። ዕብራውያን 2፡17 ደግሞ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሊቀ ካህናቱ በዓመት አንድ ጊዜ የመሥዋዕቱን ደም ይዘው ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መቅደስ እንደሚገቡ መለስ ብሎ ያስታውሳል። አሁን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፍጹም ምሕረት የተሞላና ታማኝ ሊቀ ካህን ነው።
የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔርን ቁጣ ለማስታገሥ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በዓመት አንድ ጊዜ ይገሱ በነበረበት ሁኔታ፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቁጣ ለመጨረሻው ፍጹም በሆነ መንገድ ለማስታገሥ የራሱን ደሙን ለስርየት ይዞ ገባ።
ትናንትና በሮሜ 1፡18 የእግዚአብሔርን እውነት እያወቁ ችላ ባሉ፥ ለመታዘዝ በማይፈልጉ፥ በክፉዎችና በዐመፀኞች ላይ የእግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣ እንደሚወርድ አስተውለናል። በሮሜ 1፡19፥ በመጀመሪያ ሐዋርያው ጳውሎስ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ስለ መሆናቸው ለመግለጽ ሁለት ምዕራፎችን ጽፎአል። ሰዎች እንዲህ ኃጢአተኛች ከመሆናቸው የተነሣ፥ የእግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣ ሊወርድባቸው ይገባል። ነገር ግን ሐዋርያው ወደ ሮሜ 3፡21 ሲደርስ፥ እግዚአብሔር እንዴት በኃጢአት ላይ የነበረውን የጽድቅ ቁጣ እንደ ታሠ ይገልጻል። ከዚህም በስተቀር እግዚአብሔር አስቆጥቶት ለነበረው የኃጢአታችን ችግር መፍትሔውን ሲሰጥ እናያለን። እንደዚሁም በሮሜ 3፡25-26 ውስጥ፥ እግዚአብሔር ራሱ ኢየሱስን የማስተሰሪያ መሥዋዕት አድርጎ እንዳቀረበውና፥ እኛም ይህንን በደሙ ባለን እምነት እንደምንቀበል ይገልጻል። ከዚያም ሐዋርያው ቀጥሎ ሲገልጽ፥ እግዚአብሔር የብሉይ ኪዳን አማኞችን ኃጢአት ኢየሱስ መሥዋዕት እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ ሸፍኖ ማቆየቱን ይናገራል። አሁን ስለ ኃጢአታቸው እግዚአብሔር የነበረው የጽድቅ ቁጣ፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ስለ እኛ ይሰማው የነበረው የጽድቅ ቁጣ ቀርቶአል። በኢየሱስ ሞት እግዚአብሔር በሰዎች ኃጢአት ላይ የነበረው ቅዱስ ቁጣ ለምን ጊዜውም ታግሷል። እግዚአብሔር በኃጢአታችን ምክንያት የተቆጣ ቢሆንም፥ በልጁ መሥዋዕትነት የጽድቅ ቁጣውን ገትቷል። ስለዚህ የኢየሱስ ሞት የእግዚአብሔርን ቁጣ ያስታገሠ (ያበረደ) በመሆኑ፥ በኢየሱስ የሚያምኑ ሁሉ የኃጢአት ይቅርታ ያገኛሉ።
ጥያቄ፡- የእግዚአብሔርን የጽድቅ ቁጣ ያስታሠው የኢየሱስ ሞት፥ ሰዎች የመናፍስትን ቁጣ ለማብረድ ከሚያቀርቡት መሥዋዕት አሳቡ በምን ይለያል? የራሳችሁን አሳብ ጻፉ።
ጥያቄ፡- አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ጥያቄ እንደሚያቀርብላችሁ ገምቱ፥ «እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ሆኖ እንዴት ደግሞ የቁጣ አምላክ ይባላል? ይህ እርስ በርሱ የሚቃረን አሳብ አለው። እግዚአብሔር ስለሚወደን፥ ወዲያው ይቅር ይለናል።” ታዲያ ለዚህ ሰው ምን ብላችሁ ትመልሳላችሁ?
የኢየሱስ ሞት የእግዚአብሔርን የጽድቅ ቁጣ አስታገሠ በሚለውና አንዳንድ ሰዎች የመናፍስትን ቁጣ ለማስታገሥ መሥዋዕት ያቀርባሉ በሚሉት ሁለት አሳቦች መካከል ሁለት ዐበይት ልዩነቶች አሉ። በመጀመሪያ፥ አብዛኛዎቹ ሰዎች የመናፍስትን ቁጣ ለማብረድ መሥዋዕት የሚያቀርቡት መናፍስት የሚቆጡት ችላ ስለ ተባሉ ወይም መሥዋዕት ስላልቀረበላቸው ወይም ቁጡዎች ስለሆኑ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ከእነዚህ ምክንያቶች ውስጥ በአንዱም ምክንያት አይቆጣም። እግዚአብሔር የሚቆጣው በኃጢአትና ኃጢአት በሚያመጣቸው ውጤቶች ላይ ነው። እግዚአብሔር የሚቆጣው ቅድስናው ሲጣስበት ነው እንጂ፥ ችላ ስለ ተባለ ወይም አንዳችን ነገር እንድንሰጠው ፈልጎ አይደለም። እንደዚሁም እግዚአብሔር ብድግ ብሎ ያለምክንያት አይቆጣም። እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚቆጣው በኃጢአት ምክንያት ነው። ሁለተኛ፥ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ቁርባን ለማስታገሥ ብቃት ያለው መሥዋዕት ማንም ሰው ሊያቀርብ አይችልም። ደግሞም ሰዎች ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን ለማቅረብ ሲፈልጉ፥ ፍጹማን ስላልሆኑ መሥዋዕታችውን አይቀበላቸውም። ሰዎች የመርገም ጨርቅ ብቻ ናቸው። በዚህ ፈንታ እግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣውን የሚያበርድበት መሥዋዕት ራሱ ፡ አቅርቦአል። ለዚህም የራሱን የጽድቅ ቁጣ ለማስታገስ ሲል፥ ልጁን ጌታ ኢየሱስን ፍጹም መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦአል። እኛ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ቁጣ ለማስታገስ፥ ፍጹምነት ያለው መሥዋዕት ለማቅረብ እንደማንችል እግዚአብሔር ያውቃል። ስለዚህ እግዚአብሔር አብና እግዚአብሔር ወልድ፥ ስለሚያፈቅሩን ለኃጢአታችን ቤዛ ፍጹምነት ያለው መሥዋዕት በፈቃዳቸው አቀረቡ። እግዚአብሔር መሥዋዕቱ አድርጎ ኢየሱስን ለማቅረብ በፈለገ ጊዜ ኢየሱስ አላመነታም። ኢየሱስ ራሱ አምላክ በመሆኑና እኛንም በጣም ስለ ወደደን፥ በኃጢአታችን ላይ የነበረውን ቁጣ ለማስታገስ በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ሰጠ። ምንም ዓይነት ጎደሎ ወይም ያልተሟላ መሥዋዕት እግዚአብሔር በኃጢአታችን ላይ ያለውን ቁጣ ለማብረድ አይችልም። ስለዚህ እግዚአብሔር የራሱን የጽድቅ ቁጣ ለማስታገሥ፥ በልጁ አማካይነት ራሱን አሳልፎ ሰጠ። እንዴት የሚያስደንቅ ፍቅር ነው የእግዚአብሔር የራሱ የፍቅር መሥዋዕትነት የእግዚአብሔርን የጽድቅ ቁጣ አበረደ።
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
